🔴 ዓሹራን መፆም እንዳንዘነጋ
ቡኻሪይ እንደዘገቡት ዐብዱሏህ ኢብን ዐባስ ረዲየሏሁ ዐንሁ የዓሹራን ጾም አስመልክተው ሲናገሩ የሚከተለውን ብለዋል ""ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደ ዓሹራ ቀንና እንደ ረመዷን ወር ሆን ብለው “በጉጉት ጠብቀው” ሲጾሙ አይቻቸው አላውቅም! ብለዋል።
ነቢዩም(ሰዐወ) "የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ከአላህ እጠብቃለው" ብለዋል።
📍 ዓሹራን መጾም የቱን ወንጀል ነው የሚያስምረው??
ዓሹራን መጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል እንደሚያሠርዝ ተጠቅሷል። ይህ ምህረት ጥቃቅን ወንጀሎችን ነው የሚመለከተው ወይስ ከበባዶችንም ጭምር የሚለውን አስመልክተው ኢማም አንነወዊይ የሚከተለውን ብለዋል:-
" የዓረፋ ጾምም ይሁን የዓሹራ ሌሎችም ወንጀልን ያስምራሉ የተባሉ ኢባዳዎች ጥቃቅን የሚባሉ ወንጀሎችን በሙሉ ያሰርዛሉ ጥቃቅን ወንጀሎች የሌሉበት እንደሆነ በምትኩ መልካም ስራዎች ይመዘገቡለታል አላህ ዘንድም ያለው ደረጃ ይጨምራል ጥቃቅን ወንጀሎች የሌሉበት ሆኖ አንድ ወይም ከዛ በላይ ከባድ ወንጀል ያለበት እንደሆነ ወንጀሉን ያቀለዋል ብለን አሏህ ላይ ተስፋ እናደርጋለን""
📍 ቀዷ ያለበት ሰው ዓሹራ መጾም ይችላልን?
እንደ ዓሹራ ያሉ ሱና ጾሞችን ያለምንም ጥርጣሬ ለመጾም ያለብንን ቀዷ ፈጠን ብለን ማውጣቱ ይመረጣል።ቀዳውን ሳይጾም ወቅቱ የሚያልፍ የሱና ጾም የደረሰበት ሰው በቀጣይ ለቀዳ ሰፊ ጊዜ እስካለው ድረስ ፈርዱን ቀዳ ሳያወጣ ሱና ቢጾም ችግር አይኖረውም።
የዘንድሮ ዓሹራ የሚሆነው ከነገ ወዲያ ማክሰኞ ሙሐረም 10 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ሀምሌ 9 2016 ወይም July 16 ሲሆን ከፊቱ ሰኞን ወይም ከኋላ ረቡዕን አብሮ መጾም ተገቢ ነው።
አላህ ይወፍቀን!

በጁምዓ ቀን ቀደም ብሎ መገኘት ያለው ትሩፋት!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إِذَا كَانَ يَوْمُ الْجُمُعَةِ، وَقَفَتِ الْمَلَائِكَةُ عَلَى بَابِ الْمَسْجِدِ يَكْتُبُونَ الْأَوَّلَ فَالْأَوَّلَ، وَمَثَلُ الْمُهَجِّرِ كَمَثَلِ الَّذِي يُهْدِي بَدَنَةً ، ثُمَّ كَالَّذِي يُهْدِي بَقَرَةً، ثُمَّ كَبْشًا، ثُمَّ دَجَاجَةً، ثُمَّ بَيْضَةً، فَإِذَا خَرَجَ الْإِمَامُ طَوَوْا صُحُفَهُمْ وَيَسْتَمِعُونَ الذِّكْرَ﴾
“በጁምዓ ቀን በመስጂድ መግቢያ በር ላይ የሚቆሙና ሰዎችን ቅድሚያ በቅድሚያ (እንድአመጣጣቸው) የሚመዘግቡ መላዕክቶች አሉ። በመጀመሪያው ሰዓት የመጣን ሰው ግመል ሰደቃ እንዳቀረበ ይቆጠራል። ከዛ ቀጥሎ ባለው ግዜ የመጣ በሬ እንዳቀረበ ይቆጠራል። ከዛ ቀጥሎ ባለው ግዜ የመጣ ሰው በግ እንዳቀረበ ይቆጠራል። ከዛ ቀጥሎ ባለው ግዜ የመጣ ሰው ዶሮ እንዳቀረበ ይቆጠራል። ከዛ ቀጥሎ ባለው ግዜ የመጣ ሰው እንቁላል እንዳቀረበ ይቆጠራል። ከዛ ኢማሙ ለኹጥባ ሚንበር ላይ ሲወጣ መዝገባቸውን በመዝጋት ምክሩን ለማዳመጥ ይቀመጣሉ።”
ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 929

የሩዋንዳው የ«እኛ» እና የ«እነርሱ» አስገራሚው የማንነትና የትርክት አጀማመር
🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈🎈
በሩዋንዳው የጅምላ ጭፍጨፋ(የዘር ፍጅት) መታሰቢያ ማዕከል ካሉ መረጃዎች እንደተረዳሁት «ቱትሲ» እና «ሁቱ» የሚሉ ስያሜዎች ከቀኝ ግዛት በፊት በሩዋንዳና ሩዉንዲ የብሄር ወይም የጎሳ ስያሜዎች አልነበሩም።ኑሯቸውን በግብርና አርብቶ አደርነት የሚመሩ የተለያዩ 18 ጎሳዎች በሀገራቱ ነበሩ።ከነዚህ ጎሳዎች ኑሯቸውን በግብርና ላይ ያደረጉቱ በተለምዶ «ደሃ» እንደሚባለው ለማለት "ሁቱ" ይባሉ ነበር።ኑሯቸውን በአርብቶ አደርነት የሚኖሩት ደግሞ "ቱትሲ" በሚል አልፎ አልፎ ይጠሩ ነበር። መጠሪያዎቹ የኑሮ ዘይቤንና የኢኮኖሚ ደረጃን ብቻ የሚጠቁሙ ብቻ ነበሩ።
ሩዋንዳንና ቡሩንዲን በቀኝ የገዛችው ቤልጅየም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1932 ለመግዛት እንዲመቻት ቀኝ ተገዢዎቹን በተለያየ መልኩ ለመለየትና የሚታወቁበትን መታወቂያ ለመስጠት ወሰነች።ቀጥሎም ከየትኛው ጎሳ ይሁን ማንኛውም አስር ከብትና ከዚያ በላይ ያለው ሰውን «ቱትሲ» ብላ ሰየመች።ከአስር ከብት በታች ያለውን ሰው ደግሞ «ሁቱ» ብላ ሰየመች። በዚሁ ክፍፍል መሰረት ግለሰቦችና ቤተሰቦቻቸው በሙሉ በዚሁ አዲሱ ክፍፍል ስር ተደለደሉ።
እያንዳንዱ ሰውም ማንነቱ እንዲለይ በዚሁ ክፍፍል መሠረት መታወቂያ ታደለው።ማንኛውም አገልግሎት በዚሁ ክፍፍል መሠረት እየተጠሩ መስተናገድ ሆነ።ሰዎችም በተሰጣቸው ስያሜ እኛና እነርሱ እየተባበሉ መሰባሰብ፣ስነልቦና መፍጠርና ራሳቸውን መግለጽ ጀመሩ።
ቤልጂየሞች ከአስር በላይ ከብቶች ያሏቸውንና «ቱትሲ» ያሏቸውን ወደ ራሳቸው አቅርበው ከስልጣንም ከተቀባይነትም የተወሰነ ደረጃ ሰጧቸው።
አብዛኛው አባላቱ ሁቱዎች የሆነው ይህ መንግስት ከቤልጂየም ነፃ ቢሆንም በዜጎች መካከል እርቅና መዋሃድ ባለመፈጠሩ የብሄር ዉጥረቱ ቀጠለ።በተለይ በ1973 ከሁቱ ወገን የሆኑት ጁቬናል ሀባይሪማና ስልጣን ሲይዙ ዉጥረቱ ተባባሰ።በዚህ ጊዜ ቱትሲዎች ሀገር ጥለው መሰደድና መገፋታቸው ቀጠለ።
ቱትሶዎቹ በስደት እየተደራጁ ለትግል ተዘጋጁ። የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር(the Rwandan Patriotic Front /RPF/) የተሰኘ አማፂ ቡድን አቋቋመው ትግል ጀመሩም።ይህ ሸማቂ ቡድንም ከስደተኞች የመለመላቸውን ከአስር ሺህ በላይ የሚሆኑ ሠራዊቱቶቹን ይዞ በ1990 ከዑጋንዳ በመነሳት በሀገሪቱ መንግስት ላይ ጦርነት አወጀም። መንግስትን ገልብጦ ስልጣን ለመያዝ ገሰገሰ። ለጊዜው በዚሁ ላብቃና ቀሪውን በቀጣዩ ክፍል እመለሳለሁ።ቸር እንሰንብት።

እኚ በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው አባታችን ኑርበስር ሽፋ ይባላሉ. ድንገት ባጋጠማቸው የኩላሊት ህመም ምክንያት ሁለቱም ኩላሊታቸው ሥራ በማቆሙ ለአንድ ዓመት በፅጌረዳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኩላሊት አጥበት ወይም diyalisis ሲደረግላቸው ቆይቷል. ይሁን አንጂ ይህ ወጪ በሳቸውም ሆነ በኛ በቤተሰቦቻቸው አቅም መሸፈን የማይቻል በመሆኑ የአርዳታ አጃቹን አንድዘረጉልን ስንል በፈጣሪ ስም አንጠይቃለን🙏🙏
0963161894
1000189315752(በህሪያ ኑሪ ሽፋ)
0963161894
1000189315752(በህሪያ ኑሪ ሽፋ)
ሂጅራ ባንክ ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን ዓመታዊ የስራ አፈፃፀም ግምገማ እና የአቅም ግንባታ ስልጠና መርሃግብር በዛሬው ዕለት በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል::
በመርሀግብሩ የተጠናቀቀው በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ባንኩ ላስመዘገበው አጥጋቢ ውጤት ምክንያት የሆኑ መልካም ተሞክሮዎችን እንደ ጥንካሬ በመውሰድ እንዲሁም ትኩረት የሚሹ አፈፃፀሞች ላይ በጥልቀት በመወያየትና ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት ከባንኩ ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በተጨማሪም የቀጣይ ዓመት የስራ ዕቅድ ለውይይት የቀረበ ሲሆን ገንቢ ሐሳቦች እና አስተያየቶች ቀርበው በአመራሩ አቅጣጫ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ የባንኩን ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ በመረዳት ለተሻለ ውጤት በትኩረት መስራት እንደሚገባም በመድረኩ ተገልፃል፡፡
የአፈጻጸም ግምገማና ዕቅድ ከተጠናቀቀ በኋላ ክህሎት የማሳደጊያና የአቅም ግንባታ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን አመርቂ ዉጤት ላስመዘገቡ አዳዲስና ነባር ቅርንጫፎች፣ ዲስትሪክቶች እንዲሁም ባንኩ ተወዳዳሪ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት እንዲያቀርብ ልዩ አስተጽኦ ለነበራቸው ሰራተኞች እውቅና በመስጠት መርሐ ግብሩ ማገባደጃውን አግኝቷል፡፡
#HijraBank #InterestFreeBanking #Performance_Evaluation #Excellence #Performers

ወንድማችን አስታዝ ኢብራሂም ዘይኑ ፈር ቀዳጅ ከነበሩ ዳኢዎች መካከል አንዱ የነበረ ሲሆን፤ በእውቀትና ዳዕዋ ዘርፍ አቅሙ በፈቀደ መጠን ከሦስት አስርት አመታት በላይ ለሆኑ ጊዜያት ባልተቆጠበ አቅሙ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ከሌሎች ዳኢዎቻው በመሆን የዳዕዋ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኡስታዝ ኢብራሂም ባጋጠመው የጤና ዕክልና ሌሎች ተጨማሪ ችግሮች ምክንያት ቤተሰቡ ተበትኖበት የወንድሞቹን ድጋፍ ለመጠየቅ የሚያስገድድና አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል። ከሚገኝበት አስጨናቂና ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ተላቆ ወደ ሚወደው የእውቀትናዳዕዋ ስራ በሙሉ አቅሙ እንዲገባና እንዲሁም የተበተነ ቤተሰቡን መሰብሰብ እንዲችል ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋፅኦ እንድታደርጉለት በአላህ ስም እንማፀናለን!!
አካዉንት ቁጥር፦
1000567255698 CBE
0044037320101 ZAMZAM
197146575 ABYSSINYA
ኢብራሂም ዘይኑ ሳኒ
Ibrahim zeynu sani
አካዉንት ቁጥር፦
1000567255698 CBE
0044037320101 ZAMZAM
197146575 ABYSSINYA
ኢብራሂም ዘይኑ ሳኒ
Ibrahim zeynu sani