የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ፅህፈት ቤት መደበኛ ገቢውን ከ100 በመቶኛ በላይ ማሳካቱን አስታወቀ
ጽህፈት ቤቱ በ2017 በጀት ዓመት ከመደበኛ ገቢ 181 ሚሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ አቅዶ የበጀት ዓመቱ ከመጠናቀቁ ከአንድ ወር በፊት ከ192 ሚለየን ብር በላይ ወይም 105.9 በመቶኛ ከእቅድ በላይ መሰብሰብ መቻሉን የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጌትነት እሸቱ ገልፀዋል።
ምክትል ከንቲባው የገቢ ተቋሙ አመራሮች፣ ቡድን መሪዎችንና ባለሙያዎች ተናበው፣ ተቀናጅተውና በታታሪነት ሰርተው መደበኛ ገቢውን ከእቅድ በላይ ማሳካት መቻላቸው የገለፁ ሲሆን ለዚህም በአስተዳደር ምክር ቤቱ ሥም ከፍ ያለ ምስጋናን አቅርበዋል።
ከተማና መሰረተ ልማት ፅህፈት ቤት ከከተማ አገልግሎት ገቢ 60 ሚሊየን 781ሺ 227 ብር ለመሰብሰብ ካቀደው ውስጥ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ 27 ሚሊየን 403 ሺ 754 ብር በመሰብሰብ የአመታዊ ዕቅዱን 45 በመቶ ብቻ የሰበሰበ መሆኑን የገለፁት ምክትል ከንቲባው ከገቢ ተቋሙ ልምድና ተሞክሮ በመውሰድ የከተማ አገልግሎት ገቢን 100 በመቶ ለማሳካት በቀሪው አንድ ወር ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።
አክለውም ከተማና መሰረተ ልማት ፅህፈት ቤት የአገልግሎት ገቢን 100 በመቶ ማሳካት ባለመቻሉ ጥቅል የመደበኛና የከተማ አገልግሎት ገቢ 91 በመቶ ብቻ ነው ሲሉ አቶ ጌትነት ገልጸዋል። አክለውም ከተማዋን ማሳደግ ካለብን ገቢ የመሰብሰብ አቅማችን ማሳደግ አለብን ገቢ የመሰብሰብ አቅማችን ስናሳድግ የህዝባችን የመልማት ፍላጎት ማሳካትና ከተማችን ማሳደግ የምንችል በመሆኑ ይህ መልካም ጥረት ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል አለበትም ማለታቸውን ብስራት ሬድዮ ከሰቆጣ ከተማ ኮሚኒኬሽን ያገኘው መረጃ ያሳያል።
በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል

❤14👎5
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
በአለም የክቦች የአለም ዋንጫ ክለቦች ምን ያህን ገንዘብ ያገኛሉ?
ከፍተኛ ገንዘብን የሚያሸልመዉ የመጀመሪያው የአለም የክለቦች ዋንጫ ዛሬ ሌሊቱን በአሜሪካ በኢንተር ሚያሚ እና አል አህሊ ጨዋታ ይጀመራል።
በአዲሱ ዉድድር ክለቦች አንድ ጨዋታ ባሸነፉ ቁጥር 2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚሸለሙ ታዉቋል። ቡድኖች ጨዋታቸዉን አቻ ካጠናቀቁ እያንዳዳቸው 1 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ጉርሻ ይወስዳሉ ተብሏል።
በተጨማሪም 16 ዉስጥ የሚገቡ ቡድኖች ለጥሎማለፉ በመብቃታቸዉ ብቻ 7.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይከፈላቸዋል ተብሏል።
ሩብ ፍጻሜ የሚደርሱ ቡድኖች ደግሞ ምድቡን በመቀላቀላቸዉ ብቻ 13.1 ሚሊዮን ዶላር ወደ ካዝናቸዉ ያስገባሉ። ግማሽ ፍጻሜዉን የሚቀላቀሉት ደግሞ 21 ሚሊዮን ዶላር ይወስዳሉ።
ለፍጻሜ በሚደረግ ጨዋታ የተረታዉ ቡድን 30 ሚሊዮን ፍጻሜዉን አሸንፎ የመጀመሪያውን የፊፋ የክለቦች የአለም ዋንጫን የሚያሸንፈዉ ቡድን ደግሞ 40 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያፍሳል ተብሏል።
በበረከት ሞገስ
ለስፖርታዊ መረጃዎችን ይፋዊ የዳጉ ጆርናል ስፖርት ቻናል https://www.tg-me.com/Dagujournalsport ን ይቀላቀሉ
#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት

❤15👍4🔥1
የአንጋፋው ጋዜጠኛ የደረጄ ኃይሌ 60ኛ ዓመት የልደት በዓል ዛሬ በድምቀት ይከበራል
ከፍተኛ የሆነ ተወዳጅነትን ያተረፈው ጋዜጠኛ ደረጄ ኃይሌ የሕይወቱን እና የሙያ ክህሎቱን ረጅም ጉዞ ለማስቃኘት ለማመስገን እንዲሁም 60ኛ ዓመት የልደት በዓሉን በአርትስ ቴሌቪዥን እና በወዳጆቹ አስተባባሪነት ዛሬ ታላቅ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡
በዚህ ፕሮግራም ላይ በርካታ የስነጥበብ አፍቃሪያን ቤተሰቦቹ ወዳጆቹ የአርትስ ቴሌቪዥን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት በሚገኙበት በድምቀት የሚከበር ይሆናል::
በዚህ የምስጋና ፕሮግራም ላይ ለተወዳጁ አንጋፋው ጋዜጠኛ ደረጄ ኃይሌ በአይነቱም በይዘቱም ከፍተኛ የሆነ ልዩ ስጦታ የሚበረከትለት ይሆናል::
Via አርትስ ቴሌቪዥን

❤80🔥9👍2👏1
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የ4 ዓመት ታዳጊ ህፃንን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የጭልጋ ወረዳ ፍትህ ፅ/ ቤት እድሜዋ 4 ዓመት ከ11 ወር የሆናትን ህፃን የአስገድዶ መድፈር የፈፀመው ግለሰብ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ገልጿል።
ሚያዝያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም አይከል ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 01 ልዩ ቦታው ቀጠና ሶስት እየተባለ ከሚጠራው ቦታ ከቀኑ በግምት 10፡00 ሰዓት ሲሆን ዕድሜዋ 4 ዓመት ከ11 ወር የሆናትን ህፃን ከተከራየበት ዶርም ውስጥ እየተጫወተች እያለ እሪ እንዳትል አፏን በእጁ በማፈን አስገድዶ የደፈራት ተከሳሽ
ላይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ ቁጥር 627/1/ ተላልፎ በመገኘቱ በ14/አስራ አራት/ ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣጡት የጭልጋ ወረዳ ፍትህ ፅ/ ቤት አሳውቋል።
ተከሳሹ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ ቁጥር 627/1/ ስር የተመከተውን በመጥቀስ ክስ መስርቶ ለጭልጋ ወረዳ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ህግን ምስክሮችን ካዳመጠ በኋላ ተከሳሽ ጥፋተኛ ከመባሉ በፊት እራሱን እንዲከላከል በሰጠው ብይን መሰረት ተከሳሽም በቀን 15/09/2017 ዓ.ም ዐ3/ስሶት/ የመከላከያ ምስክሮችን ይዞ በመቅረብ ያሰማ ቢሆንም በዐቃቤ ህግ በኩል የቀረበበትን ክስ እና ማስረጃዎች በአግባቡ ያላስተባበለ በመሆኑ ጥፋተኛ ተብሏል፡፡
ፍርድ ቤቱም በቀን 20/09/2017 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት የዐቃቤ ህግን እና የተከሳሽን የቅጣት አስተያየት መሰረት በማድረግ ተከሳሽን ከድርጊቱ ያርመዋል ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል ደግሞ ያስተምራል ፧ ያስጠነቅቃል ያለውን ተከሳሽ እጁን ለፖሊስ ከስጠበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ በ14/አስራ አራት/ ዓመት ፅኑ እስራት ሊቀጣ ይገባል በማለት የቅጣት ውሳኔ ሰጥቷል ሲል የጭልጋ ወረዳ ፍትህ ፅ/ ቤት የወንጀል የስራ ሂደት አሳውቋል።

👎43❤17🤬15💔2
ሞቢሊቲኢ 50 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለደንበኞች አስረከበ
ሞቢሊቲኢ ከድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በመተባበር ለ50 ደንበኞች የኤሌክትሪክ መኪኖችን አስረክቧል
ሞቢሊቲኢ ከድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ገንዘብ ቆጥበው ሲጠባበቁ ለነበሩ 50 ደንበኞች የ5ኛ ዙር የቢዋይዲ መኪኖችን በዛሬው እለት አስረክቧል።
ሞቢሊቲኢ ከቢዋይዲ ሴጉል፣ ቢዋይዲ ኢ2፣ ቢዋይዲ ዩአን አፕ፣ ቢዋይዲ ዩአን ፕላስ እና ቢዋይዲ ሶንግ ፕላስ መኪኖችን በ50% ቅድመ ክፍያ እንዲሁም ቀሪውን ከድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በመተባበር በ16.5% ወለድ ለደንበኞች በማቅረብ ላይ ይገኛል ሲሉ የሞቢሊቲኢ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ መንገሻ ተናግረዋል።
መጪውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ደንበኞች ከነዳጅ መኪና በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ባለቤት እንዲሆኑ ሞቢሊቲኢ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለደንበኞች በማቅረብ ላይ ይገኛል ሲሉ አቶ ሲሳይ መንገሻ አክለው ተናግረዋል።
ሞቢሊቲኢ በ4 ዓመት የብድር ክፍያ መመለሻ ጊዜ ያቀረበውን ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ልዩ ቅናሽ በቦሌ ቡልቡላ ሪፌንቲ በሚገኘው ዋናው ሾውሩም እንዲሁም መስቀል ፋላወር እና ሃዋሳ ፒያሳ ሩት ገበያ በሚገኙት ቅርንጫፎች አመቻችቶ ተጨማሪ መኪኖችን ለማስረከብ ዝግጅቱን ጨርሷል።
ሞቢሊቲኢ ቦሌ ቡልቡላ ሪፌንቲ በሚገኘው ዋናው ሾውሩም በዛሬው እለት ለ50 ደንበኞች የቁልፍ የማስረከብ ስነስርዓት አከናውኗል።
በሰላማዊ ነጋሲ

❤29🔥1
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
ኢትዮጵያ ቡና የሸገር ደርቢን አሸነፈ
ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 0 ነዉ ያሸነፈዉ። ለቡና ግቦቹን ዲቫይን ዋቹኩዋ በ 28ኛዉ ደቂቃ እና አማኑኤል አድማሱ በ 66ኛዉ ደቂቃ አስቆጥረዋል።

❤24🤬4👏3