Telegram Web Link
በኢትዮጵያ በዓመት በአማካይ 520 ሺህ ሴቶች ደህንነቱ ባልተጠበቀ መልኩ ፅንስ ያቋርጣሉ ተባለ

በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ለእናቶች ሞት ምክንያት የሆነውን የፅንስ ማቋረጥ አሁን ላይ መቀነስ ተችሏል ቢባልም ችግሩን ሙሉ ለሙሉ መቅረፍ ግን አልተቻለም።በፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ዶክተር ምስክር ገበየሁ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ለእናቶች ሞት 35 በመቶ ድርሻ የነበረውን ፅንስ ማቋረጥ አሁን ላይ ወደ 5 በመቶ መቀነስ ተችሏል።

በዚህም በ7ት እጥፍ ቀድሞ ከነበረበት ዝቅ ማድረግ እንደተቻለ ገልፀው ይህም ትልቅ ስኬት መሆኑን ተናግረዋል።ይሁን እንጂ ችግሩን ሙሉ ለሙሉ መቅረፍ ስላልተቻለ ለጉዳዮ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተጠቁሟል።በኢትዮጵያ በየዓመቱ በአማካይ 5 መቶ 20 ሺህ ሴቶች ደህንነቱ ባልተጠበቀ መልኩ ፅንስ እንደሚያቋርጡ የተናገሩት ዶክተር ምስክር በዚህም የተነሳ ለህልፈት የሚዳረጉ መኖራቸውንም ተናግረዋል።

ንፅህናው ባልተጠበቀ ፅንስ ማቋረጥ ምክንያት ሴቶች ለኢንፌክሽንና ለተለያዩ ችግሮች ስለሚጋለጡ  ህይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ ተነግሯል።በመሆኑም በዚህ ሁኔታ ለህልፈት የሚዳረጉትን ሴቶች መታደግና ደህንነታቸውን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል፡፡

ቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
ትራምፕ ለቢሊየነሩ ማስክ የሚደረገው ድጎማ ቢቆም ሱቁን ዙግቶ ወደ ደቡብ አፍሪካ ይመለሳል ሲሉ  ተናገሩ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማክሰኞ ማክሰኞ እለት እንዳስታወቁት የመንግስት ቅልጥፍና ክፍል ለቴስላ የሚሰጠው ድጎማ እንዲታይ ሀሳብ ያቀረቡ ሲሆን ለቱጃሩ ሰው ኤሎን ማስክ ኩባንያዎች የሚሰጡ ድጋፎች ገንዘብ ለመቆጠብ ጥቅም ላይ እንዲውል አሳስበዋል። ትራምፕ ይህንን አስተያየት የሰጡት የአለማችን ባለጸጋው ማስክ ሰኞ እለት ዳግም ትችቱን በትራምፕ አስተዳደር ላይ ማቅረቡን ተከትሎ ነው። ከፍተኛ የግብር ቅነሳ እና የወጪ ሂሳብ ረቂቅ ላይ ትችቱን አሰምቷል።

ኤሎን በታሪክ ውስጥ ከማንኛውም የሰው ልጅ የበለጠ ድጎማ ሊያገኝ ይችላል ፣ እናም ያለ ድጎማ ፣ ኢሎን ምናልባት ሱቁን ዘግቶ ወደ ደቡብ አፍሪካ ይመለሳል። ከአሁን በኋላ የሮኬት ማስወንጨፊያ ፣ የሳተላይት ወይም ኤሌክትሪክ መኪና ማምረት የለም ፣ እናም አገራችን ታተርፋለች ። ምናልባት የመንግስት ቅልጥፍና ይህንን መመልከት አለበት ብለዋል።ለትራምፕ ጽሁፍ ምላሽ የሰጠው ማስክ የራሱ ንብረት በሆነው ማህበራዊ ሚዲያ ኤክስ ላይ " ለኩባንያዎቼ የሚደረግ ድጋፍ ካለ አሁኑኑ ማቆም ትችላላችሁ" ሲል አጋርቷል።

ትራምፕ ከዚህ ቀደም በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ ግንኙነታቸው ሲሻክር በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ በተፈጠረው ሁለንተናዊ ፍጥጫ በሕጉ ላይ በተፈጠረ ግጭት የማስክን የመንግስት ድጎማ እና ኮንትራቶች እንደሚያቋርጠ ዝተው ነበር።ይህም እንደ ተንታኞች ገለጻ ከሆነ ተንታኞች የአሜሪካ ዕዳ ወደ 3 ትሪሊዮን ዶላር እንደሚጨምር ተናግረዋል። የማስክ ቢዝነሶች የሮኬት ኩባንያ እና የስፔስ ኤክስ 22 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ የፌዴራል ኮንትራት ያላቸው ሲሆን ይህው የስራ ውል የሳተላይት ክፍሉ ስታርሊንክን ያጠቃልላል።

የቴኖሎጂ ኩባንያ መሪው ቢሊየነር ኢሎን ማስክ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የግብር ቅነሳ እና የወጪ ሂሳብ ላይ ትችታቸውን አጠናክረው በመቀጠል ለአዲስ የፖለቲካ ፓርቲ እንቅስቃሴ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። የግብር እፎይታዎች፣ በጤና አጠባበቅ እና የምግብ መርሃ ግብሮች ላይ ከፍተኛ ቅነሳን በሚያስተዋውቀው የትራምፕ ባለ 940 ገጽ “ትልቁ፣ ቆንጆ ቢል” ላይ ማስክ የሰነዘሩት ትችት ዓይነት ከዲሞክራቲክ ፓርቲ እና ከአንዳንድ የትራምፕ ሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ተመሳሳይ ተቃውሞ ገጥሞታል።

በጆርጅ ሜሰን ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ፖሊሲ ​​ፕሮፌሰር የሆኑት ቢል ሽናይደር ለአልጀዚራ እንደተናገሩት ማስክ የህጉን ተቃዋሚዎች ያቀፈ ውጤታማ የፖለቲካ ጥምረት መመስረት ከባድ ሊሆንበት ይችላል ብለዋል። "ኤሎን ማስክ ቢሊየነር ነው። በአሜሪካ ውስጥ ፓርቲ ለመመስረት በቂ ቢሊየነሮች የሉም፣ በፕሬዚዳንት ትራምፕ ደስተኛ ባይሆኑም እንኳ ፓርቲ ለመመስረት በቂ አይደሉም ሲሉ ሽናይደር ተናግረዋል። "አሁን እሱ በጣም ተወዳጅ ሰው ካልሆነው ከትራምፕ ጋር ጉዳዮች አሉት ። እሱም ቢሆን ብዙ ተቃዋሚዎች ፣ ብዙ ተቺዎች አሉት ፣ በተለይም በአሜሪካ ውስጥ ባሉ ሴቶች" ሲሉ ተደምጠዋል ።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
የኢራን የዩራኒየም ማበልጸጊያ ቴክኖሎጂ እና ሳይንስ በቦምብ ሊጠፋ አይችልም ሲሉ አራግቺ አስታወቁ

የኢራን የኒውክሌር ሃይል እውቀት እና ሰላማዊ የኒውክሌር ኢንደስትሪዋ የበለጠ ለማራመድ ያላትን ቁርጠኝነት በወታደራዊ ጥቃት ብቻ መጥፋት እንደማይቻል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ አረጋግጠዋል። ከፍተኛ ዲፕሎማቱ ለሲቢኤስ ዜና ወኪል በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ እንደተናገሩይ "አንድ ሰው ቴክኖሎጂን እና ሳይንስን ወይም የሰላማዊ የዩራኒየም ማበልጸጊያን በቦምብ ማጥፋት አይችልም" ብለዋል።

የእስራኤል አገዛዝ በጁን 13 ላይ በኢራን ሪፐብሊክ ላይ ጦርነት ከፍቷል። ይህም የሀገሪቱን የኒውክሌር ተቋማት እና ሌሎች በርካታ ዒላማዎች ላይ ያነጣጠረ ነበር ብለዋል። ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ወታደራዊ እና የስለላ ድጋፍ ለጥቃቱ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እያበረከተች ያለችው ዩናይትድ ስቴትስ ስትሆን የ12 ቀናት ቆይታ የነበረው ግጭት ሊጠናቅቅ ቀናት ሲቀሩት በኢራን ማእከላዊ እና ሰሜን-ማዕከላዊ ክፍል የሚገኙትን በርካታ የኒውክሌር ቦታዎችን መታለሽ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተነጣጠሩ ቦታዎች በአሜሪካ ጥቃቶች "ተደመስሰዋል" ሲሉ የሰጡት መግለጫ ከጊዜ በኋላ ፔንታጎን በራሱ ግምገማ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኢራን ሪፐብሊክ ሙሉ በሙሉ ፍቃደኛ እና ኪሳራዋን ለመቋቋም የሚያስችል አቅም እንዳላይ ጠቁመው ሀገሪቱ በምን ያህል ፍጥነት ይህን ማድረግ እንደምትችል ተስፋ ሰጪ ፍንጭ አሳይተዋል። "በእኛ በኩል ይህ ፍላጎት ካለ እና በዚህ ኢንዱስትሪ ውስጥ እንደገና መሻሻል ለማድረግ ፍላጎቱ ካለ ፤ የጠፉትን ጉዳቶች በፍጥነት ለመጠገን እና የጠፋውን ጊዜ ለማካካስ እንችላለን" ብለዋል።

እንደ አራግቺ ገለጻ፣ እስራኤል ባደረገችው ጦርነት የሀገሪቱን ወሳኝ የመከላከል፣ የኒውክሌር ጭነቶችን ጨምሮ፣ ኢራን በኢንዱስትሪው ውስጥ ያላት ጥንካሬ ታይቷል ብለዋል። “በተጨማሪም ለ12 ቀናት የዘለቀ ጦርነትን አሳልፈናል፣ስለዚህ ሰዎች በቀላሉ ከብልጽግና ወደ ኋላ አይመለሱም፣በጦርነቱ ወቅት ራሳችንን የመከላከል አቅማችንን አሳይተናል። ባለሥልጣኑ በተጨማሪም ሀገሪቱ አዲስ ጥቃት ከገጠማት ራሷን የመከላከል እርምጃ እንደምትወስድ አስረድተዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
ሆቴል በመግባት የአልኮል መጠጥ ሲጠጡ የተገኙት ሴቶች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ

በጋምቤላ ክልል ባህልንና ሀይማኖትን በሚፃረር አለባበስ ምሽት ላይ ሆቴል በመግባት የአልኮል መጠጥ ሲጠጡ የተገኙት ሴቶች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን የዲማ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል ::

የዲማ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ኚካሃ አኳይ ለወረዳው መንግስት ኮሙኒኬሽን እንደገለፁት በዲማ ከተማ ጨለማን ተገን በማድረግ ሀይማኖትንና ባህልን በሚፃረር አለባበስ ከምሽቱ 4:ዐዐ ላይ ዳንስ ቤት በመገኘታቸው ጽ/ቤቱ ከፖሊስ ጋር በመነጋገር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን ተናግሯል ::

ጽህፈት ቤቱ ከዚህ በፊትም 18 ዓመት ያልሞላቸው 9 ወንድ ህፃናት በምሽት መጠጥ ሲጠጡ በመገኘታቸው በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ የገንዘብ ቅጣት ተቀጥቶ በዋህስ እንዲለቀቁ መደረጉን አስታውሰው የዛሬው ለየት የሚያደርገው ሀይማኖትና ባህልን በሚፃረር አለባበስ ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ ዳንስ ቤት መገኘታቸው ከባድ ያደርገዋል ብለዋል ::

በቁጥጥር ስር የዋሉት 4 ሴት ተጠርጣሪዎች በአሁኑ ሰዓት በፖሊስ አስፈላጊውን ምርመራ እየተደረገ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይ ተገቢውን ቅጣት ተቀጥቶ እንደሚለቀቁ ገልፀዋል ::

#ዳጉ_ጆርናል
በጋምቤላ ክልል ባለፋት አስራ አንድ ወራት ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

በጋምቤላ ክልል በ2017 በጀት አመት አስራ አንድ ወራት ከሁለት ቢሊዮን 8 መቶ 40 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል።በቢሮዉ የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን መሪ አቶ ሳሙኤል ገለታ ለብስራት ሬድዮ እንደገለፁት ባለፋት አስራ አንድ ወራት 2 ቢሊዮን 7 መቶ 16 ሚሊዮን  288 ሺህ 4መቶ4 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ነበር።

በዚህም 2 ቢሊዮን 8መቶ 40 ሚሊዮን 6መቶ 80 ሺህ  439  ብር  የተሰበሰበ መሆኑን  አቶ ሳሙኤል ገልፀው አፈጻጸሙ ከመቶ ፐርሰንት በላይ እንደሆነ አብራርተዋል።ይህም ከቀጥታ ታክስ፣ቀጥታ ካልሆነና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች የተገኘ ገቢ መሆኑን ቡድን መሪው ጨምረው ለጣቢያችን ገልፀዋል።

በገቢ አሰባሰብ ዙሪያ ጥሩ ውጤት መመዝገቡን የገለፁት አቶ ሳሙኤል ከአደረጃጀት ጋር ተያይዞ ሲስተዋሉ የነበሩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ ከክልል እስከ ወረዳ ክትትልና ድጋፍ የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል። ቡድን መሪዉ አክለውም በበጀት አመቱ ማብቂያ ድረስ 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዷል ማለታቸው ይታወሳል።

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
ለሁለት ተከታታይ ቀናት አውሮፓ በከባድ የሙቀት ማዕበል ተመታች

በመላው አውሮፓ ከባድ የሙቀት ማዕበል እንደቀጠለ ሲሆን ይህም የሰደድ እሳት ስጋት መጨመር እንዲሁም የሰዎች የጤና ማስጠንቀቂያዎች እንዲሰጡ አስገድዳል። በፈረንሳይ ውስጥ ያለው የሙቀት መጠን ማክሰኞ እልፕት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ተከትሎ ከፍተኛ የሙቀት ማስጠንቀቂያ መዲናዋን ፓሪስ ጨምሮ በ 16 ክፍሎች ውስጥ ተሰጥቷል። የኢፍል ታወር አናት ቀኑን ሙሉ ተዘግቶ ውሏል። ብክለት ለመቀነስ የትራፊክ እንቅስቃሴ በማገድ እና የፍጥነት ገደቦች በከተማው ውስጥ መመሪያ ተሰጥቷል።

በጣሊያን በከባድ ሙቀት የተነሳ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል። በስፔን ባርሴሎና በሰኔ ወር ከፍተኛ የሆነ የሙቀት መጠን ላይ ደርሷል ፣ ሴቪልን ጨምሮ የደቡብ ከተሞች ከ 40 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በላይ በላይ የሙቀት መጠኑ ቀጥለዋል። በቱርክ ምዕራባዊ ክልል ሰደድ እሳት አሁንም እየነደደ ሲሆን እስካሁን ከ50,000 በላይ ሰዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለው ደህንነት ወዳለበት ቀጠና ተወስደዋል። በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ፣ በእንግሊዝ ደቡብ-ምስራቅ ሞቃታማ የአየር ሁኔታ የቀጠለ ሲሆን የሙቀት መጠኑ እንደገና ከ 30 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ ይጨምራል ተብሏል።

ቅዳሜና እሁድ በፖርቹጋል እና ስፔን የሙቀት መጠኑ 46.6C እና 46C ሲደርስ የሀገር አቀፍ የሰኔ ወር የሙቀት ክብረ ወሰን ከዚህ ቀደም ከነበረው የበለጠ ሆኗል። ለኃይለኛው ሙቀት ምክንያት የሆነው የከፍተኛ ግፊት ቦታ ወደ ምስራቅ አቅጣጫ ስለሚሄድ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የሙቀት መጠኑ እንደገና ወደ ምስራቅ አካባቢዎች ይጨምራል። ቅዳሜና እሁድ በባልካን ፣ ጣሊያን እና ግሪክ እና በኢቤሪያ ባሕረ ገብ መሬት ላይ የመነስ አዝማሚያ እንደሚኖረው ይጠበቃል። ይሁን እንጂ በደቡባዊ ስፔን ውስጥ ያለው የሙቀት መጠን ለምሳሌ በኮርዶባ፣ ምንም እንኳን ቅዝቃዜ ቢኖረው ሳምንቱን ሙሉ በ40 ዎቹ ውስጥ ይቀጥላል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
ኤርትራ ሠራዊቷን እያጠናከረች ነው ተባለ

ኤርትራ ጦሯን እንደገና እያጠናከረች ነው ፤ ጎሮቤቶቿን በተለይም «ኢትዮጵያን እንዳትረጋጋ እያደረገች ነው» ሲል አንድ መንግስታዊ ያልሆነ የአሜሪካን የመብት ተመልካች ድርጅች አሳሰበ።

ዘ ሴንትሪ የተባለው ድርጅት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ባወጣው ዘገባ በጎርጎሮሳዊው 2018 የጦር መሣሪያ ማዕቀብ የተነሳላት ኤርትራ፣ ጦር ሠራዊቷን እንደገና እየገነባች ፣መከላከያዋን እያጠናከረች ነው፤ ጎረቤቶቿም እንዳይረጋጉ ማድረጓን ቀጥላለች ብሏል።

የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች በጎርጎሮሳዊው 2018 የሰላም ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ የተመድ በኤርትራ ላይ ጥሎት የነበረዉን የጦር መሣሪያ ሽያጭና ግዢ ማዕቀብ አንስቷል።

የአሜሪካዉ ድርጅት ሁኔታው ካልተለወጠ ኤርትራ በዚህ ድርጊቷ ትቀጥላለች ተብሎ ይጠበቃል ሲልም አስጠንቅቋል።

ስለዘገባው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት AFP አስተያየታቸውን የጠየቃቸው የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረመስቀል «የተፈበረከ »ያሉትን ዘገባ «የሌላውን ጥፋት በኤርትራ ላይ ያላከከ» በማለት አጣጥለውታል። አቶ የማነ በአካባቢው የተከሰተው አዲሱ ውጥረት «ሕገ ወጥ» ያሉት «ኢትዮጵያ ወደብና እና የባህር በር የማግኘት ፖሊሲዋን የማስተዋወቅዋ ውጤት ነው ብለዋል።

ጦርነቶችን በፋይናንስ የሚደግፉና በሙስና የሚገኝ ገንዘብ ጉዳይ የሚከታተለው ዘሴንተሪ ኤርትራ የሶማሊያ ጂሀዲስቶችን ትደግፋለች በሚል በጎርጎሮሳዊው 2009 ማዕቀብ ተጥሎባት እንደነበር አስታውሷል። ከዚሁ ጋር በትግራዩ ጦርነት ወቅት ተፈጸሙ የተባሉ በደሎችንም ዘገባው ገምግሟል። የአፍሪቃ ኅብረት እንዳለው ኤርትራም ተሳትፋበታለች በሚባለው በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ቢያንስ 600 ሺህ ሰዎች ተገድለዋል።

Via ዶቼ ቨሌ
#ዳጉ_ጆርናል
ትራምፕ እስራኤል ለ60 ቀናት በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ለመድረስ በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ተስማምታለች ሲሉ ተናገሩ

እስራኤል በጋዛ የ60 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነትን ለማጠናቀቅ “አስፈላጊ ሁኔታዎችን” ተስማምታለች ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናግረዋል። ትረምፕ የግል ንብረታቸው በሆነው ትሩዝ ሶሻል ላይ በለጠፉት ጽሁፍ እንደተናገሩት በቀረበው የተኩስ አቁም ስምምነት ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ “ጦርነቱን ለማስቆም ከሁሉም አካላት ጋር ትሰራለች” ብለዋል። ሰላም ለማምጣት በጣም ጠንክረው የሰሩት ኳታራውያን እና ግብፃውያን ይህንን የመጨረሻውን ሀሳብ ያቀርባሉ ሲሉ ተደምጠዋል።

አክለውም ተስፋ አደርጋለሁ ሃማስ ይህንን ስምምነት ይቀበላል ምክንያቱም የተሻለ ስለሆነ ነው ይህ ካልሆነ ግን እየባሰ ይሄዳል ሲሉ ትራምፕ ጽፈዋል። እስራኤል በስምምነቱ ቅድመ ሁኔታ መስማማቷን ግን አላረጋገጠችም፣ ከሃማስ በኩልም ምንም አይነት አስተያየት አልተሰጠም።የትራምፕ ይህ መግለጫ የተሰማው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት በሚቀጥለው ሳምንት ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር ከሚያደርጉት ውይይት በፊት ነው። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት እንደተናገሩት ኔታንያሁ በጋዛ ያለውን ጦርነት ማቆም ይፈልጋሉ ብዬ አምናለው ደግሞም ይፈፋጋሉ በሚቀጥለው ሳምንት ድርድር የምናደርግ ይመስለኛል ሲሉ ተደምጠዋል።

ጦርነቱ የሚያቆመው ታጋቾቹ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ነው ሲሉም አክለዋል። ወደ 50 የሚጠጉ የእስራኤል ታጋቾች አሁንም በጋዛ ውስጥ ይገኛሉ፣ ከእነዚህ ውስጥ ቢያንስ 20 ያህሉ በህይወት እንዳሉ ይታመናል። ባለፈው ሳምንት አንድ ከፍተኛ የሃማስ ባለስልጣን እንደተናገሩት በጋዛ አዲስ የተኩስ አቁም እና የታጋቾችን የመልቀቅ ስምምነትን ለማጠናከር ጥረታቸውን አሸማጋዮች ጨምረዋል ነገር ግን ከእስራኤል ጋር የሚደረገው ድርድር ቆሟል ሲሉ ተደምጠዋል። እስራኤል ግጭቱ ሊቆም የሚችለው ሃማስ ሙሉ በሙሉ ሲፈርስ ነው ስትል ተናግራለች። ሃማስ ለዘላቂ እርቅ እንዲፈጠር እና እስራኤል ሙሉ በሙሉ ከጋዛ እንድትወጣ ጥሪ ሲያደርግ ቆይቷል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
“የህዳሴ ግድብ ባለፉት 14 አመታት ያለ ምንም የውጪ እርዳታ ሆነ ብድር በራስ አቅም የተገነባ ነው” - ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ

ኢትዮጵያ “ባለፉት 14 አመታት ያለ ምንም የውጪ እርዳታ ሆነ ብድር በራስ አቅም የህዳሴ ግድብን ገንብታለች” ሲሉ የግድብ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አረጋዊ በርኸ (ዶ/ር) አስታወቁ።

በቅርቡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራንፕ “ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን የገነባችው በአሜሪካን የገንዘብ ድጋፍ ነው” ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፤ በፕሬዝዳንቱ ገለጻ ዙሪያ እስካሁን በመንግስት በኩል በይፋ የተባለ ነገር የለም።

የግድቡ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አረጋዊ በርኸ (ዶ/ር) ለፕረዝዳንቱ ምላሽ በሚመስል መልኩ ኢትዮጵያ “ያለ ምንም የውጪ እርዳታ ሆነ ብድር በራስ አቅም ግድቡን መስራቷን ተናግረዋል” ማለታቸውን ከፕሬስ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።  

“እስካሁን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ከ23 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቦ ለግድቡ ውሏል” ማለታቸውንም አካቷል።

“መላው ኢትዮጵያዊ በሞራል፣ በገንዘብ፣ በጉልበት፣ በእውቀትና በዲፕሎማሲ ረገድ መሳተፋቸውን በመግለጽ ርብርቡ በታሪክ ማህደር ተመዝግቦ ለትውልድ የሚዘከር ህያው ድል ነው” ማለታቸውን ዘገባው አመላክቷል።

የግድቡ ፕሮጀክት አፈፃፀም ከ98 ነጥብ 9 በመቶ በላይ መድረሱን የፕሮጀክቱ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

“ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በአገራችን ወግና ባህል እንደአገር ልንሞሸረው ወራት ቀርተውናል” ሲሉ ዳይሬክተሩ መናገራቸውንምዘገባው አስታውቋል።

Via አዲስ ስታንዳርድ
#ዳጉ_ጆርናል
በኢትዮጵያ በየዓመቱ አንድ ሺህ እናቶች ደህንነቱ ባልተጠበቀ መልኩ ፅንስ ሲያቋረጥ ህይወታቸውን ያጣሉ ተባለ

በኢትዮጵያ ለእናቶች ሞት ምክንያት የሆነውን የፅንስ ማቋረጥ አሁን ላይ መቀነስ ተችሏል ቢባልም በዓመት አንድ ሺህ እናቶች ደህንነቱ ባልተጠበቀ መልኩ ፅንስ በማቋረጥ ምክንያት ህይወታቸውን እንደሚያጡ ተገልጿል።

በፕላን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ዶክተር ምስክር ገበየሁ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ደህንነቱ ያልተጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ ምጣኔን መንግስት፣የልማት ድርጅቶች፣የግል የጤና ተቋማት እንዲሁም ማህበረሰቡ በቅንጅት በሰሩት ስራ የእናቶችን ሞት መቀነስ ተችሏል።እ.ኤ.አ በ2008 ላይ ደህንነቱ ባልተጠበቀ መልኩ ይደረግ የነበረውን ፅንስ ማቋረጥ  ቀድሞ ከነበረበት 73 በመቶ በ2014  ላይ ወደ 47 በመቶ  ዝቅ ማድረግ ተችሏል ሲሉ አክለዋል።

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ 3መቶ እስከ 4 መቶ ሺህ የሚደርሱ ሴቶች ደህንነቱ ያልተጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ ያካሂዳሉ ያሉት ዶክተር ምስክር በዓመት ከ9 መቶ እስከ 1ሺህ የሚደርሱ እናቶች በዚህ መንገድ  ጽንስ በማቋረጥ ምክንያት ህይወታቸውን ያጣሉ ብለዋል።እንደዚሁም ከመቶ ሺህ በላይ እናቶች ከዚህ ጋር በተያያዘ በሚገጥማቸው ችግር የህክምና እርዳታ ፈልገው ወደ ጤና ተቋም እንደሚሄዱ አስረድተዋል ።

ንፅህናው ባልተጠበቀ ፅንስ ማቋረጥ ምክንያት ሴቶች ለኢንፌክሽንና ለተለያዩ ችግሮች ስለሚጋለጡ  ህይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ ተነግሯል።በመሆኑም በዚህ ሁኔታ ለህልፈት የሚዳረጉትን ሴቶች መታደግና ደህንነታቸውን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል፡፡

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
#አፋልጉን

በምስሉ ላይ ያለችው እናት ዛሬ ጎፋ ገብርኤል አከባቢ ቤተ ፋጌ ቤተክርስቲያን ሄዳ አልተመለሰችም። ጠፍታብናለች ሀገሩንም አታቀዉም የመርሳት በሽታም ስላለባት ወደ ቤት መመለሻ መንገዱን አታቀውም። የለበሰችው ቀይ ጃኬት ፣ ዥንጉርጉር ቀሚስ እና ሮዝ ሻርፕ ነው። ቄራ ላፍቶና ሜክሲኮ አከባቢ ያያችሁ ካላችኩ እባካቹ በዚህ ስልክ ጠቁሙን 0911573566

#ዳጉ_ጆርናል
ሁለት የቻይና ዜጎች በአሜሪካ ጦር ውስጥ ሰላዮችን ለመመልመል ሞክረዋል በሚል ተከሰሱ

የዩናይትድ ስቴትስ የፍትህ ዲፓርትመንት ሁለት የቻይና ዜጎችን ከሀገሪቱ ወታደራዊ ማዕረግ በመመልመል ክስ ተመሰረተባቸው። የ 38 አመቱ ዩአንስ ቼን እና የ39 ዓመቱ ሊረን ራያ ለቻይና የውጭ የስለላ ድርጅት የመንግስት ደህንነት ሚኒስቴር በመወከል ተከሰዋል።

ግለሰቦቹ ለብሔራዊ ደህንነት መረጃ ክፍያዎችን ማመቻቸት፣ በባህር ኃይል ጣቢያዎች ላይ መረጃን መሰብሰብ እና ለምልመላ ሙከራ ማድረግን ጨምሮ የተለያዩ “የማይታወቅ የስለላ ተግባሮችን” ፈጽመዋል ተብሏል ። ጠቅላይ አቃቤ ህግ ፓሜላ ቦንዲ "ይህ ጉዳይ የቻይና መንግስት እንቅስቃሴ ወደ ወታደሮቻችን ውስጥ ሰርጎ ለመግባት እና ብሄራዊ ደህንነታችንን ከውስጥ ለማዳከም የሚያደርገውን ቀጣይነት ያለው እና ኃይለኛ ጥረት ያሳያል" ብለዋል ።

ከኤፍቢአይ የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ላኢ በቻይና እና በአሜሪካ መካከል "ድብቅ ስራዎችን ለማመቻቸት" ሲንቀሳቀስ ነበር። ከ2021 አካባቢ ጀምሮ፣ ህጋዊ ቋሚ ነዋሪ ነው።። ቼን ደግሞ በአሜሪካ ጦር ውስጥ ሰዎችን እንደሚያውቅ ካረጋገጠ በኋላ፣ ላይ ወደ ውጭ አገር እንዲሄድ በግንኙነቱ እንዲወያይ አሳስቦታል፣ ለቲኬቶቹም ጭምር ለመክፈል እንደሚችል መናገሩም ታውቋል።በአንድ አጋጣሚ ቼን ከባህር ኃይል ቅጥር ጋር ለመገናኘት እና የአውሮፕላን ተሸካሚ የሆነውን ዩኤስኤስ አብርሃም ሊንከንን ለመጎብኘት ወደ ሳንዲያጎ፣ ካሊፎርኒያ ተጉዟል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
የኔይማር ፊርማ ያረፈበትን ኳስ የሰረቀዉ ብራዚላዊ የ 17 አመት እስር ተፈረደበት

እ.ኤ.አ ጥር 8 ቀን 2023 በብራዚል ብራዚሊያ ከተማ በተፈጠረው ሁከት በኔይማር የተፈረመ ኳስ በመስረቅ የተጠረጠረዉ የ34 አመቱ ወጣት የ17 አመት እስራት ተፈርዶበታል ተብሏል።

ዉሳኔዉን የብራዚል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወሰነዉ ሲሆን የ34 አመቱ ኔልሰን ሪቤይሮ ፎንሴካ ጁኒየር በስርቆት ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል ብሏል።

ወንጀለኛዉ ኳሱን የሰረቀዉ በፕሬዚዳንት ቦሌሴናሮ ላይ በተነሳ ተቃዉሞ ወቅት በተፈጠረ ግርግር ሲሆን በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ እና ለወንጀል ስራ በመተባበር በሚል ክስ ቀርቦበታል። ከዚህ ዉጪም በኔይማር ጁኒየር የተፈረመዉን ኳስ መስረቁ ተረጋግጧል።

የብራዚል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነዚህ ጉዳዮች የ 34 አመቱ ጎልማሳ ወጣት ላይ የ 17 አመት እስር ወስኖበታል።

በበረከት ሞገስ

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ነገ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ነገ ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም  በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስትን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የሚሰጡ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

#ዳጉ_ጆርናል
2025/07/04 05:43:23
Back to Top
HTML Embed Code: