በአዲስ አበባ ከተማ ለህፃናት ምቹ ያልሆኑ 105 የህፃናት ማቆያ ተቋማት የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው
የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ቁጥጥር ከሚያደርግባቸው ስልቶች ውስጥ አንዱ ስጋት ተኮር (ሪስክ ቤዝድ) ሲሆን የህፃናት ማቆያ እና የታቱ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ላይ የቁጥጥር ስራ ማከናወኑ ተገልጿል።
በየቦታው ያለው የህፃናት ማቆያ እና ታቱ ንቅሳት አገልግሎት መስጫ በአብዛኛው የተቀመጠውን ደረጃ የማያሟላ እና ለጤና ችግር አጋላጭ የሆኑ አሰራሮች እንዳሉ የሚያሳዩ ጉዳዮች በመኖራቸው ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለመስራት ቅድመ ዝግጅት አድርጓል።
በሁሉም ክፍለ ከተሞች ስጋት ተኮር ቁጥጥር የተደረገ ሲሆን በዚህም በአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በሰኔ ወር በ288 የህፃናት ማቆያናተቋማት ላይ ቁጥጥር ተደርጓል።በዚህ ቁጥጥር ወቅት ለ105 የህፃናት ማቆያ ተቋማት ካለባቸው ችግር ምክንያት የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን አንድ የህፃናት ማቆያ ተቋም ስራ እንዲያቆም ተደርጓል ሲሉ በባለስልጣኑ የምግብ እና ጤና ነክ ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
እርምጃ የተወሰደባቸው ተቋማት ያለባቸው ችግር የጤና ብቃት ማረጋገጫ ሳያወጡ እየሰሩ በመገኘታቸው፤አደረጃጀታቸው ለህፃናት ምቹ ባለመሆናቸው ያለባቸው ችግር እንዲያስተካክሉ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ ተገልጿል።
በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል

ትራምፕ ቲክቶክን ለመግዛት የሀብታም ሰዎች ቡድን አለኝ ሲሉ ተደመጡ
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የክልከላ ቀን የሚጠብቀውን የቲክ ቶክ ቪዲዮ ማጋሪያ መተግበሪያ ብሔራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ ይጥላል በሚል ከመዘጋቱ በፊት ያለውን ስጋት ለመቅረፍ ገዢ አለኝ ሲሉ ተደምጠዋል። በፎክስ ኒውስ ቃለ መጠይቅ ላይ ትራምፕ መተግበሪያውን ለመግዛት ፈቃደኛ የሆኑ “በጣም የሀብታም ሰዎች” ቡድን እንዳላቸው ተናግረዋል። "ከሁለት ሳምንት በኋላ እነግራችኋለሁ" ሲሉ አክለዋል።
ሽያጩ ከቻይና መንግስት ይሁንታ ያስፈልገዋል ነገር ግን ትራምፕ ለፎክስ እንደተናገሩት ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ “ያደርጉታል” ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል። በዚህ ወር ትራምፕ የቲክ ቶክን ለአሜሪካዊ ባለሀብት ወይም ኩባንያ እንዲሸጥ የሚያስገድደው ህግ ተግባራዊ ከመሆን እንዲዘገይ ለሶስተኛ ጊዜ አራዝመዋል። በመጨረሻው ማራዘሚያ የቲክቶክ ወላጅ ኩባንያ ባይትዳንስ መተግበሪያውን እስከ ሴፕቴምበር 17 ለመሸጥ ስምምነት ላይ እንዲደርስ ይጠበቃል።
ባለፈው ሚያዝያ ወር ላይ ቲክቶክን ለአንድ አሜሪካዊ ገዢ ለመሸጥ የተደረሰው ስምምነት በትራምፕ ታሪፍ የተነሳ ከቻይና ጋር ግጭት በመፈጠሩ ድርድሩ ፈርሷል። አሀን ላይ ትራምፕ ገዥ አለ የሚሉት ከሦስት ወራት በፊት ከነበረው ጋር ተመሳሳይ ኩባንያ ስለመሆኑ ግልጽ አይደለም።የዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስ የቲክ ቶክን ሽያጭ የሚያስገድድ ህግ ባለፈው አመት በሚያዝያ ወር ያፀደቀ ሲሆን በህጉ ቲክ ቶክ ወይም ወላጅ ኩባንያው የአሜሪካን የተጠቃሚዎች መረጃ ለቻይና መንግስት አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል በሚል ስጋት መሆኑን በመጥቀስ ሲሆን ቲክ ቶክ ግን ውንጀላውን የሀሰት ሲል ውድቅ አድርጓል።
ትራምፕ በመጀመሪያ የስልጣን ዘመናቸው ቲክቶክን አያስፈልገንም ሲሉ ተችተውት ነበር፣ ነገር ግን በ 2024 ምርጫቸው ለአሸናፊነታቸው እንደ አንድ ምክንያት አድርገው በመልከት ቲክቶክ በአሜሪካ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዲውል ይደግፋሉ።ህጉ በጥር 19 ተግባራዊ መሆን ነበረበት፣ ነገር ግን ትራምፕ በአስፈፃሚ የትዕዛዝ ስልጣናቸውን በመጠቀም በተደጋጋሚ እንዳይተገበር አዘግይተዋል፣ ይህ ውሳኔያቸው የኮንግረሱ ህግ አውጪዎችን በመቃወም ትችት አስከትሏል። ቲክ ቶክ የሕጉን ሕገ መንግሥታዊነት ተቃውሟል፣ ነገር ግን ለአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢልም ጥያቄው ውድቅ ተደርጓል።
በስምኦን ደረጄ

በጋምቤላ ክልል የወንዶች ግርዛት ሽፋን ዝቅተኛ በመሆኑ የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭትን ለመግታት ጫናን ፈጥሯል ተባለ
የወንዶች ግርዛት ኤች አይቪ ኤድስን ለመከላከል ከሚረዱ መንገዶች ውስጥ አንዱ ቢሆንም በጋምቤላ ክልል ያለው የወንዶች ግርዛት ሽፋን ግን በጣም አነስተኛ መሆኑን የክልሉ ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት አስታውቋል።
በጽ/ቤቱ የዘርፈ ብዙ ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አቡላ ድንጉር ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በክልሉ በወንዶች ግርዛት ዙሪያ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ ቢቆዮም አሁንም ሽፋኑ በጣም ዝቅተኛ ነው።በክልሉ የሚታየው ያለመገረዝ ባህል ለዚህ ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ ገልፀው የወንዶች ግርዛት ሽፋኑ ከ50 በመቶ እንደማይልቅ ተናግረዋል።
ቫይረሱን ለመከላከል ከሚረዱ መንገዶች መካከል ግርዛት አንዱ መሆኑን አቶ አቡላ በመግለፅ የወንዶች አለመገረዝ ደግሞ ለቫይረሱ ስርጭት ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል።በክልሉ የኤችአይቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭት ከፍተኛ በመሆኑ የነገ ሀገር ተረካቢ በሆኑት አፍላ ወጣቶችና ልጃገረዶች ላይ እያስከተለ ያለው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ጤናማ ዜጋን ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል ነው የተባለው።
አንድ ወንድ ከተገረዘ የቫይረሱን ስርጭት በ60 በመቶ እንደሚከላከል የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ በክልሉ ያለውን የስርጭት መጠንን ለመቀነስ የወንዶች ግርዛት ሽፋንን ለማሻሻል የሚያስችሉ የግንዛቤ ስራዎች እንደሚሰሩ ተገልጿል።
ቅድስት ደጀኔ

ከጥር ጀምሮ ቢያንስ 239 ህጻናት በምዕራብ ሱዳን ህይወታቸው ማለፉ ተነገረ
በምዕራብ ሱዳን ከጥር ወር ጀምሮ ቢያንስ 239 ህጻናት በቂ ምግብ እና መድሃኒት ባለማግኘታቸው መሞታቸውን የሱዳን ዶክተሮች ኔትወርክ አስታውቋል። የሲቪል ህክምና ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ከጥር እስከ ሰኔ መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ የሰሜን ዳርፉር ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ኤል ፋሸር ከተማ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ሳቢያ ሕጻናት መሞታቸውን እና የምግብ እና የህክምና አቅርቦቶችን አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ቡድናቸው መዝግቧል። በኤል ፋሸር የህጻናት የምግብ መጋዘኖች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ረሃብ እየጨመረ እንደሚሄድ አስጠንቅቋል።
"ኔትወርኩ በሚፈፀመው ጥቃት ብፕጥልቅ ተጸጽቷል፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በዳርፉር ልጆች ላይ ከአንድ አመት በላይ ከበባ ቢፈፀምም ቸልተኝነቱም ቀጥሏል" ሲል በመግለጫው ገልጿል።ኤል ፋሸር እና አካባቢው በሰሜን ዳርፉር ግዛት የሚገኙ ካምፖች የምግብ እና የህክምና አቅርቦቶች ከሞላ ጎደል ሙሉ ለሙሉ መቅረታቸው እና ለመሠረታዊ ፍላጎቶች የማይመች እየሆኑ እንደሚገኝ አስታውቋል። በኤል ፋሸር ያለማቋረጥ እየተከበበ እና በቦምብ ጥቃት እየተፈፀመባቸው ያሉ ዜጎችን ለመታደግ አስቸኳይ ጥሪ አቅርቧል። በተጨማሪም ክልላዊ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ የቀረበውን የእርቅ ስምምነት እንዲቀበሉ እና ተግባራዊ እንዲያደርጉ ፈጣን ድጋፍ ሰጭ ሃይሎች ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳስቧል።
መግለጫው አክሉም የሰብአዊ ኮሪደሮችን ለመክፈት አፋጣኝ ዕርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፣ የአደጋ ጊዜ ዕርዳታ እና የህክምና ቁሳቁስ አቅርቦት እንዲኖር እንዲሁም በኤል ፋሸር ላይ ከአንድ አመት በላይ የቆየውን ከበባ እንዲነሳ ጥሪ አቅርቧል።በዳርፉር አምስት ግዛቶች ውስጥ ለሰብአዊ ተግባራት ዋና ማዕከል በሆነችው በከተማው ስላለው ጦርነት ዓለም አቀፍ ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም በሱዳን ጦር እና በአርኤስኤፍ መካከል የተደረገው ጦርነት ኤል ፋሸርን ከግንቦት 10 ጀምሮ አናግቷል። የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር አብደል ፈታህ አል ቡርሃን በኤል ፋሸር የሰባት ቀናት የሰብአዊ ተኩስ አቁም አጽድቀዋል። ውሳኔው የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በስልክ ያደረጉትን ጥሪ ተከትሎ የመጣ መሆኑን የሉዓላዊው ምክር ቤት መግለጫ አስታውቋል።

Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
የሜሲ ቁጥር አንድ ደጋፊ የሆኑት አዛዉንት ከዚህ ቀደም "ሜሲ ታገባኛለህ ወይ" ብለዉ የሚዲዎችን ቀልብ ስበዉ ነበር።
በትናንትናው ምሽት የፔዤ እና ሚያሚ ጨዋታ ላይም ታድያ "ሜሲን እወደዋለሁ" የሚል ጽሁፍ ይዘዉ ታይተዋል።
#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport

በሀረር ክልል ለ1ሺህ 214 የግል ድርጅትና ታክስ ከፋዮች የቀን ገቢ ግምትና የደረጃ ሽግሽግ መደረጉ ተገለፀ
ለ1ሺህ 214 የግል ድርጅትና ታክስ ከፋዮች የቀን ገቢ ግምትና የደረጃ ሽግሽግ መደረጉን የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ያሲን አብዱላሂ አስታወቁ። የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ያሲን አብዱላሂ በክልሉ ፍትሃዊ የታክስ ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ከታክስ ስርዓት ፍትኃዊነት ጋር በተገናኘ ሲነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ሁሉም ግብር ከፋይ ሚዛናዊነትና ፍትሀዊነቱን በጠበቀ መልኩ በሚያገኘው ገቢ ልክ ተመጣጣኝና ፍትሀዊ ግብርና ታክስ እንዲከፍል መደረግ አለበትም ብለዋል። እያንዳንዱ ግብር ከፋይ በተሰማራበት የሥራ ዘርፍ የንግድ እንቅስቃሴ መረጃ ላይ ተመስርቶ የሚከፍለውን ታክስ ለመወሰን ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ሲሰራ መቆየቱንም ጠቁመዋል።ግብረ ሀይሉ የንግድ ተቋማትን የንግድ ስራ እንቅስቃሴ ይዘትና ስፋት እንዲገመግም በማድረግ የደረጃ ማሻሻያዎች መደረጋቸውንም ጠቁመዋል። በንግድ ተቋማቱ በተሰራው የሪፎርም ስራም በክልሉ ለ 1 ሺ 214 የግል ድርጅትና ታክስ ከፋዮች የቀን ገቢ ግምትና የደረጃ ሽግሽግ መደረጉን ኃላፊው ገልፀዋል።
በዚህም መሰረት 186 ድርጅቶች ዓመታዊ ገቢያቸውን መሰረት ባደረገ መልኩ ደረጃቸው ከፍ እንዲል የተደረጉ ሲሆን 24 የንግድ ተቋማት ደረጃቸው ዝቅ መደረጉን ገልፀዋል። ይህም የታክስ ፍትሀዊነትን ከማረጋገጥ ባሻገር በውድድር ላይ የተመሰረተ ፍትሀዊ የታክስ እና የንግድ ስርዓትን ለማስፈን የሚያስችል መሆኑን አክለዋል።
የቀን ገቢ ግምትና የደረጃ ሽግሽጉ የገቢ ዘርፍ ፍትሃዊነትና የህግ ተገዢነትን ለማሻሻል የተጀመረ የሪፎርም አካል መሆኑንም ገልፀዋል። እያንዳንዱ የግብር ከፋይ ከ ሀምሌ 1 /2017 ጀምሮ በአዲሱ የቀን ገቢ ግምት ዓመታዊ ግብሩን እንዲከፍል እንደሚደረግ የቢሮው ሀላፊው አቶ ያሲን አብዱላሂ አስታውቀዋል።በቀጣይም በክልሉ በሁሉም የግብር ከፋይ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦች ወቅታዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ታሳቢ ያደረገ ፍትሃዊ የቀን ገቢ ግምትና የደረጃ ሽግሽግ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የቀን ገቢ ግምቱና የደረጃ ሽግሽጉ የገቢ ዘርፍ ፍትሃዊነትና የህግ ተገዢነት ለማሻሻል የተጀመረ የሪፎርም አካል መሆኑንም አክለው ገልፀዋል።
በሰመኃር አለባቸዉ

በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ መስመር ለመስራት ኮርኒስ ውስጥ የገባው ወጣት ኤሌክትሪክ ይዞት ህይወቱ አለፈ
ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ገደማ በቦሌ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 14 ገርጂ ካዲስኮ አካባቢ በግለሰብ መኖሪያ ቤት የኤሌክትሪክ መስመር ለማስተካከል ጥረት ሲያደርግ የነበረ ዕድሜዉ 27 ዓመት የሆነ ወጣት በኤሌክትሪክ ተይዞ ህይወቱ ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
ወጣቱ በመኖሪያ ቤት ከኮርኒስ ዉስጥ ያለን የኤሌክትሪክ መስመር ለመስራት ገብቶ ህይወቱ ማለፉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ።የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ህይወቱ ያለፈዉን ወጣት ከኮርኒስ ዉስጥ አዉርደዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።
ከኤሌክትሪክ ጋር የተያያዙ ስራዎች ሲከናወኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስፈልገዉ ስራ በመሆኑ በተለይም የኤሌክትሪክ ኃይል ባለበት ሁኔታ መስመሩን መነካካት መሰል አደጋ የሚያስከትል በመሆኑ ማናቸዉንም የጥገና ስራውችን በአቅራቢያ ካለ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መ/ቤት ባለሞያ መጠየቅ መፍትሄ ነዉ መሆኑን ኮሚሽኑ ጠቁሟል።
በትግስት ላቀው

ሚንስትሩ የመኪና አደጋ እንደደረሰባቸው ተረጋገጠ
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ እያሉ ከምሽቱ 1:00 አካባቢ መኖሪያ ቤታቸው የሚገኝበት ካርል አደባባይ ላይ ድንገተኛ የመኪና አደጋ ደርሶባቸው ነበር ያለው ሚንስትር መስሪያ ቤቱ በእለቱ ሚኒስትሩ ወደ ሆስፒታል አምርተው በቂ የህክምና አገልግሎት አግኝተው አሁን ላይ በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ በባህላዊ ትብብር ዙሪያ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
ሰሜን ኮሪያ እና ሩሲያ በባህልና በኪነጥበብ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል። የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና የሩሲያ የባህል ሚኒስትር ኦልጋ ሊዩቢሞቫ እሁድ እለት በፒዮንግያንግ ባደረጉት ውይይት ነው መግባባት ላይ የተደረሰው ሲል የኮሪያ ማዕከላዊ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
በገዥው ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዋና ፅህፈት ቤት የተካሄደው ውይይት በሰሜን ኮሪያ የሩሲያ አምባሳደር አሌክሳንድር ማሴጎራ ተገኝተዋል። ስብሰባው የተካሄደው የሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ፀሐፊ ሰርጌይ ሾይጉ ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ባደረጉት ሁለተኛ ጉዟቸው ፒዮንግያንግ ከጎበኙ ከቀናት በኋላ ነው። ሊዩቢሞቫ ቅዳሜ እለት ፒዮንግያንግ የደረሱት የሀገሪቱን አጠቃላይ የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት አንደኛ አመት ለማክበር ልዑካንን እየመሩ ነበር።
በውይይቱ ወቅት ኪም ስምምነቱ ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ዘርፎች የታዩትን ''ሰፊ እና ጥልቅ'' ልውውጦች እና ትብብር አድንቀው ለሁለቱ ሀገራት ህዝቦች የጋራ እድገትና ደህንነት ተጨባጭ አስተዋጾ አድርገዋል ብለዋል። የሉቢሞቫ ጉብኝቷ የተደረገው የሰሜን ኮሪያ እና የሩስያ ወዳጅነት እና አብሮነት "ጥንካሬ እንዲሁም አለመሸነፍ" ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በግልፅ እየታየ ባለበት እና የሁለትዮሽ የባህል ትብብር "በከፍተኛ ደረጃ ላይ" በደረሰበት ወቅት ነው ስትል ተደምጣለች።

በትግራይ ክልል የግዚያዊ መንግስት በሚያስተዳድራቸው ወረዳዎች ብቻ ከ650 ሺህ በላይ አካል ጉዳተኞች መኖራቸው ተነገረ
የኢትዮያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በአካል ጉዳተኞች የተደነገጉ መብቶችና ጥቅሞች አከባበርን አስመልከቶ በትግራይ ክልል ያደረገዉ የጥናት ዉጤትና የሰጣቸዉ የመፍትሔው ሀሳቦች አቅርቧል ።ከጠቅላላው የዓለም የህዝብ ብዛት መካከል አንድ ቢሊዮን የሚሆኑት በአእምሮ፣ በአካልና በስሜት ህዋሳት ላይ በሚደርስ የአካል ጉዳት ምክንያት አካል ጉዳተኞች እንደሆኑ ይገመታል ። ከዚህ ቁጥር 785 ሚሊዮን በሥራ የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ናቸዉ፡፡ በተለይም ከጠቅላላው የአካል ጉዳተኛው ብዛት 80 % የሚሆኑት አካል ጉዳተኞች በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት እንደሚገኙ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ ከዚህም በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች ውስጥ 70% የሚሆኑት የህክምናና ሌሎች መሠረታዊ የተሃድሶ አገልግሎቶች ባልተዘረጋባቸው በገጠር አካባቢዎች እንደሚኖሩ ጥናቱ አብራርቷል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ ቁጥራቸው በርከት ያሉ አካል ጉዳተኞች እንደሚገኙ የሚገመት ሲሆን 84 በመቶ አካል ጉዳተኞች ለመሰረታዊ አገልግሎት ተደራሽ እንዳልሆኑ ጥናቶች ያመላክታሉ መባሉን የኢትዮጵያ እምባ ጠባቂ ተቋም የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈጻሚ አቶ አንለይ ወርቄ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።በሌላ በኩል በትግራይ ክልል በ2016 ዓ.ም በተደረገው የዳሰሳ ጥናት ከ6,916,319 ህዝብ ብዛት መካከል የግዚያዊ መንግስት ከሚያስተዳድራቸው ወረዳዎች ብቻ ከ650,000 በላይ አካል ጉዳተኞች መኖራቸው ተነግሯል። በክልሉ የተዘረጉት የጤናና ሌሎች መሠረታዊ አገልግሎቶች በበቂ ሁኔታ ተደራሽ ባልሆኑ በገጠር አካባቢዎች የሚኖሩ መሆናቸውን መረጃው ያመላክታል፡፡
ትግራይ ከአገሪቱ ሁኔታ ለየት ባለ መልኩ ተደጋጋሚ ጦርነቶች የተካሄዱበት ክልል ስለሆነ ቁጥሩ ከፍ ያለ መሆኑ የተለያዩ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ የአካል ጉዳተኞች መብቶቻቸው ከማስጠበቅና ጥቅሞቻቸውን ከማስከበር አኳያ የአስተዳደር በደሎች መኖራቸውን የተለያዩ ምንጮች በማመልከት በህግ ማዕቀፎች አፈፃፀም ላይ ጥርጣሬ በማሳደር በተደጋጋሚ ቅሬታዎች እንደሚቀርቡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1142/2011 አንቀፅ 7(5) ተሻሽሎ በወጣው 1307/2016 መሰረት ለተቋሙ አስተዳደራዊ በደሎች የሚቀረፍበትን ሁኔታ የማጥናትና ምክረ ሀሳብ የማቅረብ ስልጣንና ተግባር ተሰጥቷል:: በዚህም መስረት መቐለ ቅርንጫፍ በአካል ጉዳተኞች የተደነገጉ መብቶችና ጥቅሞች አከባበር ላይ በትግራይ ክልል በተመረጡ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጥናት ማካሄድ ተችሏል፡፡
የጥናቱ ዋና ዓላማ ለአካል ጉዳተኞች የተደነገጉ መብቶችና ጥቅሞች መከበራቸውን በማረጋገጥ የሚስተዋል የህግ፣ የፖሊሲ ወይም የአሰራር ክፍተቶችና መንስኤዎቻቸውን በመለየት ምክረ-ሀሳብ በመስጠት አፈፃፀሙን በመከታተል ክፍተቶቹ እንዲታረሙ በማድረግ አካል ጉዳተኞች ከአስተዳደራዊ በደል የፀዳ አገልግሎት እንዲያገኙና መልካም የመንግስት አስተዳደር እንዲሰፍን እየተሰራ መሆኑን መሆኑን አቶ አንለይ ወርቄ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በኤደን ሽመልስ

ቱርክ በኢዝሚር የተቀሰቀሰውን ሰደድ እሳት እየተዋጋች ሲሆን ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው ወጥተዋል
በቱርኪ ምዕራባዊዋ ኢዝሚር ግዛት ውስጥ የሚገኙ አራት መንደሮችን እና ሁለት ሰፈሮች ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ለቀው ለመውጣት የተገደዱ ሲሆን ለሁለተኛ ቀን የእሳት አደጋ ተከላካዮች ሰደድ እሳት ለማስቆም እየተፋለሙ እንደሆነ የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል። የደን ጥበቃ ሚኒስትር ኢብራሂም ዩማክሊ ሰኞ እለት እንደተናገሩት እሳቱ በአይዝሚር በኩዩካክ እና ዶጋንቤይ አከባቢዎች ከ40-50 ኪሜ በሰአት በደረሰው ንፋስ የተነሳ በአንድ ጀምበር የተቀጣጠለ እንደሆነ ገልፀዋል።
ሄሊኮፕተሮች፣ እሳት ማጥፊያ አውሮፕላኖች እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች እና ከ1,000 በላይ ሰዎች እሳቱን ለማጥፋት እየሞከሩ እንደሚገኝ ዩማክሊ ለጋዜጠኞች በኢዝሚር በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። በቃጠሎው ምክንያት በኢዝሚር አድናን ሜንዴሬስ አየር ማረፊያ የሚደረገው እንቅስቃሴ መቋረጡን የቱርክ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በተቃጠሉ ዛፎች ምልክት የተደረገባቸው ኮረብታዎች ላይ ጭስ እየፈነጠቀ ሲሄድ የእሳት ተከላካይ ቡድኖቹ የውሃ ተጎታች እና ሄሊኮፕተሮች ውሀ ይዘው ለማጥፋት ትራክተሮችን ሲጠቀሙ የሚያሳዩ ምስሎችን የመገናኛ ብዙሃን አጋርተዋል።
የመጀመሪያው የእሳት ቃጠሎ የተከሰተው እሁድ እለት በኢዝሚር ውስጥ በሰፈሪሂሳር እና በመንደሬስ አውራጃዎች መካከል ሲሆን እስከ 117 ኪሎ ሜትር በሰአት ንፋስ ምክንያት በፍጥነት መስፋፋቱን የአካባቢው ገዥ ሱሌማን ኢልባን ተናግረዋል። እሳቱ ወደ መኖሪያ አካባቢዎች ሲቃረብ በሰፈሪሂሳር ውስጥ የሚገኙ የአምስት መንደር ነዋሪዎች ለቀው ወጥተዋል። በደቡባዊ አውሮጳ ያለው ከባድ ሙቀት የሰደድ እሳት እንዲፈጠር ምክንያት እየሆነ ይገኛል።ባለፈው ሳምንት የግሪክ የእሳት አደጋ ተከላካዮች ከአቴንስ በስተደቡብ የባህር ዳርቻ ላይ የተነሳን የደን ቃጠሎ ሲዋጉ ቆይተዋል። ሊዝበንን ጨምሮ በፖርቱጋል ደቡባዊ አጋማሽ ላይ ያሉ በርካታ አካባቢዎች እስከ ሰኞ ምሽት ድረስ በቀይ ማስጠንቀቂያ ስር ነበሩ ሲል የፖርቹጋል የባህር እና የከባቢ አየር ተቋም አስታውቋል።

በከባድ ህመም እየተሰቃዩ የሚገኙ የጋዛ ልጆችን ለማከም የህመም ማስታገሻ መድሃኒት የለም ተባለ
በጋዛ የሚገኙ ሆስፒታሎች “ሙሉ በሙሉ ተጨናንቀዋል፤ በቂ አልጋዎች የሉም፤ እነሱን ለማከም በቂ ሰራተኛ የለም፤ ታካሚዎች ወለሉ ላይ ናቸው” ስትል ከእንግሊዝ የመጣችው የህፃናት ህክምና ነርስ ሃና ግሬስ ፓን ለአልጀዚራ ተናግራለች። በርካታ ታማሚዎች እና ትንንሽ ህጻናት "በጣም በሚያሰቃዩ፣ በፈንጂ ጉዳት እና በቃጠሎ ምንም አይነት የህመም ማስታገሻ መድኃኒት ባለመኖሩ ህክምና እየተደረገላቸው አይደለም" ስትል ተናግራለች።
ግሬስ ፓን ባለፈው ሳምንት ወደ ሆስፒታል የመጣውን የሶስት አመት ህጻን ለአብነት በማንሳት መላው ቤተሰቡ በአየር ጥቃት ከተገደለ በኋላ ብቸኛው በሕይወት የተረፈው እሱ ነው ትላለች። ነገር ግን እሱን ለማከም ምንም ስፔሻሊስት አልነበረም። እናም በቂ የሆነ ፈሳሽ እና ምግብ ከሌለ ቁስሉን ለመፈወስ ብዙ ጊዜ ይወስዳል ትላለች።
ካየቻቸው አስደንጋጭ ጉዳዮች አንዱ የ30 ሳምንት ነፍሰ ጡር ሴት በድንኳኗ ውስጥ በእስራኤል በደረሰባት ጥቃት ደረቷ በጥይት ተመታለች። የሕክምና ባለሙያዎች ሕፃኗን ከሆዷ ውስጥ ሲያወጡት በበረሪ ብረት ጨቅላዋ መሞታቷን እንዳወቁ ግሬስ ፓን ተናግራለች።

ማንችስተር ሲቲ እና ኢንተር ሚላን ከክለቦች የአለም ዋንጫ ዉጪ ሆኑ
ኢንተር ሚላንን ከፍሉሚኔንሴ ያገናኘዉ እና ምሽት 4 ሰዓት የተደረገው ጨዋታ በፍሉሚኔንሴ 2 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
በተመሳሳይ ሌሊት 10 ሰዓት የተጀመረዉ እና ከደቂቃዎች በፊት የተጠናቀቀዉ የሳዑዲዉ አልሂላል እና ማንችስተር ሲቲ ጨዋታም ፤ በሂላል 4 ለ 3 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ለማንችስተር ሲቲ በርናነዶ ሲልቫ ፣ ሃላንድ እና ፎደን ግቦቹን ሲያስቆጥሩ ለአል ሂላል ማርከስ ሊዮናርዶ ፣ ማልኮም ፣ ኩሊባሊ እና በጭማሪ ሰዓት የጨዋታዉ መጠናቀቂያ ላይ በድጋሚ ማርከስ ሊዮናርዶ የአሸናፊነቱን ግብ አስቆጥሯል።
በዚህ መሰረት በሩብ ፍጻሜዉ አል ሂላል ከ ፍሉሚኔንሴ ይገናኛሉ።

እውቁ ድምፃዊ ሞት ለእስራኤል ወታደሮች ሲል በመዝፈኑ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር አወገዙ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዩናይትድ ኪንግደም ዜግነት ያለው እቁው ድምፃዊ ፓንክ ቦብ ቪላን “አሳዛኝ የጥላቻ ንግግር” በማለት ለእስራኤላውያን ወታደሮች “ሞት” በማለቱ አውግዘዋል። የግላስተንበሪ ፌስቲቫል አዘጋጆችም ራፐሩ ቦቢ ቪላን “ነፃ ፣ ነፃ ፍልስጤም” እና “ሞት ፣ ሞት ለእስራኤል መከላከያ ሰራዊት” የሚል ዝማሬዎችን ካቀረበ በኋላ “አስደንጋጭ ነበር” ብለዋል ። ሰር ኪር ስታርመር በሰጡት መግለጫ የቡድኑን ትርኢት የቀጥታ ስርጭቱን በተመለከተ መልስ የሚሰጣቸው ጥያቄዎች እንዳሉት ተናግረዋል።
"በጣም አጸያፊ ናቸው" በማለት የተሰራጨው "በጣም ጠንካራ እና አድሎአዊ ቋንቋ" ላይ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ተናግረዋል።የግላስተንበሪ አዘጋጅ ኤሚሊ ኢቪስ የቦብ ቪላንን ቃል በማውገዝ የጋራ መግለጫ አውጥቷል። “እንደ ፌስቲቫል፣ ሁሉንም አይነት ጦርነት እና ሽብርተኝነትን እንቃወማለን። ሁሌም የምናምነው በተስፋ፣ አንድነት፣ ሰላም እና ፍቅር ነው ሲሉ ተደምጧል።
የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር ለቴሌግራፍ እንደተናገሩት "ለዚህ አይነት አሰቃቂ የጥላቻ ንግግር ምንም አይነት ሰበብ የለም:: ለእንዲህ ዓይነው ሰው መድረክ ሊሰጠው እንደማይገባ ተናግሬአለሁ ይህ ደግሞ ሌሎች ፈጻሚዎች ማስፈራሪያ ወይም ብጥብጥ ለማነሳሳት ነው:: በቢቢሲ እነዚህ ትዕይንቶች በቀጥታ እንዴት ሊተላለፉ እንደቻለ ማብራራት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።