Telegram Web Link
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
ልዩ ማሳሰቢያ ከራዕይ ዮሐንስ 20 8/10/2017 ዓ.ም
በልዩ ልዩ ሥፍራ ለምትጋጩ ይኼ ለናንተ ነው ❗️

በልዩ ልዩ ሥፍራ የምትጋጩ ጊዜውን እንዳትሻገሩ ዲያቢሎስ አጥብቆ እየሠራ መኾኑን ልትገነዘቡ ይገባል❗️

የራእይ ዮሐንስ መግለጫ ከ38:25 ደቂቃ ጀምሮ
ኢትዮጵያዊነትን እንደ አጥንት እና ሥጋችን፤ ደማችን ብልቶቻችን አድርገን ልናየው እንችላለን ኢትዮጵያዊነትን። በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ደግሞ ነፍስን ፤ እስትንፋስን ፤ ሕይወትን በደም በአጥንት ፤ በሥጋ ውስጥ ሕይወት ሰጥታ እንደተመለከትነው ሁሉ በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ተዋህዶ ዕምነት ቀጠተኛይቱ ኦርቶዶክስ እምነት ሲዋሃዱ ለኢትዮጵያዊነት ሕይወትን ይህችንም የተዋህዶ ዕምነት ሕይወት ዘሪ አድርጎ ለኢትዮጵያዊነት መገለጥ መንቀሳቀስ መንገድንይሰጣል ማለት ነው። ይህም ማለት ለኢትዮጵያዊነት የሁለቱ ውህደት። የኢትዮጵያዊነት እና የተዋህዶ እምነት ውህደት። ሁለቱም ሲቀናጁ ሲዋሃዱ ልክ ደም እና ሥጋ አጥንት ከነፍስ ጋር ሲዋሃዱ ሕይወትን እንደሚዘሩሁሉ በኢትዮጵያዊነትም ውስጥም እንደዚሁ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት እና ተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነት ሁለቱምሲዋሃዱ ሕይወት ያላቸው ሆነው ይታያሉ ማለት ነው።
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ (ኢትዮጵያዊ የተክለሃይማኖት ወዳጅ🇨🇬🇨🇬🇨🇬)
📍
በስተመጨረሻም፥
#ለኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን_ቤተሰቦች

[📍] የተሸከማችሁት ኃላፊነት ትልቅ ነው። በማስተዋል ተጓዙ ለሌላው ብርሃን ሆናችሁ ተመላለሱ። የሚዘምቱባችሁን፣ የሚያስከፏችሁን፣ የሚያሰድዷችሁን ሁሉ ግድየለም ታገሷቸው። በፍቅር በትዕግሥት ልታስረዷቸው ሞክሩ። እምቢ ካሉ ከጸኑባችሁ ደግሞ ልቀቁላቸው አካባቢያቸውን። ትቢያውንም እያረገፋችሁ ከእግራችሁ ላይ መሔድ ነው። ያ ቀዬ ግን በኋላ ላይ ከባድ አደጋ ውስጥ ይወድቃል። እነዛም ሕዝቦች ይጎዳሉ። ግን ያ እንዳይሆን ምከሯቸው።

[⚜️] እናንተ ደግሞ እርስ በራሳችሁ እግዚአብሔር በሚወደው መንገድ ላይ ቆማችሁ በፍቅር መተሳሰብ በእምነት መጽናት ይገባችኋል። እግዚአብሔር አሁን ሥራውን ጀምሮ በፊት ለፊት እያያችሁ፣ እየሰማችሁ ነው፤ እያስተዋላችሁ ነው።

[⚜️] ጉድለታችሁን አርሙ ታላላቆቻችሁን አክብሩ ወንድሞቻችሁን አክብሩ ውደዱ ተዋደዱ።

[⚜️] ጽዋችሁን አክብራችሁ ያዙ።

[⚜️] በወንድምህ ላይ የምትነቅፈው ነገር እንኳን ቢኖርህ በትሕትና ነው መነጋገር ያለብህ። በመከባበር ነው መነጋገር ያለብህ! እግዚአብሔር ፍቅርን ነው እንጂ የሚወደው ጸብን አይወድም። ትሕትና ነው እንጂ የሚወደው ትዕቢትን አይወድም። እውነትን እንጂ የሚወደው ሐሰትን አይወድም። ስለዚህ ወደ ስህተት አሠራር ወደ ተሳሳተ አካሄድ አትሒዱ። እምነታችሁን የሚፈትን፣ እምነታችሁን የሚያውክ የስህተት አሠራር ውስጥ እንዳትገቡ ተጠንቀቁ።

[⚜️] ንስሐ ሁልጊዜ ግቡ! በእግዚአብሔር ፍቅር ተመላለሱ። ፍቅርን አጽኑ። በወንድማማች መዋደድ በፍቅር ተሰባሰቡ፤ ተነጋገሩ፤ ተመካከሩ፤ ተዋደዱ። በጽዋችሁም ፍቅር ይንገሥበት። ጠብ ጭቅጭቅ አያስፈልግም።

[⚜️] መማክርቶችን አክብሩ! በዚህ ሰዓት እናንተ እየመሩ ያሉ፥ ይነስም ይብዛም መንፈሳዊ ምሪትን የሚሰጡ ከእግዚአብሔር የተሰጧችሁ ወንድሞቻችሁ ናቸው። አክብሯቸው! አትናቁ! ይሄ ንቀት ማንጓጠጥ እኔ አውቃለሁ ባይነት እነዚህ ሁሉ የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚሠራው ባሕርይ አይደለም፤ ምክራችን ይሄ ነው።

[⚜️] በአሁኑ ጊዜ መንፈሳዊ መነቃቃት ሊኖረን ይገባል! በጾም በጸሎት ልንተጋ ይገባል። ቃሉን ደግሞ ያልሰማችሁ በደንብ ያላነበባችሁ ደግሞ አንብቡ ትምህርቶቹን ተከታተሏቸው። ስሟቸው። የእግዚአብሔርን ቃል በተከታታይ ትምህርት እየሰጠን ነው። እነሱን አድምጡ።

[⚜️] ዝግጅትም ይኑራችሁ! ከዚህ በላይ ምን ምልክት ትፈልጋላችሁ? ቀድሞ ስንት ጊዜ ጀምሮ እኛ ለዝግጅት መክረናል። አሁንም ዝግጅት ይኑራችሁ! ደካማ አትሁኑ! በመንፈስ ጠንካራ ሁኑ!

[️⚜️] ግዴታችሁን፥ አሥራት በኩራታችሁን፣ ቸርነት ማድረጋችሁን፣ ጸሎታችሁን እነዚህን ሁሉ እንደጀመራችሁት መጨረስ፣ መሔድ፣ መጓዝ! ሁሉንም ነገር በካሳ ታገኙታላችሁ። ሁሉንም ነገር በበረከት መልሱን ታገኙታላችሁ። እርስ በርሳችሁ ስለጤና፣ ስለ ሰላም፣ ስለ ፍቅር ስለ ውስጣችሁ አንድነት ስለዚህ ሁሉ ጸልዩ።

[📍] እግዚአብሔር እንዲያጸናችሁ፣ እንዲተክላችሁ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር ደጋግማችሁ አቤት በሉ ምክራችን ይሄ ነው።

➻ የኢ.ዓ.ብ መግለጫ፥ ጥቅምት 21፥ 2016 ዓ.ም መግለጫ (ክፍል 2)
⌚️️ ከ1፡04፡28 - 1፡09፡00
ማለፊያ

📌 #ፍቅር ከሰው ሳይሆን ከእግዚአብሔር የሚቀበሉት ነው። እግዚአብሔርን አብዝቶ በመጠየቅና ራስን በማዋረድ ውስጥ የሚገኝ ስጦታ ነው።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📌 የካቶሊክ ሥራ አስፈጻሚ የዲያብሎስ አሽከር የአገራችን የወቅቱ መሪ ከቫቲካኑ አዲስ ፖፕ ጋ የመጀመሪያውን ጥሪ ተቀብሎ የዲያብሎስን ባርኮት ለመቀበል የሄደበት ጉዞ!

▻ ለበለጠ ማብራሪያ https://www.tg-me.com/Ewnet1Nat/15967 ይሄንን መግለጫ ደጋግመው ያዳምጡ!
በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ  ቅዱስ ገዳም ቁጥራቸው ያልታወቀ በዋሻ የሚኖሩ መነኮሳት በታጣቂዎች ተገደሉ

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኘው በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የሚኖሩ መነኮሳት ሰኔ 15/ 2017 ዓ.ም. በታጣቂዎች የተገደሉ ሲሆን የተወሰኑ ታፍነው መወሰዳቸውን ገዳሙ ለማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ገልጿል።

የካቲት 2016 ዓ.ም ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት በተደጋጋሚ በገዳሙ ላይ  ተመሳሳይ ጥቃት መድረሱ የሚታወስ ነው።
ኢራን 6 ሚሳኤሎችን ኳታር ወደሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ተኮሰች
*****

ኢራን የአሜሪካን ጥቃት እንደምትበቀል ማስጠንቀቋን ተከትሎ በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ፍንዳታዎች መሰማታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ኢራን ኳታር ወደሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች 6 ሚሳኤሎችን ተኩሳለች ሲሉ የእስራኤል ባለስልጣናት ገልጸዋል።

ኳታር የአየር ክልሏን በጊዜያዊነት መዝጋቷ ከተገለጸ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ነው ከኢራን ይህን የሚሳኤል ጥቃት ያስተናገደችው።

በቢታንያ ሲሳይ
#EBC
እስራኤል በጋዛ በፈፀመችው ጥቃት ቢያንስ 43 ፍልስጤማውያንን ተገደሉ

በጋዛ በተስፋፋው ረሃብ ውስጥ ቢያንስ 43 አጥብቀው የምግብ እርዳታ የሚሹ ፍልስጤማውያን በማእከላዊ የጋዋ ግዛት አካባቢ በተፈጸመ ጥቃት ተገድለዋል ሲል የአልጀዚራ የእውነታ ማረጋገጫ ክፍል ሳናድ ዘግቧል።

እንደ ዘገባው ከሆነ ተጎጂዎቹ የተገደሉት ከዋዲ ጋዛ በስተደቡብ በሚገኘው የሳላህ አል-ዲን ጎዳና ላይ ምግብ በመጠባበቅ ላይ በነበሩበት ወቅት ነው።

በሳናድ የተገኘ የምስል ቅጅ የተጎጂዎች አስከሬን በጋዛ ናስር ሜዲካል ኮምፕሌክስ እና በአል-አውዳ ሆስፒታል ተከማችቶ ያሳያል። በእስራኤል እና በአሜሪካ የሚደገፈው የጋዛ የሰብዓዊ ፋውንዴሽን እ.ኤ.አ ግንቦት 27 ቀን እርዳታ ማከፋፈሉን ከጀመረ ወዲህ እስራኤል የእርዳታ ማዕከላት አቅራቢያ ፍልስጤማውያን ላይ ባደረሰችው ጥቃት ከ400 በላይ ሰዎችን ሲገደሉ 1,000 የሚያህሉ ቆስለዋልም ተብሏል።
በሱዳን ሆስፒታል በተፈጸመ 'አሰቃቂ ጥቃት' በርካታ ህጻናት መገደላቸውን ዶ/ር ቴድሮስ ገለጹ።

በሱዳን ሆስፒታል በተፈጸመ 'አሰቃቂ ጥቃት በአብዛኛው ህጻናትና የጤና ባለሙያዎች የሆኑ 40 ሰዎች መገደላቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገብረየሱስ ገለጹ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በሰሜን ወሎ ዞን በሀብሩ ወረዳ ውስጥ  በምትገኘው የቁጥር 04 ቀበሌ ልዮ ቦታው ወይራባና ጎረጨፌ የሚገኘው ጥብቅ ደን ባልታወቀ ምክንያት በተነሳ እሳት ደኑ እየወደመ ይገኛል።
📌 ስማችሁን ሳይሆን ሥራችሁን ተመልከቱ!!

❝ራሳችንን እናስፋፋለን፡ እኛ ብቻ እንገዛለን እንነግሣለን የእግዚአብሔር እውነት የሆነውን ሁሉ በቅርቡ እናጠፋለን❞ የምትሉ እነ አሰፋ ብትመከሩ ብትመለሱ ከእውነት ጋር ብትቆሙ ትጠቀማላችሁ። በተለይ የነጻነት ታጋዮች ነን የምትሉ ልብ ግዙ ተመከሩ ተብሏል። አበቃ!

⛳️

1፤ አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል።

2፤ እነሆ፥ ጠላቶችህ ጮኽዋልና፥ የሚጠሉህም ራሳቸውን አንሥተዋልና።

3፤ ሕዝብህን በምክር ሸነገሉአቸው፥ በቅዱሳንህም ላይ ተማከሩ።

4፤ ኑ ከሕዝብ እናጥፋቸው፥ ደግሞም የእስራኤል ስም አይታሰብ አሉ።

5፤ አንድ ሆነው በአንተ ላይ ተማከሩ፤ በአንተ ላይ ቃል ኪዳን አደረጉ፤

6፤ የኤዶማውያን ድንኳኖች እስማኤላውያንም፥ ሞዓብም አጋራውያንም፥

7፤ ጌባል አሞንም አማሌቅም፥ ፍልስጥኤማውያንም ከጢሮስ ሰዎች ጋር፤

8፤ አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፥ ለሎጥ ልጆችም ረዳት ሆኑአቸው።

9፤ እንደ ምድያምና እንደ ሲሣራ፥ በቂሶንም ወንዝ እንደ ኢያቢስ አድርግባቸው።

10፤ በዓይንዶር ጠፉ፥ እንደ ምድርም ጕድፍ ሆኑ።

11፤ አለቆቻቸውን እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፥ ታላላቆቻቸውንም እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው።

12፤ የእግዚአብሔርን መሠዊያ እንወርሳለን የሚሉትን።

13፤ አምላኬ ሆይ፥ እንደ ትቢያ በነፋስ ፊትም እንደ ገለባ አድርጋቸው።

14፤ እሳት ዱርን እንደሚያቃጥል፥ ነበልባልም ተራሮች እንደሚያነድድ፥

15፤ እንዲሁ በቍጣህ አሳድዳቸው፥ በመቅሠፍትህም አስደንግጣቸው።

16፤ ፊታቸውን እፍረት ሙላው፥ አቤቱ፥ ስምህንም ይፈልጋሉ።

17፤ ይፈሩ ለዘላለሙም ይታወኩ፤ ይጐስቍሉ ይጥፉም።

18፤ ስምህም እግዚአብሔር እንደ ሆነ፥ በምድር ሁሉ ላይም አንተ ብቻ ልዑል እንደ ሆንህ ይወቁ።

 
መዝሙር ዘዳዊት ፹፫
🟢🟡🔴
ሰኔ 20 | የመጀመርያዋ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን #በእመቤታችን ስም ታነፀች።

ይህችም በኬልቄዶን አውራጃ በቂሣርያ አገር የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ያለ ዕንጨት ያለ ጭቃና ውኃ በሦስት ደንጊያዎች በተወደደ ልጅዋ እጅ የታነፀችበት ነው።

ይኽም በዓል ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው። ‹‹ሕንጸተ ቤተ ክርስቲያን›› ይባላል።

አናጺውም እራሱ ባለቤቱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው።

ሐዋርያት በስብከትና በጥምቀት ወደ ክርስትና ያመጧቸው ምእመናን ስለበዙ ለጸሎትና ለቍርባን የሚሆናቸውን ቦታ ሻቱ። ሕንጻንም ሊሠሩ ሱባኤ ገቡ።

ጌታችንም በታላቅ ግርማ መለኮት ተገልጦ ወደ ምሥራቅ ወሰዳቸው። በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ። ጌታችንም ሦስቱን ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው።

ድንጋዮቹም እንደ ሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ። ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሠጣቸው። እነርሱም እሳት እንዳየው ሰም ከእጃቸው እየለመለሙ (እየተሳቡ) ቁመቱን 24 ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ሠርተውታል።

ይህም የሆነው እመቤታችን ካረገች ከ4ኛ ዓመቱ በ52 ዓ.ም ነው። (ታሪኩ ወደ ሰኔ 21 ይቀጥላል)

          #_እንኳን_አደረሳችሁ
         ▸
T.me/Ewnet1Nat
በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ( ባሕረ ነጋሽ) መካከል ያለው ወታደራዊ ፍጥጫ እየተባባሰ መጥቷል።
እስራኤል በደቡባዊው ሊባኖስ ድንገተኛ የቦንብ ጥቃት ሰነዘረች። እስራኤል ጥቃቱን የፈፀመችው ከሊባኖስ ጋር የተገባውን የተኩስ አቁም ስምምነት በመጣስ ነው።

ተኩስ አቁሙ ፈረሰ

እስራኤል ዛሬ በደቡባዊው ሊባኖስ ድንገተኛ የቦንብ ጥቃት መሠንዘሯ ተዘግቧል።

እስራኤል ጥቃቱን የፈፀመችው ከሊባኖስ ጋር የተገባውን የተኩስ አቁም ስምምነት በመጣስ ነው።በዚህም ከዚህ በፊት የፈፀሙት ተኩስ አቁም ፈርሰል።
2025/07/04 05:43:24
Back to Top
HTML Embed Code: