+++ እምቢ +++
የሰውን ልጅ ከብዙ መከራ ሊያወጣ የሚችል መፍትሔ ነው። ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ያልተገባ ሩካቤን እና በዚያ ምክንያት የሚፈጠር ጽንስን ቀድሞ ለመከላከል የሚረዳ በቤተ ክርስቲያን የተፈቀደ ፍቱን መድኃኒት ነው። ይህን መድኃኒት ከፋርማሲ አንገዛውም ከቅጠልም አንሸመጥጠውም። እኛው ውስጥ ያለ እና ወደ አፍ የሚዋጥ ሳይሆን ከአፍ የሚወጣ መድኃኒት ነው። በእርግጥ ከአፍ የሚወጣ ቢሆንም አወጣጡ ላይ ግን ትንሽ ሊያስቸግር እና አንደበት ላይ መረር ሊል ይችላል። ያው መጎምዘዝ የብርቱ መድኃኒቶች ጠባይ ስለሆነ ይህ ብዙ አያስገርመንም። ኸረ መድኃኒቱ ይነገረን አላላችሁም? ይኸው ያዙ መድኃኒቱ "እምቢ" የሚለው አጭር ቃል ነው።
ይህ ቃል ለብዙዎች መነሣትና መውደቅ ምክንያት የሚሆን ወሳኝ ቃል ነው። ሔዋን በእባብ ያደረ የዲያብሎስን ምክር ባትሰማ እና እምቢ ብትለው የሰው ልጅ ወደ ምድረ ፋይድ ባልወረደ ነበር። "እምቢታ" ሰይጣን እኛን ለመጥለፍ የሚያዘጋጀውን አሽክላ ቆርጠን የምንጥልበት የተሳለ ሰይፍ ነው። ጌታ በገዳመ ቆሮንቶስ ሊፈትነው የመጣን ጠላት ድል የነሣው የጠየቀውን ሁሉ ሳይቀበል ድንጋዩን ዳቦ አላደርግም፣ ወድቄ አልሰግድልህም፣ ከመቅደስም ጫፍ አልዘልም ሲል "እምቢ" በማለት ነው። ቅዱስ ያዕቆብስ "ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል" አይደል የሚለው።(ያዕቆብ 4፥7)
ለልጆቻቸው የሚሳሱና የሚጨነቁ ወላጆች ለወለዷቸው ከሚሰጧቸው ውድ ስጦታዎች አንዱ "እምቢ" ማለትን ነው። የሚሰጡበትም መንገድ ልጆቻቸው አድርጉልኝ ሲሉ የሚጠይቋቸውን አላስፈላጊ ነገሮች "እምቢ" ሲሉ በመከልከል ነው። የዛሬ ወላጆች አስፈላጊ እምቢታ የነገ የልጆች የፈተና ጊዜ መልስ ይሆናል። ዛሬ ወላጅ ሁሉን እሺ እያለ ካሳደገ፣ ነገ ልጁ ሲያድግ ክፋትና ወንጀልን "እምቢ" የሚልበት አቅም ያጣል። ለምን? ከልጅነቱ አልተማረማ።
ጲላጦስ "እምቢ" ቢል ኖሮ የአይሁድን እብደት ባገደ የንጹሑ የኢየሱስ ክርስቶስም ደም ባልፈሰሰ ነበር። እምቢ አለማለት ለክፋት እምቢታን የማያውቁ ወንበዴዎችን ያበረታታል፤ ንጹሐንን ያስፈጃል።
እስኪ ኃጢአትን፣ ክፋትን፣ ዘረኝነትን በአጠቃላይ ሰይጣንን እምቢ እንበል?
እምቢ!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
ሰኔ 18 2014 ዓ.ም.
ኮምቦልቻ
ድረ ገጹን ይጎብኙ
https://dnabel.com
(በድጋሚ የተለጠፈ)

👍1
በዚህ ዓለም ያለውን ዝና ለማግኘት ምን ያህል ደከምህ? በሰዎች ፊትስ ከፍ ብለህ ለመታየት ስንት ጊዜ ራስህን ለአደጋ ጣልህ? የታዋቂነትህ ዋጋው ስንት ነው? ነገር ግን ይህን ሁሉ መሥዋዕትነት ከፍለህ የሰበሰብከው ዝና እና ክብር ተከትሎህ ወደ ሰማይ አይሄድም። ያለበሱህ የክብር ካባ፣ በራስህ ያኖሩልህ የስኬት አክሊል እዚሁ እንዳገኘሃቸው እዚሁ ጥለሃቸው ትሄዳለህ። ጻድቁ ኢዮብ እንደ ተናገረው ከእናትህ ማኅፀን ራቁትህን እንደ ወጣህ፣ እንዲሁ ራቁትህን ትመለሳለህ።(ኢዮ 1፥21) ታዲያ እርቃኑን ያለ ንጉሥ ከተራው ሕዝብ፣ እርቃኑን ያለ ባለጠጋ ከደሃው፣ እርቃኑን ያለ ክቡር ከተናቀው በምን ይለያል?!
"ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል"
1ኛ ጴጥሮስ 1፥24
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
"ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል"
1ኛ ጴጥሮስ 1፥24
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
+++ ‹‹ወንጌሉን ተወው!›› +++
የትሕርምት ሕይወትን በሚመለከት በጻፋቸው አያሌ ድርሰቶቹ የምናውቀው ሶርያዊው አባት ማር ይስሐቅ ነነዌ በተባለችው አገር ሊቀ ጳጳስ ሆኖ ተሹሞ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በመንበረ ጵጵስናው ግን የቆየው ለአምስት ወራት ያህል ብቻ ነው፡፡ በቅዱሱ ሕይወት ዙሪያ ጥናት ያደረጉ ጥቂት የማይባሉ የነገረ አበው ሊቃውንት ‹ለምን በአጭር ጊዜ ውስጥ መንበረ ጵጵስናውን ትቶ ሄደ?› ለሚለው ጥያቄ መልስ እንዳላገኙ ይገልጻሉ፡፡
ነገር ግን ከወደ ሶርያ የሚነገር አንድ ታሪክ አለ፡፡ ይኸውም በአንድ ወቅት በብድር ምክንያት መስማማት ያልቻሉ ሁለት ክርስቲያኖች ይዳኛቸው ዘንድ ወደ ማር ይስሐቅ ይመጣሉ፡፡ ገንዘብ አበደራዊው ሰው እየተበሳጨ ተበዳሪው መክፈል ካለበት ጊዜ አሳልፎ ጭማሪ ቀናት እየጠየቀው በመሆኑ፣ አሁን የማይከፍለው ከሆነ ጉዳዩን ወደ ሸንጎ እንደሚወስደው ለቅዱሱ ተናገረ፡፡ ማር ይስሐቅም ከወንጌል ትምህርት በመጥቀስ ለወንድሙ እንዲያዝንለትና ተጨማሪ ቀናት በመስጠት እንዲታገሰው ተማጸነው፡፡ አበዳሪው ግን በሊቀ ጳጳሱ ንግግር እየተናደደ ‹አሁን ከዚህ ውስጥ ወንጌሉን አውጣው!› ሲል መለሰ፡፡ የነነዌው ሊቀ ጳጳስ ማር ይስሐቅም በዚህ ሰው መልስ በጣም በማዘን ‹‹በወንጌል የተነገረውን የጌታን ትዕዛዝ ስነግርህ ሰምተህ ካልተቀበልክ፣ ታዲያ የእኔ እዚህ መሆን ምን ይጠቅማል?!›› አለው፡፡ ከዚያ ጊዜም በኋላ የብቸኝነትና የጽሙናን ሕይወት ፍለጋ መንበረ ጵጵስናውን ትቶ ወደ አስቄጥስ በረሃ ገብቷል፡፡
ከራሳችን ሐሳብ ጋር የሚስማማውን ብቻ ሳይሆን የማይስማማውንም የወንጌል ትምህርት ሰምቶ ለመቀበል ስንቶቻችን ዝግጁዎች ነን? ልክ እንደዚህ አበዳሪ ጆሮዎቻችን ለወንጌል ትምህርት ክፍት የማይሆኑባቸው ጊዜያቶች የሉም? ‹እዚህ ላይ ወንጌሉን ተወው!›፣ ‹አሁን ወንጌልን መጥቀስ ምን አመጣው!›፣ እያልን ሳግና ቁጣ ተናንቆን የጮኽንባቸውን ሁኔታዎች አታስታውሱም?
ከራሳችን ጠባይና አኗኗር ጋር ብቻ የሚስማማውን የወንጌል ክፍል መርጠን እየተቀበልን ሌላውን ግን አትጥቀሱብኝ የምንል ከሆነ፣ ‹በቅዱስ ወንጌልህ ቃል አምናለሁ› ብለን እንዴት ልንናገር እንችላለን?! ጌታችን ወደ ጌርጌሴኖን አገር መጥቶ በመቃብር ስፍራ ይኖሩ የነበሩ ሁለት አጋንንት ያደሩባቸውን ሰዎች ፈውሶ ነበር፡፡ ከእነዚያም ሰዎች ላይ የወጡት አጋንንት ወደ እሪያዎቹ ስለ ገቡ፣ መንጋውን አጣድፈው ከውኃ ሰጥመው እንዲሞቱ አደረጓቸው፡፡ ታዲያ በከተማው የሚኖሩ ሰዎች ይህን የክርስቶስን ሥራ በሰሙ ጊዜ ወዲያው እርሱ ወዳለበት መጥተው ‹ከአገራቸው እንዲሄድላቸው ለመኑት›፡፡ በጣም ይገርማል፤ በዓለም ውስጥ ተነጻጻሪ የማይገኝላት የከበረችውን ነፍስ ከአጋንንት፡ እስራት ማላቀቁ ቢያስደንቃቸውም፣ የእሪያዎቹ መንጋው መጥፋት ግን የበለጠ ስላሳሳቸው እንዲሄድላቸው ለመኑት፡፡(ማቴ 8፡34) ፈውሱ ገንዘባቸውን ከሚነካባቸው ይልቅ የድኅነታቸውን አምላክ አባርረው ከነእስራታቸው መኖር ምርጫቸው ሆነ፡፡ ለእኛ የወንጌል መልካምነት የእኛ የሆኑት ገንዘቦቻችንን፣ ክብራችንን፣ የበላይነታችንን እስካልነካብን ድረስ ነው፡፡ ወንጌሉ ለእኛ እንዲመች እንጂ፣ የእኛ ሕይወት ለወንጌሉ የተመቸ እንዲሆን አንፈልግም፡፡ ይህ ካልሆነ ግን እንደ ጌርጌሴኖን ሰዎች ከፊታችን ዘወር እንዲያደርጉልን ‹ወንጌሉን ተዉት!› እያልን በቁጣም ይሁን በልመና መናገራችን የማይቀር ነው፡፡
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ

🙏1
+++ ከሆሣዕና በፊት የተደረገው ክልከላ +++
ጌታችን በኢያሪኮ የነበረውን አገልግሎት ፈጽሞ ሲወጣ የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት አይተው የተከተሉት ብዙ ሕዝብ ነበሩ። እነሆም ከመንገድ ዳር የተቀመጡ ሁለት ዕውሮች ኢየሱስ ክርስቶስ በዚያ እያለፈ መሆኑን ሲሰሙ "የዳዊት ልጅ ሆይ ማረን?" ብለው ጮኹ። ከእነዚህ ሁለት ዓይነ ሥውራን አንዱ በርጤሜዎስ እንደሚባል ቅዱስ ማርቆስ ይነግረናል።(ማር 10፥46) ወንጌላዊው የአንዱን ስም ለይቶ መጥራቱ ይህ ሰው በከተማው ከነአባቱ የሚታወቅ በመሆኑ ሳይሆን አይቀርም። የሆነው ሆኖ አሁን ሁለቱም ነዳያን "ማረን" ሲሉ እየጮኹ ነው።
ነገር ግን ከጌታችን ፊት ቀድመው ይሄዱ የነበሩት ሰዎች እኒህን ነዳያን "ዝም በሉ!" ብለው ገሰጿቸው።(ሉቃ 18፥39) ልብ በሉ! የገሰጿቸው ሰዎች ጌታን ከኋላ የሚከተሉ ወይም ከአጠገቡ አብረው የሚሄዱት አልነበሩም። ከፊት ከፊት የሚቀድሙት እንጂ። በእርግጥም ከጌታው ፊት ቀደም ቀደም የሚል ሰው ጠባይ ይህ ነው። ራሱን ከባለቤቱ በላይ ዐዋቂ ያደርጋል። ምስኪኖችን "ዝም በሉ" እያለ የሚያሳቅ፣ የጌታውን ቸርነት የሚሸፍን አጉል ጠበቃ ይሆናል። እስኪ አሁን "ማረን" ማለት ምን ነውር አለው?! ቃሉስ የስድብ ያህል የሚያስቆጣና "ዝም በሉ" የሚያሰኝ ነው?! እነዚህ ሁለቱ ዕውሮች የገጠሟቸው እንዲህ ያሉ "በባለቤቱ ያልተወከሉ ጠበቆች" ነበሩ። ግን አልተበገሩም "ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ ማረን" እያሉ ከቀድሞው ይልቅ አብዝተው ጮኹ።
ለሚያንኳኩ በሩን የሚከፍት በጎውንም ነገር ለለመኑት የሚሰጥ መድኃኔዓለም የእነዚህን ምስኪናን ጩኸት ሰምቶ ቆመላቸው። "ኑ" እንዳይላቸው ዓይተው መራመድ አይችሉምና ሁለቱንም እንዲያመጡለት አዘዛቸው።(ሉቃ 18፥40) ከፊተኞቹ ይልቅ ቅን የሆኑት እና ባለቤቱ የላካቸው መልካሞቹ ሰዎች "አይዟችሁ ተነሡ ይጠራችኋል" በማለት በሚያጽናና ቃል ወደ ጌታ አቀረቧቸው። ወደ እርሱም ሲቀርቡ "ምን ላደርግላችሁ ትወዳላችሁ?" ሲል የችግረኞች አምላክ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በፍቅር ጠየቃቸው። እነርሱም "እናይ ዘንድ" አድርገን አሉት። ዓይናቸውን ዳስሶ ፈወሰውና አይተው ተከተሉት።
ይህን የበርጤሜዎስን ታሪክ ቅዱስ ፊልክስዩ ደግሞ ለሚጸልይ ሰው በመስጠት ውብ አድርጎ ይተረጉመዋል። በርጤሜዎስ "የዳዊት ልጅ ሆይ ማረኝ" ብሎ ሲጮህ "ዝም በል" ብለው እንደ ገሰጹት፣ እኛም ወደ አምላካችን ጸሎት ስናቀርብ ልመናችንን እንድናቆም "አይሰማችሁም" እያሉ ኅሊናችንን በመረበሽ አጋንንት ዝም ሊያሰኙን ይሞክራሉ። ነገር ግን የዚህ መፍትሔው እንደ በርጤሜዎስ ተስፋ ሳይቆርጡ እምቢ ብሎ ወደ ፈጣሪ መጮህ ነው። ያን ጊዜ ጌታ ልመናችንን ሰምቶ "ጥሯቸው" ይላል። "አይዟችሁ ተነሡ፤ ይጠራችኋል" ብለው የራቅነውን የሚያቀርቡ እና ረድኤተ እግዚአብሔርን የሚያሰጡ ቅዱሳን መላእክትን (ቅዱሳን ሰዎችን) ወደ እኛ ይልክልናል።
በርጤሜዎስም ወዲያው ተነሥቶ ጠልፎ ሊጥለውና ሸክም ሆኖ ሊያዘገየው የሚችለውን ድሪቶ ጥሎ ፈጥኖ ወደ ጌታ እንደ ቀረበ። እኛም ወደ አምላካችን እንዳንቀርብ አንቀው የሚይዙንን እና የሚያዘገዩንን አጉል ልማዶቻችንን ጥለን ወደ እርሱ ልንቀርብ ይገባል። ይህ ከሆነ እንደ በርጤሜዎስ እሴተ ጸሎታችንን (የጸሎታችንን ዋጋ) እናገኛለን። ከዚያ መድኃኒታችንን ተከትለን እስከ ኢየሩሳሌም እንሄዳለን። "ሆሣዕና በአርያም" እያልንም የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘን እናመሰግነዋለን።

+++ ‹‹ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል›› መዝ 92፥12 +++
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተሰጋግሞ የመነሣት እድል ካገኙ እጽዋት መካከል አንዱ የዘንባባ ተክል ነው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤት ከሠራ በኋላ በመቅደሱ የውስጥ ግንቦች ላይ ከቀረጻቸው ምስሎች ውስጥ አንዱ የዘንባባን ቅጠል ነው፡፡(1ኛ ነገ 6፡29) በእስራኤላውያን ታሪክም ድል ሲቀናቸውና ሲደሰቱ በእጃቸው የሚገኘው እጽ ይኸው ዘንባባ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የብሉይ ኪዳን ጸሐፊዎች የአንድ አገር መለያ አድርገው ከሚጠቅሷቸው ምልክቶች ውስጥ ‹‹የዘንባባ ዛፍ›› አንደኛው ነው፡፡(ዘዳ 34፡3) ከዚህ ሁሉ ደግሞ በጣም የሚያስደንቀው የሐዲስ ኪዳኑ ባለ ራእይ ቅዱስ ዮሐንስ እንደ ጻፈው ሩጫቸውን በድል የጨረሱና ነጭ የለበሱ የጻድቃን ነፍሳት ‹‹የዘንባባን ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት›› መቆማቸው ነው፡፡(ራእይ 7፡19) ዘንባባ በምድር ላለ ደስታ ብቻ ሳይሆን በሰማይም ላለ የድል ነሺነትና የአሸናፊት መንፈስ መግለጫ ምልክት ሆኖ ያገለግላል፡፡
ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ጻድቃንን ለምን በዘንባባ ዛፍ ይመስላቸዋል? መዝሙረኛውስ ‹ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል› ሲል ለምን ዘመረ? ቅዱሳንን ከዘንባባ ጋር ምን አገናኛቸው?
ሁላችንም እንደምናውቀው ጣፋጭ ፍሬ ከሚሰጡ እጸዋት መካከል አንዱ ዘንባባ ነው፡፡ የዘንባባን ዛፍ ለየት የሚያደርገው ጣፋጭ ፍሬ መስጠቱ ብቻ ሳይሆን ሥሮቹ በጣም ጠንካራ እና ወደ ታች ጠልቀው የሚገቡ (የሚሰዱ) መሆናቸው ነው፡፡ ጸድቃንም እንደ ዘንባባ ፍሬ የሚጥም በጎ ምግባርን የተሸከሙ የሃይማኖት ተክል ሲሆኑ፣ የታነጹበትና የቆሙበት የእምነትና የፍቅር ሥሮችም በጣም የጸኑ እና ጥልቆች ናቸው፡፡
ሌላው የዘንባባ ዛፍ በየትኛውም ጊዜ ቢተከል ሊያፈራ የሚችልና በበረሃ የሚበቅል ልዩ ተክል ነው። ቅዱሳንም በጊዜውም ሆነ ያለ ጊዜው ጸንተው ይገኛሉ። በበረሃም እንደሚጸድቅ ዘንባባ በዚህች ክፋት በሞላባት ዓለም ውስጥ እየኖሩ በቅድስና ይገኛሉ።
የዘንባባ ዛፍ ልክ እንደ ሌሎች እጸዋት ብዙ ቅርንጫፎች የሉትም፡፡ በዚህም ምክንያት እንስሳት ፍሬው ወደሚገኝበት የዛፉ ጫፍ በቀላሉ ለመውጣትና ለመብላት ይቸገራሉ፡፡ እንዲሁ ጻድቃንም በጎ ሥራዎቻቸውንና መንፈሳዊ ደስታቸውን ከእነርሱ እንዲወስዱባቸው ለአጋንንት መግቢያ በር፣ መውጫ ቅርንጭፍ አያኖሩም፡፡ ሐሴቶቻቸውም ከፍ ያሉ ሰማያውያን በመሆናቸው ምድር ምድሩን የሚሄደው ሰይጣን በቀላሉ ሊተናኮላቸውና ደስታቸውን ሊያጠፋ አይችልም፡፡
ዘንባባ ብዙ ቅርንጫፎች የሌለው መሆኑ አንዳንዴ ድንጋይ እንዲወረወርበት እና በዱላ እንዲመታ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ እርሱ ግን ‹‹ይቅር ባይ›› ተክል ነው፡፡ በተወረወረበት ድንጋይ እና ባረፈበት ዱላ ፈንታ የሚመልሰው ጣፋጭ ፍሬውን ነው፡፡ አንተ ድንጋይ ስትወረውርበት እርሱ ደግሞ እንደ ማር የሚጣፍጠውን ፍሬ ያዘንብልሃል፡፡ ሰይጣን ለእርሱ መግቢያ ምክንያት የማይሰጡትን ጻድቃን የሚፈትነው ለክፉ ዓላማው ማስፈጸሚያ የሚያደርጋቸውን ሰዎች በመጠቀም ነው፡፡ በእነዚህም ሰዎች አማካኝነት ብዙ የስድብ፣ የጥላቻና የስም ማጥፋት ድንጋዮችን ይወረውርባቸዋል፡፡ በበቀል ዱላ ሊያቆስላቸው ይሰነዝርባቸዋል፡፡ እነርሱ ግን የሰደቧቸውን ሰዎች በመመረቅ፣ የጠላቸውን በመውደድ፣ ለበቀል ስለሚያሳድዷቸው ሰዎችም በመጸለይ ጣፋጭ ፍሬዎቻቸውን ያዘንቡላቸዋል፡፡
በሆሳዕና ዘንባባ ይዘን ዘምረን፣ እንደ ዘንባባ ዛፍ አፍርተን፣ በኋላም ከጻድቃኑ ጋር ነጭ ለብሰንና በእጆቻችን የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘን ከበጉ ፊት ለመቆም ያብቃን!
ልክ እንደ ጻድቃኑ የዘንባባ ሕይወት ይስጠን!!!

+++"ስለ እኛ የታመመውን ምን አንደበት ይናገረዋል?!"+++
እጅግ ጥልቅ የጸሎት ሕይወት የነበረው፣ አካሉ አልቆ በአጥንቶቹ እስኪቆም ድረስ የሚጾመው ተሐራሚው ቅዱስ አባ ጳጉሚስ ከእለታት በአንዱ ቀን ይህን ተመለከተ፡፡ ቅዱሱ ዓርብ ዓርብ የጌታችንን ሕማማት እያሰበ ከእንባ ጋር አብዝቶ ይሰግድ ነበር፡፡ ከዓይኑ የሚወርደው እንባ ከሰውነቱ ወዝ ጋር እየተቀላቀለ ወደ መሬት በመውረዱ ምክንያት የሚሰግድበትን ቦታ አረጠበው፡፡ አባ ጳኩሚስም ይህን ወደ ጌታው እያመለከተ "ይኸው አንተን አገኝ ብዬ እንዲህ እደክማለሁ" ሲል ተናገረ፡፡ በዚህ ጊዜም መድኃኒታችን ለአባ ጳጉሚስ ተገልጦ "እኔም እንጂ ላንተ ብዬ እንዲህ ሆኜ ተሰቅያለሁ" በማለት በእለተ ዓርብ እንደ ተሰቀለ ሆኖ የተወጋ ጎኑን፣ የፈሰሰ ደሙን አሳየው፡፡ ቅዱሱም የጌታው ሕማም ከሕሊናው በላይ ሆኖበት ወድቆ ምሕረትን ለምኗል፡፡
+++++++++++++
ሕሊናቸው የክርስቶስን ሕማም ከማሰብ አቁሞ የማያውቀው አባ መብዓ ጽዮን መድኃኔዓለምን :- ‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የዕለተ ዓርቡን መከራህን አሳየኝ፡፡ ስለ ራሴ ፈጽሞ አለቅስ ዘንድ›› ሲሉ ለመኑት፡፡ ጌታም ‹‹መከራ መስቀሌን ለማየት ትፈቅዳለህን?›› ብሎ ጠየቃቸው። ጻድቁ አባ መባዓ ጽዮንም ‹‹አዎ! አይ ዘንድ እወዳለሁ›› አሉት። ያን ጊዜም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ እጆቹና እግሮቹ ተቸንክረው ታየ፣ በራሱም ላይ የእሾህ አክሊል ደፍቶ ነበር። እንዲህ ሆኖ በሮም አደባባይ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንደታየው ታያቸው። ይህን የመድኃኔዓለም መከራ የተመለከቱ የጻድቁ ዓይኖችም ፈዝዘው እስኪጠፉ ድረስ ትኩስ እንባዎችን ሲያዘንቡ ኖረዋል።
‹‹ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ›› - ‹‹ኃይሌና መጠጊያዬ እርሱ ጌታዬ ነው!››

+++‹‹በለምጻሙ ስምዖን ቤት ሳለ›› ማቴ 26፥6+++
አይሁድ በሊቀ ካህናቱ በቀያፋ ግቢ ውስጥ ተሰብስበው በጌታ ሞት ላይ ሲመክሩ፣ መድኃኒታችን ግን በቢታንያ በስምዖን ቤት እራት ግብዣ ተቀምጦ ነበር፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ ጌታ እራት የተጠራበት ቤት ባለቤት ‹ለምጻሙ ስምዖን› እንደ ሆነ ይናገራል፡፡ ጸሐፊው ስለ ምን ይህንን ሰው ስምዖን ብቻ ብሎ አልጠራውም? ‹ለምጻሙ› የሚለው ገላጭ ቃል መጠቀም ለምን አስፈለገው? በርግጥ ስምዖን በለምጽ ንዳድ የተያዘና በአይሁድ ዘንድም እንደ ረከሰ እና በደለኛ ተቆጥሮ የሚገለል ብቸኛ ሰው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አሁን ግን ጌታ ከሐዋርያቱ ጋር ሆኖ በእርሱ ቤት ለእራት በተቀመጠ ጊዜ፣ ቅዱስ ጄሮም እንደሚናገረው ይህ ሰው ካለበት ለምጽ ሁሉ ነጽቶ ነበር፡፡ ታዲያ ወንጌላዊው ስለ ምን ከለምጹ የነጻውን ስምዖን ‹‹ለምጻሙ›› ሲል ጠራው?
ይህ ያለ ምክንያት አልሆነም፡፡ ጌታችን በስምዖን ቤት ለእራት ተቀምጦ ሳለ የሚፈጸም ቀጣይ ወሳኝ ታሪክ ስላለ፣ ‹ለምጻሙ› የሚለው ገላጭ ለዚያ መግቢያ የሚሆን ወሳኝ ቃል ነበር፡፡ ቀጥሎ የምናገኘው ታሪክም አንዲት በኃጢአት የተመረረችና ነፍሷ የጎሰቆለባት ሴት፣ መንፈሳዊውን ምሕረት ፈልጋ ጌታችን ወዳለበት መምጣቷና የያዘችውን እጅግ ውድ የሆነውን ሽቱ ከፍታ በጌታ በራሱና በእግሮቹ ላይ ማፍሰሷን የሚናገር ነው፡፡ ይህች ሴት ቀድሞ በዝሙት ትኖር ነበረች ብትሆንም ዛሬ ግን የሽቱና የእንባን መባ ይዛ ወደ ክርስቶስ ቀርባለች፡፡ በዘመኑ ብዙዎች ያስጨንቃቸውና የክርስቶስን መድኃኒትነት ይፈልጉት የነበረው ለሥጋዊ ሕመማቸው ነበር፡፡ ምንም የሥጋ ሕመም የሌለባት ይህች ሴት ግን ባልተለመደ ሁኔታ የነፍሷን ሕመም (ኃጢአት) በምሕረቱ መድኃኒትነት ለመሻር ወደ ጌታችን ስትሮጥ መጣች፡፡ ይህም ሥራዋ እጅግ በጣም የምትደነቅ መንፈሳዊት ሴት ያደርጋታል፡፡
በዚህ ወንጌል የተጠቀሰችው ባለ ታሪክ ትሠራ የነበረው ሥራ በሁሉ ዘንድ አስነዋሪ የነበረውን፣ እንኳን በአምላክ ፊት ቀርቶ በሰው ፊት እንኳን ቀና ብሎ የማያስቆመውን ዝሙት ነበር፡፡ ታዲያ ወደ ክርስቶስ ለመምጣት ድፍረት የሰጣት ነገር ምንድር ነው? እንዴት ወደ መድኃኔዓለም ቀርባ ‹‹ማረኝ›› ለማለት በቃች? ካልን መልሱ ቀላል ነው፤ ጌታ ‹በለምጻሙ ስምዖን› ቤት እንደ ተገኘ አይታ ነው፡፡ ክርስቶስ ራሳቸውን ከሚያመጻድቁ ፈሪሳውያን መካከል በአንዱ ቤት ተገኝቶ ቢሆን ኖሮ ባለ ሽቱዋ ማርያም ድፍረት አግኝታ ወደ እርሱ ባልመጣች ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን ሰዎች እንደ ርኩስና በደለኛ ቆጥረው ያገሉት በነበረው ስምዖን ቤት ነውሩን ሁሉ አስወግዶለት አብሮት ለእራት እንደ ተቀመጠ ስላየች፣ የሚበዛው ድካሜን አይቶ የበለጠ ይራራልኝ እንደ ሆነ እንጂ ለእርሱ ያደረገውን ቸርነት ለእኔ አይነሳኝም ብላ በተስፋ ወደ ፈጣሪዋ ገሰገሰች፡፡ እጅግ የሚያስደንቅ ተስፋ ነው!!!
ዛሬም መድኃኔዓለም ክርስቶስ በለምጻሙ ስምዖን ቤት አለ፡፡ ስለዚህ ‹አይሰማኝ ይሆን› የሚለውን ጥርጣሬያችንን ትተን ወገባችንን ያጎበጠውን ኃጢአት በንስሐ ከእግሩ ስር ለማራገፍ ፈጥነን ወደ እርሱ እንቅረብ፡፡ በለምጻሙ ስምዖን ቤት ለእራት የተቀመጠ አምላክ በፍጹም ጸጸት ብንመለስ የእኛንም ቤት (ሰውነት) አይንቅም፡፡ ይልቅ ሳይረፍድ ቶሎ ሄደን ከእግሮቹ ስር እንውደቅ!!!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ
በዓለ ደብረ ዘይት፣ 2015 ዓ.ም.
ድረ ገጹን ይጎብኙ
https://dnabel.com
ዩቱብ ቻናል
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg