Telegram Web Link
Forwarded from Hawassa University
ኮሌጁ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ስልጠና ሰጠ።
*//*
ግንቦት 2 ቀን 2017 ዓ/ም
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች እራሳቸውን በአዕምሮና በአካል ብቁ በማድረግ ከጥገኝነት አስተሳሰብና ፍላጎት ተላቀው ለራሳቸውና ለማህበረሰቡ ጠቃሚ ዜጋ መሆን የሚያስችላቸውን የሕይወት ስልጠና ሰጥቷል።

የኮሌጁ አካ/ጉ/ተባባሪ ዲን ዶ/ር ወንዱ መሰለ "ከጥገኝነት ነጻ ሆኖ የመኖር ክህሎትን ማሳደግ" በሚል መሪ ቃል የተሰጠውን ስልጠና ሲያስጀምሩ እንደተናገሩት ስልጠናው በአካል ጉዳተኞች በራሳቸውና በማህበረሰቡ ዘንድ የሚታየውን የ'አንችልም' እና 'አይችሉም' አስተሳሰብ በማስቀረት አካል ጉዳተኝነት ያለመቻል ምልክት አለመሆኑን የሚያረጋግጡ እውቀትና ክህሎቶችን የሚገበዩበት መሆኑን ገልጸዋል። ዶ/ር ወንዱ አክለውም ጥገኝነት በሂደት እያደገ የሚሄድና የራስን አቅም የሚያጠፋ በመሆኑ አስተሳሰቡን ከመሰረቱ መቀየር እንደሚገባና በማህበረሰቡ ላይም የአመለካከት ለውጥ የሚያመጡ ስራዎች በቀጣይነት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የሀ/ዩ ሴቶች ማህ/አ/ትግ/ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ምህረት ገነነ በበኩላቸው አካል ጉዳተኝነት በማንም ሰው ላይ በየትኛውም ጊዜ ሊከሰት የሚችል መሆኑን በመረዳት አካል ጉዳተኞች ራሳቸውን ለመቻል የሚያደርጉትን ጥረት መደገፍ ይገባል ብለዋል።

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

በዚህ ይከታተሉን:-
***
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et
Telegram: https://www.tg-me.com/HUCommunicationsoffice
👍21
Forwarded from HAYLEAB TEREFE(Mickey)
🔥ልዩ የጥበብ ድግስ 🔥
መቅረዝ የኪነ-ጥበብ አፍቃርያን ሕብረት
መቅረዝ ግንቦት 1, 2017 በሐዋሳ ዩንቨርሲቲ ዋና ግቢ አፍሪካ ሕብረት አዳራሽ ለሲሚስተሩ መዝግያ ይሆን ዘንድ ውብ የጥበብ ድግስ አካሂዷል። በድግሱም ይህ ቀራቸው ከማይባሉ ምርጥ አምደ ልዩ ልዩ የሆኑ የስነ-ፅሁፍ ስራዎች፤ግጥሞች፣ ጥዑም ዜማዎች፣ጭውውት እንዲሁም በውብ ውዝዋዜና አዝናኝ ጨዋታዎችን አካቶ አዝናኝና አስተማሪ ያላቸውን ስራዎቹን ለውድ ታዳምያን በደመቀ መልኩ አድርሷል።

በእለቱም የግቢ ተማሪዎች እና የግቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል።
በቀጣይም መቅረዝ እነዚህንና መሰል የጥበብ ስራዎችን መስራትና ጀባ ማለቱን ይቀጥላል
ታድያ በዚህ ትልቅ የጥበብ ቤት የትወና፣ የስነ-ፅሁፍ፣ የድምፅ፣ የውዝዋዜ እንዲሁም ሌሎች የጥበብ አቅሞን ለማሳደግና ፍላጎቶን እውን ማረግ ከፈለጉ ከመቅረዝ ቤት ጎራ ይበሉ እውነተኛና ልዩ ቤተሰባዊነትም ያትርፉ።

💬ለበለጠ መረጃ እንዲሁም አዲስ መቀላቀል ለምትፈልጉ በመቅረዝ
🎤በሙዚቃ🎤
🎭በትወና 🎭
🖋️በስነ-ፅሁፍ እና 🖋️
🕺በውዝዋዜ 💃አዲስ መሳተፍ ለምትፈልጉ ተማሪዎች ከታች በተቀመጡት ልታገኙን ትችላላችሁ👇


☎️0989058688 ☎️0904417552
☎️0929042323 ☎️0934700730

✉️TELEGRAM # https://www.tg-me.com/mekerezeactingstudents
📷INSTAGRAM # https://www.instagram.com/mekrez90/profilecard/?igsh=amVmdm5rcW55ejds

መልካም ፈተና ፤ መልካም እረፍት እየተመኘን
የከርሞው ሰው ይበለን!!!
መኖር መሆን ስኬት
#መቅረዝ!!!
# ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ
👍41
ለዛሬ ማታ ቀጠሮ ይዘናል!

#JCSA ONLINE TALKSHOW

በዚህ ሳምንት በJCSA የበይነመረብ እልፍኝ #ከአሰላ _ፋና_ኤፍኤም እስከ #ፋና- ሚዲያ- ኮርፖሬሽን(#FMC) የዘለቀ በሪፖርተርነት ፣በመዝናኛ ዝግጅት እንዲሁም በዋነኛነት የምርመራ ዘገባዎችን በመስራት  ለበርካታ ዓመታት በጋዜጠኝነት ሙያ የቆየ እና የካበተ ልምድ ያለው  የአሁኑ የፋና ምርመራ ክፍል ዋና አዘጋጅ #ጋዜጠኛ አፈወርቅ _እያዩ የዛሬው የJCSA የበይነመረብ ልምድ ልውውጥ (online talkshow) እንግዳ ሆኖ ይቀርባል ።

#_ዛሬ እሁድ(03/09/17) እንደተለመደው #ከምሽቱ_2:00 ሰዓት ጀምሮ በJCSA የቴሌግራም ግሩፕ ይጠብቁን👇👇

https://www.tg-me.com/HU_JCSA_Group

🎤አቅራቢ፦#ፍርዶስ ሙሃመድ (የ3ተኛ አመት የጋዜጠኝነት እና ስነ-ተግባቦት ተማሪ)

📌መርሐግብሩ የሚከወነው በጎግል ሚት(googlemeet) ሲሆን የውይይቱ ሰዓት ሲቃረብ የመወያያ ሊንኩን የምናጋራችሁ ይሆናል።

📌 #እንዳያመልጣችሁ

እዉነቱን በኃላፊነትና በሚዛናዊነት እንነግራችኋለን!!

#HU_JCSA
1
እንኳን ደስ አለን

#rvc መጻሕፍት ዳሰሳ ክፍል ዝግጅት ከባለ እንጨት ግድግዳ ቤት ወጣ ብሎ በኢትዮጵያ ራዲዮ ሊደመጥ ነው።

ከዛሬ(እሁድ 03/09/17)ከቀን 7:30 ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ሳምንታት በዚሁ ቀን እና ሰዓት ይጠብቁን።

📌 ዛሬ(እሁድ 03/09/17) 7:30 ላይ

ዝግጅቱን ለማድመጥ ከታች የተቀመጠውን ሊንክ ይጠቀሙ👇👇👇👇

Listen to EBC-NATIONAL RADIO | Zeno.FM
https://zeno.fm/radio/ebc-ethiopia-radio/

#ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ
#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ
@RvcClub
@RvcClub
2👏1
‼️ IMPORTANT UPDATE – PUBLIC LECTURE REGISTRATION ‼️

We need your PHONE NUMBER to confirm your spot!
Many of you registered already — thank you!
But the first form missed the phone number and email field, so we can't reach out to confirm participation or send certificates.

PLEASE FILL THIS NEW FORM NOW to secure your seat:
[NEW REGISTRATION LINK]
(Only those on this new list will be contacted.)
__

🎤 Hawassa University’s FIRST-EVER Public Lecture on Climate Justice!

With Certification | Limited Spots | Urgent Re-Registration.

In proud collaboration with
UNA Ethiopia – HU Chapter | Eco Justice Ethiopia | Enfluencers

Topic:
“CLIMATE JUSTICE IN ACTION:
Case Study Roles in the Global Plastics Agreement”


Speaker:
JODAHI PETROS

Research & Policy Director, Enfluencers
°Ethiopia’s Youth Delegate to Africa UN Climate Conferences (COPS)
•Representative, African UN Youth Delegate Program (2022/23)


Date: Monday, May 12, 2025
Time: 2:00 PM (EAT - Afternoon)
Venue: AU


@hulsa
WHERE WE LEAD THE LEGAL CHARGE!
👍21
#አሁን

#JCSA ONLINE TALKSHOW

JCSA የበይነመረብ እልፍኝ #ከአሰላ _ፋና_ኤፍኤም እስከ #ፋና- ሚዲያ- ኮርፖሬሽን(#FMC) የዘለቀ በሪፖርተርነት ፣በመዝናኛ ዝግጅት እንዲሁም በዋነኛነት የምርመራ ዘገባዎችን በመስራት  ለበርካታ ዓመታት በጋዜጠኝነት ሙያ የቆየ እና የካበተ ልምድ ያለው  የአሁኑ የፋና ምርመራ ክፍል ምክትል ዋና አዘጋጅ #ጋዜጠኛ አፈወርቅ _እያዩ ጋር የJCSA የበይነመረብ ልምድ ልውውጥ (online talkshow)ተጀምሯል ከታች ባለው ሊንክ ተጠቅመው ይቀላቀላሉ።
👇👇👇👇👇👇👇

https://meet.google.com/wvo-vuna-jaf

#HU_JCSA
2025/09/15 18:18:17
Back to Top
HTML Embed Code: