ቦንጋ ዩኒቨርስቲ የማህበረሰብ አገልግሎትና የአረንጓዴ አሻራን በቅንጅት አጠናክሮ እየሰራ መሆን ገለጸ
***************************************************************************
(ጳጉሜ 1/2013ዓ.ም) ቦንጋ ዩኒቨርስቲ የ2013ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራን ማጠቃለያ ፕሮግራም በዩንቨርስቲዉ ግቢ ዉስጥ ትናንት ያካሄደ ሲሆን በአካባቢዉ በሚገኙ አምስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ ዉስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦቻቸዉ ለህልዉና ዘመቻ ለሄዱ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና ለጤና ጣቢያ ባለሞያዎች ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የኮቪድ መከላከያ በስጦታ አበርክቷል፡፡
የቦንጋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጴጥሮስ ወልደ ጊወርጊስ ዩኒቨርስቲዉ ከባለፉት አመታት ጀምሮ በርካታ ሃገራዊ ብሎም የአካባቢዉን ማህበረሰብ ያማከለ የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡
በተለይም ከወቅታዊ ስራዎች አንጻር ቦንጋ ዩንቨርስቲ ሁሌም ሃገራዊ እና አካባቢያዊ ችግሮችን ሲከሰቱ ለወገኖቹ ፈጥኖ አለሁላችሁ የሚል ተቋም በመሆኑ አሻባሪዉን የትህነግ ወራሪ በሃገራችን በአማራና አፋር ክልሎች ባካሄደዉ ወረራ ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸዉ የሚዉሉ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጋቸዉንም ገልጸዋል፡፡
ከዚህም ዉስጥ የዩኒቨርስቲዉ አመራሮች፣ መምህራንና ሰራተኞች በደም ልገሳና የወር ደሞዛቸዉን የሰጡ ሲሆን በሰሜን ጎንደር አካባቢ ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸዉ ወገኖች 2000 ፍራሰሽ፣ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸዉ 19 ዊልቸር እና 100 እስሊፒንግ ባግ በደባርቅ ዩንቨርስቲ በኩል እንዲደርሳቸዉ ተደርጓል ብለዋል።፡
ከሰሜን ወሎ አካባቢ ተፈናቅለዉና ጉዳት ለደረሰባቸዉ ወገኖች 200 ፍራሽ፣ 50 ብርድ ልብስ፣ 4000 ሊትር ፈሳሽ ሳሙናና 3000 የገላና የልብስ ሳሙና በወሎ ዩኒቨርስቲ በኩል እንዲሁም ከአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች 50 ኩንታል የጤፍ ዱቄት ፣45 ኩ/ል ሩዝ፣ 5 ኩ/ል ስኳር፣ 200 አንሶላ፣ 2000 የገላና የልብስ ሳሙና በሰመራ ዩኒቨርስቲ በኩል እንዲደርሳቸዉ በማድረግ ለወገን ያለዉን ፍቅርና ሃላፊነት በመወጣት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
ትናንት ነሀሴ 30/2013 ዓም በአካባቢዉ ለሚገኙ አምስት ዞኖችና አንድ ወረዳ( ከፋ፣ ቤንች-ሸኮ፣ ምእራብ ኦሞ፣ ሽካ፣ዳወሮ ዞኖችና ኮንታ ልዩ ወረዳ) ዉስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦቻቸዉ ለህልዉና ዘመቻ ለሄዱ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና ለጤና ጣቢያ ባለሞያዎች ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የኮቪድ መከላከያ በስጦታ ሰጥቷል፡፡
አረንጓዴ አሻራን በተመለከተ በዩኒቨርስቲዉ ዉስጥ በሚገኙ ተዳፋት፣ ጫካና ጠፍ መሬት ቦታዎችን አትክልትና ፍራፍሬ፣ ቅመማ ቅመሞችን፣ ቡና፣ የሻይ ቅጠል፣ 375 አይነት የባህል መድሃኒት የሚሆኑ እጽዋቶች፣ እንሰትና የከብት መኖዎችን እያለሙና ጎን ለጎንም ንብ ማነብ፣ ከብት ርባታና ወተት ልማት ስራ እየሰራ ነዉ፡፡
ይህም ዩኒቨርስቲዉን ሳቢና ማራኪ በማድረግ ተማሪዎች እንደፈለጉ እንዲያጠኑ፣ የዩኒቨርስቲዉን ገቢ በማሳደግ እና ለበርካታ የአካባቢዉ ማህበረሰብ ግዜዊና ቋሚ የስራ እድል እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ለአካባቢዉ ማህበረሰቡም ስልጠና በመስጠት በርካታ ቁጥር ያላቸዉ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ችግኞች በመስጠት እንዲያለሙ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ የማጠቃለያ ፕሮግራሙንም በግቢዉ ዉስጥ በአዲስ በተቋቋመዉ የአባይ ልጆች ፓርክ ላይ ችግኞችን በመትከል አጠናቀዋል፡፡
ዶ/ር ጴጥሮስ በመጨረሻም ዩኒቨርስቲዉ በሁለት እግሩ እንዲቆምና ለዚህ ስኬታማ አፈጻጸም እንዲበቃ ሁሌም ከጎናችንና ሆናችሁ አጋርነታችሁን ያሳያችሁን ድርጅቶችና ተቋማት ሁሉ የስኬት ሚስጥሮች እናንተ በመሆናችሁ በቀጣይም አብሮነታችሁ የበለጠ እንዲጠናከር አደራ እላለሁ ብለዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ፕ/ሮ አፈወርቅ ካሱ እንደገለጹት ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከቦንጋ ዩኒቨርስቲ አራት ነገሮችን መማር አለባቸዉ የመጀመሪያዉ ‹በጋራ እንችላለን› የሚለዉን መፈክር በመዉሰድ ሁሉም ተቀናጅቶ መስራት አለበት በቅንጂት ከተሰራ ለዉጥ ከማምጣት እንደሚቻል አሳይቷልና ብለዋል፡፡
ሁለተኛዉ ‹እንችላለን› የሚለዉን ይዞ መሄድ አለበት ብለዋል ምክንያቱም ዩኒቨርስቲዉ በአራት አመት ችሎ አሳይቷልና ብለዋል፡፡
በሶስተኛ ይህ አካባቢ ከአመታት በፊት ተዳፋትና አስቸጋሪ ጫካ ነበር ይህንን ቦታ የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ቡና፣ ሻይቅጠልና ቅመማ ቅመሞችን፣ መኖ እና ሌሎችም በመትከል ለአይን የሚማርክ በማድረግ ለሃብት ማፍሪያ፣ ለተማሪዎች መማሪያ እና ለመምህራን መመራመሪያ አድርገዋል፡፡
አራተኛዉ ‹በእዉቀት ማገልገል› ቦንጋ ዩንቨርስቲ ከማህበረሰቡ ጋር በመሄድ መምህራን በየአካባቢዉ ተንቀሳቅሰዉ በማስተማር በእዉቀት እየደገፉ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ ሁሉም ተቋም ጠንካራ፣ ፈጣን ተምሳሌታዊ ስራዎች አጠናክረዉ መቀጠል አለባቸዉ ብለዋል፡፡

ስምንት ዩኒቨርስቲዎች በ2013 አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በድምሩ ወደ 2 ሚሊየን የሚጠጉ ችግኞች መትከላቸውን ገለጹ
=====================================
(ጳጉሜ 1/2013 ዓም) ዋቻሞ ፣ወራቤ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አሶሳ፣ መቅደላ አምባ፣ ሰላሌ ፣ ጅግጅጋ እና እንጂባራ ዩኒቨርስቲዎች በጥቅሉ ወደ 2 ሚሊዬን የሚጠጉ ችግኞችን መትከላቸውን የገለጹ ሲሆን የ2013 አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ማጠቃለያ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ተካሂዷል።
በ2013 ዓም በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ከ 1 ሚሊየን በላይ ፣ ፣ወራቤ 25,000 ፣ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በሶስቱም ካምፓሶች እና በአካባቢው 270,000 ችግኞችን ፣ አሶሳ 85,000 ችግኞች መቅደላ አምባ 31,100 ሰላሌ ዩኒቨርስቲ 300,000 እንዲሁም
ጅግጅጋ ዩኒቨርስተ 8,000 በድምሩ ወደ2 ሚሊየን ችግኞችን በመትከል በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ማሳካት ችለዋል።
በዛሬው እለት አብዛኞቹ ዩኒቨርስቲዎች የችግኝ ተከላ ማጠቃለያ መርሃ-ግብር ያካሄዱ እና “የኢትዮጵያዊነት ቀን” ያከበሩ ሲሆን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዳይሬክተር ጀነራሎች ፣ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች በወራቤ እና ዋቸሞ ዩኒቨርስቲዎች በመገኘት ዩኒቨርስቲዎቹን የጎበኙ ሲሆን በመዝግያ ፕሮግራሙ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል ።