በአወዛጋቢዉ ፍልስጥኤማዉያንን ከጋዛ ሰርጥ የማስወጣት እቅድ ላይ ትራምፕ እና ኔታንያሁ ተወያዩ
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን በዋይት ሀውስ አግኝተው ሲነጋገሩ እንደተገለጸዉ ሁለቱ መሪዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ሰርጥ በግዳጅ ለማዘዋወር ያቀረቡትን አወዛጋቢ ሃሳብ ደግመዉ አንስተዋል።
ትራምፕ እና ኔታንያሁ ለእራት በዋይት ሀውስ ሰማያዊ ክፍል ውስጥ ሰኞ ዕለት ሲገናኙ በኳታር በእስራኤል እና በሃማስ መካከል በተካሄደው ቀጥተኛ ያልሆነ ውይይት በዩናይትድ ስቴትስ የሚደገፈው የ21 ወራት የጋዛ ጦርነትን ለማስቆም ለ60 ቀናት የተኩስ አቁም ሀሳብ መጠነኛ መነቃቃት የፈጠረ ይመስላል።ኔታንያሁ በስብሰባው ላይ ለተገኙት ጋዜጠኞች እንደተናገሩት ዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል ለፍልስጤማውያን “የተሻለ የወደፊት ሁኔታ” ለመስጠት ከሌሎች አገሮች ጋር እየሰሩ መሆናቸውን በመግለጽ የጋዛ ነዋሪዎች ወደ ጎረቤት ሀገራት ሊሄዱ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።
ኔታንያሁ እንዳሉት "ሰዎች መቆየት ከፈለጉ ሊቆዩ ይችላሉ፤ ግን መልቀቅ ከፈለጉ መውጣት አለባቸው፤እስር ቤት መሆን የለበትም እንዲሁም ለሰዎች ነፃ ምርጫ መስጠት አለበት" ብለዋል፡፡ለፍልስጤማውያን የተሻለ የወደፊት ጊዜ ለመስጠት የሚፈልጉትን ሁል ጊዜ የሚናገሩትን እውን ለማድረግ የሚሹ አገሮችን ለማግኘት ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በቅርበት እየሰራን ነው። በርካታ ሀገራትን ለማግኘት እየተቃረብን ይመስለኛል ሲሉ ተደምጠዋል።
በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ፍልስጤማውያንን ወደ ሌላ ቦታ የማዛወር እና "የመካከለኛው ምስራቅ ወደ መዝናኛ መዳረሻ" ለመቀየር ሀሳባቸውን በማቅረብ ቁጣን የፈጠሩት ትራምፕ በጉዳዩ ላይ "ከአካባቢው ሀገራት" ታላቅ ትብብር ተደርጓል ብለዋል ።በስብሰባው ወቅት ትራምፕ የኢራን ባለስልጣናት ስለ ኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ለመነጋገር ቀጠሮ ለመያዝ ወደ አሜሪካ መግባታቸውን ጠቁመዋል። ድርድር የጀመረው በሚያዝያ ወር ሲሆን ነገር ግን እስራኤል ባለፈው ወር ጥቃት ከከፈተች በኋላ መቋረጡ ይታወሳል፡፡
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል

🤬40❤19👎13👍1
ዳጉ ጆርናልን ብዙዎቻችሁ እንደምትከታተሉት ትነግሩናላችሁ ፤ ጥሩ የመረጃ ምንጭ ነው ያላችሁንም በርካቶች ናችሁ እናመሰግናለን ። ታዲያ 50 ሺ መግባት የለብንም? ለወዳጅ ፣ጓደኞቻችሁ እና ቤተሰብ ሼር በማድረግ ይቀላቀሉን ሀሳቡ ከተመቻችሁ በዚህ ❤️ ግለፁልን
#ዳጉ_ጆርናል
#ዳጉ_ጆርናል
❤209👍33🔥6🤣5👎1
ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በጋዛ እና ዌስት ባንክ ከ18 ሺ በላይ ተማሪዎች ተገድለዋል ተባለ
የፍልስጤም የትምህርት ሚኒስቴር እስራኤል በጥቅምት 2023 ጦርነት ከጀመረች በኋላ በጋዛ እና በዌስት ባንክ ቢያንስ 18,243 ተማሪዎች እና ሰራተኞች መምህራንን ጨምሮ ሲገደሉ 31,643 ቆስለዋል ብሏል።
እንደ ሚኒስቴሩ ዘገባ ከሆነ በጋዛ ከ17,175 በላይ ተማሪዎች ሲገደሉ 26,264 ቆስለዋል፡፡ በዌስት ባንክ 140 ተማሪዎች ሲገደሉ 927 ቆስለዋል።መምህራን እና ከአስተዳደር ሰራተኞች መካከል በጋዛ እና በዌስት ባንክ 928 ሰዎች ሲገደሉ 4,452 ቆስለዋል።በዚህ ጊዜ ውስጥ በዌስት ባንክ 768 ተማሪዎች እንዲሁም 199 መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡
በጋዛ ቢያንስ 252 የህዝብ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ 118 ያህሉ ደግሞ ወድመዋል።በዌስት ባንክ 152 ትምህርት ቤቶች፣ ስምንት ዩኒቨርስቲዎች እና ኮሌጆች ወረራ እና ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በጄኒን፣ ቱልካረም፣ ሰልፊት እና ቱባስ በሚገኙ በርካታ ትምህርት ቤቶች ወድመዋል፡፡
በሌላ በኩል የእስራኤል ወታደራዊ ኃይል ከማክሰኞ ጠዋት ጀምሮ በጋዛ ደቡባዊ አካባቢዎች በፈጸመዉ ጥቃት ቢያንስ ባለፉት 41 ሰዎች ተገድለዋል።በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ አልዛዋይዳ ከተማ የተፈናቀሉ ንፁሀን ዜጎች ባሉበት ድንኳን ላይ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት አንድ ሰው መሞቱን እና ሌሎች መቁሰላቸውን የአል አቅሳ ሆስፒታል የህክምና ምንጮች ለአልጀዚራ አረብኛ ተናግረዋል።
ከዚህም በላይ የሆስፒታሉ ምንጮች እንደተናገሩት ከእስር የተፈቱ ስድስት እስረኞች በማእከላዊ እና ደቡብ ጋዛ ሰርጥ በደረሰው ጥቃት ተገድለዋል ብለዋል።

😭70❤14💔5🤬3😢1
ትራምፕ ዩክሬን ተጨማሪ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንደምታገኝ ተናገሩ
ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ዋሽንግተን ወደ ኪየቭ የሚላኩ ወሳኝ የጦር መሣሪያዎችን እንደምታቆም ካሳወቀች በኋላ አሜሪካ ተጨማሪ የጦር መሳሪያዎችን እንደምትልክ ተናግረዋል ።ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር ባደረጉት ውይይት ትራምፕ ከሩሲያው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ባላቸዉ ግንኙነት ደስተኛ እንዳልሆኑ እና ዩክሬን "በጣም እየተጎዳች ነው" ብለዋል።
ትራምፕ የዩክሬንን ጦርነት ለማገዝ በዋነኛነት "መከላከያ መሳሪያዎችን" እንደምትልክ ጠቁመዋል።ባለፈው ሳምንት ለአፍታ መቆሙ ከተገለጸው ትጥቅ መካከል የአየር መከላከያ ሚሳኤሎች እና የመድፍ ዛጎሎች ይገኙበታል። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የዩናይትድ ስቴትስ የአየር መከላከያ ስርዓቶች “እውነተኛ የህይወት ጠባቂዎች” በማለት በመግለጽ ድጋፉ እንዲቀጥል ተማጽነዋል።
ዋይት ሀውስ ባለፈው ሳምንት ውሳኔው "የአሜሪካን ጥቅም ለማስቀደም" መደረጉን በመግለጽ በመከላከያ ዲፓርትመንት ለሌሎች ሀገራት ባደረገው ወታደራዊ ድጋፍ ግምገማ ምላሽ መስጠቱን አስታዉቆ ነበር፡፡የትራምፕ የዉሳኔ ለውጥ የመጣው ለቀናት ገዳይ የሆነ የሩስያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና የሚሳኤል ጥቃት ዋና ከተማዋን ኪየቭን ጨምሮ በዩክሬን ከተሞች ላይ ጥፋት ካደረሰ በኃላ ነዉ።

❤23👎17👍1
የሱዳን መንግስት ኃይሎች ሁለት ጋዜጠኞችን በኤል ፋሽር በቁጥጥር ስር አዋሉ
በሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት አባል የሚመራ የታጠቀ ቡድን በከተማዋ በፕሬስ ላይ እየወሰደ ባለው እርምጃ በሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ ኤል ፋሸር ሁለት ጋዜጠኞችን አስሯል። የሱዳን ነፃ አውጪ ንቅናቄ የሽግግር ምክር ቤት ወታደራዊ መረጃ ክፍል ጋዜጠኞች መሃመድ አህመድ እና ናስር ያዕቆብ ሰኞ ከሰአት በኋላ በአቡ ሹክ የተፈናቃይ ካምፕ ውስጥ ማሰራቸውን የአካባቢው ምንጮች ለሱዳን ትሪቡን ገልጸዋል።
በሉዓላዊው ምክር ቤት አባል ሳላህ ራስስ የሚመራው ቡድኑ ከሱዳን ጦር ኃይሎች ጋር በመተባበር የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ንቅናቄዎች ጥምረት አካል ነው። ሁለቱ ጋዜጠኞች ወደ የጋራ ኃይሉ ማቆያ ማዕከላት መዛወራቸውም ምንጮቹ አክለዋል። እስሩ ኤስኤፍኤ እና አጋሮቹ ከአንድ አመት በላይ ከፓራሚሊተሪ ፈጣን ድጋፍ ሰጭ ሃይሎች (RSF) ጋር ሲዋጉ በነበሩበት በኤል ፋሸር ውስጥ በጋዜጠኞች ላይ ያለውን ከባድ ችግር አጉልቶ ያሳያል። የጋራ ሃይሉ እና የሰራዊቱ መረጃ በነጻነት የመሰብሰብ አቅማቸውን እየገደበ ነው በማለት በርካታ ጋዜጠኞች ከተማዋን ለቀው ተሰደዋል።
እስሩ የተከሰተው አንድ የኤስኤልኤም-ቲሲ ኦፊሰር በሚሰራበት የስታርሊንክ የኢንተርኔት ማእከል በያዕቆብ ላይ ተኩስ ከፍቷል ከተባለ ከአንድ ቀን በኋላ ነው። ክስተቱ የተከሰተው ያዕቆብ አገልግሎቱን ለመዝጋት እና መሳሪያዎቹን ያለ ይፋዊ ትዕዛዝ ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው ተብሏል።
የኤስኤልኤም-ቲሲ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ለሱዳን ትሪቡን በሰጠው መግለጫ ያዕቆብ መኮንን ላይ ጥቃት ፈጽሟል እና የሳተላይት ኢንተርኔት አጠቃቀምን የሚቆጣጠሩ የደህንነት መመሪያዎችን ጥሷል ሲል ከሰዋል።መግለጫው ያዕቆብ በመኮንኑ ላይ “ከባድ ስድብ” እንደፈጸመ የተገለፀ ሲሆን በጋዜጠኛው ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።
በሚሊዮን ሙሴ

❤13
በህገወጥ መልኩ ከኢትዮጵያ የሚወጣው የዝሆን ጥርስ በስፋት ወደ ኤዥያ ሀገራት እንደሚዘዋወር ተገለፀ
ህገወጥ የእንስሳት አደንና ዝውውር በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ሀብት ላይ ከተደቀኑ ችግሮች መካከል ተጠቃሽ መሆኑን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።
በባለስልጣኑ የዱር እንስሳት ህገወጥ ዝውውር ቁጥጥር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳንኤል ጳውሎስ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ለህገወጥ አደን ተጋላጭ ከሆኑት እንስሳት ውስጥ ዝሆን አንዱ ነው።
በዝሆን ላይ ከተደቀኑት ችግሮች መካከል ጥርሱን ለጌጣጌጥ መስሪያነት በመፈለግ የሚደረግ ህገወጥ አደን መሆኑን ተናግረዋል። ከኢትዮጵያ በዚህ መልኩ የሚዘዋወረው የዝሆን ጥርስ በአብዛኛው ወደ ኤዥያ ሀገራት እንደሚዘዋወር አቶ ዳንኤል ገልፀው እነዚህ ሀገራት ከዝሆን ጥርስ ለተሰራ ጌጣጌጥ ከፍተኛ ክብር ስላላቸው በብዛት ወደ እነዚህ ሀገራት ይዘዋወራል ብለዋል።
ከዝሆን የተሰሩ ጌጣጌጦች ተወዳጅነታቸው በእነዚህ ሀገራት ዘንድ ከፍተኛ ቢሆንም በይበልጥ ወደ ቻይና እንደሚዘዋወር ነው የተነገረው።ይህ ችግር ድንበር ዘለል እንደመሆኑ ድንበር ዘለል ትብብር ያስፈልጋል ያሉት አቶ ዳንኤል የዝሆን ጥርስን ጨምሮ በህገወጥ መልኩ ከሀገር የሚወጡትን እንስሳት ለመታደግ በብሄራዊ ፓርኮች ዙሪያ የሚደረጉ የቁጥጥር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
ቅድስት ደጀኔ

❤18🤔3
የዱቄት ዋጋ እንዲቀንስ የተኩስ አቁም እና እርቅ እየጠበቅን ነው ሲሉ በጋዛ ያሉ ፍልስጤማውያን ተናገሩ
በጋዛ ሰርጥ የሚኖሩ ፍልስጤማውያን ደም መፋሰስ እንዲያበቃ ያላቸውን ተስፋ እና በሲቪል ህይወት ላይ የሚደርሰው ስልታዊ ውድመት መቆም አለበት ሲሉ ለአልጀዚራ ተናግረዋል። ከቤቴ ሀኖን የተፈናቀለው ፍልስጤማዊ ካሊድ ሻባት "መንገድ ላይ ተኝተናል። የተኩስ አቁም እና የእርቅ ሂደቱ በተቻለ ፍጥነት እንዲፈፀም እንፈልጋለን፣ ወደ ፍርስራሽ ቤታችን መመለስም ቢሆንም እሱ ይሻለናል" ብሏል። አክሎም የዱቄት ዋጋ እንዲቀንስ የተኩስ አቁም እና እርቅ እየጠበቅን ነው።
አቡዳላህ አል ሻዋ የተሰኘው ሌላኛው ግለሰብ ደግሞ ሰዎች ደክመዋል እና በቃላት ተስፋ ጠግበዋል ያለ ሲሆን ተጨባጭ እርምጃዎችን ማየት እንፈልጋለን። በየቀኑ ሞት አለ፣ ረሃብ በሁሉም ቦታ አለ፣ ጤናማ ያልሆነ ምግብ እየተመገብን ነው እሱም በአብዛኛው አይገኝም። የተበከለ ውሃ እየጠጣን ነው። ቤታችንን እና ህይወታችንን አጥተናል" ብሏል።
ሌላኛው ተፈናቃይ ሳማር ኖፋል በበኩሉ ሰዎች የተኩስ ማቆም እና ወደ ሰፈራቸው መመለስ እንዲችሉ ይፈልጋሉ ብሏል። "ፍርስራሾች ቢሆኑም ወደ ቤታችን መመለስ እንፈልጋለን" "እርዳታ እና ምግብ ይግባ። ደክሞናል ይህ የህይወታችን አንድ ወይም ሁለት ቀን አይደለም፤ ሁለት አመት ለሚጠጋ ጊዜ አረመኔያዊ ጦርነት ውስጥ ነን አለም የሚረዳን መች ነው?" ሲል ተደምጧል።

😢46💔17❤12✍2
የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር የሰረቁ አራት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ
ንብረትነቱ የኢትዮጵያ መብራት ሃይል አገልግሎት የሆነውን ትራንስፎርመር ነቅለው የወሰዱ አራት ግለሰቦች በእስራት እና በገንዘብ መቀጣታቸውን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታውቋል።
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮምኒኬሽን ሀላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ትግሉ ለገሰ እንደገለፁት አንደኛ ተከሳሽ ዋቁማ ደራ ፣ሁለተኛ ተከሳሽ ሽመልስ ተስፋዬ፣ ሶስተኛ ተከሳሽ አያና ረጋሳ፣ አራተኛ ተከሳሽ ተሾመ አሽኔ የተባሉ ግለሰቦች የኢትዮጵያ መብራት ሀይል አገልግሎት ንብረት የሆነውን ትራንስፎርመር ነቅለው በመውሰድ እና በመፈታታት በማዳበሪያ ውስጥ አድርገው ሲያጓጉዙ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
አራቱ ግለሰቦች ታህሳስ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 1ሰዐት ላይ ለሰደን ሶዶ ወረዳ ኤቢሳ ቀበሌ የኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎት የሚሰጥን ትራንስፎርመር ነቅለው በመውሰድ ፈታተው በሶስት ማዳበሪያ በማድረግ በጋሪ ፈረስ ጭነው ወሊሶ ማዞሪያ የተባለው ስፍራ ሲደርሱ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ1 A15527ኦሮ ጭነው ወደ ቱሉ ቦሎ ከተማ ይዘው ሲጓዙ በቾ ወረዳ ከታ ቀበሌ ልዩ ስፍራው ኮኜ የተባለ ቦታ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል። የኤሌክትሪክ አገልገሎት የሚሰጠው ትራንስፎርመር 1 ሚሊየን 445 ሺህ 590 ብር እንደሚያወጣ ከደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዲስትሪክት ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል።
ፖሊስ አራቱ ግለሰቦች ላይ በተገኘው የሶስት ማዳበሪያ የተፈታታ ትራንስፎርመር እቃ ማስረጃ በማድረግ የምርመራ መዝገቡን አጠናክሮ ለአቃቤ ህግ ልኳል። አቃቤህግም ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በወንጀል ህግ ቁጥር 683 እና የቴሌኮምኒኬሽን እና የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶችን ለማስጠበቅ የወጣውን አዋጅ 4641/1997 ንዑስ አንቀፅ 4 በመተላለፍ የኤሌክትሪክ እና የቴሌኮምኒኬሽን አገልግሎት መሠረተ ልማት ላይ የተፈፀመ የስርቆት ወንጀል በመጥቀስ ክስ መስርቷል።
በአቃቤ ህግ የተመሠረተውን ክስ የተመለከተው የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሰኔ 17/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት አንደኛ ተከሳሽ ዋቁማ ደራ በስድስት አመት ከስድስት ወር እና በ2ሺህ ብር መቀጮ ሁለተኛ ተከሳሽ ሽመልስ ተስፋዬ ሶስተኛ ተከሳሽ አያና ረጋሳ አራተኛ ተከሳሽ ተሾመ አሽኔ የተባሉት እያንዳንዳቸው በስድስት አመት እስራት እና በ2ሺህ ብር መቀጮ እንዲቀጡ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ማስተላለፉን ምክትል ኢንስፔክተር ትግሉ ለገሰ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በሰመሀር አለባቸው

❤19
የሮም ስምምነት ፈራሚ ሀገራት ኔታንያሁ በአየር ክልላቸው እንዲያልፉ ለምን እንደፈቀዱ ማብራራት አለባቸዉ ተባለ
በተያዙት የፍልስጤም ግዛቶች የተባበሩት መንግስታት ልዩ ራፖርተር የሆኑት ፍራንቼስካ አልባኔዝ የጣሊያን፣ የፈረንሳይ እና የግሪክ መንግስታት በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሚፈለጉትን ቤንያሚን ኔታንያሁ "ለምን የአየር ክልላቸው እንዲጠቀሙ እንደፈቀዱና አስተማማኝ መንገድ ለኔታንያሁ ለምን እንዳቀረቡ ማስረዳት አለባቸው" ብለዋል።
"የጣሊያን፣ የፈረንሳይ እና የግሪክ ዜጎች እያንዳንዱን ዓለም አቀፍ የህግ ሥርዓት የሚጥስ የፖለቲካ እርምጃ አደጋ ላይ እንደሚጥላቸው ማወቅ ይገባቸዋል" ሲል አልባኒዝ በኤክስ ላይ በለጠፉት ጽሑፍ ተናግረዋል። ሁሉም የሮም ስምምነት አካል የሆኑት አገሮች የእስራኤልን ጠቅላይ ሚኒስትር “የማሰር ግዴታ አለባቸው” ሲሉ አክለዋል።
በአሁኑ ጊዜ ኔታንያሁ እያስተናገደች ያለችው ዩናይትድ ስቴትስ የሕጉ አካል አይደለችም። በተቃራኒው የትራምፕ አስተዳደር እስራኤልን ጨምሮ በአሜሪካ እና በተባባሪዎቿ ላይ “ህጋዊ እና መሠረተ ቢስ እርምጃዎችን” ወስደዋል በማለት አራት የአለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ዳኞች ላይ በቅርቡ ማዕቀብ ጥሏል።
የሮም ስምምነት 124 ሀገራት የፈረሙበትና አለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት የተቋቋመበት ስምምነት ሲሆን የዚህ ስምምነት ፈራሚ ሀገራት በፍርድ ቤቱ የሚፈለጉ ሰዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ግዴታ አለባቸው።

❤39👍6😁4🤬1
በመቀለ ከተማ ተዘርቶ የተገኘ ማሪዋና የተሰኘ አደንዛዥ እፅ ተወገደ
በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ ሰሜን ክፍለ ከተማ ላይ ተዘርቶ የተገኘ ማሪዋና የተሰኘ የአደንዛዥ እፅ ከህብረተሰብ በተገኘ ጥቆማ መወገዱን የክፍለ ከተማው ፖሊስ አስታውቋል።
በጉዳዩ ላይ ተጠርጣሪ የሆነችው እንስት የክፍለ ከተማው ነዋሪ ስትሆን ይጠቅምሻል ትከይው እኛ ራሳችን እንወስድልሻለን ካሏት ሰዎች ተቀብላ እንደዘራችው መናገሯን የሰሜን ክፍለ ከተማ ፖሊስ የወንጀል መከላከል ፅህፈት ቤት ሓላፊው ምክትል ኢንስፔክተር ፍስሃ ፀጋይ ገልፀዋል።
ሓላፊው አክለው መረጃውን ለፖሊስ የሰጡ ሰዎችን ያመሰገኑ ሲሆን በቀጣይም በህብረተሰብ ላይ አደጋ የሚያስከትሉ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከቱ ለፖሊስ በመጠቆም አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ መጠየቃቸውን ብስራት ከ መቀለ ከተማ ፖሊስ ያገኘው መረጃ የሳያል።
በሰብል አበበ

❤20👍5😁5🕊2😭2🤔1
በኬንያ በፀረ-መንግስት ተቃውሞ የሟቾች ቁጥር 31 ደረሰ
በኬንያ በተደረጉ ፀረ-መንግስት ተቃውሞዎች የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 31 ከፍ ማለቱን የተሰማ ሲሆን በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ ሰልፎቹ ከተጀመሩ ወዲህ በአንድ ቀን ከፍተኛው ቁጥር መሆኑን የኬንያ ብሄራዊ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን አስታውቋል። የብሄራዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋም የሆነው ኮሚሽኑ የፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶን የስራ መልቀቂያ ጥያቄ፣ የፖሊስ ጭካኔ ያለው የኃይል እርምጃ ተቃውሞ እና አፋጣኝ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ለመጠየቅ በተደረጉት ሀገራዊ ተቃውሞዎችን "አሁንም በንቃት እየተከታተልን ነው" ብሏል።
በቅርቡ ኮሚሽኑ ባወጣው መረጃ 107 የአካል ጉዳት መድረሱን ፣ 532 ሰዎች መታሰራቸውን እና 2 ሰዎች በግዳጅ መሰወራቸውን እንዲሁም በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንም ገልጿል። ኮሚሽኑ ሁሉንም የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አጥብቆ ያወግዛል እናም ከፖሊስ፣ ሲቪሎች እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ይጠይቃል ሲሉ ምክትል ሊቀመንበሩ ሬይመንድ ኒሪስ ተናግረዋል። ለተጎጂዎች ቤተሰቦችም መጽናናትን በመመኘት ለተጎዱት አፋጣኝ የህክምና እርዳታ እንዲደረግ ጠይቀዋል።
በኬንያ ታሪካዊው የ1990 የሳባ ሳባ ህዝባዊ አመጽ መታሰቢያ በዓል ላይ የተደራጁት ተቃውሞዎች በናይሮቢ፣ ኪሱሙ፣ ሞምባሳ፣ ኤልዶሬት እና ናኩሩ ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ተስፋፍቷል። በአንዳንድ ክልሎች ሰልፉ ሰላማዊ የነበረ ቢሆንም፣ ሌሎች ደግሞ በፖሊስ እና በተቃዋሚዎች መካከል ግጭት ሲፈጠር የዓይን እማኞች መመልከታቸውን በመግለፅ የቀጥታ ጥይቶች ጥቅም ላይ እንደዋሉ እንዲሁም ፖሊስ ከመጠን በላይ ኃይል በመጠቀም የዘፈቀደ እስር መፈፀሙ ታውቋል።

❤18😢9😱1
30 የአራራይ ታክሲ ዘርፍ ማህበር አባላት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ተረከቡ
ሄኖሲስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ከኢትዮ ኢቪ ሞተርስ ጋር በመተባበር 30 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለአራራይ የታክሲ ዘርፍ ማህበር አባላት በዛሬዉ ዕለት አስረክቧል ።
ተሽከርካሪዉን ለመረከብ ከዚህ ቀደም ለሌላ ድርጅት ገንዘብ ከፍለዉ አምስት ዓመታትን መጠባበቃቸዉን የተናገሩት አባላቱ አሁን ከሄኖሲስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ማህበር ጋር ባደረግነዉ ቁጠባ ወር ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ ተሽከርካሪዎቹን ለመረከብ ችለናል ብለዋል ።
አራራይ የታክሲ ዘርፍ ማህበር ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን ለአባላቱ ገዝቶ ለማስረከብ ሲሰራ መቆየቱን የተናገሩት የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ወንድይፍራዉ ግርማ በቀጣይም የተቀሩት የማህበሩ አባላት ተሽከርካሪዎችን በፍጥነት የሚረከቡበትን ዕድል ለመፍጠር እንሰራለን ማለታቸዉን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል ።
አራራይ የታክሲ ዘርፍ ማህበር በስሩ ከ20 በላይ አባል ማህበራትና ከ700 በላይ አባላቶች ያሉት ሲሆን ሄኖሲስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር በቀጣይ ለእነዚህ አባላት ተሽከርካሪዎቹን ማስረከብ እንደሚቀጥል አስታውቋል ።
በመባ ወርቅነህ

❤22🤔1