Telegram Web Link
ብቸኛ ንብረት ወረሽ ነኝ በሚል  አሳዳጊ  አጎቱን ገድሎ ጉድጓድ  ውስጥ የቀበረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቅንብቢት ወረዳ ታቦቴ መሐመዲ ቀበሌ ሹመሊ ጐሮ የተባለ አካባቢ ነዋሪ  የሆነው ተሼ ብርሀኑ  ተገቢ ያልሆኑ ተግባራት ሲፈፅም እንደነበረ ተገልጿል ።

ተሼ ብርሀኑ እያደገ ሲመጣ የአጎቱ ንብረቶች ብቸኛ ወራሽ መሆኑ ሲገባው የተለያዩ ነገሮችን ማቀድ ይጀምራል። በዚህም ጥር   6 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ የአጎቱን ንብረት ብቸኛ ወራሽ ነኝ በማለት አስቦ ተዘጋጅቶ እና አቅዶ እንደ አባት ያሳደጉት  አጎት በቤታቸው በር ላይ በዱላ ደብድቦ ከገደለ በኋላ ለማዳበርያ በተዘጋጀው  ጉድ ጓድ ውስጥ    መቅበሩን   የቅንብቢት ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ሀላፊ ኢንስፔክተር ጋዲሣ  አደሬ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።በአካባቢው ነዋሪዎች የሚታወቁት አቶ ሞላ ከአካባቢው መሰወርን ተከትሎ ተሼ ብርሀኑ የአጎቱ መሰወር ለፖሊስ ያመለክታል። ፖሊስም የቀረበውን ጥቆማ ተንተርሶ ክትትል ይጀምራል።

ፖሊስ በደረሰው  ጥቆማ የአቶ ሞላን ዱካ ሲከታተል ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም  በአካባቢው አንድ መጥፎ ጠረን መከሰቱንና ለዚህም ከአቶ ሞላ መሰወር ጋር የተያያዘ ሳይሆን አይቀርም የሚል ጥርጣሬ ነበር።ፖሊስ የቀረበውን ጥቆማ ተንተርሶ በአካባቢው ሲደርስ  ከአቶ ሞላ መሰወር ጋር የተያያዘ በመሆኑ በቀጥታ ተጠርጣሪ ነው ያለውን ተሼ ብርሀኑን በቁጥጥር ስር በማዋል ከዳግማዊ ሚኒሊክ የአስክሬን ምርመራ ሞያተኞች በማስመጣት አስክሬኑን ከተቀበረበት ጉድጓድ በማውጣት ለምርመራ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል ልኳል።

ፖሊስም የምርመራ ሂደቱን በስፋት ሲያጠናክር ተጠርጣሪው ተሼ አጐቱ ያላቸው ንብረት ብቸኛ ወራሽ መሆኑን በማወቁ አጎቱ መጥፋታቸውን በማሳወቅ በእሳቸው የተመዘገበውን ንብረት ለመውረስ እንዳሰበና ድርጊቱን እንደ ፈፀመ አምኖ  የድርጊቱን አፈፃፀም ለፖሊስ  እና ለዓቃቢ ህግ መርቶ ያሳያል።የምርመራ መዝገቡም ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ  በዓቃቢ ህግ በኩል በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ቁጥር 539-2 ክስ የተመሰረተ ሲሆን የክስ ሂደቱ ሲከታተል የቆየው የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት ሸኖ ከተማ ላይ ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ውሳኔ አሳልፏል።

ተከሳሽ ተሼ ብርሃኑ ሰውን ለመግደል አስቦ፣ አቅዶ እና ተዘጋጅቶ እንደ ወላጅ ያሳደጉት አጎቱ ላይ የፈፀመው የግድያ ወንጀል እጅግ ነውረኛ፣ጨካኝ እና አደገኛ መሆኑን የሚገልጽ በመሆኑ በ18 ዓመት እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ኢንስፔክተር ጋዲሣ  አደሬ ለብስራት ሬዲዮ  ተናግረዋል።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
በአዲስ አበባ ከተማ የ6ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 95 በመቶ ያህሉ አልፈዋል 

በአዲስ አበባ ከተማ የ2017 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 95 በመቶ ያህሉ 50 በመቶ እና ከዛ በላይ በማምጣት ማለፋቸውን፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ አስታውቀዋል።

የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን አስመልክቶ በተሰጠው መግለጫ፤ በ2017 ዓ.ም ፈተናውን ከወሰዱ 79ሺህ 34 ተማሪዎች መካከል 75ሺህ 85 ተማሪዎች ማለትም 95 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዛ በላይ አስመዝግበው አልፈዋል ተብሏል።

ዘንድሮ በከተማ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች መካከል ከ1 እስከ 4 ከመንግስት ትምህርት ቤቶች መሆናቸው በግልና በመንግስት ትምህርት ቤቶች መካከል ያለዉን የውጤት ልዩነት እጅግ እየተቀራረበ መምጣቱን ማሳያ መሆኑን  ኃላፊው በመግለጫቸው ጠቁመዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በበኩላቸው፤ የ2017 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ፤ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት ዓመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው ብለዋል።

#ዳጉ_ጆርናል
ቢቢሲ ‘ፀረ-ፍልስጤማዊ ዘረኝነት’ ያራምዳል የሚል ክስ ቀረበበት

107 የተቋሙ ሰራተኞች እና 300 የሚዲያ ኢንዱስትሪ ባለሙያዎች በጋራ በመሆን ለቢቢሲ አመራር ይፋዊ ደብዳቤ ፅፈዋል። በደብዳቤውም ቢቢሲ የእስራኤል ጉዳይ ላይ ሲመጣ "ሳንሱር" እና "ለእስራኤል መንግስት እና ወታደራዊ አገልግሎት የህዝብ ግንኙነት ስራ በማከናወን ላይ ነው" በማለት ተቋሙ ላይ ክስ ሰንዝረዋል።

በዴድላይን የታተመው ደብዳቤው በተለይ የቢቢሲ የጋዛ ሜዲክስ ዶክመንተሪ ፊልም እንዳይሰራጭ መወሰኑን ተከትሎ ይህ የቅርብ ጊዜ ውሳኔ "በአጀንዳ ከተመሩ ውሳኔዎች ውስጥ አንዱ ነው" ብለዋል። ሰራተኞቹ "አብዛኛው የቢቢሲ ሽፋን በፀረ-ፍልስጤም ዘረኝነት ይገለጻልም" ብለዋል።

በተጨማሪም ቢቢሲ የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት በፍልስጤማውያን ላይ በሚደረገው ጦርነት የጦር መሳሪያ ሽያጮችን ወይም የህግ አንድምታዎቻቸውን ጨምሮ ምንም አይነት ጉልህ ትንታኔ አላቀረበም ብለዋል። "ከኦክቶበር 2023 ጀምሮ የቢቢሲ ዘገባ ስለ እስራኤል/ፍልስጤም ከራሳችን የአርትኦት ደረጃዎች በታች መሆኑን ለታዳሚዎቻችን ይበልጥ ግልጽ እየሆነ መጥቷል ያሉት ሰራተኞቹ፣ በጋዛ እና በዌስት ባንክ እየተከሰተ ያለውን የቢቢሲ ሽፋን ሊሰጠው የሚገባ ነው ነገር ግን አድማጮቻችን ሊያዩት የሚችሉት ነገር በበርካታ ታማኝ ምንጮች እየተረጋገጠም ሽፋን ተነፍጎታል"ብለዋል።

"የቢቢሲ ኤዲቶሪያል ውሳኔዎች ከእውነታው የራቁ ይመስላሉም ያሉ ሲሆን ውሳኔዎች የተመልካቾችን ፍላጎት ከማገልገል ይልቅ የፖለቲካ አጀንዳን ለማሟላት የሚሰጡ ናቸው ብለን ለመደምደም ተገድደናልም" ብለዋል።

ደብዳቤውን የፈረሙት የቢቢሲ ሰራተኞች ስማቸው ይፋ ያልተደረገ ቢሆንም ጥሪያቸውን ከሚደግፉ የኢንዱስትሪው ሰዎች ግን ካሊድ አብደላ እና ሚርያም ማርጎልየስ ይገኙበታል ተብሏል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
በአዲስ አበባ የጤፍ ዋጋ ባልጨመረበት አንድ እንጀራ እሰከ 30 ብር ድረስ የሚሸጡ ነጋዴዎች መኖራቸዉ ተነገረ

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ በከፍኛ መጠን እየጨመረ የሚገኝ ሲሆን ከዚህም ዉስጥ የእንጀራ ዋጋ ጭማሪ እያሳየ መምጣቱን ሸማቾች ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ለብስራት ሬዲዮ ቅሬታቸውን ያቀረቡ ነዋሪዎች እንደተናገሩት የጤፍ ዋጋ ያለፉት ወራት ካለበት ምንም ዓይነት ጭማሪ ባላሳየበት ሁኔታ የእንጀራ ዋጋ እየጨመረ መምጣቱ ቅር እንዳሰኛቸው ተናግረዋል ።

ከዚህ ቀደም በኪሎ 140 ብር ይሸጥ የነበረው ማኛ ጤፍ አሁንም በ140 እየተሸጠ ይገኛል ። ነጭ ጤፍ በ135 ብር፣ ቀይ ጤፍ ደግሞ በ110 ብር ባለፉት ወራት ባለበት ዋጋ እየተሸጠ መሆኑን ጣቢያችን ባደረገዉ የገበያ ቅኝት ማወቅ ተችሏል ። በተመሳሳይ መልኩ ነጭ ጤፍ በኩንታል በ14ሺህ ብር ቀይ ጤፍ ደግሞ በ11ሺህ ብር ባለበት እየተሸጠ መሆኑን ሸማቾች ተናግረዋል ።

በአዲስ አበባ አንዳንድ አከባቢዎች እንጀራ ጋግረው በሚሸጡ ሱቆች ውስጥ አንድ ነጭ ጤፍ እንጀራ ከ18 እስከ 20 ብር እየተሸጠ ሲሆን አንድ ቀይ ጤፍ እንጀራ በ20 ብር የሚሸጥባቸዉ አከባቢዎች እንዳሉ ሁሉ እስከ 30 ብር የሚሸጥባቸዉ አከባቢዎች መኖራቸዉን ጣቢያችን ባደረገዉ የገበያ ቅኝት ማወቅ ችለናል ።

በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ዩክሬን የምትልከውን የተወሰነ የጦር መሳሪያ ማቆሟን ዋይት ሀውስ አስታወቀ

ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገው ጦርነት እየተባባሰ ባለበት በዚህ ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ኪየቭ የምታደርገውን የተወሰነ የጦር መሳሪያ መላክን ማቆሟን ዋይት ሀውስ አስታውቋል። የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ አና ኬሊ እንዳስታወቁት ውሳኔው የተወሰደው “የአሜሪካን ጥቅም ለማስቀደም ነው” በማለት የመከላከያ ዲፓርትመንት የአሜሪካን “ወታደራዊ እና ለሌሎች ሀገራት ድጋፍ” ግምገማ ተከትሎ እንደሆነም አክለዋል።

ሩሲያ በየካቲት ወር 2022 ዓመት በዩክሬን ላይ ሙሉ ወረራዋን ከጀመረች በኋላ አሜሪካ በአስር ቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ወታደራዊ ርዳታ ልካለች። የትራምፕ አስተዳደር አንዳንድ የአሜሪካ ክምችት በጣም ዝቅተኛ ነው የሚል ስጋት አድሮባቸዋል። የዩክሬን መንግስት በአሜሪካ ውሳኔ ላይ የሰጠው አስተያየት የለም። የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት የትኞቹ ድጋፎች እንደቆሙ ከመናገር ተቆጥበዋል።የሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው የአየር መከላከያ ሚሳኤሎች እና ጥይቶች አሜሪካ ለዩክሬን ከማትልካቸው መሳሪያዎች መካከል እንደሚገኙበት ታውቋል። ባለሥልጣናቱ ለአሜሪካ ሚዲያ እንደተናገሩት ለአፍታ ድጋፍ የተከለከሉት የፓትሪዮት አየር መከላከያ ሚሳኤሎችን፣ የጦር መሣሪያዎችን እና ሌሎች ዩክሬንን የምትጠቀምባቸው የሚሳኤል ሥርዓቶችን ያካታል ብለዋል።

አሜሪካ ይህንን ውሳኔ ብታሳልፍም ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ሩሲያ ሙሉ ወረራ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ከ500 በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ባለስቲክ እና ክሩዝ ሚሳኤሎች በመጠቀም ትልቁን የአየር ላይ ጥቃት ብትፈፅምብኝም ተቋቁሜያለሁ ስትል ዩክሬን አስቸጋሪ ጊዜ ላይ መሆኗን ገልጻ በተናገረችበት ወቅት ነው።የፔንታጎን እርምጃ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ክምችት በጣም እያሽቆለቆለ ነው በሚል ስጋት ላይ የተመሰረተ ነው ሲሉ የአሜሪካ ባለስልጣን ለሲቢኤስ ኒውስ ተናግረዋል፡ ምንም እንኳን ባለስልጣኑ ይህንን ቢሉም አና ኬሊ ግን "የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ሃይሎች ጥንካሬ ምንም ጥያቄ የለውም ይህንን ለማወቅ ደግሞ ኢራን ጠይቁ" ስትል ተናግራለች። በተናጥል የዩናይትድ ስቴትስ የፖሊሲ ምክትል ሴክሬታሪ ኤልብሪጅ ኮልቢ በሰጡት መግለጫ የመከላከያ ዲፓርትመንቱ “ለፕሬዚዳንቱ ለዩክሬን ወታደራዊ ዕርዳታ እንዲቀጥሉ ጠንካራ አማራጮችን መስጠቱን ቀጥሏል” ብለዋል ።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
በከባባድ የሙስና ወንጀሎች ላይ ጥቆማና በቂ ማስረጃ እየቀረበ አለመሆኑ ተገለፀ

የጉራጌ ዞን ፍትህ መምርያ በ2017 በጀት ዓመት 886 መዝገቦች ውሳኔ ተሰጥቶባቸው መዘጋታቸው የገለፀ ሲሆን ከነዚህ ውስጥም 750 መዛግብት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡ 11 ነፃ የተባሉ መዛግብት፣ ምስክር ባለመቅረቡ የተዘጉ 14 መዛግብት፣ ተከሳሽ ባለመቅረቡ የተዘጉ 24 መዛግብት፣ በዕርቅ እልባት ያገኙ 69 መዛግብት ሲሆኑ 78 መዛግብት ደግሞ በቀጠሮ እንደሚገኙ የጉራጌ ዞን ፍትህ መምርያ ኃላፊ አቶ ኤልያስ ሰብለጋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በበጀት ዓመቱ ውሳኔ ከተሰጠባቸው ዋና ዋና የወንጀል ድርጊቶች መካከል፤ በምሁርና አክሊል ወረዳ የግል ተበዳይን አይን ውስጥ ሚጥሚጣ በመጨመርና የተለያዩ የሰውነት ክፍሉን ደጋግሞ በጩቤ በመውጋት ጉዳት አድርሶበት ገንዘብ ዘርፎት ሲሄድ ተበዳይ ባሰማው ጩኸት ተይዞ በከባድ የውንብድና ወንጀል ተከሶ በ18 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተደረገበት ይጠቀሳል፡፡ በእኖር ወረዳ የሚስቱን እህት በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለ ተከሳሽ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት ሲሆን በእዣ ወረዳ የ4 ወር ህፃን የሆነችውን የራስዋን ልጅ በወንዝ ውሀ ውስጥ በመክተት ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገች ግለሰብ በ16 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንድትቀጣ የተወሰነባት ሲሆን በበጀት ዓመቱ ውሳኔ የተሰጠባቸው የወንጀል ድርጊቶች መሆናቸው አቶ ኤልያስ ለጣቢያችን ገልጸዋል፡፡

እንደ መምርያ በበጀት ዓመቱ ጥሩ ስራ መሰራቱን የሚገልፁት አቶ ኤልያስ ነገር ግን ስራን በተቀላጠፈ መልኩ እንዳይሰሩ አንድ አንድ ችግሮች ሲያጋጥሙዋቸው እንደነበር የሚገልፁ ሲሆን ከችግሮቹ መካከልም፣ በአሮጌ ተሽከርካሪ ምክንያት የተቋሙን አብዛኛው በጀት ለተሽከርካሪ ጥገና በመዋሉ ሌሎች ስራዎች በተገቢው መምራት አለመቻሉን፣ በከባባድ የሙስና ወንጀሎች ላይ ጥቆማና በቂ ማስረጃ እየቀረበ አለመሆኑ፣የኦዲት ሪፖርት የጥራትና ተደራሽነት ውስንነት መኖሩና የኦዲት አስመላሽ ግብረ ኃይል ውይይቶች መቆራረጥ መኖሩን፣ በየሴክተሩ የተደረጉ የኦዲት ሪፖርት መረጃዎች ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ በተገቢው ጊዜ ለዐቃቤ ህግ ያለማቅረብ ችገሮች ተስተውለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የአፈፃፀም ክስ ለመመስረት የፍርድ ባለ ዕዳ ንብረት ዝርዝር ማስረጃ ያለማቅረብ እና ፈጣን ምላሽ ያለመስጠት ችግር እና ሴቶችና ሕጻናትን በተመለከተ የሚቀርቡ የህክምና ማስረጃዎች ጥራት እና ተአማኒነት ጉድለት መኖር በበጀት ዓመቱ ከተስተዋሉ ችግሮች መካከል ቀዳሚዎቹ መሆናቸው የጉራጌ ዞን ፍትህ መምርያ ሀላፊ አቶ ኤልያስ ሰብለጋ ለብስራት ሬድዮ ጨምረው ተናግረዋል።

በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል
የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና የሩዋንዳ የሰላም ስምምነት የተፈጸሙ ከባድ ወንጀሎችን አልተመለከትም ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ወቀሰ

በቅርቡ የተፈረመው በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በሩዋንዳ መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ወንጀለኞችን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ያተኮሩ ድንጋጌዎችን ሳያካትት በከባድ ወንጀል ተጎጂዎች ላይ ፍትህን መስጠት አልቻለም ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል  አስታውቋል። ባለፈው ሳምንት በኮንጎ እና በሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዋሽንግተን ዲሲ የተፈረመው ይህ ስምምነት በምስራቅ ኮንጎ ያለውን ከፍተኛ ጦርነት ለማስቆም ተስፋን ይፈጥራል ሲሉ ባለስልጣናት ገልጸዋል።

ስምምነቱ በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት ጦርነቶች መካከል ያለው ግጭት እንዲቆምም ያስችላል። ነገር ግን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ሳይመረመሩ እና ተጠያቂነት ካልተጣለባቸው፣ ሰላማዊ ዜጎች ዋጋ የሚከፍሉበት አስከፊ የመብት ረገጣ ያስከትላል ፤ይህም ለደህንነት ዘላቂነት መቆም አለበት ብሏል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ በምስራቅ ኮንጎ የሚንቀሳቀሱ የኤም 23 አማፂያን በሰሜን እና ደቡብ ኪቩ ግዛቶች ከመንግስት ደጋፊ ታጣቂዎች (ዋዛለንዶ) ጋር መጋጨታቸውን እና የንፁሀን ዜጎች ህይወት ማለፉን ታማኝ ዘገባዎች እንደደረሱት ገልጿል። ኤም 23 ወጣቶችን አፍኖ ወዳልታወቀ ቦታ እየወሰደው መሆኑንም አክሏል። "ሩዋንዳ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ኤም 23 እና የኮንጎ መንግስት ደጋፊ የሆኑትን ዋዛለንዶ ቡድኖችን ለሲቪል ጥበቃ ቅድሚያ ለመስጠት በአስቸኳይ መጫን አለባቸው" ሲል መግለጫው ገልጿል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
ከ15 እስከ 29 የእድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ወጣቶች በይበልጥ ለኤችአይቪ ተጋላጭ እየሆኑ መምጣታቸውን የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ

ባለፉት ዘጠኝ ወራት የኤች አይ ቪ ኤድስ ምርመራ ከተደረገላቸው 216ሺህ 851 ሰዎች ዉስጥ 726ቱ ቫይረሱ በደማቸው ዉስጥ  መገኘቱን የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል ። ምርመራዉ የተካሄደው በሁለት መንገድ ሲሆን የመጀመሪያው ለሌላ ህክምና ወደ ጤና ተቋም የሚመጡ ሰዎችን በባለሙያዎች ተነሳሽነት የህመሙ መንስኤ ኤች አይ ቪ ሊሆን ይችላል በሚል መነሻነት በፍቃደኝነት ላይ ተመስርቶ የሚደረግ ምርመራ ሲሆን 20 ሺህ 194 ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸዉ 620 ዎቹ  ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተገልጿል ።

ሁለተኛው ደግሞ በፍቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ሲሆን ቫይረሱ ሊኖርብን ይችሏል የሚል ጥርጣሬ ያላቸዉ 23ሺህ 782 ሰዎች ምርመራ አድርገው 93ቱ  ቫይረሱ በደማቸው ዉስጥ ተገኝቷል ።በሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የዘርፈ ብዙ ኤችአይቪ ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ዘርፍ ቡድን መሪ ወይዘሮ ትግስት አሸናፊ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ያለፋት ዘጠኝ ወራት ሪፖርት ኤችአይቪ በአዲስ መልክ እየተከሰተ ያለዉ ከ15 እስከ 24 ዕድሜ ክልል ባሉ ሴቶችና ከ18 እስከ 29 ዕድሜ ክልል ባሉ ወንዶች ላይ መሆኑን የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል ።

ከእነዚህ 726 ሰዎች ዉስጥ አብዛኛዉን ቁጥር የሚይዙት ሴቶች ሲሆን 50ዎቹ ደግሞ እናቶች በመሆናቸው ኤችአይቪ ከእናት ወደ ልጅ በእርግዝና ፣በምጥ እና በወሊድ ወቅት የሚተላለፍ በመሆኑ ሴቶች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተነግሯል ።የኤችአይቪ ኤድስ መመርመሪያ ኪት ከአንድ ዓመት በፊት ቅያሪ በነበረበት ሰዓት እጥረት አጋጥሞ የነበረ ቢሆንም በዚህ ዓመት ምንም አይነት እጥረት አለመኖሩን ወይዘሮ ትግስት ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በተመሳሳይ መልኩ አልፎ አልፎ ለህፃናት የሚሰጥ መድኃኒት እጥረት ያጋጥም የነበረ ሲሆን በ2017 ዓመት ያጋጠመ የመድኃኒት እጥረት አለመኖሩ ተገልጿል ።

በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
የአውስትራሊያ አየር መንገድ ኳንትስ በሳይበር ጠለፋ የ6 ሚሊዮን ደንበኞቹ ግላዊ መረጃ መመዝበሩን አስታወቀ

የሳይበር የበይነ መረብ መዝባሪዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደንበኞችን ግላዊ መረጃ የያዘ የመረጃ ቋት ውስጥ ሰብረው በመግባት በአውስትራሊያ ኳንትስ አየር መንገድ ላይ ጉዳት አድርሰዋል። በአመታት ውስጥ ትልቁ ጥሰት ሲሆን ቀውሱ የአየር መንገዱን አመኔታ በማጠልሸት ስሙን መልሶ ለመገንባት እንቅፋት ሆኖበታል። ጠላፊው የጥሪ ማእከልን ኢላማ ያደረገ ሲሆን ስድስት ሚሊዮን ስሞችን፣ ኢሜል አድራሻዎችን፣ ስልክ ቁጥሮችን፣ የልደት ቀኖችን እና ተደጋጋሚ በራሪ ቁጥሮችን የያዘ የሶስተኛ ወገን የደንበኞች አገልግሎት መድረክ ማግኘት መቻሉን አየር መንገዱ ረቡዕ እለት በሰጠው መግለጫ ገልጿል።

አየር መንገዱ የጥሪ ማዕከሉ እና መረጃቸው የተበላሹባቸው ደንበኞቹ ያሉበትን ቦታ አልገለጸም። በመድረክ ላይ ያልተለመደ እንቅስቃሴ ካገኘ በኋላ ጥሰቱን እንዳወቀ እና ወዲያውኑ ለመቆጣጠር እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል። "የተሰረቀውን የመረጃ መጠን መመርመራችንን እንቀጥላለን፣ ምንም እንኳን ጠቃሚ መረጃ እንደተመነተፈ ብናምንም በኦፕሬሽንም ሆነ በደህንነት ላይ ምንም አይነት ተፅዕኖ አያስከትልም ሲል አየር መንገዱ አስታውቋል።ባለፈው ሳምንት የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል የምርመራ ቢሮ የሳይበር ወንጀል ቡድን የሆነው ስካይተርድ ስፓይደር አየር መንገዶች ላይ እያነጣጠረ መሆኑን እና የሃዋይ አየር መንገድ እና የካናዳው ዌስትጄት ጥሰት እንደተፈፀመባቸው አስታውቀዋል።

ኳንትስ አየር መንገድ ግን የሳይበር ጥቃት የፈፀመበትን ቡድን ከመናገር ተቆጥባል። የአውስትራሊያ የሳይበር ደህንነት ድርጅት የአርክቲክ ቮልፍ የደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት ማርክ ቶማስ “ይህን አካሄድ በተለይ አሳሳቢ የሚያደርገው መጠኑ እና ቅንጅቱ ሲሆን ኳንታስ በቅርብ ጊዜም በተመሳሳይ ጠለፋ ተጠቂ ነበር” ብለዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ የ2017 ዓመታዊ የቅድመ ቆጠራ ዝግጅት እየተከናወነ እንደሚገኝ አስታወቀ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመታዊ የቅድመ ቆጠራ ዝግጅት በማዕከላዊ መጋዘኖች እና በሁሉም ቅርንጫፎች እየተከናወነ መሆኑን የክምችት እና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሀመድ ጀማል ተናግረዋል።

በዚህም ሲስተሙን ዝግጁ የማድረግ  መረጃዎችን የማጥራት እንዲሁም መጋዘኖችን ለቆጠራ ዝግጁ የማድረግ ስራ በሁሉም ማዕከሎች እየተሰራ መሆኑን አንስተው ፤ ጤና ተቋማት በቆጠራ ወቅት ግብዐት እንዳይቸገሩ ከመደበኛው የስርጭት መርሀግብር ባሻገር ከዋና መስሪያ ቤት ወደ ቅርንጫፎች ተደራሽ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

አክለውም በቀሩት ጥቂት ቀናት የቅድመ ቆጠራ ስራዎችን በማጠናቀቅ ከሀምሌ 1 ጀምሮ ቆጠራ በማከናወን በአጭር ቀናት ለማጠናቀቅ እቅድ ይዘዉ እየሰሩ መሆኑን አቶ መሀመድ ተናግረዋል።

#ዳጉ_ጆርናል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከምክር ቤት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዛሬው ዕለት ከምክር ቤት አባላት የሚቀርብላቸውን  ጥያቄዎች እንደሚመልሱ እና የ2018 በጀት እንደሚያጸድቁ ይጠበቃል።

ከቀረቡት ጥያቄዎች መካካል ''ዝቋላ አቦ ገዳማዊያን ላይ እየደረሰ ያለው የሞትና የድብደባ ጥቃት ለመከላከል አግባብ ያለው የጸጥታ ሃይል የማይመድበው ለምንድነው''፣ ''በኢትዮጵያ ለሚያጋጥሙ ችግሮች  አፋጣኝ ምላሽ የማይሰጠው ለምንደነው?''፣ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የጸጥታ ችግሩ አልተቀረፈም ለምን?'' የሚሉ ይገኙባቸዋል።

ዶር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ጦርነቱ ይቅር ድርድሩ አይሳካ ነገር ግን ለፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ለኮሚሽነር ጄነራል ደምመላሽ የኢትዮጵያ ወንዞች ጠልፋችሁ ወደ አንድ ባህር አስገቡ እና ኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤት አድርጎት ብለው ቢያዙ በስንት ሳምንት ወይም ወር ውስጥ ኢትዮጵያን የወደብ ባለቤት ያደርጎታል።

አቶ ግዛቸው አየለ ''የመምህራን እና የህክምና ባለሙያዎችን የደሞዝ ማሻሻያ እንዲደረግ ጥያቄ እያነሱ ይገኛሉ ይህንን በተመለከተ ምን አይነት ምላሽ ይሰጣሉ'' የሚል ጥያቄ አቅርበዋል።

አቶ ሙባረክ ኤሊያስ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል ባሉ ዜጎች እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶች እና የጽንፈኛ ቡድኖችን መኖራቸውን ጠቅሰው  አስተማማኝ ሰላም ለመፍጠር እየተሰሩ ነው ይባላል ስራዎች ምንድናቸው? የሚል ጥያቄ አንስተዋል።

''የዲላ ሪፈራል ሆስፒታል ከሰባት ዓመት በፊት ጀምሮ እስካሁን አልተጠናቀቀም ምክንያቱ ምንድው'' የሚል ጥያቄ  ቀርቧል።

ወይዘሮ መስከረም ሃይሉ ''መንግስት የዋጋ ግሽበት እየቀነሰ እንዳለ ቢገልጽም መሬት ላይ ያለው እውነት ተመሳሳይ አደለም  የኑሮ ውድነት የዋጋ ግሽበት እና ስራአጥነት በተመለከተ አሁንም ለውጥ የለም'' ስለዚህ  ጉዳይ ማብራሪያ እንዲሰጡበት ጥያቄ ቀርቧል?

ዶ/ር ታደለ ቡራቃ የመድሀኒት አቅርቦት እና አሰጣጥ ችግር በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ እያስነሱ ይገኛሉ። በሌላው በኩል የጤና ባለሞያዎች የሚያነሱት ችግር እየተስተዋለ ነው በመሆኑም የተገልጋይ ህዝብ  እና የአገልግሎት ሰጪ ባለሞያዎች ፍላጎት በማጣጣም ህዝቡ የተሟላ ጥራት እና ብቃት ያለው የጤና አገልግሎት ከበቂ የመድሀኒት አቅርቦት ጋር እንዲያገኝ በማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ቢብራራልን ።

''በተለያዪ አካባቢዎች በተፈጥሮአዊ እና ሰውሰራሽ ምክንያቶች ከትምህርት ገበታቸው የራቁ ተማሪዎችን ለመመለስ ምን አይነት ስራ እየተሰራ ይገኛል?''

ዶክተር አበባው ደሳለኝ ''የህክምና ባለሙያዎች የስራ ማቆም አድማ አድርገው ጥያቄ  ቢያቀርቡም መንግስት የፖለቲካ  ስያሜ በመስጠት ጥያቄያቸው ሳይፈታ አዳፍኖ ቀርቷል በመሆኑም  መንግስት ድሀ ተኮር የሪፎርም አራማጅ ነኝ እያለ ስራ የሚጀምረው መቼ ነው?'' የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበዋል።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
እስራኤል በደቡባዊ ሶሪያ የሚገኘውን የኢራን 'የሽብር ቡድን' እንደያዘች ተናገረች

የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ሶሪያ የሚገኘውን “በኢራን የሚንቀሳቀስ የአሸባሪ ቡድን” መያዙን ገልፆል። የእስራኤል መንግስት በሶሪያ "ምንም አይነት የአሸባሪዎች አካል እንዳይፈጠር" እና የእስራኤል ዜጎችን እና የጎላን ሃይትስ ነዋሪዎችን ለመጠበቅ እየሰራሁ ነው ብሏል።

አከባቢው አብዛኛው አለም አቀፉ ማህበረሰብ በወረራ የተያዘ የሶሪያ ምድር እንደሆነ ቢቆጥርም፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን የእስራኤል ሉዓላዊ ግዛት ነው በማለት ለመጀመሪያ ጊዜ በስልጣን ዘመናቸው እውቅና ሰጥተዋል።

በታህሳስ ወር የረዥም ጊዜ የሶሪያ ገዥ በሽር አል አሳድ መውደቃቸውን ተከትሎ እስራኤል ወደ ፊት በመንቀሳቀስ በጎላን ሃይትስ እና በደቡብ ሶሪያ መካከል ያለውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጥበቃ ቀጠና የወረረች ሲሆን የሀገሪቱን ወታደራዊ አቅም ላይ ያነጣጠረ የአየር ላይ ጥቃት ፈፅማለች። የእስራኤል ባለስልጣናት እንዲሁ ህገወጥ ሰፈራዎችን በዚያ አከባቢ መስፋፋቱን አምነዋል።

በጎላን ኮረብታዎች ውስጥ ወደ 31 ሺ የሚጠጉ እስራኤላውያን ሰፋሪዎች በደርዘን በሚቆጠሩ ህገወጥ የእስራኤል ሰፈሮች ውስጥ ይኖራሉ። ኢራን አል አሳድን የሶሪያ ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ ለታጣቂዎች፣ የጦር መሳሪያዎች እና ወታደራዊ ስልጠናዎችን በመስጠት በስልጣን ላይ እንዲቆይ ለማድረግ ስትጥር ነበር።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

👉የዘንድሮው ዓመት በኢትዮጵያ ታሪክ በሁሉም ዘርፍ ታይቶ የማይታወቅ ድል የተመዘገበበት ነው፡፡

👉የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም በመጀመራችን ትርጉም ያለው ሚና፤ ትርጉም ያለው ውጤት ተገኝቶበታል፡፡

👉ወደ ማክሮ ኢኮኖሚ ያስገቡን ጉዳዮች አንዱ የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶች ናቸው፤ በስራ አጥነት፣ በዋጋ ግሽበት፣ በወጪና ገቢ ንግድ ሚዛን መጓደል ሊገለፅ የሚችል ነው። ሁለተኛው ለግሉ ዘርፍ የስራ አካባቢው ምቹ አልነበረም። ሶስተኛው ምርታማነት ነው።

👉በግብርናም በኢንዱስትሪም ምርታማነታችን ውስን ነበር። ይህም በርካታ ተግዳሮቶች እነዲስተናገዱ አድርጓል። አራተኛው ተወዳዳሪ የኢኮኖሚ ሁኔታን አልፈጠርንም። እነዚህን ጉዳዮች ጨክነን በመፍታት የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቱን መፍታት እንችላለን ብለን ነው ወደ ተግባር የገባነው።

👉የነበረውን ሳናፈርስ በነበረው ላይ የጎደለውን እየሞላን እና እያዘመንን የተሻለች፤ ታሪኳን ያልዘነጋች ኢትዮጵያን መስራት ይቻላል፡፡

👉እንደ እኛ ያለ የሌሎች እጅ እና ዕርዳታ እየጠበቀ ለሚኖር ሀገር ከፍተኛ ፈተና እንዳያጋጥመው ሆኗል፡፡

👉ኢትዮጵያ ሰፊ ፈተና ቢኖርባትም በመላው ሕዝብ ትብብር ባለፈው ዓመት በመላው የኢትዮጵያ የ8 ነጥብ 1 በመቶ እድገት ማምጣት ተችሏል፡፡

Via FBC
#ዳጉ_ጆርናል
2025/07/04 23:59:56
Back to Top
HTML Embed Code: