በሱሉልታ ፍተሻ ጣቢያ አካባቢ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ
ዛሬ ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4:50 ገደማ በጉለሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 7
ሱሉልታ ፍተሻ ጣቢያ ከመድረሱ በፊት ባለዉ ቁልቁለት መንገድ ላይ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
አደጋው የደረሰው ከባድ ጭነት ጭኖ ይጓዝ የነበረ ከባድ ተሽከርካሪ የጫነዉ ጭነት ተሳፋሪ ጭኖ ወደ ሱሉልታ ይጓዝ በነበረዉ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ላይ በመወደቁ መሆኑን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል። በአደጋዉ በሚኒባስ ታክሲ ዉስጥ የነበሩ አራት ተሳፋሪዎች ህይወታቸዉ አልፏል።
የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ህይወታቸዉ ያለፈዉን ሰዎች ከአራት ሰዓታት ጥረት በኋላ አስከሬናቸውን ከተጫናቸዉ ጭነትና ከተሽከርካሪ ዉስጥ አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።
የሟቾችን አስከሬን ለማዉጣት የኮሚሽኑ እና የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ክሬኖች ጥቅም ላይ የዋሉ ሲሆን በሂደቱም የአዲስ አበባ ፖሊስና ሌሎች የጸጥታ አመራርና አባላት ድጋፍ አድርገዋል።
በትግስት ላቀው
#ዳጉ_ጆርናል

Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
Breaking : አርሰናሎች ኤብሪቼ ኤዜን የዝዉዉር እቅዳቸዉ ዉስጥ እንዳስገቡት ቤን ጄኮብስ ዘግቧል። የ 68 ሚሊዮን ፓዉንድ ዉል ማፍረሻ ያለዉ ሲሆን ቶትንሃምም የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸዉ።
ስካይ ስፖርት በአንጻሩ አርሰናል እና ኤዜ በግል ጉዳዮች መስማማታቸዉን ዘግቧል። ፓላስም በሶስት ጊዜ ተቆራርጦ የሚከፈል በየአመቱ 20 ሚሊዮን ፓዉንድ እና 8 ሚሊዮን ተጨማሪ ክፍያ ይፈልጋል። ተጨዋቹም ወደ አርሰናል ለመዘዋወር ግፊት እያደረገ ነዉ ብሏል።
አርሰናል የሮድሪጎንም ሁኔታ እየተከታተለ ሲሆን ተጨዋቹ ስለ ዝዉዉር ከማሰቡ በፊት በቅድሚያ ከዣቪ አሎንሶ ጋር ስለሚኖረዉ ቆይታ ማየት ይፈልጋል።
#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport

በደቡብ ጎንደር ዞን የትራንስፖርት አገልሎት ለሶስት ቀናት በመቋረጡ ማህበረሰቡ ለእንግልት መዳረጉ ተገለፀ
በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ መካነ ኢየሱስ የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ህብረተሰቡ ለከፍተኛ እንግልት እየተጋለጠ መሆኑን የመካነ-ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ተጠሪ ጽ/ቤት አስታውቋል።በዞኑ የኮሚኒኬሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ እሱባለው መስፍን ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በአካባቢው የትራንስፓርት አገልግሎቱ ከተቋረጠ ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።
በሁሉም አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ የትራንስፖርት ሊቋረጥ የቻለው በፀጥታ ችግር እንደሆነ አቶ እሱባለው ጠቅሰው ይህም አሽከርካሪዎች ለከፍተኛ ድብደባ እንዲሁም ግድያ እና እንግልት መጋለጣቸውን ተናግረዋል።ባለሀብቶች በንብረታቸው ማዘዝና በገንዘባቸው መጠቀም፤ ነጋዴዎች ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ ሸቀጣ ሸቀጥ ማቅረብ አለመቻላቸውም ተጠቅሷል።
በተጨማሪም የትራንስፖርት አገልግሎቱ በመቋረጡ የተነሳ ሰኔ 23/2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና ለማደናቀፍ ተማሪዎች ፈተናው ወደ ሚሰጥበት ማዕከል እንዳይሄዱ አሉታዊ ጫናን ፈጥሯል ተብሏል።አሁን ላይ ችግሩን ለመፍታት የከተማው አስተዳደርና የወረዳው አመራሮች ከባለሀብቶችና አሽከርካሪዎች ጋር ውይይት እያደረጉ እንደሚገኙ ተገልጿል።
ቅድስት ደጀኔ

የእስራኤል የደህንነት ሚኒስተር ለጋዛ የሚሰጠውን እርዳታ በሙሉ እንዲቋረጥ በድጋሚ ጥሪ አቀረቡ
የእስራኤል ብሄራዊ ደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን-ጊቪር "በአሁኑ ጊዜ ወደ ጋዛ እየገባ ያለው የሰብአዊ እርዳታ ፍጹም አሳፋሪ ነው" ብለዋል። “በተደጋጋሚ ባስጠነቀቅኩ ጊዜ እና በሚያሳዝን ሁኔታ ከአንድ ወር ተኩል በፊት እርዳታ እንዳይገባ ድምጽ የሰጠ ብቸኛው ሰው ሆኜ ለሃማስ የህይወት መስመር እንደሚሰጥ እርግጠኛ ነበርኩ” ሲሉ የቀኝ አክራሪውና እና ብዙ ጊዜ አነጋጋሪ አስተያየት በመስጠት የሚታወቁተወ ሚኒስትር በኤክስ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ተናግረዋል።
ቀጥሎም “በዚያን ጊዜ አንዳንዶች ‘እርዳታው ወደ ሰሜናዊው ሴክተር እና ለ10 ቀናት ብቻ ነው የሚሄደው’ ብለው ያፌዙብኝ ነበር፣ እናም ዛሬ ምን እየተፈጠረ እንደሆነ ግልፅ ነው። ሃማስ የምግብ እና የሸቀጦችን መጠን ይቆጣጠራል፣ ይህም ለህልውናው አስተዋጽኦ ያደርጋል ብለዋል።
"ዕርዳታውን ማቆም ድል ያፋጥናል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚቀጥለው የካቢኔ ስብሰባ ላይ ወደ ጋዛ በሚገባው ዕርዳታ ዙርያ እንደገና ድምፅ እንዲሰጥ እጠይቃለሁ " ሲሉ የእስራኤል የደህንነት ሚንስቴሩ ኢታማር ቤን ጊቨር ተናግረዋል።
በሚሊዮን ሙሴ

ደሞዝ አልከፈልከኝም በሚል ምክንያት አሰሪውን የገደለው በእስራት ተቀጣ
ተከሳሹ ጌቱ መስፍን ይባላል፤ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው ነሀሴ 27 ቀን 2014 ዓ/ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ከ30 ሲሆን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ለገሃር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ኖህ ሪል ስቴት ከሚያሰራው ህንፃ 16ኛ ጅምር ፎቅ ላይ ነው።
ሟች ሀጂብ ያሲን የተባለው ግለሰብ ከኖህ ሪል እስቴት ኮንትራት በመውሰድ ከስሩ በርካታ ሰራተኞችን ቀጥሮ የሚያሰራ ግለሰብ ነው።
ሟች የዘወትር ስራውን ለማሰራት ሰራተኞችን ወደ የስራቸው ያሰማራል። ተከሳሽም ሟች የነበረበት ቦታ ጭር ማለቱን እና ማንም አለመኖሩን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመውሰድ ደሞዜን ከለከልከኝ በሚል ምክንያት በተፈጠረ አለመግባባት ሟች ሀጂብ ያሲንን ስራ እየሰራ ባለበት 16ኛ ፎቅ ላይ በፌሮ ብረት ግንባሩን በመምታት እና አንገቱን በሽቦ ገመድ በማነቅና በማሰር ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረግ ሟችን ከህንፃው ተሸክሞ በማውረድ የህንፃው መሰረት ስር የሚገኝ የተጠራቀመ ውሃ ውስጥ አስከሬኑን በመጣል ከአካባቢው ይሰወራል።
የወንጀሉ መፈፀም ሪፖርት የደረሰው ፖሊስ የምርመራ ክፍሉና የክትትልና ኦፕሬሽን ቡድኑ በመዋቀርና በመቀናጀት ወንጀል ፈፃሚውን ለመያዝ በተደረገ ጥረት ተከሳሽ ጌቱ መስፍን ወንጀሉን ከፈፀመ በኋላ ምንም እንዳልተፈፀመ በኔጌሌ ቦረና ከተማ በአንድ ተቋም ውስጥ ተቀጥሮ በመስራት ላይ እንዳለ በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል።
በተከሳሽ ጌቱ መስፍን ላይ የምርመራ መዝገቡን በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማጠናከር ለሚመለከተው የፍትህ አካል በመላክ ክስ እንደተመሰረተበት የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ተከሳሽ ጌቱ ጥፋተኛ ሆኖ በማግኘቱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት በ21 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እንደተወሰነበት ገልጿል።
ማንም ሰው ወንጀል ፈፅሞ ከህግ እና ከማህበረሰቡ ማምለጥ እንደማይቻል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጠቅሶ ያለመግባባት በሚፈጠርበት ወቅት በመነጋገር መፍታት ይገባል ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

የአሜሪካ ፖሊስ በክለቦች የአለም ዋንጫ ዉድድር ጥበቃ ለሚጠቀማቸዉ ዉሾች ጫማ መጠቀም ጀመረ
የአሜሪካ ፖሊስ በስራዎቹ ለሚያግዙትን የሰለጠኑ ዉሾች ጫማ መጠቀም ጀመሯል። የአሜሪካ ፖሊስ በክለቦች የለም ዋንጫ የጸጥታ ስራዉ ነዉ ዉሾቹን የሚጠቀመዉ።
ፖሊስ ለዉሾቹ ጫማ መጠቀም የጀመረዉ በሀገሪቱ በአሁኑ ሰዓት ካለዉ ከፍተኛ ሙቀት የተነሳ መሆኑ ተዘግቧል። በክለቦች የአለም ዋንጫ ተጨዋቾች ያለዉን ሙቀት መቋቋም ሲያቅታቸዉ ተመልክተናል።
ለአብነት ከትናንትና በስቲያ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከኡልሳን ጋር ባደረገዉ ጨዋታ የአየር ንብረቱ ወይም ሙቀቱ ከ 42 ሴንቲግሬድ በላይ ነበር።
በተቀያሪ ወንበር ላይ የሚቀመጡ ተጨዋቾችም ሙቀቱን መቋቋም አቅቷቸዉ በመልበሻ ክፍል ጨዋታዉን በቴሌቪዥን ሲከታተሉ በተደጋጋሚ ተመልክተናል።
የአሜሪካ የአሁኑ የአየር ንብረት ሁኔታ በቀጣይ አመት ሀገሪቱ ከካናዳ እና ሜክሲኮ ጋር በጋራ በምታዘጋጀው የሀገራት የአለም ዋንጫ ዉድድር ላይ ጥላ እንዳያጠላ ተሰግቷል።
በበረከት ሞገስ

በአረብ ሀገራት የሚገኙት አብዛኛዎቹ አቦሸማኔዎች በህገወጥ መልኩ ከኢትዮጵያ የተወሰዱ ናቸው ተባለ
በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ሀብት ላይ ከተደቀኑ በርካታ ችግሮች መካከል ህገወጥ የእንስሳት ዝውውር አንዱ መሆኑን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።በባለስልጣኑ የዱር እንስሳት ህገወጥ ዝውውር ቁጥጥር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳንኤል ጳውሎስ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ለተለያዩ አላማዎች ሲባል በኢትዮጵያ የሚገኙ የዱር እንስሳት ከነህይወታቸው በህገወጥ መንገድ ይዘዋወራሉ።
በዚህ መልኩ ከሀገር የሚወጡ እንስሳቶች በርካታ ቢሆኑም በቀዳሚነት አቦሸማኔ ይጠቀሳል ። አቦሸማኔ በተለይም በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል በሱማሌ ክልል መኖሪያውን በማድረጉ የአካባቢው ማህበረሰቦች ባካበቱት ተፈጥሮአዊ ዘዴ የአቦሸማኔ ቡችላዎችን በመያዝ ሶማሌላንድ አካባቢ ለሽያጭ እንደሚያቀርቡ ተጠቁሟል።
በዚህ መልኩ ይህ እንስሳ ወደ መካከለኛው የአረብ ሀገራት ጭምር ላሉ ባለሀብቶች የሚሸጥበት ሁኔታ መኖሩን የገለፁት አቶ ዳንኤል ግለሰቦቹ የራሳቸው የሆነ መካነ አራዊት ስላላቸው እንስሳቱን የመግዛት ፍላጎታቸው ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል።ወደ መካከለኛው ምስራቅ የአረብ ሀገራት የሚገኙት አቦ ሸማኔዎችም ከአፍሪካ ቀንድ በተለይም ከኢትዮጵያ የተወሰዱ ስለመሆናቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ ሲሉ ባለሙያው ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
አቦሸማኔን ጨምሮ ሌሎች እንስሳትን ከህገወጥ ዝውውር ለመታደግና ኢትዮጵያ ከእንስሳት ሀብቷ ተጠቃሚ እንድትሆን አሁን ላይ በአነፍናፊ ውሾች የታገዘ የቁጥጥር ስራ እየተከናወነ ይገኛል ተብሏል።

በኢራን የስለላ ድርጅት ውስጥ ይሰራል ተብሎ የተጠረጠረ ወጣት በእስራኤል በቁጥጥር ስር ዋለ
በሰሜን እስራኤል ከሚገኘው ከዴር አል አሳድ የመጣው የ22 ዓመት ተማሪ ኢራንን ወክሎ ተልእኮዎችን በማከናወን ክስ ሊመሰረትበት እንደሚችል ፖሊስ እና የሀገሪቱን የሺን ቤት የደህንነት አገልግሎትን ጠቅሶ ሃሬትዝ ዘግቧል።
ባሻር ሀሰን ቃሲም ሙሳ በደቡብ እስራኤል በቤር ሼቫ በማዕከላዊ ግዛት ላይ የመንገድ የተለያዩ ተቀጣጣይ ነገሮችን ካስቀመጠ እና ሰው ለመጉዳት ከሞከረ በኋላ ለኢራን የስለላ ስራ በመስራት ተጠርጥሮ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉን የእስራኤሉ ጋዜጣ ዘግቧል። ነግር ግን ሺን ቤት የሙሳን ኢላማ ማንነት ግልፅ አለመሆኑን ሃሬትዝ አክሏል።
በሌላ መረጃ

የእስራኤልጦር በዮርዳኖስ ሸለቆ አካባቢ የጦር ልምምዱን ከሀሙስ ከጠዋት ጀምሮ እስከ ከሰአት በኋላ እንደሚደረግ ገልጿል። በልምምድ ወቅት በአካባቢው ከፍተኛ የወታደራዊ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንደሚኖርም አክሏል። ልምምዱ እስራኤል በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አደራዳሪነት ከኢራን ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ከጀመረች ከቀናት በኋላ ነው።
በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
በህገ- ወጥ መልኩ ከ2 ሺህ በላይ ፕላምፕሌት ይዞ የተገኘ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
በሰቆጣ ከተማ በህገ- ወጥ መልኩ ፕላምፕሌት ከመጋዝን ውስጥ ይዞ የተገኘ ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት አስታወቀ።
የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኤልያስ አስፋ ነዋሪነቱ በሰቆጣ ከተማ 01 ቀበሌ ሲሆን ተከሳሽ አቶ ወንድሙ ቢክሰኝ በ2012 ዓ.ም የወጣው የኢፌድሪ ምግብና መድኃኒት አሥተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2012 አንቀጽ 67/4/ የተደነገገውን በመተላለፍ በምግብ እጥረት ለተጎዱ ህጻናት የመጣን 2ሺህ 1መቶ 83 ፕላምፕሌት ሚያዚያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡ 00 ሰዓት አካባቢ መጋዝን ውስጥ ይዞ መገኘቱን ተከትሎ ክስ ተመስርቷል።
የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት የወንጀል ጉዳዮች ሥራ ሂደትም ከፖሊስ ተጣርቶ የቀረበለትን የምርመራ መዝገብ በመያዝ በተከሳሽ አቶ ወንድሙ ላይ ክስ መስርቶ የሰቆጣ ወረዳ ፍርድ ቤት የፍርድ ብያኔ እንዲሰጠበት ጉዳዩን ሲከታተለው መቆየቱን አቶ ኤልያስ ገልጸዋል።ፍትህ ጽ/ቤቱ በተከሳሽ አቶ ወንድሙ ላይ ያቀረበውን ክስ የሰቆጣ ወረዳ ሲያከራክር ቆይቶ ሰኔ 2 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን ጥፋተኛ በማለት 2 ዓመት እስራትና 5ሺህ ብር እንዲቀጣና በኢግዚቪት የተያዘው 2ሺህ 1መቶ 83 ፕላፕሌትም ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ተወስኗል ሲሉ አቶ ኤልያስ ተናግረዋል።
የፍትህ ጽ/ቤት የተቋቋመው የመንግስትንና የህዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ ነው ያሉት አቶኤልያስ ወንጀል ፈጽሞ ከህግ መሰወር የማይቻል መሆኑንም አስረድተዋል። በጤና ባለሙያዎች ከታዘዘለት ግለሰብ ውጭ ፕላምፕሌት ይዞ የተገኘም ሆነ ሌሎች ወንጀሎችን የተፈጸሙ ማንኛውም ሰው በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን አውቆ ወንጀል ከመፈጸም ሊቆጠብ ይገባል ሲሉ ኃላፊው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በሰብል አበበ

ወደ ሰሜን ኮርያ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሩዝ እና ዶላር ሊልኩ የነበሩ አሜሪካውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ
የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት 1,300 የሚገመቱ የፕላስቲክ ጠርሙሶችን በሩዝ፣በዶላር እና በመፅሀፍ ቅዱስ በመሙላት ወደ ሰሜን ኮሪያ በባህር ሊልኩ ሲሞክሩ የነበሩ ስድስት የአሜሪካ ዜጎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የዜና ዘገባዎች አመልክተዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች የተያዙት አርብ ማለዳ ላይ ጠርሙሶቹን ከሰሜን ኮሪያ ጋር በተከለከለው የፊት ለፊት ድንበር አካባቢ አቅራቢያ ከሚገኘው ከጓንግዋ ደሴት ወደ ባህር ለመልቀቅ ሲሞክሩ ከተያዙ በኋላ ነው ሲል የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣን ዮንሃፕ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
ስድስቱ ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት አካባቢውን የሚጠብቅ የባህር ዳርቻ ወታደራዊ ክፍል ለፖሊስ ካሳወቀ በኋላ ነው። ደቡብ ኮሪያ ከሰሜናዊ ድንበር አቋርጠው የሚመጠ የፕላስቲክ ጠርሙሶች ወይም የሚበር ፊኛዎች ላይ የሚላኩ ቁሳቁሶች በኮሪያ ልሳነ ምድር ላይ ውጥረት ፈጥረዋል። ዮንሃፕ እንዳለው ፀረ ፒዮንግያንግ ፕሮፓጋንዳ ወደ ሰሜን እንዳይጀምር የሚከለክል አስተዳደራዊ ትእዛዝ ለአካባቢው ተግባራዊ ሆኗል ።
እ.ኤ.አ. በ 2023 ፣ የደቡብ ኮሪያ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት የ 2020 በራሪ ወረቀቶችን እና ሌሎች እቃዎችን ወደ ሰሜን ኮሪያ መላክን ወንጀል የሚያደርግ ህግን የሻረ ሲሆን የመናገር ነፃነትን ከመጠን በላይ ይገድባል ብሏል ። ነገር ግን በጁን መጀመሪያ ላይ ስልጣን ከያዙ ወዲህ የፕሬዚዳንት ሊ ጄ-ሚንግ አዲሱ የሊበራል መንግስት ከሰሜን ኮሪያ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት ለማስቀረት እና የግንባር ቀደምት የደቡብ ኮሪያ ነዋሪዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ እንዲህ ያሉ የሲቪል ዘመቻዎችን ከሌሎች ከደህንነት ጋር በተያያዙ ህጎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ እየሞከሩ ይገኛል።
በስምኦን ደረጄ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እስራኤል በዌስት ባንክ 'የግዳጅ ማፈናቀል' እየፈፀመች ነው አለ
የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) በዌስት ባንክ ውስጥ በሚገኘው ማሳፈር ያታ አካባቢ በ3 የፍልስጤም ማህበረሰቦች የሚኖሩባቸው ሁሉም ህንፃዎች እንደሚወድሙ የእስራኤል ጦር ማሳሰቢያ አውጥቷል። ቢያንስ 1,200 ሰዎች፣ ከ500 በላይ ህጻናትን ጨምሮ፣ አሁን ወታደሮቹ ያቀዱትን የማፍረስ ተግባር ከፈጸሙ “በግዳጅ የመፈናቀል” ስጋት ላይ ናቸው ሲል ኦቻ ገልጿል።
በዌስት ባንክ ውስጥ ለፍልስጤማውያን የከፋ ሁኔታ በተመለከተ የቅርብ ጊዜ የኩነት ዘገባ እንዳመናከተው፣ ኦቻ ከሰኔ 13 እስከ 23 ባለው ጊዜ ውስጥ የእስራኤል ወታደሮች 240 የፍልስጤም ቤቶችን እንደ ወታደራዊ መጠለያ እና የምርመራ ማዕከላት ለመጠቀም ለጊዜው “እንደያዙ” ዘግቧል። የቤቶቹ ባለቤቶች በግዳጅ ተፈናቅለዋል ወይም ታስረዋል ሲልም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በወታደራዊው የቤት ወረራ ወቅት ገልጿል።
በዌስት ባንክ ቱልካሬም እና ኑር ሻምስ የስደተኞች መጠለያ ካምፖች 100 የሚጠጉ ግንባታዎች በተለይም ቤቶች በዚህ ወር በእስራኤል ወታደሮች ፈርሰዋል። በምስራቅ እየሩሳሌም ውስጥ ደግሞ 320 የሚጠጉ ነዋሪዎች በሶስት የፍልስጤም ማህበረሰቦች ውስጥ እንደገና የመፈናቀል እና የማፍረስ ዛቻዎች ተደቅኖባቸዋል ሲል ኦቻ አስታውቋል።