Telegram Web Link
የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሲሚንቶ ምርት 20 ሚሊዮን ቶን ደረሰ

የማዕድን ሚኒስትሩ ሀብታሙ ተገኝ የነባር ፋብሪካዎችን ምርታማነት በማሳደግና አዳዲሶችን ወደ ሥራ በማስገባት ከሀገር ውስጥ በተጨማሪ ለጎረቤት ሀገራት ሲሚንቶ ማቅረብ የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ ነው ብለዋል።

አክለውም አራት የድንጋይ ከሰል ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችን ወደ ሥራ በማስገባት የሲሚንቶ አምራቾችን አቅም የማሳደግ ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የግብዓት አቅርቦት ምላሽ ለመስጠት በብረት፣ እምነ በረድ፣ ሲሚንቶና ሌሎች መስኮች እደገቶች እየተመዘገቡ እንደሆነም ተናግረዋል።

በድሬዳዋ ከተማ የተገነባው የፓዮኔር ሲሚንቶ ማኑፋክቸሪንግ ማስፋፊያ ፕሮጀክት በትናትናው እለት በፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔትያናሁ ሃማስ ታጋቾችን በሙሉ ለቆ ትጥቁን የሚፈታ ከሆነ ሀገራቸው በጋዛ የጀመረችውን ዘመቻ ልታቆም እንደምትችል አስታወቁ።

ኔትያናሁ ይህን ያሉት እንግሊዝ ፣ ፈረንሳይ እና ካናዳ እስራኤል በጋዛ የጀመረችውን አዲሱን ዘመቻ እንድታቆም ማስጠንቀቂያ ከሰጡ በኋላ ነው።

የብሪታንያው ጠቅላይ ሚንስትር ኪር ስታርመር ፣ የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ማርክ ካኒ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የጀመረችውን አዲሱን ዘመቻዋን ካላቆመች ማዕቀብ ሊጥሉ እንደሚችሉ በጋራ ባወጡት መግለጫ አስጠንቅዋል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔትያናሁ ለመሪዎቹ በሰጡት ምላሽ ግን "ምዕራባዉያን የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን መንገድ ተከትለው እስራኤልን ቢደግፉ ይሻላል" ብለዋል።

እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የጀመረችውን ዘመቻ ለማቆምም "ሐማስ የቀሩ ታጋቾችን ከለቀቀ፣ ትጥቁን ከፈታ እና መሪዎቹ ጋዛን ለቀው የሚሰደዱ ከሆነ ብቻ ነው " ፤ ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስራኤል ለኢራን ሲሰልሉ ነበር ያለቻቸው ሁለት ዜጎቿን በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታዉቃለች።

የእስራኤል የደህንነት ባለስልጣናት እንዳሉት ሁለቱ የ24 ዓመት ዕድሜ እንዳላቸው የተነገረላቸው እስራኤላዉያን ወጣቶች ከኢራን ተልዕኮ ተቀብለው በእስራኤል ምድር ሲሰልሉ ነበር ።

በጣቶቹ በተለይ በደቡባዊ እስራኤል በሚገኙት የክፋር አሂም ማህበረሰብ ውስጥ የእስራኤሉን የመከላከያ ሚኒስቴር እስራኤል ካትስን ስም የማጥላላት ክስም ቀርቦባቸዋል።

ወጣቶቹ ከኢራን ባለስልጣናት ተሰጣቸው በተባለው ተልዕኮ መሰረት በማህበረሰቡ ውስጥ በቀጥታ የቪዲዮ ስርጭት ሚኒስትሩን ሲሳደቡ እና ሲያጥላሉ ተደርሶባቸዋል ነው የተባለው።

በቅጥጥር ስር ስለዋሉ ወጣቶች እና ስለቀረበባት ክስ ግን ኢራን ያለችው ነገር የለም።
የአውሮፓ ህብረት በሶሪያ ላይ ተጥለው የነበሩ ማዕቀቦችን ማንሳቱን አስታወቀ

ህብረቱ ከጦርነት ማግስት ላይ የምትገኘው ሶሪያ ማገገም እንድትችል በሚል ከዚህ ቀደም የጣላቸውን ሁሉንም ኢኮኖሚያዊ ማዕቀቦች ማንሳቱን አስታውቋል።

ይህ የአውሮፓ ህብረት ውሳኔ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባሳለፍነው ሳምንት በሀገሪቱ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ እንደሚያነሱ ማስታወቃቸውን ተከትሎ የመጣ ነው ተብሏል።

የሶሪያ አዲሱ መሪ አሕመድ አልሻራ ሶሪያን ዳግም ለመገንባት ኢኮኖሚያዊ ማዕቀቦች እንዲነሱላቸው ተደጋጋሚ ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።

ማዕቀቡን ለማንሳት የተደረሰው መግባባት ከዓለም ስርዓተ የተገፉትን የሶርያን ባንኮችን ያማከለ ሊሆን እንደሚገባ የህብረቱ ዲፕሎማቶች ለሮይተርስ ተናግረዋል።

የቀድሞ የአሳድ አስተዳደር ላይ ተጥለው የነበሩ ማዕቀቦች ይቀጥላሉ ተብሏል ።

አዲሱ የሶሪያ አስተዳደርም ቃሉን ማክበር ካልቻለ እና መብት ማስከበር ካልቻለ ማዕቀቦቹ ዳግም ሊጣሉ እንደሚችሉ ተነግሯል።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፤ የጉባኤ አባላቶቹን ይፋ አድርጓል

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት አስራ አራት ዓመታት ሰባት የሃይማኖት ተቋማትን በአባልነት በማቀፍ ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
ሆኖም ጉባኤው በቅርቡ ባደረገው የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ የአባል የሃይማኖት

ተቋማቱን ፍላጎት፣ ጉባኤው የደረሰበትን የእድገት ደረጃ እና ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታውን በማገናዘብ የጉባኤውን መተዳደሪያ ደንብ ለሶስተኛ ጊዜ በማሻሻል የአሰራር እና የአደረጃጀት ማስተካከያ ማድረጉን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት፦

1ኛ/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፤

2ኛ/ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤

3ኛ/ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፤

4ኛ/ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል እና

5ኛ/ የኢትዮጵያ የሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን የጉባኤው አባል እንዲሆኑ

ማድረጉን የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አስታውቋል።
የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ የትግራይ ክልልን ጎበኙ

የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ዛሬ ወደ ትግራይ ክልል አቅንተው ከተለያዩ የክልሉ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል። በአምባሳደሩ ጉብኝት ወቅት የጸጥታ፣ ፖለቲካዊ፣ ሰብዓዊ ጉዳዮች፣ የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት አተገባበርና ቀጠናዊ ጉዳዮች በውይይቱ ዋነኛ ትኩረት ነበሩ።

ከክልሉ አመራሮች ጋር የተደረገ ውይይት
አምባሳደር ማሲንጋ ከሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል፣ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት አማኑኤል አሠፋ እና ከጸጥታ ኃይሎች ከፍተኛ አዛዦች ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

የውይይቱ ዋና ዓላማ በክልሉ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ መገምገም እና ለዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት የሚረዱ መፍትሄዎችን መፈለግ እንደነበር ተገልጿል።

የሽሬ የተፈናቃዮች መጠለያ ጉብኝት

አምባሳደሩ በጉብኝታቸው ወቅት የሽሬውን የተፈናቃዮች መጠለያ ጎብኝተዋል። ከአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር በሽሬ የተፈናቃዮች መጠለያ ከተፈናቃዮች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ዕርዳታ መስጠት ዘላቂ መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል እና መፍትሄው ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው መመለስ እንደሆነ የክልሉ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

አምባሳደሩ፣ ተፈናቃዮቹ ወደ ቀያቸው ተመልሰው ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው መረዳታቸውን ተናግረዋል።

ይህ የአምባሳደሩ ጉብኝት በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በቅርበት ለመመልከት እና ለአሜሪካ መንግስት ተጨማሪ መረጃዎችን ለማቅረብ ያለመ እንደሆነ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ የድንበር ፀጥታን ለማጠናከር ተወያዩ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የቀጠናውን መረጋጋት ለማጠናከር፣ ትብብርን ለማስፋት እና በድንበር ላይ የጋራ የፀጥታ ጥረቶችን ለማጎልበት ያለመ የከፍተኛ ደረጃ የሁለትዮሽ ውይይት በድንበር ከተማዋ ጋቢሌይ አካሂደዋል።

የልኡካን ቡድኖች

ውይይቱ በሁለቱም ወገኖች ከፍተኛ ባለስልጣናት የተመራ ሲሆን፤ የኢትዮጵያን ልኡክ የመከላከያ ሰራዊት ስምሪት ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው፣ የሶማሌ ክልል ፖሊስ አዛዥ ጄኔራል አብዲ አሊ ሲያድ እና የምስራቅ እዥ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ፍቃዱ ተሳትፈዋል።

በሶማሊላንድ በኩል ደግሞ የሶማሊላንድ ብሔራዊ ጦር አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ኒምካን ዩሱፍ እና የሶማሊላንድ ፖሊስ ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አብዲራህማን አብዲላሂ ሀሰን ከከፍተኛ ወታደራዊ እና የፖሊስ መኮንኖች ጋር በመሆን ተገኝተዋል።

የውይይቱ ትኩረት

ሆርን ዲፕሎማት እንደዘገበው፣ የፀጥታ ውይይቱ ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን ይህም የጋራ አሠራሮችንና የመረጃ ትብብርን ማጠናከር እና ሰላማዊ ድንበር ተሻጋሪ ግንኙነቶችን መደገፍን ያካትታል።

በተጨማሪም ሁለቱም ልኡካን ሰላምን ለማጽናት እና ሊከሰቱ የሚችሉ የፀጥታ ስጋቶችን ለመከላከል ቀጣይነት ያለው ስትራቴጂካዊ ትብብር ያለውን ጠቀሜታ አፅንዖት ሰጥተዋል።

በሁለቱ አካላት መካከል ያለውን መተማመን እና የአሠራር ዝግጁነት ለማጠናከር መደበኛ ስብሰባዎች አስፈላጊ መሆኑ ላይ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል። ቀጣዩ ዙር ውይይት በሶማሊላንድ ዋና ከተማ ሀርጌሳ ለማካሄድ ቀጠሮ ተይዟል።
የትግራይና ኦሮሚያ ጤና ማህበራት ለጤና ባለሙያዎች ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጠየቁ

የጤና ባለሙያዎች የጀመሩት የስራ ማቆም አድማ ስምንተኛ ቀኑን በያዘበት በአሁኑ ወቅት፣ የትግራይ እና ኦሮሚያ ክልሎች ጤና ማህበራት መንግስት ለጤና ባለሙያዎች ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጠየቁ።

የትግራይ ህክምና ማህበር ያቀረበው አቤቱታ

የትግራይ ህክምና ማህበር ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም. (ሜይ 18፣ 2025) ለጤና ሚኒስቴር በጻፈው ደብዳቤ፣ መንግሥት ለጤና ባለሙያዎች ጥያቄና መብት ተገቢውን ትኩረትና ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች የጤና ባለሙያዎችን ጥያቄ በመጣስ ተገቢ ያልሆነ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አስታውቋል።

ማህበሩ እነዚህ የታሰሩ የሞያ አጋሮቻቸው እንዲፈቱ አስፈላጊውን ጫና እንዲደረግ ሲል ለጤና ሚኒስቴር አሳስቧል። በተጨማሪም፣ ሁሉም የሞያ ማህበራት እና ጤና ባለሙያዎች ችግሮቹን ለመፍታት ግልጽና ሁሉን ያሳተፈ ውይይት እንዲደረግ ጠይቋል።

የኦሮሚያ ሐኪሞች ማኅበር ድጋፍ

በተመሳሳይ፣ የኦሮሚያ ሐኪሞች ማኅበር ትናንት ግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. (ሜይ 19፣ 2025) ባወጣው መግለጫ፣ "የጤና ባለሙያው የሚገባውን ለመስጠት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ አይፈቅድም ቢባል እንኳን እየተራበ እንዳያገለግል፣ እየተጠማ እንዳይማር፣ እየታመመ ማስታገሻ እንዳያጣ የሚያደርግ የኑሮ ሁኔታ እንዲፈጠርለት ሲታገል ቆይቷል" ሲል አውግዟል። ማህበሩ አሁን ላይ በጤና ባለሙያዎቹ እየተነሱ የሚገኙ ጥያቄዎችን እንደሚደግፍ ገልጾ፣ እየተፈጠረ ያለው ሁኔታ ተባብሶ ጉዳት ከማስከተሉ በፊት ውይይቶች እንዲደረጉና እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጠይቋል።

የጤና ባለሙያዎች የስራ ማቆም አድማ በአገሪቱ የጤና አገልግሎት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን ቀጥሏል።
Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)
Photo
አዲስ አበባ የትራፊክ መጨናነቅን ለማቃለል አዲስ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት ጀመረች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በአንድ ጊዜ 1,000 መኪኖችን የማቆም አቅም ያለውን እና በሾላ ገበያና መገናኛ አካባቢ ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ የሚያቃልለውን የየካ ቁጥር 2 የመኪና ማቆሚያ መርቀው አስጀመሩ።

የፕሮጀክቱ ገፅታዎችና አገልግሎቶች

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ይህ የመኪና ማቆሚያ ከምድር በላይ ባለ አምስት ወለል እንዲሁም ከመሬት በታች ባለ ሁለት ወለል፣ በአጠቃላይ 8 ወለሎች እንዳሉት ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ ምቹ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት እና የህዝብን እንግልት የሚያቃልል መሆኑንም ጠቁመዋል።

የመኪና ማቆሚያው የህዝብን አገልግሎት ምቾትና ክብርን የጠበቀ፣ ተገልጋዮችን ከዝናብና ጸሀይ የሚከላከል፣ የንጽህና መጠበቂያ ያለው፣ የሰውና የመኪና አሳንሰር የተገጠመለት፣ ለአካል ጉዳተኞች አካታች የሆነ አገልግሎት የሚሰጥ፣ ሶስት የመኪና ማጠቢያ ስፍራዎች ያሉት እንዲሁም ለነዋሪዎች የስራ እድል የሚፈጥር ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑንም ከንቲባዋ አመልክተዋል።

በተጨማሪም፣ በውስጡ ሌሎች አገልግሎቶችን የሚሰጡ ሱቆችና ቢሮዎች በመኖራቸው የኢኮኖሚና የማህበራዊ አገልግሎትን ለማሳለጥ እንዲሁም የትራንስፖርት ስርአቱን ለማዘመን ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጿል።

የአዲስ አበባን የፓርኪንግ አቅም ማስፋት

ይህ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ለመጀመሪያ ጊዜ በህንጻ ደረጃ የተገነባ ሲሆን፣ መሬት እና በጀት በመመደብ የተሰራው ይህ ስራ ከተማዋን እንደ ስሟ ውብ አበባ የማድረግ አካል ነው ብለዋል ከንቲባዋ።

ከለውጡ በፊት በመንግስት የተገነቡ የፓርኪንግ ቦታዎች ብዛት 2 ብቻ እንደነበሩና 500 መኪኖችን የማቆም አቅም ያልነበራቸው እንዲሁም 1 ተርሚናል ብቻ እንደነበረ የጠቀሱት ከንቲባዋ፣ ከለውጡ በኋላ በተሰራው ስራ 150 የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች እንደተገነቡና የዛሬውን ጨምሮ በአንድ ጊዜ 35 ሺሕ ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚችሉ ስፍራዎች መኖራቸውን አስታውቀዋል።

በተጨማሪም፣ 49 የሚደርሱ ተርሚናሎችን ገንብቶ የትራንስፖርት ስርዓቱን ለማዘመን እየተሰራ መሆኑንም ከንቲባ አዳነች አቤቤ አክለዋል።

ይህ አዲስ የመኪና ማቆሚያ የአዲስ አበባን የትራፊክ መጨናነቅ በማቃለል ረገድ ምን ያህል ለውጥ ያመጣል ብለው ያስባሉ?
ብሔራዊ ባንክ ስድስተኛውን የዉጪ ምንዛሪ ጨረታ በ50 ሚሊዮን ዶላር ሊያካሂድ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ገበያን ለማረጋጋትና የውጭ መረጋጋትን ለመቆጣጠር ያለመ 50 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ነገ ሐሙስ እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

ይህ ጨረታ ለንግድ ባንኮች የቀረበ ሲሆን፣ ባንኩ በየሁለት ሳምንቱ ከሚያካሂዳቸው ተከታታይ ጨረታዎች ስድስተኛው ነው።

ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው አምስተኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ፣ የአንድ የአሜሪካ ዶላር የመገበያያ ዋጋ 132.96 ብር ሆኖ ተመዝግቦ ነበር። በዚያ ጨረታ ላይ ባንኩ 60 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያቀረበ ሲሆን፣ በጠቅላላው 16 የንግድ ባንኮች የጠየቁትን የውጭ ምንዛሪ ድልድል ማግኘት ችለው እንደነበር ይታወቃል።

Capital newspaper
ትራኦሬ

የቡርኪናፋሶው ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ ከዛሬ ጀምሮ በመላው ቡርኪናፋሶ የወሲብ ድረገፆችን ሙሉ ለሙሉ አግደዋቸዋል።

ትራኦሬ ማንኛውንም የብልግና ምስል የሚያሰራጩ ድረገፆችን መዘጋታቸውን ተከትሎ "እንዚህ የብልግና ደረገፆች ህዝባችንን ከማባላግ ባለፈ እሴታችንን በእጅጉ በመሸርሸር ህዝባችንን ብቻ ሳይሆን መላው አፍሪካን እያደነዘዘ የሚገኝ አደገኛ ነገር ነው" ያሉ ሲሆን ሌሎች የአፍሪካ ሀገሮችም ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ የሀገራቸውን እና የአፍሪካን እሴት እንዲያስጠብቁ አሳስበዋል።

ይህን የኢብራሂም ትራኦሬን ድፍረት የተሞላበት ውሳኔ በርካቶች አድናቆት እየቸሩት ይገኛሉ።
245 ሚሊዮን ዶላር የመዘበሩት የቀድሞው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር በሙስና ወንጀል 10 ዓመት ከባድ የግዳጅ የጉልበት ስራ ተፈረደባቸው።

አውግስቲን ማታታ ፖንዮ 245 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ የህዝብ ገንዘብ በመመዝበር የአገሪቱ ህገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ሆነው ስላገኛቸው ነው ይህ ብይን የተላለፈው።

ከሳቸው በተጨማሪ የዲሞክራቲክ ኮንጎ ማዕከላዊ ባንክ ገዢ የነበሩት ዲኦግራቲያስ ሙቶምቦም በዚህ ምዝበራ በመሳተፍ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ጠበቃ ውሳኔው ኢፍትሃዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ነው ሲሉ መውቀሳቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ተመዝብሯል ከተባለው ገንዘብ መካከል የተወሰነው የተወሰደው የአገሪቱን ስር የሰደደ የምግብ እጥረት ለመቅረፍ ከታቀደው ትልቅ የግብርና ልማት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ጠፈር ሊጓዙ ነው ተባለ‼️

ጠ/ሚኒስትሩ ጠፈር ላይ በመሆን ለአለም ህዝብ የሰላም መልዕክት ለማስተላለፍ አቅደዋል።

የጉዞ እቅዱ ከተሳካ ወደ ጠፈር የተጓዙ የመጀመርያው የአለማችን መሪም ያደርጋቸዋል።

በአለም ታሪክ ወደ ጠፈር (space) የተጓዙ ሰዎች ቁጥር 721 እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ፣ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ የጠፈር ተመራማሪዎች ሲሆኑ ከቅርብ አመታት ግን ጥቂት ሰዎች ከፍተኛ ገንዘብ በመክፈል የዝቅተኛው ንፍቀ ክበብ የጠፈር ጉብኝት አድርገዋል።

Via መሠረት ሚዲያ
97 በመቶ የጤና ሰራተኞች ደመወዛቸው መሰረታዊ ወጪዎችን ለመሸፈን በቂ እንዳልሆነ አዲስ ጥናት አመለከተ

በአፍሪካ የህዝብ ጤና እና ትምህርት አገልግሎቶች ከባድ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የሚያሳይ አዲስ ጥናት ይፋ ሆኗል።

በአክሽንኤይድ ኢንተርናሽናል የወጣው “በአፍሪካ የመንግስት ዘርፍ ቅነሳ የሰው ልጅ ዋጋ” የተሰኘው ጥናት፣ በስድስት የአፍሪካ ሀገራት (ኢትዮጵያ፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ላይቤሪያ፣ ማላዊ እና ናይጄሪያ) የቁጠባ ፖሊሲዎች በሰው ልጅ ላይ የሚያስከትሉትን ከፍተኛ ዋጋ አጉልቶ አሳይቷል።

የጥናቱ ግኝቶች እንደሚያመለክቱት፣ 97 በመቶ የሚሆኑት የጤና ሰራተኞች ደሞዛቸው የቤት ኪራይ፣ ምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ የቤት ወጪዎችን ለመሸፈን በቂ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ፣ ከ2020 ወዲህ 84 በመቶ የሚሆኑት አስተማሪዎች እውነተኛ ገቢያቸው ከ10 እስከ 50 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።

ይህ ደመወዝ በቂ አለመሆን የሰራተኞችን የኑሮ ጫና በእጅጉ እንደጨመረ ተመላክቷል።
እንደ ግኝቱ መሰረት ፣ የመንግስት በጀት ቅነሳ እና እየጨመረ የመጣው የተማሪዎችና የታካሚዎች ቁጥር ከፍተኛ የስራ ጫና ፈጥሯል።

ተጨማሪ ያንብቡ

Capital newspaper
2025/07/05 07:04:06
Back to Top
HTML Embed Code: