Telegram Web Link
እስቲ ዋዛን በአንድ ቃል ብቻ ግለጹት !!

@Man_united_ethio_fans
@Man_united_ethio_fans
1.1K🏆62👍29🙏943🔥3
😁1.05K82👍21🙏5
🔥በየቀኑ ሽልማት, በየቀኑ ደስታ!
ዛሬ ቢያንስ 3 ፕሪማች ፣ላይቭ፣ቨርቹዋል ወይም ኢ ሶከር ትኬቶችን ይጫወቱ እና ነገ ለራስዎ ነፃ ውርርድ ያግኙ !!!
ሁልጊዜ!!!
🌟በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቀድሞውኑ የደስታው ተካፋይ ሆነዋል - እርሶም ቀጣይ ይሁኑ 🔥
𝗟𝗔𝗟𝗜𝗕𝗘𝗧- 𝗪𝗘 𝗣𝗔𝗬 𝗠𝗢𝗥𝗘!!!
𝗪𝗘𝗕𝗦𝗜𝗧𝗘 👉🏻https://copartners.lalibet.et/visit/?bta=35062&brand=lalibet
𝗙𝗔𝗖𝗘𝗕𝗢𝗢𝗞👉🏻 https://www.facebook.com/LalibetET
𝗧𝗘𝗟𝗘𝗚𝗥𝗔𝗠👉🏻 https://www.tg-me.com/lalibet_et Contact Us on 👉- +251978051653
13
Forwarded from ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ ፎቶዎች (𝚂𝚄𝚁𝚄𝚁🅰 ®𝙴𝙳)
641👏38👍16🎉9🏆9🍾9🙏3
ፓትሪክ ዶርጉ እና ዲያጎ ዳሎት ለነገው ጨዋታ ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቀዋል !!

@Man_United_Ethio_Fans
@Man_United_Ethio_Fans
704😁120💔46👏16👍11🙏5🏆5🎉3
መልካም አዳር ዩናይትዳውያን! ❤️

@Man_United_Ethio_Fans
@Man_United_Ethio_Fans
🙏500151👏12🏆9🔥85👍2
የጨዋታ ቀን [ Match Day ] ! 🔴

🦁 የ2025/26 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ !

⚽️ ማንችስተር ዩናይትድ ከ ብራይተን ⚽️

🗓 ዛሬ ጥቅምት 15 - 2018

ምሽት 1:30

⚽️ ኦልድትራፎርድ ስታድየም

የቀጥታ ስርጭት በ ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ 🔈

ድል ለውዱ ክለባችን ! ❤️

@Man_united_ethio_fans
@Man_united_ethio_fans
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
498🙏49🔥18👍17😁7🏆3
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት ጨዋታ

🔴 ማንችስተር ዩናይትድ ከ ብራይተን 🔵

|| ምሽት 01:30

🏟️|| ኦልድትራፎርድ

               ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ

የብዙሀኑ ቀልብ ማረፊያ የሆነው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬም ሲቀጥል ኦልድትራፎርድም ከ 3 ሳምንታት በኋላ ጨዋታ ታስተናግዳለች።

በቀዩ መንደር ጊዜ መግዛት የሚችል ሰሞነኛ እፎይታ ላይ የምንገኝ ሲሆን ባለፉት 5 ጨዋታዎች ሽንፈት ያልገጠመው ብራይተን ቀላል ፈተና ይሰጠናል ተብሎ አይጠበቅም።

ጨዋታውን ማሸነፍ ለዩናይትድ እጅግ ወሳኝ ሲሆን አሁን ያለውን የድል መንፈስ ለማስጠበቅ ጉልህ ሚና ይኖረዋል።

ጨዋታውን ማሸነፍ ነጥባችንን 16 አድርሶ ወደ ፊት ለመጠጋት ያስችለናል።

#ይቀጥላል

@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
276🙏21🏆11👍10💯4
#የቀጠለ

        || የእርስ በእርስ ግንኙነቶች

ማንችስተር ዩናይትድ እና ብራይተን በታሪክ እስከ ዛሬ ድረስ 35 ጨዋታዎች ላይ የተፋለሙ ሲሆን ክለባችን አብላጫ የበላይነቱን ይዟል።

ካደረግናቸው 35 የእርስ በእርስ ግንኙነቶች ውስጥ 21ዱን በድል ተወጥተን ፤ 5ቱን በመከባበደር ደምደመን በቀሪዎቹ 9 ጨዋታዎች ብራይተን ማሸነፍ ችለዋል።

ብራይተን ከሀገሩቱ ታላቁ ሊግ በግሪጎሪያኑ ቀመር ከ 1993 ከወረዱ በኋላ እስከ 2017 ድረስ ወደ ሊጉ መመለስ ተስኗቸው የነበረ መሆኑ የተገናኘንበት ጨዋታዎች መጠን መቀነስ ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ አላቸው።

በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ብራይተንን የገጠምነው 1909 ላይ በኤፍኤ ካፕ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ሲሆን ዩናይትድ በሀሮልድ ሀርስ ብቸኛ ጎል ድል ማደረጉን ታሪክ ሰንዶ አስቀምጦታል።

በሁሉም ውድድሮች ካለፉት 8 የእርስ በእርስ ግንኙነቶች ውስጥ ማሸነፍ የቻልነው 2ቱን ብቻ ነው።

ብራይተን በተከታታይ 3 ዓመታት ከኦልድትራፎርድ ሙሉ 3 ነጥብ ይዘው መውጣታቸው በጥሩ የሚታይ ቁጥር አይደለም።

ለመጨረሻ ጊዜ ብራይተንን ስንገጥም በኦልድትራፎርድ 3-1 የሆነ ሽንፈት ደርሶብናል። ብቸኛዋን የማስተዛዘኛ ጎል ብሩኖ በፔናሊቲ ማስቆጠሩ አይረሳም።

#ይቀጥላል

@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
176💔39👍6🙏4👏3🎉1
#የቀጠለ

        🎤 የአሰልጣኞች አስተያይት

🔴 ሩበን አሞሪም

"ከአንፊልዱ ድል መልስ የነበረው የአሸናፊነት መንፈስ እና ለዚህ ጨዋታ ያደረግነው ዝግጅት ላይ የነበረው ተነሳሽነት ጥሩ ነበር። ከባድ ጨዋታ ይሆናል ብዬ አስባለሁ።"

"በእኔ እምነት ብራይተን ለመመልከት አዝናኝ የሆነ ኳስ ከኋላ በቢውልድ አፕ ሲወጡም ሆነ በሽግግሮች ጥሩ ቡድን ናቸው። በዚህ የውድድር ዘመን ደግሞ ከቆሙ ኳሶች አደጋ ይፈጥራሉ። የተሟላ ቡድን ነው ማለት እንችላለን።"

"ቡድኑ የሚጫወትበትን መንገድ እና የአሰልጣኙን ሀሳብ ለመረዳት ግልፅ ነው። ሀይል እና ፍጥነትን የቀላቀለ እግር ኳስን ይጫወታሉ። በጫና ውስጥ ቢሆኑ እንኳን የሚያደርጉትን ነገር አምነውበት ነው የሚፈፅሙት የፋቢያን ሀርዝለር ትልቅ አድናቂ ነኝ።"

"በእነሱ ጥንካሬ ላላመበለጥ እና ጨዋታውን ለማሸነፍ ሙሉውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሙሉ ትኩረታችንን ሰጥተን ልንጫወት ይገባል።"

🔵  ፋብያን ሀርዝለር

"እኔ እንደማስበው ከሆነ ይበልጥ ዩናይትድ ቀጥተኛ ናቸው። ብዙ ሴስኮን ኢላማ ያደረጉ ረጃጅም ኳሶችን ይጥላሉ። ሁለተኛ ኳሶችን እያሸነፉ ኳሱን ወደ መስመር በማውጣት ከጥልቅ በሚነሱ ሩጫዎች ፔናሊቲ ቦክሱን ለማጥቃት ይሞክራሉ።"

"ጥሩ የሆነ ተናጥላዊ ጥራትም አላቸው፤ በአንድ እንቅስቃሴ መቀየር የሚችሉ ተጨዋቾች አሏቸው። በተለይ ደግሞ ከፊት ያለው መስመራቸው ይህን ማድረግ ይችላል።"

"ሩበን አለም ላይ ካሉ ምርጥ አሰልጣኞች ውስጥ አንዱ ነው። እርግጥ ነው በእንግሊዝ ህይወት ቀላል አልሆነለችም። ግን ከዚህ በፊት ያለውን ብቃት በሚገባ አስመስክሯል።"

"ከዩናይትድ ጥራት አኳያ 90 ደቂቃ በሙሉ ከ ኳስ ጋርም ሆነ ከ ኳስ ውጪ ንቁ ሆነን መጫወት ይኖርብናል።"

#ይቀጥላል

@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
220👍18🏆3👏1🤩1🙏1💔1
#የቀጠለ

  🎯 የቡድን ዜና ማንችስተር ዩናይትድ

ካለፈው ጨዋታ አዲስ የተሰማው የጉዳት ዜና የሀሪ ማጓየር እና ሜሰን ማውንት ሲሆን ለጨዋታው የመድረሳቸው ነገር ጥያቄ ምልክት ውስጥ ገብቷል።

ረጅም ከጉዳት የማገገሚያ ጊዜ ላይ የሚገኘው ሊሳንደሮ ማርቲኔዝ ወደ ሜዳ ለመመለስ ቢቃረብም ከዛሬው ጨዋታ ውጪ ነው።

ሌላኛው ተከላካይ አይድን ሄቭን ከጉዳቱ አገግሞ ዛሬም የመድረስ እድሉ እጅግ በጣም ጠባብ ነው።

በዩናይትድ በኩል ጨዋታው የሚያመልጣቸው ተጨዋቾች ፦

ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ - በጉዳት
አይድን ሄቭን - በጉዳት
❗️ሜሰን ማውንት - አጠራጣሪ
❗️ሀሪ ማጓየር - አጠራጣሪ

#ይቀጥላል

@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
261😢44🙏13👏8👍5👀4💔3
#የቀጠለ

   🎯 የቡድን ዜና ብራይተን

ኒውካስትልን በረቱበት ጨዋታ ጉዳት የገጠመው ዲዬጎ ጎሜዝ ከጉዳቱ አገግሞ ለጨዋታ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ካዎሩ ሚቶማ ለጨዋታው የመድረሱ ነገር ጥያቄ ውስጥ የገባ ተጨዋች ነው።

ጆዬል ቬልትማን እና ግሩዳ በተመሳሳይ ለጨዋታው መድረስ አለመድረሳቸው አልታወቀም።

በብራይተን በኩል ጨዋታ የሚያልፋቸው ተጨዋቾች ፦

ጃክ ሂንሽልውድ - በጉዳት
አዳም ዌብስተር - በጉዳት
❗️ካዎሩ ሚቶማ - አጠራጣሪ
❗️ጆዬል ቬልትማን - አጠራጣሪ
❗️ብሮያን ግሩዳ - አጠራጣሪ

#ይቀጥላል

@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fabs
136👍24🙏13👏1
#የቀጠለ

        👕|| የዕለቱ አልቢተሮች

የ 48 ዓመቱ የዋይተንሻው ማንችስተር ተወላጅ አንቶኒ ቴይለር ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።

ቴይለር በዚህ የውድድር ዘመን 4 ጨዋታዎችን በዋና ዳኝነት ያጫወቱ ሲሆን 14 ቢጫ ካርዶችን መዘዋል።


👉 ዋና ዳኛ = አንቶኒ ቴይለር
👉 ረዳት ዳኛ 1 = ጋሪ ቤስዊክ
👉 ረዳት ዳኛ 2 = አዳም ኑን
👉 4ኛ ዳኛ = ጋቪን ዋርድ
👉 የቫር ዳኛ = ማይክል ኦሊቨር
👉 የቫር ረዳት = ስቱዋርት በርት

@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
132💔26🙏7👍1😎1
#የቀጠለ

      🔮 የውጤት ግምቶች

ምንም እንኳን ብራይተን በኦልድትራፎርድ ባለፉት 3 ጨዋታዎች ቢረቱንም ካለን ወቅታዊ አቋም አንፃር በአቋማሪ ድርጅቶች የተሻለ እድል ተሰጥቶናል።

የጨዋታ ቅድመ ግምት የሚሰሩ ተቋማትም ማንችስተር ዩናይትድ በጠባብ የጎል ልዩነት የማሸነፍ እድል እንዳለው ተንብየዋል።

        📃 ግምታዊ አሰላለፍ

🔴 ማንችስተር ዩናይትድ (3-4-3)

ላመንስ ፣ ዮሮ ፣ ደሊት ፣ ሾው ፣ ዶርጉ ፣ ካሴሜሮ ፣ ብሩኖ ፣ አማድ ፣ ኩኛ ፣ ኤምቤሞ ፣ ሴስኮ

🔵 ብራይተን (4-2-3-1)

ቬብሩግን ፣ ዊፈር ፣ ቫን ሄክ ፣ ደንክ ፣ ካዲዮግሉ ፣ አያሪ ፣ ባሌባ ፣ ሩተር ፣ ጎሜዝ ፣ ምንቴህ ፣ ዌልቤክ

         🖥 የቀጥታ ስርጭት

ተወዳጇ ቻናላችን ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ ጨዋታውን ከጅማሬ እስከ ፍፃሜ የምታስተላልፍ ይሆናል።

ሌሎች የመከታተያ አማራጮችን የጨዋታ ሲቃረብ እንደተለመደው የምናሳውቅ ይሆናል።

የጨዋታ ቅድመ ዳሰሳውን እኔ #አዶናይ አዘጋጅቼ አቀረብኩኝ።

ሰናይ ሰንበት እና ጨዋታን ተመኘሁ ❤️

@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
210🙏14👍5
2025/10/27 11:05:45
Back to Top
HTML Embed Code: