Telegram Web Link
ቻይና የኢትዮጲያ አኩሪ ዓተር ወደ ሀገሯ እንዲገባ ፈቀደች

የቻይና መንግስት ከዋሽንግተን ጋር የገባውን የንግድ ጦርነት ተከትሎ ከኢትዮጲያ የሚመጡ የአኩሪ አተር ምርቶች እንዲገቡ የፈቀደ ስለመሆኑ ሮይተርስ ያስነበበ ሲሆን ነገር ግን ቻይና ከወጭ የሚገቡ ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኝነች ለመቀነስ እየጣረች ያለችበት ወቅት ነውና ከፍተኛ መጠን ያለው የአኩሪ አተር ምርት ከኢትዮጲያ ወደ ቻይና ይላካል ተብሎ አይጠበቅም።

ፍቃዱ ከጁላይ 3 ጀምሮ ተፈፃሚነቱ ጀምሯል የተባለ ሲሆን የቻይናን የጥራት ደረጃና ከተባይ ነፃ የሆኑ ምርቶች በቀጥታ ወደ ቻይና እንዲገቡ ይፈቀዳል ተብሏል። በቻይና መቀመጫውን ያደረገው የሻንግሀይ የአግሮ ኮንሰልታሲ ድርጅት ባለሞያ ሮዛ ዋንግ እንደሚሉት ከሆነም ይህ እርምጃ የቻይናን የአቅርቦት ምንጭ ለማስፋት ስትራቴጂ አካል ነው ተብሏል።

የቻይና መንግስት ከኢትዮጲያ የሚመጡ የአኩሪ አተር ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ በፈቀደበት በአሁኑ ወቅት ከ2019 በኃላ ለመጀመርያ ጊዜ አኩሪ አተር የጫነች መርከብ ከአርጀንቲና ቻይና መግባቷ ተዘግቧል። ይህም ቻይና ከአሜሪካ ባሻገር ተጨማሪ የንግድ አጋሮች እያፈራችና አማራጯን እያሰፋች መሆኑን ያሳያል ተብሎለታል።

ምንም እንኳ ቻይና በዋናነት አኩሪ አተር ከብራዚልና አሜሪካ እንደምታስገባ መረጃዎች ያሳያሉ። በአሁኑ ሰዓት ግን ቻይና ከኢትዮጲያ በተጨማሪ ከጁን ወር ጀምሮ ከኡራጋይም እንዲገቡ የፈቀደች ሲሆን በአጠቃላይን አርጀንቲና፣ ብራዚል፣ ሩስያ፣ ቤላሩስ፣ ኡራጋይና ኢትዮጲያ አኩሪ አተር ወደ ቻይና የመላክ ፍቃድ ያላቸው ሀገራት ሆነዋል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
32👎9👍1👏1
አል-ሺፋ ሆስፒታል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኤሌክትሪክ መቋረጥ ምክንያት አደጋ ላይ መሆናቸውን አስጠነቀቀ

በጋዛ የእስራኤል የምድር እና የአየር ጥቃት ፍጥነት እና ጥንካሬ ያለ ምንም እረፍት በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት በጋዛ ከተማ የሚገኘውን የአል-ሺፋ የህክምና ተቋምን ጨምሮ በጋዛ ዙሪያ ያሉ ሆስፒታሎች ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በከባድ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ህሙማንን እየተቀበሉና እየሰሩ ይገኛሉ ተብሏል።

የአል-ሺፋ ሆስፒታል ዳይሬክተር መሀመድ አቡ ሳልሚያ ተቋሙ ለኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫዎች ነዳጅ ባለመኖሩ የመብራት መቆራረጥ እያጋጠመው በመሆኑ በከባድ ፈተና ውሰጥ መውደቃቸውን ይናገራሉ።

በአይሲዩዎች፣ በቀዶ ሕክምና ክፍሎች እና በኩላሊት እጥበት ክፍሎች ውስጥ ያሉ የህይወት አድን መሳሪያዎች ሲቆሙ ሊፈጠር የሚችለው ነገር አስከፊ መሆኑም ገልፀዋል።

ዶ/ር አቡ ሳልሚያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ህይወቶች በአሁኑ ሰዓት የሞት ጫፍ ላይ እንደሚገኙም አስጠንቅቀዋል። በተመሳሳይ በደቡብ ጋዛ ትልቁ የህክምና ተቋም በሆነው በናስር ሆስፒታል የቀረው ነዳጅ ለቀጣዮቹ 24 ሰዓታት ብቻ እንደሚቆይ የህክምና ቡድኖቹ ተናግረዋል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
💔52😢2112🕊1
ትራምፕ ፑቲንን ከተቹ በኋላ ዩክሬን ከፍተኛ ጥቃት ደረሰባት

ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እንዳሉት ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ጦርነት ከገባችበት ጊዜ አንስቶ ትልቁ የአየር ላይ ጥቃት እንደተፈፀመባት አስታውቀዋል። በአምድ ሌሊት 728 ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና 13 የክሩዝ ወይም ባለስቲክ ሚሳኤሎች የሀገሪቱን ከተሞች እንደመቱም ገልፀዋል። ዘሌንስኪ አስፈሪ ያሉትን ጥቃቱን አውግዘዋል። ይህ ሰላም ለማምጣት፣ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚደረጉ ጥረቶች በቀጠሉበት በዚህ ወቅት ጥቃቱ መፈፀሙ ሩሲያ ሁሉንም የሰላም አማራጮች እንደምትቃወም ያሳያል ብለዋል።

ይህ የሩሲያ ጥቃት የተፈፀመው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ተጨማሪ የጦር መሳሪያ ወደ ኪየቭ እንደምትልክ ከተናገሩ በኋላ ነው ። ይህ ውሳኔ የአሜሪካ ሚዲያዎች ትራምፕ ያለፈው ሳምንት ወደ ዩክሬን የጦር መሳሪያ እንደማይልኩ የጣሉትን እገዳ እንደለውጡ ያሳያል ብለዋል። የአሜሪካው መሪ በሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ ብስጭታቸው እየጨመረ መምጣቱን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።


ትራምፕ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ፑቲን ሁልጊዜ ለእኛ በጣም ጥሩ ነው ነገር ግን አሁን ትርጉም የለሽ ሆኖ ይታያል ሲሉ ተደምጠዋል። የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ሞስኮ በጣም የተረጋጋች ነች፤ የትራምፕ አነጋገር በአጠቃላይ በጣም ከባድ ነው፣ የሚጠቀሟቸው ቃላቶች ሲሉ ተደምጠዋል። ሁለቱ መሪዎች መደበኛ ግንኙነት ሲያደርጉ ቆይተዋል ነገርግን ይህ በዩክሬን የተኩስ አቁም ስምምነትን በተመለከተ በተጨባጭ ርምጃዎች ሊተረጎም አልቻለም ። ትራምፕ በአንድ ወቅት የዩክሬን ሩሲያም የተኩስ አቁም ስምምነት በአንድ ቀን ውስጥ ማሳካት እንደሚችሉ መናገራቸው ይታወሳል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
37😁11👍6👎1
የወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማህበር ከ50 በላይ ወጣቶችን ለክረምት በጎ ፍቃድ ስራ  አሰማራ

በኢትዮጵያ ከተመሰረተ ከ75 አመት በላይ ያስቆጠረው የወጣት ወንዶች ክርስቲያን  ማህበር ወይም ወወክማ ከተመሰረተ ጀምሮ በርካታ ወጣቶችን በበጎ ፍቃድ ሲያሰማራ መቆየቱ ይታወሳል። አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች በበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ለበርካታ አመታት የተለያዩ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱንም የወወክማ ዋና ዳይሬክተር አቶ በፍቃዱ በዛብህ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

በአዕምሮ የጎለበቱ እና በመንፈስ የጠነከሩ ወጣቶችን ለማፍራት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ በማድረግ በአዲስ አበባ  እና በአምስት  ክልሎች በሚገኙ አስር ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ላይየሚገኝ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው።

የኢትዮጵያ ወወክማ ከሚሰራቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አንዱ ሲሆን በየአመቱ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎችን በበጎ ፈቃደኞች  ተፈፃሚ ማድረግ ተጠቃሽ ናቸው።በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ላይ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች በነጻ ትምህርት አግኝተው  በተለያዩ የስራ መስኮች ላይ እንደሚሰማሩ ተገልጿል።

በዚህም በሚጠናቀቀው ዓመት የክረምት ወቅት በነባር እና አዲስ ተመዝጋቢ በጎ ፈቃደኞች አማካኝነት ከትምህርት፣ ከማህበረሰብ ድጋፍ፣ ከፈጠራ፣ ከቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ከሌሎች የድርጅቱ የፕሮጀክት ስራዎች ጋር በተያያዘ ለምናከናውናቸው ተግባራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በላቀ ሁኔታ በመጠቀም ለወጣቶች ብሎም ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሚሆኑ ስራዎችን ለመስራት ዝግጅታችንን አጠናቀናል ሲሉ አቶ በፍቃዱ በዛብህ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
22🤣17😁1
በአውሮጳ በ10 ቀናት ውስጥ ብቻ 2,300 ሰዎች በከባድ ሙቀት የተነሳ ለሞት መዳረጋቸው ተሰማ

ባለፈው ሳምንት የተጠናቀቀው ከባድ የሙቀት ማዕበል በ12 የአውሮፓ ከተሞች 2,300 ሰዎች ከሙቀት ጋር በተያያዙ ምክንያቶች መሞታቸው የተሰማ ሲሆን 2/3ኛው ከተመዘገበው ሞት በቀጥታ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዘ መሆኑን አዲስ ጥናት አመልክቷል። ረቡዕ እለት ይፋ የተደረገው ጥናት እንዳመላከተው  ከጁን 23 እስከ ጁላይ 2 ባለው ጊዜ ውስጥ በነበሩት የ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ያተኮረ ሲሆን በምዕራብ አውሮፓ ትላልቅ ክፍሎች በከፍተኛ ሙቀት የተነሳ በስፔን እስከ 40 ዲግሪ ሴልሺየስ ሲደርስ በፈረንሳይ ደግሞ ሰደድ እሳት ተከስቷል።

ባርሴሎና፣ ማድሪድ፣ ለንደን እና ሚላንን ጨምሮ ከ30 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያሏቸውን 12 ከተሞችን ያካተተው ጥናቱ የአየር ንብረት ለውጥ የሙቀት ሞገድ ጨምሯል ይላል። በዚህ ወቅት ሞተዋል ተብሎ ከተገመተው 2300 ሰዎች መካከል 1500 ያህሉ ለሞት የተዳረጉት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዘ ሲሆን ይህም የሙቀት መጠኑን የከፋ ያደርገዋል ሲል በዩናይትድ ኪንግደም፣ ኔዘርላንድስ፣ ዴንማርክ እና ስዊዘርላንድ ከሚገኙ አምስት የአውሮፓ ተቋማት የተውጣጡ ከደርዘን በላይ ተመራማሪዎች ያካሄዱት ጥናት ያሳያል።

የአየር ንብረት ለውጥ ከነበረው የበለጠ ሞቃታማ እንዲሆን አድርጎታል፣ይህም አደገኛ ያደርገዋል ሲል በጥናቱ ውስጥ ከተሳተፉት ተቋማት መካከል አንዱ የሆኑት የኢምፔሪያል ኮሌጅ የለንደን ተመራማሪ ቤን ክላርክ ተናግረዋል።ተመራማሪዎቹ የሟቾችን ቁጥር ለመገመት የተቋቋሙ ኤፒዲሚዮሎጂያዊ ሞዴሎችን እና ታሪካዊ የሞት መረጃዎችን ተጠቅመዋል፣ ይህም ሙቀት ለሞት ዋና ምክንያት የሆነበትን ምክንያት ብሎም ተጋላጭነት ሲኖር የጤና ሁኔታዎች አባብሶታል ብለዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
16👍4😢3🤔1
ዜና ዕረፍት

በጥቂት ቀናት ህመም በአሜሪካ ሲያትል ከተማ ህይወቱ ያለፈው አንጋፋው ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን፣ የብዙዎችን ልብ በሀዘን ጥሏል።

ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን በተለይ "ሚዲያ ዳሰሳ" በሚለው ፕሮግራሙ በህዝብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅነትን አግኝቶ ነበር።

ለመላው ቤተሰቦቹ፣
ወዳጅ ዘመዶቹ እና
አድናቂዎቹ መፅናናትን እንመኛለን።

#ዳጉ_ጆርናል
💔49😢218😭7
የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ማክሮን እንግሊዝ ለፍልስጥኤም ሀገርነት እውቅና እንድትሰጥ ጠየቁ

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከብሬክሲት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ መሪ ጉብኝት በዩናይትድ ኪንግደም ጉብኝት ባደረጉበት ጉዞ ለፍልስጤም ግዛት እውቅና ለመስጠት እና ዩክሬንን ለመከላከል የብሪታንያ ድጋፍ እንዲጨምር ጥሪ አቅርበዋል ። ማክሮን ለሁለቱም የብሪቲሽ ፓርላማ ምክር ቤቶች ባደረጉት ንግግር በፈረንሳይ እና በእንግሊዝ መካከል የጠበቀ ግንኙነት መኖሩን ያነሱ ሲሆን ሁለቱ ሀገራት በዩናይትድ ስቴትስ እና በቻይና ላይ ያለውን "ከልክ ያለፈ ጥገኝነት" ለማስወገድ በጋራ መስራት አለባቸው ብለዋል ።

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት የሶስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት የተደረገው በንጉስ ቻርልስ ሳልሳዊ ግብዣ ነው። ማክሮን ቀደም ሲል አልጋ ወራሽ ልዑል ዊሊያም እና ባለቤታቸው ልዕልት ካትሪን ጨምሮ ንጉሣዊው ቤተሰብ በፈረስ ሰረገላ ወደ ዊንዘር ቤተመንግስት ሲያቀኑ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ከዚያም ማክሮን ወደ ፓርላማ በማቅናት ሁለቱ ሀገራት አውሮፓን ለማጠናከር በመከላከያ፣በኢሚግሬሽን፣በአየር ንብረት እና በንግድ ጉዳዮች ላይ መሰባሰብ አለባቸው ብለዋል። "ዩናይትድ ኪንግደም እና ፈረንሳይ ህብረታችን ለውጥ እንደሚያመጣ ለአለም እንደገና ማሳየት አለባቸው" ሲሉ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት በእንግሊዘኛ ተናግረዋል።

ያጋጠሙንን የዘመናችን ፈተናዎችን ለማሸነፍ ብቸኛው መንገድ እጅ ለእጅ ተያይዘን፣ ትከሻ ለትከሻ መጓዝ ብቻ ነው ብለዋል።በተጨማሪም ማክሮን በጋዛ ላይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ጠይቀዋክ።የአውሮፓ ሀገራት ከሩሲያ ወራሪ ኃይሎች ጋር በሚያደርጉት ጦርነት “ዩክሬንን ፈጽሞ እንደማይተዉ” ቃል ገብተዋል ። በመቀጠልም ዩናይትድ ኪንግደም ለፍልስጤም መንግስት እውቅና በመስጠት ከፈረንሳይ ጋር በጋራ እንድትሰራ አሳስበዋል፤ ይህ "ብቸኛው የሰላም መንገድ" በማለት ገልፀዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
70👍14
በ2017 በጀት ዓመት ጂንካን ከጎበኙ ቱሪስቶች 65 ሚሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል ተባለ

በበጀት ዓመቱ 12 ወራት ጂንካ ከተማ በ22 ሺህ የዉጭ ሀገር ቱሪስቶች እና በ135 ሺህ 750 የሀገር ዉስጥ ቱሪስቶች መጎብኘታን የከተማዋ ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል ። ከሀገር ዉስጥ እና ከዉጭ ሀገር ቱሪስቶች በአጠቃላይ 65 ሚሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን የጂንካ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ ተረፈ ለጣቢያችን ብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

ቱሪስቶቹ በአማካይ ከ6 ቀን እስከ 1ወር ለሚደረስ ጊዜ በከተማዋ ቆይታ እንደሚያደርጉም ተገልጿል ። በከተማዋ ዉስጥ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን ከመጎብኘት ባለፈ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለመስራት የሚመጡ የዉጭ ሀገር ዜጎች መኖራቸውም ተነግሯል ።

የአሜሪካ ፣የቻይና ፣የሱዳን ፣የኮሪያ ፣የአዉሮጳ እና የላቲን አሜሪካ ዜጎች በበጀት ዓመቱ ጉብኝት ካደረጉ የዉጭ ሀገራት ቱሪስቶች ቀዳሚዉን ስፍራ ይይዛሉ ተብሏል ። በሶሪያ በነበረዉ ጦርነት ምክንያት ወደ ጂንካ ከተማ በመግባት ከ3ወር በላይ የሚሆን ጊዜን በከተማዋ ዉስጥ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን እየተጠቀሙ በመቆየት ሀገራቸው ሲረጋጋ ተመልሰዉ የሄዱ የሶሪያ ዜጎች መኖራቸውን አቶ መሀመድ ተረፈ ጨምረዉ ለብስራት ተናግረዋል ።

በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
11
የእስራኤል ጦር በጋዛ ከ100 በላይ ኢላማዎችን መምታቱን አስታወቀ

እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርገውን ጥቃት በቀጠለችበት በዚህ ወቅት በሲቪል መሰረተ ልማቶች ውስጥ ተደብቀው የሚገኙ ፈንጂዎችን እና ታጣቂዎችን አጠፋለሁ በማለት የሐማስን ኢላማዎች እንዳወደመ ወታደራዊ ኃይሏ ተናግሯል።

በመግለጫው የእስራኤል ጦር በቅርብ ቀናት ውስጥ በጋዛ ከተማ ሹጃዬያ እና ዘይቱውን ሰፈሮች ውስጥ ተዋጊዎችን በማጥፋት ፣የወታደራዊ መዋቅሮችን በማፍረስ እና የሃማስ የጦር መሳሪያዎችን መምታቱን ተናግሯል።

በደቡባዊ ጋዛ፣ የእስራኤል ወታደሮች በራፋህ ከተማ አል-ጃናና አካባቢ ሌላ ቡዱን አስወግደው የትግል መሰረተ ልማቶችን አፍርሰዋልም ተብሏል።

የህክምና ምንጮች ለአልጀዚራ አረብኛ እንደገለፁት እስራኤል በጋዛ ከተማ እሮብ ከረፋድ ጀምሮ በከፈተችው ጥቃት ቢያንስ 18 ፍልስጤማውያን ተገድለዋል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
👎5716👏9💔4
እስራኤል በጋዛ ሰርጥ በፈፀመችው ጥቃት ባለፉት 24  ሰዓታት 105 ፍልስጥኤማውያን ተገደሉ

የጋዛ ጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በጋዛ ዙሪያ የእስራኤል ወታደራዊ ኃይሎች በወሰዱት ጥቃት ቢያንስ 105 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ 530 ሰዎች ቆስለዋል። ከሟቾቹ መካከል 7 ረድኤት ፈላጊዎች ንፁሃን ሲሆኑ ከ57 በላይ ቆስለዋል ሲል ሚኒስቴሩ በቴሌግራም ላይ ያሰራጩው መግለጫ አስታውቋል።

እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 7 ቀን 2023 ጀምሮ እስራኤል በጋዛ ላይ ባካሄደችው ጦርነት 57,680 ሰዎች ሲገደሉ 137 ሺ 409 ሰዎች ቆስለዋል ሲል ሚኒስቴሩ ገልጿል። በግንቦት 27 በአሜሪካ እና በእስራኤል የሚደገፈው የዕርዳታ ዘዴ ከተጀመረ በኋላ የተገደሉት የእርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር 773 የደረሰ ሲሆን ከ5,101 በላይ ፍልስጤማውያን እርዳታ በመጠባበቅ ላይ በጥቃት ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
💔58😭198👍3🤔1
ወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ሆስፒታል በአስር ዓመት ውስጥ ከ1.4 ሚሊየን በላይ ተገልጋዮችን አስተናግጃለሁኝ አለ

👉 ተቋሙ የመድኃኒት አቅርቦት ችግር በዋጋ ንረትና ተያያዥ ጉዳዮች መፈጠሩን እና ለማስተካካል እየሰራ ነው

የወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል  ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ካሊድ ሸረፋ ተቋሙ በአስር ዓመታት ያከናወናቸውን ተግባራት እና  የበጀት ዓመቱን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት  ገልጸዋል።

ተቋሙ በአስር ዓመት  ውስጥ  ከ1.4 ሚሊየን በላይ ተገልጋዮችን ማስተናገዱን የተገለጸ ሲሆን  የመድኃኒት እጥረት፣ የጤና መድህን ተገልጋዮች የሪፈር ወረቀት አለመያዝ እና  የመልካም አስተዳደር ችግሮች መኖራቸውን የወራቤ ሆስፒታል ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝ ሆስፒታል የኮሙኒኬሽን ክፍል ኃላፊ የሆኑት አብዱልጀባር አብደላ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተለያዩ ዞኖች እና ከክልሉ ውጪ ሌሎች አካባቢዎች ሪፖርቱ በቀረበበት መድረክ ላይ የተሳተፉ ሲሆን በአገልግሎት አሰጣጡ ደስተኞች መሆናቸውን በመግለጽ መሻሻል አለባቸው ያሏቸውንና ግልጸኝነት የሚፈልጉ ጉዳዮችን ማንሳታቸው ተጠቁሟል ።

የተገልጋዩ የመጸዳጃ ቤት አጠቃቀም ችግር መኖሩን በመጠቆም ፣የመኪና አደጋ በጤና መድህን ለምን አገልግሎት እንደማይሰጥ፣ የመድኃኒት እጥረትን በተመለከተ ሃሳቦች ተነስተዋል።

ዶ/ር ካሊድ በመድረኩ ላይ በሰጡት ምላሽ የመኪና አደጋ የደረሰበት ሰው እስከ 15 ሺህ ብር በመንግስት የሚሸፈን መሆኑን፣ የቆሻሻ አወጋገድንና የመጸዳጃ ቤት አጠቃቀምን ለማሻሻል የግንዛቤ ስራ እየተሰራ መሆኑን፣ ተጨማሪ የመጸዳጃ ቤት ግንባታም በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በተጨማሪም የመድኃኒት አቅርቦት ችግር በዋጋ ንረትና ተያያዥ ጉዳዮች መፈጠሩን ሆኖም ወሳኝ የሚባሉትን ከ80 በመቶ በላይ ማሳካት መቻሉንም በመግለፅ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆንም ለተሻለ አቅርቦት ይሰራል መባሉን የተቋሙ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አብዱልጀባር አብደላ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
👍3818🏆3👏1😁1🙏1
አሜሪካ በዚህ አመት 300 ቢሊዮን ዶላር የታሪፍ ገቢ ልትሰበስብ ትችላለች ተባለ

የአሜሪካ የግምጃ ቤት ፀሐፊ ስኮት ቤሴንት እንደተናገሩት ዩናይትድ ስቴትስ እስካሁን ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የታሪፍ ገቢ አገኝታለች ያሉ ሲሆን ይህ ቁጥር በ 2025 መጨረሻ ላይ ወደ 300 ቢሊዮን ዶላር ሊያድግ ይችላል ሲሉ ተደምጠዋል።

በዋይት ሀውስ የካቢኔ ስብሰባ ላይ ቤሴንት እንደተናገሩት ከሆነም ከዋና ዋናዎቹ የትራምፕ አዳዲስ ታሪፎች ገቢ መሰብሰብ የጀመሩት በሁለተኛው ሩብ አመት ውስጥ ሲሆን፣ ይህም ትራምፕ ሁለንተናዊ የ10 በመቶ ቀረጥ ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ተግባራዊ ባደረጉበት እና በብረት፣ በአሉሚኒየም እና በአውቶሞቢሎች ላይ ያለውን ቀረጥ ከፍ መደረጉን ተከትሎ ነው።

ፀሓፊው አክለው "ይህ ገቢ በዓመቱ መጨረሻ ከ300 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሊሆን ይችላል ብለን መጠበቅ እንችላለን" ብለዋል። የግምጃ ቤት ፀሓፊው ጨምረው እንዳሉት የ300 ቢሊዮን ዶላር ኢላማ በዲሰምበር መጨረሻ ይሳካል ብለው እንደሚጠብቁ ገልፀዋል።

ግምጃ ቤቱ በግንቦት ወር ሪከርድ የሆነ የ22.8 ቢሊዮን ዶላር አጠቃላይ የጉምሩክ ቀረጥ የሰበሰበ ሲሆን ይህም ከአንድ አመት በፊት ከነበረው አጠቃላይ የ6.2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ በአራት እጥፍ ጭማሪ ያለው ሆኖ ተመዝግቧል። ይህ በ2025 የበጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስምንት ወራት የጉምሩክ ቀረጥ ገቢን ወደ 86.1 ቢሊዮን ዶላር አሳድጓል። በ2025 የመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት የተሰበሰቡ ገቢዎችም በድምሩ 63.4 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
15👎9
ሩሲያ በኪየቭ ከተማ ከባድ የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃት ፈፀመች

ሩሲያ በአንድ ሌሊት በፈፀመችው ከባድ ጥቃት በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ቢያንስ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 16 ቆስለዋል ሲሉ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ተናግረዋል። ጥቃቱ በዋናነት በመዲናዋ ላይ ያነጣጠረ ሲሆን 18 ሚሳኤሎች እና ወደ 400 የሚጠጉ ሰው አልባ አውሮፕላኖች የተሳተፉበት መሆኑንም ዘለንስኪ ጨምረው ገልፀዋል። የኪዬቭ ባለስልጣናት እንደተናገሩት የሰው አልባ አውሮፕላን ፍርስራሽ በማዕከላዊ ሼቭቼንኪቭስኪ አውራጃ ውስጥ በሚገኝ የመኖሪያ ሕንፃ ጣሪያ ላይ በመምታቱ በከተማይቱ ዙሪያ የእሳት ቃጠሎዎች ተቀስቅሷል።

ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሚሳኤሎች በመዲናይቱ ላይ ሲያርፉ እና የአየር መከላከያዎች በወሰዱት እርምጃ ፍንዳታ በመቀስቀሱ የነዋሪዎች እንቅልፍ ቢያንስ ለሶስት ሰዓታት ያህል ተስተጓጉሏል። ማክሰኞ ምሽት 728 ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና 13 ክሩዝ ወይም ባለስቲክ ሚሳኤሎች በመላ ሀገሪቱ ከተሞች ላይ ጥቃት ያደረሱ ሲሆን ዩክሬን ትልቁ የሩሲያ የአየር ላይ ጥቃት ስትል መግለጿ ይታወሳል። ሃሙስ ማለዳ ላይ የዩክሬን ፖሊስ የሩስያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በኪየቭ ስምንት ወረዳዎችን መምታቱን አስታውቋል።

የመኖሪያ ሕንፃዎች፣ ተሽከርካሪዎች፣ መጋዘኖች ፣ ቢሮዎች እና መኖሪያ ያልሆኑ ሕንፃዎች ተቃጥለዋል ሲሉ የአስተዳደር ኃላፊ ቲሙር ትካቼንኮ በቴሌግራም ላይ በለጠፉት ጽሁፍ አጋርተዋል። የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ኢጆር ክላይመንኮ የ68 አመት ሴት እና የ22 አመት ፖሊስ በሜትሮ ጣቢያ ውስጥ መገደላቸውን አረጋግጠዋል። በኪየቭ ፖዲልስኪ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ማዕከል “ሙሉ በሙሉ ወድሟል” ሲሉ የከተማዋ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ ተናግረዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
35👍2👎1😁1🕊1
በጉራጌ ዞን የተለያየ የሰውነት ክፍልን በጦር መሳሪያ በመምታት የሰው ህይወት ያጠፋው ግለሰብ በ 18 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ነዋሪ የሆነው ተከሳሽ በለጠ ወርቁ የተባለው ግለሰብ ሰውን ለመግደል አስቀድሞ በማሰብ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ/ም ከምሽቱ በግምት 3፡30 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ የወንጀል ድርጊቱ ተፈፅሟል ::

በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ሚዳ ቀበሌ ሟች ጎረቤት አምሽቶ ወደ ቤቱ ሲገባ መንገድ ላይ ጠብቆ የተለያየ የሰውነት ክፍሉ በጦር መሳሪያ መቶት መንገድ ላይ ወድቆ የመሳሪያ እና የሟች የጩኸት ድምፅ የሰሙ ሰዎች ከቦታው ላይ ደርሰው ወደ ህክምና ተቋም ተወስዶ እርዳታ እየተደረገለት እያለ በደረሰበት ከባድ ጉዳት ምክንያት ጥር 6 ቀን 2017 ዓ/ም ህይወቱ ያለፈ በመሆኑ የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ሀላፊ የሆኑት አቶ ኤልያስ ሰብለጋ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል::

የአበሽጌ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ተከሳሽን ድርጊቱን ፈፅሞ ከተሰወረበት በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራውን አጣርቶ የምርመራ መዝገቡ ለጉራጌ ዞን ፍትህ መምርያ ይልካል።መዝገቡ የደረሰው የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ዋና የስራ ሂደት ዐቃቤ ህግ ተከሳሽ ላይ በ1996 ዓ/ም ተደንግጎ የወጣውን የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 539 /1/ሀ/ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በፈፀመው ከባድ ሰው መግደል ወንጀል ክስ መስርቶበታል፡፡

ተከሳሹም ክሱ እንዲደርሰው ተደርጎ ከጠበቃው ጋር በችሎት ቀርቦ የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ የክስ መቃወሚያ የሌለው መሆኑን ገልፆ የተከሰሰበትን የወንጀል ድርጊት አልፈፀምኩም በማለት ክዶ በመከራከሩ የዓ/ህግ ምስክሮች ቀርበው ተሰምተው ፍርድቤቱም ተከሳሽ የቀረበበት ክስ ላይ የዐ/ህግ ምስክሮች እንደ ክስ አመሰራረቱ ያስረዱ ስለሆነ እንዲከላከል ብይን ሰጠ፡፡ በዚህም መሰረት ተከሳሽ የመከላከያ ምስክሮችን አቅርቦ ያሰማ ቢሆንም የአ/ህግ ምስክሮች የሰጡትን ቃል ሊያስተባብሉ ባለመቻሉ የጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት ፍርድ ሰጥቷል ፡፡

ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙ የቅጣት አስተያየት እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን ተከሳሽ ከዚህ በፊት የወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆኑንና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑ በማቅለያነት እንዲያዝለት ያሳሰብ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ያቀረባቸው 2 የቅጣት ማቅለያ በመያዝ ተከሳሽን ያርማል ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል ያስተምራል በማለት ተከሳሽን በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን አቶ ኤልያስ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል
13👎4🤬3👍2🥰2
2025/07/14 17:53:50
Back to Top
HTML Embed Code: