Telegram Web Link
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የጋዝ ምርትን ለገበያ  ልታውል ነው  ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስር አብይ አህመድ በዛሬው እለት ከምክር ቤት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

በምላሻቸውም ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የጋዝ ምርትን ለገበያ  ልታውል ነው ብለዋል። ይህ የጋዝ ፕላን ባንዳዎች እዳያበላሹት ደብቀን የሰራነው የጋዝ ፕላንት ተጠናቋል ሲሉ ገልፀዋል።

ጋዝ የመጀመሪያው ፌዝ አልቋል በቅርቡ ይመረቃል እንዲሁም ሁለተኛው ፌዝ ይጀመራል ብለዋል ።

የግብርናው ሴክተር የተሟላ ውጤት የሚያስገኘው የማዳበሪያ ፋብሪካ ሲኖራት ብቻ ነውም ሲሉ ገልፀዋል ።

በምህረት ታደሰ
#ዳጉ_ጆርናል
23 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ከሴፍቲነት ተረጅነት ወጥተዋል  - ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)

በርካታ የኢትዮጵያ  ህዝብ የሚሳተፍበት  ሴክተር ግብርና ነው ።  በሴክተሩ  6.1 ፐርሰን ዕድገት እንዲያመጣ  ታቅዶ  የነበረ መሆኑን እንዲሁም   ኢትዮጵያ  የምግብ ሉዓላዊነት  ማረጋገጥ አለባት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ገልጸዋል።

ባለፉት ሁለት ዓመታት 27 ሚሊዮን  ሰዎች በሴፍቲኔት የታቀፉ የነበሩት ወደ ግብርና ዘርፍ እንዲካተቱ ሲሰራ መቆየቱ ገልጸዋል ። በዚህም 23 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ከሴፍቲነት ተረጅነት መውጣታቸውን አክለዋል።

ባለፈው ዓመት 26 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ታርሶ የነበረ መሆኑን በማስታወስ ዘንድሮ   31.8 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ማረስ መቻሉን እና 1.5 ቢሊዮን  ኩንታል መሰብሰብ ማቻሉን 24.7% አድገት ማሳየቱን ገልጸዋል ።

20 የሚሆኑ ግድቦች  እየተሰሩ ሲሆን ሲጠናቀቁ ከ220 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ማልማት ይቻላል።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
ኢትዮጵያ ውስጥ በዲጂታል ሲስተም የገንዘብ ዝውውር 12.5 ትሪሊየን ደርሷል

በፋይናንስ ዘርፍ በዚህ ዓመት ብድር ከዓምናው 75 በመቶ ጨምሯል ።ለግል ሴክተር 80በመቶ ሼር አላቸው ብለዋል።

የፋይናንስ ሴክተሩ በከፍተኛ ሁኔታ ተነቃቅቷል ብለዋል ።የማክሮ ኢኮኖሚው መሻሻል  መካከል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  የኢትዮጵያ መንግስት በቦንድ እና በተለያየ ፕሮጀክት ስም ከ850 እስከ 900ቢሊየን ብር ገደማ እዳ የነበረበት ቢሆንም የማክሮ ኢኮኖሚ መሻሻል  በመደረጉ ግን ወደ መንግስት መዘዋወር ችሏል ብለዋል።

በተጨማሪም 700 ሚለየን ዶላር  ድጋፍ በመደረጉ ንግድ ባንክ ድኗል ፋይናንሻል ሴክተሩንም ማዳን ተችሏል ብለዋል።

ፋይናንሻል ሴክተር ውስጥ ዲጂታል ሲስተም  ያለው ሚና በዚህ ሶስት ዓመት ውስጥ 55 ሚለየን የሚሆን ሰው  የሞባይል ገንዘብ ተጠቃሚ ሆኗል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የካሽ የገንዘብ ዝውውር በዲጂታል ተበልጧል ።በዲጂታል የገንዘብ ዝውውር 12.5 ትሪሊየን ደርሷል  ሲሉ ገልፀዋል።

በምህረት ታደሰ

#ዳጉ_ጆርናል
በኢትዮጵያ  46 ሺህ የሚሆኑ የታክስ ተመዝጋቢዎች ግብር አይከፍሉም  ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር )


የማዕድን ስራ ከዚህ በፊት የነበሩ መሪዎች የሰጡት ትኩረት አነስተኛ  ስለነበረ ነው እንጂ በትኩረት ሊሰራበት የሚገባ  ሴክተር ነው ተብሏል።

ባለፈው ዓመት ወርቅ 4 ቶን ወደ ውጪ የተላከ ቢሆንም በዚህ ዓመት 37 ቶን ወደ ውጪ ኤክስፖርት መደረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ አህመድ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል 46 ሺህ የሚሆኑ የታክስ ተመዝጋቢዎች ግብር አይከፍሉም ። የማይከፍሉት ሰርቼ ከሰርኩኝ ፣ ገቢ እና ወጪ ተመሳሳይ ነው ከፊሉ ደግሞ ሪፖርት ባለማቅረባቸው  መሆኑ ተገልጿል ። ንግድ ፍቃድ ወስደው ግብር መክፈል ከሚገባቸው  ውስጥ የሚከፍሉት 37 በመቶ ብቻ ናቸው።

ይህ 37በመቶ የሚባለው የሚከፍለው 60 በመቶ የሚሆነውን የኢትዮጵያ ገቢ ሲሆን 40 በመቶ የሚሆነውን  የሚሰበሰበው ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ነው ተብሏል ።

የታክስ አስተዳደር ፣ የግብር ስወራ እና የገቢ እና ወጪ አሰባሰብ ሂደት ስርዓቱን የጠበቀ አለመሆኑ በዘርፉ ከፍተኛ ችግር የፈጠሩ ምክንያቶች ናቸው ። ብሄራዊ ባንክ ምንም ብድር ሳይወሰድ ዓመቱ ማለቁ የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ  ያለው ነው ተብሏል።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
በተያዘው ዓመት 92 ቢሊየን  ብር እዳ ተፍሏል- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እህመድ(ዶ/ር)


ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ 42ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው የመንግስትን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡


በእዳ ዙሪያ  ዙሪያ በተመለከተ በሰጡት ማብራርያ   በተያዘው ዓመት 92 ቢሊየን ብር እዳ መከፈሉን ገልጸዋል፡።

የእዳ ሽግሽጉ በተመለከተ በትላንትናው እለት በፈረንሳይ የመጨረሻውን ስምምነት ገንዘብ ሚኒስቴር ተፈራርሟል።

3.5 ቢሊየን ዶላር ከዚህ ቀደም የነበሩ መንግስታት ተበድረው እዳው ወደ እኛ ተሸጋግሮ የነበረ በመሆኑ እዳው  ወደ ልጆቻችን መሸጋገር የለበትም አላግባብ ነው በማለት እዳው በአራት ዓመት ድርድር ውስጥ እንዲሰረዝ ተደረጓል።

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
ዜና ህልፈት !!!!

የሊቨርፑሉ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ዲዮጎ ጆታ በመኪና አደጋ ገና በሀያ ዘጠኝ ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል 🥺

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
ጆታ ከ 5 ቀናት በፊት ነበር የሰርግ ስነስርዓቱን የፈጸመዉ

በስፔን ዛሞራ ግዛት ዛሬ ህይወቱ አለፈ

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport
በመስከረም ወር የህዳሴ ግድብ ይመረቃል

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ክረምቱ ሲያልቅ ይመረቃል ብለዋል ።

ግድቡ ለሱዳን እና ግብፅ በረከታቸው ነው ።በግድቡ የግብፅ አስዋን ግድብ አንድም ቢሆን አልጎደለም ።

ውሀውን በጋራ እንጠቀማለን ብለናል ንግግር እና ድርድር ግን ከተፈለገ አሁንም ዝግጁ ነን ብለዋል።

በተያያዘ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ስልጣን ያለው ምክር ቤት ስለሆነ ለተፋሰሱ ሀገራት በሙሉ መስከረም ዝናብ ጋብ ሲል ህዳሴ ሲመረቅ የደስታችን ተካፋይ እንዲሆኑ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

በምህረት ታደሰ
#ዳጉ_ጆርናል
ባለፉት አምስት ዓመታት 1ሚሊየን ቤቶች ተገምብተዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ እህመድ(ዶ/ር)

የመኖሪያ ቤት ግንባታን በተመለከተ
ቤት ያላቸው የሚመስሉ ቤት አልባ ሰዎች በርካታ ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

20 እና 30 ዓመት መፀዳጃ ቤት አይቶ የማያቅ ሰው ቤት አለው ማለት ከባድ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ 42ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።

በመንግስትና  በግል ባለሀብቶች ትብብር በርካታ ህንፃ የተገነባ ሲሆን በክረምት በጎፍቃደዮች  ከ100 ሺ ያላነሱ ቤት ይታደሳሉ ።

ባለፉት አምስት  ዓመታት 1ሚሊየን ቤቶች የተገነቡ ሲሆን  በአሁኑ ሰዓት 265 ሺ ገደማ ቤቶች አየተገነቡ ይገኛል።

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ የአፍሪካ ህብረት ሄሊኮፕተር ተከሰከሰ

በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ማክሰኞ እለት በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ተከስክሶ በእሳት ጋይቷል ሲል መንግስታዊው የዜና አውታር ዘግቧል። በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ድጋፍና ማረጋጋት ተልዕኮ (አውሶም) ሄሊኮፕተር ስምንት ሰዎችን አሳፍራ ስታርፍ ወድቃለች ሲል የሶማሊያ መንግስታዊ ቴሌቪዥን በኤክስ ገፁ ላይ ያስታወቀ ሲሆን እሳቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል።

በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ስለመድረሱ አልታወቀም ። የአፍሪካ ህብረት ድጋፍና ማረጋጋት ተልዕኮ (አውሶም) ቃል አቀባይ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። በአውሮፕላን ማረፊያው የሚሰሩት ፋራህ አብዱሌ "ፍንዳታውን ሰምተናል በሄሊኮፕተር ላይ ጭስ እና የእሳት ነበልባል አይተናል" ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል። "ጭሱ ሄሊኮፕተሩን ሙሉ በሙሉ ሸፍኖታል"። አውሶም በሶማሊያ የሀገሪቱን ጦር አልሸባብን ለመከላከል ከ11,000 በላይ ወታደሮቹን አሰማርቷል።

የአልቃይዳ ክንፍ ቡድን የሆነው አልሻባብ የሶማሊያን አለም አቀፍ እውቅና ያለውን መንግስት ለመገልበጥ እና የራሱን አገዛዝ ለመመስረት ለሁለት አስርት አመታት ያህል ሲታገል ቆይቷል። በዚህም የተለያዩ የደፈጣ ውጊያዎችን እና የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃትን መዲናዋን ሞቃዲሾን ጨምሮ በተለያዩ የሶማሊያ ግዛቶች በመፈፀም ቡድኑ ይታወቃል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
በአዲስ አበባ ከተማ ገና የተወለደች ጨቅላ ህጻን መፀዳጃ ቤት ውስጥ ተጥላ ህይወቷ አልፎ ተገኘ።

ሰኔ 25 እሮብ ከምሽቱ 3:00 ገደማ በአዲስ ከተማ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 12 ኮንጎ ሰፈር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በሚገኝ የመኖሪየ ቤት መጸዳጃ ቤት ዉስጥ ገና የተወለደች ጨቅላ ህጻን ተጥላ ህይወቷ አልፎ መገኘቱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የጨቅላ ህጻኗን አስከሬንን ከመጸዳጃ ቤቱ አዉጥተዉ ለፖሊስ ማስረከባቸውንም የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ።

ህጻኗን ማን በመጸዳጃ ቤት ዉስጥ ከተታት የሚለዉን ጉዳይ ፖሊስ እያጣራ ይገኛል ተብላል።

እራሳቸዉን መከላከል የማይችሉ ገና የተወለዱ ህጻናትን በዚህ ሁኔታ ህይወታቸዉ እንዲያልፍ ማድረግ በህግ ሆነ በሞራል ተጠያቂነትን ያስከትላል ሲል ኮሚሽኑ ማስታወቁን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

እንዲህ አይነቱ ወንጀል ከመፈጸም ህጻናትን ተረክበዉ በእንክብካቤ ለሚያሳድጉ ተቋማት ወይም ከፖሊስ ጋር ተነጋግር መፍትሄ መስጠት እየተገባ የጨቅላ ህጻናትን ህይወት በዚህ ሁኔታ እንዲያልፍ ማድረግ ተቀባይነት የለዉምም ሲል ኮሚሽኑ አሳስቧል።

በትግስት ላቀው
#ዳጉ_ጆርናል
ዛምቢያ ወደ ሲንጋፖር የሚላከውን ዚንክ ኦክሳይድ ለመስረቅ የሞከሩ አራት ቻይናውያንን በቁጥጥር ስር አዋለች

የዛምቢያ ፖሊስ አራት የቻይና ዜጎችን እና ሶስት የአካባቢውን ነዋሪዎች ከ45 ሺ የአሜሪካን ዶላር በላይ የሚገመት ዚንክ ኦክሳይድ ለመስረቅ ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ጭነቱ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሉቡምባሺ ግዛት ከሚገኘው የማዕድን ማውጫ ሲሆን በሲንጋፖር ወደሚገኘው ትራፊጉራ ኤዥያ ትሬዲንግ የተጓዘ መሆኑን የፖሊስ ቃል አቀባይ ራኤ ሃሙንጋ ከዋና ከተማዋ ሉሳካ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ጭነቱ በታንዛኒያ ዳሬሰላም ኮሪደር በኩል ከክልሉ ሊወጣ ነበር ተብሏል። ነገር ግን የደህንነት ቁጥጥር ስርአቶች ተሽከርካሪው መውጣቱን ካሳወቁ በኋላ ተይዘዋል ። ሃሙንጋ እንደተናገሩት ፖሊሶች እቃው ሲወርድበት የነበረውን ቦታ በመውረር ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር አውለዋል። "ተጠርጣሪዎቹ በአሁኑ ጊዜ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙ ሲሆን የጭነት ተሽከርካሪው እና ምርቱ በማስረጃነት ተይዛል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
በትግራይ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ኤምባሲዎችን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው “በፍጥነት” ሚናቸውን እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ

የትግራይ ክልል “ወደ ጦርነት እንዳይገባ” የሃይማኖት አባቶች፣ ባለሃብቶች፣ ምሁራን እና ኤምባሲዎች ሚናቸውን “በፍጥነት” እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ። በትግራይ ውጊያ ከተጀመረ፤ ከዚህ በፊት ከነበረው የተለየ እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጠንቅቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 26፤ 2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ነው። በሁለት ክፍል የቀረበው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ቅድሚያውን እና ሰፊውን ጊዜ የሰጠው፤ የኢኮኖሚ ጉዳዮችን በተመለከተ ለቀረቡ ጥያቄዎች ነበር።

ሶስት ሰዓት ገደማ ከፈጀው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ውስጥ የሰላም እና ጸጥታ ጉዳይ የተመደበለት አንድ ሰዓት ያልሞላ ጊዜ ነበር። በዚህኛው የማብራሪያ ክፍል ከተነሱ ጉዳዮች ውስጥ ትግራይ እና ኤርትራን የተመለከቱት ይገኙበታል።

“የትግራይ ህዝብ መቶ ፐርሰንት ጦርነት አይፈልግም” ያሉት አብይ፤ ከህዝብ ፍላጎት እና አሁን ካለው ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታ ውጭ በክልሉ ውጊያ ቢቀሰቀስ “ዓለም ደንታ የለውም” ብለዋል። “[ዓለም] ብዙ ውጊያ እያስተናገደ ስለሆነ፤ ጆሮም የለውም፣ ጊዜም የለውም። ዓለም ጊዜ ቢኖረው ኖሮ ሱዳንን ያዳምጥ ነበር” ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተደምጠዋል።

Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
#ዳጉ_ጆርናል
በኢንዶኔዥያ ባሊ 65 ሰዎችን አሳፍራ የነበረች መርከብ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ይዛ መሰወሯ ተገለፀ

በባሊ ሪዞርት ደሴት ላይ መርከቧ በመስጠሟ ቢያንስ አራት ሰዎች መሞታቸውን እና 38ቱ ጠፍተዋል ሲሉ የአከባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል። በኢንዶኔዥያዋ የሪዞርት ደሴት በባሊ 65 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ በመስጠሙ ቢያንስ አራት ሰዎች መሞታቸውን እና በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ጠፍተዋል ተብሏል።

የኬ.ኤም.ፒ ቱኑ ፕራታማ ጃያ የምስራቅ ጃቫ ባንዩዋንጊ ወደብ ፣ የኢንዶኔዥያ ፍለጋ እና ነፍስ አድን ኤጀንሲ ፣ መርከቧ ባዳን ናሽናል ፔንካሪያን ዳን ለቃ ከወጣች በኋላ ብዙም ሳይቆይ ሰምጣለች። የነፍስ አድን ሰራተኞች 38 ሰዎችን እየፈለጉ ነው ብለዋል።

በነፍስ አድን ስራው ውስጥ ከተገኙት 23 ሰዎች መካከል ዘጠኝ መርከበኞችን ያካተተ መሆኑን ባለስልጣናቱ ገልጸዋል። የባንዩዋንጊ ፖሊስ አዛዥ ራማ ሳምታማ ፑትራ እንደተናገሩት ብዙዎቹ የተረፉት በውቅያኖስ ውስጥ ለሰዓታት ሲንከራተቱ ከቆዩ በኋላ በመጀመሪያ ራሳቸውን ስተው ነበር ብለዋል።

ሳውዲ አረቢያን በመጎብኘት ላይ ያሉት የኢንዶኔዥያው ፕሬዝዳንት ፕራቦዎ ሱቢያንቶ አፋጣኝ አስቸኳይ የደህንነት ምላሽ እንዲሰጡ ያዘዙ ሲሆን የካቢኔው ፀሐፊ ቴዲ ኢንድራ ዊጃያ በሰጡት መግለጫ የአደጋው መንስኤ "መጥፎ የአየር ጠባይ" ነው ብለዋል።

የባህር ላይ አደጋዎች በኢንዶኔዥያ ደሴቶች ውስጥ የተለመደ ክስተት ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ በመጋቢት ወር 16 ሰዎችን አሳፍራ የነበረች ጀልባ ከባሊ ወጣ ብሎ በሚገኝ የውሃ አካል ውስጥ ተገልብጣ አንዲት አውስትራሊያዊት ሴት ገድላ ቢያንስ አንድ ሌላ ሰው አቁስላለች። በ2018 በሱማትራ ደሴት ውስጥ ካሉት ጥልቅ ሀይቆች በአንዱ ውስጥ ጀልባ በመስጠሟ ምክንያት 150 ሰዎች መሞታቸውም አይዘነጋም።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
#አፋልጉን

እኚህ በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው አባት አቶ #መኮንን ይመር ይባላሉ በሰኔ 24 ቀን 2017 10:00 ሰዓት አካባቢ ከመኖሪያ ቤታቸው አዲስ አበባ ጎሮ ትምህርት ቤት አካባቢ የወጡ ሲሆን እስካሁን አልተመለሱም።

ለለሚ ኩራ ጎሮ ፖሊስ መምሪያ ያሳወቅን ሲሆን ምናልባት የድሮ ሰፈራቸው 6ኪሎ አካባቢ እንዲሁም ይኖራሉ ተብሎ የታሰቡ ቦታዎች ሁሉ ብንፈልግም ልናገኛቸው አልቻልንም።

አቶ መኮንን ይመር አልፎ አልፎ የመርሳት ችግር ያለባቸው ሲሆን

እድሜ - 80
ቁመት - 1.80
ያገኛቸው በዚህ ስልክ እንዲያሳውቀን ስንል እንማፀናለን።

ፈላጊ ልጆቻቸው:—0995459778
0913902318
0912184048

#ዳጉ_ጆርናል
ኢትዮጵያ ባለፋት 11 ወራት ለሽያጭ ያቀረበቻቸው ሁሉም የቡና ዓይነቶች ያስገኙት ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ጭማሪ አሳይቷል

ኢትዮጵያ  በበጀት ዓመቱ አሥራ አንድ ወራት  4መቶ9 ሺህ 605 ቶን ቡናን ለውጪ ገበያ አቅርባ 2.244 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ አግኝታለች ሲል የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል።

በባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳህለ ማርያም ገብረ መድህን ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት አፈጻጸሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ1.035.38 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም 86 በመቶ ጭማሪ ተመዝግቦበታል፡፡

ባለፋት  አሥራ አንድ ወራት የተላከዉ ቡና በመዳረሻ ሀገራት ሲታይ ጀርመን ፣ ሳዉድ አረቢያ እንዲሁም አሜሪካ ትልቁን የውጪ ምንዛሬ ገቢ  በማስመዝገብ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን ይዘዋል ብለዋል፡፡

ለሽያጭ ከቀረቡት የቡና ዓይነቶች መካከል በገቢ ደረጃ ነቀምቴ ቀዳሚውን ድርሻ መያዙን አቶ ሳህለማርያም ገልፀው ሲዳማ  እና ጅማ ይከተላሉ ብለዋል።

በጥቅሉ የስድስቱ ዋና ዋና የቡና አይነቶች በአጠቃላይ በመጠን እና በገቢ 88 በመቶ ድርሻ አላቸው በማለት ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡

የእነዚህ ስድስት የቡና ዓይነቶች አፈፃፀም ከ2016 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር በገቢ ሲወዳደር ሁሉም የቡና ዓይነቶች ጭማሪ አሳይተዋል።

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
ጆታ ወዴት ነበር ሲጓዝ የነበረዉ?

የሊቨርፑል እና የፖርቱጋሉ የፊት መስመር ተጨዋች ዲዬጎ ጆታ በዛሬዉ እለት ማለዳ ላይ ህይወቱ ማለፉ አለምን አስደንግጧል። ማህበራዊ ሚደያዉ በተለይም የኤክስ ገጽ በሙሉ በ ጆታ እና ወንድሙ ህልፈት የተሰማዉን ሀዘን እየገለጸ ነዉ።

ጆታ በስፔን ዛሞራ ግዛት በደረሰበት የመኪና አደጋ ነበር ከወንድሙ ጋር ህይወታቸዉን ያጡት።

ለመሆኑ ጆታ ወዴት ነበር ሲጓዝ የነበረዉ የሚለዉን የስፖርቱ ሚዲያዎች አጣርተዋል። ዳጉ ጆርናል ስፖርትም ለመመልከት ሞክሯል።

እንደዘገባዎቹ ከሆነ ጆታ ወደ ሰሜናዊ ሳንታዴር ነበር ከወንድሙ ጋር በመሆን ሲጓዝ የነበረዉ። ለምን ካሉ ደግሞ ወደ ብሪታንያ ግዛት የሚያደርሰዉን ጀልባ ለመሳፈር ነበር ሲል ሲኤንኤን ፖርቱጋል ዘግቧል።

እንደ ሚረር ዘገባ ከሆነ ደግሞ ጆታ በቅርቡ ከሳምባ ጋር በተገናኘ ህመም የቀዶ ህክምና አድርጎ ነበር ተብሏል። በዚህ የተነሳም ዶክተሮች የአዉሮፕላን በረራን ለተወሰነ ጊዜ እንዳያደርግ መክረዉት ነበር።

በዚህ የተነሳ ጆታ ለቅድመ ዉድድር ዝግጅት ወደ ሊቨርፑል ለመመለስ አስቦ በመጓዝ ሳለ ነዉ የትራፊክ አደጋዉ ያጋጠመዉ ተብሏል።

አደጋዉ የደረሰበት አዉራ ጎዳናም በስፔን ከፍተኛ የመኪና አደጋ የሚታይበት እና አደገኛዉ መንገድ ነዉ ብሏል ዘገባዉ።

በበረከት ሞገስ

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport
ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ ባንክ ኃላፊ በአስቸኳይ ስራ እንዲለቁ ጠየቁ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጄሮም ፓውል ላይ የሰነዘሩትን ትችት በማጠናከር የፌደራል ሪዘርቭ ሊቀመንበር በአስቸኳይ ስራ እንዲያቆሙ ጠይቀዋል። ትራምፕ የግል ንብረታቸው በሆነው ትሩዝ  የማኅበራዊ መድረክ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ "'በጣም ዘግይቷል' በአስቸኳይ ስራ መልቀቅ አለባቸው" ብለዋል። በተጨማሪም ፓውል በማዕከላዊ ባንክ ዋሽንግተን ዋና መሥሪያ ቤት እድሳት ላይ በሰጡት ምስክርነት ላይ ምርመራ እንዲደረግ የዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል የቤቶች ተቆጣጣሪን ገልፀው ተናግረዋል።

ትራምፕ በመጀመሪያ የስልጣን ዘመናቸው ፓውልን የፌዴሬሽኑ ሊቀመንበር አድርገው ሾመዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የወለድ ምጣኔን አልቀነሰም በማለታቸው ደጋግሞ ሲወቅሰው ቆይተዋል። ነገር ግን ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን የማውረድ ስልጣናቸውን እስከምንድ ድረስ እንደሆነ ግልፅ አይደለም።

ፕሬዚዳንቱ በ​​ፓውል ላይ ትችታቸውን ቢቀጥሉም ፣ በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ “ፓውልን የማባረር ምንም ፍላጎት እንደሌላቸው” ተናግረዋል ። ትራምፕ የኢኮኖሚ እድገትን ለማሳደግ የፌደራል ሪዘርቭ የወለድ ተመኖችን እንዲቀንስ ይፈልጋሉ። ፓውል እንደተናገሩት የትራምፕ የታሪፍ ፖሊሲዎች ተጽዕኖ ባይኖራቸው ኖሮ ፌዴሬሽኑ ቀድሞውኑ ተመኖችን ይቀንስ ነበር ብለዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
በደሴ ከተማ የስድስት ዓመት ህፃን ላይ የአስገድዶ መድፈር ሙከራ የፈፀመው ግለሠብ በእስራት ተቀጣ

ደምሴ እሸቱ አበበ የተባለው ተከሳሽ በደሴ ከተማ መናፈሻ ክፍለ ከተማ ነብሶ አገር ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ/ም ልዩ ቦታዉ አዉራ ጎዳና በተባለ አካባቢ የ6 ዓመት ህፃን አስገድዶ ለመድፈር ሙከራ ማድረጉ ተገልፆል።

የወንጀል ድርጊቱ መፈፀሙ ከህብረተሰቡ ጥቆማ የደረገሰው ፖሊሰም ግለሰቡን ቁጥጥር ሰር ሊያውል መቻሉ ተገልፆል። የደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ 5ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ክፍል የምርመራ መዝገብ አጣርቶ ለሚመለከተዉ የፍትህ አካል መዝገቡን ይልካል።

የደሴ ከተማ ፍርድ ቤትም መዘገቡን መርምሮ በማየት ተከሳሽ ደምሴ እሸቱ አበበ በተከሰሰበት ወንጀል ዐቃቢ ህግ በህፃናት ላይ የሚፈፀም የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ መስርቶ ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት በ ወንጀል ህግ 149(1) መሰረት ጥፋተኛዉን ያርማል ሌላዉንም ይማርበታል በሚል መሰረት በ18 ዓመት እስራት እዲቀጣ ወስኖበታል።

የደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊሰ መምሪያ የ5ኛ ዋና ፖሊሰ ጣቢያ ህብረተሰቡ ከዚህ ቅጣት እንዲማርና ማንኛዉንም የወንጀል ተሳታፊ ግለሰቦችን በማጋለጥ የህብረተሰቡን ሰላም መጠበቅ እንድችል መልዕክቱን ማስተላለፉ ብስራት ሬድዮ ከ5ኛ ዋና ፖሊሰ ጣቢያ ህዝብ  ግንኙነት ክፍል ያገኘው መረጃ ያሳያል።

በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል
2025/07/05 05:03:28
Back to Top
HTML Embed Code: