Telegram Web Link
#አብሽር_ባለ_ዱዓው

- ዛሬም  በዱዓ ነው
- ዱሮም እንዳለፈው
- ነገ-ንም እንደዛው
- ይቀጥላል በዛው
- አሏህ አሸናፊው
- ሰጭ ነው ለለመነው
- ምንም አይሰለቸው
- መስጠት ልማዱ ነው
- ብቻ አንተ ጠይቀው
- ሀጃህን ንገረው
- ግን እሱን እመነው
- እዳጠረጥረው
- ጥሪህ ተሰሚ ነው
-አብሸር ባለ ዱዓው

📝 አብደረህማን ዑመር
          
አንዳንድ ጊዜ ምን ያህል ጠንካራ እንደሆንሽ ለማወቅ በህይወትሽ ውስጥ አስቸጋሪ ጊዜዎችን ማለፍ አለብሽ።
ጀግና ወንድ የሴትን ልጅ ዋጋ ጠንቅቆ ያውቃል ❗️

አንድት ነፍሰ ጡር ሴት ባሏን እንድህ ብላ ጠየቀችው። "ምን የምንወልድ ይመስልሃል  ወንድ ወይስ ሴት?" ባል:-"ምንም ቢሆን ግድ የለኝም ፈጣሪ የሰጠንን በፀጋ እቀበላለሁ ብቻ ጤነኛ ልጅ ይስጠን አንቺም በሰላም ተገላገይልኝ እንጅ፤ነገር ግን ወንድ ልጅ ከሆነ ህግ አስተምረዋለሁ ፣ስፓርት እንድሰራ አደርጋለሁ ሌሎች ጠቃሚ የሆኑ ክህሎቶችን አስተምረዋለሁ።" ሚስት:-"ሃ....ሃ..ሃ እና ሴት ልጅ ብትሆንስ?"
ባል:-" ሴት ልጅ ከወለድን ምንም ነገር ማስተማር አይጠበቅብኝም። ምክንያቱም ሁሉን ነገር የምታስተምረኝ እሷ ነች። እንደ አድስ እንደት መልበስ እንዳለብኝ፣እንደት መመገብ እንዳለብኝ፣ምን መናገር እንዳለብኝ እና እንደለለብኝ የምታስተምረኝ እሷ ነች። ባጭሩ ሁለተኛ እናቴ ትሆናለች።

ምንም የተለየ ነገር ባላደርግ እንደ ጀግናዋ ትቆጥረኛለች። የሆነ ነገር ብከለክላት ሁሌም ትረዳኛለች። ሁልጊዜ ባሏን በመልካም ነገር ሁሉ ከኔ ጋር ታወዳድራለች። እድሜዋ ምንም ያህል ቢሆን ሁልጊዜ እንደ ልጅነቷ እንዳደርግላት ትፈልጋለች። ለእኔ ስትል ከአለም ጋር ትጣላለች እና አንድ ሰው እኔን ቢጎዳ ያንን ሰው በጭራሽ ይቅር አትለውም።"ሚስት:- "ታዳ ሴት ልጃችን ያን ሁሉ ነገር ስታደርግ ወንድ ልጃችን ግን አያደርግም እያልክ ነው?"

ባል:-"አይ እንደዛ ማለቴ አይደለም የኔ ውድ!ምን አልባት እሱም እንድሁ ሊያደርግ ይችላል። ነገር ግን እነዚህን ነገሮች ለማዳበር ይማራል። ሴት ልጅ ግን ከነዚህ ነገሮች ጋር አብረው ይወለዳሉ። ባጭሩ የሴት ልጅ አባት መሆን ለማንኛውም ወንድ ኩራት ነው። "አላት።ሚስት:-"ነገር ግን ለዘለዓለም ከእኛ ጋር አትቆይም"አለች።ባል:-"አዎ ነገር ግን ከእሷ ጋር በልቧ ለዘለዓለም እንሆናለን። እሷ የምትሄድበት ቦታ ምንም ለውጥ አያመጣም"አላት።

ሴት ልጆች ልዩ ስጦታ ናቸው። ቅድመ ሁኔታ ከለለው ፍቅር እና እንክብካቤ ጋር አብረው የሚወለዱ ዘመናቸውን ሁሉ ዋጋ እየከፈሉ ትውልድን የሚያስቀጥሉ ልዩ ፍጥረት ናቸው።

ለእራሱ ክብር ያለው ጀግና ወንድ የሴት ልጅን ዋጋ ጠንቅቆ በማወቅ ለሴት ልጅ ትልቅ ክብር አለው።የተከበረ ወንድ በሴት ልጅ ላይ አይሰለጥንም ፣በጥፋቷ አይፈርጃትም፣ከስህተቷ ዋጋዋ እንደሚበልጥ ያውቃል እና ይሰስትላታል እንጅ አይፈርድባትም። ያዝንላታል እንጅ አይጎዳትም። ያስተምራታል እንጅ አይቀጣትም። እድል ይሰጣታል እንጅ እድሏን አያጠፋባትም። ይቅር ይላታል እንጅ አይረግማትም። ይጠብቃታል እንጅ አሳልፎ አይሰጣትም። ይንከባከባታል እንጅ አያንገላታትም። ክብሯን ይጠብቅላታል እንጅ ክብራን አያሳጣትም።

منقول
ለይለተል  ቀድር

በዘንድሮ ረመዷን ለይለተል ቀድር በጣም ከሚጠበቅበት ነገ ማታ(ሀሙስ ማታ) ነው ምክንያቱም ጁምአና 21ኛው ለሊት ስለገጠመ ስለዚህ ከወዲሁ እንዘጋጅ

(1) إِنَّآ أَنزَلْنَٰهُ فِى لَيْلَةِ ٱلْقَدْرِ
(2) وَمَآ أَدْرَىٰكَ مَا لَيْلَةُ ٱلْقَدْرِ
(3) لَيْلَةُ ٱلْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٍ
(4) تَنَزَّلُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ وَٱلرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْرٍ
(5) سَلَٰمٌ هِىَ حَتَّىٰ مَطْلَعِ ٱلْفَجْرِ

(1) እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ #ሌሊት አወረድነው፡፡
(2) መወሰኛይቱም #ሌሊተ ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?
(3) መወሰኛይቱ #ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡
(4) በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡
(5) እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡  አልቀድር  97:1-5

አላህ(ሱወ) ‹‹መወሰኛቱ ለሊት #ከሺ ወር በላጭ ናት››  ቀድር፡3

🪐🌍ይቺ #ለሊት  በአለማት ውስጥ በአመቱ ምን ምን እንደሚፈጸም ውሳኔ የሚተላመፍበት ናት.

🧎ቀደምት ህዝቦች ከሺ አመት በላይ እድሜ ስለነበራቸው  ይህ ህዝብ ያለችውን ትንሽ እድሜ ከነሱ ጋር ለማስተካከል የተሰጠ እድል ነው.

📣ነብዩ(ሰዐወ) እንዲህ  ያሉትም ለዚህ ነዉ ‹‹ የተባረከዉ ወር መጣላቹ … በርሱም አንዲት #ሌሊት አለች ከአንድ ሺ ወር በላይ ዋጋ ያላት፣   የዚችን #ሌሊት ትሩፋት መጎናፀፍ ያልቻለ፣ (ሌላ በጎ እድልም)  እርም   ይሆንበታል››

🧎በተጨማሪ ነብዩ(ሰዐወ)  ‹‹ለሰላት ቆሞ ሀያሉዋን #ለሊት በኢባዳ በኢማን ከልብ ምንዳ አገኛለሁ ብሎ ያሳለፋት ሁሉም ያለፈ ወንጀሉ ይማሩለታል››
አሰላሙ አለይኩም ወሯህመቱሏሂ ወበረካቱህ  ዛሬ የምትመለከቱትን ቻሌንጅ ይዘን መተናል። ቻሌንጁ የጀመርነው  ከዚህ በፊት ለ62 እህቶች ጅልባብ ማሰባሰብ ስራ ጀምረን ነበር። ያንን ማሟላት ስላልቻልን የሁላችንም ግዴታ በመሆኑ ሁላችንም በጋራ  እናሟላው ዘንድ ነው።
ኢንሻ አላህ ሁላችንም ይህንን ቻሌንጅ እንቀላቀል!!


http://www.tg-me.com/nikab_jilbab_group
አስርቱ ውድ ሌሊቶችና ለይለተል ቀድር


ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸው እንዲህ ብለዋል።

«በአላህ አምኖና ከሱ ምንዳንም አስቦ የረመዷን አስርት የመጨረሻ ቀናቶችን የቆመ (በኢባዳ ህያው ያደረገ) በርግጠኝነት ለይለተል ቀድር አገኘ ብለን ቁርጥ አድርገን መናገር እንችላለን።

📕 فتاوى أركان الإسلام 429

ልብ ያለው ልብ ይበል!!


በትንሽ ልፋት ብዙ አጅር ማለት ይህ ነው። አስር ቀን ብቻ በኢባዳ አሳልፈህ ከሰማንያ ሶስት አመታት በላይ የሆነ የኢባዳ አጅር ማግኘት የምትፈልግ ከሆነ እነዚህን አስር ሌሊቶች ሳትዘናጋ በመልካም ስራ ህያው አድርጋቸው። ይህንን ታላቅ ትርፋማ እድል በከንቱ አያምልጥህ። ምናልባትም ይህ የእድሜህ የመጨረሻው አሽረል አዋሒር ሊሆን ይችላልና በአግባቡ ተጠቀምበት።

=
Sadik_Ibnu_Heyru
ለይለተል ቀድር የመደበቁ ጥበብ
አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
የለይለተል ቀድር ሌሊት በእርግጠኝነት እንዳናውቀው የተደረገበት፦

◤ጥበብ
◤ምክንያት

🎙 አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

=
በዱአው ውስጥ ያወሳህ
መውደድ ከሚጠበቅበት በላይ ይወድሃል
ከዚ በላይ ውዴታ በምንም ሊገለፅ አይቻልም
አንድ ሷሊሕ ሰው ተጠይቁ፡-** 
"ለምን ይህን ያህል ሱጁድ ያስረዝማሉ? ብዙ የሚያስጨንቃችሁ ነገሮች አሉ?" 
እሳቸውም፡- 
"አይደለም። ነገር ግን፣ ብዙ ወንድሞች አሉኝ። በቂያማ ቀን እርስ በርስ እንረዳዳለን ብለን ቃል ገብተናል። ይህ ወንድማማችነታችን፣ በእነዚህ ወርቃማ ቀናት ውስጥ በጣም አስፈላጊ ነው። እያንዳችንም ለሙስሊም ወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችችን ዱዓ እናድርግ። 

ነብዩ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንደተማሩን፡- 
"ማንኛውም ሰው ለወንድሙ  እሱ በሌለበት (በስውር) ዱዓ ቢያደርግ፣ ለእሱ ተመድቦ የተሾመው መልኢካ፣ 'ለአንተም ተመሳሳይ ይሁንልህ' ይላል። መልአኩም ለዚያ ዱዓ 'አሚን' ቢል፣ ዱዓው የመስማት ባለቤት ይሆናል።" 

አቡ ደርዳእ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንዲህ አሉ፡- 
"እኔ ስጂድ ውስጥ ለ70 ወንድሞቼ ስማቸውን ጠቅሼ ዱዓ አደርጋለሁ።" 

ይህ ከባድ ነገር ነውና በደንበረ አስተውሉት። 
ይህ በውስጡ ከራስ የወንድምን ጥቅምን  በቅንነት ማስበለጥ የኢስላማዊ ወንድማማችነት መገለጫ ተግባር አንዱ ነው።
አሁንም አንዱ ሷሊሕ ሰው እነዲህ እንዳለ ተዘግቧል፡- 
"ማን እንደ ወንድም ያለ ነገር አለ?! ስትሞት፣ ቤተሰቦችህ ርስትህን ይካፈላሉ፤ እሱ ግን ለአንተ በስውር ያለቅስልህና ዱዓ ያደርግልሃል። አንተ የዛኔ (ቀብር ውስጥ) ከመሬት ሥር  ነህ።
በእነዚህ በረከት የተሞሉ ሌሊቶች፣ ሁላችንም ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን ዱዓ እንወጥር። ምናልባት አንድ ሳሊሕ ወንድም ወይም ዱዓዋ ተቀባይነት ያላት እህት ትኖራለች እና በዱዓ እንጠናከር።  እርስ በርስ ዱዓ እንደራረግ፣ እናም በዱዓችሁ ውስጥ አስታውሱኝ። ለማለት ነው።
#ሀጃህን ሁሉ ለአላህ መንገር
አንዳንዴ ሰው ፊት አውጥተህ የማተነፍሰው የውስጥ ስብራት ይኖርሀል በዱንያ ውጣ ውረድ ይደክምሀል የሆነ መፍትሄ ያጣህለት ምትነግረው የጠፋለት ጥያቄ በውስጥህ አለ ።
ያኔ መሸሻህ እሱ ብቻ እንደሆነ አውቀህ ከልብህ በቤቱ ትማፀነዋለህ ያ ሩቅ የመሰለህ ጌታህ ያ አልፈታ ያለህ ችግር ያ ውስብስ ያለብህ ቋጠሮ ሁሉ በልኩ ሲቀና ባላሰብከው መንገድ ሲስተካከል ታየዋለህ ዱዓህ ምላሽ አጥቶ ቢቆይ እንኳ ለውስጥ ሰላምን ታገኛለህ የማታውቀው የቀረልህ ብዙ ይኖርሀል ባለህ ተብቃቅተህ በእርጋታ እንድትኖር ይረዳሀል ።

#አላህዬ ብለህ አምረርረህ አልቅስ ወንጀሌ የማያስጠጋ ብኩን ባርያህ ብሆን እንኳ በራህመትና በእዝነትህ ሸፍነኝ በለው ።

#የለመኑትን የማይነሳ የጠየቁትን የማይረሳ ታላቁ ጌታህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ የሚል የብስራት ዜና ነግሮሀልና

( وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ )
( ለምኑኝ እቀበላችኋለው )
የሚገርም ፈገግ የሚያደርግ ጥያቄ


አንድ ክርስቲያን ልጅ
ሙስሊም ሴቶች ገነት አይገቡም ባላቸውን ገነት ለማስገባት ነው ሚለፉት ይባላል አንዴት ነው ብሎ ጠየቀ ምን ልበለው eski ሃሳብ ስጡ
እኛ ሙስሊሞች የማሪያም እና የኢየሱስ ወዳጅ እንጂ ጠላት አይደለንም!!
🌾 ስለዘካተል-ፊጥር አጭር ማስታወሻ🌾

1⃣ ትርጉም:- ዘካተል-ፊጥር(ሶደቀተል-ፊጥር):- የረመዷንን ወር ፆም በመጨረስ ግዴታ የሚሆን ሶደቃ(ምጽዋት) ነው።

2⃣ የመደንገጉ ሒክማ(ጥበብ)

💡ለፆመኛው ሰው በረመዳን ፆም ላስገኛቸው ያልተገቡ እና ውድቅ ንግግሮች ማጥሪያ

💡ለሚስኪኖች በጎ ለመዋል እና የዒድ ቀን ከልመና እንዲብቃቁ ማድረግ

💡የዒዱን ቀን ደስታ አብሮ ለመጋራት

💡አላህ  የረመዷንን ፆመ ለመጨረስ ስላበቃን ለአላህ ምስጋናን የምንገልፅበት

3⃣ ሑክሙ(ሸሪዐዊ ድንጋጌው)

✔️ዘካተልፊጥር መስጠት ግዴታ ነው።

ከዐንደላህ ቢን ዑመር(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው እንዲህ አለ:-
"የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘካተል-ፊጥርን ግድ አደረጉ። ከተምር አንድ ዘንቶ፣ ወይም ከገብስ አንድ ዘንቶ(ግድ አደረጉ)።  ሙስሊም የሆኑ ባሪያም ጨዋም ላይ፣ ሴትም ወንድም ላይ፣ ትንሽም ትልቅም ላይ (ግድ አደረጉ)። ሰዎች ወደ(ዒድ) ሶላት ከመውጣታቸው በፊት እንድትሰጥም አዘዙ።"(ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል።)

4⃣ ግዴታ የሚሆንባቸው ሰዎች

▫️የዒድ ለሊት እና ቀን ለራሱ እና በርሱ ላይ መቀለብ ግዴታ ከሚሆኑበት ሰዎች ቀለብ በላይ ያለው ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

5⃣ ማውጣት ግድ የሚሆነው ከማን ነው?

ከራሱ እና በርሱ ስር ላሉ የሚቀልባቸው ሰዎች(እንደ ሚስቶች፣ ልጆች...)

ሆድ ውስጥ ላለ ጽንስ ማውጣት የተወደደ ነው።

6⃣ የሚወጣው ምንድን ነው?

✔️ዘካተል-ፊጥር የሚወጣው በአካባቢው በአብዛኛው ለምግብነት ከሚውል እህል ነው።

የእህሉን ዋጋ በገንዘብ ቀይሮ መስጠት አያብቃቃም።

7⃣ የሚወጣው የእህል መጠን

ለእያንዳንዱ ሰው አንዳንድ ዘንቶ

ዘንቶ:- በመካከለኛ ሰው እጅ አራት እፍኝ🤲 የሚይዝ መስፈሪያ ነው።

8⃣ ለማን ነው የሚሰጠው?

🔖 በሚያወጣው ሰው አገር ላሉ ደሀ እና ሚስኪኖች

9⃣ የሚወጣበት ጊዜ

📍በላጩ ጊዜ የዒድ ቀን ጧት ከዒድ ሶላት በፊት ነው።

📍ከዒድ አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀደም ብሎ መስጠት ይቻላል።

🕌 ከዒድ ሶላት ቡኃላ ማዘግየት አይፈቀድም።
ዘካ የሚሰጠው ለምን አይነት ሰው ነው?
~~~
የዘካ ባለሐቆች 8 ናቸው። በቁርኣን እንዲህ ተዘርዝረዋል:–

(إِنَّمَا الصَّدَقَاتُ لِلْفُقَرَاءِ وَالْمَسَاكِينِ وَالْعَامِلِينَ عَلَيْهَا وَالْمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمْ وَفِي الرِّقَابِ وَالْغَارِمِينَ وَفِي سَبِيلِ اللَّهِ وَابْنِ السَّبِيلِ ۖ فَرِيضَةً مِنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ)

"ግዴታ ምጽዋቶች (የሚከፈሉት) ለድሆች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች፣ ልቦቻቸውም (በእስልምና) ለሚለማመዱ፣ ጫንቃዎችንም (በባርነት ተገዢዎችን) ነፃ በማውጣት፣ በባለ እዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሰሩ፣ በመንገደኛም ብቻ ነው፡፡ ከአላህ የተደነገገች ግዴታ ናት፡፡ አላህም አዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡" [አተውባ: 60]

መጠነኛ ማብራሪያ.....

① ድሃ ማለት:– ለመኖር (ልብሱ፣ ጉርሱ፣ ትዳር ለመመስረት፣ ለመማር፣) ምንም ነገር የሌለው ወይም ትንሽ ነገር ያለው ማለት ነው። እነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት ዘካ ሊሰጠው ይችላል።

② ምስኪን ማለት: – ለመኖር የሚሆን ነገር በተወሰነ መጠን ያለው ሲሆን የሚበቃው ግን አይደለም።

③ ዘካ ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች:– ዘካ እንዲሰበስቡ በመሪ የሚላኩ ሰዎች ናቸው። ዘካ ሶስት ነገሮችን ይፈልጋል። መሰብሰብ፣ መጠበቅና ማከፋፈል። በሶስቱም ዘርፍ ላይ የሚሰማሩ ሰራተኞች ሃብታም ቢሆኑ እንኳ ዘካ ይሰጣቸዋል።
ልብ በሉ! ለዚሁ ስራ በመንግስት የሚሾሙትን እንጂ የግለሰቦች ወኪሎችን አይመለከትም። ደሞዝተኛ ሰራተኛም እዚህ ውስጥ አይገባም።  

④ ልቦቻቸው (በእስልምና) የሚለማመዱ ማለት ሁለት አይነት ናቸው።

አንደኛ፡- ሙስሊም ያልሆነ ሰው ነው። ሙስሊም ባይሆንም ለተሻጋሪ ፋይዳ ሲባል ነው ሊሰጠው የተፈቀደው።
– ቢሰጠው ይሰልማል ወይም ሌላ ፋይዳ ይገኝበታል ተብሎ ተስፋ የሚጣልበት ከሆነ፣
– የሚያደርሰው ጉዳት ኖሮ በዚህ ማስቆም የሚቻል ከሆነ

ሁለተኛ፡- ሰለምቴ ነው።
– በዲኑ እንዲጠነክር ወይም ለሌላ ሰው መስለም/ መጠንከር ሰበብ ይሆናል ተብሎ ከተገመተ
– በሙስሊሞች ላይ ጉዳት የሚያደርስ ሆኖ በዚህ ማስቆም የሚቻል ከሆነ። [መጅሙዑል ፈታዋ፣ ኢብኑ ተይሚያ: 28/290]

⑤  እራሳቸውን ከአሳዳሪዎቻቸው በመግዛት ነፃ ለማውጣት የሚጣጣሩ ባሪያዎች ዘካ ከሚገባቸው ናቸው።

የተጠለፉ/ የተማረኩ ሙስሊሞችን ማስለቀቅም ከዚሁ ውስጥ ይካተታል።

⑥ ባለ እዳ:– የተጣሉ ሰዎችን ለማስታረቅ አስቦ እዳ የገባ ሰው ሃብታም እንኳን ቢሆን ዘካ ሊሰጠው ይችላል።
በራሱ ጉዳይ እዳ የተጫነው ከሆነ በኑሮው ባይቸገር እንኳ እዳውን ለመክፈል ሊሰጠው ይችላል።

⑦ በአላህ መንገድ የሚሰራ ማለት:– ለጂሃድ ዘማች ማለት ነው። ለትጥቅ፣ ለስንቅና አጠቃላይ ዝግጅት ዘካ ይሰጣል።

⑧ መንገደኛ:– አገሩ መግቢያ ከዘካ ገንዘብ ይሰጠዋል።
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 26/2013)
🌙ረመዳን 26⭐️

...የረመዳን 27ተኛ ለሊት ለይለቱል ቀድር ይበልጥ የሚከጀልባት ለሊት..

▪️በለይለተል-ቀድር የሚሰራ ዒባዳ ከ1 ሺህ ወራቶች (83 ዓመት) ዒባዳ የሚበልጥ ሲሆን ከነቢዩ (ሰዓወ) ሰሀባዎች ውስጥ፥  ሰይዱና ዑመር(ረዓ)፣ ኢብኑ ዐባስ ፣ኡበይ ኢብኑ ከዕብ፣ ሙዓዊያ፣ ሁዘይፋና ሌሎችም( አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው)  ለይለተል-ቀድር 27 ሌሊት ላይ ናት ይሉ ነበር!

⚡️ይህች የረመዳን 27ተኛ ለሊት ዛሬ ሰኞ ምሽት ላይ ናት፡

በዚህች ለሊት ሁላችንም ለዱኒያችንም ለአኼራችንም ዱዓ ልናደርግ፣ ለሀገራችንም ሆነ ለመላው አለም የሰው ልጆች ዱዓ የምናደርግበት ሊሆን ይገባል::

ለሊቱን በኢባዳ ማሳለፍ ፣ይበልጥ ወደ አላህ ተናንሰን መቃረብ እና ማሃርታውን መጠየቅ ፤ከአሳማማሚው የጀሀነም እሳትም እንዲታደገን ጌታችንን መማፀን አንዘንጋ!

🤲አላህ ወንጀላችን ይማረን ለይለቱል ቀድርን ይወፍቀን 🤲
27ኛዋ ሌሊት!
~
ስለ ለይለተል ቀድር የትኛውም ቁጥር ቢገመት የ27ኛዋ ግን ይለያል። ከየትኛውም ሌሊት በተለየ ከፍ ያለ ግምት ይሰጣታል። ይቺን ሌሊት ፈፅሞ ዘንግቶና ቸልተኛ ሆኖ ማሳለፍ አይገባም። ስለዚህ ለክብደቷ የሚመጥን ትጋት ይኖረን ዘንድ እንዘጋጅ። ሶላት፣ ቁርኣን መቅራት፣ አዝካር፣ ድምፅን ዝቅ፣ ቀልብን ስብር አድርጎ ደግሞ ደጋግሞ በዱዓእ የሙጥኝ ማለት ያስፈልጋል። ኢኽላስ እና ኹሹዕ መዘንጋት የሌለባቸው ትጥቆች ናቸው። ባይሆን የሱብሕን ነገር አደራ! ብልጥ ነጋዴ ትርፍ ፍለጋ ወረቱን አይጥልም።
🌺. ቀነ ጁሙዓዎ ጥሩ አሻራን ጥሎ እንዲያልፍ ያድርጉ!...

. ስገዱ!
. ዚክር ሶለዋት አብዙ!
. ሶደቃ ስጡ!
. የተራበን አብሉ!
. ቁርኣንን አንብቡ!
. አላህን አጥሩ ምህረትንም ለምኑ!

🌙. ይህች ውብ ቀን ዳግም አትገኝምና!!!

      ❤️. ሰሉ አለ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)
         😊. ውብ የዒባዳ ጁምዓ ይሁንላችሁ. 😍

➧. . #ረመዳን_28
ነገ እሁድ ዒድ ነው።
ሰበር ዜና!!!

በሳኡዲ ዛሬ ጨረቃ በመታየቱ ነገ እሁን የሸዋል የመጀመሪያ ቀን እና ዒድ ይሆናል።`
2025/07/04 15:45:47
Back to Top
HTML Embed Code: