በአዲስ አበባ ከተማ በጥበቃ ስራ ከሚሰሩበት ተሸከርካሪ የሰረቁ ሦስት ግለሰቦች በወላይታ ሶዶ ከተማ በቁጥጥር ስር ዋሉ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ የክልሉ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃ ደህንነትና ከአዲስአበባ ፖሊስ ጋር በመሆን በተሠራ ስራ ተጠርጣሪዎቹ ከተሽከርካሪው ሊያዙ ችለዋል።
ድርጊቱን የፈፀሙት ተከሳሾች የስርቆት ወንጀሉን የፈጸሙት በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ውስጥ የጥበቃ ስራ ከሚሠሩበት ድርጅት እንደሆነ የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ግለሰቦቹ ተሽከርካሪዎችን ሠርቀው የተሰወሩ ቢሆንም ከተሰረቁት ተሽከርካሪዎች ውስጥ አንዱን የክልሉ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመሆን በትላንትናው እለት ማለትም ሰኔ29 ቀን2017ዓ/ም በሶዶ ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
የተያዙት ተጠርጣሪዎችንና ተሽከርካሪውን የወንጀል ድርጊቱ ወደ ተፈጸመበት አዲስ አበባ ፖሊስ ተልኳል፡፡በአጠቃላይ አምስት ተሽርካሪዎች የተሰረቀ ሲሆን አምስት ግለሰቦች ወንጀሉን እንደፈጸሙ ተገልጿል፡፡ በወላይታ ሦስት ተከሳሾች ከአንድ ተሸከርካሪ ጋር መያዙን የተነገረ ሲሆን በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ይህን መሰል ድርጊቶች እየተበራከቱ በመምጣታቸውም በቀጣይ የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል

❤24👍5
ኢራን በእስራኤል እና በአሜሪካ የሚፈፀመው የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ ጥቃት 'ከባድ' የአካባቢ አደጋዎች ያደርሳል ስትል አስጠነቀቀች
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ባለፈው ወር የእስራኤል ገዥ አካል እና ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን የኒውክሌር መሥሪያ ቤቶች ላይ ያደረሱት ጥቃት ከባድ የሰው እና የአካባቢ አደጋዎችን እንደሚያስከትል በመግለፅ “ሊጠገን የማይችል” የስነምህዳር ጉዳት እንደሚያደርስ አስጠንቅቀዋል። ከፍተኛ ዲፕሎማቱ ጥቃቱን “ግዴለሽ ሆነ እና ጨካኝ” ሲሉ አውግዘዋል። ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት በብራዚል ሪዮ ዴ ጄኔሮ የብሪክስ ታዳጊ ኢኮኖሚ ሀገራት ቡድን የመሪዎች ስብሰባ ላይ ነው።
እ.ኤ.አ. ከሰኔ 13 እስከ 25 ባለው ጊዜ ውስጥ በአገዛዙ ባልተቀሰቀሰ ጦርነት ወቅት የእስራኤል ጥቃት በርካታ የኢራን የኒውክሌር ግንባታዎችን ኢላማ አድርጓል። ዩናይትድ ስቴትስም ጥቃቱን መጨረሻ አካባቢ ተቀላቀለች፣ በመካከለኛው እና በሰሜን መካከለኛው የኢራን ክፍሎች ለሰላማዊ የዩራኒየም ማበልጸጊያ የሚያገለግሉ ቁልፍ ቦታዎችን ተመተዋል። "ሁለቱ የኑክሌር ኃይል የታጠቁ ሀገራት የኑክሌር ጦር መሳሪያ በሌላት ኢራን ላይ የሚያጠቁበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው" ሲሉ አራግቺ ተደምጠዋል።
አክለውም ኢራን የኑክሌር ስምምነት (NPT) አባል ብትሆንም እንዲሁም የሀገሪቱ ሰላማዊ የኒውክሌር እንቅስቃሴ በአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) አጠቃላይ ጥበቃ ቢረጋገጥም ሁለቱ ሀገራት ግን በጣም አደገኛ ጥቃቶችን መፈጸማቸውን አስታውሰዋል። የእስራኤል አገዛዝ እና ዩናይትድ ስቴትስ የኤጀንሲውን የቅርብ ጊዜ ፀረ-ኢራን ውሳኔን ተጠቅመው ጥቃቱን ለማስረዳት ሞክረዋል። በከባድ የምዕራባውያን ጫና የተነደፈው ውሳኔ፣ አገሪቱ በታሪክ ውስጥ የተቆጣጣሪውን አካል ፍተሻ ደረጃ አሟልታ ብትገኝም ኢራን የኤጀንሲውን የጥበቃ ግዴታዎች “አታከብርም” በማለት ከሰዋታል ሲሉ ወቅሰዋል።
በስምኦን ደረጄ

❤34👍2👎1🕊1
13 በመቶ የሚሆኑ የኢትዮጵያ እናቶች የልጅነት እርግዝና ተጋላጭ ናቸዉ ተባለ
በኢትዮጵያ መሰረታዊ የሚባሉ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች የልጅነት ጋብቻ ፣ግርዛት ፣ አካላዊ አዕምሮአዊ እንዲሁም ስነ ልቦናዊ ጥቃቶች መሆናቸው ተነግሯል።
በኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች የሚያገቡ ሴቶች ቁጥር በጣም ከፍተኛ ሲሆን ይህም 13 በመቶ የሚሆኑ የኢትዮጵያ እናቶች የልጅነት እርግዝና የሚፈጠርባቸው መሆኑን በፕላን ኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ክፍል ሃላፊ ዶክተር ምስክር ጌታሁን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።ትዳር ውስጥ ከሚገቡት ታዳጊዎች መካከል 75 በመቶ የሚሆኑት አምስተኛ ክፍል ሳይደርሱ ትምህርት የሚያቋርጡ መሆናቸው ተነግሯል።
በ2016 ከ15 እስከ 49 ባሉ ሴቶች ላይ በተሰራ ጥናት በሶማሊ 99 በመቶ፣ በአፋር ደግሞ 91 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች መገረዛቸውን ተረጋግጧል ። በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የጸጥታ ችግሮች ህጉ እንዳይተገበር እና የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እንዳይደርጉ እንቅፋት ስለሚሆን በታሰበው ልክ ጥቃቶችን ማስቆም እንዳልተቻለ ገልጸውልናል።
የጠለፋ ፣ የአስገድዶ መደፈር ፣ የስነልቦና እና የአዕምሮ ጥቃቶች ቀላል የማይባሉ መሆኑን እና ሁሉም የሚመለከተው አካል በሙሉ ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ነግረውናል።
ለሴቶች ስጋት የሚሆንባቸው ሳይሆን የሚደግፍ ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ እና ጥቃት ያደረሱ ሰዎች በቀላል መንገድ የሚለቀቁ ሳይሆን ህጉን መሰረት ባደረገ መልኩ አስተማሪ የሆነ ቅጣት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ይህም ለሌሎች መማሪያ እንደሚሆን ዶክተር ምስክር ጌታሁን ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
በኤደን ሽመልስ

❤22👎3🤔3🙏1
ለህፃናት ለመጀመሪያ ጊዜ የወባ መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዲዉል ተፈቀደ
ለህፃናት ተስማሚ የሆነው የመጀመሪያው የወባ ህክምና አገልግሎት ጥቅም ላይ እንዲውል ተፈቀደ፡፡ህክምናዉ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ በአፍሪካ ሀገራት ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። እስካሁን ድረስ በተለይ ለሕፃናት የተፈቀደ የወባ መድኃኒት የለም።በምትኩ ለታዳጊ ወጣቶች በተዘጋጁ ስሪቶች ታክመዋል ይህም ከመጠን በላይ አደጋን ያመጣል የሚል ስጋትን ፈጥሯል፡፡
እ.ኤ.አ. በ 2023 የቅርብ ጊዜ አህዛዊ መረጃ እንደሚያየዉ በወባ ምክንያት በዓመት 597 ሺ የሚጠጉ ሰዎች ሞት ተመዝግቧል ።ከሞላ ጎደል ሁሉም የሟቾች ህልፈት የተመዘገበዉ በአፍሪካ ዉስጥ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ሶስት አራተኛው የሚሆኑት ከአምስት አመት በታች ያሉ ህጻናት ናቸው።በልጆች ላይ የወባ ሕክምና ቢሰጥም እስካሁን ድረስ ከ 4.5 ኪሎ ግራም ወይም ከ 10 ፓውንድ በታች ለሆኑ ትንንሽ ሕፃናት የተለየ መድኃኒት አልነበረም።
ይልቁንም ለትላልቅ ህጻናት ተብለው በተዘጋጁ መድሃኒቶች ታክመዋል፡፡ለነዚህ ትልልቅ ህጻናት የሚሰጠዉ መድኃኒት የጉበት ተግባር ገና በማደግ ላይ በሚገኘዉ ሰውነታቸው ላይ መድሀኒቶቹ አደጋዎችን ያስከትላሉ፡፡ይህም የሕክምና ክፍተት ተብሎ ወደሚጠራው ደረጃ እንዳመራ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
አሁን ኖቫርቲስ በተባለው የመድሀኒት ኩባንያ የተሰራ አዲስ መድሃኒት በስዊዘርላንድ ባለስልጣናት የተፈቀደ ሲሆን በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ የወባ በሽታ ባለባቸው ክልሎች እና ሀገራት ሊሰራጭ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።ኖቫርቲስ ለትርፍ ያልተቋቋመ በመሆኑ መድኃኒቱን በስፋት ለማስተዋወቅ እያቀደ ይገኛል።

❤19👏1🙏1
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በ17 የግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች የክትትል ካሜራ ቴክኖሎጂ ተግባሪያዊ አደረገ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በስሩ የሚገኙ 17 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች የስራ እንስቃሴዎች ከማዕከል ለመከታተልና ለመቆጣጠር የሚያስችል የሰርቪሊያንስ ካሜራ ቴክኖሎጂ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመተባበር ወደ ተግባር መግባቱን አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የኮሙኒኬሽን ክፍል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሰውነት አየለ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት የሰርቪሊያንስ ካሜራ ቴክኖሎጂ በሁሉም ቅርንጫፎች የሰራተኞች የስራ እንቅስቃሴ፣ የግብር ከፋዮች መስተንግዶና አገልግሎት አሰጣጥን ለመከታተልና ችግሮች ለማረም የሚያግዝ መሆኑ ገልጸዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የሰርቪሊያንስ ካሜራው ከማዕከል ሊተላለፉ የሚገባቸው መረጃዎችን በተመሳሳይ ሰዓት ለማድረስ እንዲሁም የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን በመከታተል እንዲታረሙ ለማድረግ ያስችላል ተብሏል፡፡በአሁኑ ወቅት የቴክኖሎጂው የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቅቆ ወደ ተግባር የገባ ሲሆን ሁለተኛው ምዕራፍ እስከ መስከረም ወር ለማጠናቀቅ እየተሰራም ይገኛል፡፡
በሁለተኛ ምዕራፍ ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ከማዕከል ወደ ሁሉም ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ድምፅን ያካተተ የቪዲዮ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ፣ ለግብር ከፋዮች ግንዛቤ የሚፈጥሩ አጫጭር መረጃዎችና ትምህርቶች ለመስጠት ይረዳል ተብሏል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 1 ከፍተኛ ፣ 5 መካከለኛ፣ 11 አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ያሉት ሲሆን በስሩ ከ7 ሺህ በላይ ሰራተኞች የሚመራ ተቋም መሆኑ አቶ ሰውነት አየለ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

😁16❤11🤣3
በሰባት ዓመት ታዳጊ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ የሰባት ዓመት ታዳጊን ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ።
በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዳንጋራ ሳላጣ ማዘጋጃ ነዋሪ የሆነው ተመስገን ማቲዎስ ማንዳዶ የሰባት ዓመት ታዳጊዋን አስገድዶ በመድፈር ሀምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ፍ/ቤት በዋለው ችሎት 18 ዓመት እስራት ተቀጣ።
ተከሳሽ ተመስገን ማቲዎስ የተባለው ግለሰብ ዕድሜ 26 ዓመት ሲሆን ውብዓለም ደነቀ ሴ ከገበያ በማታለል ወደ ቤቱ ወስዶ በዕለቱ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ በግሉ መኖሪያ ቤት አስገድዶ መደፈር ድርጊት መፈጸሙን ብስራት ሬዲዮ ከወረዳዉ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

🤬22❤9🔥2😁2👍1👎1
በአል-አቅሳ ሆስፒታል ቀዶ ህክምና በሞባይል መብራት (ፍላሽ ላይት) እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
በጋዛ እየተባባሰ ያለውን የሰብአዊ ቀውስ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በደረሰበት በዚህ ወቅት የአል-አቅሳ ሰማዕታት ሆስፒታል ዶክተሮች በተቋሙ ውስጥ ያለውን የነዳጅ አቅርቦት በጣም አነስተኛ በመሆኑ ህይወት አድን የሆኑ የህክምና አገልግሎቶችን ቀዶ ህክምናን ጨምሮ በሞባይል ስልክ መብራቶች እየተጠቀሙ እያከሙ ነው ተብሏል።
በኤሌክትሪክ እና በነዳጅ እጦት ምክንያት በሞባየል ፍላሽ ላይት ላይ ብቻ በመተማመን የህክምና ሰራተኞች በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የአደጋ ጊዜ ውስብስብ የቀዶ ጥገና ሂደቶችን ሲያደርጉ ታይተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት እና ሌሎች የሰብአዊ እርዳታ ኤጀንሲዎች ቀደም ሲል በጋዛ የተበላሹ የጤና መሠረተ ልማቶች ሙሉ በሙሉ ሊወድቁና ስራ ሊያቆሙ እንደሚችሉ አስጠንቅቀው ነበር።
የጋዛ አከባቢ የሚገኙ ሆስፒታሎች በአየር ድብደባ፣ በኤሌክትሪክ መቆራረጥ እና በእስራኤል ከበባ ምክንያት ጄነሬተሮችን ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልገው ነዳጅን ጨምሮ አስፈላጊ የሆኑ ሸቀጦችን ባለማግኘታቸው ምክንያትና በተደጋጋሚ የጥቃት ኢላማ በመደረጋቸው ሳብያ ለመዝጋት ተገደዋል።
የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የህክምና ባለሙያዎች አስከፊ የህይወት መጥፋትን ለመከላከል ነዳጅ እና የህክምና አቅርቦቶችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ አስቸኳይ አለምአቀፍ ጣልቃ ገብነትን እየጠየቁም ነው።
በሚሊዮን ሙሴ

😭136💔51❤14
በጋምቤላ ክልል በሜዳ ላይ ከመፀዳዳት የፀዱ ቀበሌዎች ሽፋን ከ20 በመቶ ያነሰ ነው ተባለ
በጋምቤላ ክልል በኑዌር ብሄረሰብ ዞን ማኩዌይ ወረዳ ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ ቀበሌዎች እወጃ መድረክ ተካሂዷል።የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር አቤል አሰፋ በመድረኩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፋት መልእክት በክልሉ መጸዳጃ ቤትን ቆፍሮ የመጠቀም ልምድ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየተሻሻለ ቢመጣም በታቀደው ልክ አለመሆኑን ተናግረዋል።
በክልሉ ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት የፀዱ ቀበሌዎች ሽፋኑ ከ20 በመቶ ያነሰ ነው ያሉት ሀላፊው የተሻሻለ መፀዳጃ ቤት ሽፋን ደግሞ 23 በመቶ አካባቢ እንደሆነ መናገራቸውን ብስራት ሰምቷል።እንደዚሁም ከሜዳ ላይ መፀዳዳት ነፃ ለሆኑት ቀበሌዎች ይህን የጤና ችግር ለመቅረፍ "ሜዳ ላይ መፀዳዳት ይብቃ" ትውልድ ይዳን ! መፀዳጃ ቤት መጠቀም ልማዳችን ይሁን ብላችሁ ለዚህ ደረጃ በመብቃታችሁ ያስመሰግናችኋል ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም የግልና የአካባቢ ንፅህናን በመጠበቅ ከበርካታ ተላላፊ በሽታዎች እራሳችሁን እንድትጠብቁ ሲሉ አሳስበዋል።የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወንድም አገኘሁ በላይነህ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በክልሉ የሚገኙ በርካታ ቀበሌዎች ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ያላደጉበት ምክንያቱ ብዙ ነው።
በዋነኛነት የአመራር ቁርጠኛ አለመሆን፣የባለሙያዎች ተነሳሽነት ማነስ፣በቂ ድጋፍና ክትትል አለመኖር፣የህብረተሰቡ አመለካከት አለመለወጥ እንዲሁም የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች በአግባቡ ከማህበረሰቡ ጋር አለመስራት ተጠቃሽ ናቸው።ይህም በመሆኑ በክልሉ በርካታ ህፃናት በተቅማጥ በሽታ እና በአንጀት ጥገኛ ትላትል በመጠቃት ፣ለምግብ እጥረት በመጋለጥ ለመቀንጨርና ለሞት ሲዳረጉ ቆይተዋል ሲል ቢሮው አስታውቋል።
ቅድስት ደጀኔ

😁36❤10👀5💔2
አሜሪካ ከፍተኛ ታሪፎችን ለመጣል የያዘችዉን እቅድ ብታዘገይም በአንዳንድ ሀገራት ላይ ግን አዲስ ታክስ ጣለች
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከአሜሪካ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ ምርቶች ላይ ከፍተኛ ቀረጥ ለመጣል በይፋ እንደሚዘገይ የገለጹ ሲሆን፥ ጃፓንና ደቡብ ኮሪያን ጨምሮ 14 ሀገራት የሚገጥማቸውን ቀረጥ በዝርዝር የሚገልጹ ደብዳቤዎችን ግን ልከዋል።
የቅርብ ጊዜው ዉሳኔ የተሰማዉ ዋይት ሀውስ በአንዳንድ በጣም አስጨናቂ በሆኑ ግብሮቹ ላይ በዚህ ሳምንት ጊዜው እንዲያበቃ በቀጠረበት ወቅት ነው።ፕሬዝዳንቱ ከጃፓንና ከደቡብ ኮሪያ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ25በመቶ ቀረጥ እንደሚጣል ዛቻቸዉን በማጠናከር ከኦገስት 1 ጀምሮ ለአለም መሪዎች የቀረጥ ማስጠንቀቂያ ሌሎች ደብዳቤዎችን አጋርተዋል።
ቀደም ሲል ከዋይት ሀውስ ባለስልጣናት ጋር የንግድ ስምምነቶችን ለመድረስ እንደሚፈልጉ በመግለጽ ከፍተኛ ታሪፎች በጁላይ 9 ተግባራዊ እንዳይደረጉ ታግዶ ነበር።ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ተመራማሪው አዳም አህመድ ሳምዲን ለቢቢሲ እንደተናገሩት የንግድ ስምምነቱ ለመድረስ ዓመታት የሚወስድ በመሆኑ ማራዘሙ ምንም አያስደንቅም ብለዋል።
ምንም እንኳን ቬትናም ከዩናይትድ ኪንግደም ቀጥሎ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ ሁለተኛዋ ሀገር ብትሆንም ከሙሉ ስምምነት ይልቅ ንግግሮችን የሚያፋጥን "ሰፊ ማዕቀፍ" ነበር ብለዋል ።በተጨማሪም ሰኞ እለት ትራምፕ ለ14 ሀገራት መሪዎች የተላኩ ደብዳቤዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በማጋራት የቅርብ ጊዜውን የታሪፍ እቅዳቸውን አሳዉቀዋል፡፡ በዚህም መሰረት “ከሀገርዎ ጋር ባለን ግንኙነት ላይ በመመስረት ታሪፉ ወደ ላይ ወይም ወደ ታች ሊሻሻል ይችላሉ” ብለዋል ።

❤22
በቤንች ሸኮ ዞን በበጀት ዓመቱ ከ1ሚሊዮን ኩንታል በላይ የፍራፍሬ ምርት ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡ ተነገረ
ቤንች ሸኮ ዞን የኢትዮጵያ ፍራፍሬ አምባሳደር በመባል በ2006 ዓ.ም ስያሜ ማግኘቱ ይታወቃል ። በዞኑ ከቡና በተጨማሪ እንደ ሙዝ ፣አቮካዶ ፣ፖፖያና ሌሎችም የፍራፍሬ ምርቶች በብዛት እንደሚመረቱ የዞኑ ግብርና አስታውቋል ።
በ2017 በጀት ዓመት 181,794 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ በሆርቲካልቸር እና በዋና ዋና ሰብሎች ከ189 ሄክታር በላይ መሬትን በዘር መሸፈን መቻሉን የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ጉብላ ከጣቢያችን ብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ተናግረዋል ። በተለያዩ የሆርቲካልቸር ሰብሎች ከ67ሺህ ሄክታር በላይ መሬትን በዘር ለመሸፈን በዕቅድ ተይዞ በዓመቱ መጨረሻ ከመቶ ፐርሰንት በላይ ማሳካት መቻሉን የዓመቱ ሪፖርት ያሳያል ተብሏል ።
በተጨማሪም እንደ ዞን 90,933.93 ሄክታር መሬት በነባር ፍራፍሬ የተሸፈነ መሬት መሆኑ ተገልጾ ከዛ ውስጥ ምርት ከሚሰጥ 59,515.125 ሄክታር መሬት ይሰበሰባል ተብሎ የሚጠበቅ የፍራፈሬ ምርት 13,999,880 ኩንታል እንደነበር ተገልጿል ። በዚህም የተነሳ ከ52,813.48 ሄክታር መሬት ከ11 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ምርት የተገኘ ሲሆን ምርታማነት በሄክታር 221 ኩንታል ማድረስ መቻሉ ተነግሯል ። ከ1ሚሊዮን 127ሺህ 921 ኩንታል በላይ የፍራፍሬ ምርት በበጀት ዓመቱ ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን አቶ መስፍን ጨምረዉ ገልፀዋል ።
በመባ ወርቅነህ

❤15👍1
ኔታንያሁ ከሃማስ ጋር የሚያደርገውን ድርድር እንዲያቆም ተጠየቁ
በሰሜን ጋዛ ቤይትሃኖን ሰኞ አመሻሹ ላይ በመንገድ ዳር በተጠመደ ቦምብ ቢያንስ አምስት የእስራኤል ወታደሮች መሞታቸውን በተዘገበበት በዚህ ወቅት አክራሪ ፅዮናውያን ከሀማስ ጋር የሚደረገው የተኩስ አቁም ድርድር እንዲቆም እየጠየቁ ይገኛል።
ይሄን ጥያቄ ካቀረቡት ፅዮናውያን መካከል ደግሞ የቀኝ አክራሪው የእስራኤል የብሄራዊ ደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን-ጊቪር ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ "በዶሃ ከሃማስ ነፍሰ ገዳዮች ጋር ለመደራደር የሄደውን ልዑካን ወዲያው እንዲመለሱ" ጥሪ አቅርበዋል።
በቴሌግራም ላይ በተጋራ መግለጫው ላይ "የእኛን ተዋጊዎች ከሚገድሉት ጋር መደራደር አያስፈልግም፤ አጥንታቸው ልንሰብረውና በረሀብ ልንገድላቸው እንዲሁም በሰብአዊ እርዳታ መታገዝ የለባቸውም" ሲል በቴሌግራም ላይ በወጣው መግለጫ ተመላክቷል።
በተጨማሪም ጋዛ ሙሉ በሙሉ እንዲከበብ፣ ፍልስጤማውያን እንዲፈናቀሉ እና የእስራኤል ዜጎች በክልል እንዲሰፍሩ ጥሪ አቅርበዋል፣ “እነዚህ ሙሉ ለሙሉ የድል ቁልፎች ናቸው እንጂ በሺዎች የሚቆጠሩ አሸባሪዎችን የሚፈታ እና [የእስራኤልን ጦር] በታጋዮቻችን ደም ከተቆጣጠሩት ግዛቶች የሚያስወጣ የግዴለሽነት ስምምነት አያስፈልግም” ብለዋል።

👎91❤13👍11🤬8😁1🕊1👀1
ትላንት በዲላ ከተማ አንዲት አስተናጋጅ ላይ በጠርሙስ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረበ።
ፖሊስ ክሱን ለማጣራት ተጨማሪ 7 ቀናት እንዲሰጡት ፍርድ ቤቱን የጠየቀ ሲሆን፣
ፍርድ ቤቱም ጥያቄውን በመቀበል ተጠርጣሪው ከ7 ቀናት በኋላ ዳግም እንዲቀርብ ወስኗል።
Via ጉርሻ

💔124😭58🤬25❤19👍6
በሀረር ክልል በበጀት ዓመቱ 40 ቋሚ እና 100 ተንቀሳቃሽ ቅርሶች መመዝገብ መቻሉ ተገለፀ
በሀረር ክልል በበጀት ዓመቱ 40 ቋሚ ቅርሶችን ለመመዝገብ በታቀደው መሰረት 40 በጀጎል ውስጥ የሚገኙ ባህላዊ ቋሚ ቅርሶችን ለመመዝገብ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም 100 ተንቀሳቀሽ ቅርሶችን ለመመዝገብ በታቀደው መሰረት 100 በብሔራዊ ሙዚየም የሚገኙ የባህላዊ እቃዎች ለመመዝገብ መቻሉን የሀረሪ ክልል የባህል ቅርስ እና ቱሪዝም የእቅድ ዝግጅት ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አፈንዲ አብዲ ኡስማኤል ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ለተቋም አቅም ግንባታ በፌዴራልና በተለያዩ ድጋፍ እድራጊ ድርጅቶች ደረጃ የቁሳቁስ፣ የገንዘብ እና የስልጠና ድጋፍ 500ሺህ ብር የሚገመት ቁሳቁስ እና ሌሎች ድጋፎች ለማሳባሰብ ታቅዶ 700ሺህ ብር በላይ ቁሳቁስ እና ሌሎች ድጋፎች በማሰባሰብ 100 በመቶ እቅዱን ለማሳካት ተችላል።
በበጀት ዓመቱ ውስጥ በብልሹ አሰራር ዙሪያ የመጡ ጥቆማዎችን ለማስተካከል በታቀደው መሰረት የመጡ ጥቆማዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥና ቦታቸው ድረስ በመሄድና መረጃዎችን በማሰባሰብና በማጣራት ትክክለኛ ውሳኔ እንዲተላለፍና የማስተካከያ ሥራ ሙሉ በሙሉ ተከናውኗል።እንዲሁም በበጀት ዓመቱ ጎጂ ባህላዊ ልምድ በ10 በመቶ ለመቀነስ በታቀደው መሰረት ቢሮው ከሴቶች፣ህፃነት እና ወጣቶች እና ሌሎች ሴክተር መስራቤቶች ጋር በጋራ በመሆን በክልሉ አሉታዊ መጤ ልማዳዊ ድርጊቶች እና አደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚዎችን ቁጥር ለመቀነስ አላማ ያደረገ ስራ መሠራቱን ገልፀዋል።
በሰመሃር አለባቸዉ

❤16👍5🔥3