Telegram Web Link
የገንዘብ አያያዛችን ጉዳይ!

በሚከተሉት አምስት የገንዘብ ዘርፎች መብሰል፣ ማደግና ሚዛናዊ መሆን የገንዘብ ነጻነትን ይሰጣል፡፡

1. ገንዘብን የማግኘት ክህሎት - የገንዘብ ገቢያችሁን ይጨምረዋል!

2. ገንዘብን ለጤናማ ዓላማ የመጠቀም ጥበብ - ገንዘብን በበጀት የመጠቀም ብልሃታችሁን ያሳድገዋል!

3. ገንዘብን ኢንቨስት በማድረግ የማባዛት ብቃት - በኢኮኖሚ ልቆ የመገኘትን መንገድ ይጠርግላችኋል፡፡

4. ገንዘብን የማጠራቀም ዲሲፕሊን - ለድንገተኛ ነገር ዝግጁ ያደርጋችኋል!

5. ገንዘብን የመስጠት ፈቃደኝነት - የሰብአዊነትና የእርካታ ስሜትን ይሰጣችኋል!

በእነዚህ ወሳኝ የገንዘብ ሂደቶች በበሰልንና ሚዛናዊ በሆንን ቁጥር የገንዘብ ነጻነትንና እድገትን እናገኛለን፡፡

ለዚህና ለመሰል ከገንዘብ ጋር ለሚገናኙ እውቀቶች የሚጠቅማችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

እናመሰግናለን!
https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ጀምሮ ማቆም! የብዙዎች ትግል!

ለምንድን ነው የጀመርነውን ነገር መቀጠል የሚያስቸግረን?

1. የትኩረት ችግር

አንድ ሰው የተበታተነ አሳብ ካለው አንድን ነገር ጀምሮ እንዲቀጥልና ወደፍጻሜ እንዲገሰግስ አይፈቅድለትም፡፡ በጀመረው ስራ ላይ ከማተኮር ይልቅ በየእለቱ እንደመጣው ጉዳይ ሃሳቡን ስለሚቀያይር በአንድ ነገር ላይ በመቆየት እስከጥጉ የማድረስ ብቃቱ አይኖረውም፡፡

2. እንቅፋቶችን አስቀድሞ አለማሰብ

ሊገጥሙን የሚችሉ እንቅፋቶችን እቅጩን መተንበይ ባንችልም ዋና ዋና ችግሮች አስቀድመን ማየት ግን እንችላለን፡፡ ጥንቃቄ-ተኮር ትንበያ ከጅማሬ ግለት የተነሳ አስተሳሰባችን ተጋርዶ ከመገስገስና፣ እንቅፋት ሲመጣ ከመደናገጥ ይጠብቀናል፡፡

3. በቁርጠኝነት አለመጀመር

አንድን ነገር በቁርጠኝነት መጀመር ማለት አንዴ ጀምሬዋለሁ በሚል እሳቤ በጭፍንነት ወደፊት ብቻ ማየት ማለት አይደለም፡፡ ከጀመርን በኋላ በየጊዜው ግምገማና ማስተካከያ ማድረግ አስፈላጊ ቢሆንም፣ መነሻው የቁርጠኝነት ጉድለት ሲሆን ግን ውጤቱ ክስረት ነው፡፡

4. ሰው አስደሳችነት

አንድን ነገር ከጀመርን በኋላ ለሰዎች አመለካከት፣ ስሜትና የሃሳብ ስንዘራ አላግባብ ትኩረት በመስጠት የስሜት ውጣ ውረድ ውስጥ መግባት አቅማ ያሳጣናል፡፡ አንድን ነገር ለመቀጠል ከሁሉም በፊት በጉዳዩ እኛ ማመን ይኖርብናል፡፡
ሳታስቡና ሳትዘጋጁ አትጀምሩ፣ አንዴ ከጀመራችሁ በኋላ አታቁሙ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
በገንዘብ እንዳናድግ የሚያደርጉን አመለካከቶች
በገንዘብ እንዳናድግ የሚያደርጉን አመለካከቶች

በገንዘብ አቅም የማደግ ሁኔታ ከምንም ነገር ጋር ከመነካካቱ በፊት ከአመለካከታችን ጋር ይነካካል፡፡ በምንም የኑሮ ደረጃ ላይ ብንሆን፣ አመለካከታችንን ጤናማና ሚዛናዊ አደርገን ከጀመርን ቀስ በቀስ ማደጋችን አይቀርም፡፡

ለዛሬ ሶስቱን ልጥቀስ . . .

1. የገንዘብ ጉዳይ ከእድል ጋር እንደሚገናኝ ማሰብ፡፡

ልክ ነው! ሰዎች በአጋጣሚም እንበለው በእድል ገንዘብን ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ያንን ያገኙትን ገንዘብ ግን እንዴት መጠቀም፣ ማባዛት፣ መቆጠብና ኢንቨስት ማድረግ ካላወቁበት ተመልሰው መከሰራቸው አይቀርም፡፡

2. ሰዎች ሃብታም የሆኑት ሌላውን በመጨቆ እንደሆነ ማሰብ፡፡

ልክ ነው! አንዳንድ ሰዎች በተዛባ መንገድም ሆነ ሌላው በመጨቆን ሃብታም ሆነው ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም፣ ምንም እንኳን በሌብነትና በተንኮል የገንዘብ ሃብትን ቢያገኙም፣ ያላቸው የባህሪይ ድህነት ጊዜ ጠበቆ ወደታች እንደሚያወርዳቸው ግልጽ ነው፡፡

3. በገንዘብ የማደግ ፍጎት ትክክል እንዳልሆነ ማሰብ፡፡

ልክ ነው! ማሕባዊ እሴቶቻችን እና ኃይማኖታችን በገንዘብ ላይ ጥንቃቄ እንዲኖረን ያስተምሩናል፡፡ ሆኖም፣ ገንዘብን የማግኘት ሂደት በትክክለኛው መንገድ ከተያዘ ጥቅሙ እጅግ የላቀ እንደሆነ ማሰብ አለብን፡፡

“ታዲያ ትክክለኛው አመለካከት ምንድን ነው?” ለምትሉ መንገዱን የሚያመላክታችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ስኬት እና ስህተት!

ስኬት ጭንቅላታችሁ ላይ እንዲወጣ አትፍቀዱለት - የሌለ ትምክህት ውስጥ ይጨምራችኋልና!

ስህተት ልባችሁን እንዲነካው አትፍቀዱለት - የሌለ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ይጨምራችኋልና!

በስኬታችሁ ጊዜ ለዚያ ያበቃችሁን ፈጣሪን እና ለሁኔታችሁ መዋጮ ያደረጉን ሰዎች አመስጋኝ ሁኑ፡፡

በስህተታችሁ ጊዜ ሞካሪዎች ስለመሆናችሁና ከሁኔታው ትምህርትን ስላገኛችሁ ደስተኞች ሁኑ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ለወጣት ተማሪዎች የተደረገ ቅናሽ!

ወጣት ተማሪዎች ለዚህ ስልጠና የተደረገላችሁን 50% ቅናሽ ተጠቃሚ ለመሆን፣ ተማሪ መሆናችሁ እና የምትማሩበትን ትምህርት ቤት በመጥቀስ inbox አድርጋችሁ ጥያቄ ስታቀርቡ መረጃው ይላክላችኋል፡፡

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
በገንዘብ አያያዝ ማደግ!

በሚከተሉት አምስት የገንዘብ ዘርፎች በሚዛናዊነት መብሰል፣ ማደግና መሻሻ የገንዘብ ነጻነትን ይሰጣል፡፡

1. ገንዘብን የማግኘት ክህሎት

2. ገንዘብን ለጤናማ ዓላማ የመጠቀም ጥበብ

3. ገንዘብን ኢንቨስት በማድረግ የማባዛት ብቃት

4. ገንዘብን የማጠራቀም ዲሲፕሊን

5. ገንዘብን የመስጠት ፈቃደኝነት

በእነዚህ ወሳኝ የገንዘብ ሂደቶች በበሰልንና ሚዛናዊ በሆንን ቁጥር የገንዘብ ነጻነትንና እድገትን እናገኛለን፡፡

ለዚህና ለመሰል ከገንዘብ ጋር ለሚገናኙ እውቀቶች የሚጠቅማችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

የስልጠና እድል!

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ነጻ የሆነ ሕይወት !!!
ነጻ የሆነ ሕይወት !!!

ወደ እናንተ የሚሳቡትን ሰዎች የሚወስነው በራሳችሁ ላይ ያላችሁ አመለካከትና ከዚያ አመለካከታችሁ የተነሳ የምታንጸባርቁት ሁኔታ ነው፡፡

1. ራሳችሁን ከሆናችሁት በላይ ማሰብና ያንን ማንጸባረቅ

ይህ ሁኔታ የሌላችሁን ማንነትና ስኬት እንዳላችሁ በማሳየታችሁ ምክንያት ያንን የሌለ ነገር ለማግኘትና ለመጠቅም የሚፈልጉ ሰዎች ወደ እናንተ እንዲቀርቡ ያደርጋቸዋል፡፡ የዚህ ሁኔታ መጨረሻው ያልሆናችሁትንና የሌላችሁን ነገር ፈልገው ከመጡ ሰዎች ጋር ወራትና ዓመታት ካሳለፋችሁ በኋላ እንደገና ከዜሮ መጀመር ነው፡፡ ይህ ደግሞ የክስረት ሁሉ ክስረት ነው፡፡

2. ራሳችሁን ከሆናችሁት በታች ማሰብና ያንን ማንጸባረቅ

ይህ ሁኔታ ከማንታችሁ፣ ካላችሁና ከምትችሉት በታች ሆናችሁ ራሳችሁን በማቅረባችሁ ምክንያት ሕይወታችሁን እንደፈለጉ ለማድረግ እንደሚችሉ የሚያስቡና ያንን የሚፈልጉ ሰዎች ወደ እናንተ እንዲሳቡ ያደርጋቸዋል፡፡ የዚህ ሁኔታ መጨረሻው ብዙ ነገር ማከናወን የሚችለው ማንነታች በሰዎች ቁጥጥር ስር ሆኖ በከንቱ የማለፉና ከአቅሙ በታች የመኖሩ ሁኔታ ነው፡፡

3. ራሳችሁን በሆናችሁት መጠን ማሰብና ያንን ማንጸባረቅ

ይህ ሁኔታ ትክክለኛውን ማንነታችሁን፣ ያላችሁበትን ደረጃና የተሳካውንም ሆነ ያልተሳካውን በትክክል አይተው ከነማንነታችሁ የሚቀበሏችሁን ትክክለኛ ሰዎች ወደ እናንተ እንዲሳቡ ያደርቸዋል፡፡ የዚህ ሁኔታ መጨረሻው ከሩቅ ሲያዩዋችሁና በቅርብ ሲያገኟችሁ አንድ አይነት ሁኔታን በማግኘታቸው ምክንያት በእናንተ ላይ ትልቅ አመኔታን ይዘው የሚነሱ ሰዎችን መሳብ ነው፡፡ ይህ ግንኙት ዘላቂና ስኬታ ግንኙነቶች የሚጀመሩበትና ወደፊት የሚዘልቁበት አይነት ግንኙነት ነው፡፡

የራስ በራስ ጥያቄ!

• በማሕበራዊ ሚዲያ ራሴን አቅርቤ የምታወቅበትና ሰዎቹ በአካል ቢያገኙኝ ሊያዩት የሚችሉት ሁኔታ ክፍተት አለው?

• ስለማንነቴም ሆነ ስላለኝ ነገር የምናገረውና በእርግጥም የሆንኩትና ያለኝ ነገር ልዩነት አለው?

• ሰዎች በቀረቡኝና ባወቁኝ መጠን ይንቁኛል ብዬ በማሰብ የምሸማቀቅበት ሁኔታ አለኝ?

ሰዎች ላልሆናችሁት ማንነት ከሚወዷችሁና ለሌላችሁ ነገር ከሚቀርቧችሁ፣ በእውነተኛው ማንነታችሁ ቢጠሏችሁና ባላችሁበት የሕይወት ደረጃችሁ ምክንያት ቢርቋችሁ ይሻላችኋል፡፡

እንዴት ያለ ነጻ የሆነ ሕይወት !!!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የገንዘብ ፍሰት እውነታዎች!

1. ገንዘብን የማግኛውን መንገድ ካላወኩበት በሰው ላይ ጥገኛ እንደሆንኩ እኖራለሁ፡፡

2. የማገኘውን ገንዘብ በትክክለኛው መንገድ ማውጣትና መጠቀም ካልመድኩ ገንዘቡ የት እንደሚገባ ግራ እንደተጋባሁ እኖራለሁ፡፡

3. በእጄ ያለውን ገንዘብ ኢንቨስት በማድረግ ካላባዘሁት በአኗኗሬ ኋላ ቀር እሆናለሁ፡፡

4. ከማገኘው ገንዘብ ላይ መቆጠብን ካልተለማመድኩ ድንገተኛ ነገር ሲከሰት ግራ እጋባለሁ፡፡

5. ካለኝ ገንዘብ ላይ ለሰዎች መስጠትን ካልተለማመድኩ የመዝራት እና የማጨድን የማያለወጥ ሕግ ስለምገድበው ወደ እኔ የሚመጣውን የገንዘብ ፍሰት አቀዋርጠዋለሁ፡፡

በእነዚህ ወሳኝ ልምምዶችና በመሰል ርእሶች ዙሪያ የተዘጋጀው ስልጠና አያምልጣችሁ፡፡

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo

እናመሰግናለን!
አምስቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ሃሳብ (Comment) ሰጪነት መርሆች
አምስቱ የማሕበራዊ ሚዲያ ሃሳብ (Comment) ሰጪነት መርሆች

በማሕበራዊ ገጾች ያለንን ተሳትፎ የመልካም ተጽእኖ ምንጭ ማድረግ ከፈለግን እነዚህ አምስት ሕጎች ይጠቅሙናል፡፡

1. የምትሰጡት ሃሳብ (Comment) አሉታዊ ከሚሆን ይልቅ አዎንታዊ ቢሆን ይመረጣል፡፡

ምንም እንኳን አንዳንድ ጊዜ አሉታዊ-ተኮር የሆኑ ሃሳቦችን ለመሰንዘር የሚጋብዙን ሁኔታዎች ቢከሰቱም፣ እነሱን ሃሳቦቻችንንም እንኳን ልናመጣ የምንፈልገውን ለውጥ በማጉላት አዎንታዊ ቀለም መስጠት እንደምንችል እናስታውስ፡፡

2. በምትሰጡት ሃሳብ (Comment) ሰዎችን መንቀፍ ላይ ከማተኮር ይልቅ ሰዎችን መደገፍ ላይ ማተኮር ይመረጣል፡፡

ምንም እንኳን አንዳንድ ጊዜ ስህተት አራማጅን ሰው መንቀፍ አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜ ቢኖርም፣ አብዛኛው ዝንባሌያችንና ልምምዳችን ግን የሚደገፉትን ከመደገፍ ይልቅ የሚነቀፉትን መንቀፍ ላይ የሚያተኩር እንዳይሆን መመልከት አስፈላጊ ነው፡፡

3. በምትሰጡት ሃሳብ (Comment) አማካኝነት አንድን ሰው ለማድነቅ ብላችሁ ሌሎችን አለማንቋሸሽ ይመረጣል፡፡

ምንም እንኳን አንዳንድ ጊዜ ሰዎችን ስናደንቅ ሊደነቁ የማገባቸውን የሌሎች ሰዎች ሁኔታ ማጋለጣችን ባይቀርም፣ ቀጥተኛ በሆነ መልኩ ሰዎችን ማንቋሸሽ የእኛን የተቀባይነት ደረጃና የመልእክት ጥንካሬ ስለሚያወርደው በጥንቃቄ ማድረግ መልካም ነው፡፡

4. በምትሰጡት ሃሳብ (Comment) አማካኝነት የምትሞግቱት ነገር ካለ ከሰዎቹ ጋር ከመጋጨት ይልቅ ሃሳባችሁን ከሃሳባቸው ጋር በማጋጭ የበረታው ሃሳብ እንዲያሸነፍ መፍቀድ ይመረጣል፡፡

ምንም እንኳን አንዳንድ ጊዜ የሰዎችን ጤና-ቢስ ሃሳብ ለመሞገት የሰዎቹን ማንነት መጥቀስ የግድ ቢሆንም፣ ዋናው ትኩረታችን ግን የሰዎቹን ስም፣ ህልውና እና ማንነት ማንቋሸሽ ሳይሆን የተዛባ ሃሳባቸውን ማዳከም እንደሆነ አንዘንጋ፡፡

5. በምትሰጡት ሃሳብ (Comment) ላይ እርግጠኝነት ከሌላችሁ ሃሳብ ከመስጠት ይልቅ ዝም ማለት ይመረጣል፡፡

ምንም እንኳን አንዳንድ ጊዜ በአንዳንድ ነገሮች ላይ ቀለል ያሉ ሃሳቦችን መሰንዘር ችግር ባይኖረውም፣ የከረረ ስሜትንና አቋምን ለመግለጽ የሚጋብዝ ሁኔታ ሲገጥመን ግን በነገሩና በእውነታው ላይ እርግጠኛነትን መያዛችንን አንዘንጋ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የትም የማይሄደው መርከብ
በአላማ የመኖር ቁልፍ
የትም የማይሄደው መርከብ
በአላማ የመኖር ቁልፍ

(“25 የስኬት ቁልፎች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

በአንድ ከተማ ውስጥ በየምሽቱ ሰዎችን እየጫነ ለሰዓታት በባህሩ ላይ ወዲህና ወዲያ በመሄድ ካሳለፈ በኋላ በመጨረሻ ሰዎቹን የነበሩበት ስፍራ መልሶ የሚያራግፋቸው መርከብ እንዳለ ይነገራል፡፡

ይህ ግዙፍ መርከብ በውስጡ አለ የተባለ በማንኛውም ዘመናዊ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ነገሮችን አካቷል፡፡ መዝናኛው፣ መዋኛው፣ መጫወቻው፣ የሚበላውና የሚጠጣው ሙሉ ነው! የዚህ መርከብ ስም፣ “የትም የማይሄደው መርከብ” በመባል ይታወቃል፡፡

ይህ መርከብ በየምሽቱ ሰዎችን በመጫን ወዲህና ወዲያ ይሄዳል፣ ነገር ግን የትም አይደርስም፡፡ በጉዞው ወቅት ተሳፋሪዎቹ ይጫወታሉ፣ ይበላሉ፣ ይጠጣሉ፣ ይደንሳሉ፣ ይተዋወቃሉ፣ ያወራሉ … በመጨረሻ ግን ራሳቸውን የተነሱበት ቦታ ላይ ያገኙታል፡፡ በእለቱ በተከናወነው ነገር “እጅግ ደስ ከተሰኙ” በኋላ ሌላ የደስታ ምንጭ ፍለጋ ወደየስፍራቸው ይሰማራሉ - ጉዞአቸው ግን የትም አልወሰዳቸውም!

“ታላላቅ አእምሮዎች ዓላማ አላቸው፣ ሌሎቹ ግን ምኞት ብቻ ይዘዋል” - Washington Irving

በዚህች ምድር ላይ ከ7 ቢልየን ሕዝብ በላይ ወዲህና ወዲያ ሲመላለስና ዓለም ሕይወት ባላቸው ፍጡራን መሞላቷን ማየት ደስ ያሰኛል፡፡ ሆኖም ይህንን ደስ የሚያሰኝ ነገር ጥቁር ነጥብ የሚጥልበት አንድ አሳዛኝ ነገር አለ፣ ቁጥራቸው ጥቂት ያልሆኑ ሰዎች የሚሄዱበትን አያውቁም፡፡

እነዚህ ሰዎች በቀን ውስጥ ብዙ እንቅስቃሴ ቢያስመዘግቡም፣ የእነዚህ እንቅስቃሴዎች ድምር ውጤቱ ዜሮ ወይም ባዶ ነው፡፡

የብዙ ቁጥሮች ድምር ዜሮ የሚሆነው እንዴት ነው? መልሱ ቀላል ነው፡፡ የብዙ ቁጥሮች ድምር ዜሮ የሚሆነው የተደመሩት ቁጥሮች በሙሉ ዜሮ ሲሆኑ ነው፡፡ የየእለት እንቅስቃሴአችን ዜሮ የሚሆንበት ብቸኛ ምክንያት ካለምንም ዘላቂ እይታ ስለምንተገብረው ነው፡፡

የእለቱ ተግዳሮት የሚያመጣብን ትግልና የጊዜው መልካም ገጠመኝ የሚሰጠን ጊዜአዊ ደስታ ልንገነባው ከሚገባን አጠቃላይ የሕይወት ዓላማ አይነ-ህሊናችንን ይጋርዱታል፡፡ ግንባታ-የለሽ ደስታ፣ ግንባታ-የለሽ ጨዋታ፣ ግንባታ-የለሽ ስራ፣ ግንባታ-የለሽ ወዳጅነት፣ ፍጻሜ የለሽ ሩጫ … ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፡

አንድ ሰው ስኬታማነትን በብርቱ ከፈለገ፣ በሕይወቱ ያለው ዓላማ ጉዳይ ግድ ሊለው ይገባል፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ስልጠናው ልክ የነገ ሳምንት ይጀምራል !!!

ሳትዘናጉ ተመዝገቡ!

የምዝገባ መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገልጹ መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
#Temer real estate

09-46-14-24-08

ፒያሳ ሊይሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት አጠገብ 3ኛ ሳይታችን ሽያጭ ጀምረናል።

➢ ሙሉ ክፍያ ከ6.9 ሚሊዮን ብር ጀምሮ

➢ ከባለ 1 እስከ ባለ 3 መኝታ ቤቶች

➢ ከ63 ካሬ እስከ 146 ካሬ

👉ቅድመ ክፍያ 10% ብቻ

ከ 30% ጀምሮ ለሚከፍሉ ደንበኞቻችን 25% ቅናሽ ያገኛሉ።

በተጨማሪም የንግድ ሱቆች ፒያሳ አድዋ00 ፊት ለፊት ከ3.9ሚሊዮን ብር ጀምሮ

👉 በተለያዪ አካባቢዎች የመኖሪያ ቤቶች እና ሱቆች አሉን ።

1ኛ  ሳር ቤት አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት ሳይት

2ኛ  አያት ፈርስ ቤት ሳይት

3ኛ  ጋርመንት አፍሪካ CDC ፊት ለፊት ሳይት

4ኛ  አያት አደባባይ ፊት ለፊት ሳይት

5ኛ  አያት ሎማያድ ሳይት

6ኛ  ሱማሊ ትራ ሳይት ለሽያጭ አውጠናል

👉 ማሳሰቢያ ፤- ምንም አይነት የዋጋ ጭማሬ አናደርግም ።

ለበለጠ መረጃ

09-46-14-24-08
መኖር!

ያለፈውን ስህተታችሁን
እያሰባችሁ፣ “ምነው ባላደረኩት ኖሮ” እያላችሁ ከመጸጸት ይልቅ ትምህርታችሁን ወስዳችሁ መኖር!

ስለሁኔታዎቻችሁ ከመጨነቅ ይልቅ መለወጥ የምትችሉት ላይ እየሰራችሁ የማትችሉትን ግን በመቀበል መኖር!

ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ እየጠበቃችሁ ሳይሆን ሲቀር ቅሬታ ውስጥ ከመግባት ይልቅ ለተደረገላችሁ እያመሰገናችሁ መኖር!

የሰላም ኑሮ ተመኘሁላቸሁ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
2025/06/30 14:19:06
Back to Top
HTML Embed Code: