Telegram Web Link
ስንቄ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ጠቅላላ ገቢው 15.4 ቢሊዮን ብር  መሆኑን አስታወቀ

በዚህም ባንኩ ገቢው የ173 በመቶኛ እድገት ማሳየቱ የተነገረ ሲሆን ያልተጣራ ትርፌ ደግሞ 3.5 ቢሊየን ብር ነው ብሏል።

ስንቄ ባንኩ ለኢኮኖሚ ዘርፎች ማለትም ለግብርና፣ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ ለስራ ፈጣሪ ወጣቶች እንዲሁም ለሴቶች የሰጠሁት ጠቅላላ ብድር መጠን የባንክ ለባንክ ብድርን ሳይጨምር 56.7 ቢሊየን ብር ደርሷል ብሏል።

ይህም ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ102 በመቶ ጭማሬ ማሳየቱን የተናገረው ስንቄ ባንክ ይህ የብድር መጠን ባንኩ ስራ ከጀመረበት የመጀመሪያው አመት ጋር ሲነፃፀር የ218 በመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል።

በመደበኛ የባንክና ማይክሮፋይናንስ አገልግሎት ከሚሰጠው ብድር በተጨማሪ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ተግባራዊ አደረሉት ባለው ወቢ የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎት በኩል ያለ ምንም ማስያዣ ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ከ240 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች 1.2 ቢሊዮን ብር ብድር አቅርቤያለሁ ብሏል።

የባንኩ ጠቅላላ ካፒታል መጠን ባሳለፍነው በጀት አመት ከነበረበት 9.7 ቢሊዮን ብር የ2.7 ቢሊዮን ብር ወይም የ28 በመቶ እድገት ማስመዝገቡ የተነገረ ሲሆን ጠቅላላ ተቀማጩ ደግሞ 102.5 ብር ደርሷል መባሉን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

590 ቅርንጫፎች እንዳሉት የተናገረው ባንኩ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ 17 ቅርንጫፎች አሉኝ ብሏል።81 በመቶ የሚሆነው የባንኩ ቅርንጫፎች የሚገኙት በገጠሪቱ የሀገሪቱ አካባቢ መሆኑም ተነግሯል።

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
👎4010🤔4
በህገወጥ የማዕድን ዝውውር ላይ በተደረገ ቁጥጥር  ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ መደረጉን ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የማዕድን ልማት ፅ/ቤት የሚሰራውን ህገወጥ አሰራር ለመቆጣጠር አዲስ የማዕድን  ልማት ሪፎርም ስራ ላይ በማዋል ህገወጥ የማዕድን እንቅስቃሴ ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የዞኑ ማዕድን ልማት ፅ/ቤት ገልጿል ።

የሰሜን ሸዋ ዞን ማዕድን ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቂናጤ ጫላ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ህገወጥ የማዕድናት  ዝውውርን ለመግታት በመንገድ  እና  በማዕድን ልማት ኢድስትሪዎች  ላይ በተደረገ ቁጥጥር እና እርምጃ ሶስት ሚሊየን ብር  ለመንግስት ገቢ መደረጉ ገልፀዋል።

በመንገድ ላይ በተደረገ ቁጥጥር በአስራ አንድ ተሽከርካሪዎች በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዙ የነበሩ ጥቁር ድጋይዎች፣  አሸዋ እና የተፈጨ ድንጋይ በቁጥጥር ስር የዋለ መሆኑን ገልፀዋል።

ከማዕድን ልማት ደንብ እና መመሪያ ውጭ ሰላሳ ሰባት የማዕድን ልማት ስራ ላይ የተሰማሩ ኢንድስትሪዎች ላይ  እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል። በአጠቃላይ ከህገወጥ የማዕድን ዝውውር ቁጥጥር በተሰራ ስራ ከታቀደው እቅድ በላይ በመሰራቱ ሶስት መቶ ሚሊዮን ብር ለመንግስት ገቢ ሊሆን ችሏል ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓት የግንባታ ማዕድኖች በተተመነላቸው ዋጋ መሰረት የሚተላለፉ ሲሆን ማንኛውም በማዕድን ውጤቶች ላይ የሚሰራ ሕገወጥ ስራን ህብረተሰቡ ተከታትሎ ለፍትህ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥም አቶ ቂናጤ ጫላ ጨምረው ገልፀዋል።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
14👎6😁2
በደብረ ማርቆስ ከተማ የፍቅር ጓደኛ ሆኖ በመቅረብ የግድያ ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በአብማ   ክፍለከተማ ቀበሌ 01 ልዩ ቦታው ዩንቨርሲቲ እንግዳ መቀበያ ህንፃ ግንባታ ፊትለፊት ከሚገኘው  አካባቢ የወንጀል ድርጊቱ  ተፈፅሟል።

በአካባቢው የሻይ ቤት ባለቤት የሆነችውን ሸዋዬ አለኸኝ የተባለችውን ግለሰብ  የፍቅር ጓደኝነት  በማቅረብ አብረን እንኑር በማለት ጥያቄ ያቀርብላታል።

በነጋታው ተከሳሹ ባልታወቀ ምክንያት   አንገቷን ጠምዝዞ በማነቅ በመግደሉ  የአካባቢው ማህበረሰብ ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠቱ ፖሊስ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል አስፈላጊው የምርመራ ስራ በማጣራት መዝገቡን ለሚመለከተው የፍትህ አካል መላኩን የ1ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የታክቲክ ወንጀል መርማሪ ሳጅን አበበ ገልጸዋል ።

የምስራቅ ጎጃም ዞን አቃቢ ህግ ከፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ በማደራጀት እና በማስረጃ በማጠናከር ክስ መስረቶ መዝገቡን ለምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማስተላለፍ መቻሉን መርማሪው መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል ።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት ተከሳሽ ቢንያም ፈንታ ትዕዛዙ ጥፋተኛ መሆኑ በሰው እና በህክምና ማስረጃ በመረጋገጡ በ8 አመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን ተገልጿል ።ከተፈጸመው የወንጀል ድርጊት አኳያ አቃቢ ህግ የቅጣት ይግባኝ መጠየቁን እና ተከሳሹ ከዚህ በፊት በ2012 ዓ.ም በማታለል እና በማጭበርበር ወንጀል ተከሶ በሌለበት 1አመት ከ5 ወር ተቀጦ ፖሊስ ሲያፈላልገው እንደነበረ ብስራት ሬዲዮ ከደብረ ማርቆስ ከተማ ፖሊስ  ያገኘው  መረጃ ያመላክታል።

#ዳጉ_ጆርናል
👎449💔7😁3🤣2👍1
ኢትዮጵያ ባለፋት አሥራ አንድ ወራት ከቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ሽያጭ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ የአሜሪካን ደላር ገቢ አገኘች

ኢትዮጵያ ባለፋት አስራ አንድ ወራት  294ሺህ 222 ቶን የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ምርትን ለውጪ ገበያ ማቅረቧን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል።

በባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና የኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳህለ ማርያም ገብረ መድህን ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት
ለውጪ ገበያ እንዲቀርቡ ከተደረጉት ምርቶች 1.557 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ነበር።

በአስራ አንድ ወሩ 425 ሺህ 385 ቶን ቡና ሻይና ቅመማ ቅመምን ለአለም ገበያ መላክ እንደተቻለ ገልፀው 2.259 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል ብለዋል፡፡

በዚህም ከእቅድ በላይ ገቢ ተገኝቷል የተባለ ሲሆን አፈጻጸሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተላከው ጋር ሲነጻጸር  በገቢ 1.041.65 ቢሊዬን ዶላር ጭማሪ ተመዝግቧል፡፡

ቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
😁157👍2👎1🤔1🤣1
ከ25 ሺህ በላይ ከባድና ቀላል የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ መንስኤ መለየታቸው ተነገረ

በሀገር አቀፍ ደረጃ የኃይል መቆራረጡንበክረምቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር 100 ሺህ ችግኞችን ለመትከል ቅድመ ለዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ አንዋር አብራር ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናገሩ፡፡

ተቋሙ ለኃይል መቆራረጥ መንስኤ የሆኑ ዛፎችን መቁረጥ ብቻ ሳይሆን ለሀገራዊ አረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበረከት ማቀዱን የገለፁት ሥራ አስፈፃሚው፤ ለዚህም ንቅናቄ 20 ሚሊዮን ብር ወጪ ይደርጋል ብለዋል፡፡

የችግኝ ተከላ ንቅናቄው በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም የተቋሙ ሪጅኖች እና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት የሚከናወን መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡  በዘላቂነት ለመቀነስ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኔትዎርክ ኢንፍራስትራከቸር እና ኦፕሬሽን ኤክሰለንስ ዳይሬክተር  አቶ ፈሪድ አብዱሰላም ለመገናኛ ብዙሃኑ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የሃይል መቆራረጡን ወደ ዜሮ ለማምጣት የ100 ቀን ዕቅድ ተለይቶ ሲሰራ መቆየቱን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ፤ በጂፒኤስ ቴክኖሎጂ በመታገዝ በአዲስ አበባ ያሉ 152 የመካከለኛ መስመሮች እና እነዚህን መስመሮች የሚሸከሙ 59 ሺህ 48 ምሰሶዎች ላይ በተደረገ ጥልቅ ፍተሻ ከ25 ሺህ 973 ከባድና ቀላል የኃይል መቋረጥ መንስኤ የሆኑ የግኝት ነጥቦች ተለይተዋል ብለዋል፡፡ 

የኃይል መቋረጥ ችግሩን ለመቅረፍ ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ 28 ሪጅኖች ላይ ከ250 ሺህ በላይ የግኝት ነጥቦች መገኘታቸውንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ለኃይል መቋረጥ መንስዔ የሆኑት ግኝቶችም ከመስመሮች ጋር የዛፎች ንክኪ ያለባቸው፣ መቀየር የሚያስፈልጋቸው ምሰሶዎች፣ ከግንባታዎችና እርስ በእርሳቸው የተቀራረቡ መሥመሮች፣  የረገቡ እና የተለያዩ የመስመር ችግር ያለባቸው ናቸው ተብሏል፡፡

ይህን ተከትሎ አዲስ አበባ ላይ ከተገኙ ግኝቶች መካከል እስካሁን 56 በመቶ ወይም ለ14 ሺህ 649 ያህሉ አስፈላጊው ማስተካከያ ተደርጓል፡፡

በክረምቱ ወቅት የኤሌክትሪክ አደጋ ተጋላጭነት የሚጨምር በመሆኑ ህብረተሰቡ በዝናብ አልያም በነፋስ ተበጥሶ የወደቀና የተንጠለጠለ የኤሌክትሪክ ገመድ ከመንካት እንዲቆጠብ፤ አልያም መሰል ችግሮችን ሲመለከቱ ደግሞ በ905 ነጻ የስልክ መስመር በመደወል እንዲይሳውቅ ጥሪ ቀርቧል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል
19😁6🔥4
በዲዬጎ ጆታ ህልፈት የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት ላይ የቀድሞ የቡድን አጋሮቹ እንዲሁም የልብ ጓደኞቹ ሩበን ኔቬስ እና ካንሴሎ በእንባ ሲታጠቡ

#ዳጉ_ጆርናል
😢68💔383
ሀሽሽ በምሳ ዕቃ ቀላቅሎ ዝዋይ ማረሚያ ቤት ሊያስገባ የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

ሰኔ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ዝዋይ ማረሚያ ማዕከል የታሰረበትን የህግ ታራሚ ቤተሰብ ለመጠየቅ በጎርጓዳ ሳህን ምግብ ይዞ ያመራው ግለሰብ በምሳ ዕቃው ውስጥ በሺሽ ደብቆ ሊያስገባ በመሞከሩ በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል።

የማዕከሉ የማረሚያ ፖሊስ አባላትም የተለመደውን የዕለት ከእለት ተግባራቸውን በማከናወን ላይ በነበሩበት አጋጣሚ ጠያቂው ግለሰብም ለታራሚ ቤተሰቡ ይዞት የመጣውን የምግብ ሳህን ማስፈተሽ እንደጀመረ ፖሊስ አስታውቋል።

የማረሚያ ፖሊስ አባላቱ በፍተሻ ወቅት ጠያቂ ግለሰቡ ላይ የተለየ መረበሽና መጨናነቅ ማስተዋላቸውን ተከትሎ ጥርጣሬ ውስጥ እንዳስገባቸው የተገለፀ ሲሆን ቀጥሎም ከምግቡ በታች ዘልቀው ጎድጓዳ ሳህኑን ይፈትሻሉ።

በእዚህን ወቅት ላይ ፖሊሶች ሳህኑ ተከፍቶ መልሶ እንደተበየደ ያስተውላሉ። ምክንያቱም ጎድጓዳ ሳህኑ ውስጥ ምግብ ብቻ ሳይሆን ወደ ማረሚያ ቤት እንዳይገቡ ከተከለከሉ ባዕድ ነገሮች መካከል የሆነውን ሀሺሽ ከምግቡ በታች በሳህኑ ላይ ሌላ ሳህን ተደርቦ ተበይዶ ሊገኝ ችሏል።

ቀጥሎም የማረሚያ ፖሊስ አባሎች ባደረጉት ብርቱ የፍተሻ ጥበብ በመጠቀም ግለሰቡ በቁጥጥር ውሎ በኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለባቱ ፖሊስ ጣቢያ ተላልፎ በመሰጠት የምርመራ ሂደቱ በመጣራት ላይ ይገኛል ተብሏል።

ማንም ሰው በማረሚያ ቤት ለሚከናወነው የማረም ማነፅ ተግባራት እንቅፋት የሚሆን ወንጀል ፈፅሞ ሲገኝ በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን የዝዋይ ማረሚያ ማዕከል መልዕክቱን አስተላልፏል።

ምንጭ:- የዝዋይ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን

#ዳጉ_ጆርናል
😁33🤣1310👏2🤔2👎1
ቅዳሜን ከእኛ ጋር" ፕሮግራም በተወዳጁ ብስራት ኤፍ.ኤም 101.1 ዛሬ ይመለሳል፤ ስንመለስ...

[ ] በልዩ ፕሮግራም ቅዳሜን ከእኛ ጋር ዛሬ የሬዲዮ ሞገዳችሁን 101.1 ላይ ካደረጋችሁ አብረን እንቆያለን።

[ ] ከቀናት በፊት ሰርግ አሁን ደግሞ ሞት አሳዛኙ የዲያጎ ጆታ ፍፃሜን እናነሳለን 💔

[ ] ባለፈው ሳምንት ስለ ቤንያሚን ኔታንያሁ ሰፋ ያለ ዘገባን አስደምጠናችኋል ዛሬ ደግሞ ስለ ቅዱሱ ስፍራ አል አቅሷ እናወራለን።

[ ] የቅዳሜ ወሬዎችን እያነሳሳን እንቆያለን ምርጥ ምርጥ ሙዚቃ ትጋበዛላችሁ፤ ተረክም አለ ፣ ስፖርታዊ ጥንቅር ከወቅታዊ መረጃዎች ጋር ተዘጋጅቷል።

ስፖንሰሮቻችን ፦
👉 ዘመን ባንክ
👉 ቨርጂኒያ ፋርማሲውቲካልስ
👉 ጣዕም ዳቦና ኬክ ቤት-ሻወርማን ይቅመሱ
👉 ጃፋር የመፅሃፍት መደብር
👉 አውት ዲተርጀንት -የፅዳት መላ

ሁሌም ቅዳሜያችሁን ከ 5 እስከ 7 በተወዳጁ ጣቢያ ብስራት ኤፍ.ኤም 101.1 ላይ እንጠብቃችኃለን።

#ቅዳሜን ከእኛ ጋር
ለአዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎች ቴሌግራም ቻናላችንን #ዳጉ_ጆርናል ይቀላቀሉ
ሊንክ :- @zena24now
24👎3
2025/07/13 20:46:45
Back to Top
HTML Embed Code: