" በሰው ፊት ትልቅ መስሎ መታየት ያስፈራል! "
በስመ ሥሉስ ቅዱስ፥ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ!
=>ታላቁ ጻድቅ #አባ_ዓቢየ_እግዚእ ለደቀ መዛሙርቶቻቸው "ዘሰ ውዱስ በኀበ ሰብእ: ኅሡር ወትኁት ውእቱ በኀበ #እግዚአብሔር (በሰው ዘንድ ምስጉን የሆነ ክርስቲያን በፈጣሪው ዘንድ የተናቀ: ታናሽ ነው)" እያሉ ያስተምሩ ነበር::
+#የክብር_ባለቤት #ጌታችንም "ነስኡ እሴቶሙ (ዋጋቸውን በውዳሴ ከንቱ ወስደዋል) ብሏል:: (ማቴ. 6:2)
+በዚህ ምድር የውዳሴ ከንቱን ያህል ጨካኝ ጠላት የለም:: ብዙዎቻችን እግዚአብሔርን ልናከብር በወጣንበት መድረክ ራሳችንን አስከብረን (እኛው ተመልከን) ወርደናል::
+ሊቁ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈ_ወርቅ ውዳሴ ከንቱን በእንጭጩ እንድንቀጨው ይመክረናል:: አልያ ዋርካ ካከለ በኋላ ለመንቀል ሳይሆን ለመነቅነቅ እንኳ ከባድ ኃይልን ይፈልጋል::
+ብዙ የመድረክ ሰዎች የተወድሶ በሽታ ስለ ለከፈን በየጉባኤው ካልተመሰጋገንን እግዚአብሔር የከበረ አይመስለንም:: የእኛ ሕዝብ ደግሞ በትንሽ ምክንያት ክንፍ አስበቅሎ መልአክ ማድረጉን ያውቅበታል::
+በዛው ልክ ትንሽ ውድቀት ያገኘው ቀን ደግሞ "መልአክ" ያለውን ሰው ጥፍርና ቀንድ አስበቅሎ ባንዴ ሰይጣን ያደርገዋል::
+ይህንን እንድል ያስገደደኝ በአገልግሎት በቆየሁባቸው ዘመናት ያየሁዋቸው ብዙ ነገሮች ናቸው:: "ብዙ ቢያወጉ ይዘነጉ: ብዙ ቢተቹ ይ'ሰለቹ" ነውና ይህቺን #የጌታ_ቃል ብቻ ላክል::
+"#ገቢረክሙ_ኩሎ_ዘአዘዝኩክሙ_በሉ_አግብርት_ጽሩዓን_ንሕነ (ያዘዝኳችሁን ሁሉ ፈጽማችሁ፥ የማንጠቅም ባሮች ነን በሉ)":: (ሉቃ. 17:10)
+ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ:: (ሮሜ. 13:3) ግን ለማን? ምን ዓይነት ክብር? እንደሚገባ እንለይ:: ደግሞም በመጠን እናድርገው:: በልኩ ያልሆነ መደናነቅና መመሰጋገን አመስጋኙንም: ተመስጋኙንም አይጠቅምም:: አንድም በቁሙ ባዕድ አምልኮ ነውና::
+ለዛው አይደል አበው "አመስጋኝ አማሳኝ (አጥፊ)" ሲሉ የነገሩን::
በሉ እንግዲህ! ከሚያደንቁን ይልቅ የሚተቹንን እንድንቀርብ: በጎው ትህትና ገብቶን ለርስቱ እንድንበቃ የቅዱሳን አምላክ ይርዳን::
የጻድቁ አቡነ ዓቢየ እግዚእ አማላጅነትም አይለየን፡፡
<< እኛንም በጸሎት አስቡን! >>
<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>
<< አሜን >>

✝✝✝ ተአምሪሁ ለጻድቅ አቡነ ዓቢየ እግዚእ - - - ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም:: አሜን:: ✝✝✝
☞ከበዙ ተአምራቱ አንዱን፡-
=>ጻድቁ #አባ_ዓቢየ_እግዚእ በገዳማቸው #ተንቤን (መረታ) ሳሉ አንዲት መበለት መጥታ "አባቴ! የምጠጣውን ጸበል ባርከህ ስጠኝ?" አለቻቸው:: ጻድቁም በውሃው ላይ ጸሎትን አድርሰው : በመስቀላቸው ባርከው ሰጧት::
+ወደ ባልንጀራዋ ስትደርስ ግን ሐሳቧን ቀየረችና "ልጠጣው" ብላ የተቀበለችውን ማይ (ጸበል) ልትጠመቅበት (ልትጸበልበት) ወሰነች:: ባልንጀራዋንም "በላዬ ላይ አፍሺልኝ" ስትል አዘዘቻት::
+ባልንጀራዋም "እሺ" ብላ ልታፈስላት (ልትጸብላት) በፋጋ (ግማሽ ቅል) ያለውን ጸበል አነሳች:: ልታፈሰው ስትዘቀዝቀው ግን ከሆነው ነገር የተነሳ 2ቱም ደነገጡ:: ጸበሉ የረጋ ደም ወደ መሆን በቅጽበት ተለውጧልና::
+ፍጹም ፍርሃት የወደቀባቸው ሴቶቹ እየተሯሯጡ ወደ አባ ዓቢየ እግዚእ በዓት ደረሱ:: ከውጭ ሆነውም "አባ! አባ! የሰጠኸን ጸበልኮ የረጋ ደም ሆነ" አሏቸው:: ጻድቁም እንዳላዋቂ "ምን አጠፋችሁ?" ሲሉ ጠየቁ::
+"አባታችን! ምንም አላጠፋንም:: ብቻ አፍሺልኝ ብየ ስሰጣት እንዲህ ሆነ" ስትል አንዷ መለሰች:: ጻድቁ ግን በየውሃት "ልጆቼ! ሁሌም : 'ምንም አላጠፋንም' አይባልም:: ሰው ሆኖ የማይበድል የለምና::
+ . . . አንቺም ልጄ! እኔን ያልሺኝ 'የምጠጣው ጸበል ስጠኝ' ነበር:: ግን ልትጸበይበት ወደድሽ:: ስሕተትሽ ከዚህ ይጀምራል:: (የቅዳሴ ጸበል ለመጸበል አይሆንምና)
¤በዚያ ላይ "አልቦ ዓቢይ ኃጢአት ከመ ወልጦ ቃል . . . ከውሸት በላይ ከባድ ኃጢአት የለም::" (ዮሐ. 8:44)
+ . . . በተጨማሪ ደግሞ ያለ ስልጣኗ እህትሽን 'አጥምቂኝ' አልሻት:: ስለነዚህ ነገሮች ጸበሉ ተለውጦባችኋል" ብለው ወደ ጸበሉ በመስቀል አማተቡ:: "እፍ" ሲሉትም የረጋ ደም የነበረው ማይ ወደ ጸበልነቱ ተመለሰ:: ይህንን ያዩ ሴቶቹ በግንባራቸው ተደፍተው ለጻድቁ ሰገዱ::
=>ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም:: አሜን::
<<< በበዓሉም (ግንቦት 19 ቀን) ጎንደር በሚገኘው ቤተ መቅደሳቸው ተገኝተን እናክብራቸው ! >>>
<<< ከጻድቁ በረከት አይለየን !! >>>
✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞

✞✝✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✝✞
❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖
❖ ግንቦት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+✝+ አባ ዓቢየ እግዚእ +✝+
❖ጐንደር ከተማ ነዋሪ ከሆኑ: ወይም ከተማዋን
የሚያውቁዋት ከሆነ አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎ:: (እንደ ወትሮው ሁሉ) ከተማዋ ውስጥ ጅብና እባብን
የመሠሉ አራዊት ነዋሪውን ሲገድሉ: ወይም ሲያቆስሉ
ተመልክተው: ካልሆነም በታሪክ ሰምተው ያውቃሉ?
☞ መልስዎ "በጭራሽ አላውቅም" እንደሚሆን
እገምታለሁ:: (ምክንያቱም ሆኖ አያውቅማ!)
+ነገሬን እንዲረዱኝ ሌሎች የሃገራችን ዋና ዋና ከተሞችን
ልብ ይበሉልኝ:: እንኳን በሌሊት በቀንም አራዊቱ
አይጠፉባቸውም::
"ታዲያ ጐንደር ከተማ ውስጥ ጅብ የማይገባው: እባብና
ጊንጥ ሰው የማይገድለው ግን ለምን?" ካሉ በጻድቁ
በአባ ዓቢየ እግዚእ ቃል ኪዳን ምክንያት ነው:: (ሁሉም የሃገራችን ከተሞች የተባረኩ መሆናቸውን ሳንዘነጋ ማለት ነው)
+ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
+አባ ዓቢየ እግዚእ የተወለዱት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን
ትግራይ ተንቤን (መረታ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ
ወላጆቻቸው ያፍቅረነ እግዚእና ጽርሐ ቅድሳት ይባላሉ:: አጥምቀው
'ዓቢየ እግዚእ' ሲሉ ስም ያወጡላቸው የወቅቱ ዻዻስ ሰላማ መተርጉመ
መጻሕፍት ናቸው:: ትርጉሙም "በጌታ ዘንድ ታላቅ ሰው"
ማለት ነው::
+ዓቢየ እግዚእ በሕጻንነታቸው ሌሊት ሌሊት ባሕር ውስጥ
ሰጥመው ሲጸልዩ አድረው ቀን ቀን እየተማሩ ብሉይ
ከሐዲስ ጠነቀቁ::
ገና በወጣትነታቸው ወደ ታላቁ መነኮስ አቡነ መድኃኒነ
እግዚእ ደብረ በንኮል ሔደው መንኩሰዋል::
+በገዳሙ በጾም: በጸሎትና በስግደት ተወስነው ከኖሩ
በኋላ ወደ ዋልድባ ሔደው የተሰወረች ቤተ ክርስቲያን
አግኝተዋል::
በጊዜው በ40 ቀን አንዲት ቅጠል ብቻ ለቁመተ ሥጋ
ይበሉ ነበር::
+ከዚያም ወደ ሃገራቸው ተንቤን ተመልሰው ዛሬም ድረስ
ድንቅ ሆኖ የሚታየውን ገዳም መሥርተው ብዙ መናንያንን
አፍርተዋል::
ዓቢየ እግዚእ ገዳማዊና ጻድቅ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ
አባትም ነበሩ:: ከትግራይ እስከ ደንቢያ ደግሞ ሃገረ
ስብከታቸው ነው::
+አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት
ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ:: ቀኑ ነሐሴ 10
ነውና ተከዜ
እስከ ገደፉ ሞልቶ ለ3 ቀናት ባለመጉደሉ ከ1,000 በላይ
ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ:: ጻድቁ ባካባቢው የነበሩት ኢ-
አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው
ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ::
+ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ
ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ:: ይሕን ድንቅ ያዩ ከ1,000
በላይ
አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል:: ይሕም
ዘወትር ነሐሴ 10 ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው (ጐንደር)
ይከበራል::
+ከዚያም እያስተማሩ ጐንደር ደረሱ:: ያኔ ጐንደር በቀሃና
አንገረብ ወንዞች የታጠረች አንዲት መንደር ነበረች:: ጻድቁ
ቀን ቀን እየሰበኩ ማታ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናቸው የታነጸበት
ሥፍራ ላይ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር::
+በዚያ ዘመን ጐንደር ውስጥ ጅብ: እባብና መሠል አራዊት
ገብተው ሕዝቡን ጨረሱት:: ይሕንን የተመለከቱት አባ
ዓቢየ እግዚእ ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ:: በፍጹም ልባቸውም
ስለ ሕዝቡ ለመኑ::
+የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ወደ ጻድቁ ቀርቦ "በስምሕ
የተማጸኑ: በቃል ኪዳንህ ያመኑ: በምድር አራዊት
አይሠለጥኑባቸውም::
በሰማይም እሳትን አያዩም:: ጐንደርንም አራዊት ገብተው
ሰውን አይጐዱም::" ብሏቸው አርጓል::
+ጻድቁም የወንጌል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ
ገዳማቸው ተንቤን ተመልሰዋል::
ይሔው እኛ ምን ብንከፋ: ጻድቁንም ብንረሳቸው
እግዚአብሔር ግን ዛሬም በጻድቁ ምልጃ ከተማዋን ጠብቆ
ይኖራል:: ነገን ደግሞ እርሱ ያውቃል:: ዛሬ ቤተ ክርስቲያኑ የታነጸበት ቦታ (ጎንደር ቀበሌ 09 ኪዳነ ምሕረት) ጻድቁ የጸለዩበት ቦታ
ነው:: እንኳን በወርሃዊ በዓላቸው (በ19) ይቅርና
በዓመታዊ በዓላቸው (ግንቦት 19) ለንግስ የሚመጣው
ሰው ቁጥር ያስተዛዝባል::
+አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን ለብዙ ዘመናት
በቅድስና ኑረው: 3 ሙታንን አስነስተው: ብዙ ድውያንን
ፈውሰው: ብሔረ ብጹዓንን ጎብኝተው: የድኅነት ቃል ኪዳንም
ተቀብለው: በ140 ዓመታቸው ግንቦት 19 ቀን አርፈዋል::
የጻድቁ ክብር ለሁሉ ነውና እባካችሁ እናስባቸው::
+<< ተአምሪሁ ለጻድቅ አቡነ ዓቢየ እግዚእ - - - ጸሎቱ
ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ
ዓለም:: አሜን:: >>+
+<< ከበዙ ተአምራቱ አንዱን >>+
=>ጻድቁ አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው #ተንቤን
(መረታ) ሳሉ አንዲት መበለት መጥታ "አባቴ!
የምጠጣውን ጸበል ባርከህ ስጠኝ?" አለቻቸው:: ጻድቁም
በውሃው ላይ ጸሎትን አድርሰው : በመስቀላቸው ባርከው
ሰጧት::
+ወደ ባልንጀራዋ ስትደርስ ግን ሐሳቧን ቀየረችና
"ልጠጣው" ብላ የተቀበለችውን ማይ (ጸበል)
ልትጠመቅበት (ልትጸበልበት) ወሰነች:: ባልንጀራዋንም
"በላዬ ላይ አፍሺልኝ" ስትል አዘዘቻት::
+ባልንጀራዋም "እሺ" ብላ ልታፈስላት (ልትጸብላት) በፋጋ
(ግማሽ ቅል) ያለውን ጸበል አነሳች:: ልታፈሰው
ስትዘቀዝቀው ግን ከሆነው ነገር የተነሳ 2ቱም ደነገጡ::
ጸበሉ የረጋ ደም ወደ መሆን በቅጽበት ተለውጧልና::
+ፍጹም ፍርሃት የወደቀባቸው ሴቶቹ እየተሯሯጡ ወደ አባ
ዓቢየ እግዚእ በዓት ደረሱ:: ከውጭ ሆነውም "አባ! አባ!
የሰጠኸን ጸበልኮ የረጋ ደም ሆነ" አሏቸው:: ጻድቁም
እንዳላዋቂ "ምን አጠፋችሁ?" ሲሉ ጠየቁ::
+"አባታችን! ምንም አላጠፋንም:: ብቻ አፍሺልኝ ብየ
ስሰጣት እንዲህ ሆነ" ስትል አንዷ መለሰች:: ጻድቁ ግን
በየውሃት "ልጆቼ! ሁሌም : 'ምንም አላጠፋንም'
አይባልም:: ሰው ሆኖ የማይበድል የለምና::
+ . . . አንቺም ልጄ! እኔን ያልሺኝ 'የምጠጣው ጸበል
ስጠኝ' ነበር:: ግን ልትጸበይበት ወደድሽ:: ስሕተትሽ ከዚህ
ይጀምራል:: (የቅዳሴ ጸበል ለመጸበል አይሆንምና)
¤በዚያ ላይ "አልቦ ዓቢይ ኃጢአት ከመ ወልጦ ቃል . . .
ከውሸት በላይ ከባድ ኃጢአት የለም::" (ዮሐ. 8:44)
+ . . . በተጨማሪ ደግሞ ያለ ስልጣኗ እህትሽን
'አጥምቂኝ' አልሻት:: ስለነዚህ ነገሮች ጸበሉ
ተለውጦባቹሃል" ብለው ወደ ጸበሉ በመስቀል አማተቡ::
"እፍ" ሲሉትም የረጋ ደም የነበረው ማይ ወደ ጸበልነቱ
ተመለሰ:: ይህንን ያዩ ሴቶቹ በግንባራቸው ተደፍተው
ለጻድቁ ሰገዱ::
=>ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን
ለዓለመ ዓለም:: አሜን::
❖አምላካችን በወዳጆቹ ምልጃ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ
ይሠውርልን::
❖ግንቦት 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)
2.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም (የ12ቱ ሐዋርያት መቃብር
ከጌታ የተገለጠላቸው ኢትዮዽያዊ)
3.አቡነ ብስጣውሮስ ዘሐይቅ እስጢፋኖስ (ኢትዮዽያዊ)
4.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት ታላቁ (7 ጊዜ ሙቶ የተነሳ)
5."805,007" ሰማዕታት (በአንድ ቀን ብቻ የተገደሉ)
6.አባ ይስሐቅ ገዳማዊ
❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2፡ ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
3፡ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ
4፡ አባ ስነ ኢየሱስ ጻድቅ

++"+ በተኩላና በእባብ ላይ ትጫማለህ::
አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ::
በእኔ ተማምኗልና አስጥለዋለሁ::
ስሜንም አውቁዋልና እጋርደዋለሁ::
ይጠራኛል እመልስለትማለሁ::
በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ::
አድነዋለሁ: አከብረውማለሁ::
ረጅም እድሜን አጠግበዋለሁ::
ማዳኔንም አሳየዋለሁ:: +"+ (መዝ. 90:13-16)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ::
በእኔ ተማምኗልና አስጥለዋለሁ::
ስሜንም አውቁዋልና እጋርደዋለሁ::
ይጠራኛል እመልስለትማለሁ::
በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ::
አድነዋለሁ: አከብረውማለሁ::
ረጅም እድሜን አጠግበዋለሁ::
ማዳኔንም አሳየዋለሁ:: +"+ (መዝ. 90:13-16)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Memhir Esuendale:
#Feasts of #Ginbot_19
✞✞✞On this day we commemorate Abba Abiye Egzi, the Ethiopian Saint✞✞✞
✞✞✞In the name of the Father, the Son and the Holy Spirit, one God. Amen!✞✞✞
✞✞✞ Abba Abiye Egzi✞✞✞
=>If you are a resident of the City of Gondar (in Ethiopia) or know the City, let me ask you a question. Have you ever seen or heard in history of wild beasts like hyenas or reptiles like snakes kill a resident or injure him/her?
✞I guess your answer to be “No, not at all!”
✞And so that you would understand my point, take notice of the major cities of our country. Let alone at night, wild animals can be found in them during the day.
✞Thus, if you ask, “Why is it that hyenas do not enter or snakes and scorpions kill people in the City of Gondar?” the answer is because of the covenant of the Righteous Abba Abiye Egzi. (This is without forgetting the fact that all our country’s cities are blessed.)
✞And if asked how that came to be, it was as follows.
✞Abba Abiye Egzi was born in Tembien (Mereta), Tigray, in the 14th century. His blessed parents were called Yafekrene Egzi and Tserha Kidesat. The then Bishop, Abune Selama the Translator (Selama ll - 1348 - 1388), after baptizing the Saint, was the one who gave him the name Abiye Egzi. And it means “A great man before God”.
✞Abiye Egzi completed the Old and New Testaments in his childhood by praying all night in a river and learning during the day. And when he was in his youth, he went to Abune Medhanine Egzi, the great monk at Debre Benkol and became an ascetic (a monk).
✞After he lived in the monastery by fasting, prayer and making prostrations, he went to Waldiba and found a Church that was hidden from sight. And at that time, he ate only a leaf (a single leaf) in 40 days for the sustenance of his body.
✞Then, he went to his birth place Tembien, and established his great monastery, which is still found there, and he bore many ascetics. Abiye Egzi was not only a monastic and a righteous father but he was also an apostolic. And his area of ministry reached from Tigray to Dembiya.
✞One day, when the Saint travelled with his disciples to preach, he reached the Tekeze River. And as the day was Nehasse 10 (August 16) – in the winter season, he arrived there as a thousand people were expressing grief because the river had filled to its banks and it had not receded for 3 days. The Saint, though the people were non-believers, as he was compassionate, prayed saying, “God of Moses” and entered into the depth of the water.
✞And as St. Michael was with him, Tekeze parted to the left and the right, and the middle became dry ground. Hence, the gentiles, who were more than 940 in number, that saw this phenomenon, believed and were baptized by the hands of the Saint. Thence, this miracle is always commemorated on Nehasse 10 (August 16) in his Church (in Gondar).
✞Subsequently, he arrived at Gondar as he ministered. And at that period, Gondar was a small village encompassed by the Rivers Qeha and Angereb. And the Saint used to teach [in Gondar] during the day and he used to pray all night long where his church now stands.
✞During those days, wild animals like hyenas, snakes, and the like used to enter the village, and they killed many people. And Abiye Egzi who saw this, cried out to God. And he supplicated wholeheartedly for the people.
✞And the Lord, Who does not deny what He is beseeched, appeared to the Saint, and said to him, “Those who beseech in your name and believe in the covenant I gave you will not be harmed by wild beasts here on earth, nor will they see eternal fire in heaven (in the next life). And wild animals will no longer enter into Gondar and cause harm to people.” Then, He ascended.
✞Thereafter, the Saint, once he had completed his mission [in Gondar], returned to his monastery in Tembien. And though we are very wicked and forgot [to remember] the virtuous, God still protects the City through the intercession of the Saint.

And He only knows what will happen in the future.And the area where his church is built today (Gondar Kebele/Municipality 09 Kidane Mehret), on one occasion was the place where the Saint prayed [as mentioned earlier]. However, the amount of people who come for his annual commemorations (on Ginbot 19/May 27 and on Nehasse 10/ August 16) let alone for his monthly feasts (on the 19th of each month) do put us in judgment.
✞Abba Abiye Egzi, after living in holiness for many years in his monastery in Tembien, after raising 3 dead people, healing many of the sick, visiting the Realm of the Blessed and receiving a covenant, passed away on this day, Ginbot 19 (May 27), at the age of 140 years. And as the glory of the Saint is for us all, let us commemorate him.
✞✞✞A miracle of the Righteous Abune Abiye Egzi. May his prayer and blessing be with us all the faithful forever and ever. Amen.
✞One of his numerous miracles [is as follows].
=>While the Righteous Abba Abiye Egzi was in his monastery in Tembien (Mereta), one widow came to him and asked, “My Father! Bless and give me holy water that I may drink.” Thus, the Saint prayed upon water, blessed it with his cross and gave her.
✞Nonetheless, when she reached her friend, she changed her mind and decided to bathe with the holy water that she took to drink. And she told her friend, “Pour it over me”.
✞And her lady friend replied with “Alright” and held the holy water in half of a bottle gourd vessel. And when she turned it over to pour, from what transpired, both were shocked. And that was because the holy water had immediately changed to coagulated blood.
✞Then both women, who were in complete fear, ran and reached the cell of Abba Abiye Egzi. And from outside, they said, “Father! Father! The holy water that you gave us became blood.” And the Saint, as if he did not know, asked, “What have you done wrong?”
✞And one answered, “Our father, we did not do anything wrong. I just gave her so she could pour it over me and this happened.” However, the Saint in meekness said, “My children! ‘We did not do anything wrong’ should always not be given as an answer as there is no person who will not transgress as long as he/she is a human.”
✞He continued, ”And you my daughter! You asked me, ‘Give me holy water that I may drink’. But then you wanted to pour and bathe with it. Your error begins here.” (As the holy water from the Divine Liturgy is not used for bathing/ cleansing.)
*And on top of that there is no greater sin than lying. (John 8:44)
✞Then he added, ”Also in addition to that, you asked your sister, who does not have the authority, to baptize you (pour over you the holy water). And for these things, the holy water changed before you.” And after stating these words, he made the sign of the cross over the coagulated blood and when he breathed over it the water that had become a solidified blood changed back to being holy water. And the women who saw this bowed down to the Saint.
✞May his prayers and blessings be with us all Christians forever and ever. Amen.
✞✞✞ May God keep our country from all wickedness by the intercessions of his beloved [Saints].
✞✞✞ Annual feasts celebrated on the 19th of Ginbot
1. Abba Abiye Egzi the Righteous (Ethiopian)
2. Abune Yoseph (Joseph) the Light of the World (To whom was revealed the tombs of the 12 Apostles by the Lord)
3. Abune Bestawros of Hayk Estifanos (Ethiopian)
4. St. Isidorus (Isidore/Esdros) the Great Martyr (Who had died 7 times and was resurrected)
5. 805,007 Martyrs (Killed in one day)
6. Abba Isaac the Monastic
✞✞✞ Monthly Feasts
1. St. Gabriel the Archangel
2. St. Isidorus (Isidore) the Martyr
3. St. Yemrehana Krestos (Emperor of Ethiopia 11th Century)
4. Abba Sene Iyesus the Righteous
✞✞✞“Thou shalt tread upon the lion and adder: the young lion and the dragon shalt thou trample under feet. Because he hath set his love upon me, therefore will I deliver him: I will set him on high, because he hath known my name.

He shall call upon me, and I will answer him: I will be with him in trouble; I will deliver him, and honour him.With long life will I satisfy him, and shew him my salvation.”✞✞✞
Psalm 90:13-16
✞✞✞ Salutations to God ✞✞✞
(Translated by Mhr. Esuendale Shemeles with the permission of Dn. Yordanos Abebe)

🕊መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስኅ ግቡ🕊
(ማቴ ፫:፫)
✨በአማን ተንሥአ መድኃኒነ!✨
🌿ብፁዕ አባ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘኤለ ገዳማተ እምኀበ እግዚኡ ይነሣእ እሴተ ቦአ ሀገረ ደብረ ሊባኖስ በፍሥሐ ወበሰላም።
⚜ሰአል ለነ ጊዮርጊስ ኀበ እግዚአብሔር ወጸሊ በእንቲአነ ሐረድዎ ወገመድዎ ወዘረዉ ሥጋሁ ከመ ሐመድ ወወሰድዎ ኀበ ሰብአ ነገሥት ረገጸ ምድረ አንሥአ ሙታነ አባ ጊዮርጊስ በሰላም ዐደወ መንግሥተ ክብር ወረሰ።
🌿ወልደ እግዚአብሔር አምላክነ ወመድኃኒነ ዕቀብ ሕይወተነ እም ገሀነመ እሳት ወእምኵሉ መንሱት በእንተ ቅዱስ ስምከ ወበእንተ ማርያም እምከ ወበእንተ ቅዱስ መስቀል ወበእንተ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወበእንተ ዮሐንስ መጥምቅከ ወበእንተ ኵሎሙ ቅዱሳን ወሀባ ሰላመ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ ወለቅድስት ቤተክርስቲያን።
⚜ሰላም ለክሙ ጻድቃን ወሰማዕት እለ አዕረፍክሙ በዛቲ ዕለት መዋዕያነ ዓለም አንትሙ በብዙኅ ትዕግሥት። ሰአሉ ቅድመ ፈጣሪ በኩሉ ሰዓት እንበለ ንስሐ ኪያነ ኢይንሣእ ሞት።
🌿አንቅሐኒ በጽባሕ ክሥተኒ ዕዝንየ በዘአጸምእ አምላኪየ አምላኪየ እገይሥ ኀቤከ ዘይሰማዕ ግበር ሊተ ምሕረተከ በጽባሕ"
⚜ነቢያት ወሐዋርያት፥ ጻድቃን ወሰማዕት፤ ደናግል ወመነኮሳት፥ አዕሩግ ወሕጻናት፤ ገዳማውያን ወሊቃውንት፤ ሰአሉ ለነ ኲልክሙ፥ ቅድመ መንበሩ ለጸባኦት።
🌿እግዝእትየ ፍትሕኒ እማዕሠሩ ለሰይጣን፤
እሙ ለመድኅን ወለተ ብርሃን።
✝ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር
🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ታሪክ እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል)
🌿አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር)
🔗https://www.tg-me.com/zikirekdusn
▶️https://www.youtube.com/@ZikereKedusan

✝✝✝ እንኳን አደረሳችሁ ✝✝
☞በዓለ ልደቱ ለቅዱስ ወክቡር ይምርሃነ ክርስቶስ (ካህን፡ ወንጉሥ፡ ወጻድቅ) #ዘኢትዮጵያ፡፡
"" ከበረከቱ ይክፈለን፡፡ ""
✝ዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ ዘጎንደር✝
'
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://www.tg-me.com/zikirekdusn

✝✝✝ የዓለም ብርሃን፡ አርከ ሐዋርያት (የሐዋርያት ወዳጅ)፡ ወገባሬ መንክራት (ድንቅ አድራጊው) #አቡነ #ዮሴፍ ዘእንጅፋት (ዘወለቃ) ✝✝✝
=>ጣዕመ በረከቱ ይደርብን፡፡
✝ዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ ዘጎንደር✝
'
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://www.tg-me.com/zikirekdusn
=>ጣዕመ በረከቱ ይደርብን፡፡
✝ዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ ዘጎንደር✝
'
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://www.tg-me.com/zikirekdusn
❖እንኳን አደረሳችሁ!
"ፀሐይ ብሩህ፤
ወወርኅ ንጹሕ፥ ዓቢየ እግዚእ፤
ሣህልከ ይርከበነ፤
አባ ዓቢየ እግዚእ!"
"ብርሃናዊ ፀሐይ፥ ንጹሕ/የጠራ ጨረቃ የተባልክ አባታችን ዓቢየ እግዚእ ሆይ፤ ይቅርታህ (ፈጥኖ) ይደረግልን!"
"ሰአል ለነ፥ አስተምሕር ለነ፤
ዓቢየ እግዚእ አቡነ፤
መንስኤ ሙታን፤
መምህር ዘበአማን፤
ምዑዝ ከመ ዕጣን!"
ቸሩ መድኃኔ ዓለም ከጻድቁ ቃል ኪዳን፥ ረድኤት፥ በረከትን ያሳትፈን!

Audio
"" ስለምን ዝም ትላለህ? "" (ዕብ. ፩:፲፫)
"ቅዱስ አርሳንዮስ ጽምው"
(ግንቦት 13 - 2017)
"ቅዱስ አርሳንዮስ ጽምው"
(ግንቦት 13 - 2017)