በኢትዮጵያ ህገወጥ የእንስሳት ዝውውርን ማስቆም አልተቻለም ተባለ
ኢትዮጵያ የዱር እንስሳትና የእፅዋት ሀብት ያላት ሀገር ብትሆንም ይህ ሀብቷ ግን በበርካታ ችግሮች ውስጥ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።በባለስልጣኑ የዱር እንስሳት ህገወጥ ዝውውር ቁጥጥር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳንኤል ጳውሎስ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የዱር እንስሳትና የእፅዋት ሀብትን ለመጠበቅ በመጠለያና ፓርኮች አካባቢ የቁጥጥር ስራን የሚሰሩ ሰራተኞች ጥቃት እንዳይፈፀም የሚያስችል ስራን ያከናውናሉ።
ነገር ግን በእነዚህ ስፍራዎች ከህገወጥ ሰፈራ አንስቶ ህገወጥ የአደን ተግባራት ጭምር ይስተዋላሉ። እነዚህ ሁሉ በተፈጥሮ ሀብቱ ላይ ከተደቀኑ ችግሮች መካከል ተጠቃሽ ናቸው ያሉት አቶ ዳንኤል የዱር እንስሳት ከነ ህይወታቸው ጭምር እየተያዙ በህገወጥ መልኩ ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ እንደዚሁም ከሀገር አልፈው ወደ ውጪ የሚዘዋወሩበት ሁኔታ መኖሩን ገልፀዋል።እንስሳቱ ለምግብነት፣ለጌጣጌጥ መስሪያነትና ለሌሎች አላማዎች በሚል በህገወጥ መልኩ እንደሚዘዋወሩ አቶ ዳንኤል ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
የዱር እንስሳትን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም ተገቢውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማግኘት የቁጥጥር ስራዎች መጠናከር እንደሚገባቸው ተገልጿል።ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በህገ ወጥ የዱር እንስሳት ውጤቶቻቸው ዝውውር እና ቁጥጥር ዙሪያ ለሚመለከታቸው አካላት ስልጠና መስጠቱን አስታውቋል።ለአምስት ቀናት በቆየው ስልጠና የዱር እንስሳት ውጤቶቻቸው ዝውውርን ለመከላከል የሚያስችሉ ሰነዶች የቀረቡ ሲሆን ሰልጣኞች ከህገወጦች የሚያዙ የዱር እንስሳት ውጤቶችን መለየት የሚያስችል የተግባር ላይ ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል።
በተጨማሪም በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ላይ የሚገኙትን የአነፍናፊ ውሾች የፍተሻ ተግባር የሚያከናውኑበትን ሁኔታ መጎብኘት ችለዋል።
ቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል

በአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ የተፈጸመዉ ጥቃት ከኳታር ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ስትል ኢራን ተናገረች
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሰኞ በአሜሪካ በሚመራው አል ኡዴይድ ወታደራዊ ጦር ሰፈር ላይ የተፈጸመው ጥቃት ከኳታር ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ተናግረዋል ።መሰረቱ በኳታር ነው፣ ያሉት ባካይ ግን የኢራን ድርጊት "ራስን የመከላከል ተግባር" ነው ብሏል።"ኢራን የኳታርን ግዛት እና ሌሎች ጎረቤት ሀገራትን በተመለከተ ለመልካም ጉርብትና ፖሊሲዋ ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ ነች" ሲሉ ባካይ በኤክስ ላይ አጋርተዋል።
የአሜሪካ እና እስራኤላውያን የወንጀል ጥቃቶች በኢራን ላይ የተሳሳቱ ፖሊሲዎች በእኛ እና በቀጠናው ወንድማማች አገሮች መካከል መለያየት እንዳይፈጥሩ ወስነናል ያሉት የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኳታር በአካባቢው ያለውን መባባስ ለመከላከል ስላደረገችዉ ምስጋናቸውን ገልጿል።የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማጂድ ታክት-ራቫንቺ እና የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ ቢን አብዱላዚዝ አል-ኩላይፊን ለአገራቸው ስላደረገችዉ "ገንቢ ሚና" አመስግነዋል::
ታክት ራቫንቺ ኢራን "በመልካም ጉርብትና እና ከፍተኛ ጥቅም ላይ የተመሰረተ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለመቀጠል እና ለማጠናከር ቆርጣለች" ሲሉ ተናግረዋል።ኢራን በኳታር አል ኡዴይድ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ በኒውክሌር ተቋሞቿ ላይ ላደረሰችው ጥቃት አጸፋ የተኩስ ሚሳኤሎችን መተኮሷ ይታወሳል። በምላሹ ኳታር ድርጊቱን አጥብቆ በማውገዝ የኢራን አምባሳደርን አስጠርታለች፡፡
በስምኦን ደረጄ

ትራምፕ የኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር አልጠፋም በሚል ሾልኮ የወጣውን የደህንነት መረጃ ውድቅ አደረጉ
ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በኢራን ላይ ባደረሰችው ጥቃት ዙሪያ ሾልኮ ስለወጣው መረጃ ምላሽ ሰጥተዋል። የግል ንብረታቸው በሆነው ትሩዝ ሶሻል ላይ ባጋሩት መረጃ፣ ትራምፕ የአሜሪካን ሚዲያ እና ዘገባዎቻቸውን ነቅፈዋል። የሐሰት ዜና ሲ ኤን ኤን እና ከወደቀው ኒውዮርክ ታይምስ ጋር ተጣምረው አጋርተዋል ብለዋል። በኢራን ውስጥ ያሉ እጅግ በጣም አስፈላጊ ወታደራዊ መሳሪያዎች ታሪካዊ በሆነው ጥቃት ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል ሲሉ ተደምጠዋል።
የትራምፕ አስተዳደር አሜሪካ በኢራን ላይ ያደረሰችው ጥቃት የኒውክሌር ፕሮግራሟን አላወደመውም የሚለውን ዘገባ ውድቅ ማድረጉን ቀጥሏል።

የአሜሪካ ጥቃት የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር አለማጥፋቱን የስለላ ሪፖርት አመላከት
(ዝርዝሩን በስምኦን ደረጄ)
ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን የኒውክሌር መሥሪያ ቤቶች ላይ የፈጸመችው ጥቃት የሀገሪቱን የኒውክሌር መርሃ ግብር አላጠፋም እናም ምናልባትም በወራት ውስጥ ዳግም እንዲመለስ ያደርገዋል ሲል ፔንታጎን ጥቃቱን በተመለከተ አስቀድሞ ባደረገው የመረጃ ግምገማ ገልጿል። የኢራን አብዮታዊ ሪፐብሊክ የበለፀገ የዩራኒየም ክምችት በቅዳሜው የቦምብ ጥቃቶች አልተወገደም ሲሉ የመከላከያ መረጃ ኤጀንሲ ግምገማን የሚያውቁ ምንጮች ለሲቢኤስ ተናግረዋል። ዋይት ሀውስ እንዳለው ግን "የተሳሳተ" ግምገማ በዝቅተኛ ደረጃ የተሰራ የስለላ ግኝት ነው በማለት አጣጥሏል።
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን የሚገኙትን የኒውክሌር ቦታዎች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ሲሉ ሚዲያዎች "በታሪክ ውስጥ ስኬታማ ከሆኑ ወታደራዊ ጥቃቶች መካከል አንዱን ለማዋረድ እየሞከሩ ነው" ሲሉ ከሰዋል።ዩናይትድ ስቴትስ 18 ሜትር (60 ጫማ) ኮንክሪት ወይም 61 ሜትር (200 ጫማ) መሬት ውስጥ ዘልቆ መግባት በሚችሉ "በቤንከር ባስተር" ቦምቦች በኢራን ውስጥ ሶስት የኒውክሌር ተቋማትን ፎርዶ፣ ናታንዝ እና ኢስፋሃንን መታለች። ነገር ግን የፔንታጎን የስለላ ግምገማን የሚያውቁ ምንጮች የኢራን የኒውክሌር ስፍራ በአብዛኛው "ያልተበላሹ" እና ተጽእኖው ከመሬት በላይ ባሉ ሕንፃዎች ላይ ብቻ የተገደበ ነው ይላሉ።
ወደ ሁለት የኒውክሌር መስሪያ ቤቶች የሚገቡት መግቢያዎች ተዘግተዋል፣ አንዳንድ መሠረተ ልማቶች ወድመዋል ወይም ተበላሽተዋል፣ ነገር ግን አብዛኛው ከመሬት በታች ያሉ ህንጻዎች ከፍንዳታው አደጋ አምልጠዋል። ማንነታቸው ያልታወቁ ምንጮቹ ለአሜሪካ ሚዲያ እንደተናገሩት ጥቃቱ ኢራንን ወደ ኋላ የመለሰው “ከጥቂት ወራት በላይ ነው” ተብሎ ተገምቷል እናም ማንኛውም የኒውክሌር ፕሮግራሟን እንደገና መጀመር እና ለመጠገን ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይችላል ። የኢራን የበለጸገው የዩራኒየም ክምችት ከጥቃቱ በፊት መንቀሳቀሱንም ምንጮች ለሲቢኤስ አረጋግጠዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ 14,000 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ግዙፍ የኦርዳንስ ቦምብ የኢራንን የመሬት ውስጥ ማበልፀጊያ ተቋማትን ሊያወድም የሚችል ብቸኛው መሳሪያ እንደሆነ ይታሰብ ነበር። ቴህራን የኒውክሌር መርሃ ግብሯ ለሰላማዊ ዓላማ ነው ስትል ሁልጊዜም ትደመጣለች።የቅዳሜውን የአሜሪካን ጥቃት ተከትሎ በነበሩት የመጀመሪያ ሰአታት ውስጥ የጋራ ጦር ሃላፊዎች ሊቀመንበር ጄኔራል ዳን ኬን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት በተቋማቱ ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመገምገም ጊዜ ይፈልጋል ብለዋል። ነገር ግን "ሦስቱም ቦታዎች በጣም ከባድ ጉዳት እና ውድመት ደርሶባቸዋል" ሲሉ አክለዋል።የሳተላይት ምስሎች በፎርዶ ኑክሌር ቦታዎች ላይ በሚገኙ ሁለት የመግቢያ ስፍራዎች ዙሪያ ስድስት አዲስ ጉድጓዶች፣ እንዲሁም ግራጫ ብናኝ እና ፍርስራሾችን ያሳያሉ። ድረ-ገጾቹ ከመሬት በታች ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰባቸው ግን በምስሎቹ ላክ ግልጽ አይደለም።
የኢራን የመንግስት ብሮድካስት ምክትል የፖለቲካ ዳይሬክተር ሀሰን አቤዲኒ በአሜሪካ ኢላማ የተደረጉት ሶስት ቦታዎች ጥቃቱ ከመፈፀሙ ከተወሰነ ጊዜ በፊት ተወስደዋል ብለዋል እናም ኢራን ቁሳቁሶቹ ቀድሞውኑ ስላሸሸችው ትልቅ ጉዳት አላጋጠማትም ብለዋል ። በሌላ በኩል የአሜሪካ ባለስልጣናት ተልዕኮውን የተሳካ ነው ሲሉ የእስራኤል ባለስልጣናትም አድንቀዋል። የመከላከያ ሚኒስትር ፔት ሄግሰት ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ "ሁሉንም አይቻለሁ የእኛ የቦምብ ጥቃት ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ የመፍጠር አቅምን ያጠፋ ነበር" ብለዋል ። "ቦምቦቹ አውዳሚ አልነበሩም የሚል ሰው ፕሬዚዳንቱን እና የተሳካውን ተልዕኮ ለማዳከም እየሞከረ ነው" ሲሉ ሄግዝ ተደምጠዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስማን የዴሞክራቲክ የምክር ቤቱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባል ብራድ ሼርማን ለቢቢሲ እንደተናገሩት የትራምፕ አስተዳደር ድልን ለማወጅ ግልፅ ያልሆኑ ቃላትን እየተጠቀመ ነው ብለዋል። የቦምብ ጥቃት ተልዕኮው ምን እንዳከናወነ እስካሁን ግልፅ አይደለም። አስተዳደሩ በፈፀመው ጥቃት ዘጠኝ የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎችን ለመፍጠር በቂ ስለሆነው የኢራን ዩራኒየም ስለማጥፋቱ አልተናገረም ብለዋል። ሸርማን አክለው "የኢራን የኒውክሌር ፕሮግራሙን አጥፋን ሲሉ፣ ሴንትሪፉጁስ ተደምስሷል እና ወደፊት ዩራኒየም የመፍጠር አቅሙ ወይም ክምችቱን እየደመሰሰ መሆኑን እንኳን አይናገሩም" ሲሉ ተደምጠዋል። የምክትል ፕሬዝዳንት ቫንስ መግለጫን ጨምሮ ሁሉም ምልክቶች የሚያመለክቱት ክምችቱን ያገኘን አይመስለንም ብለዋል ። ጥቃቱ ከመድረሱ ቀናት በፊት የጭነት መኪናዎች ወደ አንዱ መገልገያ ሲሄዱ የሚያሳዩ ምስሎች የሉም ሲሉ ጠቁመዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ማክሰኞ እንዳሉት ከኢራን ጋር ያለው ጦርነት በሰኔ ወር ከጀመረ ወዲህ እስራኤል የኢራንን የኒውክሌር ፍላጎት በመገደብ እንዲሁም የሚሳኤል ጦር መሳሪያዎቿን በማውደም ውጤታማ ሆናለች ብለዋል። ኔታንያሁ በጽህፈት ቤታቸው ባወጡት የቪዲዮ መግለጫ ላይ “በእኛ ላይ የነበሩትን ሁለት ፈጣን የህልውና ስጋቶች አስወግደናል፤ በኒውክሌር መጥፋት ስጋት እና 20,000 የባላስቲክ ሚሳኤሎች ተወግደዋል ብለዋል። የሳውዲ የዜና አውታር አልሃዳት ስማቸው ያልተገለጸ የእስራኤልን ምንጭ ጠቅሶ እንደዘገበው እስራኤል አብዛኛው የኢራን የበለጸገ ዩራኒየም በፍርስራሹ ውስጥ የተቀበረ መሆኑን ታውቃለች ብሏል። አሜሪካ 18 የስለላ ኤጀንሲዎች አሏት፤ አንዳንድ ጊዜ በተልዕኳቸው እና በአካባቢው ባላቸው እውቀት ላይ ተመስርተው የሚጋጩ ዘገባዎችን ያዘጋጃሉ። ለምሳሌ የአሜሪካ የስለላ ማህበረሰብ በኮቪድ-19 አመጣጥ ላይ አሁንም ስምምነት ላይ አልደረሰም። ወደፊት የስለላ ሪፖርቶች በተቋማቱ ላይ የተለያየ ጉዳት ደረጃን የሚያሳዩ ተጨማሪ መረጃዎችን ሊያካትቱ ይችላሉ።
የሳይንስ እና የአለም አቀፍ ደህንነት ተቋም ፕሬዝዳንት እና የምስጢር የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ልማት ኤክስፐርት ዴቪድ አልብራይት ኢራን በአሜሪካ ጥቃት የደረሰባት ጉዳት ማለት የኒውክሌር መርሃ ግብሯን ወደነበረበት ለመመለስ ከፍተኛ ጊዜ፣ኢንቨስትመንት እና ጉልበት ይጠይቃል ብለዋል። አልብራይት በኤክስ ላይ በለጠፉት ጽሁፍ ኢራን “በዩናይትድ ስቴትስ እና በእስራኤል ከፍተኛ ክትትል ላይ ናት” ሲሉ አክለው ተናግረዋል፣ እናም እንደገና ለመገንባት ከሞከሩ ለተጨማሪ ጥቃቶች ይጋልጣሉ። ሰኞ እለት ኢራን በሺዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች መገኛ በሆነው ኳታር በሚገኘው አል-ኡዲድ አየር ሰፈር ላይ የሚሳኤል ጥቃትን በአሜሪካ ላይ የአፀፋ እርምጃ ወስዳለች። ያ ጥቃቱ በአብዛኛው የተጠለፈ ሲሆን ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም። ኢራን ከወሰደችበት አፀፋ በኋላ፣ በፕሬዚዳንት ትራምፕ እና በኳታር ሸምጋዮች የተኩስ አቁም ስምምነት በኢራን እና በእስራኤል መካከል ተደርሷል።

ኢራን ለእስራኤል ሲሰልሉ የነበሩ ሶስት ሰዎችን በስቅላት ቀጣች
የኢራን የፍትህ አካላትን ጠቅሰው የሀገሪቱ የዜና ወኪሎች እንደዘገቡህ ለእስራኤል በመሰለል የተከሰሱ ሶስት ሰዎችን ቴህራን በስቅላት ቀጥታለች። የሚዛን ኤጀንሲ "ግድያ ለመፈጸም" መሳሪያዎችን በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ሞክረው እንደነበርም በዚህም በፍርድ ቤት ተፈርዶባቸዋል ብሏል። ኢድሪስ አሊ፣ አዛድ ሾጃይ እና ረሱል አሕመድ እስራኤልን “ለመተባበር” ሲንቀሳቀሱ ተይዘው ለፍርድ የቀረቡ ሰዎች ናቸው ሲል ዘገባው አክላል።
ኢራን ለ12 ቀናት በዘለቀው ግጭት ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ነበራቸው ተብለው የተከሰሱ 700 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሏንም የሃገሪቱ የመረጃ ምንጭ ኑር ኒውስ ዘግቧል።ከኒውክሌር ሳይንቲስቶች ግድያ ጀምሮ የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር ለመናድ በደረሰው ሂደት ሰላዮቹ ሚና እንደነበራቸው ተመላክቷል።
በቅርቡ ከእስራኤል ጋር ለአስርት አመታት ከዘለቀው የጀርባ ጦርነት በኃላ የፊት ለፊት ግጭት ውስጥ ገብታ የነበረችው ኢራን ከሞሳድ ጋር ግንኙነት ነበራቸው ያለቻቸውን እና በርካታ ግለሰቦችን በሞት መቅጣቷ ይታወሳል።

በባሌ ዞን ከ6ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ቁሳቁሶች በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዙ በቁጥጥር ስር ዋሉ
በባሌ ዞን ሀረና ቡሉቅ ወረዳ በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዙ የነበሩ የሞተር ብስክሌት ጎማዎች ፣መለዋወጫ እና የተለያዩ የመድኃኒት ዓይነቶች እንዲሁም የሶላር ድንጋዮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት አስታዉቋል ።
የሀረና ቡሉቅ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ጎሳዬ ንጉሴ እንደገለፁት በሀረና ቡሉቅ ወረዳ መካነ ጎቦሌ በተባለ ስፍራ ሶስት ቦንዳ የሞተር ብስክሌት ጎማ ከመነዳሪዎች እና ሰባት ቦንዳ የተለያየ የሞተር ብስክሌት መለዋወጫዎች በአጠቃላይ 1ሚሊዮን 7መቶ 50ሺህ ብር የሚገመቱ ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል ።
በተጨማሪም 500ሺህ ብር የሚገመት መድኃኒት እና 3 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የሶላር ባትሪ ድንጋይ በቁጥጥር ስር መዋሉን የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሀላፊ መግለጫ አመላክቷል ።
በአጠቃላይ 6ሚሊዮን 240ሺህ ብር የሚያወጣ ንብረት በቁጥጥር ስር ዉሎ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ እና ዉሳኔ ሲያገኝ ለሚመለከተው የጉምሩክ መስሪያ ቤት ገቢ እንደሚደረግ ምክትል ኢንስፔክተር ጎሳዬ ንጉሴ ገልጸዋል ።
በመባ ወርቅነህ

አሜሪካ የኢራንን የኒውክሌር ክምችት አልመታችም ሲሉ የካሊፎርኒያ ኮንግረስማን ተናገሩ
የዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስማን የትራምፕ አስተዳደር የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር ድል ለማወጅ “ግልጽ ቃላትን” እንዲጠቀም ጠይቀዋል። ዴሞክራቱ ብራድ ሼርማን ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኢራን አሁንም የዩራኒየም ክምችቷን እንደያዘች በመግለፅ ይህም በግምት "ለዘጠኝ የኑክሌር ጦር መሳሪያዎች" በቂ ይሆናል ሲሉ ተደምጠዋል። ዩናይትድ ስቴትስ ለዩራኒየም ማበልፀግ አስፈላጊ የሆኑትን ሴንትሪፉጅ እንዳስወገደች የሚገልፅ ከኋይት ሀውስ የተሰጠ ምንም ነገር የለም ሲሉ አክለው ተናግረዋል።
የኢራን የመንግስት ብሮድካስት ምክትል የፖለቲካ ዳይሬክተር ሀሰን አቤዲኒ በአሜሪካ ኢላማ የተደረጉት ሶስት ቦታዎች ጥቃቱ ከመፈፀሙ ከተወሰነ ጊዜ በፊት ተወስደዋል ብለዋል እናም ኢራን ቁሳቁሶቹ ቀድሞውኑ ስላሸሸችው ትልቅ ጉዳት አላጋጠማትም ብለዋል ። በሌላ በኩል ግን የአሜሪካ ባለስልጣናት ተልዕኮውን የተሳካ ነው ሲሉ የእስራኤል ባለስልጣናትን ጨምረው አድንቀዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ፔት ሄግሰት ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ "ሁሉንም አይቻለሁ የእኛ የቦምብ ጥቃት ኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ የመፍጠር አቅምን ያጠፋ ነበር" ብለዋል ። "ቦምቦቹ አውዳሚ አልነበሩም የሚል ሰው ፕሬዚዳንቱን እና የተሳካውን ተልዕኮ ለማዳከም እየሞከረ ነው" ሲሉ ሄግዝ ተደምጠዋል።

በእስራኤል ኢራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ይመልከቱ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/puuEkWZf1gM?si=rq0vNfJCKFRDxr6t

ነዳጅ ደብቀዉ የተገኙ ሁለት ማደያዎች የንግድ ፈቃዳቸዉ ተሰርዞ ከገበያ እንዲወጡ ተደረገ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀድያ ዞን ሾኔ ከተማ እና በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ 234 ሺህ 572 ሊትር ነዳጅ ደብቀዉ የተገኙ ሁለት ማደያዎች ንግድ ፈቃዳቸዉ ተሰርዞ ከገበያ እንዲወጡ መደረጉን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታውቋል፡
በሾኔ ከተማ የሚገኝ እና ግሎባል በሚል ስያሜ የሚጠራ ነዳጅ ማደያ 94 ሺህ 572 ሊትር ነዳጅ ደብቆ የተገኘ ሲሆን በዱራሜ ከተማ የሚገኘው ኖክ ማደያ ደግሞ 140ሺህ ሊትር ነዳጅ ደብቆ መገኘቱን የገለፀዉ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሁለቱም ማድያዎች የንግድ ፈቃድ ተሰርዞ ከገበያ እንዲወጡ ማድረጉን አስታዉቋል።
በተጨማሪም በፌደራል አዋጅ ቁጥር1363/2017 መሰረት ነዳጅ በሚደብቁ ህገ-ወጥ የነዳጅ ማደያዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰድ መጀመሩን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ም/ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በክልሉ በቂ የሆነ የነዳጅ አቅርቦት መኖሩን የገለፀዉ ቢሮዉ የነዳጅ ዋጋ በመጨመር ያልተገባ ትርፍ ለማግኘት ነዳጅ በሚደብቁ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መዉሰዱን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጿል።ህብረተሰቡ መሰል ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት በ9348 ነጻ የስልክ መስመር በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል፡፡
በሳምራዊት ስዩም

በእስር ላይ የሚገኙት የቻድ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ተሰማ
የቻድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ሱሰስ ማሳራ መታሰራቸውን በመቃወም የረሃብ አድማ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። የቻድ ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ ለስ ትራንስፎርማተርስ መሪ እና የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት ማሳራ በግንቦት 14 በሎጎን ኦክሳይደንታል ግዛት ውስጥ በተፈጠረው የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት በዋና ከተማዋ ኒጃሜና በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በማህበራዊ ሚዲያ ፅሁፎች ላይ ጥላቻን እና ሁከትን በማነሳሳት፣ ከታጠቁ ወንበዴዎች ጋር በመተባበር እና በግድያ ወንጀል ተባባሪ በመሆን በርካታ ክሶች ተመስርቶባቸዋል። ከማክሰኞ ጀምሮ ከሁላችሁም ጋር በመተባበር እና የማይገባን ኢፍትሃዊ ድርጊት በመቃወም የርሃብ አድማ እጀምራለሁ ሲሉ ማስራ ለፓርቲያቸው ደጋፊዎቻቸው በጻፉት ደብዳቤ ላይ ተናግረዋ።
ከ40 ቀናት በፊት ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ደጋፊዎቼ ሁሉ የታሰርኩበትን ምክንያት ለማወቅ እየጣሩ እንደሆነም ተናግረዋል። እ.ኤ.አ በሜይ 2024 በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተወዳድረው የነበረ ሲሆን በወቅቱ የሽግግር ፕሬዚደንት የነበሩት ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ ምርጫውን አሸንፈዋል። ባለፈው ወር ሂዩማን ራይትስ ዎች ማስራ “በትክክለኛ ወንጀል ካልተከሰሱ” ባስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቋል።

🌟 እውነተኛ ቅናሽ አስገራሚ እድል!
ቤት መግዛት ወይም ለንግድዎ ሱቅ ይፈልጋሉ ? 🏡
በዚህ የካቦድ የሪል ስቴት ኤክስፖ የሚፈልጉት ቦታ ከልዩ ቅናሽ ጋር ያግኙ ! 💼📊
🎯 ቦታ፡ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሙዚየም
📅 ቀን፡ ሰኔ 27-29
ቤት ለገዢው, ሱቅ ለነጋዴው! 🏠🛍️
ካቦድ የሪል ስቴት ኤክስፖ
ለመመዝገብ የሚከተለውን መተግበርያ ይጠቀሙ፦ https://www.kabodmarketingsolution.com/

ባለፋት ዘጠኝ ወራት የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከ 6ሺህ 6 መቶ በማይበልጡ ቱሪስቶች መጎብኘቱ ተነገረ
ባለፋት ዘጠኝ ወራት 96 ሺህ የሚደርሱ ቱሪስቶች የኢትዮጵያን ዋና ዋና ፓርኮች እና የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎችን ጎብኝተዋል ሲል የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።በባለስልጣኑ የዱር እንስሳት አጠቃቀም ዴስክ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ወርቁ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በዘጠኝ ወሩ ይህን ያህል ቱሪስቶች የጥበቃ ቦታዎችን ቢጎበኙም በፀጥታ ችግር ምክንያት የቱሪስት ፍሰቱ መቀዛቀዙን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ካሏት ዋና ዋና የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች መካከል አንዱ የሆነው የነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ አንፃራዊ ሰላም የታየበት ቦታ በመሆኑ ከሌሎች ፓርኮች በቀዳሚነት ተጎብኝቷል ያሉት አቶ ዳንኤል የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ደግሞ የሁለተኛ ደረጃን መያዝ ችሏል ብለዋል።ፓርኩ በዩኔስኮበዓለም ቅርስነት ከተመዘገበ ወዲህ የቱሪስቶችን ቀልብ በመሳብ ረገድ ጥሩ መሻሻሎች እየታዮ እንደሚገኙ ገልፀው ባለፋት ዘጠኝ ወራት 7ሺህ የሚጠጉ ቱሪስቶች እንደጎበኙት አስረድተዋል።
የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ከሀገር ውስጥ ይልቅ በውጪ ሀገር ቱሪስቶች ይበልጥ መጎብኘቱን የገለፁት አቶ ዳንኤል በእግር መጓዝንና ተራራን መውጣት የፈለጉ ስፍራውን ለጉብኝት ተመራጭ ያደርጉታል። በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በኢትዮጰያ ሁለተኛው በዓለም ደግሞ 11ኛው ታላቅ የተፈጥሮ ቅርስ ሆኖ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣የሳይንስና፣የባህል ድርጅት(ዮኔስኮ) መመዝገቡ ይታወሳል።በ 1962 ዓ.ም የተቋቋመው ፓርኩ የቆዳ ሥፋቱ 2 ሺህ 150 ካሬ ኪሎ ሜትር ቦታ ይሸፍናል፡፡
በውስጡም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ትልቁ ተራራ ቱሉ ዲምቱ የሚገኝ ሲሆን የተለያዩ ብርቅዬ የእፅዋት እና የዱር እንሥሣት ዝርያዎች እንደሚገኙ ይነገራል።

የሱዳን ታጣቂ ቡድን ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በካቢኔ ቦታዎች አለመስማመቱን ተከትሎ ግጭት መፈጠሩ ተነገረ
በ2020 የሰላም ስምምነት ላይ በተቀመጠው መሰረት የሱዳን የሚኒስትርነት ቦታውን እንደሚቀጥል በመግለፁ ምክንያት በሱዳን ውስጥ ከፍተኛ አቅም አለው ተብሎ የሚታመን ታጣቂ ቡድን ከአዲሱ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር አለመግባባት ውስጥ ገብቷል። ውዝግቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ካማል ኢድሪስ ሰኔ 19 ላይ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን ያካተተ የገለልተኛ ቴክኖክራቶች ካቢኔ ለማቋቋም ማቀዳቸውን ካስታወቁ በኋላ አዲስ መንግሥት ለመመስረት የሚገጥስማቸውን ፈተና አጉልቶ ያሳያል።
ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጋር ግጭት ውስጥ የገባው ቡዱን የጁባ የሰላም ስምምነት ቁልፍ ፈራሚ የሆነው የፍትህ እና የእኩልነት ንቅናቄ (ጄኤም) ሲሆን አዲሱን ውሳኔ አልቀበልም በማለት ሀላፊነት እንደማይለቅ አስታውቋል። የጄኤም ቃል አቀባይ መሀመድ ዘካሪያ ፋራጃላህ በሰጡት መግለጫ "ለጁባ የሰላም ስምምነት፣ መርሆዎች እና መብቶች ሙሉ በሙሉ ቁርጠኝነት እንዳላቸው በማረጋገጥ በእሳቸው ስር የተፈቀዱትን የስራ አስፈፃሚ ቦታዎች ይዘው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
እ.ኤ.አ. በ 2020 የተደረሰው ስምምነት ፣ የታጠቁ ቡዱኖች 25 በመቶ የመንግስት የስራ ቦታዎች ተሰጥቷቸዋል፣ እነዚህም ስድስት የካቢኔ መቀመጫዎች ፣ ሶስት የሉዓላዊ ምክር ቤት መቀመጫዎች እና ዋና የክልል ገዥ ቦታዎች ያካትታሉ። ፋራጃላህ ስምምነቱ እነዚህ ቦታዎች እስከ ሀገሪቱ የሽግግር ጊዜ ማብቂያ ድረስ መያዛቸውን ያረጋግጣል ስለዚህ አንለቅም ብለዋል።
የጄኤም ቃል አቀባይ ምንም እንኳ አሁን አለመግባባቶች ቢኖሩም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ምክክር አሁንም እንደቀጠለ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
በሚሊዮን ሙሴ

በጋምቤላ ክልል የክረምት ወቅትን ተከትሎ የኃይል መቆራረጥ እንዳይኖር ያረጁ የኤሌክትሪክ መስመሮችን የመወጠር ስራ እየተሰራ ይገኛል ተባለ
በጋምቤላ ክልል ከኤሌክትሪክ ሀይል ተደራሽነት ጋር በተገናኘ የመልሶ ግንባታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል።የጋምቤላ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ አማረ ገብረመድህን ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በጋምቤላ ከተማ የኃይል አቅርቦትን አስተማማኝና ተደራሽ ለማድረግ አዲስ የኃይል መስመር ዝርጋታ ለማከናወን ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል።
ከዚህ ቀደም የነበረው የኃይል መስመር ዝርጋታ በእንጨት ምሰሶ የተከናወነ በመሆኑ በእርጅና ምክንያት እየወደቀ የኃይል መቆራረጥ የሚያስከትል መሆኑ ተነግሯል።አሁን ላይ ለችግሩ መፍትሄ ለማምጣት አዲስ የኃይል መስመር ዝርጋታ ለማካሄድ እየተሰራ ነው ያሉት አቶ አማረ ያረጁ ምሰሶዎችንና መስመሮችን የመቀየሩ ስራ በክልሉ ይስተዋል የነበረውን የኃይል አቅርቦት መቆራረጥ ችግርን በመፍታት የተሻለ አገልግሎት እንዲኖር ለማስቻል እንደሚረዳ ተናግረዋል።
በተለይም ደግሞ የክረምት ወቅትን አስመልክቶ አሁን ላይ የረገቡ የኤሌክትሪክ መስመሮችን የመወጠር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ አቶ አማረ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።የኃይል መሠረተ ልማት አገልግሎትን ተደራሽነት ለማረጋገጥ የመስመርና የትራንስፎርመር ችግርን ለመቆጣጠር የሚያስችል ቡድን መዋቀሩ ተመላክቷል።

ዩናይትድ ኪንግደም የኒውክሌር ጦር መሳሪያ መያዝ የሚችሉ ተዋጊ ጄቶችን ልትገዛ ነው
የብሪታኒያ መንግስት ትልቅ የተባለውን እና የኒውክሌር መከላከያ ማስፋፊያ አድርጎ የገለፀውን ታክቲካል የኒውክሌር ጦር መሳሪያ መተኮስ የሚችሉ ደርዘን ኤፍ-35 ኤ ተዋጊ ጄቶች እንደሚገዛ አስታውቋል። የሎክሂድ ማርቲን ጀቶች ግዢ የብሪታንያ አየር ሀይል ከቀዝቃዛው ጦርነት ማክተሚያ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዲይዝ ያስችለዋል ሲል ዳውንኒንግ ስትሪት አስታውቋል።
"በጣም እርግጠኛ ባልሆነበት ወቅት ሰላምን እንደ ቀላል ነገር መውሰድ አንችልም ለዚህም ነው መንግስቴ በብሄራዊ ደህንነታችን ላይ ኢንቨስት እያደረገ ያለው" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር በሰጡት
መግለጫ ተናግረዋል።ብሪታንያ የመከላከያ ወጪን በመጨመር ወታደራዊ ኃይሏን እያሳደገች ነው፣ የባህር ሰርጓጅ መርከቦችን ጨምሮ፣ ከሩሲያ እየጨመረ ያለው ጠላትነት እየተጋፈጠች ትገኛለች። ዩናይትድ ስቴትስ የአውሮፓ ደኅንነት ተሟጋች ከነበረችበት ከባሕላዊ ሚናዋ በማፈግፈጓ ብሪታኒያ ክፍተቱን ለመሙላት እየጣረች ነው።
የብሪታኒያ መንግስት የጄቶች ግዢ ባለሁለት አቅም ያላቸውን አውሮፕላኖች ለኔቶ በማዋጣት ግጭት በሚፈጠርበት ጊዜ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዲይዝ እንደሚያስችላት ተነግሯል።የኔቶ ዋና ፀሃፊ ማርክ ሩት “ይህ አሁንም ሌላ ጠንካራ የብሪታንያ ለኔቶ የሚደረግ አስተዋፅዖ ነው” ብለዋል። የብሪታንያ የኒውክሌየር መከላከያ በአሁኑ ጊዜ በትሪደንት ሰርጓጅ ላይ፣ የተመሰረተ ስርዓት ላይ ብቻ ያረፈ ሲሆን ይህም ባለፈው አመት በተደረገ ሙከራ የተሳሳተ ሙከራ ሆኗል። ይህም በ 2016 አንድ ኮርስ ከተቋረጠ በኋላ ሁለተኛው ተከታታይ የሙከራ ውድቀት ነው።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
የብሪታኒያ መንግስት ትልቅ የተባለውን እና የኒውክሌር መከላከያ ማስፋፊያ አድርጎ የገለፀውን ታክቲካል የኒውክሌር ጦር መሳሪያ መተኮስ የሚችሉ ደርዘን ኤፍ-35 ኤ ተዋጊ ጄቶች እንደሚገዛ አስታውቋል። የሎክሂድ ማርቲን ጀቶች ግዢ የብሪታንያ አየር ሀይል ከቀዝቃዛው ጦርነት ማክተሚያ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዲይዝ ያስችለዋል ሲል ዳውንኒንግ ስትሪት አስታውቋል።
"በጣም እርግጠኛ ባልሆነበት ወቅት ሰላምን እንደ ቀላል ነገር መውሰድ አንችልም ለዚህም ነው መንግስቴ በብሄራዊ ደህንነታችን ላይ ኢንቨስት እያደረገ ያለው" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር በሰጡት
መግለጫ ተናግረዋል።ብሪታንያ የመከላከያ ወጪን በመጨመር ወታደራዊ ኃይሏን እያሳደገች ነው፣ የባህር ሰርጓጅ መርከቦችን ጨምሮ፣ ከሩሲያ እየጨመረ ያለው ጠላትነት እየተጋፈጠች ትገኛለች። ዩናይትድ ስቴትስ የአውሮፓ ደኅንነት ተሟጋች ከነበረችበት ከባሕላዊ ሚናዋ በማፈግፈጓ ብሪታኒያ ክፍተቱን ለመሙላት እየጣረች ነው።
የብሪታኒያ መንግስት የጄቶች ግዢ ባለሁለት አቅም ያላቸውን አውሮፕላኖች ለኔቶ በማዋጣት ግጭት በሚፈጠርበት ጊዜ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዲይዝ እንደሚያስችላት ተነግሯል።የኔቶ ዋና ፀሃፊ ማርክ ሩት “ይህ አሁንም ሌላ ጠንካራ የብሪታንያ ለኔቶ የሚደረግ አስተዋፅዖ ነው” ብለዋል። የብሪታንያ የኒውክሌየር መከላከያ በአሁኑ ጊዜ በትሪደንት ሰርጓጅ ላይ፣ የተመሰረተ ስርዓት ላይ ብቻ ያረፈ ሲሆን ይህም ባለፈው አመት በተደረገ ሙከራ የተሳሳተ ሙከራ ሆኗል። ይህም በ 2016 አንድ ኮርስ ከተቋረጠ በኋላ ሁለተኛው ተከታታይ የሙከራ ውድቀት ነው።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
በእስራኤል ኢራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ይመልከቱ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/puuEkWZf1gM?si=rq0vNfJCKFRDxr6t
#ዳጉ_ጆርናል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/puuEkWZf1gM?si=rq0vNfJCKFRDxr6t
#ዳጉ_ጆርናል
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቻይና ጉዋንግ ዶንግ 4.5 በሬክተር ስኬል የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ባጋጠመበት ወቅት አንድ ታዳጊ ያደረገዉ ነገር መነጋገሪያ ሆኗል
በቻይና ጉዋንግ ዶንግ 4.5 በሬክተር ስኬል የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ አጋጥሟል።
በቤት ዉስጥ ከነበረ ካሜራ የተቀረጸ ምስዕል እንዳሳየዉ አንድ የቤተሰብ አባል የሆኑ ሰዎች የመሬት መንቀጥቀጡ ባጋጠመበት ወቅት ራት በመመገብ ላይ ነበሩ።
በዚህ መካከል የተሰማቸዉን የመሬት ንዝረት ለመሸሽ መለዉ ቤተሰብ ሲሯሯጥ አንድ ታዳጊ ልጃቸው ግን በጠረቤዛዉ ላይ እየተመገበ የነበረዉን ምግብ ትቶ ለመሮጥ ልቡ ፈራ ተባ ሲል ታይቷል።
ታዳጊዉ መላዉ ቤተሰብ ከቤት ለመዉጣት ሲሯሯጥ ከጀመረዉ ሩጫ እየተመለሰ "አንድ ለመንገድ" በሚመስል መልኩ ጠብሰቅ እያደረገ ሲጎርስ ታይቷል።
ሳቅን የፈጠረዉ የተዳጊዉ ድርጊት የብዙ ሰዎችን አስተያየት አስተናግዷል። "ከሞት ሆዱ በለጠበት" ያሉም ነበሩ። ሌሎችም "ታዳጊዉ በረሃብ ዉስጥ ሆኖ መሞት አልፈለገም ነበር" ሲሉ ቀልደዋል። አንዳንዶችም "የመጨረሻዉ ራት" ሲሉ ሃሳባቸውን ጥፈዋል።
ከተሰጡ አስተያየቶች ዉስጥ "በረሃብ ከመሞት በመሬት መንቀጥቀጥ መሞትን መርጧል" ያሉም አልጠፉም። "ምግቡ እንዴት ቢጣፍጥ ነዉ" ብለዉ ጥያቄ ያነሱም አሉ።
በበረከት ሞገስ