Telegram Web Link
ነጻው ስልጠና ከ 15 ደቂቃ በኋላ ይጀምራል!

የስልጠናው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

ዛሬ ምሽት ከ2፡30 እስከ 3፡30

በሰዓቱ እዚሁ ቻናል ላይ በመግባትና join የሚለውን በመጫን ይከታተሉ!
👍16576🔥7😁2🎉2🤩2
Live stream started
Live stream finished (1 hour)
ዛሬ “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence) በሚል የተዘጋጀው ስልጠና በሺዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች ነበሩት፣ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡

በዚሁ ርእስ ላይ ያዘጋጀሁትን ስልጠና መረጃ አቀብላችኋለሁ፡፡

Have a good night!
👍16591🔥54🎉9🤩3
የስልጠና እድል!

የስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

እናመሰግናለን!
87👍55😁4🔥3
አንዳንዴ . . . ያለ ነው!

አንዳንድ ጊዜ ማመንታት ያለ ነው - በፍጹም ግን ወደ ኋላ አንመለስም!

አንዳንድ ጊዜ መፍራት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንንበረከክም!

አንዳንድ ጊዜ ተስፋ መቁረጥ ያለ ነው - በፍጹም ግን አናቆምም!

አንዳንድ ጊዜ መሸነፍ ያለ ነው - በፍጹም ግን ሕይወት ከሚያቀብለን የየእለት ጦርነት አንሸሽም!

አንዳንድ ጊዜ መድከም ያለ ነው - በፍጹም ግን ዝለን አንወድቅም!

አንዳንድ ጊዜ ግራ መጋባት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንቅበዘበዘም!

አንዳንድ ጊዜ በሰው መገፋት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከዚያ ሰው ውጪ መኖር አየቅተንም!

አንዳንድ ጊዜ ድብርት ያለ ነው - በፍጹም ግን ደንዝዘን አንቀርም!

አንዳንድ ጊዜ ለጥያቄ መልስ ያለማግኘት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከመጠየቅ አናርፍም!

አንዳንድ ጊዜ ክፋት ያሸነፈ መምሰሉ ያለ ነው - በፍጹም ግን መልካምነትን አንጥልም!

መልካም ቀን!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍20167🔥16😁1🎉1
የስልጠና እድል!

የስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

እናመሰግናለን!
53👍27😁4
"በእውነቱ ሁለት አእምሮዎች አሉን፣ አንዱ የሚያስብ (one that thinks) እና አንድ የሚሰማው (one that feels)" – Daniel Goleman

አንደኛው የስሜት ብልህነት ነው፡፡ በእንግሊዝኛው “emotional quotient” (EQ) በመባል ይታወቃል፡፡

ሁለተኛው የአእምሮ ብልህነት ነው፡፡ በእንግሊዝኛው “intelligence quotient” (IQ) በመባል ይታወቃል፡፡

• ጥናቶች እንደሚነግሩን ከሆነ በስራም ሆነ በማንኛውም የማህበራዊ ኑሮ 80 በመቶው ስኬታችን የሚመጣው ከስሜት ብልህነት (Soft Skills) ነው፡፡

• የአእምሮ ብልህነት (Hard Skills) የሚሰጠን የስኬት መጠን ግን 20 በመቶ ብቻ ነው፡፡

• በሌላ አባባል ከፍ ያለ የአእምሮ ብልህነት (IQ) ኖሮንና አእምሯችን በብዙ እውቀት ተሞልቶ ሳለ፣ ስሜታዊ ብልህነት ከሌለን የራሳችንንና የሌሎች ሰዎችን ስሜት አያያዝ ካላወቅህበት የአእምሮ እውቀትህ ብቻውን የትም አያደርሰንም፡፡

በዚህ ርእስ ላይ የበለጠ ግንዛቤ በማግኘት ስኬታማ ጉዞ ለመጀመር የሚያስችላችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

የስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
👍9438😁2🔥1
በተሰማራችሁበት በማንኛውም መስክ ውስጥ ካላችሁ ትምህርትም ሆነ የእውቀት ክህሎት በበለጠ ሁኔታ የተጽእኖ ሰው የሚደርጋችሁ የስሜት እና የማሕበራዊ ብልህነታችሁ መሆኑን ታውቃላችሁ?

. የስሜት ብልህነት ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ፣

. ከአእምሮ ብልህነት በምን እንደሚለይ ለመገንዘብ፣

. የሁለቱን የየራስ ጥቅም ለመለየት፣

. የስሜት ብልህነት ማዳበሪያ መንገዶችን ለመማር፣

ፖስተሩ ላይ ያለውን መረጃ በመመልከት የምዝገባውን መረጃ መጠየቅና መቀበል ትችላላችሁ፡፡

የምዝገባ መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገልጡ መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
👍686
ጠዋት ስትነሱ!

መጀመሪያ የምታስቡት ሃሳብ ምን እንደሆነ በሚገባ ተመልከቱትና ያላችሁበትን የስሜት ሁኔታ ይነግራችኋል፡፡

• በእለቱ የምታከናውኗቸው ተግባሮቻችሁ ከባድ እንደሆኑ ካሰባችሁ እቅድ የማውጣት ክህሎት ላይ መስራት አለባችሁ፡፡

• ትናንት ስሜታችሁ ላይ አጉል ተጽእኖ ስለነበረው ሰው ካሰባችሁና ከተረበሻችሁ የሰዎችን ሁኔታ አያያዝ ላይ መስራት አለባችሁ፡፡

• ምንም የምትሰሩት ስራ እንደሌላችሁ ካሰባችሁ የፈጠራ እና አዳዲስ ነገር የመጀመር አቅማችሁ ላይ መስራት አለባችሁ፡፡

• ሁኔታችሁ ሊለወጥ እንደማይችል የተስፋ መቁረጥ ሃሳብ ካሰባችሁ የሰዎችን የምክር እገዛ የመጠየቅና የመጠቀም ሁኔታ ላይ መስራት አለባችሁ፡፡

ሃሳቦቻችሁንና እነሱ የወለዷቸው ስሜቶቻችሁን በፍጹም ችላ አትበሏቸው፡፡ ተገቢውን ምላሽ ስጧቸው፡፡

ስላላችሁበት ሁኔታ ሰዎችን መውቀስ አቁሙና አንድ ነገር አድርጉ፡፡

ያላችሁበትን ሁኔታ ለመርሳት ማሕበራዊ ሚዲያ ላይ በመዋል አትደበቁ፡፡

ቀና በሉና ራሳችሁ ላይ ስሩ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
121👍74🤩2
ከስሜት ብልህነት መገለጫዎች አንዱ

ስሜትን አለማፈን ወይም እንደመጣም አለመልቀቅ

በስሜት ብልህነት የበሰሉ ሰዎች አንድ ስሜት ሲሰማቸው እንደመጣ ከመልቀቅም ስሜቱን አምቆ ከመያዝና ከማፈንም ራሳቸውን የሚጠብቁ ናቸው፡፡

በስሜት ብልህነት ስንበስል ትክክለኛውን ስሜት፣ በትክክለኛው ሰው ላይ፣ ቦታ፣ ጊዜ እና መጠን መግለጥን እንለማመዳለን፡፡

ስሜትን እንደመጣ የመልቀቅ ልምምድ ጉዳት ምን እንደሆነና እንዴት ከዚህ ልምምድ መውጣት እንደምንችል ለማወቅ፣

ስሜትን አጉል የማፈን ልምምድ ጉዳቱ ምን እንደሆነና እንዴት ከዚህ ልምምድ መውጣት እንደምንችል ለማወቅ፣ የተዘጋጀላችሁን ስልጠና መውሰዳችሁን አትዘንጉ፡፡

በዚህ ርእስ ላይ የበለጠ ግንዛቤ በማግኘት ስኬታማ ጉዞ ለመጀመር የሚያስችላችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

የስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
👍8515
ልክ እንደ መልህቅ!

የልጅነት አጉል ትውስታዎቻችን በስነ-ልቦናው አለም መልህቅ በመባል (anchor) ይታወቃሉ፡፡

አንድ ጀልባ (ወይም መርከብ) በባህር ዳርቻ በመልህቅ (anchor) ከተያዘ በኋላ ምንም እንኳን ወዲህና ወዲያ ቢንቀሳቀስም የትም መሄድ እንደማይችል ሁሉ፣ በልጅነታችን የደረሰቡን ሁኔታዎች የትም መሄድ እስከማንችል ድረስ አንቆ ይይዘናል፡፡

የልጅነታችሁ የተዛባ የአስተዳደግ ቀውሰ (childhood trauma) በዛሬው ስሜታችሁ፣ ስነ-ልቦናችሁና ማሕበራዊ ግንኙነታችሁ ላይ ጣልቃ የመግባት አቅም አለው፡፡

አንዳንድ ነገሮች ስታዩ፣ ስትሰሙና ሲያጋጥማችሁ የሚቀሰቀሱ (triggered የሚሆኑ) ስሜቶች የዚህ ምልክቶች ናቸው፡፡

ይህንን ሁኔታ መፍትሄ ካልፈለጋችሁለት በስራችሁ፣ በማሕበራዊ ግንኑታችሁም ሆነ በፍቅር/ትዳር አጋርነታችሁ ላይ እንዳወካችሁ ይኖራል፡፡

ለራሳችሁ እንኳን የማይገባችሁን ስሜትና ባህሪይ ስታንጸባርቁ ራሳችሁን ታገኙታላችሁ፡፡ ካለፈ በኋላ ትጸጸታላችሁ፣ መልሳችሁ ግን እዚያው ላይ ትገኛላችሁ፡፡

ከዚህ ሁኔታ ለመውጣት የመጀመሪያው እርምጃ ጸሎት ማድረግ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ሆኖም፣ የራሳችሁንም ሃላፊነት መወጣትም አስፈላጊ ነው፡፡

ለዚህ እንዲረዳችሁ በማሰብ ነው ይህንን ስልጠና ያዘጋጀሁላችሁ፡፡

ለበለጠ መረጃ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ inbox በማድረግ የምዝገባውን መረጃ ተቀበሉ

@DrEyobmamo
👍9616🔥7
ስሜታችሁን ትገዙታላችሁ፣ ወይም ደግሞ ስሜታችሁ ይገዛችኋል!

ስሜታችሁን የመግዛታችሁ ምልክቶች

• ስሜቶቻችሁን እንደመጣ ባለመልቀቅ መረጋጋት

• ስሜቶቻችሁን ካለልክ አለማፈን

• ስሜቶቻችሁን በትክክለኛው ሰው፣ ቦታ፣ ጊዜና መጠን መግለጥ

• ካለፉት አጓጓል ስሜታዊነቶች ትምህርት በመውሰድ ራስን ማሻሻል

ስሜታችሁ እናንተን የመግዛቱ ምልክቶች

• ለስሜታችን ጊዜን መስጠት አለመቻልና እንደመጣ መልቀቅ

• ስሜትን ከገለጡ በኋላ መጸጸት፣ ተመልሶ እዚያው መገኘት

• ስሜትን መግለጽ አለመቻልና ለረጅም ጊዜ አምቆ መፈንዳት

• ትክክል እንዳልሆነ የምውታቁትን ስሜታዊነት አሁንም ሲገልጹ ራስን ማግኘትና አለመሻሻል

በዚህ ርእስ ላይ የበለጠ ግንዛቤ በማግኘት ስኬታማ ጉዞ ለመጀመር የሚያስችላችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

የስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
62👍58🤩2😁1
ለምንድን ነው . . .
👍95
ለምንድን ነው . . .

• ሰዎች እውቀት እያላቸው ልክ ምንም እውቀት እንደሌለው ሰው የሚኖሩት?

• ሰዎች ገንዘብ እያላቸው ልክ ምንም ገንዘብ እንደሌለው ሰው የሚኖሩት?

• ሰዎች ብዙ ጓደኛ፣ ዘመድና ወዳጅ እያላቸው ማንም እንደሌለው ሰው የሚኖሩት?

• ብዙ ሕልሞች እያላቸው ምንም እንደሌለው ሰው የሚኖሩት?

• አስገራ ራእይና ዓላማ እያላቸው ምንም እንደሌለው ሰው የሚኖሩት?

• በርካታ እድሎች እያላቸው ምንም አማራጭ እንደሌለው ሰው የሚኖሩት?

መልሱ አጭርና ግልጽ ነው፡- በስሜትና በማሕበራዊ ብልህነት ስላልበሰሉ!

ምንም አይነት አስገራሚ ነገር ቢኖረንም፣ ስሜታችንን በሚገባ መገንዘብ፣ መያዝና ማስተዳደር ካልቻልን፣ ያለን ነገር ሁሉ በዜሮ ነው የሚባዛው፡፡ ምክንያቱም የምንገነባውን ነገር የስሜታችን ሁኔታ ስለሚያፈርሰው ማለት ነው፡፡

ምንም አይነት ታላላቅ ክህሎች፣ ብቃቶች፣ እድሎችና የሰው-ለሰው ግንኙነቶች (connections) ቢኖረንም፣ ስሜታችንን በሚገባ መያዝና መግለጽ እስከምንችል ድረስ ያለን ነገር ሁሉ ባዶ ነው፡፡ ምክንያቱም የምንገነባውን ነገር በስሜት ያመብሰላችን ሁኔታ ስለሚያፈርሰው ማለት ነው፡፡

በዚህ ርእስ ላይ የበለጠ ግንዛቤ በማግኘት ስኬታማ ጉዞ ለመጀመር የሚያስችላችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

የስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
👍10923🔥2🤩2
የስሜት ብልህነትና የገንዘብ ብልጽግና ግንኙነት

የስሜት ብልህነትን ያዳበሩ ሰዎች . . .

• ከፍተኛ የሆነ ዲሲፕሊን ስላላቸው ገንዘብን ለማግኘት ጠንክሮ የመስራት ብልጫ አላቸው፡፡

• እጃቸው የገባውን ገንዘብ ለትክክለኛው ዓላማና በተገቢው መንገድ የማውጣት ጥንካሬ አላቸው፡፡

• ያላቸው የገንዘብ ሁኔታ ከፍ ሲል በቶሎ በመጓጓት ከመወሰን፣ ዝቅ ሲል ደግሞ በቶሎ ተስፋ ከመቁረጥ የሚጠብቃቸው የስሜት ሚዛናዊነት አላቸው፡፡

• ዛሬ ለጊዜው ተደስተው ነገ ከሚከፍሉ፣ ዛሬ ከፍለው ነገ በዘላቂነት የመደሰትን ያዳበረ የስሜት ጽንአት አላቸው፡፡

በዚህ ርእስ የበለጠ እውቀትና ልምምድ ለማዳበር የሚጠቅማችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋ፡፡

የስልጠው ርእስ፡-
“የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
👍9934😱3😁1🤩1
ሁለቱ በፍጹም ልታፍሩባቸው የማይገባችሁ ነገሮች

1. ማንነታችሁ

አንዳንድ ሰዎች ካለማቋረጥ በማንነታችሁ እንድታፍሩ፣ እንድትሸማቀቁና በዝቅተኝነት ስሜት አንገታችሁን አቀርቅራችሁ እንድትኖሩ የማድረግ ፍላጎት አላቸው፡፡ ማንነታችሁ ማለት ከፈጣሪ የተሰጣችሁ መልካችሁ፣ ቁመናችሁ፣ ዘራችሁ፣ ቋንቋችሁ፣ እና የመሳሰሉት ልትቀይሯቸው የማትችሏቸው ነገሮች ናቸው፡፡

በእነዚህ እናንተን ልዩ በሚያደርጉ ውብ ነገሮች አንጻር የግድ እነሱን ስላልመሰላችሁ ወይም ለየት ስላላችሁ ጥሩ ያልሆነን ስሜት እዲሰማችሁ አያድርጓችሁ፡፡ በአጉል ባህሪያችሁ እፈሩ እንጂ በማንነታችሁ አትፈሩ፡፡

2. በወቅቱ የሚሰማችሁ ስሜት

አንዳንድ ሰዎች አንድን ስሜት እንዲሰማችሁ የሚያደርጉ ተግባሮችን ይፈጽሙና ከዚያ የተነሳ አንድ ስሜት ሲሰማችሁና ስትገልጡት ከሁኔታችሁ በመነሳት ሕሊናችሁን ለመኮነንና ለመደብደብ ይሞክራሉ፡፡ እውነታው ግን የተገፋ ሰው የመገፋት ስሜት፣ የተጎዳ ሰው የመጎዳት ስሜት፣ የተካደ ሰው የመካድ ስሜት . . . መሰማቱ የማይቀረ ነው፡፡

ስለዚህ፣ ከምታልፉበት ሁኔታ የተነሳ ለሚሰማችሁ ስሜት ማንም ሰው ምንም አይነት የወቀሳ ጫናን እንዲያሳድርባችሁ አትፍቀዱ፡፡ ስሜትን ካለአግባብ የመግለጽ አጉል ልማድ ካላችሁ በዚያ እፈሩ እንጂ በሚሰማች ስሜት አትፈሩ፡፡

መልካም ቀን እመኝላችኋለሁ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/ዝ
👍16367🔥1😱1
መለስ በሉና አስቡት!

• ከዚህ በፊት ጀምራችሁ ብትቀጥሏቸው እጅግ ጠቃሚ የነበሩ፣ ነገር ግን ዲሲፕሊን በማጣት ያቆማችኋቸውን ነገሮች . . .

• ማቆም እንዳለባችሁ እያወቃችሁ ያላቆማችኋቸውና ላልተጠበቀ ችግር ያጋለጧችሁ ልምምዶች . . .

• መለያየት ከማይገባችሁ ሰዎች ጋር ካለአግባብ የተጋጫችሁባቸውና የተለያያችሁባቸው ሁኔታዎች . . .

• ዝም በማለት ብታልፏቸው ደግመው የማይመጡ የሰዎች ሁኔታዎች ላይ የማይገቡ ነገሮችን በመናገራችሁ ምክንያት አልበርድ ያሉ ሁኔታዎች . . .

• በሰማችሁት ማስረጃ የሌለው መረጃ ብቻ ስሜታችሁ ላይ ተጽእኖ ስለመጣ የወሰናችኋቸው አጉል ውሳኔዎች . . .

ሌሎችም መሰል ልምምዶች በስሜት ብልህነት ብትበስሉ ኖሮ ከብዙ አስቸጋሪ ውጤት ራሳችሁን ትጠብቁ ነበር፡፡

ይህንን ሂደት በሚገባ ለመገንዘብና በስሜትና በማሕበራ ብልህነት ለመብሰል የሚረዳችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

የስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
👍9432
ልዩነትን በጨዋነት መያዝ!
👍316
ልዩነትን በጨዋነት መያዝ!

የሚከተሉት አራት ሃሳቦች ለአንዳንዶቻችን አዲስ ቢሆኑም፣ ለአብዛኛዎቻችን ግን በስሜት ከንፈን ከሄድንበት ጽንፍ እንደገና ወደ ቀድሞው ሚዛናዊነታችን የሚመልሱን ሃሳቦች ናቸው፡፡

1. ራስን በመውደድና በራስ ወዳድነት መካከል ያለው ልዩነት

በግል ሕይወት ዓለም ራሱን የማይወድ ሰው የለም፡፡ ሚዛናዊ የሆነ ራስን መውደድ ለራስ በመጠንቀቅ፣ ራስን በመንከባከብ፣ ራስን በመቀበል፣ አንድን ነገር ለማግኘትና ራስን ለማሳደግ በመሯሯጥንና በመሳሰሉት ሊገለጥ ይችላል፡፡

ራስ ወዳድነት ግን ሰውን በመጣል ለመነሳት መሞከር፣ ሰው እንዲጠላ በማድረግ ለመወደድ መሞከር፣ የሌላውን ስም በማጥፋት የራስን ስም ለመትከል በመሞከርና በመሳሰሉት ሊገለጥ ይችላል፡፡

ማንም ራሴን እንድጠላ ሊያደርገኝ ያለመቻሉን ያህል፣ ማንም በሌላው ሰው ላይ ክፉ እንድሆን ሊያነሳሳኝ አይችልም፡፡

2. በውድድርና በፉክክር መካከል ያለው ልዩነት

በንግዱ ዓለም ከሌላው ነጋዴ ጋር ሳይወዳደር ትርፋማ መሆን የሚችል ሰው የለም፡፡ ሚዛናዊ የሆነ ተወዳዳሪነት ከሌላው ይልቅ ብዙ በመልፋት፣ ሌላው ከሚያቀርበው የተሻለ ጥራት ያለው ነገር በማቅረብ፣ ከሌላው የላቀ የደንበኛ አያያዝና አገልግሎት አሰጣጥ በማዳበር፣ ብዙ ከማግበስበስ ይልቅ ተመጣጣኝ ትርፍ በማግኘት በልጦ መገኘትና የመሳሰሉትን ነገሮች ይወክላል፡፡

አጉል ተፎካካሪነት፣ ለመነሳት ሌላውን መጣል፣ የሌለውን ንግድ ማጥላላት ሃሰተኛ ወሬን ማስወራት፣ ዋና ትኩረትን የግል እድገት ላይ ሳይሆን የሌሎች መውደቅ ላይ ማድረግ፣ ለማትረፍ ሕገ-ወጥ መንገዶችን መጠቀምና የመሳሰሉትን ሁኔታዎች ማሳየትን ያመለክታል፡፡

ማንም ንግዴን እንዳላሳድግ ሊያሳምነኝ ያለመቻሉን ያህል፣ ማንም በሌላው ነጋዴ ላይ የክፋትን መንገድ እንድከተል ሊያሳምነኝ አይችልም፡፡

3. በወገን ፍቅርና በወገንተኝነት መካከል ያለው ልዩነት

በወገን ዓለም ውስጥ ለተወለደበት ቤተሰብ፣ ተወልዶ ላደገበት ዘርና ለውድ ሃገሩ የማይቆረቆር ሰው የለም፡፡ሚዛናዊ የሆነ የወገን ፍቅር ለወገኖች በመድረስ፣ ወጎቹን በመውደድ፣ ወገኖቹን ለማሳደግ የሚችሉትን ማድረግ፣ ለወገን መስዋእትነት መክፈልና የመሳሰሉትን ያቀፈ ነው፡፡

ወገንተኝነት ትኩረቱ ከእኛ ወገን ሌላ የሆነውን በማጥቃት፣ በመጥላት፣ አጠገቤ አይድረሱ በማለት፣ እንዲጠፉ ለማድረግ በመሞከር፣ የእነሱን ቀምቶ ለወገን ለማስተላለፍ በመሞከር፣ የበታችነት እንዲሰማቸው በማድረግ፣ ጥላቻን በመንዛትና በመሳሰሉት ሊገለጥ ይችላል፡፡

ማንም ወገኔን ችላ እንድል ማድረግ ያለመቻሉን ያህል፣ ማንም ወገኔ ያልሆነውን ሰው እንዳሳድደው ሊያሳምነኝ አይችልም፡፡

4. በኃይማኖተኝነት በአክራሪነት መካከል ያለው ልዩነት

በኃይማኖት ዓለም ውስጥ የራሱን ኃይማኖት የማይወድና እንዲስፋፋለት የማይፈልግ የኃይማኖት ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡ ሚዛናዊ የሆነው ኃይማኖተኝነት ለእምነቱ በመቆም፣ እምነቱ የሚያስተምረውን በጎ ነገር በመተግበር፣ ተመሳሳይ እምነት ካላቸው ሰዎች ጋር በመገናኘት፣ ስለእምነቱ ለሌሎች በጨዋነት ለማሳወቅ በመሞከር፣ ይህ ስሜት ደግሞ የሌላ እምነት ሰዎችም ሊኖራቸው የሚችል ስሜት እንደሆነ አምኖ በመቀበል ያንን በማክበርና በመሳሰሉት ይገለጣል፡፡

አክራሪነት ከእኔ እምነት ውጪ እምነት ያለው ሰው በሙሉ መፈጀት አለበት በሚል ሃሳብ፣ በተሳዳቢነት፣ ስለራስ እምነት ከማስተማር ይልቅ የሌሎቹን ሲነቅፉ በመዋል፣ በጨካኝነትና በመሳሰሉት ሊገለጥ ይችላል፡፡

ማንም እምነቴን እንዳልከተል ሊያደርገኝ ያለመቻሉን ያህል፣ ማንም የሌላን እምነት ተከታዮች እንዳጠቃ ሊያሳምነኝ አይችልም፡፡

ልዩነቱን እንወቅ! ሚዛናዊ እንሁን! እንብሰል! አእምሯችንን እንጠቀም! ለጽንፈኝነት እምቢ እንበል! ሰው እንሁን!

መልካም ቀን!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
98👍74🎉2🔥1
2025/07/13 11:18:39
Back to Top
HTML Embed Code: