በህገወጥ አደን ምክንያት በባቢሌ መጠለያ የሚገኙ የዝሆኖች ቁጥር ቀንሷል ተባለ
የሰው ሰራሽ ጫናዎችና የህገወጥ አደን ተግባራት በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ላይ አሉታዊ ተፅእኖን እያሳደሩ ይገኛሉ ሲል የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።
ባለስልጣኑ በባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማካሄዱ ተገልጿል።የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ በመድረኩ ላይ ባስተላለፋት መልዕክት የአየር ንብረት ለውጥ ፣የብዝሀ ህይወት ውድመት እና የአካባቢ ብክለት ዓለማችንን በከፍተኛ ሁኔታ እያስጨነቁ ያሉ ችግሮች ናቸው ብለዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያን ጨምሮ አብዛኛዎቹ የጥበቃ ቦታዎች ወደ ከፋ ችግር እየገቡ ያሉት በአንድም በሌላም ከእነዚህ ችግሮች ጋር ተያያዥነት ባላቸው ምክንያቶች እንደሆነ አስረድተዋል።ከዚህ ችግር ለመውጣት ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የመፍትሄ አካል በመሆን የተፈጥሮ ሀብትን በሀላፊነት ሊጠብቅ ይገባል ሲሉ አሳስስበዋል።
በባለስልጣኑ የጥበቃ ቦታዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ አቶ ካሳዬ ዋሚ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ህገወጥ አደንን ተከትሎ በመጠለያው የሚገኙ ዝሆኖች ቁጥር እየቀነሰ መጥቷል።በዚህም የተነሳ ከዚህ ቀደም በመጠለያው ከ3መቶ እስከ ከ4 መቶ በላይ ዝሆኖች ይገኙ እንደነበር ገልፀው በአሁኑ ወቅት ላይ ግን ከ1መቶ 35 በላይ ዝሆኖች ብቻ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
በመሆኑም የፓርኩን ህልውና ለመጠበቅ የጥበቃ ቦታውን ዳር ድንበር እንዴት መጠበቅ ይቻላል በሚለው ዙሪያ በውይይት መድረኩ የቀጣይ ጊዜ የመፍትሄ አቅጣጫ ተቀምጧል ሲሉ አቶ ካሳዬ ጨምረው ለጣቢያችን ገልፀዋል።
በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል

የመንግስት ስራተኛ የሆነው ግለሰብ 100 ሺህ ተቀጣ
በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በእግረኞች መንገድ ላይ በኮድ 4 ተሽከርካሪ ሲሄድ የተገኘ አንድ አሽከርካሪ 100,000 ብር ተቀጥቷል።
ይህ ግለሰብ ህብረተሰቡ የሰጠውን ጥቆማ ተከትሎ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን፣ ከፌደራል ፖሊስ ሲቲዝን ኢንጌጅመንት እና ከአዲስ አበባ ትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር ውሎ ነው ይህ ቅጣት የተላለፈበት።
ጉዳዩን ይበልጥ የሚያስገርመው ደግሞ ተሽከርካሪው የመንግስት ንብረት፣ በተለይም የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ-ፈቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት የሚጠቀምበት መሆኑ ነው።
ይህ የሚያሳየው ህግን መጣስ የሚያስከትለው ቅጣት
* ለመንግስትም ሆነ ለግል፣
* ለግለሰብም ሆነ ለድርጅት
ምንም አይነት ልዩነት እንደማይደረግ ነው።
ምንጭ :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን

ሕይወት ለማዳን ሕይወቱን ያለፈው የእሳት አደጋ ባለሙያ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ
በትላንት ሰኔ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ዕለት በአጋጠመ አደጋ የሰዉን ህይወት ለመታደግ ሲል መስዋዕት የሆነዉ የአደጋ ጊዜ ሰራተኛ የቀብር ስነ-ስርዓት ተፈጸመ።
በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኛ የነበረዉ ዮናታን ገብሬ በትላንትናዉ እለት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በአጋጠመ አደጋ በአደጋ ዉስጥ የነበሩ ሰዎችን ለመታደግ ሲል መስዋዕት ሆኗል።
የቀብር ስነ-ስርዓቱም የኮሚሽኑ ከፍተኛና የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም የኮሚሽን መ/ቤቱ ሰራተኞችና ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት ዛሬ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በቀጨኔ መድሀኒዓለም ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

ፊቤላ ኢንዱስትሪያል በ30 ሚሊየን ብር ወጪ ያስገነባውን የመማሪያ ክፍሎች አስረከበ
በበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ፊቤላ ኢንዱስትሪያል በ30 ሚሊየን ብር ወጪ በቡሬ ከተማ የዕድገት በህብረት መጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያስገነባቸውን 15 የመማሪያ ክፍሎች አስረከበ።
በ1971 ዓ.ም የተመሰረተው ትምህርት ቤቱ፤ በዕድሜ ብዛት የመማሪያ ክፍሎቹ ፈራርሰው ለመማር ማስተማር ሂደት ምቹ አልነበሩም።
የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ አበበ አለማየሁ በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት፤ ባለሀብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ የመማሪያ ክፍሎችን ችግር በመረዳት በአጭር ጊዜ ውስጥ ባለ ሁለት ወለል 15 የመማሪያ ክፍሎች አስገንብተው አስረክበዋል።
የፌቤላ ኢንዱስሪያል ተወካይ ኃላፊ አቶ ዳዊት ገ/ስላሴ በበኩላቸው፤ ፊቤላ ኢንዱስትሪያል በከተማዋ ከፈጠረው የሥራ እድልና የቴክኖሎጂ ሽግግር በተጨማሪ ማህበራዊ ግዴታውን እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ለዚህም የቡሬና አካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ ከ200 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ወጭ አድርጓል ነው ያሉት።
የዕድገት በህብረት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ 30 ሚሊየን ብር ወጪ ማድረጉን ገልጸው፤ ለሁሉም ክፍሎች ደረጃውን የጠበቀ ወንበርና ጠረጴዛ አሟልቷል ብለዋል።
በላይነህ ክንዴ ግሩፕ በፋውንዴሽኑ አማካኝነት በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ባለፉት አራት ዓመታት ከ900 ሚሊየን ብር በላይ ለማህበራዊ ኃላፊነት ወጪ አድርጓል።
የፍጻሜ ምዕራፍ ላይ ለሚገኘው የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ቀሪ ሥራዎች ማጠናቀቂያ የሚውል ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደርጓል።

ኔታንያሁ ኢራን ለፈፀመችው የሚሳኤል ጥቃት 'ከባድ ዋጋ' ትከፍላለች አሉ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የኢራን የሚሳኤል ጥቃት በቢየር ሼቫ በሚገኘው የእስራኤል ሶሮካ ሆስፒታል ላይ ጉዳት ማድረሱን ተከትሎ "ከባድ ዋጋ እንደምትከፍል" ዝተዋል።
"ዛሬ ጠዋት የኢራን አሸባሪ አምባገነኖች በቢየር ሼቫ በሚገኘው በሶሮካ ሆስፒታል እና በሀገሪቱ በሚገኙ ሲቪሎች ላይ ሚሳይሎችን ተኩሰው ጉዳት አድርሰዋል" ሲሉ ኔታንያሁ በኤክስ ገፃቸው ላይ በለጠፉት ጽሑፍ ያስታወቁ ሲሆን "በቴህራን ውስጥ ያሉ አምባገነኖች ከባድ ዋጋ እንዲከፍሉ እናደርጋለን" ሲሉም አክለዋል።
የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካዜም ጋሪባባዲ በበኩላቸው አሜሪካ ቀጥተኛ ወታደራዊ ጣልቃገብነት እንዳታደርግ ሌላ ተጨማሪ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።
ጋሪባባዲ ለሮይተርስ የዜና ወኪል በሰጡት አስተያየት ኢራን ግጭቱ እንዲስፋፋ እንደማትፈልግ ነገር ግን አስፈላጊ ከሆነ እርምጃ ለመውሰድ እና ለአጥቂዎች ትምህርት ለመስጠት ዝግጁ ናት ብለዋል። የኢራን ወታደራዊ ውሳኔ ሰጪዎች "በጠረጴዛው ላይ ሁሉም አስፈላጊ አማራጮች" አሏቸውም ብለዋል።
በሚሊዮን ሙሴ

ግሎው ኢትዮ-ቱርኪዬ የሚዲያ ባለሙያ ሊያ ሳሙኤልን በ3.5 ሚሊየን ብር ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ
ግሎው ኢትዮ-ቱርኪዬ አጠቃላይ የጸጉር ንቅለ ተከላና የቆዳ ህክምና ማዕከል እና የሚዲያ ባለሙያ ሊያ ሳሙኤል አብረው መስራት የሚያስችላቸውን የፊርማ ስነ ስርዓት አከናውነዋል፡፡
የፊርማ ስነ ስርዓቱ የተከናወነው ሊያ ሳሙኤል፣ ግሎው ኢትዮ-ቱርኪዬ የሚሰራቸውን ስራዎች ህዝብ ዘንድ እንዲደርሱ እና እንዲተዋወቁ የብራንዱን አምባሳደርነት እንድትወክል ሲሆን የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ጨምሮ የተለያዩ ምርቶቹን በተለያዩ መንገዶች የምታስተዋውቅም ይሆናል፡፡
የሚዲያ ባለሙያ ሊያ ሳሙኤል ከግሎው ኢትዮ-ቱርክዬ የ3.5 ሚሊየን ብር ስምምነት እንደፈፀመች በተለይም ለብስራት ሬድዮ ተናግራለች።አሁን ላይ ለተለያዩ የጤና ምርመራ እና ህክምናዎች የጸጉር ንቅለ ተከላ እና ከውበት ጋር የተያያዙ ህክምናዎችን ጨምሮ ከሀገር ውጪ መጓዝ በአለም አቀፍ ደረጃ እያደገ የመጣ ክስተት ሲሆን ቱርክ ለእንደዚህ አይነት የህክምና አይነቶች ቀዳሚ መዳረሻ ሆናለች።
ግሎው ኢትዮ-ቱርኪዬ አጠቃላይ የጸጉር ንቅለ ተከላና የቆዳ ህክምና ማእከል ይህንን ክፍተት ለመሙላት እና በሀገር ውስጥ መሰል አገልግሎቶችን ለመስጠት ሁሉን አቀፍ፣ በአንድ ማእከል ብቻ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የቆዳ እንክብካቤ፣ የጸጉር ንቅለ ተከላ፤ የዋግምት ህክምና፤ የሰውነት ቅርጽን ማስተካከል እንዲሁም ከውበት ጋር የተያያዙ የውበት መጠበቂያ ፕሮዳክቶችን ከቱርክ በመጡ እንዲሁም ቱርክ ሰልጥነው በመጡ ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ለማቅረብ አላማውን አድርጎ የተነሳ ማእከል ነው።
ግሎው ኢትዮ-ቱርኪዬ አጠቃላይ የጸጉር ንቅለ ተከላና የቆዳ ህክምና ማዕከልን ሲቋቋም ዋነኛ አላማው ከፍተኛ ችሎታ ባላቸው ባለሙያዎች፣ የላቀ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የእያንዳንዱን ደንበኛ ልዩ ፍላጎቶች በማሟላት ደንበኞች በራስ መተማመን፣ ውበት እና ምቾት እንዲሰማቸው በሚያስችላቸው አጠቃላይ የውበት፣ የፀጉር ንቅለ ተከላ እና የቆዳ እንክብካቤ መፍትሄዎች አማካኝነት መፍትሄ መስጠት እና የውጭ ምንዛሬን ከማዳን ባሻገር ሰዎች የትም ሳይሄዱ ሀገራቸው ላይ ውጪ ሀገር ሄደው የሚያገኟቸው የህክምና አገልግሎት እዚሁ ሀገራቸው ላይ እንደ አማራጭ ማቅረብ ነው፡፡
ሊያ ሳሙኤል እውቅ የማስታወቂያ ባለሙያ፤ ታዋቂ የቴሌቭዥን ፕሮግራም አቅራቢና የሶሻል ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪ በመሆኗ ግሎው ኢትዮ-ቱርኪዬ አጠቃላይ የጸጉር ንቅለ ተከላና የቆዳ ህክምና ማዕከልን እንድታስተዋውቅ እንደተመረጠች ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቭዥን ሰምቷል።
በሰላማዊ ነጋሲ

ወላይታ ሶዶ ከተማ የ8 ዓመት ህጻን አስገድደው ከደፈሩ በኋላ ገድለው የሰቀሏት ሁለት ግለሰቦች በእስራት ተቀጣ
በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ፋና ወንባ ቀበሌ የአስገድዶ መድፈር እና የግድያ ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች በእስራት መቀጣታቸው የከተማው ፖሊስ አስታወቀ።
ተከሳሾች ዳዊት ሻንቆ እና ታምራት ኦሳ የተባሉ ሲሆን የ8 ዓመት ህጻን የሆነችውን መሳይ አስናቀን ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከአባቷ ቤት አታለው ወደ ጫካ በመውሰድ አስገድደው ከደፈሩ በኋላ ገለው 'ራሷን ያጠፋች ለማስመሰል ጎረቤት በሚገኝ ባዶ ቤት በማስገባት አስክሬኗን በእንጨት ላይ በመስቀል ከአከባቢው መሠወራቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ፖሊስ ከአከባቢው ማህበረሰብና ከመንግስት አካላት ጋር በመሆን ባደረጉት ብርቱ ክትትል ለ4 ወራት ያህል ከተሰውሩበት መያዛቸው ተገልጿል።በፖሊስ የተጣራው የምርመራ መዝገብ የደረሰው የወላይታ ዞን ዐቃቤ ህግ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክሱን ያቀርባል።
የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተከሳሾች የቀረበባቸውን ክስ በአሳማኝ ሁኔታ መከላከል ባለመቻላቸው ጥፋተኛ በማለት ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተከሳሽ ዳዊት ሻንቆ እና ታምራት ኦሳ በተባሉ በእነዚህ ግለሰቦች ላይ የዕድሜ ልክ ጽኑ አስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በሳምራዊት ስዩም

የእስራኤል ጦር የአራክ ሬአክተር ማጥቃቱን አረጋገጠ
የእስራኤል ጦር ተዋጊ ጄቶች የአራክ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫን ጨምሮ በደርዘን የሚቆጠሩ የኢራን ጣቢያዎችን በአንድ ሌሊት ማጥቃቱ ገልፆል። ጦሩ በተለይ "በፕሉቶኒየም ምርት ውስጥ ቁልፍ አካል የሆነውን የማብላያ ኮር መዋቅር" ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈፀሙ ገልፆል።
በናታንዝ የሚገኘውን "የኑክሌር ጦር መሳሪያ ልማት ጣቢያ" ለባለስቲክ ሚሳኤሎች የሚያስፈልጉ አካላትን የሚያመርቱ በርካታ ፋብሪካዎችን መምታቱም ተናግሯል።
የአራክ የውሃ ተቋም ከቴህራን በስተደቡብ ምዕራብ 190 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ተቋም ሲሆን በ2000ዎቹ መጀመሪያ ላይ ግንባታው የተጀመረ የኢራን ሰፊው የኒውክሌር ፕሮግራም አካል ነው።በፍጥነት ጉልህ የሆነ አለምአቀፍ ትኩረትን የሳበ ነበር።
ቦታው የከባድ ውሃ ማምረቻ ፋብሪካን እና የ IR-40 ሬአክተርን ያካትታል። የከባድ ውሃ ልከኝነት ለምርምር፣ አይሶቶፕ ለማምረት እና ፕሉቶኒየምን እንደ ተረፈ ምርት ለማምረት ያስችላል። የተባበሩት መንግስታት፣ የአውሮፓ ህብረት እና ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ አራክ ለኢራን የፕሉቶኒየም መንገድና የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ሊሰጥ ይችላል በማለት ስጋታቸውን ያለማቋረጥ ሲገልፁበት የቆዩ ተቋም ነው።
እ.ኤ.አ. በ 2015 የጋራ አጠቃላይ የድርጊት መርሃ ግብር (JCPOA) ፣ ኢራን ሪአክተሩን ለሰላማዊ አጠቃቀም እና የፕሉቶኒየም ምርትን ለመገደብ ተስማምታለች።

ባለፋት ዘጠኝ ወራት በአማራ ክልል በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ ለይስማ ንጉስ ሙዚየም የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ማሟላት አልተቻለም ተባለ
ባለፋት ዘጠኝ ወራት በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ለሚገኘው ይስማ ንጉሥ ቤተ መዘክርቅርሶችን ለማደራጀት የሚስፈልጉ ግብዓትን ለማሟላት በእቅድ ተይዞ እንደነበር የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።
የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አበበ እምቢአለ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት ለሙዚየሙ ግብአት ለማሟላት በእቅድ የተያዘ ቢሆንም በአካባቢው ያለው የፀጥታ ችግር በቦታው ተገኝቶ ሙዚየሙ ያለበትን ደረጃ ገምግሞ መስራት አልተቻለም ፡፡
ነገር ግን የቅርስ ማሰባሰብ ስራ ለመስራት አንድ ጊዜ መድረክ በመፍጠር በደሴ ከተማ ውይይት መካሄዱን የገለፁት አቶ አበበ በቀጣይ በሀገር ደረጃ የሚመለከታቸውን ባለድርሻና አጋር አካላት ያሳተፈ መድረክ ለማካሄድ ታቅዷል ብለዋል።
ይህን እውን ለማድረግ የሚያስችች ቢጋር ተዘጋጅቶ ፀድቋል ሲሉ ተናግረው ከዚህ መድረክ በኋላ ቅርስ በማሰባሰብ የተለያዩ ግብዓቶችን የማሟላት ሰራ ይሰራል በማለት ጨምረው ለጣቢያችን ገልፀዋል፡፡25 ሚሊዮን ብር ወጪ ተመድቦለት የውጫሌ ውልን በሚዘክረው በታሪካዊው ቦታ (ይስማ ንጉስ) አካባቢ ሙዚየሙ መገንባቱ ይታወሳል።

ኢራን መሳሪያዋን ተጠቅማ አጥቂዎችን ትምህርት ከማስተማር ወደኃሏ እንደማትል ዛተች
የኢራን ፕሬዝዳንት እያንዳንዱን የመንግስት አካል "ኢራንን እንዲያገለግል" በማህበራዊ ሚዲያ ድህረ ገጽ ላይ ባሰፈረት መልዕክት መመሪያ ሰጥተዋል። "ሁሉም ሚኒስቴሮች እና የመንግስት ኤጀንሲዎች ኢራንን በሙሉ ሃይላቸው እና ገንዘባቸው እንዲያገለግሉ ተልእኮ ተሰጥቷቸዋል።ከትዕግስት እና ድጋፍ ጋር ምንም አይነት አገልግሎት ሳያስቀሩ መስጠት አለባቸው ሲሉ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዝሽኪያን ተናግረዋል። "በፈጣሪ ቸርነት እና በመተሳሰብ እነዚህን አስቸጋሪ ቀናት እናልፋለን" በማለት ፔዝሽኪያን አክለው ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል በኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ የምታደርገውን ጥቃት ለመቀላቀል በሚያስቡበት በዚህ ወቅት የኢራን ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሜሪካን አስጠንቅቀዋል። የኢራን መንግስት ሚዲያ ካዜም ጋሪባባዲ እንደዘገበው “አሜሪካ እስራኤልን ለመደገፍ በንቃት ጣልቃ መግባት ከፈለገች ኢራን መሳሪያዋን ተጠቅማ አጥቂዎችን ትምህርት ከማስተማር እና ራሷን ከመከላከል ውጭ ሌላ አማራጭ አይኖራትም ብለዋል።
"ለአሜሪካ የምንሰጠው ምክረ ሀሳብ የእስራኤልን ጥቃት ለማስቆም ካልፈለጉ ቢያንስ ራሳቸውን ችለው እንዲቆሙ ነው" በማለት የኢራን "ወታደራዊ ውሳኔ ሰጪዎች በጠረጴዛው ላይ ሁሉም አስፈላጊ አማራጮች አሉ" ብለዋል ። የሩሲያእ ኢንተርፋክስ የዜና ወኪል የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭን ጠቅሶ እንደዘገበው በኢራን እና በእስራኤል ግጭት ውስጥ በአሜሪካ የሚፈጽመው ማንኛውም ጣልቃገብነት “አስፈሪ የሆነ የእርስ በእርስ ግጭት” ይፈጥራል ብለዋል። ትራምፕ አሁንም ጣልቃ በመግባት አማራጮችን እየገመገሙ እንደሚገኝ ተመላክቷል።
በስምኦን ደረጄ