መድኃኔዓለም ሆይ፣

የቅዱሳንን ጥሪ ለሚሰማ ጆሮህ እና

ድሆችን ለሚመለከቱ ዐይኖችህ ሰላም እላለሁ::

ፈጣሪየ ክርስቶስ ሆይ፣ ከላይ በዘባነ

ኪሩቤል ላይ ተቀምጠህ የባህሮችን

ጥልቀት ትመለከታለህ ::አቤቱ ሰውነቴን

ከሰይጣን ፈተና ከዐመጸኛ ከተንኮለኛ

አድናት::አቤቱ ባሕሩን አድርቀህ ደረቁ

ሳር የምታለመልም ችሎታ ያለህ አሸናፊ አምላክ ነህና::

📒መልክአ መድኃኔዓለም📒
“ከልቦቻችን በማይነቀሉ የፍቅሩ ችንካሮች ተቸነከርን:: ያዝነው አንለቀውም እርሱም አቀፈን አልተወንም:: ወደ እርሱ በሃይማኖት አቀረበን:: ከእርሱም ወደ ቀኝ ወደ ግራ አንሸሽም:: እንደ ቀለበት በልባችን እንደ ማኅተም በክንዳችን አኖርነው:: እንደ ዕንቁ በልባችን ሳጥን አስቀመጥነው:: እንደ ወርቅ በሕሊናችን መዝገብ አኖርነው::

እንደ ግምጃ ለበስነው:: እንደ ሐር ግምጃ ተጎናጸፍነው:: እንደ ወታደር ሰይፍ ታጠቅነው:: ለጦር ዕቃ እንደተዘጋጀ የድል ጋሻ ተደገፍነው:: ተከዜና ግዮን በኢሎል ወር እንደሚሞሉ ፍቅሩ በልባችን መልቶአል:: እንደ መከር ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ እንደ ክረምት ጊዜም የጤግሮስ ወንዝ ስንዴ ሲያሹት እንደሚሆን እንደ ኤፍራጥስ ወንዝ ልባችንን በወንጌል ፈሳሽነት አረሰረሰው:: መርከባችንንም በሃይማኖት ወንዝ አስዋኘው"

ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
መጽሐፈ ምሥጢር 24:20
Audio
🌊የኤፍራጥስ ወንዝ🌊

ቅዱስ ኤፍሬም

ዲ.ን ሔኖክ ኃይሌ

🎤ሐና ማርያም🎤
“መኑ ይእቲ ዛቲ እንተ ትሔውጽ ከመ ጎሕ ሠናይት ከመ ወርኅ ወብርህት ከመ ፀሓይ” (ይኽቺ እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ እንደ ጨረቃ የተዋበች፤ እንደ ፀሓይም የጠራች ዐላማ ይዞ እንደተሰለፈ ሰራዊት የምታስፈራ ማን ናት?) መኃ ፮
+ የዝምታ ጩኸት +

እስራኤል ጭንቅ ላይ ናቸው:: ከባርነት ተላቅቀው ከግብፅ ከወጡና ጉዞ ከጀመሩ በኁዋላ ፈርኦን የለቀቀው ሕዝብ ጉልበት ቆጭቶት በቁጣ ነድዶ ሠራዊቱን አስከትቶ በፈጣን ሠረገላ እየጋለበ መጣባቸው:: ከፊታቸው ደግሞ የሚያስፈራ ባሕር ተደቅኖአል::

ሕዝቡ የፈረደበት ሙሴ ላይ ጮኹበት:: መጽሐፈ መቃብያን "ያንን ሁሉ ሕዝብ ሲጠብቅ ያልተበሳጨ ሙሴን አስበው" እንደሚል እንደ ሙሴ ትሑትና ታጋሽ መሪ ታይቶ አይታወቅም:: ልክ በዚያች ዛፍ ላይ እሳት ሲነድባት እንዳልተቃጠለች እስራኤላውያንም ሙሴ ላይ ለዓመታት ቢነዱም አላቃጠሉትም::

"በግብፅ መቃብር ጠፍቶ ልታስፈጀን ነው?" "ከሞት ባርነት በስንት ጣዕሙ?"
እስራኤል በኤርትራ ባሕር ዳርቻ ሙሴን በቁጣ እየጮኹ አስጨነቁት::

መሪነት ከባድ ነው:: ያንን ሁሉ ድንቅ ነገር አድርጎ እግዚአብሔር ነፃ ሲያወጣቸው ሙሴ ለእነርሱ ቤዛ ሆኖ ተሹሞ ብዙ ዋጋ ከፍሎአል:: ውለታውን ረስተው አፋጠጡት::

"ሙሴም ለሕዝቡ፦ አትፍሩ፥ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘላለም አታዩአቸውምና ቁሙ፥ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ። እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ፡ አላቸው"

ሙሴ ሕዝቡን ከጩኸታቸው ሲያረጋጋ ሳለ የእግዚአብሔር ድምፅ ወደ ሙሴ መጣ
"ሙሴ ሆይ ለምን ትጮኽብኛለህ?" አለው::

ልብ አድርጉ የጮኸው ሕዝቡ ነው ሙሴ አረጋጋ እንጂ ቃል አልተናገረም::

ሆኖም ሙሴ አፉ ዝም ቢል ልቡ ይጮኽ ነበር:: ከእስራኤል ጩኸት ይልቅ የሙሴ ዝምታ እግዚአብሔር ጆሮ ደረሰ:: እግዚአብሔር ኤልያስ እንዳላገጠባቸው የአሕዛብ አማልክት በጩኸት ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለም:: በትዕቢትና አመፅ ከሞላበት ጩኸት ይልቅ በተሰበረ ልብ የሚቀርብ ዝምታ እግዚአብሔር ጋር ይጮኻል::

የእስራኤል ጩኸት ፍርሃት ይነዛል:: ልናልቅ ነው የሚል ሽብር ይፈጥራል:: የሙሴ ዝምታ ግን ባሕር ይከፍላል::

ጌታ ሆይ ጩኸታችን አልሆነልንም:: ዝምታችንን ሰምተህ ሀገራችንን ከከበባት ጥፋት ታደግልን::
የእኛ መጨቃጨቅና ጠብ ባሕር አይከፍልም::
የእኛ ጩኸት ከመነካከስ በቀር አያሻግርም::
በአርምሞ የሚለምኑህን በእኛ ፊት ዝም አሉ የምንላቸው በአንተ ፊት ግን የሚጮኹትን ሰምተህ ታደገን::

የኤርትራ ባሕር በዝምታ ተከፈለ:: እስከ ራማ የተሰማው ራሔል ስለ ልጆችዋ ያለቀሰችው ዕንባ ባሕር ከፈለ:: እመቤታችን ሆይ ስለ እኛ ስለልጆችሽ እባክሽን አልቅሺ:: የራሔል ዕንባ ራማ ከደረሰ የአንቺ ዕንባ የት ሊደርስ ነው? በየበረሃ እየወደቀ ስላለው ልጅሽ ስለሞተለት ወንድም እባክሽን ለምኚ::

በሙሴ በትር ባሕሩ ተከፈለ:: የኤርትራ ባሕር (ቀይ ባሕር [በግሪኩ erythos ማለት ቀይ ነው]) እጅግ ባለ ታሪክ ባሕር ነው:: ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ደረቅ ሆኖ ፀሐይ ያየውና ግማሽ ሚልየን የሚሆን ሕዝብ በመካከሉ ተራምዶ ያለፈበት ይህ ባሕር እንንደ ግድግዳ የቆመ ብቸኛው የዓለማችን ባሕር ነው::

በዚህ ባሕር እስራኤል ሲሻገሩ ፈርኦን ከነሠራዊቱ ሰጠመ:: በእግር የሔዱት የተሻገሩትን ባሕር በሠረገላ የሔዱት አቃታቸው:: የኤርትራ ባሕር ለእስራኤል ትንሣኤ ሲሆን ለፈርኦን ግን መቃብር ሆነ:: ፈርኦን ደንግጦ መመለስ የነበረበት ባሕሩ ሲከፈል ሲያይ ነበር:: ፈርኦንን ያደቆነ ሰይጣን ግን ባሕር መካከል ሳያቀስስ አልለቀቀውም::
እግዚአብሔር ማን ነው? ብሎ ነበር በዚያ ባሕር ተዋወቀው:: እሱ ሲሰጥም እስራኤል በኩራት "እግዚአብሔር ማን ነው? " ለሚለው የፈርኦን ጥያቄ ከባሕር ማዶ ሆነው መልስ ሠጡ "እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው" አሉ:: እስራኤል በኤርትራ ባሕር መሻገራቸው የጥምቀት ምሳሌ ሆኖ "በባሕርና ደመና ተጠመቁ" ተብሎላቸዋል:: ፈርኦን ግን እስራኤል በተጠመቁበት ጠበል ውስጥ ሰጠመ::

የኤርትራን ባሕር ሲሻገሩ ከሙሴ ሌላ እስራኤልን ሲመራ የነበረ ጠባቂ ነበረ:: እርሱም የእስራኤል ጠባቂ (advocate of Israel) በመባል የሚታወቀው ቅዱስ ሚካኤል ነበር::

"በእስራኤልም ሠራዊት ፊት ይሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ሄደ፤ የደመናውም ዓምድ ከፊታቸው ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ቆመ" ዘጸ 14:19 እንዲል ቅዱስ ሚካኤል እስራኤልን ቀን በደመና ሌሊት በብርሃን ዐምድ እየተመሰለ በመንገድ መራቸው::

ኢትዮጵያውያን ያለነው ከባሕሩ ዳርቻ ላይ ነው:: ሁሉም መሻገር ይፈልጋል:: ከእኛ መካከል እንደ ፈርኦን ሰጥሞ የሚቀር ይኖራል:: እንደ እስራኤል የሚሻገር ይኖራል: : ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ለእኛም ድረስልን:: ይህንን ክፉ ዘመን በክንፎችህ አሻግረን::
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!

ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :-

የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
የቴሌግራም ቻናል : https://www.tg-me.com/deaconhenokhaile
የዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g

If you want to read this article in English :
https://www.facebook.com/111834437163039/posts/129065678773248/
እርሱ ምኞቴ ነው!
ስዕል የመሳል ፍላጎቴ አላስቀምጥ ቢለኝ የገዛሁትን የስዕል መሳያ ይዤ ወደ ቤቴ እየገባሁ አንድ ወዳጄ እንዲህ አለኝ፦
"የያዝሽው ምንድን ነው?"
መለስኩለት"ስዕል መሳያ"
"ክርስቶስን ልትስይ ነው?"አለኝ በለበስኩት ነጠላ  መንፈሳዊነቴን አግዝፎ የሚያይ ሰው ስለነበር መሰለኝ ይሄ ሐሳብ የመጣለት እኔም ፈጠን አልኩና"እርሱ ብቻ ነው የሚሳል?" አልኩት
"እርሱን ብቻ ነው የምታውቂ" አለኝ ይሔ ንግግሩ ልቤ ላይ ቀረ
እንዴት አትሉኝም?
ቃለ ምልልሴን ገትቼ መንገዴን ቀጠልኩ በልቤ እንዲህ እያልኩ፦
ወዳጄ አሁን ያልከው ምኞቴ ነው!
እርሱን ብቻ ባውቅ ሌላ ባላውቅ ደስ ይለኝ ነበር።
ሲፈልጉት ቸል የማይል፣ሁሌም አብሮ የሚኖር ወዳጅ፣ምሽግ፣አምባ፣መጠጊያ እርሱን ብቻ ባውቅ ምኞቴ ነው።
ክፉ ቀን ደግ ቀን አይል የዘላለም ወዳጅ፣ የልብ ደስታ እርሱ ብቻ ነውና እርሱን ብቻ ባውቅ ምኞቴ ነው።
ቅዱሳን ያወቁት አውቀው ደስ የተሰኙበት፣ዓለም ላይ የቃረሙትን ምናምንቴ እውቀት ያስናቃቸው እርሱ አይደል?
ወዳጄ ተሳስቶ ነው እርሱን ብቻ ነው ምታውቂ ያለኝ።
እርሱን ብቻ ማወቅ ግን ለእኔ  ምኞቴ ነው!
አንድ ጥያቄ አለኝ ለእናንተ!
እግራችን ድጁ ይሔዳል ግን ክርስቶስ ያውቀዋል?
እጃችን እመቱን ይነካል ግን ክርስቶስ ያውቀዋል?
ዐይናሽን ጉልላቱን ይመለከተዋል ግን ክርስቶስን ያውቀዋል?
ልባችንስ?
መልሱን በልባችሁ❤️
ወስብሐት ለእግዘአብሔር🙏
@zeboanerges
            23.01.15
#ነቢየ_ጽድቅ
¤ #መፍቀሬ_ጥበብ
#ጠቢበ_ጠቢባን
¤ #መስተሳልም_ወመስተፋቅር
#ሐናጼ_መቅደስ
¤ #ንጉሠ_እስራኤል
#ወልደ_ዳዊት . . .

#ቅዱስ_ሰሎሞን

ለኢትዮዽያውያን ደግሞ በሃይማኖትም ሆነ በተዘምዶ አባታችን ነው::
ከንግሥተ ሳባ #ምኒልክን (ቦይነ ሐኪምን) ወልዶ ተዛምዶናልና::

የበዓሉ በረከት ይደርብን

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር
'
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://www.tg-me.com/zikirekdusn
📝"ተላከ ከአብጋር ዑካማ ለእውነተኛው መድኅን

ለኢየሱስ ክርስቶስ፣በኢየሩሳሌም

ለተገለጥከው።ሰላም ለአንተ ይሁን።

ሥር ሳትምስ ቅጠል ሳትበጥስ ስለምታደርገው

የማዳን ስራ እና ስለ አንተ ዝና ሰምቻለሁ።

እንደነገሩኝ ከሆነ ዕውሩን ታበራለህ ፤ሽባውን

ትተረትራለህ፤ይህንን ስሰማ ወድ እኔ መጥተህ

ከዚህ ከሚያሰቃየኝ የደዌ ዳኛ የአልጋ ቁራኛ

ትገላግለኝ ዘንድ እለምንሃለሁ ። ይህንን ደብዳቤ

ልኬብሃለሁ ። አይሁድ በአንተ ላይ

እንደተነሱብህ ሰምቼአለሁ።ሊገድሉህ ይፈልጋሉ

አሉ ። ምንም እንኳን ከተማዬ ጠባብ ብትሆንም

ውብ ናት! ለእኔ እና ለአንተ ትበቃናለችና ወደ እኔ ና!"
Audio
🎧 ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ🎧

🎤 #በሐና ማርያም🎤

@zeneser
ከፀሐይ አጠገብ የነበረው ኮከብ

የአምላክ ሰው መሆንና ተወልዶ የማደጉ ዜና ሲነገር ሁልጊዜም የሚዘነጋ ክብሩ ግን ከብዙ ቅዱሳን ክብር የሚበልጥ አንድ ታላቅ ሰው ዛሬ በልቡናዬ ውል አለ፡፡ መቼም ከፀሐይ አጠገብ ያለ ኮከብ በፀሐይ ብርሃን ምክንያት መሸፈኑ አይቀርምና በተወለደው የጽድቅ ፀሐይ ፣ የሰላም ንጉሥ በልደቱ ደስታ ተውጠን ፣ በገብርኤል ብሥራት ፣ በድንግል ምስጋና ፣ በመላእክት ዝማሬ ተስበን የዘነጋነውን ፣ ድምቀት ሳያንሰው የተሸፈነውን ኮከብ የቅዱስ ዮሴፍን ነገር ባሰብኩኝ ጊዜ ክብሩን ለመናገር ልቡናዬ ተጨነቀ፡፡

በቅድስናው እያመንን ፣ ውለታውንም እያወቅን የምንዘነጋውን ምናልባትም አንዳንድ ሰዎች የድንግል ማርያምን ዘለዓለማዊ ድንግልና ለማቃለል ስሙን በክፉ ማስረጃነት ሲያነሱብን ከእነርሱ ሸሸን ብለን ሳናውቅ ከበረከቱ የሸሸነውን ጻድቅ ዛሬ ልዘክረው ብል ልቤ በጥፋተኝነት ስሜት ተጨነቀብኝ፡፡

ስለ እርሱ ብዙ ያልዘመርንበትን ፣ ብዙ ያልተቀኘንበትን ዘመን ሳስብ ‘ላዕከ ማርያም ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ስለረሳንህ ቀኛችን ትርሳን ፣ ስላላሰብንህም ምላሳችን ከትናጋችን ይጣበቅ’ ብዬ ይቅርታውን ለመለመን ተመኘሁ፡፡

ቅዱስ ዮሴፍን ማን ብለን እንጥራው? እርሱ እንደሆን እንደ አብርሃም ዘመዶቹን የተወ አማኝ ፣ እንደ ይስሐቅ የታዘዘውን ብቻ ያደረገ ትሑት ፣ እንደ ያዕቆብ በእምነት ግብጽ የወረደ ስደተኛ ነውና እርሱን ለመግለፅ እንደምን ያለ ቋንቋ እንጠቀም ይሆን?

እስቲ ንገሩኝ? ‘መልካሙን እረኛ’ ክርስቶስን የጠበቀውን እረኛ ቅዱስ ዮሴፍን ከቶ በምን ቃል እንገልጸዋለን? የአብን ልጅ ያሳደገውን (ሐፃኔ ወልደ አብ) ቅዱስ ዮሴፍን በምን ቅኔ እናወድሰው?

ሕዝቅኤል ያያትን የእስራኤል አምላክ ገብቶባት ለዘላለም የተዘጋችውን ደጅ የጠበቀውን ታማኝ ዘብ ፤ ‘ከበሩ ደጀ ሰላም መንገድ በዚያ ይገባል በዚያም ይወጣል’ ተብሎ የተነገረለትን የተዘጋችው በር ደጀ ጠኚ ፣ ከታላቅዋ ተራራ ከድንግል ማርያም ያለ ሰው እጅ ድንጋይ ተፈንቅሎ ሲወርድ ቆሞ የተመለከተውን የሐዲስ ኪዳኑን ዳንኤል ከቶ እንዴት ባለ ቃል እንገልጸዋለን?

በቤተ ልሔም ግርግም ውስጥ በላምና አህያ መካከል የተኛውን ሕፃን የተመለከተውንና እንደ ነቢዩ ዕንባቆም
‘በማዕከለ ክልዔ እንስሳ ርኢኩከ’ /በሁለት እንስሳ መካከል አየሁህ/ ሊል የሚቻለውን የቅዱስ ዮሴፍን ክብር በምን አቅማችን እንግለጸው?

ወደ ግብጽ ወርዶ ለወገኖቹና ለዓለም ሁሉ ምግብን እንዳቆየው የብሉይ ኪዳኑ ዮሴፍ ወደ ግብጽ በመከራ ተሰድዶ የሕይወት እንጀራ ክርስቶስን ለሁላችን ላቆየልን ጻድቅ እንዴት ያለ የምስጋና ቃል እናዋጣ?

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ለቅዱስ ዮሴፍ ዝክር ሐምሌ 26
ከብርሃን እናት ገፆች የተቆረሰ
(ወተዘከረኒ ለኃጥእ ገብርከ ተክለ ማርያም )
🛑🛑የምስራች እንኳን ደስ አላችሁ የተዋህዶ ልጆች አክሊል ሚዲያ ተተኪ ዘማርያን የምናፈራበት መዝሙራት ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃዎች የተለያየ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚተላለፍበት መንፈሳዊ ሚዲያ ተከፈተ አሁኑኑ ሰብስክራይብ ያድርጉ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ ለነፍስዎ ብዙ ነገር ያተርፋሉ@aklil media


https://youtu.be/-S_ZG86A9Bc?si=0HlMPv5UnuqJ9Vv4
Audio
🎤በሞት የተገለጠ ፍቅር🎤

💠 💠 💠 💠

✍🏽 ጸሐፊ ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ
🤑💵 🇫 🇴 🇷 🇪 🇽 𝗧𝗿𝗮𝗱𝗶𝗻𝗴 መማር የምትፈልጉ አንድ የሚገርም የ Forex  ቻናል ያውቃሉ

💶  𝗖𝗶𝘁𝘆 𝗙𝗼𝗿𝗲𝘅 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮 💶

@CityForexEthiopia ይባላል ።
ተመዝገባችሁ መማር የምትፈልጉ አናግሯቸው እስከ 𝟰𝟬% Discount የሚደርስ ቅናሽ አድርገዋል !

    ☎️   +251977338586       🇪🇹
    ☎️   +251977338586       🇪🇹

ይህን ይጫኑ የ Telegram ቻናላቸውን ለማግኝት  👇👇

https://www.tg-me.com/+haUXQMQqaqFjNDc8
https://www.tg-me.com/+haUXQMQqaqFjNDc8
https://www.tg-me.com/+haUXQMQqaqFjNDc8


👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆

🎯 𝗔𝗱𝗱 𝗬𝗼𝘂𝗿 𝗖𝗵𝗮𝗻𝗻𝗲𝗹
2024/05/05 08:06:23
Back to Top
HTML Embed Code: