#በስመ_አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ_አምላክ፤ አሜን።
     
◆በሰሙነ ሕማማት ውስጥ ያሉትን ዕለታት ሊቃውንት ከጌታ መከራ ጋር በማመሳጠር ስያሜና ትርጓሜ ሰጥተዋቸዋል፡-

◆ ሰኞ ◆
●ይህ ዕለት አንጽሆተ ቤተመቅደስና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡፡ የሆሳዕና ዕለት ቢታኒያ ያድራል በማግስቱም ከቢታኒያ ሲመጣ ተራበ (ማር 11፡11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት፣

#በለስ_የተባለች_ቤተ_እስራኤል_ናት
ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት ጌታ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከእስራኤል ተወለደ ሰው ሆኖ መጥቷልና፣ ቀድሞ የበኩር ልጄቼ ካላቸው ከእስራኤል ፍቅርን ሃይማኖትን ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር መባልን እንጂ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸውና ከመረጣቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋበት)

#በለስ_ኦሪት_ናት
እሱ ከልዕልና ወደ ትህትና ሥጋ ለብሶ ሰው ሆኖ ሲመጣ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት፤ ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ…(ማቴ 5፡17) በማለት ፈጸማት ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና ፍሬ ባንቺ አይሁን አላት፣ ድኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡

#በለስ_ኃጢዓት_ናት
ጌታችን የባሕርይ ክብሩን ትቶ ነውር ነቀፋ ሳይኖርበት፣ ኃጢዓት በደል ሳይገኝበት ወደ ውርደት ሞት (የመስቀል ሞት) ሲመጣ የበለስ ቅጠል ሰፊ አንደሆነች ሁሉ ኃጢዓት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢዓትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄደ (ከኃጥአን ጋር ዋለ) ነገር ግን ኃጥእ ከመባል በቀር በመዋሉ ኃጢዓት አለመስራቱን ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፣ በኃጢዓት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፡፡ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፤ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡

◈ከዚህ ቀጥሎ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ ቤተ ጸሎት፤ ቤተመስዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው፤ ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች እናንተ ግን የወንበዶዎች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው ገርፎም አስወጣቸው ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርነው የአዳም ልጆች ኃጢዓት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢዓታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ በዚህ በስሙነ ሕማማት ካህናትና ምዕመናን በቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፣ በስልስት፣ በስድስቱ ሰዓትና፣ በተሰዓቱ ሰዓት መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፣ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም የደረሰበትን መከራ ሐዘኑንና ፭ሺህ ፭ መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ሕይወት ውስጥ ይኖር እንደነበር ለማዘከዘር ይህን ያደርጋሉ፡፡

   ◈ማክሰኞ◈

#የጥያቄ_ቀን

●ይኸውም የሆነበት ምክንያት ሹመትን ወይም ስልጣንን ለሰው ልጅ ሰጠ ጌታችን ፣ ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ምክንያት በዚህ ዕለት ስለ ሥልጣኑ በጻሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋል ነው፡፡ ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንስ ስልጣን ማን ሰጠህ? የሚል ነበር፡፡ (ማቴ 21፡23-27 ፣ ማር 11፡27-33 ፣ ሉቃ 20፡1-8) ጌታም መልሶ እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ፣ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች ከሰማይ? ወይስ ከሰው? አላቸው፤ እነሱም ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል፣ ከሰው ብንል ሕዝብ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፣ እንደ መምህርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን ተባብለው ከወዴት እነደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፣ እርሱም እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም አላቸው ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንደሚያደርግ አጥተውት አልነበረም፣ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ ነው እንጂ፡፡ ጌታ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ እንዲል (ማቴ 16፡7) እንደ ፈሪሳውያን ከክፋት ከጥርጥር መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡

●በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ይባላል፡፡ ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ መክሮ መመለስ እንደሚገባን ሲገልጽልን ነው፡፡ (ማቴ 21፡28 ፣ ማቴ 25፡46 ፣ ማር 12፡2 ፣ ማር 13፡37 ሉቃ 20፡9 ፣ ሉቃ 21፡38) በዚህ ሳምንት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ የሃይማኖት ትምህርት ሲማር ሲጠይቅ መሰንበት ይገባዋል፡፡

◈ረቡዕ◈

#የምክር_ቀን

●ይህ ዕለት የምክር ቀን ይባላል፣ ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጻሕፋት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር የጀመሩበት ወይም የያዙበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ወቅቱ አይሁድ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት በመሆኑና ብዙ ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረከ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለነበር ምናልባት ሁከት ይፈጠራል ብለው በክፉ ምክራቸው እጅግ ተጨንቀው ሳለ ከደቀመዛሙርቱ መካከል አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ በክፉ ምክራቸው በመሳተፍ ጌታን በመሳም አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ቃል ስለገባላቸው ጭንቀታቸው ተወገደ ለወረታውም ሰላሣ ብር መዘኑለት (ማቴ 26፡1-5 ፣ ማቴ26፡14-15 ፣ማር 14፡1-2፣ ሉቃ 22፡1-6) የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምዕመናን በዚህ ዕለት በቤተክርስቲያን ተሰብስበው ከእህል ከውሃ ተለይተው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ፣ ስለዚህ የሚያወሳውን ሁሉ በመዘመርና በማንበብ እንዲሁም እስከ ስርቀተ ኮከብ (እስከ ኮከብ መውጫ) በመጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይሰነብታሉ፡፡

#መልካም_መዓዛ

●ይህ ዕለት (ረቡዕ) መልካም መዓዛ ያለው ቀንም ይባላል፣ ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢዓት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ፣ ኃጢዓትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፣ በአልባሲጥሮስ ብልቃጥ የሞላ ሽቱ ይዛ በመሄድ በጠጉሩ (በራሱ) ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ነው፡፡

#የእንባ_ቀን

●ይህም ስያሜ የተሰጠበት ምክንያት ይህችው ማርያም እንተእፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢዓቷን ይቅር እንዲልላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፣ በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና፡፡ (ማቴ 26፡6-13 ፣ ሉቃ 7፡36 ፣ ማር 14፡3-9 ፣ ዮሐ 12፡1-8) የማርያም እንተእፍረትን ኃጢዓት ይቅር ብሎ መባዋን የተቀበለ አምላክ ዛሬ በመካከላችን አለና በማንኛውም ጊዜና ሰዓት የራሳችንን ኃጢዓት በማሰብ በማልቀስና የተወደደ መስዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር በማቅረብ በመልካም ሥራዋ ልንመስላት ይገባል፡፡

◈ጸሎተ_ሐሙስ◈
●በፍጥረታት የሚለመንና የሚመሰገን አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለምንና አላዋቂ የሆነውን ሥጋ የተዋሐደ አምላክ፣ ፍጹም ሰውም መሆኑን ለመግለጥና ለአርያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ በጌተሰማኒ በአታክልቱ ሥፍራ ሦስቱን የምስጢር ሐዋርያት ይዞ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ይህ ዕለት ጸሎተ ሐሙስ ተብሏል፡፡ (ማቴ 26፡36-46፣ ዮሐ 17)

#ሕፅበተ_ሐሙስ

●የነገስታት ንጉሥ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም ፣ መጥቶ ሲያስተምር መምህርነቱን ልዩ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል ከቃል ይልቅ ተግባር ይሰብካልና የተግባር መምህር በመሆን አርአያ መሆኑ ነው፡፡ በዚህ ዕለት መምህራቸው ሆኖ ሳለ ክርስቶስ በአጭር ታጥቆ አደግድጎ ወገቡን አስሮ የደቀመዛሙርቱን እግር ያጥብ ዘንድ በትህትና ዝቅ አለ፡፡ ይህም የሚያሳየው ከትህትናው ባሸገር የዓለምን ኃጢዓት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው ‹‹ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘያአትት ኃጢዓተ ዓለም›› ተብሎ እንደተጻፈ፡፡ ይህንን ለማስታወስ ዛሬም ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳትና የደብር አስተዳዳሪዎች በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብህን ኃጢዓት እጠብ ሲሉ በዕለቱ በአጸደ ቤተክርስቲያን የተገኙትን ምዕመናንን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ሲያጥቡ ያረፍዳሉ፡፡

#የምስጢር_ቀን

●ከሰባቱ ምስጢራተ ቤተከርስቲያን አንዱ በዚህ ቀን ተመስርቷል፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሴተ ሐሙስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ለእራት ተቀመጠ ህብስቱንም አንስቶ ባርኮ ከቆረሰ በኋላ ‹‹ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ ሚቆረሰው ሥጋዬ ነው እንካችሁ ብሉ››፣ የወይኑንም ጽዋ አንስቶ ‹‹ይህም ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚፈሰው ደሜ ነው ከእርሱም ጠጡ›› በማለት እኛ ከእርሱ ጋር፣ እርሱ ከእኛ ጋር አንድ የምንሆንበትን ምስጢረ ቁርባን ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ ለደቀመዛሙርቱ የገለጠበት ዕለት በመሆኑ የምስጢር ቀን ተብሏል፡፡ በዚህ ዕለት ቅዳሴ ይቀደሳል የሚቀደሰውም በለሆሳስ ሲሆን እንደቃጭል ሆኖ የሚያገለግለውም ጸናጽል ነው፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ ሲመጡ ድምጻቸውን ዝግ አድርገው፣ በለሆሰስ እየተነጋገሩ መምጣታቸውን ለማሰብ ነው፣ በቅዳሴውም ጸሎተ ተአምሆ፣ ኑዛዜ አይደረግም ሥረዓተ ቁርባን ግን ይፈጸምበታል፣ ይህም የሆነው ጌታችን የሰጠውን ዘላለማዊ ቃል ኪዳን ለማሰብ ነው በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ተዘጋጅቶ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን መቀበል ይኖርበታል፡፡

#የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ

●ይህንን ስያሜ ያገኘበት ምክንያት በእንሰሳት ደም የሚቀርበው የኦሪት መስዋዕት ማብቃቱን ገልጦ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መስዋዕት አድርጎ የአቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ ‹‹ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው ከእርሱም ጠጡ›› በማለት አዲስ ኪዳንን መሥርቷል፡፡ (ሉቃ 22፡20) ኪዳን ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት መሐላ ማለት ነው በዚህ መሰረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘላለማዊ ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት መሆኑን በማሰብ የቃል ኪዳኑ ፈጻሚዎች ጠባቂዎች መሆን እንደሚገባን እንማራለን፡፡

#የነፃነት_ሐሙስ

●በአዳምና በሔዋን አለመታዘዝ ምክንያት ልጆቻቸው ሁሉ ለ ፭ሺህ ፭ መቶ ዘመን የኃጢዓትና የዲያብሎስ ባሪያ ሆነው ይኖሩ ነበረ፡፡ ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለኃጢዓትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃት፣ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ የነፃነት ሐሙስ ተብሏል፡: ራሱ ጌታችን ስለሰው ልጅ ነፃነት ሲናገር ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ባሪያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ›› በማለቱ ይህ ዕለት ከባርነት ነጻ የወጣንበት መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳናል፡፡ (ዮሐ 15፡15) ስለዚህም እያንዳንዱ ክርስቲያን ከኃጢዓት ባርነት ርቆ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጁትን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን መምራት ይኖርበታል፡፡ እርሱ ጠላቶቹ ሳለን ወዳጆች አድርጓናልና፡፡ በዚህ ዕለት ሦስት ዓበይት ነገሮች መከናወናቸውን መጽሐፍ ቅዱስ መዝግቦልናል፡-

➩አይሁድ የፋሲካን ዝግጅት ያደረጉበት ዕለት ነው ፋሲካ ማለት የቃሉ ትርጉም ማለፍ መሻገር ማለት ሲሆን ይኸውም እስራኤላውያን ከግብፅ የባርነት ቀንበር ተላቀው ወደ ከነዓን ምድር ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት በእያንዳንዳቸው ቤት የበግ ጠቦት እንዲያርዱ ደሙን በመቃናቸው ላይ እንዲቀቡ ሥጋውንም ጠብሰው ወገባቸውን ታጥቀው፣ በትራቸውን ይዘው ፈጥነው እንዲበሉ በታዘዙት መሠረት ፋሲካንና ደም መርጨትን በእምነት አደረጉ (ማቴ 26፡17-19 ፣ ማር 14፡ 12-16 ፣ ዘፀ 12፡1-52) ይህንንም ያደረጉት ስለ ሁለት ምክንያቶች ነበረ መጀመሪያ አጥፊው የፈርኦናውያንን ግብጻውያንን የበኩር ልጆች ሲያጠፉ የእነሱን እንዳያጠፋ የበጉን ደም በመቃናቸው ቀብተው ፋሲካን በዕምነት አድርገዋል፣ ሌላው ማርና ወተት የምታፈሰውን ምድረ ርስት ከነዓንን ለመውረስ የበጉን ሥጋ ተዘጋጅተው በልተው ፋሲካን ማድረግ ነበረባቸውና ነው፡፡ በዚህ መነሻነት በየዓመቱ እስራኤላውያን በመጀመሪያ ወራቸው በ 14 ኛው ቀን በግ እያረዱ የፋሲካን በዓል ያከብራሉ፡፡ ሀገራችንም አስቀድማ ብሉይ ኪዳንን የተቀበለች ሀገር እንደመሆኗ ይህ ድርጊት ይፈጸምባት ነበር፡፡ በሐዲስ ኪዳን ግን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ነው መርገማችን የሻረልን ሞታችንን የሻረልን በመሆኑም ራሱን የተወደደ መስዋዕት አድርጎ ያቀረበ የዋህ በግ ነው፡፡ ሐዋርያው ‹‹ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዷል እንዲል›› 1ቆሮ 5፡6 የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ፋሲካችን ነው፡፡ (1ጴጥ 1፡18)

➩ጌታ_ረዥም_ትምህርት_አስተምሯል በዚህ ዕለት እንደ ማክሰኞ ለደቀመዛሙርቱ ረዥም ትምህርትን አስተምሯል (በዮሐ 14፡17) የትምህርቱም ዋና ዋና ክፍሎች ምስጢረ ሥላሴ (የሦስትነት ትምህርትና ምስጢረ ሥጋዌ (የአምላክ ሰው መሆን፣ ምስጢረ ትንሣኤ ሙታንና የዳግም ምጽዓት ትምህርት ነው) እነዚህን ትምህርቶች በጥልቀት መማር እንደሚገባ ሲያስረዳን በተአምራት ሊገለጥላቸው ሲችል በረጅም ትምህርት እንዲረዱት አድርጓል፡፡ ተማሪዎቹም እሱ እያስተማራቸው ሳለ ያልገባቸውን እየጠየቁ ተረድተዋል፣ እኛም በቤተክርስቲያን ተገኝተን መማርና ያልገባንን ጠይቀን መረዳት እንደሚገባን እንማራለን፡፡

➩ይሁዳ_ጌታን_በመሳም_አሳልፎ_ሰጥቶታል በዚህ ዕለት ‹‹እንጀራዬን የበላ እሱ ተረከዙን በእኔ አነሳ›› (መዝ 40፡9) ተብሎ እንደተጻፈ የቃሉን ትምህርት ከሰሙና የእጁን ተአምራት ካዩት ከደቀመዛሙርት መካከል አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ የተባለው ‹‹ጌታ ሆይ መምህር ሆይ›› ብሎ በሽንገላ ጌታውን አሳልፎ የሰጠበት ዕለት ነው፡፡ ጭፍሮችም በዚህ ዕለት ሌሊት የክብር ባለቤት የሆነውን ጌታችንን ይዘው ወደ ፊት፣ ወደ ኋላ እየጎተቱ እያዳፉ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ወስደውታል፡፡ (ማቴ 26፡47-58)

◈የስቅለት_ዓርብ◈

የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት
Forwarded from ✟ መዝሙር ቤት ✟
ምን አይነት መዝሙር ይፈልጋሉ
Forwarded from ቤተ_ልሔም~Bethelhem (፩ Mekuriya Murashe)
#የሊቁ_የቅዱስ_ያሬድ_የዜማ_ምልክቶች

፪. ይዘት ( . ) ፡- በአይሁድ ጭፍሮች ለመያዙ።
፪. ሂደት ( — )፡- ታስሮ ለመጎተ።
፫. ጭረት ( ﺮ )፡- ለግርፋቱ ሰንበር።
፬. ድፋት (┌┐)፡- አክሊለ ሾክ ለመድፋቱ።
፭. ደረት (└┘)፡- ሲሰቅሉት በመስቀሉ ላይ አንጋለው ከደረቱ ላይ ቆመው እየረገጡት ለመቸንከሩ።
፮. ርክርክ ( ፡ )፡- ለደሙ ነጠብጣብ አወራረድና ለችንካሮች ምልክት።
፯. ቁርጥ ( ├ )፡- በጦር ተወግቶ ፈጽሞ መሞቱ ለመታወቁ።
፰. ቅንአት ( ﺭ )፡- በቅንአት አይሁድ ለመግደላቸው።

ከላይ የተጠቀሱት ምልክትና መስታወሻዎች ሲሆኑ ፰ መሆናቸው ፰ቱ ማኅበረ አይሁድ ተባብረውና ተማክረው በብዙ መከራ ለመግደላቸው ምሳሌ ነው፡፡

እነርሱም ፡-
፩. ጸሐፍት ፈሪሳውያን
፪. ሰዱቃውያን
፫. ረበናት /አይሁድ መምህራን/
፬. መገብተ ምኵራብ /የምኵራብ ሹማምንቶች/
፭. ሊቀ ካህናት
፮. መላሕቅተ ሕዝብ /የሕዝብ ሽማግሌዎች/
፯. ኃጥአን
፰. መጸብኃን ቀራጮች ናቸው፡፡

በሊቃውንት የተጨመሩ ምልክቶች፡-
፱. አንብር ( ⊏ )
፲. ድርስ ( ስ )
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን የማኅበር ጸሎት ሲደርስ በጣዕመ ዜማ ወይም በመዝሙር ማመስገንና መጸለይ የተለመደና የተወደደ ሥርዓት ነው፡፡

Join us on telegram
      
www.tg-me.com/MekuriyaM
#እሑድ
ሆሣዕና በአርያም እያልኵ ዘመርኵለት።
#ሰኞ
በኃጢአት ፍዳ ተይዤ እንዳልቀር መረቀኝ።
#ማክሰኞ
ልቤን አደንድኜ የመረቀኝን እሱ ያልተገባ ጥያቄን ጠየቅኩት።
#ረቡዕ
ልሰቅለው ፈለግኵና እንዴት አድርጌ መያዝ እንዳለብኝ ከጓደኞቼ ጋር ተመካከርኵበት።
#ሐሙስ
ዝቅ አለና እግሬን አጠበኝ።
#አርብ
ሰቀልኩት😔


ይ ሁ ዳ


@MekuriyaM
Forwarded from ቤተ_ልሔም~Bethelhem (Mekuriya Murashe ፩)
​​በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ እንግዳ ቃላት እና ትርጉማቸው ፡-

በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡

#ኪርያላይሶን
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን»ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ «አቤቱ ማረን»ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ«ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡

#ናይናን
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡

#እብኖዲ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው

#ታኦስ
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡

#ማስያስ
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው

#ትስቡጣ
«ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው

#አምነስቲቲ_ሙኪርያቱ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡

#አምንስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

#አምንስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

#ሼር

@MekuriyaM
Forwarded from ቤተ_ልሔም~Bethelhem (፩ Mekuriya Murashe)
#እሑድ
ሆሣዕና በአርያም እያልኵ ዘመርኵለት።
#ሰኞ
በኃጢአት ፍዳ ተይዤ እንዳልቀር መረቀኝ።
#ማክሰኞ
ልቤን አደንድኜ የመረቀኝን እሱ ያልተገባ ጥያቄን ጠየቅኩት።
#ረቡዕ
ልሰቅለው ፈለግኵና እንዴት አድርጌ መያዝ እንዳለብኝ ከጓደኞቼ ጋር ተመካከርኵበት።
#ሐሙስ
ዝቅ አለና እግሬን አጠበኝ።
#አርብ
ሰቀልኩት😔


ይ ሁ ዳ


@MekuriyaM
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
📢መልካም ዜና 🖊️

✔️ለሁላቹም በመጀመርያ እንኳን አደረሳቹ ፣ መንፈሳዊ ቻናል ወይ ግሩፕ ያላቹ wave folder ጀምርናል ከርሶ ሚጠበቀዉ ቻናሎትን ወይ ግሩፕትን ፣ማስመዝገብ፣ ነዉ ለሁላቹም።
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
🏠ስለ ቤተ ክርስቲያን መወቅ ወይም መማር ይፈልጋሉ ለምሳሌ 🏠

🔔እንዴት ሴጣንን ድል መንሳት እችላለሁ?

🔔መናፍቃን ለሚጠይቁን ጥያቄ መልስ እንዴት ላግኝ ?

🔔ስርአት ቤተክርስቲያን ምንድነዉ ለማወቅ ?

🖊️እና ስለ እንደዚ አይነት ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ከስር ያሉትን አማራጭ ይጠቀሙ።
ቤተ_ልሔም~Bethelhem pinned «#እሑድ ሆሣዕና በአርያም እያልኵ ዘመርኵለት። #ሰኞ በኃጢአት ፍዳ ተይዤ እንዳልቀር መረቀኝ። #ማክሰኞ ልቤን አደንድኜ የመረቀኝን እሱ ያልተገባ ጥያቄን ጠየቅኩት። #ረቡዕ ልሰቅለው ፈለግኵና እንዴት አድርጌ መያዝ እንዳለብኝ ከጓደኞቼ ጋር ተመካከርኵበት። #ሐሙስ ዝቅ አለና እግሬን አጠበኝ። #አርብ ሰቀልኩት😔 ይ ይ ሁ ዳ ዳ @MekuriyaM»
​​ሰሙነ ሕማማት
👉 ዓርብ

የስቅለት ዓርብ ይባላል፦
ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።
ዝርዝሩን - @MekuriyaM


መልካሙ ዓርብ ይባላል፡-
ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ሕግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምሕረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።
እኔ እሆንን😪

www.tg-me.com/MekuriyaM
​​​​​​"​​ሕማማተ መስቀል" ተብለው የሚዘከሩት አሥራ ሦስት ሲሆኑ እነዚህም፦
            
1. በብረት ሐብለ መጋፊያና መጋፊያው እስኪጋጠም ድረስ
#የኋሊት_መታሰሩ
2. ከአፍንጫው ደም እስኪውጣ ድረስ 25 ጊዜ በጡጫ
#መመታቱ
3. 65 ጊዜ
#ከግንድ_ማጋጨታቸው
4. 120 ጊዜ
#በድንጋይ_ፊቱን_መመታቱ
5. 365 ጊዜ
#በሽመል_መደብደቡ
6. 80 ጊዜ
#ጽህሙን_መነጨቱ
7. 6666 ጊዜ
#መገረፉ
8.
#አክሊለ_ሦክ በራሱ ላይ መደፋቱ
9. 136 ጊዜ በምድር ላይ
#መውደቁ
10. ሳዶር፡ አላዶር፡ ኤዴራ፡ ዳናትና ሮዳስ በሚባሉ 5ቱ ቅንዋተ መስቀል
#በችንካር_መቸንከሩ
11. መራራ
#ሐሞትን_መጠጣቱ
12. መስቀሉን ተሸክሞ
#መንገላታቱ
13. በመስቀል
#መሰቀሉ ናቸው።


         •➢ ሼር // SHARE

  •✥•🍁 @MekuriyaM 🍁•✥•
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━✧
#​​​​​​አክፍሎት

በሰሙነ ሕማማት ዕለተ አርብ ከስግደት በኋላ ምዕመናን በየቤታቸው ጥቂት ነገር ለቁመተ ሥጋ ቀምሰው እስከ እሑድ /የትንሣኤ ሰዓት/ ይሰነብታሉ፡፡ ይህ አክፍሎት ይባላል፡፡

ከአርብ እስከ ቅዳሜ ሌሊት ለእሑድ አጥቢያ ማክፈል የብዙዎች ነው። አንዳንዶች ግን ከሐሙስ ጀምረው ያከፍላሉ፡፡ ይህም እመቤታችን፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ የጌታን ትንሣኤ ሳናይ እህል ውሃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሣኤ መቆየታቸውን ተከትሎ የመጣ ትውፊት ነው፡፡

ይህንን ትውፊት አስመልክቶ ሄሬ ኔዎስ፣ አውሳብዮስ የተባሉ ጽሕፈት፣ ሐዋርያት በሰሙነ ሕማማት ከደረቅ ዳቦ እና ከትንሽ ውሃ በቀር እንደማይመገቡ እና ከሐሙስ ጀምረው እንደሚያከፍሉ ጽፈዋል፡፡

ይህም ብቻ ሳይሆን ሐዋርያት ሌሎቹንም እንድያከፍሉ እንዲያሳስቡና ከሐሙስ ጀምሮ ያልተቻላቸው ቢያንስ ከአርብ ጀምሮ እንዲያከፍል ማዘዛቸውን ጽፈዋል፡፡ የኛ ቤተክርስቲያን ትምህርትም ይሄው ነው፡፡

ምንጭ፦ ስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት

#ሼር
@MekuriyaM
#ስንት_ነው_ሕማምህ?

 
ይለካል?
ይታያል?
ስፍር ነው?ሚዛኑን ይደፋል?
ከሆነስ ስንት ቁጥር ያልፋል ?
አጥንትህ ለቁጥር ግርፋት ካበጀው
ደምህ ምድ'ር አጥኖ ለመረማመጃ ሕዝቡን ካስቸገረው 
የሾህ ጉንጉን ሰርጾህ ስርህ ከዘለቀው
ይህን ሁሉ ሕመም እያሰቡ ማልቀስ እስከስንት ዕለት ነው
አንድ ቀን ይበቃል?
ሳምንትስ ይበቃል?
ዓመት ቢታመሙ ያርብለት ስቃይህ በምን መጠን ያልቃል
ጠማኝ ስትላቸው ሆምጣጤ ላጠጡት
ደፋ ቀና አድርገው ለተዛበቱብህ   ስቃይህን ላደሩት 
በጥፊ እየመቱ በፌሽታ ታጅበው  ለተቀባበሉህ
ምን ብናዝንላቸው ትምራቸው ይሆን አርብ ለገደሉህ 
ነገሩ
የነሱስ አንዴ ነው ዘመናት አይደለ
ከዘመንም ዘመን
ስበድልህ ያለሁ ትላንት ያላረመኝ የገደልኩኝ ነገን
ትምረኛለህ ወይ?
ያለመጠን ሽጬ ሰውነቴ አንተን በበደል ላጠመቅኩ
ምሕረትህ አለ ወይ
ከተፉብህ በላይ
አንተነት አካሌን እራሴን ላረከስኩ
ትምረዋለህ ወይ ግድንግዱ ልጅህን ዓመት ላሳዘነህ
መስቀል ላይ ስትውል ከመስቀልህ ግርጌ     ለተሰናበተህ
አንተ ደም ስትረጭ
የእናትህ ለጋ ልብ በእንባ ብዛት ሲቀጭ
በአለም ጌጥ ተታሎ አርብህ ለጠፋበት
ምሕረት ያለህ እንደው ልምጣ ከደጃፍህ ልክ እንደበደሌ ከፊት ልቁምበት

      ✍️#ቤተልሔም_ፍቅሬ

@MekuriyaM
እንዲህ ያለ ፍቅር
ዘማሪ ዲያቆን መኩሪያ ሙራሼ|@yemezmurgetemoche|
እንዲህ ያለ ፍቅር

እንዲህ ያለ ፍቅር
ሞቶም የሚያፈቅር
አላየሁም እኔ
ካንተ ውጭ  መድኅኔ

ምኞቴን አንግሼ
ትዕዛዝህ አፍርሼ
ከገነት ተባረርኩ
ወደ ምድር ወረድኩ
          ይቅር ባይ ነህ አምላኬ
          ለመንኩህ ተንበርክኬ

እንዳልጠፋ ዐስበህ
ፍቅር ከላይ ሳበህ
ሞቴን ሻርከውና
አልከኝ ልጄ ሆይ ና
          ይቅር ባይ ነህ አምላኬ
          ለመንኩህ ተንበርክኬ
         ...
ከዘለዓለም መርገም
ነጻ ያወጣኝ የለም
አንተ ግን ጌታዬ
አበስከው እንባዬ
          ይቅር ባይ ነህ አምላኬ
          ለመንኩህ ተንበርክኬ
      ...
ሰይጣንን ጠርቀህ
በደሌንም ፍቀህ
በፊትህ ያቆምከኝ
አምላክ ክበርልኝ
          ይቅር ባይ ነህ አምላኬ
          ለመንኩህ ተንበርክኬ

ዘማሪ ዲያቆን መኩሪያ ሙራሼ
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
🏠ስለ ቤተ ክርስቲያን መወቅ ወይም መማር ይፈልጋሉ ለምሳሌ 🏠

🔔እንዴት ሴጣንን ድል መንሳት እችላለሁ?

🔔መናፍቃን ለሚጠይቁን ጥያቄ መልስ እንዴት ላግኝ ?

🔔ስርአት ቤተክርስቲያን ምንድነዉ ለማወቅ ?

🖊️እና ስለ እንደዚ አይነት ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ከስር ያሉትን አማራጭ ይጠቀሙ።
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
"የፋሲካ" ፆም ስንት ሳምንት አለዉ?
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
"ኢየሱስ ክርስቶስ " ሞቶ በስንት ቀን ተነሳ?
2024/05/04 06:54:22
Back to Top
HTML Embed Code: