Telegram Web Link
የቅርፅ ውድድር እና ሰሞነኛው ውዝግብ

የቅዳሜን ከእኛ ጋር እንግዳ አማድ ጋር ቆይታ ይኖረናል

#ዳጉ_ጆርናል
73🤣14👍5🤷‍♂4🔥2
#Breaking
ለአንዱአለም ጎሳ የተሰጠው ሽልማት ተነጥቋል።


የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ለአርቲስት አንዷለም ጎሳ የሰጠውን ሽልማት መንጠንቁ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂው እያስፔድ ተስፋዬ አስታውቋል።

ዳጉ ጆርናልም የሽልማት ኮሚቴው በኦሮምኛ ቋንቋን ያወጣውን መግለጫ ተመልክቷል።

በዘንድሮው የሀጫሉ ሁንዴ ሽልማት መድረክ አንዷለም ጎሳ ተሸላሚ መሆኑ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያስነሳ እንደነበር አይዘነጋም።

#ዳጉ_ጆርናል
73👏48👍1
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
የዲዬጎ ጆታ እና የአንድሬ ሲልቫ የቀብር ስነስርዓት ተፈጽሟል።

ጆታ እና ወንድሙ በተወለዱበት ጎንዶማር ነዉ ቀብራቸዉ የተፈጸመዉ።

በቀብር ስነስርዓቱ ላይ ምሽት ለአልሂላል ጨዋታ ያደረገዉ እና የጆታ የቅርብ ጓደኛ ሩበን ኔቬስ ተገኝቷል።

የሊቨርፑል አሰልጣኝ አርሰ ስሎት እና አምበሉ ቫን ዳይክ እንዲሁም ሌሎች ተጨዋቾች ፤ የማንችስተር ዩናይትዱ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ፣ የማን ሲቲዎቹ ሩበን ዲያዝ እና በርናንዶ ሲልቫ የፖርቱጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ እና ተጨዋቾች በቀብሩ ላይ ተገኝተዋል።

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
💔4224😢9
የ"ሁሉ ስፖርት" የመኪና (የቢዋይዲ ሲጉል ) ሽልማት አስረከበ

የሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል ወጣቶች በተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተሳታፊ በመሆን በአዕምሮ እና በአካል ብቁ እና ንቁ እንዲሆኑ ለማገዝ በማሰብ በአሁነ ጊዜ ለዳርት ፣ለብስክሌት ፌዴሬሽን ፣ ለኢትየጵያ ፕሪሞየር ሊግ እና መሰል ስፖርታዊ ተቋማት የስፖርት ትጥቆችን በማቅረብ ስፖርቱ እንዲያድግ አስተዋፅኦ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን አሁን ደግሞ በጀት በመመደብ ዘርፉን ለማሳደግ እንቀስቃሴ ላይ መሆኑ ተነግሯል ።

ማህበራዊ ሃላፊነታችንን ለመወጣት በበርካታ በጎ ስራዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ ነን ያሉት የድርጅቱ ሽያጭ ክፍል ሀላፊ አቶ ፍፁም ተሾመ በየአመቱ 5 በመቶ የተጣራ የድርጀቱን ትርፍ ትርጉም ላለው የማህበረሰብ ተነሳሽነት እንሰጣለን ማለታቸዉን ብስራት ሰምቷል ።

ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እና ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመስራት ላይ ሲሆን በተመሠረተ በስምንት አመት ውስጥ ከ100 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልል ከተሞች የስራ ዕድል መፍጠሩም
ተገልጿል ። የዘንድሮውን ክረምት ምክንያት በማድረግ ለስፖርቱ መነቃቃት የሚያግዘዉን የሁሉ ስፖርት ፌስቲቫልን አንዲሁም የተለያዩ የስፖርት ሁነቶችን ለማከናወን ከፍተኛ በጀት መመደቡ ተነግሯል ።

ይህ የክረሞት የስፖርት ፕሮጀክት በተለያዩ ክልል ከተሞች በተለየዩ የስፖርት አይነቶች የሚከናወን ስለመሆኑም አቶ ክብሮሞ ገብረመስቀል አክለዋል ፡፡ ድርጅቱ አገልግሎቱን በሌሎች የአፍሪካ ሃገራት የማስፋፋት ዕቅድ መያዙ የተገለፀ ሲሆን በዛሬዉ ዕለት ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ለተወጣጡ አሸናፊዎች የቢዋይዲ ሲጉል ፣የኤሌክትሪክ ሳይክል ፣ስማርት ስልክ ፣ፕሌይ ስቴሽን እና ስማርት ቴሌቪዥን ሽልማት አበርክቷል ።

የዘንድሮው የ"ሁሉ ስፖርት ፌስቲቫል በዛሬው ዕለት ሲካሄድ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎችን ጨምሮ ሌሎችም አጋር አካላት የተገኙ ሲሆን ለደንበኞች ይበልጥ ምቹ ፣ቀላልና ቀልጣፋ የሆነዉ አዲስ ዌብሳይት ይፋ ተደርጓል ።

በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
20👎10
በብሩህ ማይንድስ ኮንሰልት የተዘጋጀውና ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው ልዩ ምልከታ የኢንተርፕርነርሺፕ መርሃ ግብር ተጠናቀቀ

ከ4000 ሰው በላይ ጎብኚዎችና 40 ተሳታፊዎች የታደሙበት ልዩ ምልከታ የኢንተርፕርነርሺፕ ውይይት መርሀግብርና የገንዘብ አቅርቦት ለሥራ ፈጣሪ ኢንተርፕራይዞች የተሰኘው አውደ ርዕይ በኢትዮጵያ የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ የሚታየውን ችግር ለመፍታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በ5ኛው ዓመታዊ የልዩ ምልከታ የኢንተርፕርነርሺፕ አውደርዕይ እና የፓናል ውይይት ላይ ለጀማሪ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶች እና ለአነሥተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች መሠረታዊ ማነቆዎች በሆኑ የብድር አቅርቦት ፈተናዎች ዙሪያ መፍትሄ አመላካች የሆኑ የፖሊሲ ግብዓት ምክረ-ሀሳቦች ቀርበዋል፡፡

ከዚህ ጎንለጎን በሰሞንኛው አውደ-ርዕይ እና መድረክ ላይ ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች በቀላሉ ገንዘብ የሚያገኙበትን አማራጮች ለመፍጠር ከአበዳሪ ድርጅቶች የማገናኘት ስራ መከናወኑን የሁነቱ አዘጋጅ የሆነው የብሩህ ማይንድስ ኮንስልት መስራች አቶ ሰለሞን ደሳለኝ ተናግረዋል።

ብሩህ ማይንድስ ኮንሰልት የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ላይ ጥናትና ምርምር፣ ሥልጠናዎችንና የንግድ ልማት አገልግሎት የሚያከናውን አማካሪ ተቋም ነው።

ተቋሙ የሥራ ፈጠራና ወጣቶች ልማት ለማሻሻል በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ የበኩሉን አዎንታዊ ሚና ለመጫወት ብዙ ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከነዚህ ጥረቶች ውስጥ አንዱ የሥራ ዕድልና የሥራ ፈጠራን ለማበረታታት ባለ ድርሻ አካላት በቅርበት በመወያየት የተሻለ ከባቢ እንዲፈጠር “ልዩ ምልከታ” የተባለ መድረክ አዘጋጅቶ ላለፉት አምስት ዓመታት ሲያከናውን መቆየቱን ጠቅሷል።

#ዳጉ_ጆርናል
14👍6
2025/07/12 17:56:11
Back to Top
HTML Embed Code: