በዩናይትድ ኪንግደም ለ42 ዓመታት ልጆችን ወልደው የኖሩት ግለሰብ እንግሊዛዉ እንዳልሆኑ ተነገራቸው

በዩናይትድ ኪንግደም ለ42 ዓመታት ያህል የኖሩት የ74 አመቱ ጡረተኛ ጋናዊ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በቋሚነት በእንግሊዝ እንዲቆዩ ከመፍቀዱ ውጪ ለቀጣዩ አስር አመታት እንግሊዛዊ መሆን እንደማይችሉ አሳውቋቸዋል።

ኔልሰን ሻርዴይ፣ ከላበእንግሊዝ ዋላሴይ ዊረል በተባለ አካባቢ ሲኖሩ ለበርካታ አመታት በይፋ ራሳቸውን እንደ ብሪቲሽ ዜጋ ያስቡ ነበር። በ2019 ግን ያጋጠማቸው ጉዳይ እንግሊዛዊ እንዳልሆኑ ተረድተዋል። ምንም እንኳን እድሜያቸውን በሙሉ ግብር ቢከፍልም፣ እንግሊዛዊ ለመሆን በቂ እንዳላደረጋቸው እና ነፃ የብሄራዊ ጤና አገልግሎት ለመጠቀም በሺዎች የሚቆጠሩ ፓውንድ የመክፈል ግዴታ ይኖርባቸዋል።

የሀገር ውስጥ ጽሕፈት ቤቱ በመካሄድ ላይ ስላለው የሕግ ጉዳይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። አሁን ጡረታ የወጡት ሻርዴይ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ እንግሊዝ የመጡት እ.ኤ.አ በ1977 ነበር። በተማሪ ቪዛ ለመስራት የቻሉ ሲሆን አካውንቲንግ ተምረው አጠናቀዋል።በትውልድ ሀገራቸው ጋና መፈንቅለ መንግስት ከተፈፀመ በኋላ ቤተሰቦችምቸው ለትምህርት ክፍያ ገንዘብ ሊልኩላቸው አልቻሉም። በዚህም ተከታታይ ጫና ያላቸውን ስራዎች ለመስራት ተገደዋል።

በዳቦ ቤት እና የኪፕሊንግ ኬክ ቤት በሳውዝሃምፕተን አቅራቢያ እና በዊንቸስተር በሚገኘውን የቤንዲክ ቸኮሌት ለዓመታት ሲቀሩ በእንግሊዝ የመኖር ወይም የመሥራት መብታቸውን ተጠይቀው አያውቁም ተብሏል። እንግሊዛዊት ሴት አግብተው የራሳቸውን ንግድ ለመምራት ወደ ዋላሴ አቅንተው ነበር። የኔልሰን ኒውስ የሚባል የዜና ወኪል በመሆንም ለዓመታት ሰርተዋል። ጋብቻቸው በፍቺ ሲደመደም ሌላ እንግሊዛዊት ሴት አግብተው ያዕቆብ እና አሮን የሚባሉ ሁለት ወንድ ልጆችን ወልደዋል።

ሻርዴይ በምችለው መንገድ በሙሉ ልጆቼን ለማስተማር የተቻለኝን ሁሉ ሞክሬያለሁ ሲሉ ተናግረዋል። ልጆቼን ጠንክረው እንዲማሩ፣ ጥሩ ስራ እንዲሰሩ እና ለራሳቸው ብቁ እንዲሆኑ ስነግራቸው ነበር እናም ሁለቱም ወደ ዩኒቨርሲቲ  ከገቡ በኃላ ወደ ምርምር ሳይንቲስት እና የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ ሆነው እየሰሩ ይገኛሉ ይላሉ። ቤቴን ሳይቀር ብዙ እቃ በዱቤ ስገዛ ኖሬያለሁ ለ42 ዓመታት ከእንግሊዝ አልወጣሁም ይላሉ።

በ 2007 የዝርፊያ ወንጀልን በመከላከላቸው ከፖሊስ የጀግንነት ሽልማት ተሰጥቷቸዋል ።ነገር ግን እ.ኤ.አ በ2019 የእናታቸውን ሞት ተከትሎ ወደ ጋና ለመሄድ ፓስፖርት ሲጠይቁ፣ እንግሊዛዊ እንዳልሆኑ ተነግሯቸዋል። የሀገር ውስጥ ቢሮ በዩናፕትድ ኪንግደም ውስጥ የመኖር መብት እንደሌላቸው አሳውቋል። ይህንኑ የደረሰባቸውን ግፍ እየታገሉ ሲሆን እንግሊዛዊ ለመባል ገና ዓመታትን መጠበቅ ይኖርባቸዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
የዋርካ አካዳሚ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተመረቀ

ዋርካ አካዳሚ ከትምህት አመራርና ፔዳጎጂ፣ ከሳይኮሎጂ፣ በዓለም አቀፍ ኪነጥበብ፣ ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ከባንኪንግና አለምአቀፍ ፋይናንስ አመራር ሙያዎች በተውጣጡ ባለሙያዎች የተቋቋመ ተቋም ነው፡፡

ትምህርት ቤቱም በመጪው 2017 አ.ም የትምህርት ዘመን ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍሎቸን በመክፈት ትምህርት ይጀምራል፡፡

ትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማሩን ሂደት በሚያግዙ ዘመናዊ መሰረተ ልማቶች የተሟላ ሲሆን ተጨማሪ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ከውጪ በማስገባት ሂደት ላይ ይገኛል፡፡

ዋርካ አካዳሚ የተማሪዎችን የፈጠራ መንፈስ የሚያነቃቃና በትምህርት ፣ብቃትና በቴክኖሎጂ እውቀት የሚጎለብቱበት ከባቢ ለመፍጠር አልሞ የተነሳ የትምህርት ተቋም ሲሆን በእያንዳንዱ የመማሪያ ክፍሎች ውስጥም ከ25 በላይ ያልበለጡ ተማሪዎችን እንደሚኖሩ ነው የተገለፀው።

ለዚህ በምክኒያትነት ከተቀመጡት ውስጥ ተማሪዎች በጥራት እንዲማሩና መምህራንም ለእያንዳንዱን ተማሪ ተገቢውን ትኩረት ሰጥተው ለማስተማር እንዲያግዛቸው በማሰብ ነው ተብሏል።

ዋርካ ከትምህርት ልህቀት በተጨማሪ የተማሪዎችን ሁለገብ እድገት ላይ የሚያተኩሩ ዘዴዎችንና ስርዓቶችን በመቅረጽ ልጆች በሰብአዊ ክህሎታቸው፣ በስነምግባር፣ በባህሪና በአካል የሚበለጽጉበትን ሁኔታ ለመፍጠር እንደሚሰራም ነው የተገለፀው።

ትምህርት ቤቱ ለመምህራንና ሰራተኞች ተከታታይ ስልጠናዎችን በመስጠት ጥራትን ለመጠበቅና ለማሻሻል የሚሰራ ሲሆን ካደጉ ሀገራትም ልምድ ለመቅሰም ዋርካ አካዳሚ ደቬንቸር ከተሰኘው በስዊዘርላንድ የሚገኝ ተቋም ጋር ስምመነትአድርጓል።

በመአዛ ሀይሌ
#ዳጉ_ጆርናል
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ቪኤአር (VAR) እንዲቀር በሚያደርግ ሐሳብ ላይ ድምፅ ሊሰጡ ነው ተባለ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በሚቀጥለው ወር በሚካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ቪኤአር (VAR) ይቅር ወይስ ይቀጥል የሚለውን በድምፅ ይወስናሉ ተብሏል።

ቪኤአር (VAR) በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ጥቅም ላይ መዋል የጀመረው በአውሮፓውያኑ 2019 ሲሆን ዓላማው በወሳኝ ውሳኔዎች ላይ ዳኞችን ማገዝ ቢሆንም በተለይ በዘንድሮው የውድድር ዓመት በርካታ አከራካሪ ውሳኔዎች ተሰጥተዉበታል ይባላል።

ዎልቭስ ለፕሪሚዬር ሊጉ ባስገባው የመፍትሔ ሐሳብ መሠረት ቀሪዎቹ 20 ክለቦች በቪኤአር ዕጣ ፈንታ ላይ ድምፅ ለመስጠት በመጭው ሰኔ ይሰየማሉ።

ክለቡ እንዳለው ምንም እንኳ "ቪኤአር ለበጎ ሥራ" ቢሆንም ጥቅም ላይ የዋለው "ያልታሰባበቸው በርካታ አሉታዊ ጎኖቹ በደጋፊዎች እና በእግር ኳስ መካከል ያለው ግንኙነት እንዲጠለሽ እያደረጉት ነው።"

የዎልቭስ መግለጫ አክሎ እንደሚለው "የውሳኔን ትክክለኛነት ትንሽ ከፍ ለማድረግ በሚል የጨዋታው መንፈስ እየተነካ ነው።" በፕሪሚዬር ሊጉ ሕግ መሠረት ማንኛውም አዋጅ እንዲፀድቅ ሁለት ሶስተኛ ድምፅ ማግኘት አለበት። ይህ ማለት ከ20 ቡድኖች ቢያንስ 14 ቡድኖች ሊደግፉት ይገባል።

#ዳጉ_ጆርናል
በሻሸመኔ ከተማ ንፋስ በቀላቀለ ከባድ ዝናብ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በከተማዋ ሙሉ በሙሉ ተቋረጠ

በሻሸመኔ ከተማ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ መስመር ላይ ጉዳት በመድረሱ የኃይል አቅርቦት መቋረጡ ተገልጿል።

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን እሮብ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ከባድ ዝናብ በኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመርና የኃይል መስመር ተሸካሚ ምሶሶዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሻሸመኔ ከተማ ዲስትሪክት ሃላፊ የሆኑት አቶ ጣሂር አህመድ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በዚሁ ምክንያት ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ጀምሮ በሻሸመኔ ከተማ እና በዙሪያው በሚገኙ ከተሞችና አካባቢዎች የሃይል አቅርቦቱ ተቋርጧል።

የተቋረጠውን የሃይል አቅርቦት ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን በሻሸመኔ ከተማ እና በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙ ደንበኞቻች አገልግሎቱ እኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቅ እናበአካባቢው የወደቁ ምሰሶዎች ጉዳት እንዳያደርስ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አቶ ጣሂር አህመድ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
በኢትዮጵያ ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ለአይነስውነት ተጋላጭ መሆናቸው ተገለፀ

በኢትዮጵያ አይነ ስውርነት ወይንም የእይታ ችግር መጠነ ሰፊ የሆነ ቀዉስ እያስከተለ እንደሚገኝ የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል ።በሆስፒታሉ የአይን ህክምና ክፍል ሀላፊ ዶክተር ሰለሞን ቡሳ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩትአስራ አምስት አመት በፊት በተደረገ ሀገር አቀፍ ጥናት መሰረት 1 ነጥብ 6 በመቶው የኢትዮጵያ ህዝብ ለአይነ ስውርነት ተጋልጧል።

50 በመቶ የሚሆነው አይነስውርነት መነሻው የሞራ ግርዶሽ ነው ያሉት ዶክተር ሰለሞን እንደ ትራኮማ ያሉ ሌሎች የጤና እክሎች አሉታዊ ተጽእኖ እንዳላቸው ገልፀዋል።በአሁኑ ሰአት 2 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ለአይነ ስውርነት ተጋላጭ እንደሆኑ ገልፀው ከእነዚህ ውስጥ 7 ነጥብ 8 የሚሆኑት አነጣጥረው የማየት ችግር አለባቸው ብለዋል።

እንዲህ ባለው የእይታ ችግር የተጠቁ ሰዎች የእይታቸውን መጠን ተመርምረው ማወቅና መነፅርን በመጠቀም ማስተካከል የሚችሉበት ሁኔታ ሊኖር አንደሚችልም ተናግረዋል።በእይታ ችግር የሚሰቃዮ ዜጎችን ችግር ለመፍታት የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ያስገነባው የመነፅር ማምረቻና መሸጫ ክፍል ስራ መጀመሩን ዶክተር ሰለሞን ገልፀዋል።

ሆስፒታሉ CBM ከተባለ ድርጅት ጋር በመተባበር ያስገነባውን የመነፅር ማምረቻና መሸጫ ክፍል ርክክብ አድርጎ መነፅሩን ለማምረት የሚያስፈልጉ የተለያዩ ግብዓቶችን ሲያሟላ መቆየቱ ተገልጿል። ከዚህ ቀደም የሆስፒታሉ ተገልጋይ ማህበረሰቦች አስፈላጊውን የአይን ህክምና ምርመራ ካደረጉ በሗላ መነፅርን ከግቢ ውጭ የሚገዙ በመሆናቸው ለአላስፈላጊ ወጪ ሲዳረጉ ቆይተዋል በማለት የህክምና ባለሙያው አስረድተዋል።

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን በፓኪስታን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቪዲዮሊንክ ቀረቡ

የፓኪስታን በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን በሀገሪቱ የፀረ ሙስና ህግ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን በሚመለከት ጉዳይ ከእስር ቤት በቪዲዮ አገናኝ በኩል ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ምናባዊ ገለጻ አድርገዋል።ከነሃሴ 2023 ወዲህ ካን በከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ሲቀርብ የመጀመሪያው ነው።

ሆኖም የ 71 አመቱ ካን የሀሙሱ የፍርድ ቤት ውሎ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ድረ-ገጽ ላይ በቀጥታ ያልተላለፈ ሲሆን በሀገሪቱ የዜና ማሰራጫዎች ላይ እንዳልተዘገበ ታዉቋል፡፡ችሎቱ ለምን በዜና ማሰራጫዎች ወይም በጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረ-ገጽ እንዳልተላለፈ የማስታወቂያ ሚኒስትሩን አታላ ታራርን ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

የካን ፓርቲ የሆነዉ ፓኪስታን ተህሪክ ኢ-ኢንሳፍ ዋና ዳኛ ቃዚ ፌዝ ኢሳ ችሎቱ ለህዝቡ እንዳይተላለፍ ባለመፍቀድ ከመንግስት ጋር ተመሳጥረዋል ሲል ከሷል።የተቃዋሚዉ ፓርቲ መሪ አሚር ሙጋል እንደተናገሩት "ፓርቲያችን የሀገሪቱ ዋና ዳኛ ከደህንነት ተቋሙ ጋር ተመሳጥረዋል ብሎ ያምናል እናም አላማቸው ፓርቲያችንን በሁሉም መንገድ መጉዳት ነው" ሲሉ ለአልጀዚራ ተናግረዋል።

በምህረት ታደሰ
#ዳጉ_ጆርናል
በስዊዲን የጎተንበርግ ከተማ ምክር ቤት ከእስራኤል የሚፈጸሙ ግዢዎች ላይ እገዳ እንዲጣል ጥሪ አቀረበ

የስዊድን መገናኛ ብዙሃን የሀገሪቱ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ የሆነችው ጎተንበርግ የአስተዳደር አካል ከእስራኤል ሸቀጦችን መግዛት ማቆም እንደሚፈልግ አስታዉቋል፡፡የስዊድን ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ፣ ግራ ፓርቲ እና አረንጓዴ ፓርቲ በማዘጋጃ ቤቱ አስተዳደር ኮሚቴ ውስጥ አብላጫውን የያዘው ጥምረት ያለዉ ሲሆን የከተማው ምክር ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሌሎች ግዛቶችን ከሚይዙ ሀገራት የሚመጡ የምርት ግዢ ሙሉ በሙሉ እንዲያቆም ሐሳብ አቅርቧል።

በጎተንበርግ የሚገኘው የማዘጋጃ ቤት ቦርድ ሊቀመንበር ጆናስ አቴኒየስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ “እስራኤል በዌስት ባንክ ላይ ህገ-ወጥ ወረራ እያካሄደች ነው፤ በጋዛ ውስጥ በሲቪሎች ላይ መጠነ ሰፊ የግድያና የመብት ጥሰት ተባብሷል ፤ እናም የእኛ የታክስ ገንዘብ ለወረራ ሃይሎች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ የለበትም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ይህዉ ክልከላ ሩሲያ ዩክሬንን በመዉረሯ እንዲሁም ሞሮኮ ምዕራባዊ ሳህራ ላይ በምታሳድረዉ ጫና የተነሳ ከእስራኤል በተጨማሪ  ሞስኮና ራባት ላይ ዉሳኔዉ የሚተገበር ይሆናል፡፡

የእስራኤል ወታደሮች የመኖሪያ ሕንፃዎችን እና አምቡላንስ ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን የፈጸሜ ሲሆን በጃባሊያ ከባድ ውጊያ ቀጥሏል።በጋዛ ሰሜናዊ ክፍል የፍልስጤም ቡድኖች ወራሪ የእስራኤል ወታደሮችን አድፍጠዉ እያጠቁ ሲሆን ከጋዛ የተተኮሰ ሮኬት የተነሳ ረገብ ብሎ የነበረዉ ግጭት በአካባቢዉ ተቀስቅሷል፡፡የጋዛ ጤና ሚኒስቴር ባወጣዉ መግለጫ ከጥቅምት 7 ጀምሮ እስራኤል በጋዛ ላይ ባካሄደችው ወታደራዊ ጥቃት 35 ሺ 2 መጾ 72 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ 79 ሺ 205 ሰዎች መቁሰላቸዉን አስታዉቋል፡፡

የሚኒስቴሩ መግለጫ እንዳስታወቀው ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ቢያንስ 39 ሰዎች ተገድለዋል፡፡በቀጠለዉ ወጊያ የእስራኤል ጦር 40 ሮኬቶች ከሊባኖስ ወደ እስራኤል ይዞታ ወደ ጎላን ኮረብታዎች መተኮሳቸውን ተከትሎ በሂዝቦላና በእስራኤል መካከል የተኩስ ልዉዉጥ እየተደረገ ይገኛል፡፡

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
በወላይታ ዞን ቡዳ ናችሁ በማለት የግድያ ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ ቡጌ ማዘጋጃ አከባቢ ቡዳ ናችሁ በማለት ባልን በመግደል ሚስትን ያቆሰለው ግለሠብ በእስራት  መቀጣቱን ፖሊስ አስታውቋል።

ተከሳሽ አርሷደር ጳውሎስ የተባለው ግለሰብ ተበዳይ ታንጋ ጋኔቦ እና ባለቤታቸው ገበያ ውለው ሲመለሱ ቡዳ ናችሁ በማለት ተበዳይን  በስለት ወግቶ ሲገድል ባለቤታቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የክስ መዝገቡ ያስረዳል።

ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ግለሰብ  ቀደም ብሎም ቡዳ ናችሁና አጠፋችሁአለሁ ብሎ ይዝት እንደነበረ ተገልጿል።የምርመራ መዝገብ የደረሰው የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 06 ቀን 2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት ውሳኔ ሰጥቷል።

ተከሳሽ ጳውሎስ ማጣሉ በሰራው ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ18 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ሀይሌ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በጩቤ ተወግታ ህይወቷ ማለፉ ተሰማ

በአሶሳ ዩኒቨርስቲ በማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ በጅኦግራፊ ትምርት ክፍል ዉስጥ የ4ኛ ዓመት ተማሪ የነበረችዉ ደራርቱ ለሜሳ በስለት ተወግታ ህይወቷ ማለፉን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

የአሶሳ ዩኒቨርስቲ የተማሪዋን ህልፈት ተከትሎ ባወጣዉ የሀዘን መግለጫ ግንቦት 07/2016 ዓ.ም ተማሪ ደራርቱ ምክኒያት ሳይጠቅስ በድንገት ህይወቷ አልፏል ብሏል።

ዩኒቨርስቲው በተማሪ ደራርቱ ለሜሳ ድንገተኛ ህልፈት የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በሙሉ የተሰማሀውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻልም ብሏል። ዳጉ ጆርናል እንዳገኘዉ መረጃ ከሆነ ግን ተማሪዋ በስለት ጥቃት ደርሶባት ህይወቷ ማለፉን ነዉ።

የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ለተማሪ ደራርቱ ቤተሰቦች እና ወዳጆች ሁሉ መጽናናትን ተመኝቷል።

#ዳጉ_ጆርናል
አሜሪካ በሁለት የሱዳን የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች የጦር አዛዦች ላይ ማዕቀብ ጣለች

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣናትና የመብት ተሟጋች ድርጅቶች በሱዳን አል ፋሸር ከባድ ጦርነት ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎች ስጋት ላይ ናቸው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።የመብት ድርጅቶች እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰሜን ዳርፉር ክልል እየተባባሰ የሄደውን እልቂት የሚያስከትል ጥቃትን ተከትሎ አሜሪካ በሁለት የሱዳን ፈጣን ድጋፍ ሰጭ ሃይሎች (RSF) አዛዦች ላይ ማዕቀብ ጥላለች።

ማዕቀቡ ያነጣጠረው የ RSF የማዕከላዊ ዳርፉር አዛዥ አሊ ያጎብ ጂብሪል እና የቡድኑን የስራ ማስኬጃ እቅድ የሚመራውን ዋና ጄኔራል ኦስማን መሀመድ ሃሚድ ላይ ነው ሲል የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስቴር ገልፆል።"የሱዳን ህዝብ ይህ ግጭት እንዲያበቃ መጠየቁን ሲቀጥል እነዚህ አዛዦች ትኩረታቸውን ወደ አዲስ ግንባሮች በማስፋፋት እና ተጨማሪ ግዛቶችን ለመቆጣጠር በመዋጋት ላይ ናቸው" ሲል የግምጃ ቤት ባለስልጣኑ ብሪያን ኔልሰን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

RSF ባለፉት ሳምንታት የሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ የሆነችውን ኤል ፋሸርን ከከበበ በኃላ በወታደራዊ ቡድኑ እና በሱዳን ጦር ሃይሎች መካከል ጦርነቱ ተባብሷል። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ቃል አቀባይ በኤል ፋሸር የተፈጠረው ሁከት ከ800ሺ በላይ ንፁሀን ዜጎችን አደጋ ላይ ጥሏል ማለታቸው አይዘነጋም። ቃል አቀባዩ “ብዙ ሰዎች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ከባድ መሳሪያ መጠቀማቸውንንና በደርዘን የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን፣ ከፍተኛ መፈናቀል እና የሲቪል መሰረተ ልማቶችን መውደም በተመለከቱ የወጡ ሪፖርቶች ጉተሬዝን አስጨንቋል” ብለዋል። በአካባቢው ያሉ ሲቪሎች ቀድሞውንም እያንዣበበ ያለውን ረሃብ እየተጋፈጡ እንደሆነም ተገልፆል።

በ2023 ሚያዝያ አጋማሽ ላይ በRSF እና በሱዳን ጦር ሃይሎች መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በመላዉ ሱዳን ቢያንስ 15ሺ 500 ሰዎች መሞታቸውን የመንግስታቱ ድርጅት ይግለፃል።  ከ 8.8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ቤታቸውን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል።“እስካሁን ሰሜን ዳርፉር ከሌሎች የዳርፉር ክፍሎች ጋር ሲወዳደር በአንጻራዊ ሁኔታ ደህና መሸሸጊያ ነበረ።  አሁን፣ በጎዳናዎች ላይ ተኳሾች አሉ፣ ከባድ ተኩስ እየተካሄደ ነው፣ እናም በከተማው ውስጥ የትኛውም ቦታ ምንም አይነት መሸሸግያ ቦታ የለውም ብሏል።

የዩናይትድ ስቴትስየጣለቺው ማዕቀብ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉትን ኢላማ የተደረጉ ግለሰቦች ንብረቶችን ከእንቅስቃሴ ያቆማል እንዲሁም ማንኛቸውም የአሜሪካ ዜጎች ወይም ድርጅቶች ከነሱ ጋር የንግድ ስራ እንዳይሰሩ ይከለክላል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
ኪሊያን ምባፔ በሰም ከተሰራው የእርሱ አምሳል ጋር እየተፍታታ የሚያሳየው ምስል በብዙሃኑ ዘንድ ፈገግታን ፈጥሯል 😊 🪞

#ዳጉ_ጆርናል
2024/05/16 21:25:00
Back to Top
HTML Embed Code: