Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ነጭ ነጯን ውሸት - ከዘመድኩን"

የውሸት አባት፣ ጸላዔ ሠናያት ዲያብሎስ የእግዚአብሔርን እውነት ለመገዳደር የማይፈነቅለው ጉድ የለም። በየትኛውም ክርስቲያናዊ ሕይወት ፈተናው የሚስተዋል ቢሆንም በኢትዮጵያ ትንሣኤ ዙሪያ ግን ከሚያደርገው ዘመቻ ይህንን መጥቀስ ይቻላል፦

1. ቢቻል ሙሉ በሙሉ ማስካድ፦ እውነቱን በሙሉ ውሸት ማስባል
▸ ይሄ ደረጃ የእውቀት ክፍተትን እና ሥጋዊ መለኪያን በመጠቀም ሰዉን ዝግ ልቡና እንዲኖረው የሚያደርግ ነው።

2. ካልሆነ እውነቱን የሚመስል ግን እውነት ያልሆነ እንቅስቃሴ ማስጀመር፦ ጥቂት መረዳትና ልቦና ያላቸው በመጀመርያው ስለማይወድቁ፥ ልክ ስልክ "ሃይ ኮፒ" ተብሎ ሐሰተኛውን ከትክክለኛው ለመለየት በሚያዳግት መልኩ እንደሚሠራው ስለ ትንሣኤው የሚያወሩ ሐሰተኞችን መፈልፈል ነው።

3. "መምህር፣ አገልጋይ፣ አባት" ተብዬዎችን በመጠቀም የተስፋው ቃል ላይ ጥርጣሬና ጥላቻ መዝራት

▸ ከላይ ያሉት ሁለቱ ካልተሳኩ ከቤ/ክ በላይ ክብርና ዝናን የተቆጣጠሩ ሰዎችን በመጠቀም ሰውን አምላኪውን ወገን ማሸፈት ነው።

ሀገር ውስጥ ያሉ 'መምህራን' ጭምር "ትንቢት አትስሙ፣ መልእክት አትቀበሉ" የሚሉን ሲሆኑ መልሰው ራሳቸው "ከአባቶች የተላከ መልእክት ነው" ብለው ላኪውን እንዳንጠይቅ ሲያደርጉ ታዝበናል።

"የአባቶች ትንቢት መልእክቱ ንስሐ ግቡ ብቻ ነው" ያሉን መምህራን "የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃንም እኮ ከዚህ ሌላ አላለም" ሲባሉ በነሱ በኩል ባለመተላለፉ የከፋቸውም አይጠፉም።

ነፍስን ከማዳን እና ባዶ ዝናን ከማዳን የቱ ዋጋ አለው?

📌 ከ"በረኸኞቹ" የተላከ መልእክት ሲል የነበረው ማነው?

📌 "በ2015 ዓ.ም ዘመነ ሉቃስ ንጉሡ ይመጣል" ሲለን የነበረውስ ማነው?

📌 "ታቦተ ኢየሱስ ባለበት ቦታ ትተርፋላችሁ" ያለንስ?

× | ግንቦት 2016 ዓ.ም
  www.tg-me.com/Ewnet1Nat
Audio
የግንቦት 9 ስንክሳር የቅድስት እሌኒ እረፍት .
Audio
ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ዘዓርብ.
🟢 🟡 🔴
ግንቦት 11 | #_ቅዱስ_ያሬድ ተሰወረ።

ቅዱስ ያሬድ የተወለደው በ505 ዓ/ም አክሱም አካባቢ ሲሆን እናቱ ክርስቲና (ታኡክልያ) አባቱ ደግሞ ይስሐቅ (አብድዩ) ይባላሉ።

ሊቁ በሕጻንነቱ ትምህርት አልገባው ብሎ ይቸገር ነበር። ትምህርት እንቢ ያለው ሰነፍ ስለ ነበር አይደለም። በጥበበ እግዚአብሔር እንጂ።

ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር። ልቡናው ደግሞ በእመቤታችንና በልጇ ፍቅር የታሠረ ነበር። አንድ ቀን ግን መምህሩ የነገሩት ቀለም አልያዝህ አለው። ሲፈትኑትም ባለመመለሱ ተገረፈ።

ዱላው በጣም ስለ ተሰማው ቅዱሱ ከመምህሩ ኮብልሎ ማይ ኪራሕ አካባቢ ሲደርስ ደክሞት አርፎ እግዚአብሔር ትጋትንና ተስፋ አለመቁረጥን ከትል አስተማረው።

ከዚህ በኋላ ቅዱስ ያሬድ ወደ መምህሩ ተመልሶ ይቅርታ ጠይቆ ትምህርት ጀመረ። ሊቁም ትጋትንና ጸሎትን ከሰጊድ ጋር አበዛ።

ያን ጊዜ ሰማያዊ ዜማ አልተገለጠም ነበርና በጸሎት ላይ ሳለ ተደሞ መጣበት። ሦስት መላእክት በሦስት ወፎች አምሳል መጥተው አነጋገሩት። ድንገትም ነጥቀው ወደ ሰማያት አደረሱት።

ሊቁ በሰማያት ልዩ ምሥጢር፣ ልዩ ምስጋናና ልዩ ዜማን አዳመጠ። ይህንን ምስጋና ብዙ ቅዱሳን ቢሰሙትም ቅዱስ ያሬድ ግን ይዞት እንዲወርድ ተፈቀደለት።

ሊቁ ወደ ምድር ተመልሶ በታላቅ ተመስጦ አክሱም ጽዮን ውስጥ በሃሌታ አመሰገነ። ቅዱስ ያሬድ ለተወሰነ ጊዜ በአክሱምና ደብረ ዳሞ ሲያገለግል ቆይቶ ከመሬት ክንድ ከስንዝር ከፍ ብሎ ለእመቤታችን አንቀጸ ብርሃንን ደርሶላት ከሃገሩ ወጣ።

በ576 ዓ/ም በተወለደ በ71 ዓመቱ በዚህች ቀን ተሰውሯል።

የቅዱሱ ጸሎትና በረከት ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይጠብቅልን።       
#_እንኳን_አደረሳችሁ
            ▸ www.tg-me.com/Ewnet1Nat
#ሰላም_ለአጽፋረ_እግርከ
ከዋክብተ ጽባሕ ጽዱላት፥
እስከ ምዕራብ እግር አብርሃ
መልዕልተ አጻብዕ ሰማያት፥
#ከመ_ተሰወርከ_ያሬድ
እምቅድመ ዐይኑ ለሞት፥
አድኅነነ በጸሎትከ እምዕለት እኪት፥
ወባልሓነ እምኵሉ መንሱት።

❮ ትርጉም ❯ #የሚያበሩ_የንጋት_ከዋክብት_ለኾኑ #የእግርኽ_ጥፍሮች_ሰላምታ_ይገባል

ጣቶችኽ ሰማያት ላይ እስከ ምዕራብ ድረስ ይበራሉና፤ #ቅዱስ_ያሬድ ከሞት ፊት እንደተሰወርኽ በጸሎትኽ ከክፉ ቀን አድነን፤ ከፈተናም ሁሉ ሰውረን።

#መልክዐ_ቅዱስ_ያሬድ
. 🟢 🟡 🔴
ግንቦት 12 | በዚህች ቀን፦

◈1◈ በኢየሩሳሌም ሀገር ወደሚኖር ነቢይ ዕንባቆም የመላእክት አለቃ #_ቅዱስ_ሚካኤልን እግዚአብሔር ላከው።

እርሱም የማሳውን እህሎች ለሚያጭዱ ምሳ ሊወስድ ወዶ ተሸክሞ ሳለ ቅዱስ ሚካኤልም ዕንባቆምን ምግብን እንደተሸከመ በአናቱ ጠጉር ይዞ ወደ ባቢሎንም አገር አደረሰው። ዳንኤል ወደ አለበት የአንበሶች ጒድጓድ አስገባው።

◈2◈ የዓለሙ ሁሉ መምህር የሆነ የከበረ አባት #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ አረፈ። ድሃን በመበደሏ ንግሥት አውዶክስያን ቢያወግዛት ወደ ግዞት ሰድዳው በስደት አረፈ።

◈3◈ የኢትዮጵያ ብርሃኗ ሐዲስ ሐዋርያ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፍልሠተ ዐፅማቸው ተከናወነ። ይህም የተደረገው ጻድቁ ካረፉ ከ57
ዓመታት በኋላ ነው። በዕለቱም ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተፈጽመዋል።

◈4◈ #ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ ቃል ኪዳን የተቀበለችበት ነው። በዚህች ቀን ስሟን ለጠራና መታሠቢያዋን ላደረገ የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች።

◈5◈ በኢየሩሳሌም አገር በጎልጎታ ላይ ከፀሐይ በልጦ በሚበራ ብርሃን #የከበረ_መስቀል መገለጥ ሆነ። በዚህም ቀን በ6 - 9 ሰዓት ፀሐይን እስኪሸፍናት ድረስ በምድር ላይ ያበራበት የተአምሩ በዓል ነው።

◈6◈ የመላልዔል ልጅ የማቱሳላ አባት #ቅዱስ_ያሬድ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

#_እንኳን_አደረሳችሁ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ነጭ ነጯን ውሸት - ከዘመድኩን"

የውሸት አባት፣ ጸላዔ ሠናያት ዲያብሎስ የእግዚአብሔርን እውነት ለመገዳደር የማይፈነቅለው ጉድ የለም። በየትኛውም ክርስቲያናዊ ሕይወት ፈተናው የሚስተዋል ቢሆንም በኢትዮጵያ ትንሣኤ ዙሪያ ግን ከሚያደርገው ዘመቻ ይህንን መጥቀስ ይቻላል፦

1. ቢቻል ሙሉ በሙሉ ማስካድ፦ እውነቱን በሙሉ ውሸት ማስባል
▸ ይሄ ደረጃ የእውቀት ክፍተትን እና ሥጋዊ መለኪያን በመጠቀም ሰዉን ዝግ ልቡና እንዲኖረው የሚያደርግ ነው።

2. ካልሆነ እውነቱን የሚመስል ግን እውነት ያልሆነ እንቅስቃሴ ማስጀመር፦ ጥቂት መረዳትና ልቦና ያላቸው በመጀመርያው ስለማይወድቁ፥ ልክ ስልክ "ሃይ ኮፒ" ተብሎ ሐሰተኛውን ከትክክለኛው ለመለየት በሚያዳግት መልኩ እንደሚሠራው ስለ ትንሣኤው የሚያወሩ ሐሰተኞችን መፈልፈል ነው።

3. "መምህር፣ አገልጋይ፣ አባት" ተብዬዎችን በመጠቀም የተስፋው ቃል ላይ ጥርጣሬና ጥላቻ መዝራት

▸ ከላይ ያሉት ሁለቱ ካልተሳኩ ከቤ/ክ በላይ ክብርና ዝናን የተቆጣጠሩ ሰዎችን በመጠቀም ሰውን አምላኪውን ወገን ማሸፈት ነው።

ሀገር ውስጥ ያሉ 'መምህራን' ጭምር "ትንቢት አትስሙ፣ መልእክት አትቀበሉ" የሚሉን ሲሆኑ መልሰው ራሳቸው "ከአባቶች የተላከ መልእክት ነው" ብለው ላኪውን እንዳንጠይቅ ሲያደርጉ ታዝበናል።

"የአባቶች ትንቢት መልእክቱ ንስሐ ግቡ ብቻ ነው" ያሉን መምህራን "የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃንም እኮ ከዚህ ሌላ አላለም" ሲባሉ በነሱ በኩል ባለመተላለፉ የከፋቸውም አይጠፉም።

ነፍስን ከማዳን እና ባዶ ዝናን ከማዳን የቱ ዋጋ አለው?

📌 ከ"በረኸኞቹ" የተላከ መልእክት ሲል የነበረው ማነው?

📌 "በ2015 ዓ.ም ዘመነ ሉቃስ ንጉሡ ይመጣል" ሲለን የነበረውስ ማነው?

📌 "ታቦተ ኢየሱስ ባለበት ቦታ ትተርፋላችሁ" ያለንስ?

× | ግንቦት 2016 ዓ.ም
  www.tg-me.com/Ewnet1Nat
እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፦
   ፩ኛ. ትዕቢተኛ ዓይን፥
   ፪ኛ. ሐሰተኛ ምላስ፥
   ፫ኛ. ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
   ፬ኛ. ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥
   ፭ኛ. ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
   ፮ኛ. በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር
   ፯ኛ. በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።
~× ምሳሌ 6÷16-19 ×~
▰ ▰ ▰
"ነጭ ነጯን ውሸት" መናገርን ሳንቲም መልቀሚያው ያደረገው ዘመድኩን በቀለ ከዓመት በፊት ደብረ ኤልያስ መልክዐ ሥላሴ ገዳም ላይ ከጥፋት ሰዎች ጋር መናጆ ሆኖ ንጹሐን እንዲፈጁ ቅስቀሳ እንደሠራ ይታወቃል።
👇 👇
https://www.tg-me.com/Ewnet1Nat/9857

በጉዳዩ ቤተ ክህነቱም ዝም፣ ቤተ ሕዝቡም ዝም ሆነ እንጂ¡

እናም ይሄ "የኢትዮጵያ ትንሣኤ አብሣሪ ነኝ" የሚለን ሰው፥ አሁን ደሞ በጥቅምት 2013 ዓ.ም በኃይለኛው ሲያራግበው የነበረውን የ"ንጉሱ 2015 ይመጣል"ን ማደናገሪያውን አላልኩም እያለ ነው።

እነዚህን አሉባልታዎች በሚዲያ ሲያሰራጩ የነበሩ ሰዎችን መልሶ የሚጠይቅ አንድ ደፋር እውነተኛ ክርስቲያን ምነው ጠፋ?

የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃንን ባልዋለበት ማንሳት፣ ባላለው ነገር ማማት አንበሳን በ'ቆሎ' እንደ መጠርጠር ማለት ነው!

በጨለማ የተጓዝንበት ዘመን ይበቃል።
ወደ እውነቱ ብቻ አማትሩ! ልብ ግዙ!
እየተማራችሁ እለፉ!

❲ውድ ወገኖቻችን አስረጂ ይሆኑ ዘንድ ከላይ ጠቃሚ ነገሮች አያይዘናል። እየተመለሳችሁ በደንብ ተመልከቷቸው። ከታችም ስለ አቡነ ዘወንጌል እና ተያያዥ ጉዳዮችን ከጥሩ ምንጭ ማስረጃን ታገኙበታላችሁ❳
የአምኃ_ኢየሱስ_ገብረ_ዮሐንስ_ለሰባተኛ_ጊዜ_ትምህርታዊ_የሆነ_የጽሑፍ_መልእክት_ነው።.pdf
2.4 MB
📌የአምኃ ኢየሱስ ገብረ-ዮሐንስ ለሰባተኛ ጊዜ ትምህርታዊ የሆነ የጽሑፍ መልእክት ነው‼️ PDF
#Share አድርጉት!
#7 የአባ አምኃ ኢየሱስ ገብረ ዮሐንስ ለሰባተኛ ጊዜ ትምህርታዊ የሆነ የጽሑፍ መልእክት ነው
አባ አምኃ ኢየሱስ ገብረ ዮሐንስ
ስለ ዘመድኩን በቀለ እና አስገራሚው የአባ አምኃ ኢየሱስ መልእክት

❗️ የአባ አምኃ ኢየሱስ ገብረ ዮሐንስ ለሰባተኛ ጊዜ ትምህርታዊ የሆነ የጽሑፍ መልእክት ነው።

× ሚያዝያ 27 2013 ዓ.ም ተላልፎ በድምፅ ንባብ የቀረበ ×
Audio
የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክትን ያገኘነው ከአባ ዘወንጌል ነው

የወንድሞቻችን ገብረ ሥላሴ እና ሀብተ ማርያም እጅግ ድንቅ ምስክርነት እና ትምህርታዊ አስተያየት

ለኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች በሙሉ ። አዳምጡት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ

× ከሁለት ዓመት በፊት 15/8/2014
የተለቀቀ ×
🟢 🟡 🔴
ግንቦት 14 | ሙሽራው #_ቅዱስ_ገብረክርስቶስ ከጫጉላ ቤቱ ወጥቶ የመነነበት ዕለት ነው፡፡

ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ ወላጅ አባቱ የቍስጥንጥንያው ንጉሥ ቴዎዶስዮስና እናቱ ንግሥት መርኬዛ በስለት ያገኙት ብቸኛ ልጃቸው ነው።

የአባቱን ንግሥና እንዲወረስ የሮሙን ንጉሥ ሴት ልጅ አጋቡት፡፡ እርሱ ግን ዓለምን ፍጹም በመናቅ የክርስቶስን መስቀል ለመሸከም የተዘጋጀ ነበርና የሠርጉ ዕለት ሌሊት የእርሱንም ሆነ የሙሽይቱን ድንግልና እንደጠበቀ ከጫጉላ ቤት ወጥቶ በመርከብ ተሳፍሮ ሩቅ ሀገር ሔደ።

ከነዳያን ጋር ተደባልቆ በመለመን ለምኖ ያገኘውንም ለሌሎች እየመጸወተ በጾም በጸሎት ተጠምዶ 15 ዓመት ኖረ፡፡

ቅድስናው ቢታወቅበት ወደሌላ ሀገር በመርከብ ሲጓዝ ፈቃደ እግዚአብሔር መርከቢቱን ያለ አቅጣጫዋ ወስዶ አባቱ ደጅ አደረሰው፡፡

በአባቱና በንጉሡ ደጅ የኔ ቢጤ ለማኝ ሆኖ ለአባቱ ውሾች የሚሰጠውን ፍርፋሪ እየተመገበ አሁንም 15 ዓመት ሙሉ በትዕግስት ተቀመጠ፡፡

የአባቱ አሽከሮች እንኳን እጣቢና ቆሻሻውን ሁሉ እየደፉበት ሲያሠቃዩት የአባቱ ውሾች ግን የእግሩን ቁስል ይልሱለት ነበር፡፡ በመናቅ ስለ ጽድቅ ተሰዶ እየለመነ ያገኘውን እየመጸወተ በጾም በጸሎት እየተጋደለ 30 ዓመት ሙሉ ተቀመጠ፡፡

በጣም የሚገርመው ደግሞ መጀመሪያ ላይ ወላጆቹ ሚስት አድርገው ያመጡለት የሮሙ ንጉሥ ሴት ልጅ ለባሏ ታማኝ ሆና 30 ዓመት ሙሉ በእናት አባቱ ቤት በትዕግስት ስትጠብቀው መኖሯ ነው፡፡

አምላከ ገብረ ክርስቶስ በዚህ በመከራና በፈተና ዘመን ጽናቱን ያድለን።
www.tg-me.com/Ewnet1Nat
🟢 🟡 🔴
ግንቦት 15 | #ቅዱስ_ናትናኤል_ሐዋርያ ዐረፈ፨

ለሐዋርያው ወላጆቹ ያወጡለት ስም ስምዖን ሲሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ናትናኤል ብሎታል። በባልንጀሮቹ ሐዋርያት ደግሞ የቃናው ስምዖን (ገሊላ ቃና አካባቢ ስላደገ) አንዳንዴም ቀናተኛው ስምዖን ይሉት ነበር። ምሑረ ኦሪት ነበርና ዘወትር ለሕግ ይቀና ነበር።

ቅዱሱ ሐዋርያ የተወለደው ከእሥራኤላውያን ወላጆቹ ጌታችን በተወለደበት ዘመን አካባቢ ነው። ይህ በምን ይታወቃል ቢሉ እርሱ ሕጻን እያለ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ እርሱ ግን በእግዚአብሔር ጥበብ ተርፏል። እናቱ በቅርጫት ውስጥ አድርጋ የበለስ ዛፍ ላይ አስቀምጣው ተደብቃ ታጠባው ነበር።

በገሊላ ቃና ሰርግ የደገሰው ዶኪማስ የቅዱስ ናትናኤል የአጎት ልጅ ነው። ጌታና ደቀ መዛሙርቱን ዶኪማስ የጠራበት አንዱ ምክንያትም ይኼው ነው።

ቅዱስ ናትናኤል ኦሪትን ከገማልያል ተምሮ፣ ከበለስ ቁጭ ብሎ ይተክዝ ነበር። "መሲሕ ምነው ቀረህ" እያለም ይተክዝ ነበር። ማዕምረ ኅቡዓት አምላካችን ክርስቶስ ይህንን አውቆ በፊልጶስ አማካኝነት ጠርቶታል።

ፊሊጶስ ናትናኤልን ጠርቶት ወደ ጌታችን ካመጣው በኋላ ናትናኤል ጌታችንን ‹‹ወዴት ታውቀኛለህ?›› ሲለው ጌታችንም ‹‹ፊሊጶስ ሳይጠራህ ከበለስ ሥር ሳለህ ዐውቅሃለሁ›› በማለት ከሕፃንነቱ ጀምሮ የጠበቀው አምላኩ እርሱ መሆኑን ነግሮታል።

ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል በባቢሎን፣ በሶርያ፣ በግብፅና በኑቢያ እየተዘዋወረ ወንጌልን ሰብኳል፡፡ ብዙውን የአገልግሎት ጊዜውን ያሳለፈው በሰሜን አፍሪቃ ነው፡፡

ከዚህም በኋላ ከሀድያን ይዘው በዕንጨት ላይ ሰቀሉት። በዚህም ምስክርነቱን ፈጽመ፤ መንግሥትን ወረሰ።

በገድለ ሐዋርያት ላይ ቅዱሱ ሰማዕት የሆነው በ150 ዓመቱ ነው ይላል። ይህም ከሐዋርያት አባቶች በመጨረሻ ያረፈው እርሱ ነው ያሰኛል።

🌿
ከኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃናዊ_መንግስት_በድምጽ_ሚያዝያ_07_2016_ዓ_ም_የተለቀቀ_መግለጫ.pdf
258.4 KB
ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግስት በድምጽ ሚያዝያ 07 2016 ዓ.ም የተለቀቀ መግለጫ Pdf
2024/05/22 23:37:05
Back to Top
HTML Embed Code: