Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል
የዙል-ሒጃህ ማስታወሻ ዛሬ ሃሙስ (ግንቦት 29/2016) ዙል-ቀዕዳህ 29 ሲሆን ምናልባትም ይህ ወር በ29 ካለቀ ነገ ጁሙዓህ ዙል-ሒጃህ 1 ስለሚሆን ኡድሒያ የማረድ እቅድ ያለው ሰው የዛሬ ቀን ጸሐይ ከመጥለቋ በፊት ሰውነት ላይ መነሳት ያለባቸው ጸጉሮችንና ጥፍርን ማንሳት ተገቢ ነው። ነቢዩ ﷺ በሐዲሣቸው የሚከተለውን ብለዋል፥ "አንዳችሁ ኡድሒያ ለማረድ ካሰበ የዙል-ሒጃህ ወር ከገባ በኋላ እርዱን እስኪፈጽም…
🔴ጨረቃ በመታየቷ የዙልሒጃ ወር ነገ ጁምዓ አንድ ብሎ ይጀምራል! አስሩን ቀናት በመልካም ስራ እናሳልፋቸው!
⚫️ ለሀገራዊ ምክክር ሂደት የሚቀርቡ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አጀንዳዎች
📌 3ኛ የኢትዮጵያን ታሪክ የሙስሊሙን ታሪክ ያካተተ ማድረግ
ሁሉም ህዝብ በራሱ ደረጃ የሚነገር የተናጠል ታሪክ ያለው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የወል ታሪኮችም በርካቶች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ታሪክ የሚል ርእስ የያዙ ሀገር አቀፍ ታሪኮች የሙስሊሙን ታሪክ በተለጣፊና ተጨማሪነት ወይንም የጎንዮሽና የተቀናቃኝ ታሪክነት አድርገው በመሳል ሲያቀርቡ ይስተዋላል፤
በመሆኑም የሙስሊሙ ታሪክ የሀገሪቱ አንኳር ታሪክ አካል ሆኖ ስለኢትዮጵያ ታሪክ ሲወራ ሙስሊም አካታች የሆነ ታሪክና ትርክት እንዲዘጋጅ በሀገራዊ የምክክር መድረኩ በአጀንዳነት እንዲያዝልን እንጠይቃለን፡፡

ለሀገራዊ ምክክር ሂደት የሚቀርቡ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አጀንዳዎች
4ተኛ - በታሪክ ውስጥ የሃይማኖት ጭቆናዎች ጭምር ሆነው ሳሉ የብሄር ጭቆና ብቻ ተደርገው የቀረቡትን ዳግም መከለስ
📕📕📕📕📕📕📕📕📕📕📕📕📕📕📕
በታሪክ የነበሩ ጭቆናዎችን ፣በተለይ በሃይማኖት መሠረት የተፈፀሙትን ታሪኮች ማተት፣ ማረጋገጥ ፣እውቅና መስጠት፣ጭቆናዎች የሃይማኖት ጭምር ሆነው ሳለ የብሄር ጭቆና ብቻ ተብለው የተሰየሙትን ዳግም መከለስ እና ማስተካከያ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
በመሆኑም የሃይማኖት ጭቆናዎችን በሀገራዊ የምክክር አጀንዳ ውስጥ እንዲካተትልን እንጠይቃለን፡፡

5ተኛ ~ በታሪክ ፍሰት የጊዜ አከፋፈሎችን ሙስሊም አካታች በሆነ መንገድ ዳግም መቃኘት
📕📕📕📕📕📕📕📕📕📕📕📕📕
ታሪክ ከሚበየንባቸው መንገዶች አንዱ የታሪክ አተራረክ የግዜ ፍሰት ነው፡፡ በክፍለዘመን ደረጃ፣ በየአስርት ዓመቱ፣ ...ወዘተ በአንድ ሀገር ምን ተከሰተ፣ ማን ጀምሮ ማን ተከተለ፣ ...ወዘተ የሚለው ትረካ የታሪኩን ሰንሰለት አንድ ወጥነት ያለው ባህልና ማህበረሰብን ብቻ ዋና የሰንሰለቱ አካል አድርጎ የሌሎችን የጊዜ ሰንሰለት እውቅና በመንፈግ ከግዜ ሰንሰለት ውጭ የተካሄዱ ትርፍ ክስተቶች አስመስሎ በህዝቡ ውስጥ ይቀርፃል፡፡ ስለዚህም የተሳሳተ የታሪክ የግዜ ትረካን ለማስተካከል አዳዲስ የታሪክ ፍሰትን በጊዜ ሂደት የሚያትት አካሄድ የማስተዋወቁ ሥራ የብሄራዊ ምክክሩ አጀንዳ ሆኖ እንዲያዝ እንጠይቃለን፡፡

🛑 የአረፋ ቀን ፆም!
ነቢዩ (ﷺ) ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦
“ያለፈውንና የመጪውን አመት ወንጀል ያስምራል።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1162
🛑 የአረፋ ቀን ፆም የሚፆመው ነገ ቅዳሜ ሰኔ 8 ነው።
⚫️ ቀዳ ያለበትም ሰው ቢሆን የዐረፋን ቀን ጾም መጾም ይችላል።
⚫️ ማንኛውም ከነጋ በኋላ ምግብና መጠጥ ያልቀመሰ ሰው ከነጋ በኋላም ቢሆን ነይቶ ጾም መጀመር ይችላል። ነገር ግን ምንዳው የሚጀምረው ከነየተበት ሰዓት ጀምሮ ነው።
⚫️ከ9ኛው ቀን በፊት ምንም ላልጾመ ሰውም ቢሆን 9ኛው ቀን ብቻ መፆም ይቻላል/ችግር የለውም።
⚫️በዐረፋ (9ኛው ቀን) ላይ ይበልጥ የሚወደዱ 3 ዒባዳዎች፣
1/ ቀኑን መጾም
2/ ዚክር ማብዛት በተለይም ተክቢር
3/ ዱዓእ ማብዛት
⚫️ለዐረፋ ቀን ራሱን የቻለ ዱዓእ የለውም ሁሉም የቻለውንና የሚፈልገውን ዱዓእ ማድረግ ይችላል።
🛑 የአረፋ ቀን ፆም የሚፆመው ነገ ቅዳሜ ሰኔ 8 2016 ነው።

Arafaah Liman Arafah!
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
Guyyaan borii guyyaa mana Qulqulleessu, jijjirraa maggaarajaati fi Guyyaa bashannanaati miti.
Guyyaan borii Rabbiin namoottan arafaatin/arafaa dhaabataniin malaa'ikotarratti ittiin boonu, ilmi namaa baay'inaan ibiddarraa kan bilisa jedhamu, waan mararrayyu guyyaa du'aa'iwwan guutumaan guututti qeebalama argatanii dha.
Laylatul qadr beekamu baatus guyyaan arafaa immoo ni beekama. Halkan laylatul qadr malaa'ikoonni ni buuti guyyaa arafaa immoo Allaahun (bu'iinsa isaan malu) bu'a.
Nama fayyaadhaan guyyaa borii qunnaamuf ibaadaa godhuu qabuu fi danda'uu isinif haa qoodu
Ganama
* fajriin duratti laylirraa salaatu, suhuura nyaachu fi istigfaara heddummeessu!
* salaata fajriin booda takbiiraa jalqabuu, haga aduun baatutti Qur'aana qar'uu, taahlila taahmiida jechu walumaa galatti zikriin dabarsuu(azkaarassabaah osoo hindagatamiin)
* yeroo aduun baatu achumatti sigaajaa keenyarraa osoo hinka'in salaata mindaa/ajrii rasuula wajjin(saw) hajjuu argachuuf salaatu.
* Ibaadaa guyyaa keessa goonuf nugargaara yoo jenne xiqqoo haa rafnu. Yeroo kaanu xiqqomaan rak'aa 4 haa salaannu.
Sa'aa booda
* salaata zuhrin booda Qur'aana haa qaraanu. Khuxbaa Arafaa(ergaa masjiida namiraah irraa dabarfamu) sirnaan hordofuu
* kitaaboota ykn vidiyoowwan onnee keenya jiisuu danda'aniin yeroo keenya haa dabarsinu
* akkasumatti asriin boodas Qur'aanaa fi zikriin haga magribni dhihaatutti isaan dabarsu
Yeroon guddaa isa ammaa kana.
* kan dhukkubsate ka itti yaalamu kan abdii kute abdiin isaa ka lubbuu itti hoortu sa'aa dinqii.
Du'aa'ii!!! Du'aayii qofa!
guyyaa kanatti ibiddarraa bilisa jedhamuu baatun kasaaraa dha. Fedhii qabaanne fedhii keenya osoo hin guutin hafuun wallaalummaa dha!
"Namni gaara arafaarratti dhaabatu hin dandeenne daangaa Rabbiin isa beeksiseerratti haa dhaabbatu.
Namni muzdalifaa buluu hin dandeenne ajaja Rabbii isaa irrratti haa bulu.
Namni minaarratti qalma qalu hin dandeenne fedhi lubbuu isaa haa qalu.
Namni gara mana Rabbii isaa sababa fageenyaatin deemuu hin dandeenne Allaahu hidda dhigaa isaa irra itti dhihaatu haa kajeelu!" Ibnu Rajab
Araaramatu nuu wayya!
Huzeyfa sultan

🐏 ኡድሒያን የሚመለከቱ ወሳኝ ነጥቦች
🔴 ኡድሒያ ማለት በዐረፋ በዓል ቀን እና ቀጥሎ ባሉ ተከታታይ ሶስት ቀናት ውስጥ ወደ አላህ ለመቃረብ ተብሎ የሚታረድ የቤት እንሥሳ ማለት ነው።
"ኡድሒያ" የተባለው የእርዱ ሰዓት የሚጀምረው የዒድ ቀን ረፋድ (ዱሓ) ላይ ስለሆነ ነው።
🔴 ኡድሒያ ማረድ የዲን አካልና ተወዳጅ ተግባር መሆኑ ላይ ሁሉም ሊቃውንት ይስማማሉ፤ ብዙሃኑ ሊቃውንት ዘንድ ሱንናህ እንጂ ስለት (ነዝር) ለሌለበት ሰው ግዴታ አይደለም። አቡ ሐኒፋን ጨምሮ በርካታ ግዴታ ነው የሚል አቋም ያላቸው ሊቃውንት ስላሉና በዒድ ቀን ማረድ ልዩና ከፍ ያለ ምንዳም ስላለው አቅም ያለው ሰው ኡድሒያ ማረድ ባይተው ይመረጣል፤
🔴 ከቤት እንስሳት (ከግመል፣ ከከብት ፣ ከበግና ፍየል) ውጪ ሌላን እንስሳ ለኡድሒያ ማረድ እንደማይቻል የፊቅህ ሊቃውንት በሙሉ (ከሐሰን ኢብኑ ሳሊሕ በስተቀር) ይስማማሉ።
🔴 ለኡድሑያ የሚታረደው እንስሳ ወንድም ይሁን ሴት ለውጥ የለውም፤ ሁለትም ጾታዎች ለኡድሒያ እንደሚሆኑ (እንደ ሚበቁ) የፊቅህ ሊቃውንት ይስማማሉ።
🔴 የዒድ ቀን ከሰላተል-ዒድ በፊትና፣ ከ 14ኛው ቀን የጸሐይ መጥለቅ በኋላ የሚታረድ እርድ ከኡድሒያ አይቆጠርም።
🔴 በመሰረቱ የኡድሑያ እንስሳ መግዣ ገንዘቡን ሰደቃ ከመስጠት ይልቅ ኡድሒያ ማረዱ በአጅር ይበልጣል። ይህም የሆነው ኡድሒያ በዕለቱ ተወዳጅና ከዒድ ሰላት ጋር የተያያዘ ዒባዳህ ስለሆነ ነው። (ኢብኑልቀይም)
ነገር ግን ገንዘቡን መስጠቱ ለተቸገረ ሰው ይበልጥ የሚጠቅምበት ሁኔታዎች ላይ በላጩ ገንዘብ መስጠቱ ይሆናል። (ኢብኑ ዑሠይሚን)
🔴 ብዙሃኑ የፊቅህ ሊቃውንት ዘንድ ለኡድሒያ እርድ በላጭና ተመራጩ እንስሳ በቅደም ተከተል ግመል፣ ከዛም ከብት፣ ከዛ በግ ወይም ፍየል ነው።
ይህ የሚባለው ግን ግመል ወይም ከብት አንድ አባወራ ለብቻው የሚያርድ ከሆነ ነው። ለጋራ ወይም በቅርጫ ከሆነ ግን የሚያርደው ከግመልና ከከብት ይልቅ በግ ወይም ፍየል ይሻላል።
ኢማሙ ማሊክ በሁሉም ሁኔታ ላይ በላጩ በግና ፍየል፣ ከዛም ከብት፣ ከዛ ግመል ነው የሚል አቋም አላቸው።
ይህ በላጩና ይበልጥ ተወዳጁን ከመግለጽ አንጻር ነው እንጂ ከ4ቱ የቤት እንስሳት ውስጥ ማንኛውንም ቢያርዱ ትክክል ይሆናል።
🔴 ለኡድሒያ የሚታረድ ማንኛውም እንስሳ ቁመናና መልኩ የሚያምረው፣ ስጋው ይበልጥ ጣፋጭና ንጹህ ይሆናል የሚባለውና በዋጋም ውድ የሆነው ከዚህ ተቃራኒ ከሁኑ እንስሳት ይልቅ ለኡድሑያ ተወዳጅ እንደሚሆን ሊቃውንት ይስማማሉ። (አን'ነወዊይ)
ይህም ኡድሒያ የሚታረደው ለአላህ ተብሎ ስለሆነና ለርሱ የሚደረግ ነገር በሙሉ ንጹሁ፣ ትልቅና የሚያምር መሆን ስለሚገባው ነው።
🔴 ለኡድሒያ የሚታረድ እንስሳ እድሜው በግ ከሆነ 6 ወርና ከዛ በላይ፣ ፍየል ከሆነ 1አመትና ከዛ በላይ፣ ከብት ከሆነ 2 አመትና ከዛ በላይ፣ ግመል ከሆነ 5አመትና ከዛ በላይ መሆን አለበት።
ዕድሜው እዚህ ከተጠቀሰው በታች የሆነ እንስሳ ለኡድሒያ በቂ አይሆንም።
🔴 በተፈጥሮ ምንም ቀንድ የሌለው ወይም ቀንዱ በጣም ትንሽ የሆነ፣ ጭራ ወይም ላት የሌለው፣ የተኮላሸ፣ ጆሮው የተሰነጠቀና ከግማሽ በታች የሚሆነው ብቻ የተቆረጠ እንስሳን ለኡድሒያ ማረድ ችግር የለውም።
በላጩ ግን ቀንድ ያለውና አካላቱ ሙሉ የሆኑትን ማረዱ ነው።
🔴 ግልጽ የሆነና እንደልቡ ተንቀሳቅሶ እንዳይበላ የሚያደርግ ሸፋፋነት ያለበት፣ አንድ ወይም ሁለቱም አይኑ የማያይ፣ በጣም ከመክሳቱ የተነሳ ቅልጥም፣ ጮማና ሞራው ያለቀ/የሌለው፣ ግልጽ የሆነ በሽታ ወይም የበሽታ ምልክት ያለበት ማንኛውም እንስሳ ለኡድሒያ አይሆንም።
ከላይ ከተጠቀሱት እንከኖች ጋር ተመሳሳይና የባሰ እንከን ያለበትንም ማረድ አይቻልም።
ነገር ግን ከእነዚህ እንከኖች መካከል ቀላልና ግልጽ ያልሆነ ያለበትን ማረድ አማራጭ ካጡ እንደሚቻል ሊቃውንት ይስማማሉ።ጤነኛና ከእንከን ንጹህ ሆኖ የገዙት እንስሳ ያለጥንቃቄ ጉድለት ከላይ የተጠቀሱ እንከኖች ቢገጥሙት ማረድ ይቻላል፤ አቅም ያለው ሰው ሌላ ቢቀይር ግን ይመረጣል።
🔴 አንድ በግ ወይም ፍየል ለአንድ አባወራ እስከ ቤተሰቦቹ፣ አንድ ከበት ወይም ግመል ለ7 እና ከዛ በታች ለሆኑ አባወራዎች ( ቤተሰቦች) ይበቃል።
አንድ ሰው ኡድሒያው ላይ ማንኛውንም (በህይወት ያለም ይሁን የሞተን) ሰው በምንዳው ማጋራትና ማካተት ይችላል።
ለአንድ አብሮ ለሚኖር ቤተ ሰብ አንድ ኡድሒያ የሚበቃ ከመሆኑም ጋር አቅም ያለው በሙሉ በስሙ ኡድሒያ ቢያርድ መልካም ይሆናል።
🔴 አንድ እንስሳ ቤት ውስጥ ተወልዶ ያደገ (የረባ)ም ይሁን፣ እራሱ ወይም ገንዘቡ በስጦታ መልኩ የተገኘም ይሁን በማንኛውም ህጋዊ በሆነ መንገድ የራስ የተደረገ ከሆነ ለኡድሒያ ነይቶ ካረዱት በቂ ይሆናል። የግድ በጊዜው ለኡድሒያ ተብሎ በራስ ገንዘብ የተገዛ ካልሆነ አይባልም።
🔴 አንድን እንስሳ ለኡድሒያ ከወሰኑት በኋላ ሀሳብ ቀይሮ ማረዱን መተው፣ መሸጥ ወይም ለሌላ ሰው ስጦታ መስጠት አይቻልም።ግዴታ ላልሆነ ኡድሒያ የተዘጋጀ እንስሳ ያለጥንቃቄ ጉድለት ቢጠፋ ሌላ መተካት ግዴታ አይሆንም።
🔴 ለኡድሑያ የታረደን እንስሳ ቆዳውንም ይሁን ምኑንም መሸጥ፣ ለአራጅ ክፍያ ይሆን ዘንድ ብሎ ምንም ነገር መስጠት አይቻልም።በምንም መልኩ ክፍያው ላይ ተጽዕኖ ሳይኖረው ለአራጅ እንደተጨማሪ ስጦታ ወይም ሰደቃ መስጠት ግን ይቻላል።
ኡስታዝ አሕመድ አደም

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
📣 2ኛው ቲጃራ ቢዝፕርነር ኮንፈረንስ 📣
የራስዎን Printing & Packaging ወይም የህትመት እና የምርቶች ማሸግያ ንግድ ለመጀመር ህልም አለዎት? ህልምዎን እውን ለማድረግ ይህ ለእርስዎ የማይገኝ አጋጣሚ ነው! 🌟
በ2ኛው ቲጃራ ቢዝፕርነር ኮንፈረንስ ይቀላቀሉንና ከአነስተኛ ካፒታል እስከ ትልቅ ኢንቨስትመንቶች የራስዎን Printing & Packaging ንግድ እንደሚጀምሩ ይወቁ። ከኢንዱስትሪ ባለሞያዎች በዋጋ ሊተመን የማይችል እውቀትና ልምድ ይቅሰሙ፣ ከስራ ፈጣሪዎች ጋር ኝኑነት በመፍጠር የስራ ፈጠራ ጉዞዎን ይጀምሩ 💼✨
📅 ቀን: ሰኔ 16/2016 ወይም June 23/2024
📍 ቦታ፡ ኦሮሞ ባህል ማዕከል (ከአ.አ ስታድየም ፊት ለፊት)
💵 የመግቢያ ዋጋ 300 ብር
መሳተፍ የሚችሉት 300 ሰዎች ብቻ ናቸው
🎟️ አሁኑኑ ይመዝገቡ፡ https://forms.gle/VfKigu8kdXEbayLK7
ፍላጎትዎን ወደ ትርፍ ለመቀየር የሚያግዝዎት ይህ አስደናቂ እድል እንዳያመልጥዎት። ከ300ዎቹ ለመሆን ዛሬውኑ ቦታዎን ይያዙና ወደ ሥራ ፈጠራ ህልምዎ የመጀመሪያውን እርምጃ ይውሰዱ!
#TijaraBizpreneurConference #PrintingAndPackaging #Entrepreneurship #BusinessGrowth #SmallBusiness
#ቲጃራ_ቢዝፕርነር_ኮንፈረንስ #ህትመትና_ማሸግ #የስራ_ፈጠራ #ቢዝነስ_እድገት #አነስተኛ_ንግድ

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
Innaa Lillaahi wa innaa ilayhi raajiun!
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
የኡስታዝ አቡበከር አህመድ ባለቤት የወይዘሮ ሀናን መሀመድ አባት ሀጂ ሙሀመድ አህመድ በሂክምና ሲረዱ ቆይተው አርፈዋል። አላህ በራህመቱ ጀነተል ፊርደውስን ይለግሳቸው። ለወዳጅና ዘመድ በሙሉ መፅናናትን ያጎናጽፋቸው።
የቀብር ስነ ስነ ስርዓታቸውም ዛሬ (በእለተ ረቡዕ) ከዙህር ሰላት በኋላ በጅማ ከተማ ራህማ መስጂድ ተሰግዶ በአቅራቢያው ባለ የሙስሊም መካነ መቃብር የሚፈጸም ይሆናል።
Innaa Lillaahi wa innaa ilayhi raajiun!
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
Abbaaan haadha manaa Ustaaz Abubaker Ahmad addee Hanaan Muhammed kan ta'an Haji Muhammad Ahmad gara fuula gama Rabbiityi imalan. Rabbin ija rahmataatin ileelee isaanifis jannatal firdawusiin habadhaasuni. Maati isaani maras sabri hakennuufi.
Sirni awwaacha isaani guyya hara'a, Roobi salaata Zuhrin booda magaalaa Jimmaatti masjida Rahmaatti itti salaatamee bakka awaalchaa muslimaa naanno sana jirutti raawwatama.

“ከቀናችሁ ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ። ሰለዋታችሁ ለኔ ይቀርብልኛልና።”
ረሱል (ﷺ)
ረሱል (ﷺ)
🛑 የጁምዓ ሰላት አንደ ረከዓ እና ሁለት ረከዓ ያገኘ ሰው እንዴት እንደሚሰግድ ያውቃሉ?
★ T.me/ahmedin99
📌 ሶላቱል ጁምዓን በዑዝር ምክንያት መሳተፍ ያልቻሉ ሙሳፊር ያልኾኑ ሙስሊሞች፤ ሶላቱ-ዙህርን እንደተለመደው አራት ረከዓህ መስገድ ግዳጃቸው ነው፡፡ እንዲሁም ወደ ጁምዓ መስጂድ አርፍደው የመጡና፤ ከዚያም ኢማሙ ላይ ከሁለተኛው ረክዓህ ሩኩዕ መነሳት በኋላ የደረሱበት ሰዎች፤ ምንም ረክዓህ ስላላገኙ፤ የቀረውን የሱጁድ እና የተሸሁድ ስርአት ከኢማሙ ኋላ በመከተል ይሰግዱና፤ ኢማሙ ሲያሰላምት፤ እነሱ በመነሳት ባለ አራት ረከዓህ ሶላት (ዙህር) ይሰግዳሉ፡፡ ግን ኢማሙ በሁለተኛው ረክዓህ ሩኩዕ ላይ እያለ ከደረሱበትና እነሱም ያንን ሩኩዕ ኢማሙ ሳይነሳ በፊት ከደረሱበትና ሩኩዕ ካደረጉ አንድ ሙሉ ረክዓህ አግኝተዋልና፣ ኢማሙ ባሰላመተ ጊዜ፤ እነሱ ይነሱና የቀረውን አንድ ረክዓህ በመስገድ ያሰላምታሉ ማለት ነው፡፡ አንድን ሙሉ ረክዓህ ለማግኘት የመጨረሻው ጊዜ ኢማሙን ሩኩዕ ላይ እያለ መድረስና፤ ከሩኩዕ ቀና ሳይል እኛም አላሁ አክበር ብለን በቆምንበት ቦታ ከሐረምን በኋላ ወዲያው ሩኩዕ ማድረጋችን ነውና፡፡
ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ አንሁ) ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፡- "ከጁምዓ ሶላት አንድን ረክዓህ ያገኘ ሰው፤ የቀረውን ሌላ ረክዓህ ወደሱ ይጨምር፡፡ ሁለቱም ረክዓዎች ያመለጡት ሰው አራትን ረክዓህ ይስገድ" (አል-በይሀቂይ፡ ሱነኑል-ኩብራ 5531፣ ጦበራኒይ፡ አል-ሙዕጀሙል ከቢር 9545)፡፡
📌 ግለሰቡ የጁምዓ ሶላት ሁለቱም ረክዓዎች አምልጠውት ኢማሙ ከማሰላመቱ በፊት ቢደርስና፤ ከኋላቸው ነይቶ ቢቀመጥ፤ ኢማሙ ያሰላመተ ጊዜ እሱ ተነስቶ አራት ረክዓህ የሚሰግድ ከኾነ፤ መጀመሪያውኑ ነይቶ የሚቀመጠው ዙህርን ሶላት ነው ወይስ ጁምዓን? ለሚለው ጥያቄ፡- ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን (ረሒመሁላህ) የሰጡት ምላሽ፡- ግለሰቡ ሁለቱ ረክዓዎች አምልጠውት ኢማሙን በተሸሁድ ላይ ኾኖ ካገኘው፣ በዙህር ኒያ ከኢማሙ ጋር ተሸሁድ ይቀመጥና ኢማሙ ሲያሰላምት ተነስቶ አራት ይሰግዳል የሚል ነው፡፡ (አሽ-ሸርሑል ሙምቲዕ፡ 4/160)፡፡
📌 የጁምዓ ቀን ሶላት (ሶላቱል ጁምዓ) ከበፊቱ የሚሰገድ (ሱንነቱል-ቀብሊያ) የለውም፡፡ ነገር ግን ከቤቱ ለጁምዓ ሶላት ተዘጋጅቶ መስጂድ የመጣ ሰው ኢማሙ ወደ ሚንበር እስኪወጣ ድረስ፤ አላህ ያገራለትን ያህል ሶላት መስገድ ይችላል፡፡ ይህ ሙጥለቅ (በመጠን ያልተገደበ የኾነ) የሱንና ሶላት ተብሎ ይጥጠራል፡፡ ከአዛን በኋላ ግን የሚሰገድ የኾነ የሱንና ሶላት የለውም፡፡ ሰልማኑል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "አንድ ሙስሊም በጁምዓ ቀን ሰውነቱን የታጠበ ከኾነ፣ ጥሩ መዓዛ ባለው ቅባት የተቀባ ወይንም ሽቶን በልብሱ የነሰነሰ ኾኖ ወደ መስጂድ ኼዶ፤ በሁለት ሰዎች መሐል፤ በመሐላቸው በመለየት ሳይቀመጥ (ሳያስቸግር)፤ ከዚያም የተጻፈለትን (አላህ ያገራለትን ያህል) ከሰገደ፣ ኢማሙም መናገር ሲጀምር በዝምታ ካዳመጠ፤ ቀጣዩ ጁምዓ እስኪመጣ ድረስ በዚህ መሐል ያለው ኃጢአት ይማርለታል" (ቡኻሪይ 883)፡፡
📌 ጁምዓ ሶላት ከበኋላው የሚሰገድ የኾነ ሶላት (ሱነኑል በዕዲያ) አለው፡፡ ግለሰቡ እዛው መስጂዱ ውስጥ ከኾነ የሚሰግደው ባለ ሁለት ረክዓህ ሶላት ሁለት ጊዜ በመስገድ እስከ አራት ረክዓህ መስገድ ሲችል፤ በቤቱ መስገድ ከፈለገ ደግሞ ሁለት ረክዓህ ይሰግዳል ማለት ነው፡፡ ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ከናንተ ውስጥ ከጁምዓህ በኋላ መስገድን የሚፈልግ ሰው አራት (ረክዓህ) ይስገድ" (ሙስሊም 2075)፡፡
ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ሶላቱል ጁምዓን ከሰገደ በኋላ ወደቤቱ ሄደና ሁለት ረክዓህ ሶላትን ሰገደ፡፡ ከዚያም፡- ‹‹የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ያደርጉ ነበር›› በማለት ተናገረ፡፡ (ሙስሊም 2076)፡፡
📌 በጁምዓ ቀን ኢማሙ ኹጥባህ እያደረገ በዚህ መሐል መስጂድ የገባ የአላህ ባሪያ፤ መቀመጥን ከፈለገ ቅድሚያ ቀለል ያለ ሁለት ረክዓህ መስገድ ተገቢው ይኾናል፡፡ ሶላቱንም ቀለል እና ፈጠን በማድረግ፤ በቀሪው ጊዜ የኢማሙን ኹጥባህ ለመስማት መጓጓት አለበት፡፡ ምንም ሳይሰግድ መቀመጡ ሱንናን መቃረን ይኾንበታል፡፡ ጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡- "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በጁምዓ ቀን ለሰዎች ኹጥባ እያደረጉ አንድ ሰው ገባና (ተቀመጠ)፡፡ እሳቸውም ‹‹እንትና! ሰግደሀልን?›› አሉት፡፡ ሰውየውም፡- አልሰገድኩም! አለ፡፡ እሳቸውም፡- ተነስና ሁለት ረክዓህ ስገድ! በማለት አዘዙት" (ቡኻሪይ 930፣ ሙስሊም 2055)፡፡
ኡስታዝ አቡ ሀይደር

«ጨረቃን ታመልካላችሁ እንዴ?»
🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋🕋
በአሕመዲን ጀበል፥ክፍል አንድ
ስለኢስላም ያላቸው ግንዛቤ አናሳ የሆኑ አልያም ጥቂትም ቢሆን ለማወቅ ያልሞከሩ አካላት ዘንድ የተለያዩ ብዥታዎች አሉ።ከነኚህ መካከል በፌስቡክ ኮመንት ላይ ከዚህ ቀደም ያነበብኩት «ሙስሊሞች ግን ሁሌ በረመዳን <ጨረቃ ከታየች ረመዳን ነገ ይያዛል።/ረመዳን ከታየች በዓል ነው> የምትሉት ጨረቃን ታመልካላችሁ እንዴ?» የሚለው ተጠቃሽ ነው። ይህን መሰል ብዥታ ለመፈጠሩ አንዱ ምክንያት በአጠቃላይ ስለዘመን መቁጠሪያዎች በተለይም ደግሞ ስለየሙስሊሞች የቀን መቁጠሪያ ግንዛቤ እጦት የሚመነጭ ነው።ሊጠናቀቅ አንድ ቀን ብቻ በቀረው የ1445 ዓመተ ሂጅራ ፍጻሚ ወይም የ1446 ዓመተ ሂጅራ ዋዜማ ላይ ሆኜ ስለዚህ ርዕሰ ጉዳዩ ከሃይማኖቱ ባህሪ ጋር በማያያዝ ጥቂት ማለትን ወደድኩ።
ኢስላም ከአላህ ዉጭ ለየትኛውም አካል ሙስሊሞች እንዲሰግዱ ወይም በማንኛውም መልኩ እንዲያመልኩ አይፈቅድም። ፀሐይ፥ጨረቃ፥ ከዋክብት፥ ነቢያት፥ ጻድቃን፥ቅዱሳን፥ አውሊያ፥ ባለአውሊያ፥ ሼህ፥ የአላህ መልዕክተኞች፥ መላዕክት(ገብርኤል፥ሚካኤል፥ወዘተ) ወይም ከአላህ ዉጭ ያለ የትኛውም አካልን ማምለክ በኢስላም ከተግባሩ በጸጸት እስካልተመለሰ ድረስ ግለሰቡ ምህረት የለሽ ከባድ ኃጢአትን በመፈጸሙ ለገሃነም ይዳረጋል። የትኛውም ዓይነት አምልኮ ጨረቃንም ሆነ ፀሐይን እንዲሁም ሌሎች ፍጥረታትን በሙሉ ለፈጠረው አንድ ፈጣሪ አላህ ብቻ የሚገባው። የሚሰገውም ለእርሱ ብቻ ነው። ይህም በበርካታ የቁርኣን ምዕራፍ ተጠቅሷል። ለአብነትም አላህ(ጥራት ይገባውና) እንዲህ ይላል፦
وَمِنْ ءَايَـٰتِهِ ٱلَّيْلُ وَٱلنَّهَارُ وَٱلشَّمْسُ وَٱلْقَمَرُ لَا تَسْجُدُوا۟ لِلشَّمْسِ وَلَالِلْقَمَرِ وَٱسْجُدُوا۟ لِلَّهِ ٱلَّذِى خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ
«ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው። ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ።እነርሱን ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ። እርሱን ብቻ የምትግገዙ እንደኾናችሁ(ለሌላ አትስገዱ)።»(ፉሲለት፡37)
ስሌትና ኢስላም
🎯🎯🎯🎯🎯
ኢስላም በአምስት መሥረቶች ላይ የተገነባ ሃይማኖት ነው። እነርሱም ከአላህ ዉጭ በእውነት የሚመለክ አለመኖሩንና ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ. ዐ .ወ) የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን መመስከር፥ በቀንና በሌሊት ዉስጥ አምስት ጊዜ ሰላትን መስገድ፥ የረመዳንን ወር መጾም፥መጠኑን ከሞላ ሀብት ላይ ዘካ(ምጽዋት) መስጠት እና በእድሜ ዘመን አንድ ጊዜ ሐጅ ማድረግ የሚሉ ናቸው። ከእነዚህ መካከል የአራቱ አተገባበር የጊዜ፥የዘመን አቆጣጠርን፥የመጠንና የሁኔታዎች ስሌትን የሚጠይቁ ናቸው። ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ በተናጠል እንመልከታቸው።
ሀ) ሰላት፦ ሙስሊሞች በ24 ሰዓት ዉስጥ አምስት ጊዜ ወቅቱን ጠብቀው መስገድ ይገባቸዋል።ከሰላት አሰጋገድ ባሻገር በትክክለኛ ሰዓት ለመስገድ የጊዜ አቆጣጠርና በመካ የሚገኘውን መስጂደል ሀራም(ካዕባ) አቅጣጫን(ቂብላን) ማወቅ ይጠበቅባቸዋል።
ለ) የረመዳን ጾም፦ የረመዳንን ወር ለመጾ የረመዳን ወር መድረሱን፥ መግባቱንና መች እንደሆነ(ጾም መያዣ ቀን)፥ ወሩ የሚጠናቀቀው በ30 ወይም በ29 ቀናት መሆኑን(የጾም ፍቺ ቀንን) እንዲሁም በየእለቱ የጾም ሰዓታትን ማለትም ጸም መጀመሪያ(ሱህር ማብቂያ/ንጋት) እና ማፍጠሪያ (የፀሐይ መጥለቂያ) ጊዜን ማወቅ ይጠበቃል።
ሐ) ዘካ(የግዴታ ምጽዋት)፦ ከምን ዓይነት ንብረቶች ምን ያክል ዘካ እንደሚሰጥ መጠንን፥ ለነማን እንደሚሰጥ(የተቀባዮችን ዓይነትን)፥ መች አንደሚሰጥ ጊዜውን ማወቅና ማስላትን ይጠይቃል።
መ) ሐጅ፦ የሐጅ ወር(ዙልሂጃ) ስንተኛው ወር፥ መች እንደሆነና ወሩ መግባቱን ማወቅ፥ የሐጅ ስነ ስርዓት የሚጀመርበትን ቀንና የሚጠናቀቅበትን እለት፥ በየእለቱ ምን ምን ተግባራት በምን ሰዓት እንደሚከናወኑ ማወቅን ይጠይቃል።
እነዚህ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች በርካታ ኢስላማዊ የአምልኮ ሂደቶች የጊዜንና የዘመንን፥ የሁኔታንና የስፍራን፥ የመጠንና የደረጃ ሁኔታን ከግምት ማስገባትን የሚጠይቁ አሉ።ይህ በመሆኑ ሙስሊሞች እነዚህን በትክክል ለመረዳትና ለመተግበር የግድ የጊዜ፥የዘመን፥ የአቅጣጫና ሌሎች ስሌቶችን ማወቅ ይጠበቅባቸዋል። ለዚህም ነው አላህ(ሱ.ወ) ትኩረት ሰጥቶ በቁርኣን የጠቀሳቸው። ቀጥለን እነኚሁኑ አብረን እንመልከት።
ሀ) ዘመን መቁጠሪያ እና የሒሳብ ስሌት
📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣
ሰከንዶች ተጠራቅመው ደቂቃ፥ ደቂቃዎች ሰዓት፥ ሰዓታት ቀን፥ ቀናት ሳምንታትና ወራት፥ ወራት ዓመት፥ ዓመታት የሰው የሕይወት ዘመን(እድሜ) እና ክፍለ ዘመናት እየሆኑ ጊዜን ይቆጠርባቸዋል።በዚህ መልኩ የሰው ልጅ የዘመን ክፍልፋዮች ወይም ጊዜ ድምር በመሆኑ ለዘመን የተለየ ትኩረት ሊሰጥ ግድ ይለዋል።ምክንያቱን ጊዜን በትክክል መረዳት፥ መለካትና ማስላት ለዚህ ዓለምም ሆነ ለቀጣይ ዓለም ስኬት እጅግ ወሳኝ ነው።ለዚህም ነው አላህ(ሱ.ወ) ስለዘመናት እና ሒሳብ እንድናውቅ የሚፈልገው።ለዚህም ነው በቀን ፀሐይን በምሽት(ሌሊት) ደግሞ ጨረቃን በመለኪያ(መስፈሪያነት) ምልክት እንዳደረገልን የነገረን። እንዲህም ይለናል፦
هُوَ ٱلَّذِى جَعَلَ ٱلشَّمْسَ ضِيَآءً وَٱلْقَمَرَ نُورًا وَقَدَّرَهُۥ مَنَازِلَ لِتَعْلَمُوا۟ عَدَدَٱلسِّنِينَ وَٱلْحِسَابَ
«እርሱ ያ ፀሐይን አንጸባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ ነው። የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለእርሱ መስፈሪያዎችን የለካ ነው።»(ዩኑስ፡5)
በሌላ የቁርኣን ምዕራፍ ላይ ይህንኑ ሀሳብ እንዲህ በማለት ይደግመዋል፦
وَجَعَلْنَا ٱلَّيْلَ وَٱلنَّهَارَ ءَايَتَيْنِ فَمَحَوْنَآ ءَايَةَ ٱلَّيْلِ وَجَعَلْنَآ ءَايَةَ ٱلنَّهَارِمُبْصِرَةً لِّتَبْتَغُوا۟ فَضْلًا مِّن رَّبِّكُمْ وَلِتَعْلَمُوا۟ عَدَدَ ٱلسِّنِينَ وَٱلْحِسَابَ
«ሌሊትንና ቀንንም (ለችሎታችን) ምልክቶች አደረግን።የሌሊትንም ምልክትም አበስን። የቀንንም ምልክትም የምታሳይ አደረግን።(ይህም የኾነበት) ከጌታችሁ ትርፍን ልትፈልጉ የዓመታትንም ቁጥርና ሒሳብንም ታውቁ ዘንድ ነው።»(አል-ኢስራእ፡12)
ለ) ጊዜን መረዳትና መለካት
🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊
የሰው ሕይወት(እድሜ) ራሱ የጊዜ ድምር በመሆኑ ስኬታማ እንዲሆን ከፈለገ እንቅስቃሴዎቹን በሞላ ከጊዜ ጋር አቆራኝቶና አስማምቶ መጓዝ ግድ ይለዋል።ለዚህም ይመስላል አላህ(ሱ.ወ) ሰላትን በአንድ ጊዜ ላይ ሰብሰብ አድርገን እንድንሰግድ ከማዘዝ ይልቅ በቀን ዉስጥ በተለያዩ አምስት ጊዜያት ከፋፍሎ ጊዜውንም ጠብቀን አንድንሰግድ ግዳጅ ያደረገብን።እያንዳንዱ ሳላት በወቅት የተወሰነ የመስገጃ ጊዜ አለው።አማኞችም ይህንን ተረድተው መተግበር ግዴታ ተደርጎባቸዋል። አላህ(ሱ.ወ) እንዲህ በማለት ይነግረናል፦
إِنَّ ٱلصَّلَوٰةَ كَانَتْ عَلَى ٱلْمُؤْمِنِينَ كِتَـٰبًا مَّوْقُوتًا
«ሰላት በምእመናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና።»(አል-ኒሳእ፡103)

አምልኮን በጊዜ መፈጸም ግዴታ ከሆነ ስለጊዜ በሚገባ መረዳት ግድ ይላል ማለት ነው።ለዚህ እንዲያግዘን አላህ(ሱ.ወ) ቀናችንን በቀንና በምሽት ከፍሏል።ፀሐይንና ጨረቃን ደግሞ የጊዜ አቆጣጠርን አንድንረዳ አድርጎልናል። እንዲህ ይለናል፦
فَالِقُ ٱلْإِصْبَاحِ وَجَعَلَ ٱلَّيْلَ سَكَنًا وَٱلشَّمْسَ وَٱلْقَمَرَ حُسْبَانًا ذَٰلِكَتَقْدِيرُ ٱلْعَزِيزِ ٱلْعَلِيمِ
«እርሱ ጎህን(ከሌሊት ጨለማ) ፈልቃቂ ሌሊትንም ማረፊያ ፀሐይንና ጨረቃንም (ለጊዜ) መቁጠሪያ አድራጊ ነው።ይህ የአሸናፊው የዐዋቂው(አላህ) ችሎታ ነው።»(አል-አንዓም፡96)
ሐ) አቅጣጫን መረዳት
⇶⇶⇶⇶⇶⇶⇶⇶⇶
ሙስሊሞች በተለያዩ ስፍራና ሀገር ቢኖሩም በአንድ ነብይና ቁርኣን የሚመሩ ዓለም ዓቀፍ አንድ ሕዝብ ናቸው።
በየእለቱ ሰላትን ሲሰግዱ የፊታቸውን አቅጣጫ በአቅራቢያቸው ወይም ሰፈራቸው ወዳለ መስጂድ አያዞሩም።ይህ ቢሆን ሁሉም ወደ ሰፈሩና መንደሩ ወዳሉ መስጂዶች አቅጣጫ ዞሮ ስለሚሰግድ የአቅጣጫ፥ የመስመርና የአካሄድ ልዩነት ሊከሰት ይችል ነበር።
ኢስላም የአንድነት ሃይማኖት በመሆኑ ሙስሊሞች በጋራም ሆኑ በተናጥል ሰላትን ሲሰግዱ ወደ ተመሳሳይ አቅጣጫ ዞረው መስገድ እንዳለባቸው ደንግጓል። ይህ የአቅጣጫ አንድነት በሕይወት ካሉት ጋር ብቻ ሳይሆን ወደ ቀጣዩ ዓለም ከተሻገሩ የነቢዩ ሙሐመድ(ሰ. ዐ .ወ) ተከታይ ሙስሊሞቸም ጋር ተመሳሳይ ነው። እነርሱም በሕይወት ሳሉ በዚያው አቅጣጫ ሲሰግዱ ነበር።እስከ እለተ ትንሳኤም በየተራ በየዘመናቱ የሚኖሩ ሙስሊሞች በዚያው አቅጣጫ ገና ይሰግዳሉ።
መስጂዶችም ሲሰሩ ይህንኑ የሰላት የቂብላ አቅጣጫን ጠብቀው ነው።በመስጂዶች ዉስጥ ሲሰገድም መስጊዱ የትም ይሁን የት የሚሰገድባቸው ወደ ተመሳሳይ የሰላት አቅጣጫ ተኩኖ ነው።ነቢዩ ሙሐመድ(ሰላምና ሰላት በርሳቸው ላይ ይሁንና) ነቢዩ ኢብራሂም ወደ ሰሩት መስጂድ (ካዕባ) ሙስሊሞች ዞረው እንዲሰግዱ መደረጉን ይወዱ ይወዱና ይመኙ ነበር።እየሰገዱም ይህንን ከአላህ ይከጅሉ ነበር።ይህ አላህ(ሱ.ወ) እንዲህ በማለት ነቢዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) እና ተከታዮቻቸውን በቁርኣን ያዘዘው ነው፦
قَدْ نَرَىٰ تَقَلُّبَ وَجْهِكَ فِى ٱلسَّمَآءِ فَلَنُوَلِّيَنَّكَ قِبْلَةً تَرْضَىٰهَا فَوَلِّ وَجْهَكَشَطْرَ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ وَحَيْثُ مَا كُنتُمْ فَوَلُّوا۟ وُجُوهَكُمْ شَطْرَهُۥ
«የፊትህን ወደ ሰማይ መገላበጥ በእርግጥ እናያለን።ወደ ምትወዳትም ቂብላ እናዞርሃለን።ስለዚህ ፊትህን ወደ ተከበረው መስጊድ(ወደ ካዕባ) አቅጣጫ አዙር።የትም ስፍራ ብትሆኑም(ስትሰግዱ) ፊቶቻችሁን ወደርሱ አቅጣጫ አዙሩ።»(አል-በቀራህ፡144)
ሙስሊሞች በመስጊድ ብቻ ሳይሆን የትም ስፍራ በየትኛውም ሰዓት ለጉዞ በወጡበትም ጭምር ሰላት ሲሰግዱ ሁሉም ወደ አንድ አቅጣጫ ዞረው እንዲሰግዱ ነው የታዘዙት።ያም አቅጣጫ ነቢዩ ኢብራሂም(ዐሰ) የገነቡት በመካ የሚገኘው የተከበረውና ወደተከለለው መሰጂድ (መስጂደል ሀራም) ወይም የካዕባ አቅጣጫ ነው። እንዲህ በማለትም ሙሰሊሞችን አዟል፦
وَمِنْ حَيْثُ خَرَجْتَ فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ وَحَيْثُ مَا كُنتُمْفَوَلُّوا۟ وُجُوهَكُمْ شَطْرَهُۥ
«ከየትም ከወጣህበት ስፍራ ፊትህን ወደ ተከለለው መስጊድ አቅጣጫ አዙር።»(አል-በቀራህ፡150)
ሰላትን ለመስገድ ብቻ ሳይሆን በየትም ስፍራና ሁኔታ ስንጓዝ የጉዟችን አቅጣጫን ማወቅ እጅግ ወሳኝ ነው።በተለይ በዚህ ዘመን ኮመፓስ፥ ጂፒኤስና ሌሎች አቅጣጫ ጠቋሚ መሣሪያዎች ባልነበሩበት ጊዜ ሁሉም ሙስሊም በያለበት በቀላሉ የተለያዩ አቅጣጫዎችን የሚያውቅበትን መንገድ መኖሩ እጅግ አስፈላጊ ነው።አላህ(ሱ.ወ) በቀንም ሆነ በጨለማ ዉስጥ፥ በየብስም ሆነ በባህር ጉዞ ላይ ሳለን የምንፈልገውን አቅጣጫ እንድናውቅ ከዋክብትን እንዳገራልን እንዲህ በማለት ይገልጽልናል፦
وَهُوَ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلنُّجُومَ لِتَهْتَدُوا۟ بِهَا فِى ظُلُمَـٰتِ ٱلْبَرِّ وَٱلْبَحْرِ قَدْفَصَّلْنَا ٱلْـَٔايَـٰتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ
«እርሱም ያ ከዋክብትን በየብስና በባሕር ጨለማዎች ዉስጥ በእርሷ ትመሩ ዘንድ ለእናንተ ያደረገ ነው።»(አል-አንዓም፡97)
በሌላ ምዕራፍ ላይም በከዋክብት ስለሚመሩ ሰዎች እንዲህ ብሏል፦
وَعَلَـٰمَـٰتٍ وَبِٱلنَّجْمِ هُمْ يَهْتَدُونَ
«ምልክቶችንም(አደረገ)።በከዋክብትም እነሱ ይምመራሉ።»(አል-ነሕል፡16)
በጥቅሉ ፀሐይ፥ጨረቃና ከዋክብት ጊዜንና አቅጣጫን ከማወቅ ባሻገር ለሰው ልጆች የተለያዩ ጥቅሞች እንዲሰጡ አድርጎ አላህ ለሰው ልጆች አግርቷቸዋል።ስለፀሐይ፥ጨረቃና ከዋክብት እውቀት ያካበተ ሰው የፈጣሪያችንን የአላህን ተዓምራቶችን መረዳት አያዳግተውም። አላህ(ሰዉ) እንዲህ በማለት ይህንኑ ሀሳብ ይጠቅሳል፦
وَسَخَّرَ لَكُمُ ٱلَّيْلَ وَٱلنَّهَارَ وَٱلشَّمْسَ وَٱلْقَمَرَ وَٱلنُّجُومُ مُسَخَّرَٰتٌۢبِأَمْرِهِۦٓ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَـٰتٍ لِّقَوْمٍ يَعْقِلُونَ
«ለእናንተም ሌሊትንና ቀንን፥ ፀሐይንና ጨረቃን፥ ገራላችሁ።ከዋክብትም በፈቃዱ የተገሩ ናቸው።በዚህ ዉስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምራቶች አልሉ።»(አል-ነህል፡12)
ቁርኣን ለጊዜ፥ዘመን አቆጣጠር፥ ሒሳብና አቅጣጫን ለማወቅ ሙስሊሞችን ማነሳሳቱ በተለይ ከፀሐይ፥ከጨረቃና ከከዋክበት ጋር አጣምሮ መጥቀሱ ሙስሊሞች ከጊዜ፥ ከዋክብትና ጠፈር ጋር ልዩ ምርምር እንዲያደርጉ ገፊ ምክንያት መሆን ችሏል። ይህም በኢስላማዊ ስልጣኔ ዘመናት ሙስሊሞች ከሌሎች በላቀ ሁኔታ ስለ ስነ-ፈለክ፥ ስለመልከዓ ምድር፥ አቅጣጫዎች፥ ካርታዎች፥ ስለ ፍጠረተ ዓለም፥ ስለ-ሒሳብና ሌሎች በርካታ የሳይንስ ዘርፎች ገንነው መታወቅ ችለዋል።የሰላት ሰዓትን ለሁሉም ሙስሊም ለማሳወቅ የተደረገ ጥረት የጊዜ መቁጠሪያ ሰዓትን ሙስሊሞች እንዲፈጥሩም አድርጓቸዋል።ለአሁኑ በዚሁ ላብቃ። በቀጣይ ክፍል ደግሞ አላህ ካገራልን ስለኢስላማዊ የዘመን አቆጣጠር(የሒጅራ ዘመን አቆጣጠር) አብረን አንመለከታለን።

በምስሉ ላይ የሚታየው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 2 አአ B52179 ፒን ካፕ (ሲንግል ገቢና) ሃይሉክስ D4D መኪና ዓለምገና ኬንቴሪ አዲስ ሰፈር ከቆመበት ጊቢ ውሰጥ በቀን 29/10/2016 ለሊት ላይ ተሰርቆብናል።በጥበቃ ላይ የነበረው ግለሰብም በተጠቀሰው ቀን ከምሽቱ 1:00 ላይ በቦታው የነበረ ሲሆን ዛሬ እሁድ 30/10/2016 ላይ ስልኩን ዘግቶ ተሰውሯል።ስለዚህ ይህን መኪና ያያችሁ ከታች በተጠቀሱት የስልክ ቁጥሮች እንድታሳውቁን በአላህ ስም እንጠይቃለን።
0911179220
0919965732
0911179220
0919965732