Telegram Web Link
እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሠላም አደረሣችሁ! አደረሠን ሲል DBU DAILY የ 2018 ዓ.ም የአዲስ ዓመት መልካም ምኞቱን ያስተላልፋል፡፡


@DBU11
@DBU111
👏24👍4😢3👌3
48ሺህ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት አምጥተዋል ።

በ2017 ፈተና ከወሰዱ 585 ሺህ 882 ተማሪዎች መካከል  48ሺ ዘጠኝ መቶ ሀያ ዘጠኝ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ማስመዝገባቸዉን መግለጫዉን እየሰጡ የሚገኙት የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ተናግረዋል፡፡

ካለፈዉ አመት ጋር ሲነፃፀር 12ሺ በላይ ተማሪዎች በተጨማሪ ማሳለፍ ተችሏል ብለዋል፡፡



@DBU11
@DBU11
👍10🤬6
የዘንድሮ ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እስከ ነገ ድረስ ይፋ ይደረጋል

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)  ውጤቱ እስከ ነገ ቀን 6፡00 ድረስ እንደሚለቀቅ ተናግረዋል።

በሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና በኬሚስትሪ የትምህርት ዓይነት ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን እና በአፕቲትዩድ ደግሞ ዝቅተኛው ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

@DBU11
@DBU11
👍3😢1
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል፡፡

ውጤት ለመመልከት አድራሻዎች:-

1. በዌብ ሳይት፡ https://result.eaes.et
2. በቴሌገራም፡ https://www.tg-me.com/EAESbot
3.  በአጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS)፡  6284 ላይ ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ

@dbu11
@dbu111
👍2
update

በሰኔ 2017 ዓ.ም የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 48,929 ወይም 8.4% ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቁን ቲክቫህ በዘገባው አስነብቦናል።

ወንድ 30,451 እና ሴት 18, 478 ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸው ተገልጿል።

ፈተናቸውን ከወሰዱ 585,882 ተማሪዎች መካከል 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ካስመዘገቡ መካከል የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች 5.2 በመቶ፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ደግሞ 11.4 በመቶ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) መግልለፃቸውንም ዘግቧል።

በየዓመቱ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሚወስዱ ተማሪዎች መካከል ከ15-20% የሚሆኑት የሚልፉበት ደረጃ ለመድረስ እስከ ሁለት ዓመት ሊወስድ እንደሚችል ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

@dbu11
@dbu111
👍2
በዘንድሮው ብሔራዊ የዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ተመዘገበ።

የዶዶላ ኢፈ ቦሩ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ የሆነው ካሊድ በሽር በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 591 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን ከ FBC ገፅ አንብበናል፡፡

@dbu11
@dbu111
👏57👌2👍1
ስለ መግቢያ የሚታወቀው የመግቢያ ቀን መስከረም 8 እና 9 ነው ።

@DBU11
@DBU11
👍3
ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ነባር መደበኛ ተማሪዎችን መስከረም 5 2018 ጀምሮ እየተቀበለ ይገኛል ።

@DBU11
@DBU11
👍3
ከዩንቨርስቲያችን በቅርብ ርቀት የሚገኘው የኃይለማርያም ማሞ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በደብረብርሀን ከተማ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ሚኪያስ ኪዳኔ 572/600 በማምጣት ነው በከተማው ካሉ የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ቀዳሚ ውጤት ያስመዘገበው ።

ለዩንቨርስቲው ጎረቤት የሆነው ፈታውራሪ ገበየሁ በተለምዶ ባሶ ትምህርት ቤት የደብረብርሀን ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ቱቶሪያል ይሰጡ እንደነበር የመረጃ ምንጮቻችን አሳውቀውናል የዚሁ ትምህርት ቤት ተማሪ አየናቸው ሽዋሰገድ 518 ማምጣት ችሏል።

ከ Millinium ሳሮን ፍሰሐ የሐይለማርያም ማሞ ተማሪ ሚኪያስን በ 552 ትከተለዋለች።

መልካም የትምህርት ዘመን ይሁንላችሁ።

@dbu11
@dbu111
👏32👍7😢2
2018.docx
16 KB
በ2018 ዓ.ም ተማሪ የሚያስገቡ ሰራተኞች ስም ዝርዝር እና ስልክ ቁጥር


@DBU11
Regular Male-2018(ii).xls
2.2 MB
የወንዶች የዶርም ምደባ

@DBU11
Regular-17 2017.xls
469 KB
የሴቶች የዶርም ምደባ

@DBU11
2025/10/22 15:18:45
Back to Top
HTML Embed Code: