እናት ባንክ በአካታች የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ቀዳሚ ባንክ ሆና ተመረጠች
እናት ባንክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር ባካሄዱት የአካታች የባንክ አገልግሎት የምዘና መስፈርት ከሀገሪቱ ባንኮች ቀዳሚ ሆና በመመረጥ እውቅና እንደተሰጣት ብስራት ሰምቷል።
እናት ባንክ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጎልብት ሁሉን አቀፍ የሴቶች አካታች የባንክ አሰራርን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፁት የባንኩ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዓለም ባንክ የሥርዓተ-ፆታ ፈጠራ ጋር በመተባበር በአካሄዱት የ2025 የባንኮች የስርዓተ ፆታ አካታችነት ምዘና መስፈርት መሰረት እናት ባንክ የተሻለ ስራ በመስራቱ ከ30 የኢትዮጵያ ባንኮች የመጀመሪያና ብቸኛ ትራንስፎርሚሽናል ባንክ መባሉንም ተገልፆል፡፡
ከ55 በመቶ በላይ የባንኩ የቦርድ አባላት ሴቶች መሆናቸው እንዲሁም ከ22 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ስራ ፈጣሪ ሴቶች 1.4 ቢሊዮን ብር ካለዋስትና በማበደር የራሳቸውን ስራ እንዲጀምሩ ማስቻሏ ከተመረጠችባቸው ተግባራት ተጠቃሽ ናቸው ተብሏል።
እናት ባንክ ከምስረታዋ አንስቶ ሴቶች ወደ ተቋሟ ከፍተኛ አመራርነት ሚና እንዲመጡ በልዩ ሁኔታ እየሰራች መሆኑ የተነገረ ሲሆን ባንኳ ካላት ከ25 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች ውስጥ ከ15 ሺህ በላይ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውም ተገልጿል።
በቀጣይ እናት ባንክ በመላ አገሪቱ የቅርንጫፍና የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ተደራሽነቱን በማስፋት አዳዲስ አካታች የባንክ አሰራሮችን በመተግብር በአካታች የባንክ አሰራር የተገኙ ውጤቶችን ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተነግሯል።
በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል

የኢራን ፔዝሽኪያን እስራኤል ማጥቃት ከቀጠለች ኢራን የበለጠ ጠንካራ ምላሽ እንደምትሰጥ ተናገሩ
የኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ግጭቱን ለማስቆም ብቸኛው መንገድ እስራኤል የምታደርገውን የአየር ጥቃት እንድታቆም ነው ብለዋል።በኢራን ሚዲያ በተላለፈዉ የፕሬዝዳንቱ መግለጫ "ሁልጊዜ ሰላም እና መረጋጋትን እንከተላለን" ብለዋል::"አሁን ባለው ሁኔታ ዘላቂ ሰላም የሚኖረው የጽዮናዊው ጠላት ጦርነቱን ካቆሙ እና የሽብር ቅስቀሳዎቹን ለማስቆም ጠንካራ ዋስትና ከሰጡ ብቻ ነው።"ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ፔዝሽኪያን "ይህን አለማድረግ ግን ከኢራን የበለጠ ኃይለኛ እና ጸጸት የሚያስከትክ ምላሽ እንደሚሰጥ" አስጠንቅቀዋል፡፡
በሌላ በኩል የኢራን የኒውክሌር ምርምር ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤትን ጨምሮ ከ60 በላይ የሚሆኑ የጦር አውሮፕላኖችን በቴህራን እና በሌሎች ቦታዎች በደርዘን የሚቆጠሩ ኢላማዎችን መምታታቸውን የእስራኤል ጦር አስታዉቋል።በደቡባዊ እስራኤል ቤርሳቤህ ከተማ የቴክኖሎጂ ፓርክን በመምታት የኢራን ሚሳኤል ቀደም ብሎ በተፈጸመ ጥቃት ህንጻዎች ላይ ጉዳት አድርሷል። የሞተ ሰው ባይኖርም ሰባት ሰዎች ግን በጉዳት ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።
በቴህራን ዩኒቨርሲቲ የአለም አቀፍ ግንኙነት ፕሮፌሰር ፎአድ ኢዛዲ ለአልጀዚራ በጄኔቫ ስለሚካሄደዉ ጉባኤ አስመልክቶ እንደተናገሩት የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ምንም አይነት ድርድር ለማድረግ እንዳልተዘጋጁ ግልፅ ነው የእስራኤል ጥቃት በመቀጠሉ የተነሳ ነዉ ብለዋል፡፡"ሲደራደሩ መስጠት እና መቀበል ነው" ነገር ግን በቴህራን እና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ቦምቦች እየተጣሉ ኢራን በዚያ የመስጠት እና የመቀበል ዘይቤ ውስጥ መሳተፍ አትችልም ሲሉ ተደምጠዋል ።
አራግቺ በጄኔቫ "ከድርድር የተለየ ንግግር ያደርጋሉ" በማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአውሮፓ ባለስልጣናትን ከኢራን የፈለጉትን አይነት ስምምነት ማለትም የባለስቲክ ሚሳኤሎችን መተው የሚባለዉ ነገር አይፈጠርም፤ ምክንያቱም ኢራን መከላከያ የሌላት መሆን ስለማትችል ነዉ ብለዋል፡፡"ኢራን የባሊስቲክ ሚሳኤሎች ባይኖሯት ኖሮ ዛሬ ቴህራን ውስጥ የእስራኤል እና የአሜሪካ ወታደሮች ታገኛላችሁ ብዬ አስባለሁ" ሲሉ አክለዋል፡፡
በስምኦን ደረጄ

በምዕራብ አርሲ ዞን በቁጥጥር ስር የዋለ 99 ኩንታል ካናቢስ እና ኮኬን በትላንትናው ዕለት ተወገደ
በምዕራብ አርሲ ዞን ሻላ ወረዳ በድብቅ ተከማችቶ ሲጓጓዝ የነበረ 99 ኩንታል ካናቢስና ኮኬን የተባለ አደገኛ እፅ የአከባቢው ማህበረሰብ በተገኘበት እንዲወገድ መደረጉን የምዕራብ አርሲ ዞን ፖሊስ ዋና መምሪያ ገልጿል።
የዞኑ ፖሊስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ቶለሣ መልካ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በምዕራብ አርሲ ዞን በሚገኙ አራት ወረዳዎች ሻሸመኔ ፣ሻላ ፣ነገሌ አርሲ እና ወንዶ ገነት አካባቢዎች አደንዛዥ እፅን በድብቅ ከቦቆሎ እና ማሽላ አዝርዕት ጋር ቀላቅሎ የመዝራት ድርጊቶች አሁንም ሊቆሙ አለመቻላቸውን ተናግረዋል።
ይህንን ሕገወጥ ተግባር ለመቆጣጠር ከተለያዩ የፀጥታ አካላት እና ከማህበረሰቡ ጋር በጥምረት እየተሠራ እንደሚገኝ ገልፀዋል። በዚህም የተነሳ በሻላ ወረዳ በድብቅ የተከማቸና ሊጓጓዝ ያለ 99 ኩንታል ካናቢስ እና ኮኬን የተባሉ አደገኛ እፅች በቁጥጥር ስር ውለዉ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም የአካባቢው ማህበረሰብ በተገኙበት መወገዱ ተገልጿል።
በዞኑ በየጊዜው በድብቅ የሚመረተውን አደንዛዥ እፅ በመደለል ፣በመሸጥ እና በማጓጓዝ ግንባር ቀደም ተዋናይ የሆኑ ደላሎች እና ነጋዴዎች አርሶአደሮችን በጥቅም በመደለል ከአዝዕርት ጋር ቀላቅለዉ እንዲዘሩ እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
ፖሊስ የችግሩን አሳሳቢነት ተረድቶ በሀሺሽ አምራቾች፣አዘዋዋሪ ነጋዴዎች እና ደላሎች ላይ አስፈላጊውን የፍትህ ውሳኔ በማሰጠት የህግ የበላይነትን እያስከበረ ይገኛል ሲሉ ኮማንደር ቶሎሣ አክለዋል። ከዚህ ቀደም አደገኛ እፅ በማሳው ሲያመርት የተያዘ አርሶአደር ማሳዉ እንዲወረስ ተደንግጎ የነበረ ቢሆንም ህብረተሰቡ በድብቅ ጓሮ ውስጥ ከሰብል ጋር ቀላቅሎ ማምረት መቀጠሉን መረጃዎች ያሳያሉ።
በመባ ወርቅነህ

የአያቶላ አሊ ካሜኔይ ከፍተኛ አማካሪ ሻምካኒ እያገገሙ መሆኑ ተነገረ
የኢራን መንግስት ሚዲያ ከሳምንት በፊት እስራኤል ባደረሰችው ጥቃት ክፉኛ ቆስለው ስለነበሩት የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሜኒ የቅርብ አማካሪ አሊ ሻምካኒ የህክምና ሁኔታ ወቅታዊ መረጃ ሰጥቷል። የታስኒም የዜና ወኪል እንደዘገበው ሻምካኒ ምስጋና ለሐኪሞች ሌት ተቀን ጥረት አሁን በተረጋጋ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። "በህይወት አለው እናም እራሴን ለመሰዋት ለማድረግ ዝግጁ ነኝ" ሲለ ለከፍተኛ መሪው እና ለኢራን ህዝብ በላከት መልእክት አስታውቀዋል።
በሌላ በኩል በቴህራን የሚገኙ ኢምባሲዎችን በጊዜያዊነት መዝጋታቸውን ሀገራት እያስታወቁ ይገኛል። አውስትራሊያ፣ ስሎቫኪያ እና ቼክ ሪፐብሊክ በቴህራን የሚገኙ ኤምባሲዎቻቸውን የፀጥታ ሁኔታ እያሽቆለቆለ በመሄዱ ስራቸውን አቋርጠው እንደሚገኙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው ይፋ አድርገዋል። የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔኒ ዎንግ መንግስታቸው ሁሉም የአውስትራሊያ ባለስልጣናት ከቴህራን ኤምባሲ እንዲወጡ መመሪያ መስጠቱን ገልፀው አምባሳደሩ በአካባቢው እንደሚቆዩ ተናግረዋል ።
በኢራን ውስጥ ያሉ ሁሉም የአውስትራሊያ ዜጎች በሰላም እንዲወጡ ምክር ለግሰዋል። ስሎቫኪያ እና ቼክ ሪፐብሊክ በቴህራን የሚገኙትን ኤምባሲዎቻቸውን በጊዜያዊነት መዝጋታቸውን አስታውቀዋል።ጀርመን እና የአውሮፓ አጋሮቿ በኒውክሌር እና በሚሳኤል ፕሮግራሞቿ ላይ ማረጋገጫ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነች ከኢራን ጋር ለተጨማሪ ውይይት ክፍት መሆናቸውን የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታውቀዋል።

በመተማ ከተማ ለምን በከብቶችህ ፍየሎቼን ታስረግጥብኛለህ በማለት የ14 ዓመት ታዳጊ ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
ተከሳሽ ጋሻው ካሴ የተባለው ግለሰብ ሰውን ለመግደል በማሠብ ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ/ም በግምት ከቀኑ 12:00 ሰዓት ሲሆን በመተማ ዮሐንስ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 03 እና 01 መካከል በሚገኝና ልዩ ስሙ ማንጎ አትክልት ቦታ ተብሎ ከሚጠራው አከባቢ ላይ እድሜው 14 አመት የሆነውን ታዳጊ ሟች ተመስገን ጋሻው ላላዬይ የግድያ ወንጀል በመፈፀም ተከሷል።
ወንጀል ፈፃሚው ግለሰብ "ለምን በከብቶች ፍየሎቼን ታስረግጥብኛለህ" በማለት ወደ ፀብ የገባ ሲሆን ተጣልተው ከተገላገሉ በኋላ ይዞት በነበረው ፈራድ 2 ጊዜ ጭንቅላቱን በመምታት የግድያ ወንጀል መፈፀሙ ተገልፆል።
ይህን ተከትሎም የምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች የስራ ሂደት ዐቃቤ ህግ በወንጀል ህግ ቁጥር 539 ንዑስ አንቀፅ /1/ሀ መሠሰረት በከባድ የግድያ ወንጀለ የከሰሰው ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የከሳሽን ማስረጃ ከሠማ በኋላ በወንጀል ህግ ቁጥር 540 መሰረት በተራ የሰው መግደል ወንጀል ክሱን በመቀየር እንዲከላከል ብይን በመስጠቱ የመከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርብ ቢነገረውም ሊያቀርብ ካለመቻሉም በተጨማሪ ምስክር ማቅረብ አልፈልግም በማለት ፈርሞ ያስገባ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መርምሮ ተከሳሽ ላይ የጥፋተኞነት ውሳኔ አስተላልፏል።
ፍርድ ቤቱ ሰኔ 2 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት በመቀበል ተከሳሽን ያስተምራል ሌሎችን መሰል ድርጊት ከመፈፀም ያስጠነቅቃል በማለት እጁ ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ በሚታሰብ የ12 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ማስተላለፉን ብስራት ከምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ የልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች የስራ ሂደት ያገኘው መረጃ ያሳያል።
በሰብል አበበ

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቻይና የዩናይትድ ኪንግደም የጦር መርከብ በታይዋን ሰርጥ ላይ የሚያደርገውን ፓትሮል ተቸች
የቻይና ጦር በቅርቡ የብሪታንያ የጦር መርከብ በታይዋን ባህር ማለፍ የጀመረችው “ሰላምና መረጋጋትን የሚጎዳ” “ሆን ተብሎ የሚቀሰቅስ” ረብሻ ነው ብሎታል። የብሪታኒያው ሮያል ባህር ሃይል በበኩሉ የኤችኤምኤስ ስፓይ ጥበቃ እሮብ እለት ለረጅም ጊዜ ሲታቀድ የቆየው የስምሪት አካል እና በአለም አቀፍ ህግ መሰረት የተደረገ ነው ብሏል። ጥበቃው በአራት ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያው በብሪታንያ የባህር ኃይል መርከብ የተደረገ ሲሆን የዩናይትድ ኪንግደም አገልግሎት አቅራቢዎች ቡድን ለበርካታ ወራት የሚቆይ ስምምነት ነው።
ቻይና ታይዋንን እንደግዛቷ ትቆጥራለች። ራሷን ከቻይና ነጥላ የምታየው ታይዋን ግን ይህንኑ ውድቅ ታደርጋለች። ደሴቱን "እንደገና ለማዋሃድ" የኃይል እርምጃ ግን ቻይና እንደማትወስድ ገልጻለች።የቻይና የባህር ሃይል ቃል አቀባይ እንግሊዝ የኤችኤምኤስ ስፓይን ጉዞን “በአደባባይ ማሞካሸቷን” ተችተው የእንግሊዝ ድርጊት “የህግ መርሆዎችን ማዛባት እና ህዝቡን ለማሳሳት የሚደረግ ሙከራ ነው” ብለዋል። "እንዲህ ያሉት እርምጃዎች ሁኔታውን የሚያውኩ እና በታይዋን የባህር ወሽመጥ ላይ ሰላምና መረጋጋትን የሚጎዱ ሆን ተብሎ የሚደረጉ ቅስቀሳዎች ናቸው" ብለዋል።
የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ የዩናይትድ ኪንግደም ፓትሮን በታይዋን የባህር ዳርቻ የመርከብ ነፃነትን ያስጠበቀ ተግባር ሲል አሞካሽቷል። የአሜሪካ የጦር መርከቦች በባህር ዳርቻው ላይ የመርከብ ነጻነትን እንቅስቃሴን አካሂደው እንደነበር ይታወሳል። ለመጨረሻ ጊዜ እንዲህ አይነት ጉዞ በእንግሊዝ የባህር ኃይል መርከብ የተካሄደው እ.ኤ.አ. በ2021 የጦር መርከብ ኤችኤምኤስ ሪችመንድ ወደ ቬትናም ነበር። በወቅቱ ይህንኑ እንቅስቃሴ በተመሳሳይ መልኩ ቻይና ወታደሮቿን በመላክ መርከቧን እንድትከታተል አድርጋለች።

በእስራኤል ኢራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ጋር ይከታተሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/d45g1548L5Y?si=lQAUN_d-D8cTHNQZ
#ዳጉ_ጆርናል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/d45g1548L5Y?si=lQAUN_d-D8cTHNQZ
#ዳጉ_ጆርናል
አሰሪያችን ለሻወር በሰጣቸው ገንዘብ መልሱ የኔ ነው በሚል አለመግባባት ጎደኛውን የገደለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
በደቡብ ክልል ጌድዮ ዞን ተወልዶ ያደገው የሱፍ ገነሞ ከፀጋዬ በዳኔ ጋር በስራ ምክንያት የተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውረዋል።
ለስራ ሁለቱ ወጣቶች ምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 01 ውስጥ ሃርሜ ሬስቶራንት የተባለ ምግብ ቤት በአስተናጋጅነት ተቀጥረው መስራት መጀመራቸው የዶዶላ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ዋና ክፍል ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አብድላዚዝ አህመድ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።የሱፍ እና ፀጋዬ በሬስቶራንቱ የአስተናጋጅነት ስራ እየሰሩ እያለ ሚያዝያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ተስተናጋጅ ቀለል ሲል የካፍቴርያው ባለቤት የሱፍ እና ፀጋዬ ሻወር እንዲወስዱ በማለት አንድ መቶ ብር በፀጋዬ አማካይነት የሰጧቸው መሆኑ ተነግሯል።
ሁለቱም የሻወር አገልግሎት ከተጠቀሙ በኋላ ለእያንዳዳቸው ሃያ ሃያ ብር በአጠቃላይ አርባ ብር ከፍለዉ ቀሪ ስልሳ ብር ፀጋዬ ይቀበልና ወደ ኪሱ ያደርጋል። በዚህ ጊዜ የሱፍ መልሱን አምጣ እንጂ ይለዋል ጸጋዬ የምን መልስ ለኔ የተሰጠ ነው በሚል ግጭት ውስጥ መግባታቸውን የሱፍ ለፖሊስ በሰጠው ቃል አረጋግጧል።በዚህም ንዴት ውስጥ በመግባት ፀጋዬን በቦክስ ጆሮ ግንዱ ላይ እንደመታውና ወዲያው በጆሮው ደም እንደፈሰሰ ይወድቃል።
በአካባቢው የነበሩ ሰዎች የወደቀውን ፀጋዬን አንስተው ወደ ጤና ጣቢያ የወሰዱት ቢሆንም የደረሰበት አደጋ ከፍተኛ በመሆኑ ህይወቱ አልፏል።ፖሊስም የደረሰውን አደጋ መረጃ ደርሶት የድርጊቱን ፈፃሚ በመከታተል ከካፍቴርያው ሻንጣውን ይዞ ለመውጣት እና ለማምለጥ ሲሞክር በቁጥጥር ስር ያውለዋል።ፖሊስም የምርመራ መዝገቡን በተለያዩ ማስረጃዎች በማጠናከር ለዓቃቢ ህግ የላከ ሲሆን ዓቃቢ ህግ በወንጀል ህግ ቁጥር 539/2 በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ መስርቷል።
ክሱን ሲከታተል የቆየው የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ የሱፍ ገነሞ ሰው ለመግደል አስቦ፣አቅዶ እና ተዘጋጅቶ፣ የፈፀመው ተግባር ባይሆንም በወቅቱ ባለመረጋጋት የሰው ህይወት ላይ አደጋ አድርሶ ህይወት በማጥፋቱ በማስረጃ በመረጋገጡ ጥፋተኛ ተብሎ ሰኔ 10ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በአስራ አምስት ዓመት እስራት እና በስድስት ሺህ ብር እንዲቀጣ የወሰነበት መሆኑን የዶዶላ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር አብድላዚዝ አህመድ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በኤደን ሽመልስ