Telegram Web Link
"ህብረ-ብሄራዊት ኢትየጵያን ለመፍጠር በትውልድ አስተሳሰብ ላይ ሊሰራ ይገባል " ፕ/ር ታከለ ታደሰ፣ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት
=========================
(ጳጉሜ 2/2013ዓም) ፕ/ር ታከለ ታደሰ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ትናንት ዩኒቨርስቲውን ለጎበኙ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዳይሬክተር ጀነራሎች ፣ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች ባደረጉት ገለጻ "በዩኒቨርስቲው አካባቢን ጤናማ ለማድረግ ችግኝ እንተክላለን፣ ጤናማ የሆነ አተያይ ያለው ዜጋ ለመፍጠር በአስተሳሰብ ላይም እንሰራለን " ብለዋል።

በዩኒቨርስቲው ህብረ-ብሄራዊነትን ለማረጋገጥ እና ለወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ከመላ ኢትዮጵያ ወደ ወላይታ ዩኒቨርስቲ ተመድበው ተምረው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በውጤታቸው አወዳድሮ በመቅጠርና በዩኒቨርስቲው በማስቀረት ጭምር እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል ።

ፕ/ር ታከለ በተጨማሪም ዩኒቨርስቲው እንደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋምነቱ በአገር በቀል እውቀቶችም ተገቢውን ትኩረት መስጠት በመስራት ላይ እንደሚገኝ የገለጹ ሲሆን የዩኒቨርስቲው የተለያዩ ክፍሎች እና የአገር በቀል እውቀቶች ማሳያ የሆነው የወላይታ ባህል ሙዚየምም ተጎብኚቷል።

በሙዚየሙ ውስጥ የወላይታ ብሔርን ባህላዊና ታሪካዊ ትውፊት የሚገልጹ ከ350 የሚበልጡ ቅርሶች እንደሚገኙ እና "ቅርስ ያለው ታሪክ አለው" በሚል መርህ በ2012 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ-ገንደባ ካምፓስ እንደተመሰረተ ለጎብኚዎቹ ተገልጿል ።
2025/07/14 00:35:08
Back to Top
HTML Embed Code: