በኢራን ላይ የደረሱት ጥቃቶች ከእስራኤል ጋር ሲነጻጸር በ5 እጥፍ ይበልጣል ተባለ
በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ መቀመጫውን ያደረገው የየመከላከያ አስተሳሰብ የ Critical Threats ፕሮጀክት እና የጦርነት ጥናት ተቋም (CTP-ISW) እንደዘገበው የእስራኤል ጦር በኢራን ውስጥ ባሉ ቦታዎች ላይ የአየር ጥቃቶችን ኢራን በእስራኤል ኢላማዎች ላይ ካደረሰችው ጋር ሲነጻጸር በአምስት እጥፍ ይበልጣል። የእስራኤል ጦር በሰኔ 13 ኢራን ላይ ጥቃት ከሰነዘሩበት ጊዜ ጀምሮ 197 ጊዜ የአየር ድብደባ ማድረጋቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።
በአንጻሩ፣ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ፣ በእስራኤል ውስጥ የኢራን ባሊስቲክ ሚሳኤል ጥቃቶችን ወይም የመጥለፍን ተፅዕኖ 39 ጊዜ ያህል መሆኑን ሪፖርት አረጋግጧል።እስራኤል እና ኢራን ለቀናት በቀጠለው የሚሳኤል ጥቃት በቴህራን ላይ ድብደባ ደርሴል። በማዕከላዊ እስራኤል የእሳት ቃጠሎ አስከትሏል። የእስራኤላውያን የእሳት አደጋ ተከላካዮች እሳቱን በመቆጣጠር ላይ ሲሆኑ በርካታ መኪኖችን ያወደመ ይመስላል።
የእስራኤል ጦር አርብ ዕለት በዋና ከተማዋ ቴህራን እና በኢራን ገጠራማ አካባቢዎች ጥቃቱን ከጀመረ ወዲህ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኢራን ሲገደሉ በአንፃሩ በእስራኤል ቢያንስ 24 ሰዎች ተገድለዋል። መቀመጫውን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በእስራኤል ጥቃት ቢያንስ 585 ሰዎች በመላው ኢራን ሲገደሉ 1,326 ቆስለዋል ብሏል። ቡድኑ ከሟቾቹ ውስጥ 239 ሲቪሎች እና 126 የጸጥታ አባላት መሆናቸውን ገልጿል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል

በጋሞ ዞን የሦስት ዓመት ህፃን ሰርቃ በመኖሪያ ቤቷ አልጋ ስር እጁና እግሩን በማሰር አፉን አፍና የተገኘችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ከንባ ወረዳ ካምባ ከተማ ጠፍቶ ሲፈለግ የነበረው ህፃን በህይወት መገኘቱን የከተማው ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።ህፃን ናታን ቦጋለ ሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ከቤት ወጥቶ ከሠፈር ህፃናት ጋር ወደሚጫወትበት ቦታ ያቀናል፣ ከወጣበት ሰዓት ጀምሮ ከሠፈር ልጆቹ መሃል እንደተሰወረ ሲታወቅ ቤተሰቦቹና የአከባቢው ሕብረተሰብ ፍለጋ ያደርጋል፡፡
የሕጻኑን መጥፋት ያረጋገጡት ወላጅ ቤተሰቦች ለፖሊስ ቀርበው ጉዳዩን ያመለክታሉ፡፡ ፖሊስም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማዉጣት ሕፃኑ የጠፋበትን ሙሉ አካባቢ ብርበራ በማካሄድ ተጠርጣሪ ያምቡቄ ኤዳ የተባለች ግለሰብ ከምትኖርበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ማግኘቱን አስታዉቋል፡፡
የሦስት ዓመቱ ታዳጊ ሰኔ 10 ከቀኑ 8:30 ተከሳሽ በምኖርበት መኖሪያ ቤት አልጋ ሥር እጁ፣እግሩ ታስሮ አፉ ታፍኖ ከታገተበት በህይወት መገኘቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በማገት ወንጀል የተከከሰሰችው ግለሰብ በሕግ ቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተጣራባት መሆኑን የተገለፀ ይህን መሰል ወንጀል በአከባቢው ያልተለመደና አስነዋሪ ድርጊት በመሆኑ በሕፃናት ላይ ለሚፈፀም ወንጀል ፖሊስ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
በሳምራዊት ስዩም

በመካከለኛው ምስራቅ ከእስራኤል በመቀጠል ከፍተኛው የአይሁድ አማኞች በኢራን ይገኛሉ
በኢራን እና በእስራኤል መካከል እየተባባሰ የመጣውን ግጭት አስመልክቶ የኢራን አይሁድ ማህበረሰብ ሀገሪቱን ለዘመናት ቤታችን ብለው ይጠሯታል። በግምታዊ መረጃ መሰረት ከ17,000 እስከ 25,000 የሚደርሱ ኢራናውያን አይሁዶች በአብዛኛው እንደ ቴህራን፣ ኢስፋሃን፣ ሺራዝ፣ ሃመዳን እና ታብሪዝ ባሉ ትላልቅ ከተሞች ይኖራሉ። ከእስራኤል ቀጥሎ ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአይሁድ እምነት ተከታዮች ይገኛል።
በኢራን ፓርላማ የሆነው መጅሊስ፣ ለአይሁድ ማህበረሰብ አንድ መቀመጫን በምክር ቤቱ ውስጥ ይፈቅዳል።በኢስፋሃን ከተማ ውስጥ ከታወቁት የአይሁድ ምኩራቦች አንዱ አል አቅሳ ከሚባለው መስጊድ አጠገብ ይገኛል። በቴህራን ከተማ ውስጥ ቢያንስ 50 ምኩራቦች ይገኛሉ ። የአይሁዶች ማህበረሰብ በቴህራን ውስጥ የሃይማኖት ልዩነት ሳይፈጥር ሁሉንም ታካሚዎች የሚያስተናግድ ሆስፒታል ያስተዳድራል። አይሁዳውያን ክምከኢራን ጋር ያላቸው ግንኙነት ከ2,700 ዓመታት በፊት የጀመረ ሲሆን በቴህራን የአብሪሻሚ ምኩራብ ከፍተኛ ራቢ የሆኑት ዩነስ ሃማሚ ላሌዛር ይናገራሉ።
አይሁዳዊቷ አስቴር እና አጎቷ መርዶክዮስ የተቀበሩት በምእራብ ሃመዳን ከተማ እንደሆነ ይታመናል። በአይሁድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምሮት መሠረት አስቴር ከፋርስ ንጉሥ ከዜርክስ ጋር ትዳር መስርታለች። በቅርብ ታሪክ ውስጥ፣ አገሪቱ ከስፔን ኢንኩዊዚሽን ለሸሹ አይሁዶች አስተማማኝ መሸሸጊያ ሰጥታለች። የጀርመኑ ናዚ መሪ አዶልፍ ሂትለር አውሮፓን በወረረበት ወቅት የፖላንድ አይሁዶች ኢራን ጥገኝነት ጠይቀዋል። ነገር ግን በሣፋቪድ እና በቀጃር ዘመን አይሁዶች በግዳጅ እምነታቸውን እንዲቀይሩ በመደረጉ፣ የ1979 አብዮት ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢራናውያን አይሁዶች ወደ አሜሪካ እና እስራኤል ተሰደዋል።

በደብረ ማርቆስ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸ ከ1ሺ ኩንታል በላይ ጤፍ እና በቆሎ በቁጥጥር ስር ዋለ
በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር አብማ ክፍለ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ የተከዘነ ጤፍ እና በቆሎ በቁጥጥር ስር መዋሉን በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳድር የ1ኛ ዋና ፖሊስ ፅ/ቤት ለብስራት ሬዲዮ የላከው መረጃ ያመላክታል።በአብማ ክፍለ ከተማ ውሰታ ገበያ በረንዳ ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ የተከዘነ 946 ኩንታል በቆሎ እና 154 ኩንታል ጤፍ በማህበረሰቡ በደረሰ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተገልጿል ።
በተመሳሳይ ዜና በተድላ ጓሉ ክፍለ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ወደ አጎራባች ወረዳ ሊሄድ የነበረ 3,011 ሊትር ቤንዚል በፀጥታ ሃይሉ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተጠቁሟል።በከተማዋ የሚፈፀሙ ህገወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር የፀጥታ መዋቅሩ ከማህበረሰቡ ጋር በቅንጅት እየሰራ ስለመሆኑ ተነግሯል።
ህገ ወጥ ተግባርን ህዝቡ እያጋለጠ እንደሚገኝ የተነገረ ሲሆን ይህ ተጠናክሮ መቀጠል የሚኖርበት መሆኑን የኑሮ ውድነቱን ለማባባስ ምርትን የአላግባብ የሚከዝኑ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባም ተጠቁሟል።
በኤደን ሽመልስ

የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የፍትህ ሚኒስትር በሌብነት ቅሌት ሳቢያ ከስልጣናቸው ለቀቁ
የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የፍትህ ሚኒስትር በሕዝብ ሀብት መዝረፍ በተከሰሱበት ቅሌት ወቅት ሥራቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል። የ37 አመቱ ኮንስታንት ሙታምባ ከፕሬዚዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኬዲ ጋር ለፍትህ መንገድ ጥርጊያ በሚል ባደረጉት ውይይት ስራቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል ሲል ረዳታቸው ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። የፕሬዚዳንቱ ፅህፈት ቤት ምንጭ እንዳረጋገጠው ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኬዲ የሙታምባን መልቀቂያ መቀበላቸውን እና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርበው መደበኛ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።
በግንቦት 2024 የተሾመው ሙታምባ በሰሜናዊ ምስራቅ ኪሳንጋኒ ከተማ ለእስር ቤት ግንባታ የተመደበው 19 ሚሊዮን ዶላር በመመዝበራቸው በምርመራ ላይ ይገኛሉ። የስራ መልቀቂያቸው የተሰማው የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ፊርሚን ምቮንዴ በሰበር ሰሚ ችሎት ሚኒስትሩ ዋና ከተማዋን ኪንሻሳን ለቀው እንዳይወጡ ከከለከሉ በኋላ ነው።ባለፈው እሁድ የሀገሪቱ ምክር ቤት ያለመከሰስ መብታቸውን ካነሳ በኋላ ክስ እንዲመሰርት ተፈቅዷል።
ሙታምባ ጉዳዩ በእኔ ላይ "የፖለቲካ ሴራ" በማለት ክሱን አውግዘዋል። ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሙታምባ በርካታ እስረኞችን ያለአግባብ የከባድ ቅጣት እስረኞች እንዲፈቱ አድርገዋል ያለ ሲሆን ከእስር ከተፈቱት የተወሰኑትን በነፍስ ግድያ፣ ማሰቃየት ወይም በትጥቅ ዝርፊያ ፈጽመዋል ሲል ከሷል። ሙታምባ በ2023 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተወዳድረዋል። የፍትህ ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በኋላ ሙስናን ከስር በመቅረፍ የፍትህ ስርዓቱን ለማሻሻል ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀው ነበር።

Forwarded from ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal (#Me_Lion)
በእስራኤል አራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ጋር ይከታተሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/e4whZmVDFao?si=xKiZJdAhf3GiQA-g
#ዳጉ_ጆርናል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/e4whZmVDFao?si=xKiZJdAhf3GiQA-g
#ዳጉ_ጆርናል
በጋምቤላ ክልል ባለፋት ዘጠኝ ወራት ከ1.9 ሚሊዮን በላይ ኮንዶም ተሰራጭቷል ተባለ
በጋምቤላ ክልል የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ በመሆኑ የነገ ሀገር ተረካቢ በሆኑት አፍላ ወጣቶችና ልጃገረዶች ላይ እያስከተለ ያለው ጉዳት ከፍተኛ ነው ሲል የክልሉ ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት አስታውቋል።
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ በክልሉ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የበርካታ ወገኖች ህይወት በኤች አይ ቪ ኤድስ ምክንያት ማለፉን መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።አያይዘውም በክልሉ ያለዉ ስርጭት ባለፉት ዓመታት ከነበረበት የመቀነስ አዝማሚያ ቢያሳይም የሚፈለገውን ያህል ውጤት ማምጣት አለመቻሉን ተናግረዋል።
በጽ/ቤቱ የዘርፈ ብዙ ምላሽ የኤች አይ ቪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አቡላ ድንጉር በበኩላቸው ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ባለፋት ዘጠኝ ወራት ለ 1ነጥብ 9 ሚሊዮን ሰዎች የኮንዶም ስርጭት ተከናውኗል።የኮንዶም ስርጭቱም በነፃ መከናወኑን የገለፁት አቶ አቡላ ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መከፋፈሉን አብራርተዋል።
በዋነኛነት ለወሲብ ሰራተኞች፣ለረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች፣ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቃሽ የሆኑና ጨምሮ ለሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ማሰራጨት ተችሏል ሲል ጽ/ ቤቱ ጨምሮ ገልጿል፡፡
ቅድስት ደጀኔ

በናይጄሪያ ከደረሰው አስከፊ የጎርፍ አደጋ በኃላ እስካሁን ከ700 በላይ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም
በናይጄሪያ ሰሜን ማእከላዊ ኒጀር ግዛት ከሶስት ሳምንታት በፊት ከባድ የጎርፍ አደጋ ካጋጠማት በኃላ ከ700 የሚበልጡ የሞክዋ ማህበረሰብ አባላት እስካሁን ድረስ ጠፍተዋል ሲል የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ረቡዕ እለት ዘግበዋል። የኒጀር ግዛት ገዥ ኡማሩ ባጎ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ግዛቱ በቅርቡ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ቢያንስ 207 ሰዎች መሞታቸውን ዴይሊ ትረስት ዘግቧል።
በሜይ 29፣ በደቡብ ነጋዴዎች እና በሰሜናዊ የግብርና አምራቾች መካከል ያለው ቁልፍ የንግድ ትስስር በሆነው የሞክዋ አካባቢ አስተዳደር ለሶስት ቀናት ሳያቋርጥ ከጣለው ዝናብ በኋላ ከባድ የጎርፍ አደጋ አጋጥሟል። ፕሬዝደንት ቦላ ቲኒዩ የብሄራዊ የድንገተኛ አደጋ አስተዳደር ኤጀንሲ እና የጸጥታ ሃይሎች በተጎዱ ማህበረሰብ ውስጥ የፍለጋ እና የነፍድ አድን ስራዎችን እንዲያጠናክሩ አዘዋል። ገዥ ባጎ ደግሞ ከ3,000 በላይ አባወራዎች ተፈናቅለዋል ብለዋል።
ከ 700 በላይ ሰዎች አሁንም የጠፉ ሲሆን የት እንዳሉ ለማወቅ ገና አልቻልንም። የጎርፍ አደጋው ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፤ ሲሉ አክለዋል። 283 ቤቶችና 50 ሱቆችም ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ገልፀዋል። የግዛቱ ርዕሰ መስተዳድሩ አያይዘውም የጎርፍ አደጋውን መንስኤ ለማወቅ የክልሉ መንግስት ከሙያ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የግምገማ ውጤት እየጠበቀ ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ የአንጀት ካንሰር በአስከፊ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው ተባለ
👉 ዓይደር ሆስፒታል በወር በአማካይ እስከ 50 ለሚሆኑ ታካሚዎች የአንጀት ካንሰር ህክምና እየሰጠ ነዉ
በዓለም ዙሪያ ሆነ በኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣው የአንጀት ካንሰር በዓለም አቀፍ ደረጃ ከጡት ካንሰር እና ከ ማህፀን በር ጫፍ ካንሰር በመቀጠል በሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ገዳይ በሽታ ነው። በዓይደር ኮምፐርሄንሲቭ ሲፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአንጀት ካንሰር ህክምና በአንድ ወር በአማካይ ከ30 እስከ 50 ለሚሆኑ ታካሚዎች ህክምና እንደሚሰጥ እና አብዛኛዎቹ ታካሚዎች ደግሞ ከ45 ዓመት በላይ የሆናቸው ሴቶች መሆናቸዓ በሆስፒታሉ የካንሰር ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ደስታ ሙሉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
የአንጀት ካንሰር መንስኤው የአመጋገብ ችግር እንደሆነ የገለፁት ስፔሻሊስቱ ይህም ማለት ጥሬ ስጋ መመገብ፣ ከፋብሪካ የወጡ ምግቦችን ማዘውተር፣ ሲጋራ ማጨስ እና የአልኮል መጠጦች አብዝቶ መጠጣት ለአንጀት ካንስር ዋና አጋላጭ ምክንያቶች መሆናቸውን እና በተጨማሪም በዘር የሚተላለፍ የካንሰር አይነት እንደሆነም ተናግረዋል። ከ50 አመት እድሜ ክልል በላይ የሚሆኑ ሰዎችም ለካንሰር ተጋላጭ እንደሆኑ ገልፀዋል። ይህ የካንሰር አይነት በዘር ሊተላለፍ ይችላል ያሉን ዶ/ር ደስታ እስከ 10 በመቶ የሚሆን የትልቁ አንጀት ካንሰር ከወላጅ ወደ ልጅ የሚተላለፍ ነው።
የአንጀት ካንሰር ምልክቶች ለማስረዳት የሚከብዱ አንድ አንድ ስሜቶች የሚስተዋሉ ሲሆን በፊንጢጣ የሚወጣ ደም እና ከባድ ድርቀት ምልክቶቹ እንደሆነም አንስተዋል፡፡ አያይዘውም ደረጃው ከፍ እያለ ሲመጣ ወደ ጉበት እና ሳንባ በመሄድ ዓይንን ቢጫ የማድረግ እና እግርን የማሳበጥ እንዲሁም ሳልን እንደሚያመጣም ገልፀዋል።በቶሎ ወደ ጤና ተቋም የሚመጡ ታማሚዎች በቀዶ ህክምና፣ የኬሞና የራድዮ ቴራፒ ህክምና ይሰጣቸዋል የሚሉት ስፔሻሊስቱ ነገር ግን ታማሚዎቹ በቶሎ ወደ ህክምና ተቋም ቢመጡም ካንሰሩ በፍጥነት ተሰራጭቶ የሚገኝበት ወቅት እንዳለም ዶክተር ደስታ ሙሉ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በሰብል አበበ

የእስራኤል ታንኮች የምግብ እርዳታ ለማግኘት በጋዛ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ በፈፀሙት ጥቃት 59 ሰዎች ተገደሉ
የእስራኤል ታንኮች በጋዛ ውስጥ ከጭነት መኪናዎች እርዳታ ለማግኘት ሲሞክሩ በተሰበሰበው ሕዝብ ላይ ተኩሰው ቢያንስ 59 ሰዎች መሞታቸውን የህክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል። ተስፋ የቆረጡ ነዋሪዎች ለምግብ ፍለጋ ሲታገሉ ደም አፋሳሽ ክስተቶች ከተፈጠሩባቸው ሁኔታዎች መካከል አንዱ ነው።
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተጋራ ቪዲዮ በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ በካን ዮኒስ ጎዳና ላይ በደርዘን የሚጠጉ አስከሬኖች እንደነበር ያሳያል። እ.ኤ.አ ከጥቅምት 2023 ጀምሮ በጋዛ በሃማስ ከሚመራው የፍልስጤም ታጣቂዎች ጋር ጦርነት የገጠመው የእስራኤል ጦር በአካባቢው መተኮሱን አምኖ ጉዳዩን እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል።
ሮይተርስ ያነጋገራቸው እማኞች እንደተናገሩት የእስራኤል ታንኮች መንገዱን ከሚጠቀሙ የእርዳታ መኪኖች ምግብ ለማግኘት በማሰብ በዋናው ምስራቃዊ መንገድ በካን ዮኒስ በኩል በተሰበሰቡ በሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ቢያንስ ሁለት የመድፍ ዛጎሎችን ተኩሰዋል። በናስር ሆስፒታል ከሮይተርስ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረገው የዓይን እማኝ አላአ “በድንገት ወደ ፊት እንድንሄድ ፈቀዱልን እና ሁሉም እንዲሰበሰብ አደረጉ፣ ከዚያም መተኮስ ጀመሩ” ሲል ተናግሯል፣ በናስር ሆስፒታል የቆሰሉ ተጎጂዎች መሬት ላይ እና ኮሪደሮች ላይ ወድቀው በቦታ እጦት ሲሰቃዩ ታይተዋል።

በእስራኤል ኢራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ጋር ይከታተሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/e4whZmVDFao?si=xKiZJdAhf3GiQA-g
#ዳጉ_ጆርናል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/e4whZmVDFao?si=xKiZJdAhf3GiQA-g
#ዳጉ_ጆርናል
ባለፉት 11 ወራት በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ ስርቆት የፈፀሙ 24 ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ
አብዛኛው የኢትዮጲያ ኢኮኖሚያዊ እና የማህበራዊ ልማት እንቅስቃሴዎች መሰረት የሚያደርጉት በኤሌክትሪክ ላይ በመሆኑ አስተማማኝ ኤሌክትሪክ ማቅረብ የህልዉናና ልማትነን የማፋጠን ጉዳይ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታዉቋል ።
ባለፋት ወራት በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማትና ኃይል ስርቆት ላይ 239 ወንጀሎች ለፖሊስ ክስ የተመሠረቱ ሲሆን በገንዘብ ሲተመን የ218 ሚሊዮን ብር ኪሳራ በተቋሙ ላይ መድረሱ ተነግሯል ።
ከእነዚህ ከቀረቡ 239 ወንጀሎች ዉስጥ ባለፋት 11 ወራት 24 ግለሰቦች ብቻ ጥፋተኝነታቸዉ ተረጋግጦ ከ4ወር እስከ 10 ዓመት እስራት እንዲቀጡ መወሰኑ ከደረሰዉ ጉዳት አንፃር ወንጀለኞችን ተከታትሎ ከመያዝ እና ለፍርድ ከማቅረብ አንፃር ሰፊ ክፍተት መኖሩን የሚያሳይ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የህግና ስነምግባር ስራ አስፈፃሚ አቶ አበበ ተስፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
የተሟላ የህግ ማዕቀፍ እና የአስፈፃሚ አካላት አደረጃጀት ቢኖርም እነዚህን ወንጀለኞች ተከታትሎ ተገቢዉን ምርመራ በማድረግ በህግ ከማስጠየቅ አንፃር ሰፊ ስራ እንደሚጠይቅ አቶ አበበ አክለዋል ። በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ የሚደርሱ ዉድመቶች ለደንበኞች የቅሬታ ምንጭ እየሆኑ መምጣታቸዉን የገለፁት ስራ አስፈፃሚዉ በተለይም ከፍተኛ የሀይል ማስተላለፊያ መስመሮች አከባቢ ጥቃት ሲደርስ ሰፊ ተደራሽ ህዝብን ስለሚሸፍን የሚኖረዉ ተፅዕኖ ከፍተኛ ነዉ ብለዋል ።
ከሰሞኑ በአማራ ክልል ባህርዳር አከባቢ በሚገኙ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ በደረሰ ዝርፊያ በርካታ ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንደተቋረጠባቸዉ አቶ አበበ ጨምረዉ ለብስራት ተናግረዋል፡፡
በመባ ወርቅነህ

ሰሜን ኮሪያ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን የሩስያ ኩርስክን ግዛት መልሶ ለመገንባት እንደምትልክ አስታወቀች
ሰሜን ኮሪያ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን በሩሲያ በጦርነት የተመሰቃቀለውን የኩርስክ ግዛት መልሶ ለመገንባት እንደምትልክ የሞስኮ የጸጥታ ሃላፊ አስታውቀዋል።ከሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ ኡን ጋር በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ የተነጋገሩት የሩስያ የፀጥታው ምክር ቤት ፀሃፊ ሰርጌ ሾይጉ ቡድኑን “ወንድማማች ረድኤት” ሲሉ ገልጸዋል በማለት የሩሲያ መንግስታዊ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ጎረቤት ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን እቅዱን በፍጥነት አውግዘዋል።ሴኡል በቡኩሏ ይህ እርምጃ የተባበሩት መንግስታት በሰሜን ኮሪያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ መጣስ ነው ስትል ተናግራለች። በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገውን ጦርነት እንድትዋጋ እንደረዱት በሪፖርቱ ወቅት በሁለቱ ሀገራት መካከል ጥልቅ የሆነ ወታደራዊ ትብብር ለወራት እንደነበር መረጃዎች ሲሽከረከሩ ቆይተዋል።
እሮብ እለት ላይ የሩስያ ታስ የዜና ወኪል ሾይጉን ጠቅሶ እንደዘገበው ሰሜን ኮሪያ የኩርስክ ክልልን መልሶ ለማቋቋም የሚረዳ "ግንበኞችን ፣ ሁለት ወታደራዊ ብርጌዶችን ወይም 5,000 ወታደሮች " እንዲሁም 1,000 ፈንጂ አምካኞችን እንደምትልክ በዘገባው ላይ ተገልጿል። "ይህ ከኮሪያ ህዝብ እና መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለአገራችን የተደረገ ወንድማዊ እርዳታ ነው" ሲሉ ሾይጉ መናገራቸውን የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ ያሳያል። የሰሜን ኮሪያ መንግስት መገናኛ ብዙሃንም ስብሰባው ኪም እና ሾይጉ ሌሎች "የረጅም ጊዜ እቅዶችን" ሲወያዩ እንደነበር አክሎ ገልጿል።

ብስኩት ልግዛልሽ በማለት አታሎ የስምንት ዓመት ታዳጊን አስገድዶ የመድፈር ጥቃት የፈጸመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
በምስራቅ ቦረና ዞን ነገሌ ወረዳ አስተዳደር በስምንት ዓመት ታዳጊ ላይ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት የፈጸመው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱ ተገልጿል ።
የምስራቅ ቦረና ዞን ፖሊስ ዋና መምሪያ የሴቶች እና ህጻናት ጉዳይ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ዘውድነሽ አበበ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ተከሳሽ ዮሴፍ ፈጠነ የታዳጊዋ ወላጆች ወደ ስራ መሄዳቸውን ጠብቆ ብስኩት ልግዛልሽ በማለት አታሎ ወደ ራሱ መኖሪያ ቤት በመውሰድ ጥቃቱን እንደፈጸመባት ተጠቁሟል።
ህጻኗ ደም እየፈሰሳት መንገድ ላይ ወድቃ ያገኟት ነዋሪዋች ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ ወደ ህክምና ቦታ ተወስዳ እርዳታ እንድታገኝ መደረጉ ተገልጿል ። ተጎጂዋ ህክምና ከተሰጣት በኋላ ለፖሊስ በሰጠችው መረጃ መሰረት ጥቃቱን የፈጸመባት የ31 ዓመቱ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋል ችሏል።
ፖሊስ አስፈላጊውን በምርመራ በሀኪም እና ከሰዎች በተገኛ መረጃ መሰረት በማጠናከር መዝገቡን ለዓቃቢ ህግ ልኳል ። ዓቃቢ ህግ በወንጀል ህግ ቁጥር 6 /27 በህጻናት ላይ በሚፈጸም የህጻናት የግብረስጋ ድፍረት በደል በመጥቀስ ክስ መስርቷል።
ክሱን ሲከታተል የቆየው የምስራቅ ቦረና ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተለሳሽ የሱፍ ፈጠነ ዕድሜዋ ባልደረሰች ልጅ ላይ አታሎ የመድፈር ጥቃት በመፈጸም ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በአስራ አምስት ዓመት እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ዋና ኢንስፔክተር ዘውድነሽ አበበ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ፑቲን የኢራኑን መሪ ካሜኔይን ለመግደል ስለሚቃጣ ማንኛውም ሙከራ የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ አደረጉ
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እስራኤል ወይም አሜሪካ የኢራንን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኒን ለመግደል ሙከራ ሊያደርጉ ይችላሉ በሚለው ግምት ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ከአለም አቀፍ ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት የጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት የኢራን እና እስራኤል ግጭት ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ግፊት ማድረጋቸውን እንደቀጠሉ ተናግረዋል። በሴንት ፒተርስበርግ ከተካሄደው ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ፎረም ጎን ለጎን ሐሙስ ዕለት ስለ ካሜኒ ለተጠየቁት ጥያቄዎች ሲመልሱ "ከቻልኩ ይህ ለጥያቄዎ በጣም ትክክለኛው መልስ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፤ ስለዚህ ጉዳይ መወያየት እንኳን አልፈልግም ሲሉ ተደምጠዋል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ግጭቱ በኢራን የአገዛዝ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል ሲሉ ተናግረዋል። የእስራኤል ጥቃቶች ከፍተኛ የጦር መሪዎችን እና ከፍተኛ የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ላይ ያነጣጠሩ መሆናቸውም ይታወቃል። መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የኢራን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እንደገለፀው ካለፈው አርብ ጀምሮ የእስራኤል ባደረገችው ጥቃት ቢያንስ 585 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን 239 ንፁሀን ዜጎች መሞታቸው ይታወሳል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዋሽንግተን ካሜኔ ያሉበትን ቦታ ታውቃለች ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል። ምንም እንኳን አሜሪካ እስራኤል በኢራን ላይ የምታደርገውን ጥቃት ልትቀላቀል እንደምትችል ባይገልፁም ዩናይትድ ስቴትስ ለጊዜው እርምጃ እንደማትወስድ ተናግረው ነበር። ፑቲን የኢራን ህዝብ ከመንግስት ጀርባ አንድነቱን እንደቀጠለ ተናግረዋል። "ዛሬ በኢራን ውስጥ በሁሉም የውስጣዊ የፖለቲካ ሂደቶች ውስብስብነት እዚያ እየተከናወኑ እንደሆነ እና በሀገሪቱ የፖለቲካ አመራር ዙሪያ የህዝቡ ውህደት እንዳለ እናያለን" ብለዋል ።