እስራኤል በድጋሚ ጥቃት ብትሰነዝር ከባድ ጥፊ ይጠብቃታል ሲሉ የኢራን ከፍተኛ ጄኔራል ተናገሩ
የኢራን ጦር ኃይሎች ዋና አዛዥ እስራኤል በሀገሪቱ ላይ ሌላ የጥቃት እርምጃ ከወሰደች ከባድ ጥፊ እንደሚደርስባት አስጠንቅቀዋል። ሜጀር ጀነራል አብዶልራሂም ሙሳቪ ለሊባኖስ አል-ማያዲን የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገሩት የኢራን ጦር ኃይሎች ባለፈው ወር የእስራኤል እና የአሜሪካ ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ሁሉንም አቅማቸውን እንዳልተጠቀሙ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። "የእስራኤል አገዛዝ በቅርቡ በኢራን ላይ ባደረገው ወረራ ከባድ ሽንፈት ደርሶበታም፣ እናም ይህ የመሰለ ስህተት ከደገመ ከኢራን ህዝብ እና የጦር ኃይሎች የበለጠ ከባድ ጥፊ እንደሚደርስበት እናስጠነቅቃለን" ብለዋል ።
ሙሳቪ እስራኤላውያን እና ደጋፊዎቻቸው በኢራን ሪፐብሊክ ላይ ጉዳት ለማድረስ ኃይላቸውን ለአመታት ሲያሰባስቡ መቆየታቸውንም ጠቁመዋል። ኢራንን ኢላማ ለማድረግ እና ሀገሪቱን ለመከፋፈል እየፈለጉ ነው ለዚህም ደግሞ የኒውክሌርን ጉዳይ እንደ ምክንያት በመጠቀም ላይ ይገኛሉ ሲሉ ተደምጠዋል። እ.ኤ.አ ሰኔ 13፣ እስራኤል በኢራን ላይ ግልፅ እና የማያዳግም ወረራ ስትል በከፈተችው የጦር ዘመቻ በርካታ ከፍተኛ የጦር አዛዦች፣ የኒውክሌር ሳይንቲስቶችን እና ሲቪሎችን ህይወት ቀምቷል።ዩናይትድ ስቴትስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተርን፣ አለም አቀፍ ህግን እና የኑክሌር መከላከል ስምምነትን በመጣስ ሶስት የኢራን ኒውክሌር ጣቢያዎችን በቦምብ በማፈንዳት ወደ ጦርነቱ ገብታለች።
በምላሹም የኢራን ጦር ሃይሎች በኳታር የሚገኘውን
በምዕራብ እስያ ትልቁን የአሜሪካን አል-ኡዴይድ የጦር ሰፈርን ኢላማ አድርጋለች። ሰኔ 24 ቀን ኢራን በእስራኤል ገዥ አካልም ሆነ በዩናይትድ ስቴትስ ላይ ባደረገችው የተሳካ የበቀል እርምጃ ህገወጥ ጥቃቱን ለማስቆም መቻሏን ቴህራን ተናግራለች።የእስራኤል አገዛዝ ለመደራጀት የተኩስ አቁም እንዲደረግ ለመጠየቅ መገደዱን ዋና ጄኔራሉ ተናግረዋል።ሙሳቪ ቴህራን ለፍልስጤም እና ለህዝቦቿ ድጋፍን ጨምሮ በማናቸውም መሰረታዊ መርሆዎቿ ፈጽሞ ተስፋ እንደማይቆርጥ ገልፀዋል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል

በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሱ ሶስት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ
በምዕራብ ሸዋ ዞን ሆለታ ከተማ በጅልዱ እና ቶኬ ኩታዬ ወረዳዎች ውስጥ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሱ ሶስት ግለሰቦች ላይ የእስራት ቅጣት መወሰኑን የምዕራብ ሸዋ ዞን አቃቤህግ ፅህፈት ቤት መግለጫ አመላክቷል።
ብስራት ሬዲዮ ከምዕራብ ሸዋ ዞን አቃቤህግ ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ተከሳሽ ተስፋዬ አበበ የተባለው ግለሰብ በሆለታ ከተማ ቢርቢርሳ ቀበሌ ውስጥ የ15 ዓመቷ ታዳጊ ላይ የመድፈር ጥቃት በመፈፀሙ በእስራት ሊቀጣ መቻሉን ፅህፈት ቤቱ ገልጿል።
ተከሳሹ መስከረም 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዐት ላይ የ15 ዓመቷ ታዳጊ ላይ በተደጋጋሚ የመድፈር ጥቃት ሲፈፅም በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል። ፖሊስም በቁጥጥር ስር ያዋለውን ግለሰብ ላይ ምርመራውን አጠናክሮ ተጎጂዋን በሆስፒታል በማስመርመር የህክምና ማስረጃ ውጤት ያገኘ ሲሆን የምርመራ መዝገቡንም በበቂ ማስረጃ በማጠናከር ለአቃቤ ህግ የላከ ሲሆን አቃቤህግም በወንጀል ህግ ቁጥር 620 ንዑስ አንቀፅ 2 በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ የመሠረተበት ሲሆን ክሱን ሲከታተል የቆየው የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሰኔ 19/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ተስፋዬ አበበ በ15 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።
በተመሣሣይ በምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ ወረዳ ቆርቾ ዴራ የተባለ አካባቢ በ8 ዓመት ህፃን ልጅ ላይ የመድፈር ጥቃት የፈፀመው ግለሰብን በእስራት ተቀቷል። ተከሳሽ ሽብሩ ግርማ የተባለው ግለሰብ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዐት ላይ የ8 ዓመቷ ታዳጊ መፀዳጃ ቤት ውስጥ አፍኖ በመያዝ ተሸክሟት ወስዶ በወላጆቿ ቤት የመድፈር ጥቃት እንደፈፀመባት በማስረጃ መረጋገጡን ፅህፈት ቤቱ ገልጿል።
ተጓጂዋ በደረሰባት የመደፈር ጥቃት ለከፍተኛ ጉዳት የተዳረገች ሲሆን ፖሊስ በክትትል ጉዳት ያደረሰውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር በማዋል የምርመራ መዝገቡን በህክምና እና በሌሎች ማስረጃዎች በማጠናከር ለአቃቤ ህግ የላከ ሲሆን አቃቤ ህግም በወንጀል ህግ ቁጥር 627 ንዑስ አንቀፅ 1 በህፃናት ላይ የሚፈፀም የግብረስጋ ድፍረት እና በደል ክስ መስርቷል። ክሱን ሲከታተል የቆየው የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ሽብሩ ግርማ በ14 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።
በሌላ በኩል በምዕራብ ሸዋ ዞን ቶኬ ኩታዬ ወረዳ ጉደር ከተማ ውስጥ በ12 ዓመቷ ታዳጊ ላይ የመድፈር ጥቃት የፈፀመው ግለሰብ በእስራት ተቀጥቷል። ተከሳሽ ገመቹ ታዬ የተባለው ግለሰብ ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም በጉደር ከተማ ውስጥ የ12 ዓመቷን ታዳጊ አታሎ በመውሰድ የመድፈር ጥቃት እንደፈፀመባት በማስረጃ መረጋገጡን ፅህፈት ቤቱ ገልጿል። የምዕራብ ሸዋ ዞን አቃቤ ህግም የምርመራ መዝገቡን ከፖሊስ ተቀብሎ በተከሳሹ ላይ በወንጀል ህግ ቁጥር 627 ንዑስ አንቀፅ 1 በህፃናት ልጅ ላይ የግብረስጋ ድፍረት እና በደል ክስ የመሠረተ ሲሆን ክሱ የተከታተለው የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤትም ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ገመቹ ታዬ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ13 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲል የምዕራብ ሸዋ ዞን አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት መግለጫ አመላክቷል።

Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
ሊቨርፑል በጆታ እና ወንድሙ አንድሬ ህልፈት ደጋፊዎች የተሰማቸውን ሀዘን ጽፈዉ እንዲገልጹ በክለቡ የሀዘን መግለጫ ደብተር እንዱሁም በዲጂታል ደግሞ በመላዉ አለም የሚገኙ ደጋፊዎቹ ሀዘናቸዉን እንዲገልጹ አመቻችቷል።
በኢትዮጵያ ያላችሁ የሊቨርፑል ደጋፊዎች በዚህ👇🏼 ሊንክ በመግባት ሀዘናችሁን መግለጽ ትችላላችሁ።
https://www.liverpoolfc.com/news/lfc-opens-books-condolence-honour-diogo-jota-and-brother-andre
#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport

አሜሪካ በኢራን ላይ በፈፀመችው ጥቃት የቴህራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር ከአንድ እስከ ሁለት አመት ወደኃላ መልሷታል ተባለ
የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ጥቃት በኢራን ላይ የወሰደው እርምጃ የሀገሪቱን የኒውክሌር መርሃ ግብር ከአንድ እስከ ሁለት አመት ወደ ኋላ እንዲመለስ አድርጎታል ሲል ፔንታጎን አስታውቋል።ይህ ግምገማ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብሩ ተደምስሷል ማለታቸውን ተከትሎ የተሰጠ ነው። የመከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሴን ፓርኔል በዋሽንግተን ኢላማ የተደረጉት ሦስቱ የኢራን የኒውክሌር መስሪያ ቤቶች ወድመዋል ሲሉ የፕሬዚዳንቱን አስተያየት ደግመዋል። ጥቃቶቹንም “ደፋር ኦፕሬሽን” ሲሉ አሞካሽተዋል።
ፓርኔል ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት የኢራን የኒውክሌር መርሃግብር ቢያንስ ከአንድ እስከ ሁለት አመት ወደ ኋላ መልሰነዋል ብለዋል። በሰኔ 21 ቀን ዩናይትድ ስቴትስ የቢ-2 ድብቅ ቦምቦችን በኢራን ላይ ከጣለችበት ጊዜ አንስቶ ፣ ትራምፕ ጥቃቶቹ የሀገሪቱን የኒውክሌር ፋሲሊቲዎች አላበላሹም የሚሉ አስተያየቶችን ያለማቋረጥ ተችተዋል። የኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር “ከዚህ በፊት እንደነበረው አይደለም ተደምስሷል” ሲሉ ተናግረዋል። ባለፈው ወር ለበርካታ ሚዲያዎች ሾልኮ የወጣው የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ጥናት የመጀመሪያ ደረጃ ግምገማ እንደሚያሳየው ጥቃቱ የኢራንን የኒውክሌር ፕሮግራም ዋና ዋና ክፍሎች ማፍረስ ባለመቻሉ ስራው በወራቴች ብቻ እንዳዘገየው አመላክቷል።
ቴህራን በበኩሏ ስለ ኒውክሌር ጣቢያዎቿ ሁኔታ ዝርዝር መረጃ ስትሰጥ ቆይታለች። አንዳንድ የኢራን ባለስልጣናት ተቋማቱ በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። ነገር ግን ጠቅላይ መሪ አሊ ካሜኔይ ባለፈው ሳምንት እንደተናገሩት ትራምፕ የጥቃቱን ተፅእኖ አጋነውታል ብለዋል። በእስራኤል እና በኢራን መካከል ለ12 ቀናት የዘለቀው ጦርነት እና የአሜሪካ ጥቃት ያስከተለው የገለልተኛ አካል ግምገማ የለም። በሣተላይት ምስሎች በኩል የሚታዩ ትንታኔዎች በመሬት ውስጥ ባሉ ቦታዎች በተለይም በሀገሪቱ ትልቁ የማበልጸጊያ ተቋም ፎርዶ የጉዳቱን መጠን ሙሉ በሙሉ ማወቅ አልተቻለም።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በበጀት ዓመቱ ከ9 ሺህ በላይ ህገ-ወጥ የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ዙሪያ ከዘርፉ አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር ገምግሟል፡፡
በበጀት ዓመቱ ህገ-ወጥ ንግድን በመከላከልና በመቆጣጠር ፍትሃዊ የንግድ ስርዓት እንዲሰፍን ሰፊ ስራ መሰራቱን የተገለጸ ሲሆን በ68 ሺ 3 መቶ 33 የንግድ ድርጅቶች ላይ የበር ለበር ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ በዘጠኝ ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና አራት በህገ-ወጥ የንግድ ሥራ ተሰማርተው የተገኙ ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል፡፡
የህብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ተጋላጭነት ለመቀነስ የእሁድ ገበያዎችን ቁጥር ወደ 24 ማሳደግ መቻሉን ተጠቁሟል። በገበያዎቹ ላይ የሚቀርቡ መሰረታዊ የግብርና እና ኢንዱስትሪ በተመጣጣኝ ዋጋና ጥራት እንዲቀርቡ የተሻለ ክትትልና ቁጥጥር መደረጉን ጠቁመዋል፡፡
አክለው በበጀት ዓመቱ የነበረውን ጥንካሬ ይበልጥ በማጠናከር እና እንደ ውስንነት የተነሱ ጉዳዮችን በማረም በቀጣይ በጀት ዓመት የበለጠ ውጤታማ ስራ ለመስራት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
በኤደን ሽመልስ

በጎፋ ዞን በ2017 በጀት ዓመት 3 ሺህ 596 የወንጀልና የፍትሃ ብሔር ክስ መዝገቦች ውሳኔ ማግኘታቸውን ተገለጸ
በተያዘው በጀት ዓመት ከቀረቡ 3 ሺህ 767 የወንጀልና የፍትሐብሔር ክስ መዝገቦች ውስጥ 3 ሺህ 596 መዝገቦች ውሳኔ ማግኘታቸውን የጎፋ ዞን ፍትህ መምሪያ አስታውቋል።
የጎፋ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ብላቴ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት በቅንጅታዊ አሠራር የሶስትዮሽና ሁለትዮሽ እንዲሁም የትራንስፎርሜሽን መድረኮች ግንኙነትና ውጤታማነት ዙሪያ ከዚህ በፊት ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር መደረጉ ለአፈጻጸሙ ትልቁን ሚና መጫወቱን ገልጸዋል።
የምክክር መድረኩ በዋናነት የሕግ የበላይነትን ማስከበር፣ የመልካም አስተዳደር፣ የሰብዓዊ መብት አያያዝና በሌሎች በጥንካሬና በቀጣይ በጀት ዓመት መስተካከል በሚገቡ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ እና የዘርፉን ትራንፎርሜሽን አጀንዳ እንዲሁም ለ90 ቀናት በሴክተሩ በተለዩ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑንም አብራርተዋል። ባለፉት በጀት ዓመት ከቀረቡ 3 ሺህ 767 የወንጀልና የፍትሐብሔር ክስ መዝገቦች 3 ሺህ 596 ውሳኔ ማግኘታቸውንና አፈፃፀሙም 95 በመቶ መሆኑን ኃላፊው በሪፖርታቸው ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ 33 የሙስና ክስ ወንጀል መዝገቦች ቀርበው በ29 መዝገቦች ላይ ክስ የተመሠረተና በድርድር ያለቀ 4 መዝገብ ሲሆን፣ የዘርፉ የማጥራት ምጣኔ 98 በመቶ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።በተጨማሪም የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት ለማስመለስ ከቀረበው 15 ሚሊዮን 211 ሺህ 664 ብር በዐቃቤ ሕግ ክስ በመመሰረትና ክስ ሳይመሰረት በድርድር የተመለሰ 11 ሚሊዮን 229 ሺህ 591 ብር ወደ መንግሥት ካዝና እንዲመለስ መደረጉን በሪፖርታቸው አመላክተዋል።
የሴቶችና ሕፃናት ደህንነት ከማስከበር አንጻር በበጀት ዓመቱ ከቀረቡ 623 መዝገብ ላይ ክስ ቀርቦ በሁሉም ላይ የዐቃቤ ሕግ የተለያየ ውሳኔ የተሰጠ ሲሆን የማጥራት ምጣኔ 98 በመቶ መመዝገቡ ተገልጿል።
በሰብል አበበ

ሩሲያ የዩክሬን ግዛት የሆነችውን ሉሃንስክ መቆጣጠሯን ገለፀች
የዩክሬን ምስራቃዊ ሉሃንስክ ክልል የሩሲያ ኃይል ማክሰኞ እለት ሙሉ በሙሉ እንደተቆጣጠረ አስታውቋል ፣ ይህም ሩሲያ ሙሉ በሙሉ ከያዘቻቸው አራት የምስራቅ ዩክሬን ክልሎች የመጀመሪያ ያደርገዋል ። "ከሁለት ቀናት በፊት የሉሃንስክ ህዝቦች ሪፐብሊክ ግዛት 100 በመቶ ነፃ መውጣቱን የሚገልጽ ዘገባ ደርሶኛል" ሲል ሊዮኒድ ፓሴችኒክ የሩሲያ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።
የሩሲያ ወታደራዊ ዘጋቢዎች ሁለት መንደሮች ከዩክሬ. ነፃ ሆነው መቆየታቸውን ጠቁመው ሉሃንስክ በ2022 አንድ ጊዜ በዩክሬን በመልሶ ማጥቃት ተይዛ ነበር። የሩሲያ ኃይሎች በ 33 ወራት ውስጥ መላውን ግዛት እንደገና ለመቆጣጠር ዘምተዋል ፣ የሩሲያ ጦር ሙሉ በሙሉ ወረራ ከጀመረ ከሶስት ዓመታት በላይ በሆነ ጊዜ ውስጥ በዩክሬን ላይ ሌላ ጉዳት አስከትሏል።
ዩናይትድ ስቴትስ የወቅቱ አስተዳደር በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ቃል የተገባላቸውን አንዳንድ የጦር መሣሪያዎችን ወደ ኪየቭ እንደማይልክ አስታውቋክ። "ይህ ውሳኔ የአሜሪካንን ጥቅም ለማስቀደም የተደረገው ሀገራችን በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ሌሎች ሀገራት ወታደራዊ ድጋፍ መገምገሙን ተከትሎ ነው ሲል ዋይት ሀውስ ማስታወቁ ይታወሳል።

እስራኤል በተኩስ አቁም ስምምነት ወቅት በኢራን እና ሶሪያ ጉዳይ ከሩሲያ ጋር በሚስጥር ውይይት አድርጋለች ተባለ
እስራኤል ከቴህራን ጋር ባደረገችው የተኩስ አቁም ስምምነት ከሩሲያ ጋር በኢራን እና በሶሪያ ጉዳይ ዙሪያ ሚስጥራዊ ድርድር አድርጋለች ሲል አንድ ዘገባ ይፋ አድርጓል። የእስራኤል መንግሥት ብሮድካስቲንግ ካን እንዳስታወቀው ቴል አቪቭ ከሞስኮ ጋር ኢራንን እና ሶሪያን በሚመለከት ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ለመፈለግ በከፍተኛ ደረጃ ግንኙነት ስታደርግ ቆይታለች።
ሩሲያ በእስራኤል እና በኢራን መካከል ለመደራደር ያቀረበችውን ጥያቄ ተከትሎ የእስራኤል ባለስልጣናት የተኩስ አቁም ከታወጀ ከአንድ ሳምንት በኋላ ከሞስኮ ጋር መነጋገር እንደጀመሩ ተሰምቷል። በሪፖርቱ ውስጥ ስለ ንግግሮቹ ይዘት የተለየ ዝርዝር ነገር አልቀረበም። ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል በኢራን ጉዳይ ላይ ከአሜሪካ ጋር ሰፊ ስምምነት ለማድረግ እንደምትፈልግም ተነግሯል።
እንደ ዘገባው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጉዳዩን በሚቀጥለው ሳምንት ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በዋሽንግተን ሊያደርጉት ባቀዱበት ወቅት ያነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። እስራኤል በኢራን ላይ ከዚህ ቀደም ከሊባኖስ ጋር ከተደረሰው ስምምነት ጋር ተመሳሳይ የሆነ ማዕቀፍ ለመድረስ እንደታሰበ ተዘግቧል። ከኢራን ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ መሆን ከጀመረ በኋላ፣ የእስራኤል ባለስልጣናት የአብርሃም ስምምነት ተብሎ የሚጠራውን ስምምነቶችን ለማስፋት ሲወያዩ የቆዩ ሲሆን የዚሁ ጥረት አካል የሆነው ከሶሪያ ጋርም ድርድር እየተደረገ ይገኛል ተብሏል።