Telegram Web Link
በዳሰነች ወረዳ በ ቱርካና እና  ኦሞ ወንዝ ሙላት ምክንያት ከ79 ሺህ 828 በላይ አርብቶ-አደሮች ተፈናቀሉ

በ ደቡብ_ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በቱርካና እና በኦሞ ወንዝ ሙላት ምክንያት ከ79 ሺህ 828 በላይ አርብቶ-አደሮች መፈናቀላቸውን የወረዳው አስተዳደሪ አቶ ታደለ ሀቴ ገለጹ።

መንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት የተገነቡ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በውሃ በመዋጣቸው ምክንያት ከአገልግሎት ውጭ እንደሆኑም ገልጿል።

የቱርካና ሐይቅ በ8 ዓመት ጊዜ ውስጥ 65 ኪ. ሜትሮችን ተጉዞ የወረዳው ዋና ከተማ ወደሆነችው ኦሞራተ 2 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንደደረሰና በቀጣይም ከተማው ሙሉ በሙሉ የመዋጥ አደጋ እንደጋረጠባት አቶ ታደለ ተናግረዋል፡፡ ይህም በከተማዋ ነዋሪዎች ዘንድ ስጋት አሳድሮባቸዋል ብለዋል።

ይህን የተገለጸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢ እና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዳሰነች ወረዳ በመገኘት ከወረዳው የስራ ሃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ነው።

በዚሁ ወቅት የወረዳው አስተዳዳሪ፤ የሜትሮሎጂ ትንበያዎች እንደሚጠቁሙት፣ በቀጣዮቹ የክረምት ወራት ከፍተኛ የሆነ ውሃ ወደ ኦሞ ወንዝና ቱርካና ሀይቅ ስለሚገባ ችግሩ ከዚህ ሊከፋ ይችላል ሲሉ ስጋተቸውን ለቋሚ ኮሚቴው አክለው ገልጸዋል።
🔥4😭2
እስራኤል በመላው ዓለም የሚገኙ ኤምባሲዎቿን ዘጋች ‼️

እስራኤል በኢራን ላይ የፈፀመችውን ጥቃት ተከትሎ በመላው ዓለም የሚገኙ ኤምባሲዎቿንና የቆንስላ ፅህፈት ቤቶቿን በጊዜያዊነት ዘግታለች።

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው ተለዋጭ መልእክት እስኪሰጥ ድረስ በመላው ዓለም የሚገኙ የእስራኤል ኤምባሲዎችና የቆንስላ ፅ/ቤቶች ተዘግተው ይቆያሉ ተብሏል፡፡

በውጭ ሀገራት የሚገኙ እስራኤላውያን ጥንቃቄ እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ ማሳሰቡን ዘገባው አክሏል።

የእስራኤል ጦር በኢራን ላይ በፈፀመው የአየር ጥቃት በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የኒውክሌር ጣቢያዎች እና ወታደራዊ ኢላማዎችን መምታቱ ተነግሯል፡፡
🔥105
እስራኤል አዲስ ጥቃት መፈፀሟ ተነገረ !

የእስራኤል አየር ሃይል አመሻሹ ላይ በኢራን መአከላዊ ክፍል በመዝለቅ ጥቃት መፈፀሙን አስታወቀ ።

የእስራኤል የስለላ ድርጅት እንደገለፀዉ ከሆነ አመሻሹ ላይ የፈፀመዉ ጥቃት የኢራንን የጸጥታ ተቋም ልብ ውስጥ ዘልቆ በመግባት ከኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ጋር ግንኙነት ያላቸውን ቦታዎች ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን የአየር መከላከያ እና የባለስቲክ ሚሳኤል ማዕከላትን ኢላማዎች መምታቱን ገልጿል።

ጥቃቱን በተመለከተ ከቴህራን በኩል በተገኘ መረጃ በተራራ ውስጥ በጥልቀት የተገነባው ፎርዶ የኑክሌያር ማብሊያ ጣቢያን ጨምሮ በርካታ ሰዉ የሚኖርባቸዉ አካባቢዎች በቦንብ መደብደቡን በጥቃቱም 78 ሰዎች መሞታቸውን እና ከሟቾቹ መካከል ህጻናትን ጨምሮ ሲቪሎች እንደሚገኙበት የኢራን መንግስት ቲቪ  ገልጿል ።
11
ቃሉን እንዳነበብን የሚመለከተን ሰዎች ደንገጥ ማለታችን ስለማይቀር ደንግጠን መቅረት ሳይሆን ወደእግዚአብሔር መቅረብና ኃጢአታችንን ተናዝዘን ንስሐ መግባት ይገባናል። እግዚአብሔር ሁሌም መሃሪ ነው እኛ አልቀርብ አልጸጸት አልማር አልን እንጂ።

ቸሩ መድኃኔዓለም ልቦና ይስጠን ለሁላችንም! በሰው ዘንድ መከበር መፈለግን (ከንቱ ውዳሴን) ያስወግድልን!
😭199
ኢራን በእስራኤል ላይ በርከት ያለ የሚሳኤል ጥቃቶችን ሰነዘረች።

በእሰራኤል የአደጋ ጊዜ ደውሎች ማስጠንቀቂያ የተሰማ ሲሆን የእስራኤል ጦርም ሚሳኤሎቹን በማክሸፍ ላይ ተጠምዷል።

በሚሳኤል ጥቃቱ ስለደረሰ ጉዳት ምንም ያልተባለ ሲሆን እስራኤላውያን ወደ ቦምብ መከላከያ ስፍራዎች እንዲገቡ ታዘዋል።

ዛሬ ቀን ላይ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ከኢራን የሚቃጣን የሚሳኤል ጥቃት ለመመከት ዝግጁ መሆናቸውን መግለፃቸው ይታወሳል።
14
ኢራን በእስራኤል ላይ የፈጸመችው የአፀፋ ምላሽ ከትላንት ምሽት ጀሞሮ እስከ ዛሬ ንጋት የቀጠለ ሲሆን ኢራን በመቶዎች የሚቆጠሩ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን በእስራኤል ላይ ተኩሳለች። በዚህም እስካሁን ብዙ ጉዳት አድርሳለች።

እስካሁን በደረሰው ጥቃት የእስኤራሉ "ፔንታጎን" የሚባለው "ኪርያ" የተሰኘው ዋናው የመከላከያ ሚኒስትር ህንፃ፣ የተወሰኑ የጦር ሰፈሮች፣ ዲሞና የተሰኘው የኒኩሌር ምርምር ጣቢያ እና በከተማዋ ማዕከል የሚገኝ አንድ ሰማይ ጠቀስ ህንፃ እንደተመታ ተዘግቧል። 4 የሚሆኑ ሰዎች እንደሞቱ እና 70 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው ታውቋል።

የእስራኤል የአየር መቃወሚያ ሚሳኤሎቹን በሰማይ ላይ አጋይቶ ያስቀረ ቢሆንም ፈጣን ባላስቲክ ሚሳኤሎች በመሆናቸው እና ቁጥራቸው ብዙ በመሆኑ ሁሉንም መከላከል አልተቻለም። በጠዋቱም ሚሳኤሎቹ ያደረሱትን ጉዳት የመጨረሻው ቪዲዮ ላይ ማየት ይቻላል።
13🔥3
እስራኤል ሌላ ዙር ጥቃት ፈፀመች‼️
በቴላቪቭ  በርካታ ፍንዳታዎችን እና ውድመትን ያስከተለው ጥቃት በኢራን ላይ መፈፀሟ ተነገረ‼️
በቴህራን የኢራን መንግስት ቲቪ እንደዘገበው ከሆነ ዛሬ አመሻሹ ላይ እስራኤል ከ150 በላይ ቦታዎች ላይ ጥቃት መፈፀሟን እና በተፈፀመው ጥቃትም በኢራን ደቡባዊ ቡሻህር ግዛት ውስጥ ከጋዝ ማውጫ ጨምሮ በርካታ ቦታዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የገለፀ ሲሆን በጥቂቱም   20 ህጻናትን ጨምሮ ወደ 60 የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸውን እና በመላ ሀገሪቱ ተጨማሪ ጥቃቶች መፈፀሙን ዘግቧል ።
18😭4
🟢🟡🔴
ሰኔ 8 | #_የእመቤታችን_ማርያም ቅዳሴ ቤት ተከናወነ፨

በዚች ቀን አምላክን የወለደች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የእመቤታችን ማርያም በስደቷ ወቅት ልጇ ያፈለቀው የውኃ ምንጭ ዘንድ ያለች የቤተ ክርስቲያንዋ ቅዳሴ ነው።

ይኽም ከእመቤታችን 33ቱ ዋነኛ በዓላት አንዱ ነው።

ይህም እንዲህ ነው፦ ለጻድቁ ዮሴፍ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልም ተገልጾለት ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ አገር ሒድ አለው። ዮሴፍም ነቅቶ ተነሣ።

ክብር ይግባውና ሕፃኑን ጌታችንን እናቱንና እኅቷ ሰሎሜን ይዞ ወደ ግብጽ አገር ሔዱ። በዚያም በውስጧ ባሉ በብዙ አገሮች እየዞሩ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ኖሩ። የእመቤታችን ስደት የጀመረው ግንቦት 24 ቀን ነው። ለ3 ዓመት ከ6 ወርም ተወዳጅ መድኃኒት ልጇን ይዛ በስደት ቆይታለች።

ሄሮድስም ከሞተ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ ሁለተኛ ተገለጠለት። ወደ እስራኤልም አገር ሕፃኑንና እናቱን ይዞ እንዲመለስ አዘዘው።

በሚመለሱም ጊዜ ወደ መዓልቃ ደረሱ። ከዚያም ወደ መጣርያ አገር ደረሱ ይቺም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ውኃ ያፈለቀባትና የመታጠቢያ ቦታ የሆነች ናት። እርሷም እስከ ዛሬ አለች።

ሰዎችም ከአገሩ ሁሉ ከየነገዱ ሁሉ መጥተው አምላክን ወደ ወለደችና በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ወደ ጸናች ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም ይለምናሉ። ከተባረከውም የውኃ ምንጭ ታጥበው ከደዌያቸው ሁሉ ይድናሉ። በዛሬዪቱ ቀን ከከበረች ቤተ ክርስቲያንም ይባረካሉ።

እርሷን እመቤታችንን ለመረጣትና ለወደዳት በሥጋም እናቱ ላደረጋት ስለርሷም ዘመድ ለሆነንና ወደርሱ ላቀረበን ወራሾቹም ላደረገን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።

                🌹
T.me/Ewnet1Nat
43🙏1
2025/07/09 11:08:02
Back to Top
HTML Embed Code: