የኢራን 'ሰባሪና አስጨናቂ' የበቀል እርምጃ መጀመሩ ተገለፀ
ኢራን በእስራኤላውያን ጥቃቶች ላይ "አስጨናቂና ሰባሪ" የተባለውን የበቀል እርምጃ መጀመሯን የገለፀች ሲሆን በብሄራዊ የቴሌቭዥን ጣብያዋ በተላለፈው መልእከትም "ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት፣ ለጽዮናዊው አገዛዝ አስከፊ ጥቃት ወሳኝ ምላሽ የተጀመረው በመቶዎች የሚቆጠሩ የባለስቲክ ሚሳኤሎችን በመተኮስ ነው" ብሏል።
የእስራኤል ጦር በበኩሉ ኢራን በእስራኤል ላይ ሚሳኤል መተኮሷን ቀጥላለች ያለ ሲሆን በመግለጫውም “ሌላ በደርዘን የሚቆጠሩ ሚሳኤሎች ወደ እስራኤል ተኩሳለች" ብሏል።
ጦሩ አክሎም "የምትሰሙት ፍንዳታ ድምፅ ከተጠለፈ ወይም ከመከነ ሚሳኤል የሚወጣ ነው የአየር መከላከያ ስርዓቱ በየጊዜው ጥቃት አድራሽ መሳርያዎችን እየለየ ያመክናል" ሲልም ተደምጧል።
በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል

👍67❤26😁16🕊5🔥4🤔2🤝2🥰1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የቴልአቪቭ ሰማይ ከደቂቆች በፊት!
#ዳጉ_ጆርናል
#ዳጉ_ጆርናል
👍72🔥14👎9😁9🕊4❤3😭3
የኢራን የበቀል ጥቃት በእስራኤል ወታደራዊ ካምፖች ላይ ያነጣጠረ ነው ተባለ
የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ የኢራን ኃይሎች በእስራኤል ውስጥ በደርዘን በሚቆጠሩ ወታደራዊ ማዕከላት እና የአየር ሰፈሮች ላይ የፈጸመውን ሰባሪና እና የተመጠነ የበቀል ጥቃት በጠቅላይ መሪ አሊ ካሜኒ ትእዛዝ የተፈፀመ መሆኑ ተናግሯል።

👍88❤19🥰10🔥6🤷♂4👎4🕊2👌1
በቴልአቪቭ የጀመረው የኢራን የበቀል እርምጃ ወደ እየሩሳሌም ቀጥሎ በከተማይቱ የፍንዳታ ድምፅ መሰማት ጀምሯል ተባለ
ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ከሆነ በአሁኑ ሰዓት በእየሩሳሌም በርከት ያለ የፍንዳታ ድምፅ እየተሰማ ነው ብሏል።
ተጨማሪ ይዘን እንመለሳለን!

❤83👍23🔥9🕊5👌3👎2😢1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍102❤39🕊6🥰5😁5🔥4😢3🤔2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኔታንያሁ 'ተጨማሪ በመንገድ ላይ ነው' ሲሉ ተናገሩ
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ለኢራን ህዝብ ባደረጉት የቪዲዮ ንግግር ኢራን ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት "ኦፕሬሽን ራይዚግ ላዮን" የሚል ስያሜ እንዳለው በመግለፅ "የእስላማዊ መንግስትን የኒውክሌር እና የባሊስቲክ ሚሳኤል ስጋትን ለማክሸፍ" የተደረገ ነው ብለዋል።
ኔታንያሁ አክለው ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ የእስራኤል ሃይሎች “ከፍተኛ የጦር አዛዦችን፣ ከፍተኛ የኑክሌር ሳይንቲስቶችን፣ ለኢስላሚክ አገዛዙ በጣም አስፈላጊ የሆነውን የማበልጸጊያ ፋሲሊቲ እና ከፍተኛውን የባላስቲክ ሚሳኤል ጦር መሳሪያ” እንዳስወገዱ ተናግረዋል።
ኔታንያሁ "ተጨማሪ ጥቃት በመንገድ ላይ ነው ያሉ ሲሆን አክለውም አገዛዙ ምን እንደመታቸው አያውቁን በቀጣይም ምን እንደሚመታቸውና እንደሚጎዳቸው አያውቁም" በማለት የመጪው ጥቃት ከፋት ምን ያክል ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቶል።

👎100❤62😁11🔥7👍3🕊1
የፀጥታው ምክርቤት ለስብሰባ ተቀመጠ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት በእስራኤልና ኢራን ጉዳይ ለመምከር አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ በአሁኑ ሰዓት ኒውዮርክ በሚገኘው ዋና መስርያቤቱ ውይይት ጀምሯል።

👎98👍18😁16❤4🌚3
አሜሪካ የኢራን ሚሳኤሎችን በማምከን መሳተፏ ተገለፀ
የአሜሪካ ጦር ወደ እስራኤል ያቀኑትን የኢራን ሚሳኤሎችን ለመምታት ረድቷል ሲሉ ሁለት የአሜሪካ ባለስልጣናት ለሮይተርስ ተናግረዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉት ባለስልጣናቱ፣ ተዋጊ ጄቶች ወይም የጦር መርከቦች በመጠቀም የመከላከል ሥራውን ስለመፈጸማቸው ጨምሮ ተጨማሪ መረጃ አልሰጡም።

👎72👍57❤19😁16🕊3🤷1
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
ከሱፐርማርኬት ሰራተኝነት እስከ ማንችስተር ሲቲ የእግርኳስ ቡድን የደረሰዉ ቲጃኒ ራይንደርስ...
በናይጄሪያዊዉ ቲጃኒ ባባንጊዳ ስም የተሰየመዉ ቲጃኒ ራይንደርስ የእንግሊዙን ማንችስተር ሲቲ ተቀላቅሏል።
ተጨዋቹ በቀደመ ህይወቱ በ 2017/18 የውድድር ዘመን ለዞዌል ቡፍን በ18 ዓመቱ ፈርሞ ነበር።
ታድያ የመጀመሪያ ቡድን እግር ኳስ ለመድረስ ቢቃረብም ወላጆቹ የገንዘብን ዋጋ እንዲረዳ በሚል በአልዲ ሱፐርማርኬት እንዲሰራ አድርገዉት ነበር።
ቲጃኒ ስለ ወቅቱ ሲናገርም "መደርደሪያዎቹን አስተካክዬ ከኋላ እሰራ ነበር እና በወር ጥቂት መቶ ዩሮዎችን አገኝ ነበር። በአልዲ የነበረኝ ቆይታ በጣም ጥሩ ነበር፣ የሳንቲምን ሁለቱንም ጎኖች እንዳይ ረድቶኛል" ብሏል።
ከአልዲ እስከ ማንቸስተር ሲቲ በትህትና እና በትጋት በመስራት ዛሬ ላይ በአለማችን ቁጥር አንድ ትልቅ ሊግ የማንችስተር ከተማን ሰማያዊ ጎን ይወክላል።
ቲጃኒ ከኳስ ተጨዋችነት በተጨማሪ የስራን እና የገንዘብን ትርጉም በሚገባ የተረዳ ሰዉ ነዉም ይሉታል። ሜዳ ላይ ያንን ሰራተኝነቱን ያሳያል። አይደክሜ ሯጭ እንደሆነም ይነገርለታል።
በፔፕ ጋርዲዮላ ስር የኬቨን ዴብራየንን ሚና ተክቶ ሊጫወት እንደሚችል ይጠበቃል።
በበረከት ሞገስ
ለስፖርታዊ መረጃዎችን ይፋዊ የዳጉ ጆርናል ስፖርት ቻናል https://www.tg-me.com/Dagujournalsport ን ይቀላቀሉ
#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት

❤31🔥2
በዳሰነች ወረዳ በ ቱርካና እና ኦሞ ወንዝ ሙላት ምክንያት ከ79 ሺህ 828 በላይ አርብቶ-አደሮች ተፈናቀሉ
በ
መንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት የተገነቡ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በውሃ በመዋጣቸው ምክንያት ከአገልግሎት ውጭ እንደሆኑም ገልጿል።
የቱርካና ሐይቅ በ8 ዓመት ጊዜ ውስጥ 65 ኪ. ሜትሮችን ተጉዞ የወረዳው ዋና ከተማ ወደሆነችው ኦሞራተ 2 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንደደረሰና በቀጣይም ከተማው ሙሉ በሙሉ የመዋጥ አደጋ እንደጋረጠባት አቶ ታደለ ተናግረዋል፡፡ ይህም በከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ ስጋት አሳድሮባቸዋል ብለዋል።
ይህን የተገለጸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢ እና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዳሰነች ወረዳ በመገኘት ከወረዳው የስራ ሃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ነው።
በዚሁ ወቅት የወረዳው አስተዳዳሪ፤ የሜትሮሎጂ ትንበያዎች እንደሚጠቁሙት፣ በቀጣዮቹ የክረምት ወራት ከፍተኛ የሆነ ውሃ ወደ ኦሞ ወንዝና ቱርካና ሀይቅ ስለሚገባ ችግሩ ከዚህ ሊከፋ ይችላል ሲሉ ስጋተቸውን ለቋሚ ኮሚቴው አክለው ገልጸዋል።
#ዳጉ_ጆርናል
በ
ደቡብ ኢትዮጵያ
ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በቱርካና እና በኦሞ ወንዝ ሙላት ምክንያት ከ79 ሺህ 828 በላይ አርብቶ-አደሮች መፈናቀላቸውን የወረዳው አስተዳደሪ አቶ ታደለ ሀቴ ገለጹ።መንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት የተገነቡ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በውሃ በመዋጣቸው ምክንያት ከአገልግሎት ውጭ እንደሆኑም ገልጿል።

😢25❤9😁2😱1