Telegram Web Link
ገንዘባችሁን ምን ላይ ብታውሉት ያዋጣል?

ያላችሁን ማንኛውም መጠን ገንዘብ በቤታችሁ  ከማስቀመጥ እስከ የውጪ ምንዛሬ ገዝቶ እስከመሸጥ ያሉ 7 አማራጮችን በምሳሌ እና በምክንያት እንመልከት!

አንድ ሚሊየን ብር ያለው ሰው ምን ቢያደርግም ሚሊየን ብሩን ከዋጋ ማጣት ማትረፍ ይችላል?

የምትጠቀሙበት ትንታኔ https://youtu.be/n-PuA3jszpM
ከIMF ጋር ሪፎርም ውስጥ ከገባ በኋላ የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ትሪሊየን ብርን ለመጀመሪያ ጊዜ በበጀት መልክ ተዋውቋል!

ለማስታወስ ሰኔ 2016 ከሪፎርም በፊት (ሪፎርሙ የጀመረው ሃምሌ ነበር) የቀረበው በጀት 971 ቢሊየን ብር ነበር ከወራት በኋላ ሪፎርሙን ተከትሎ የበጀት ክለሳ በማድረግ ወደ 1.4 ትሪሊየን ብር አደገ!

መንግስት ለ2018 የሚሆን 1.93 ትሪሊን ብር በጀት አቅርቧል!

ከዚህ ውስጥ 1 ትረሊየን ብሩን ከግብር ብቻ እሰበስበዋለው እያለ ነው!

የዚህ በጀት መጠን ማደግ እና ለ2 ትሪሊየን ብር መጠጋቱ እድሉ ብዙ ነው!

መንግስት ከግብር ብቻ ሊሰበስብ ያሰበው 1 ትሪሊየን ብር ደግሞ ስጋቱ ብዙ ነው!

ያሰበውን ገቢ ካልሰበሰበ ቀጣይ እርምጃው ምን ሊሆን ይችላል የሚለው አሳሳቢ ነው!

የዚህን በጀት እድል እና ስጋት እንዲሁም በቀጣይ ሊከሰት የሚችል አካሄድን በሰፊው እንመልከተው….https://youtu.be/lUnHeZifpTw
የ2018 በጀት ዝርዝር ማብራሪያ.pdf
1.8 MB
የ2018 በጀት ዝርዝር ማብራሪያ ሰነዱን ማንበብ ለምትፈልጉ አስቀምጫለሁ!

#ለመረጃ፡ በ 2018 ነዳጅ እና ስኳር የተጨማሪ እሴት ታክስ እንደሚጣልባቸው የበጀት ረቂቁ ያሳያል!
የፌደራል የ2018 በጀት 21% ድርሻ ከውጭ እርዳታ እና ብድር የሚጠበቅ ነው!

የውጭ እርዳታ እና ብድር የሀገር ውስጥ በጀት አካል የሚደረግበት አመክንዬ.....

የሚጠበቅ የውጭ እርዳታ እና ብድር ካልተገኘ መንግስት ምን አይነት አማራጭ ሊወስድ ይችላል?

ኢትዮጵያ ከየትኞቹ ዓለም አቀር ተቋማት እና ሃገራት እርዳታ እና ብድር እየጠበቀች ነው?

በዝርዝር እንመልከተው...https://youtu.be/e37o-4RnORo
አዲሱ የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ.pdf
864.3 KB
#ለመረጃ፡ አዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ሲጸድቅ ከ10,000 ብር በላይ ግብይትን በጥሬ ገንዘብ መፈጸም የሚያስቀጣ ይሆናል ተብሏል።

#ለምሳሌ፦ የ15,000 ብር ግብይት በጥሬ ገንዘብ ቢፈፀም ለነጋዴው፣ ከ10 ሺህ ብር በላይ ያለው በወጪነት አይያዝም፣ ለተቀባዩ ደግሞ ከ10,000 በላይ ያለው ቀሪ 5,000 ብር እጥፍ ማለትም 10,000 ብር ይቀጣል እንደማለት ነው።

የገንዘብ ሚኒስቴር የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያ የመጀመሪያ ረቂቅ አዘጋጅቷል! የረቂቁን የአማርኛ ቅጂ ማንበብ ለምትፈልጉ....
በ2018 መጀመሪያ አንድ ሊትር ቤንዚን 216 ብር.....ድጎማ ይነሳል! ቫት ይጨመራል!

የነዳጅ ድጎማ ይነሳል! የነዳጅ ድጎማ ሲነሳ የአንድ ሊትር ዋጋ ምን ያህል ይሆናል?

ነዳጅ ታክስ ይጣልበታል፡ በነዳጅ ላይ ቫት እና ኤክሳይዝ ታክስ ሲጨመር የአንድ ሊትር ዋጋ ምን ያህል ይሆናል?

በ2018 ነዳጅ በዓለም ዋጋ ሲሸጥ እና ቫት እና ኤክሳይዝ ታክስ ሲጨመርበት በሚፈጠረው የነዳጅ ዋጋ ለውጥ ኢኮኖሚው ምን ይጠብቀዋል?

በዝርዝር እንመልከተው....https://youtu.be/MBEg2E1z7yY
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ስራ የሚጀምረው የውጭ ባንክ! Kenya Commercial Bank (KCB)!

የየትኛውን ሃገር ባንክ ጠብቀን የየትኛው ሃገር ባንክ ፍላጎቱን ይዞ ኢትዮጵያ ድረስ መጣ?

ከባንኩ ልምድ በመነሳት በየትኛው መስፈርት ኢትዮጵያ ውስጥ የመሳተፍ እቅድ እንደሚኖረው እንመልከት!

ስለ KCB ባንክ ፈተሽ እናድርግ!https://youtu.be/VOrwwkgCyv4?si=H9FkvAHS5KBnMRhD
ድሃ መሆን ከባድ ብቻ ሳይሆን ውድ ነው! Being Poor Is Expensive!

ድህነት ውስጥ ያለ ሰው ድሃ መሆን ምን ያህል ውድ መሆኑን ይረዳል!

መንግስት ድሃ ዜጎቹ ያሉበትን ድህነት ማወቅ አለበት! የድሆች መንግስት ድሃ ነው!

ከአዲሱ መነጋገሪያ ፊልም Straw በመነሳት ሃሳቡን በምሳሌ እንመልከተው!https://youtu.be/gSE-2DjikQI
የትምህርት ቤት ክፍያ እስከ 65% ይጨምራል! ፍታዊነት፤ ስጋት፤ አማራጭ እና ቢሆን የሚሻለው…..

አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ 1,585 የግል ትምህርት ቤቶች መካከል 1,227 ማለትም 77 በመቶዎቹ ለ2018 እስከ 65 በመቶ የክፍያ ጭማሪ እንዲያደርጉ ተፈቅዷል!

የተዘጋጀው ደንብ ቀሪዎቹ 23 በመቶዎቹ ማለትም 358 የግል ትምህርት ቤቶች ክፍያ የመጨመር ተራቸው በ2019 ነው!

ለትምህርት ቤቶቹ ደረጃ ተሰቷል! በደረጃ የጭማሪ ልዩነት ምን እንደሚመስል እንመልከት!

የልጆቹ የትምህርት ቤት ክፍያ በግማሽ የጨመረበት ወላጅ ምርጫው ምንድን ነው?

በዝርዝር የጥናቱን ውሳኔ እንመልከተው…https://youtu.be/nUAtp0PbgkQ
ዘመናዊ እና ጥራታቸውን የጠበቁ አፓርትመንት ቤቶችን በተለያዩ ቦታዎች ገንብቶ በማሥረከብ የሚታወቀው #ቴምር_ሪልእስቴት አሁን ደሞ በመሀል ፒያሳ ከ ፍሬንድሺፕ ፓርክ አጠገብ የመጨረሻው እና 3ኛው ብሎካችን ለሽያጭ አቅርበዋል!

ከዚ ቀደም አነስተኛ ካሬ ያላቸው ቤቶችን ፈልጋችሁ አልቆባችሁ ለነበራችሁ ደንበኞች ለናንተ የሚሆኑ ተመጣጣኝ የካሬ አማራጮችን ማለትም 63 ካሬ ከ 690ሺ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ ይዘን መተዋል!

በተጨማሪም በመሀል ፒያሳ የግድ ሱቆችን 900,000ሺ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ ሽያጭ ላይ ናቸው!

👉ለበለጠ መረጃ  እና ሳይት ጉብኝት
በ 09-97-33-56-50 ይደውሉ
አዲሱ ግብር የሚከፈልበት የደሞዝ መጠን! የኢሠማኮ አማራጭ ቁጥሮች!

በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲቀርብበት የነበረው የሰራተኞች የደሞዝ ግብር መጠን በገንዘብ ሚኒስትር ረቂቁ ቀርቦ ውይይት ላይ ነው!

ነገር ግን በመንግስት እየቀረበ ያለው የደሞዝ ግብር መጠን (ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ደሞዝ) እና የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ያቀረቡት መነሻ የሰማይ እና የምድር ያህል ልዩነት አለው!

የተቀመጠውን የደሞዝ እና የግብር መጠን በዝርዝር ከነምክንያቱ እንመልከተው....https://youtu.be/dAydraFIzwk
#ለመረጃ፡ የግንቦት ወር የዋጋ ንረት ከሚያዝያ ወር ጋር በተመሳሳይ 14.4% ሆኖ ተመዝግቧል ሲል መንግስት አሳውቋል!
ኢትዮጵያ በኑሮ ውድነት በአፍሪካ ቀዳሚ ደረጃ ይዛለች።

በአፍሪካ በ2025 ለኑሮ በጣም ውዷ ሀገር ኢትዮጵያ ሆነች! ከነበረችበት 4ኛ ደረጃ ወደ 1ኛ ደረጃ ወርዳለች! 2025 Cost of Living Index!

https://youtu.be/S2UAUHU1BGQ
አትሸወዱ! ቁጥሮች ድሃም ሃብታምም ያደርጋሉ! Purchasing Power Parity

አንዳንድ የኢኮኖሚ ለውጥ መለኪያ ቁጥሮች የህዝቡን ጓዳ በቅርበት አያውቁትም!

ኢኮኖሚክስ የሌላ ሀገር ነዋሪዎች አንድን ቁስ ለመግዛት ከሚያወጡት ወጪ ኢትዮጲያዊያን በሃገራቸው ለተመሳሳይ ቁስ የሚያወጡት የተለየ እንዲሆን አይመክርም ነበር…..

ነገር ግን በሸቀጦች ዋጋ እና በኑሮ ውድነት ኢትዮጲያዊ የሚፈተነው ከሌሎች ሀገራት ዜጎች የተለየ ሊሆን ይችላል!

ምክንያቶቹ ከምትመለከቱት የተለየ ናቸው! በዝርዝር እንመልከታቸው! https://youtu.be/0cl9lfwLR7c
2025/07/08 20:23:16
Back to Top
HTML Embed Code: