Telegram Web Link
#Sleeping_Prince በድንገት ነቁ በሚል የሚሰራጨው መረጃ የሳዑዲ መንግስት ያላረጋገጠው ሀሰተኛ ዜና ነው።

#ዳጉ_ጆርናል
ኢራን በእስራኤል የወደብ ከተማ ሀይፋ እና በመዲናዋ ቴላቪቭ በፈፀመችው ጥቃት ሶስት ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆሰሉ

የኢራን ሚሳኤሎች የእስራኤልን ቴል አቪቭ እና የወደብ ከተማዋን ሀይፋን ዛሬ ሰኞ በመምታቱ ቤቶችን አውድሟል።  የአለም መሪዎች በዚህ ሳምንት በቡድን 7 ስብሰባ ላይ በሁለቱ የቀድሞ ጠላት ሀገራት መካከል የሚካሄደው ጦርነት ወደ ሰፊ ቀጠናዊ ግጭት ሊመራ ይችላል የሚል ስጋት አድሮባቸዋል። የእስራኤል ሚዲያ እንደዘገበው በሀገሪቱ ላይ በተፈፀመው ጥቃት ሶስት ሰዎች ሲገደሉ በደርዘን የሚቆጠሩ ደግሞ ቆስለዋል ብለዋል ።

በሃይፋ የወደብ ከተማ 30 ያህል ሰዎች ቆስለዋል ሲሉ የአደጋ ጊዜ ባለስልጣናት ተናግረዋል። በደርዘን የሚቆጠሩ የአደጋ ጊዜ የመጀመሪያ ምላሽ ሰጪዎች ወደ ጥቃት ዞኖች ሲጣደፉ የሚያሳይ ምስሎች ተሰራጭቱምተዋል። በወደቡ አቅራቢያ በሚገኝ የኃይል ማመንጫ ላይ የእሳት ቃጠሎ ታይቷል ሲል መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በቴላቪቭ ላይ በርካታ ሚሳኤሎች እና ፍንዳታዎች የነበሩ ሲሆን እየሩሳሌም ላይ ተመሳሳይ ጥቃት እንደነበር የቪዲዮ ምስል አመላክቷል።

በከተማዋ ከሚገኝ የአሜሪካ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ጥቂት መቶ ሜትሮች ርቆ የሆቴሎችን እና ሌሎች በአቅራቢያ ያሉ ቤቶችን መስኮቶችን የሰባበረ ጥቃት ደርሴክ። በቴል አቪቭ ሰፈር ውስጥ የሚገኙ በርካታ የመኖሪያ ሕንፃዎች ወድመዋል።

በኢራን የሟቾች ቁጥር 224 ደርሷል፤ ከነዚህም መካከል 70 ሴቶች እና ህጻናት ይገኙበታል። የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ጓድ (IRGC) የስለላ ሃላፊ እና ሌሎች ሁለት ጄኔራሎች እሁድ ዕለት በእስራኤል ጥቃት ተገድለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለቱ ወገኖች ስምምነት ማድረግ አለባቸው ሲሉ ጥሪ በማቅረብ ስብሰባዎች እየተደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ “እዚህ ያለውን ጉዳይ ማባባስ ሳይሆን ኢራን የኒውክሌር አቅሟን እንዳታዳብር ማስቆም ነው” ብለዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
አስከሬን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ መኪና ተገልብጦ የ5 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በሰቆጣ ወረዳ 07 ቀበሌ ዳብል ማሪያም ዲብር ሳይል አፈራ ጎጥ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።

የሰሌዳ ቁጥር አማ 30336 ኮድ 3 የሆነ ሚኒባስ ከደሴ ወደ ሰቆጣ አስከሬን ጭኖ ሲመጣ በደረሰ ድንገተኛ የትራፊክ አደጋ 3 ወንድ 2 ሴት በድምሩ የ5ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በተከሰተው የትራፊክ አደጋ 7 ወንድ 4 ሴት ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን በሰቆጣ ፖሊስ ጽ/ቤት የመንገድ ደህንነት ትራፊክ ክፍል ሃላፊ ኢንስፔክተር ሲሳይ አበራው ገልጸዋል።

#ዳጉ_ጆርናል
መርማሪዎች ከተከሰከሰው የኤር ህንድ የአብራሪዎች ክፍል ውስጥ የድምጽ ቅጂ አገኙ

መርማሪዎች ከተከሰከሰው አውሮፕላን የበረራ ክፍል ውስጥ የድምጽ መቅጃውን (ሲቪአር) ከኤር ህንድ አውሮፕላን ማግኘታቸውን ገልፀዋክ። ወደ ለንደን ሲያቀና የነበረው ኤር ህንድ አይሮፕላን ቦይንግ 787-8 ድሪምላይነር አውሮፕላን ከህንድ ምዕራባዊ አህመዳባድ ከተማ ሃሙስ እለት ሲነሳ ተከስክሷል። ቢያንስ 270 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን አብዛኛዎቹ ተሳፋሪዎች ናቸው። ሲቪአር የአብራሪዎቹን ንግግር፣ ማንቂያ መልዕክት እና ድምፆችን ጨምሮ ከኮክፒት ክፍል ይይዛል።

እንደ ከፍታ፣ ፍጥነት እና ሞተር አፈጻጸም ያሉ ወሳኝ የበረራ መለኪያዎችን የሚመዘግብ የበረራ መረጃ መቅጃ (ኤፍዲአር) አርብ እለት ከፍርስራሹ ውስጥ ተገኝቷል።ሁለቱም CVR እና FDR በጋራ የአውሮፕላን "ጥቁር ሳጥን" በመባል የሚታወቁ ናቸው። የበረራውን የመጨረሻ ጊዜዎች እንደገና ለማጤን እና የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ባለሙያዎችን በመርዳት በአየር አደጋ ምርመራዎች ውስጥ ወሳኝ መሳሪያ ነው። ጥቁር ሳጥኑ፣ ስሙ ባይገልፀውም፣ ከአደጋ በኋላ ሁለት ብሩህ ብርቱካናማ መሳሪያዎች በውስጡ ይዟል።አንዱ ሲቪአር ሲሆን ሌላው ኤፍዲአር  ይባላሉ። ሁለቱ እነዚህ መሳሪያዎች ከአደጋ በኃካ ለትንተና የተነደፉ ናቸው።

የህንድ መገናኛ ብዙሃን ምንጮችን ጠቅሰው እንደዘገቡት የቦይንግ እና የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር እንዲሁን የአሜሪካ የአቪዬሽን ደህንነት ኤጀንሲ ባለስልጣናትም የአደጋውን ቦታ ጎብኝተዋል። በተናጥል በህንድ መንግስት የተቋቋመው ከፍተኛ ኮሚቴ የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ የሚያስችል ከፍተኛ ኮሚቴ ሰኞ የመጀመሪያውን ስብሰባ አድርጓል። ኮሚቴው በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያ ሪፖርት እንደሚያቀርብ ኦል ህንድ ራዲዮ ዘግቧል።ወደፊት ተመሳሳይ አደጋዎችን ለመከላከል የሚረዱ አዳዲስ መደበኛ የአሠራር ሂደቶችን እንደሚያቀርብ ገልጿል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
የ 40 አመቱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በትናንትናው እለት የለቀቀዉ ምስዕል ነዉ👇🏼

ሮናልዶ ተክለ ሰዉነቱ ከዚህ ቀደም ባደረስናችሁ መረጃ መሰረት ዊፕ የተሰኘ ተቋም ባደረገዉ ግምገማ ባዮሎጂካል ዕድሜ 28 አመት ነው ብሎ ነበር።

ይህ ማለት ከትክክለኛው ዕድሜው በ 12 ዓመት ያነሰ ነው ማለት ነዉ። በእርግጥም የክርስቲያኖ ሰዉነት አስገራሚ ነዉ።

ሮናልዶም ይሄንን የተቋሙን ሪፖርት ሲመለከት "ይህ ማለት ተጨማሪ አስር ኳስ የመጫወቻ እድሜ አለኝ ማለት ነዉ" ብሏል።

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport
ፍርድ ቤት ችሎት ላይ ሀሰተኛ ምስክርነት የሰጡት  ሁለት ወንድማማቾች በእስራት ተቀጡ

በምዕራብ ሀረርጌ ዞን አንጨር ወረዳ ጨለለቃ ከተማ  ፍርድ ቤት ችሎት ላይ ሀሰተኛ ማስረጃ በመሆን በፍትህ አሰራር ሂደት ላይ የተዛባ ውሳኔ ለማሰጠት የሞከሩ ሁለት ወንድማማቾች በእስራት ተቀጡ።

የአንጨር ወረዳ ፍርድ ቤት እንደገለፀው
1ኛ ተከሳሽ አልዬ ሁሴን ፣ 2ኛ ተከሳሽ ሳዳም ሁሴን የተባሉ ሁለት ወንድማማቾች በወንድማቸው ሙሣ ሁሴን እና  ዓቃቢህግ መካከል ባለው የወንጀል ክስ ክርክር ለወንድማቸው የመከላከያ ማስረጃ ሆነው ቀርበው በሀሰት ሲመሰክሩ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ተጣርቶባቸው በእስራት ተቀጥተዋል።

ሁለቱ ወንድማማቾች በሀሰት ማስረጃ የፍትህ ሂደቱን ለማዛባት ባደረጉት ጥረት በወንጀል ህግ ቁጥር 453 በሀሰተኛ ምስክር እና  ማስረጃ ክስ የመሰረተባቸው መሆኑን መግለጫው አመላክቷል።
 
በዓቃቢ ህግ የተመሰረተውን ክስ ሲከታተል የነበረው የአንጨር ወረዳ ፍርድ ቤት ሁለቱ ተከሳሽ ወንድማማቾች የዳኝነት ስርዓት በሚካሄድበት ሂደት የአንድ ወገን ለመጥቀም ሀሰተኛ ማስረጃ ሆነው በመቅረባቸው ሰኔ 4ቀን 2017 ዓ.ም እያንዳዳቸው በአንድ ዓመት ከሁለት ወር እስራት እንዲቀጡ የአንጨር ወረዳ ውስኔ መስጠቱ ብስራት ሬዲዮ ከወረዳው ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
የኒውክሌር ድርድር የሚቀጥል ከሆነ አሜሪካ የእስራኤልን ጥቃት እንድታወግዝ ኢራን ጠየቀች

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንደተናገሩት እሁድ እለት ሊካሄድ የታቀደው የአሜሪካ-ኢራን የኒውክሌር ድርድር ከተሰረዘ በኋላ ድርድር እንዲቀጥል ከተፈለገ እስራኤል ኢራን ላይ ያደረሰችውን ጥቃት "ማውገዝ" አለባት ሲሉ ለአሜሪካ መልዕክት አስተላልፈዋል። ኢስሜል ባጋይ አሁን ባለው ሁኔታ ድርድሩን “ትርጉም የለሽ” በማለት በድጋሚ  ዩናይትድ ስቴትስ በጥቃቱ “ተባባሪ” ነች ብለዋል። በተጨማሪም የኢራን ፓርላማ ከኒውክሌር መስፋፋት ስምምነት (NPT) ለመውጣት ከወሰነ "አስገዳጅ" እንደሚሆን ተናግረዋል።

ኢራን ሁል ጊዜ የኒውክሌር መርሃ ግብሯ ሰላማዊ ነው ስትል እስራኤል ግን ይህንን ውድቅ አድርጋለች። በሌላ በኩል ሁሉም ኢራናውያን "በአንድነት እንዲቆሙ፣ እንዲጸኑ እና ኢራን የምትደርስበትን የወንጀል ጥቃት እንዲጋፈጡ" የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጥሪ አቅርበዋል። ሰኞ እለት በኢራን ፓርላማ ስብሰባ ላይ ፔዝሽኪያን እንደተናገሩት ኢራን "ዲፕሎማሲ እድል ሰጥታ ለድርድር እና ለውይይት መንገድ ከፍታለች" ብለዋል። "ጠላት ኢራንን እና ህዝቦቿን በአሸባሪነት ሊያጠፋቸው አይችልም ።ከእያንዳንዱ ኢላማ ጥቃት በኋላ ባንዲራውን የሚይዙ እና መንገዱን የሚቀጥሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጀግኖች አሉ" ብለዋል ። ፔዝሽኪያን ሀገራቸው "የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ለመያዝ እንደማትፈልግ" ነገር ግን "ኢራን ከኒውክሌር ሃይል ህዝቦቿን በሚጠቅም ምርምር የመጠቀም መብት እንዳላት" በድጋሚ ተናግረዋል።

በሌላ መረጃ ፖላንድ በእስራኤል ከጉብኝት ላይ የሚገኙ 200 የሚጠጉ ዜጎቿን ለማስወጣት በዝግጅት ላይ ስትሆን በዮርዳኖስ ዋና ከተማ በኩል ለማለፍ አቅዳለች ሲሉ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ሄንሪካ ሞስኪካ-ዴንዲስ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "በሚቀጥሉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ ዝግጁ እንደምንሆን እንገምታለን፣ ከእስራኤል የሚወጡት በቱሪስትነት የመጡትን እና ለአጭር ጊዜ የሚቆዩትን ይመለከታል ሲሉ ተደምጠዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
በእስራኤል አራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ይመልከቱ👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/kdOk0mCXBao?si=HvJ7F3JLOhE8Eet7
በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ 150 ሚሊዮን ሴቶች ወሲባዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል

👉በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ሴት ልጅ ከወንድ ቤተሰብ  በሚመጣ ሀብት ማለትም   ከብት እንዲሁም ወርቅ  እንደየ አካባቢው  የመቀየር  ስርዓት መኖሩ
ተነግሯል።

የሴት ልጅ ላይ የሚደርስ ጾታዊ  ጥቃት የሰብዓዊ  መብት ጥሰት ከመሆኑ በላይ በኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶችን ወደ ተለያዩ ችግሮች የሚከት ጤናን  የሚጎዳ  እና  ስር የሰደደ ችግር መሆኑ ተገልጿል ።በተለያዩ አካባቢዎች የሴት ልጅ ጥቃት ከባህል አኳያ የሚደርስ ሲሆን  ከእነዚህ መካከል የልጅነት ጋብቻ ፣ የሴት ልጅ ግርዛት በተለያዩ አካባቢዎች የሚዘወተሩ እና እንደ ባህል የሚታዩ ልምዶች መሆናቸው ተጠቁሟል። በተለያዩ አካባቢዎች ሴት ልጅ ከወንድ ቤተሰብ  በሚመጣ  ሀብት ማለትም  ከብት እንዲሁም ወርቅ  እንደየ አካባቢው የመቀየር  ስርዓት መኖሩ ተነግሯል።

በዚህም ሚስት ለማግኘት የሚበቃ ከብት የሌላቸው የወንድ ቤተሰቦች በአንዳንድ አካባቢዎች ትዳር ለማግኘት በመቸገራቸው  ወደ ሌላ አካባቢዎች እንደሚሰደዱ በፕላን ኢትዮጵያ  የኮሙኒኬሽን ክፍል ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ምስክር  ጌታሁን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።በኢትዮጵያ ያለ እድሜ ጋብቻ ፣ጾታዊ  እኩልነት፣ እንዲሁም በትዳር ውስጥ በኢኮኖሚ የሚደርሱ ጫናዎች  እና ጥቃቶች ትኩረት  ሊሰጣቸው የሚገባ ጉዳዮች ናቸው ተብሏል።  በዓለም ላይ ከሶስት ሴቶች አንዷ በህይወት ዘመኗ  አካላዊ ወይም  ለስነልቦናዊ ለሆነ ጾታዊ ጥቃት ትጋለጣለች ። በአፍሪካ ከስምንት ሴቶች መካከል አንዷ ከ15 ዓመት በታች እያለች እንደምትዳር ተገልጿል ። በ2016 የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው በአፍሪካ 25 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች  አካላዊ ጥቃት የሚደርስባቸው ሲሆን 36 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ስነልቦናዊ ጥቃት ይደርስባቸዋል ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ  150 ሚሊዮን ሴቶች ወሲባዊ ጥቃት፣  200 ሚሊዮን የሴት ልጅ ግርዛት እና 700 ሚሊዮን ያለእድሜ ጋብቻ ይፈጸምባቸዋል ።  በተጨማሪም በየቀኑ  137 ሴቶች  በቅርባቸው ሰው ወይም በትዳር አጋራቸው ህይወታቸው  እንደሚያልፍ ተነግሯል።በኢትዮጵያ  የሚፈጸሙ ጥቃቶች ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ስለማይደረግ እና ሴቶችም ሲደፈሩ በግዴታ እንዲያገቡ የሚደረጉበት ሁኔታ ሰፊ መሆኑ እና በተለያዩ ምክንያቶች የተረጋገጠ መረጃ ማግኘት እንዳይቻል እንቅፋት መሆኑን  በፕላን ኢትዮጵያ  የኮሙኒኬሽን ክፍል ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ምስክር ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
ግጭቱ በዚህ ፍጥነት ከቀጠለ መጀመሪያ መከራ የሚጋፈጡት የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ናቸው ስትል ቻይና አስታወቀች

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጉዎ ጂያኩን በቤጂንግ በተደረገ የቀጥታ ስርጭት የዜና ኮንፈረንስ ላይ እንደተናገሩት ቻይና “እስራኤል በኢራን ላይ የምታደርሰው ጥቃት በጥልቅ ያሳስባታል” ብለዋል።

"ሁለቱም ወገኖች በተቻለ ፍጥነት ውጥረቱን ለማርገብ እርምጃዎችን እንዲወስዱ እንጠይቃለን ያለው ሚኒስቴሩ ክልሉ ወደ ከፍተኛ ትርምስ እንዳይገባ እና ወደ ትክክለኛው መንገድ በውይይት እና በምክክር ለመፍታት ሁኔታዎችን እንዲፈጥሩ እንጠይቃለን" ብለዋል።

"በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለው ግጭት ተባብሶ ከቀጠለ አልፎ ተርፎም እየሰፋ ከሄደ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የመጀመሪያ ገፈት ቀማሽ ይሆናሉ" ሲሉም ተደምጠዋል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
ቦካ ጁኒየርስ ታማኝ ታዳጊ ደጋፊዉን ማስታወቂያ አሰራ

በ2023 የተቀረጸዉና ብዙ የእግርኳስ አፍቃሪዎች የተመለከቱት አንድ ቪዲዮ ነበር። አንድ የቦካ ጁኒየርስ ታዳጊ ደጋፊ በምስዕሉ ላይ በስሜት ሲናገር ይታያል።

ይህ ታዳጊ የቦካ ጁኒየርስ ደጋፊ ቃለ መጠይቁን ካደረገ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በመላዉ አለም ሲሰራጭ ብዙ አልቆየምም ነበር።

ታዳጊዉ ሲናገር "እኔና አባቴ የኮፓ ሊበርታዶሬስን የፍፃሜ ጨዋታ ለመመልከት ወደ ብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ ለመጓዝ የኔን ፕሌይስቴሽን 5 እና የአባቴን ሞተር ብስክሌት ሸጠናል" ሲል ይደመጣል።

በስሜት የሚናገረዉ ታዳጊ ቀጥሎም " ወደ ጨዋታዉ መግቢያ ቲኬት የለንም ግን በስታዲየም በራፍ ላይ ከደጋፊዎች ጋር አንድላይ ለመሆን ነዉ እንደዛ ያደረግነዉ። ይህ ቦካ ነዉ" ሲልም በስሜት ያክላል።

ታድያ በዚህ ሳምንት አዲሱን እና የቀጣይ አመቱን መለያዉን ያስተዋወቀዉ ቦካ ጁኒየርስ አዲሱን መለያ በዚህ ታዳጊ አስተዋዉቋል። በማስታወቂያዉ ላይም ይህንን ታዳጊ ደጋፊ አካትተዉታል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በእስራኤል እና ኢራን ጦርነት የተነሳ ከአዲስአበባ ወደ ቴላቪቭ የሚያደርገዉን በረራ አቋረጠ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በእስራኤል እና ኢራን ጦርነት የተነሳ ከአዲስአበባ ወደ ቴላቪቭ የሚያደርገዉን በረራ ማቋረጡን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ እና በቴልአቪቭ መካከል በሁለቱም አቅጣጫ የሚደረጉ በረራዎች በአዉሮፓዉያን አቆጣጠር እስከ ሰኔ 22 ቀን 2025 ድረስ መቋረጣቸውን ባወጣዉ መግለጫ አሳዉቋል።

አየርመንገዱ ለተፈጠረዉ ችግር ይቅርታ ጠይቆ ደምበኞቹ የቲኬት መሸጫ ቢሮዎቹን እንዲያናግሩ መክሯል። አየርመንገዱ በረራዉን መቼ እንደሚጀምር እና አዲስ መረጃዎችን እንደሚያሳዉቅ ጠቅሷል።

እስራኤል እና ኢራን መጠነ ሰፊ ጦርነት ከጀመሩ ቀናት ተቆጥረዋል።እስካሁንም በሁለቱም ወገን የሰዉ ህይወትና ንብረት ላይ ትልቅ ጉዳት ደርሷል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል
2025/07/05 17:40:10
Back to Top
HTML Embed Code: