Telegram Web Link
በሰሜን ምስራቃዊ ናይጄሪያ ቦኮ ሃራም በፈጸመው ጥቃት 9 ሰዎች ተገደሉ

በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ቦርኖ ግዛት ውስጥ በሚገኘው በማላም ፋቶሪ ማህበረሰብ ላይ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት ቢያንስ 9 ሰዎች ሲገደሉ አራት ቆስለዋል። የአካባቢ መስተዳድር ኮሚሽነር ሱጉን ማይ ሜሌ ድርጊቱ የተፈፀመው ከግዛቱ ዋና ከተማ ማይዱጉሪ በ270 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው ብለዋል። በተጨማሪም በአሁኑ ጊዜ በውጭ አገር ይፋዊ ጉዞ ላይ የሚገኙት የግዛቱ ገዥ ባባጋና ኡማራ ዙሉምን በመወከል የተጎጂዎችን ቤተሰቦች ለማጽናናት የልዑካን ቡድን መርተወ ወደ ስፍራው አምርተዋል።

የቦርኖ ግዛት መንግስት እና ወታደሩ የህብረተሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ የተቻለውን ሁሉ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። ማላም ፋቶሪ ከስትራቴጂካዊ ጠቀሜታው የተነሳ ሰላም እና መረጋጋትን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ ነን ለዚህም የአካባቢው አስተዳደር እና ህዝቡ ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ለማስወገድ የበለጠ እንዲሰሩ እና በጸሎት እንዲተጉ አሳስበዋል። ኮሚሽነሩ አክለውም ወደፊት በቦኮ ሃራም ታጣቂዎች የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል በአካባቢው የመንግስት መስሪያ ቤት ዙሪያ ጠንካራ የፀጥታ ኃይል እንደሚሰማራ ተናግረዋል።

ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ማንኛውም ሰው መዘዝ እንደሚጠብቀው በመግለጽ ነዋሪዎች በማንኛውም መንገድ ከቦኮ ሀራም አማፅያን ጋር እንዳይተባበሩ አስጠንቅቀዋል። ለተጎጂ ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው 500 ሺ ናያራ ወይን 326 ዶላር የተበረከተ ሲሆን፥ ለአራቱ ተጎጂዎች ደግሞ ለእያንዳንዳቸው 250 ሺ ናያራ (163 ዶላር) አግኝተዋል። የኢንፎርሜሽንና የውስጥ ደኅንነት ኮሚሽነር ኡስማን ታርም በማላም ፋቶሪ 3,000 የተፈናቀሉ ቤተሰቦችን ለማቋቋም መታቀዱን አስታውቀዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
16💔6😢4😁1
በክረምት ወራት ቁጥሩ የሚጨምረውን የልጆች ስርቆት ወንጀል ለመከላከል አስፈላጊ ጥንቃቄ እንዲደረግ የፌደራል ፖሊስ አሳሰበ

ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ተከትሎ በመዘናጋት ምክንያት የሚፈፀም የልጆች ስርቆትን እና ሌሎችንም መሠል አደጋዎች ለመከላከል ከወዲሁ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አሳሰበ ።የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሳዲያ አብድሮ የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ፀጥታና ደህንነት በመጠበቅ ረገድ ፖሊስ የማይተካ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል ።

በህፃናት ልጆች ላይ የሚፈፀሙ የስርቆት ወንጀሎችን ለመከላከል ከማህበረሰቡ ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተነግሯል ። ልጆች ለጨዋታ በሰፈር እና በመዝናኛ ስፍራዎች በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የወላጆች ጥብቅ ክትትል ሊለያቸዉ አይገባም ተብሏል ።በልጆች ላይ የሚፈፀሙ የእገታ እና የስርቆት ወንጀሎች አላማቸው ገንዘብ መሰብሰብ መሆኑን የተናገሩት ረዳት ኮሚሽነሯ ይህን ለመከላከል ህብረተሰቡ ቤት በሚያከራይበት ወቅት የተከራዮችን ማንነት ማረጋገጥ ፣ፀጉረ ለዉጦች ባሉበት ልጆችን ያለጠባቂ ባለመተዉ ፣ራቅ ወዳለ አከባቢ ብቻቸዉን እንዲሄዱ  ባለመፍቀድ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች የልጆች ማዘውተሪያ ስፍራዎች እጥረት ባለመኖሩ እንዲሁም በየአካባቢው ባማረ ሁኔታ ተገንብተዉ ለማህበረሰቡ ክፍት የሆኑ የመዝናኛ ስፍራዎችን መጠቀም እንደሚገባ አሳስበዋል ። በቅርቡ ከጅግጅጋ ሁለት ልጆች ተሰርቀዉ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ላይ ሳሉ ኬላ ላይ በተደረገ ፍተሻ ወንጀለኞቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ልጆቹን ከአደጋ መታደግ መቻሉን ረዳት ኮሚሽነሯ ተናግረዋል ።

ወንጀል በሚፈፀምበት ወቅት ወላጆች በ911 ነፃ የመስመር ስልክ በመጠቀም  ለፌዴራል ፖሊስ ጥቆማ መስጠት ይችላሉ ተብሏል ። በተጨማሪም የፌዴራል ፖሊስ EFPA መተግበሪያን በመጠቀም የወንጀል ድርጊቶችን በድምፅ እና በምስል በማጋራት የተለመደዉ ትብብር እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል ።

በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
21🙏2👌2👏1
1🤔1
በፓኪስታን ከቤት ያመለጠው አንበሳ በሶስት ሰዎች ላይ ጥቃት ካደረሰ በኋላ የአንበሳው ባለቤት በቁጥጥር ስር ዋለ

በፓኪስታን ከቤት ያመለጠው አንበሳ በአንዲት ሴት እና በትንንሽ ልጆቿ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ የአንበሳውን ባለቤቶች ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏል። ከምስራቃዊቷ የላሆር ከተማ የተገኘው ድራማዊ የሚመስለው የድብቅ ካሜራ ምስል እንዳመላከተው የሲሚንቶ ግንቡ የዘለለው አንበሳ ሴቲቱን ሲያባርራት እና በፍርሃት ሁኔታውን ሲከታተሉ የነበሩ ሰዎች ለደህንነታቸው ሲሮጡ ይታያልል። ሴትየዋ ጨምሬ የአምስት እና የሰባት አመት እድሜ ያላቸው ልጆቿ በእጃቸው እና በፊታቸው ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ነገርግን አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ፖሊስ የአንበሳውን ባለቤቶች ያለፍቃድ ያቆዩት የዱር እንስሳ እና በቸልተኝነታቸው በማምለጡ ምክንያት ክስ መስርቷል። አንበሳው ተይዞ ወደ ዱር እንስሳት ፓርክ እንዲዘዋወር ተደርጓል።ትልልቅ እንስሳዎችን እንደ የቤት እንስሳ በፓኪስታን የመያዝ ልማድ አለ። አናብስት፣ አቦሸማኔዎች፣ ነብር፣ ፑማዎችን እና ጃጓሮችን ነዋሪዎች ካስመዘገቡ በኋላ ለአንድ እንስሳ የአንድ ጊዜ ክፍያ 50,000 ሩፒ ወይም 176 የአሜሪካን ዶላግ ከፍሎ መያዝ ህጋዊ ነው። ይሁን እንጂ እንደነዚህ ያሉት እንስሳት ከከተማው ወሰን ውጭ መቀመጥ ይኖርባቸዋል። ክስተቱ ያጋጠመው በፑንጃብ ግዛት የምትገኘው ላሆር የፓኪስታን ሁለተኛ ትልቋ ከተማ ናት።

የልጆቹ አባት የአንበሳው ባለቤቶች ጥቃቱ በቤተሰቤ ላይ ሲደርስ ቆመው ይመለከቱ እንደነበር ተናግሯል። አንበሳውን ለማስቆም ምንም ያደረጉት ነገር የለም ብለዋል። ቪዲዮው ላክ ሴትየዋ ራሷን ለማስመለጥ ስትታገል እና ከሰዎች እርዳታ ለመጠየቅ ወደ ኋላ ስትሸሽ ያሳያል። ከክስተቱ ከቀናት በኋላ የፑንጃብ ባለስልጣናት በህገወጥ መንገድ የተያዙ የዱር እንስሳት ላይ እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል። አምስት ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውለው 13 አናብስትን አስመልሰዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
😁2219💔5
በ33 የጤና ባለሙያዎች እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ

የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን የጤና ባለሙያዎችላይ የቁጥጥር ስራ ማከናወኑን አስታውቋል

በተደረገ የቁጥጥር ስራ 33 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች በሙያ ስነምግባር ምክንያት እርምጃ    እንደተወሰደባቸው የባለስልጣኑ የምግብና ጤና ነክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ለቁጥጥር አጋዥ የሆኑ በርካታ የኦፕሬሽን ስራዎች በመሰራታቸው በባለስልጣኑ ሰራተኞች እና በህብረተሰቡ ጥቆማ ባለሙያዎቹ ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል።

በቀጣይም የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ በ8864 ነጻ የስልክ መስመር ጥቆማ ቢሰጥ ባለስልጣኑ እርምጃ ይወስዳል ሲሉ አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
👎2310🤔4👌2
ትራምፕ የጋዛን የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ግፊት በሚያደርጉበት በዚህ ወቅት ኔታንያሁ አሜሪካን እየጎበኙ ነው

ከ21 ወራት ጦርነት በኋላ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በዋሽንግተን ሲገናኙ አዲስ የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንደሚኖር ያለው ተስፋ እየጨመረ ነው። ትራምፕ ቀደም ሲል ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ግጭቱን ለማስቆም ከኔታንያሁ ጋር “በጣም ጽኑ እምነህ” እንዳላቸው እና በዚህ ሳምንት “ስምምነት ይኖረናል” ብለው እንደሚያስቡ ተናግረዋል። አንጋፋው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር አይውሮፕላን ከመሳፈራቸው በፊት "የተነጋገርነውን ስምምነት ለማሳካት በተስማማንበት ሁኔታ እየሰራን ነው" ብለዋል።

"ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ያለው ውይይት ሁላችንም ተስፋ የምናደርገውን ይህን ውጤት ለማስቀጠል እንደሚረዳ አምናለሁ።" አሜሪካ ባቀረበችው የ60 ቀናት የተኩስ አቁም እና የታጋቾችን የመልቀቅ ስምምነት ላይ በእስራኤል እና በሃማስ መካከል የተደረገ ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይት እሁድ ማምሻውን በኳታር ተደርጓል።ነገር ግን፣ ስምምነቱ እንዳይደረስ በተከታታይ ያቆዩ ቁልፍ ልዩነቶች መወጣት ይቻል እንደሆነ ግልጽ አይደለም።በእስራኤል የዕለት ተዕለት የቦምብ ድብደባ በቀጠለው በከፋ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ፍልስጤማውያን እና አሁንም በሃማስ ቁጥጥር ስር ያሉ የእስራኤል ታጋች ቤተሰቦች ዘንድ ተስፋ ብቻ እየገለጹ ይገኛል።

በሰሜን ጋዛ ከምትገኘው ከቤት ላሂያ ከልጆቹ እና ከልጅ ልጆቹ ጋር ወደ ጋዛ ከተማ የሸሸው ናቢል አቡ ዳያህ "ከ60 ቀናት በኋላ ጦርነቱ እንደገና እንዳይጀመር እሰጋለሁ ጦርነትን ሙሉ በሙሉ ማቆም እንጂ የተኩስ አቁም አልፈልግም ።" ሲል ተደምጧል።ትራምፕ ወደ ስልጣን ከተመለሱ ስድስት ወራት እየተቃረበ ባለበት በዚህ ወቅት ኔታንያሁ ለሶስተኛ ጊዜ ዋይት ሀውስን እየጎበኙ ነው። ነገር ግን ዩናይትድ ስቴትስ የእስራኤልን የኢራን የኒውክሌር ጣቢያ ላይ ጥቃት ከሰነዘረች በኋላ በእስራኤል እና በኢራን መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት መደረሱን ተከትሎ መሪዎቹ ለመጀመሪያ ጊዜ ይገናኛሉ። በቅርቡ የተካሄደው የ12 ቀን የእስራኤል ኢራት ግጭት የተኩስ አቁም የጋዛን ጦርነት ለማስቆም የበለጠ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠሩ ተመላክቷል። ለወራት ዝቅተኛ ተወዳጅነት ደረጃ የተሰጣቸው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር በኢራን ላይ በከፈተት ጥቃት ሰፊ ህዝባዊ ድጋፍ ተሰጥቷቸዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
👎3124🔥3👍2
በመኪና አደጋ የተጎዳን ግለሰብ ሳያገኝ መንገድ ላይ ጥለው የተሰወሩ ግለሰቦችንና ተባባሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ


ሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 8:0 ላይ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 2A አዲስ አበባ 73886 አይነቱ ፕላትዝ የሆነ ተሽከርካሪን የምታሽከረክር ግለሰብ ከዊንጌት ወደ አስኮ በመጓዝ ላይ እያለች ጨረታ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ አንድ እግረኛ ላይ ጉዳት ታደርሳለች፡፡

አደጋ አድራሿ በአካባቢው ከነበሩ ግለሰቦች ጋር በመተባበር አደጋ የደረሰበትን ተጎጂ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የግል የህክምና ተቋም ይዘውት እንደሄዱና ካርድ ካወጡ በኋላ የተጎጂው ማንነት የሚገልፅ መታወቃያ የሌለው በመሆኑ እርዳታ ለመስጠት እንደሚቸገሩና ወደ ሌላ ሆስፒታል ይዛው እንደሄዱ ግለሰቧ ለፖሊስ ከሰጠችው ቃል ማወቅ ተችሏል።

አሽከርካሪዋ ያጋጠማትን ችግር ለባለቤቷ በስልክ ደውላ ማሳወቋን ተከትሎ ባለቤቷ ከጓደኛው ጋር በመምጣት እሷን በሌላ መኪና ወደቤቷ በመሸኘት የአደጋ አድራሿ ባለቤትና ጓደኛው ተጎጂውን ይዘው ይሄዳሉ፡፡

ግለሰቦቹ ተጎጂውን ይዘውት ከሄዱ በኃላ ምንም አይነት ህክምና ሳያገኝ እስከ ምሽቱ 2፡00 ሲጠባበቁ ቆይተው ባለመንቃቱ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7ልዩ ቦታው አቧሬ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ ጭር ያለ ቦታ አጥር ጥግ ጥለውት መሰወራቸው ተረጋግጧል።

ሪፖርት የደረሰው ፖሊስ ግለሰቡ ወደ ሆስፒታል እንዲሄድ ካደረገ በኃላ ባደረገው ምርመራ ስለ አደጋው ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ በመቀበል ባደረገው ክትትል አደጋ ያደረሰችውን አሽከርካሪ፣ ባለቤቷን እንዲሁም ከፖሊስ ማስረጃ ሳያገኝ አደጋ ያደረሰውን ተሽከርካሪ የፊት መስታወት የቀየረን ግለሰብን ይዞ ምርመራው መቀጠሉን እና የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል
54👍22🤬11
የሱዳን ጦር ካርቱም ከተቆጣጠረ ወዲህ ከ3 ሺ በላይ አስከሬኖችን ማግኘቱ ገለፀ

የሱዳን ባለስልጣናት ከተማይቱን ከወታደራዊ ሃይል መልሶ ከተቆጣጠረ በኋላ በዋና ከተማይቱ ካርቱም ጎዳናዎች እና ቤቶች የተገኙ 3ሺ 800 አስከሬኖችን ቀብረናል ሲሉ የፎረንሲክ ባለስልጣን ሃላፊ አስታውቀዋል። ለወራት በዘለቀው ከባድ የከተማ ጦርነት በርካታ ነዋሪዎች በሁከቱ ተገድለው ወደ መቃብር ቦታ መድረስ ባለመቻላቸው ሟቾችን በየቤቱና በየአደባባዩ በጊዜያዊ መቃብር እንዲቀብሩ አስገድዷቸዋል።

የፎረንሲክ ባለስልጣን ኃላፊ ሂሻም ዘይን አል-አቢዲን በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንዳሉት በግንቦት ወር ካርቱምን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ካወጀ በኋላ ቡድኖች መላካቸው እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የጅምላ መቃብሮች ማግኘታቸውንም አስታውቀዋል። ከተጎጂዎቹ መካከል ብዙዎቹ ከተማዋን በሚቆጣጠሩበት ወቅት በፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች (RSF) ተገደው እንዲሰወሩ እና እንዲገደሉ ተደርገዋል ተብሎ ይታመናል።

የሰፊው ዋና ከተማ አካል በሆነው በኦምዱርማን አሮጌ ሰፈሮች ውስጥ የመቃብር ቦታዎችን ለመቃኘት የፎረንሲክ፣ የጸጥታ እና የአካባቢ ባለስልጣናትን ያካተተ ኮሚቴ ተቋቁሟል ሲል ዘይን አል-አቢዲን ተናግረዋል። የጤና ሚኒስቴሩ መግለጫውን በቅርቡ ለተነሳው ውዝግብ ተጠቅሞ የነበረ ሲሆን አንድ የፎረንሲክ ባለስልጣን የልጇን አስከሬን ለቀብር ለማጓጓዝ ከአንዲት ሴት አራት ሚሊየን የሱዳን ፓውንድ ጠይቋል የሚለውን ውንጀላ ውድቅ አድርጓል። ባለሥልጣኑ በቀረበው ቅሬታ ላይ የሰላ ትችት እንደገጠመው የገለጸው ሚኒስቴሩ፣ አገልግሎቱን በነጻ የሚሰጥ መሆኑን በድጋሚ ገልጿል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
💔2214😱5
በ2017 በጀት አመት ከ2 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ህፃናትን ከመቀንጨር ለመታደግ በሰቆጣ ቃል ኪዳን ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል

የምግብና ስርአተ-ምግብ ስትራቴጂ እና ሰቆጣ ቃልኪዳን ፕሮግራም እንዲሁም የማህበረስብ አቀፍ ጤና መድህን የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጻም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል።የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በዚህ ወቅት የምግብና ስርአተ-ምግብ ስትራቴጂ አፈጻጻም ጤናማ እና አምራች ዜጋ ለመፍጠር እያገዘ ይገኛል ማለታቸውን ብስራት ሰምቷል።

የሰቆጣ ቃል ኪዳን የ15 ዓመታት ስትራቴጂ ትግበራ በ334 ወረዳዎች ላይ ሲከናወን መቆየቱን  ሚኒስትሯ አብራርተዋል:: ባለፋት አራት አመታት ተስፋ ሰጪ በሆነ መልኩ ሲተገበር መቆየቱን ተናግረው በነፍሰ ጡር እና በሚያጠቡ እናቶች እንዲሁም በህፃናት ላይ የሚከሰተውን መቀንጨር ዜሮ ለማድረግ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ጥረት መደረጉን ገልፀዋል።

በ2017 በጀት ዓመትም ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ  ነፍሰ ጡርና የሚያጠቡ እናቶችን እንዲሁም ከ2 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ከሁለት አመት በታች ያሉ  ሕጻናትን ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ አስረድተዋል፡፡ የሰቆጣ ቃል ኪዳን ተፅዕኖን ለማሳደግ በ2018 ዓ.ም በሁለተኛ ምዕራፍ  ትግበራውን ወደ 520 ወረዳዎች ለማስፋፋት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ሚኒስትሯ ጨምረው  ገልፀዋል፡፡

መቀንጨርን ዜሮ ለማድረስ የምግብና ሥርዓተ ምግብ ተግባራትን ሽፋን ከፍ በማድረግና ለ15 ዓመታት ፍኖተ ካርታው ሃብት በመመደብ በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተመሳሳይ ሥራዎችን ማከናወን ይገባል። መንግስት እድሜያቸው ከሁለት አመት በታች በሆኑ ህፃናት ላይ የሚከሰተውን መቀንጨር በ2022 አ/ ም ዜሮ ለማድረግ የሰቆጣ ቃልኪዳን ፕሮግራምን በ2007 ዓ.ም ይፋ በማድረግ ትግበራውን በማከናወን ላይ ይገኛል።

በ15 አመት ፍኖተ ካርታው መሰረት ከ7ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ህፃናትን ከመቀንጨር ለመታደግ የተገባ ሀገራዊ ቃል ኪዳን ነው።

ቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
15👌1
በፑቲን ከሥልጣናቸው የተባረሩት ሚኒስትር ራሳቸውን አጠፉ

የቀድሞ የሩሲያ የትራንስፖርት ሚኒስትር ሮማን ስታሮቮይት ራሳቸውን በጥይት ገድለው መገኘታቸውን የሩሲያ መርማሪ ኮሚቴ አስታውቋል። ግለሰቡ ራሳቸውን አጥፍተዋል ከመባሉ ቀደም ብሎ ሰኞ ዕለት በፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከሥልጣናቸው ተሰናብተዋል።

ስታሮቮይት ከሥልጣን የተነሱበት ምክንያት ያልተገለፀ ሲሆን፣ ብዙም ሳይቆይ ምክትላቸው አንድሬ ኒኪቲን በምትካቸው ተሾመዋል። የምርመራ ኮሚቴው ሁኔታውን ለማጣራት እየሰራ መሆኑን የገለፀ ሲሆን ስታሮቮይት እአአ በግንቦት 2024 ነበር የትራንስፖርት ሚኒስትር ሆኖ ተሹመው የነበረው።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
💔31👀179🤔8👎2
ሁቲዎች የእስራኤል ጥቃት እስኪያበቃ ድረስ ጋዛን መደጋፍ እንደሚቀጥሉ አስታወቁ

አንድ ከፍተኛ የሃውቲ ባለስልጣን ቡድኑ ለፍልስጤማውያን ያለውን ድጋፍ በቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፣ ጋዛን ለመደገፍ የሚደረገው እንቅስቃሴ እስራኤላውያን ጥቃት እስኪያቆሙና ከበባው እስኪያነሱ ድረስ አይቆምም ብለዋል።

እሁድ እለት የመን ላይ መገኛውን ያደረገው ቡድኑ በእስራኤል ቤን ጉሪዮን አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ባለስቲክ ሚሳኤል መተኮሱን አስታውቋል። ይህን ተከትሎም የእስራኤል ጦር በቀይ ባህር ዳርቻ የሚገኙትን የሆዴዳህ፣ ራስ-ኢሳ እና አስ-ሳሊፍ ወደቦችን እንዲሁም ራስ ካትብ የኃይል ማመንጫን ኢላማ አድርጓል።

በጋላክሲ ሊደር መርከብ ላይም የራዳር ሲስተም በሃውቲዎች ተይዞ ቀሪው በሆዴይዳ ወደብ ላይ እንዳለም ተናግሯል። ሰነዓን እንዲሁም የምዕራብ እና ሰሜናዊ የየመንን ሰፊ ክፍል የተቆጣጠሩት ሁቲዎች ከህዳር 2023 ጀምሮ በእስራኤል ላይ የሚሳኤል እና የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ሲፈጽሙ የቆዩ ሲሆን የዚህ ምክንያት ደግሞ እስራኤል በጋዛ ላይ የጀመረችውን ጦርነት ነው።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
77🔥10👎6🙏4👏3😁1
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ11 ወራት ከ18.2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተገለጸ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ ለቋሚ ኮሚቴው ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ከመደበኛ እና ከማዘጋጃ ቤቶች ገቢ ከ21 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ በ11 ወር ከ15 ቀናት ውስጥ ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ የተሰበሰበ ሲሆን ከባለፈዉ ዓመት ተመሣሣይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡

ከታክስ እና ንግድ ማጭበርበር እንዲሁም ገቢ ስወራ በ6 ዞኖች እና በክልል ማዕከል የተሰራ የኢንተለጀንስ ጥናት በ107 ታክስ ከፋዮች ላይ የማጣራት ሥራ ተሰርቶ 1 ሺህ 450 ታክስ ከፋዮች በተገኘ ሐሰተኛ  ደረሰኝ 86 ሚሊዮን ብር ያልከፈሉትን ታክስ እንደከፈሉ በማድረግ በተመላሽ ስም ከየተቋማቱ መወሰዱ ታውቋል።ተቋማዊ የውስጥ ስጋትን ለመቀነስ የኦዲት ምርመራ በመስራት በቅድመ መከላከል  ሰባት  ዞኖችና ላይ በተሰራ ኦዲት ከ52 ጥራዝ ደረሰኝ 51 ሚሊዮን ብር የመንግስት ሀብት ማዳን ተችሏ::

በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ከ15 ቀናት ከገጠር መሬት መጠቀሚያና ከእርሻ ሥራ ገቢ ግብር ብር ከ486 ሚሊዮን በላይ ለመሰብሰብ በዕቅድ ተይዞ  ከ312 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል።በበጀት ዓመቱ በ12 ማዕከላት ላይ አዲስ የሲግታስ ዝርጋታ ሥራ በመከናወኑ በክልሉ ከ64 የታክስ ማዕከላት ወደ 80 ዕድገት ማሳየቱ ተመላክቷል።

የክልሉ አስተባባሪ አካላት ለገቢ አሰባሰብ ሥራ የተለየ ትኩረት መስጠታቸው ፣ ጠንካራና ተከታታይ የክትትል ፣ ድጋፍና ግብረ-መልስ ስርዓት መዘርጋቱ ፣ የህግ ማዕቀፎችን በማሻሻል የታክስ መሰረቱን የማስፋት ስራዎች መከናወኑ እና ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት የገቢ መጠኑ 5.8 ቢሊዮን ብር በላይ  ዕድገት ማሳየቱ በጠንካራ የተስተዋሉ ጉዳዮች መሆናቸውንም አክለዋል።

በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል
10👎1
2025/07/13 20:43:07
Back to Top
HTML Embed Code: