Telegram Web Link
ውሃ

ውሃ ለሕይወት አስፈላጊ ነው። በርካታ ዓለም አቀፍ መመሪያዎች አንድ ሴት በቀን ሁለት ሊትር፣ ወንድ ደግሞ 2.5 ሊትር ውሃ ቢጠጣ ለጤና መልካም መሆኑን ይመክራሉ።

ብዙዎቻችን ፕሮቲን፣ ቫይታሚን፣ ካርቦሃይድሬት እና ፋይበር ላይ እናተኩራለን። ውሃን በሕይወታችን ውስጥ እንደ ጠቃሚ ንጥረ ነገር አድርገን አናስብም።

ውሃ በሁሉም የሰውነታችን ተግባራት ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የሃርቫርድ የሕክምና ትምህርት ቤት የውሃን አንዳንድ ቁልፍ ሚናዎች እንደሚከተለው ዘርዝሯል።

በሰውነታችን ውስጥ የውሃ ወሳኝ ሚና፤

• ንጥረ-ነገሮችን እና ኦክስጂንን ወደ ሴሎች ማጓጓዝ
• ከሽንት ከረጢት ውስጥ ባክቴሪያዎችን ማስወገድ
• የምግብ መፈጨትን መርዳት
• የሆድ ድርቀትን መከላከል
• የደም ግፊትን መደበኛ ማድረግ
• መገጣጠሚያዎችን ማለስለስ
• የአካል ብልቶችን እና ጡንቻዎችን መከላከል
• የሰውነት ሙቀትን መቆጣጠር
• የኤሌክትሮላይት (ሶዲየም) ሚዛንን መጠበቅ
በዓለማችን ታዋቂ ከሆኑ የመረጃ መለዋወጫ መተግበሪያዎች አንዱ የሆነው ቴሌግራም መስራች እና ኃላፊ ፓቬል ዱሮቭ ለወለዳቸው 100 ልጆች 13.9 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሃብቱን ሊያወርስ እንደሆነ አስታወቀ።
እነዚህ መቶ ልጆች የተወለዱት ከ15 ዓመት በፊት ለአንድ ክሊኒክ በለገሰው ስፐርም አማካኝነት መሆኑን ተናግሯል።😱ወይ ቴሌግራም😂
በአውሮፓ አቆጣጠር በ2015 ቱርካዊው የእግር ኳስ ተጫዋች ዴሚር ቤይ በጀርመናዊቷ ዳኛ በቀይ ካርድ ከሜዳ ይወጣል ምክንያቱም ከሜዳው ሲወጣ ለሴቷ ዳኛ

🗣️| ኩሽና ውስጥ ነው መሆን  ያለብሽ በማለት ይናገሯታል

ሴቷ ዳኛዋ በሪፖርቷ ላይ የተናገራትን የፃፈች ሲሆን በዚህም መሰረት ፊፋ ዴሚርቤይን ከ5 ጨዋታዎች ቅጣት በተጨማሪ የሴቶችን እግር ኳስ ጨዋታን እንዲዳኝ የቅጣት ውሳኔ ይተላለፍበታል።

ዴሚር ቤይ የሴቶችን ጨዋታ ሲመራ 8 ሴት ተጨዋቾችን በቀይ ካርድ ያስወጣቸዋል።

ለምን ይህን እንዳደረገ ሲጠየቅ፡-

🗣| ምክንያቱም ሴቶች በኩሽና ነው ውስጥ መሆን ያለባቸው በማለት በድጋሚ ግትርነቱ አሳይቷል😁
"ጀግናው 💪

የዛሬው ምስል ነው!

ጀግናው ልጇ ለትምህርቱ ክሰል ሸጣ ለለፋችለት እናቱ ያሳየው ክብርና ምስጋና ድንቅ ነው።

ይሄ ነው እውነተኛ ፍቅር! በክሰል ሽያጭ ልጇን አስተምራ ለዚህ ያበቃች እናት፣ በምርቃቱ ቀን ደግሞ ክሰል በመሸከም የእናቱን ውለታ በአደባባይ ያመሰገነ ምርጥ ልጅ!

እንኳን ደስ አላችሁ!
እናትህን እንዲህ በክብር እንድታኖር ያደረገህ
ፈጣሪ ይመስገን
!

ብድር መላሽ ያድርግህ!

🙏🙏🙏❤️❤️❤️

ጉርሻ
ፌቨን ጉርጂ ትባላለች።በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በባህርዳር ዩንቨርስቲ ብቻ በተሰጠው ሳይበር ሰኪዩሪቲ ዲፓርትመንት ተማሪ ስትሆን ከ 53 ኮርሶች 42 A+ የሰራች ጀግና ሴት💪
የቀራት ሺልማት ደግሞ የለም።

ከሴቶች ትልቅ ነጥብ በማምጣት ሜዳሊያ ተሸላሚ።
ከዲፓርትመንቷ ትልቁን ነጥብ በማምጣት ሜዳልያ ተሸላሚ እና ከግቢው ትልቁን ነጥብ በማምጣት የዋንጫ ተሼላሚ ናት።

በእውነት እንኳን ደስ አለሽ።
ዛሬ የተመረቃችሁ በሙሉም ከዚህ ለመድረስ ስንት መከራ አይታችኋል እና እንኳን ደስ አላችሁ🙏
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿ቡካዮ ሳካ፡ " አያቴ (ቡካዮ የሚለውን ስም) ያወጣችልኝ ከትርጉሙ የተነሳ ነው። ትርጉሙም "ፈጣሪ በሕይወቴ ላይ ደስታን ጨመረልኝ" ማለት ነው። አያቴ በቤተሰቡ ላይ ደስታን እንድጨምር ፈለገች።"
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሩሲያ ቡርኪናፋሶን የኒኩሊየር ባለቤት ልታደርግ ነዉ !

| ሩሲያ ቡርኪናፋሶውን የኒውክሌር ሀይል ተጠቃሚ ለማድረግ
የሚያስችል ፕሮጀክት ለመስራት መስማማቷ ተነገረ ።

እንደ ዘገባዉ ከሆነ ቡርኪናፋሶ የኒውክሌር ሃይል ለማግኘት በምታደርገው ጥረት ለማሳካት የኒውክሌር ሀይል ማመንጫ ባለቤት መሆን የሚያስችላትን ታሪካዊ ስምምነት የመጨረሻውን አስተዳደራዊ ሰነድ ከሩሲያ ጋር በይፋ ተፈራርማለች።

የምዕራባውያን አጋሮች እየራቀች ከሩሲያ ጋር የነበራት ግንኙነት እያሳደገች የምትገኘው ቡርኪናፋሶ ለሰላማዊ ዓላማ የኃይል አቅምን እና ደህንነትን ለማሳደግ ከሩሲያ ጋር የኒውክሌር ግንባታ ስምምነትን አጠናቀቀች። ተብሏል።

የቡርኪናፋሶ የኢነርጂ ሚኒስትር ያኮባ ዛብሬ ከሩሲያ የመገናኛ ብዙሃን ምንጭ ስፑትኒክ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለፁት ከሆነ ከዓለም አነስተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ካላቸው አገሮች አንዷ የሆነችው ቡርኪና ፋሶ፣ የኒውክሌር ኃይልን በመጠቀም የኃይል አቅም ለመጨመር እና የኢነርጂ ደህንነትን ለማሻሻል እየጨመረ ያለውን የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ሀይል ፍላጎት ለማሟላት በማሰብ ከሩሲያው መንግሥታዊው የአቶሚክ ኢነርጂ ጋር ኒኩለርን ሰላማዊ አላማ ለማዋል ግንባታ ለመጀመር የመጨረሻዉን ስምምነት ተፈራርመናል ። ይህም የኑክሌር መሠረተ ልማት ግንባታ ላይ በሁለቱ አገሮች መካከል ሰፊ ትብብር እንዲኖር መንገድ ይከፍታል። ብለዋል ።

"ፊርማው ለቡርኪና ፋሶ አዲስ ተስፋን የሚከፍት ሲሆን መከተል የነበረባቸውን በርካታ እርምጃዎች መጨረሻ ያሳያል” ሲል ጎባ ተናግሯል።

ስምምነቱ ከሩሲያው ሮሳቶም ጋር በመተባበር የሚተገበር ሲሆን የኒውክሌር መሠረተ ልማት ግንባታን ማሰልጠንና ዩራኒየም ማበልፀግን እንደሚያካትት ከ ዘጋርዲያን ያገኘነው መረጃ ያሳያል ።

ከአሁን በፊት በተመሳሳይ ከማሊ ጋር መሰል ስምምነት ያደረገች ሲሆን ቡርኪናፋሶ እና ማሊ ከሩሲያ ጋር ያደረጉት የኑክሌር ስምምነት በሩሲያ እና በምዕራብ አፍሪካ ሀገር መካከል ባለው ትልቅ የኑክሌር ትብብር ማዕቀፍ ውስጥ የመጨረሻው አስተዳደራዊ ደረጃ ማሳያም ተደርጎ ተወስዷል ።

ጎባ ከስፑትኒክ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ "ቀደም ሲል እንዳልኩት ይህ በጣም ጠቃሚ እርምጃ ነው፣ ምክንያቱም እነዚህ ሁለቱ ሀገራት ተባብረው በትብብር ለመስራት እና በትብብር ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት በማሳየታቸው የኤሌክትሮኑክሌር መርሃ ግብር በቡርኪናፋሶ እውን ይሆናል" ብሏል።

በቡርኪናፋሶ ሊገነባ የሚችለው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ሀገሪቱ የኢነርጂ መሠረተ ልማቷን ለማጎልበት እና የኢኮኖሚ ዕድገቷን ለማሳደግ በምታደርገው ጥረት ውስጥ እንደ ወሳኝ ልማትና የክሬምሊን የኑክሌር ዲፕሎማሲ አካል ነው የተባለ ሲሆን ሩሲያ በበኩሏ "የኑክሌር ፕሮጄክቱ ሀገራት ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት የኢነርጂ ደህንነትን እንዴት ማረጋገጥ እንደሚቻል በሚመለከቱበት ወሳኝ ወቅት ላይ ነው" ማለቷን ስፑትኒክ ዘግቧል ።

#yeneta_tube
ዛሬ የተመረቃችሁ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ⚡️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ከሚከተሉት ምስሎች አንዱ ትክክለኛ ፎቶ ሲሆን ሶስቱ በAI የተሰሩ ምስሎች ናቸው። ትክክለኛውን ፎቶ ቁጥር ኮሜንት ላይ አስቀምጡ ዳይ!😀
አሜሪካና እንግሊዝ ኢራቅን ለነዳጅና ለሀብቷ ሲሉ ለመውረር ባሰፈሰፉበት ወቅት ላይ በ 2003 ጃንዋሪ 27 በወቅቱ የአለም አቀፉ አቶሚክ ኤነርጂ ሀላፊ የነበሩት መሀመድ አል ባራዲ ፡ እውነታው እናንተ እንደምትሉት አይደለም አሉ ።
.......
ኢራቅ ለሰላማዊ ግልጋሎት የገነባችውን ፡ የአቶሚክ መሰረተ ልማት በሚገና ፈትሸናል ። ግን ኒውክሊየርን ለጦር መሳሪያነት ለመጠቀም እንደተዘጋጀች የሚያሳይ አንድም ማረጋገጫ አላገኘንም ሲሉ ተናገሩ ።
....
ሆኖም የአቶሚክ ሀላፊው ማረጋገጫ ሰሚ አጣ ።
.....
ከ 18 ቀናት በኋላ በፌብሪዋሪ 14. . የአቶሚክ ሀላፊው በድጋሚ ኢራቅ እናንተ እንደምትሉት ለአለም ስጋት አይደለችም ፡ ምንም አይነት የኒውክሊየር ጦር መሳሪያ እየሰራች አይደለም ሲሉ ተናገሩ ።
....
ኢራቅን ለመውረር አንዴ ቆርጠው የተነሱት አሜሪካና አጋሮቿ ግን በድጋሚ የተሰጣቸውን ማረጋገጫ ከመስማት ይልቅ ፡ ኢራቅን ለመውረር መዘጋጀታቸውን ቀጠሉ ።
......
የአቶሚክ ሀላፊው መሀመድ አልባራዲ ሰሚ ያጣውን የኤጀንሲውን ማረጋገጫ እንደገና ከ23 ቀናት በኋላ በማርች 7 ለሶስተኛ ጊዜ ተናገሩ ።
እባካችሁ የእኛን ቃል ስሙ ፡ ኢራቅ ምንም አይነት የኒውክሊየር መሳሪያ እየሰራች አይደለም በማለት ሰሚ ያጣውን ጩኸታቸውን አሰሙ ። ሆኖም ይህ ምስክርነት በአሜሪካና እንግሊዝ መንግስታት ውድቅ ሆነ
......
ይህ የመጨረሻው የመሀመድ አልባራዲ ምስክርነት በተሰማ በ13 ኛው ቀን በማርች 20 /2003 ኢራቅ ምንም አይነት አውዳሚ መሳሪያ እንደሌላት የተነገረውን ማረጋገጫ ችላ ብለው የኢራቅ ከተሞችን በቦንብ መደብደብ ጀመሩ ጥንታዊ ስልጣኔ ከዘመናዊው ጋር አጣምራ ውብ የሆነችውን ባግዳድን ጨምሮ ፉልጃ ፡ ባስራ ፡ ሞሱል ፡ ራማዲ ፡ ቲክሪት ፡ ነጃፍ ፡ ካራባላና ፡ ኪርኩክ የሚባሉት ከተሞችን ጨምሮ ፡ አብዛኛው የኢራቅ ምድር ፡ በአሜሪካና እንግሊዝ አዝማችነት ፡ ከሰማይ በሚዘንብ ቦንብ ታረሱ ፡ ሀያላኑ ሀገራት 29 ሺህ 199 ጊዜ እየተመላለሱ ኢራቅን በአውሮፕላን ደበደቡ ።

26 ሚሊዮን ኪሎ የሚገመት ቦንብ የወረደባት ኢራቅ በአሳዛኝ ሁኔታ ወደመች ።
መቶ ሺህ ዜጎቿ ሞቱባት ።
......
ኢራቅ እንዳልነበር ሆነች ።
......
መሪዋ የነበሩትን አዛውንቱን ሳዳም ሁሴንን ፡ ለዛውም በበአል ቀን ፡ የአረፋ እለት በገመድ ሰቅለው ገደሏቸው ።
........
ይህ ከሆነ ከአመታት በኋላ ጆርጅ ቡሽ ብቅ ብሎ ፡ ኢራቅ የኒውክሊየር መሳሪያ እንዳላት የደረሰን መረጃ የተሳሳተ ነበር ሲል ቀለል አድርጎ ተናገረ ።
....
በወቅቱ የእንግሊዝ ጠ/ሚኒስትር የነበረው ቶኒ ብሌየርም ፡ የተሳሳተ መረጃ ተቀብለው በኢራቅ ላይ ስለተወሰደው እርምጃ ሲያስብ ፀፀት እና ሀዘን ይሰማኛል አለ ።
.....
ይህ ከሆነ አመታት አለፈ. .. ያቺ cradle of civilization ትባል የነበረችው ኢራቅ ብዙ አመታትን ወደኋላ ተመለሰች ።
እስከዛሬም ድረስ ከህመሟ አላገገመችም ።
.....
እንግዲህ ይህን ሁሉ ያደረጉ ሀገራት ዛሬም ኢራንን ሊበሉዋት ከበዋት ቆመዋል ።
የአለም አቀፉ አቶሚክ ኤነርጂ ሀላፊም ኢራን እንደምትሉት የአቶሚክ ቦምብ እየሰራች አይደለም ሲሉ ደጋግመው እየተናገሩ ነው ።
ግን ማንም ሊሰማቸው አይፈቅድም

አለም እንዲህ ነች ።
"ግድባችን በህዝባችን ገንዘብ እንጂ በውጭ እርዳታ አልተሰራም" ሲሉ የውሀ እና ኢነርጂ ሚንስትር ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ ለትራምፕ ጽሑፍ ምላሽ የሚሆን በማህበራዊ ገጻቸው ላይ አስፍሯል።
"ገንዘብ የለኝም ብለክ አትዘን
ማዘን ብቻ በቂ አይደለም
  ለቅሶም ጨምርበትና ወጥረክ ስራ 😂🤣"

👍የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ😁
🙊ጣልያናዊ ዜግነት ያለው ሰርጂዮ ቦዲኒ ከ 115 የተለያዩ ሀገራት 1 ሺህ 444 የተለያየ ይዘት ያላቸውን ጋዜጦች በመሰብሰብ ስሙን በአለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ማስፈር ችሏል፡፡እንደ ቦዲኒ ገለፃ ጋዜጦችን መሰብሰብ የጀመረው ገና የ 10 አመት ታዳጊ እያለ ነበረ!!!😱
‹‹የድመት ሰው እሸቴ››
(The Cat Man Eshete) የተሰኘ አዲስ ዘጋቢ ፊልም

የዓለም የስደተኞች ቀን ምክንያት በማድረግ በኒውዮርክ ከተማ ለተፈናቀሉ ድመቶች የሚሆን ጊዜያዊ መጠለያ ያቀረበውን ኢትዮጵያዊ ስደተኛ እሸቴ እና ይህን ስራ እንዲሰራ ያደረገውን ሙሉ ታሪክ የሚያሳይ ዶክመንተሪ ፊልም ለዕይታ በቅቷል።

ይህም በአካዳሚ ሽልማት በእጩነት በተመረጠችው የፊልም ባለሙያዋ ላውራ ቼክዌይ የተሰራ ‹‹የድመት ሰው እሸቴ›› (The Cat Man Eshete) የተሰኘ አዲስ ዘጋቢ ፊልም ነው፡፡

"አንዳንድ ሰዎች ግድ የላቸውም። ቤት የለሽ ህይወትን ለማሸነፍ የምጥር ጎበዝ አድርገው ነው እኔን የሚያዩኝ" ሲል እሸቴ በዚህ ዶክመንተሪ ላይ ተናግሯል።

ኢትዮጵያዊው ስደተኛ እሸቴ በ1974 የጀመረውን የእርስ በርስ ጦርነት ሸሽቶ ከጎንደር ወደ ሱዳን የሄደ በመጨረሻም ወደ አሜሪካ አቀና ሰው ነው።

ይህ ዘጋቢ ፊልም ግን ስለ እሸቴ መሰደድ ብቻ ሳይሆን ምንም እንኳን እሼቴ በመኖሪያ ቤት እጦት ሲሰቃይ ቢቆይም፤ እሱ ተፈናቃይ ሆኖ ሳለ ለተፈናቀሉ ድመቶች ጊዜያዊ መጠለያን በመስራት ማሳደጉ የኢትዮጵያዊነትንና የሰው መሆንን ትርጉም በጉልህ ያሳያል፡፡

ከ10 ዓመታት በላይ ሲንከባከባቸው የቆዩት የእሸቴ ድመቶች፣ በህዝብ ስምና እሱ በሚያደንቃቸው ወይም በሚወዳቸው ቦታዎች እና ሀገራት ነው የተሰየሙት።

ከዚህም ውስጥ በአልበርት አንስታይል ስም የተሰየመ ድመት አለው፡፡ እሸቴ የመኖሪያ ቤት ድጎማ ቢኖረውም የድመቶቹን ደህንነት ለማረጋገጥ ሲል አብሯቸው ብዙ ቀናትን በጎዳና ላይ ያሳልፋል።

የፊልም ባለሙያዋ ላውራ ቼክዌይ፤ በዶክመንተሪው እሸቴ ዓለም ውስጥ የገቡት በራሱ ዓይን እና በራሱ አንደበት የመረጠውን ታሪክ በማካፈሉ እንደሆነ አንስታለች።

ፊልሙን ሰርቶ ማጠናቀቅ ቀላል እንዳልነበር የምትናገረው ላውራ ቼክዌይ፤ ቀረጻ በሚደርግበት ወቅት እሸቴ ሞባይል ስላልነበረው በስፍራው መኖሩን በእግር እየሄደች ስታረጋግጥ እንደነበር ተናግራለች፡፡

ለእሸቴ ደግሞ ታሪኩን በዓለም ላይ ማውጣቱ በጣም የተደሰተበት ጉዳይ ነው።

"ይህ አንዳንድ የህይወቴንና የስደት ጉዞዬን ያሳያል። በዚህም ለምወዳቸው ድመቶቼ እና ለምወዳት ውብ እናት ሀገሬ ኢትዮጵያ ያለኝን ፍቅር ለመግለጽ እድል አግኝቻለሁ" ሲል ለኦኬይ አፍሪካ ተናግሯል።

ሁሉም ከፍቅር የመነጨ እንደሆነና የልጅነት ጊዜውም በፍቅር እና ደስታ የተሞላ መሆኑን ይገልፃል።

በልጅነቱ ጎረቤቶቹ ሁሉንም ነገር ተሳስቦና እስከ ቁራሽ እንጀራ ድረስ ተካፍለው ሲበሉ እንደነበር ያስታውሳል።

ድመቶቹን አሰባስቦ የመንከባከብ ስሜቱም የመጣው ከዚህ ነው፡፡
“መንከባከብ ተፈጥሮዬ ነው፤ ይህንን ደግሞ እናቴም ታውቃለች፣ እኔ ስለ ሌሎች መስዋዕትነት እከፍላለሁ ቤተሰቦቼ ተፈጥሮዬን በትክክል ያውቃሉ። ይህ መቼም አይለወጥም“ ሲል ገልጹዋል፡፡

እሸቴ በሱዳን የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ለአምስት ዓመታት ኖሯል፤ በዚህ ጊዜ በተስፋ ማጣት እና በቤተሰብ ናፍቆት ብዙ ጨለማ ቀናትን አሳልፏል።

እሸቴ የስደት ጉዞውን ለመግለጽ የተጠቀመው ቃል “የምድር ላይ ሲኦል” የሚለውን ነው። እያንዳንዱ ሰከንድ አደገኛና በማንኛውም ጊዜ ምን ሊፈጠር እንደሚችል እንደማይታወቅ ገልጿል።
ከሰሞኑ በህንድ ሀገር የሚገኝ አንድ የተኩላ እና ልዩ የሆነ የካውሺያን ሼፐርድ ድቅያ የሆነውን ውሻ በዓለማችን ውድ በሆነ ዋጋ ተሸጧል።

ይህን ውሻ የገዛው ሰው ውሻ የሚያረባ እና በዓለም ላይ ከሚገኙ ብርቅዬ ከ150 በላይ ውሻዎችን በመሰብሰብ ይታወቃል።

ሳቲሽ እንደተናገረው  ከሆነ ለዚህ ውሻ ያወጣው 5 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር እንደሚገባው ተናግሯል።

ከዚህ በተጨማሪም ይህ ውሻ አስደናቂ የሆነ ዝርያ ያለው መሆኑን እና ገና በ 8 ወሩ 75 ኪሎግራም የሚመዝን እንዲሁም  76 ሴንቲ ሜትር እንደሚረዝም ተናግሯል።

ውሻው ብዙም የሚገኝ ዓይነት ዝርያ አደለም  ያለው ባለቤቱ ስታየው ራሱ ተኩላ ነው የሚመስለው። ይህ ዝርያ ከዚህ በፊት በዓለም ላይ ተሸጦ አያውቅም ብሏል።

(Oddity centeral)
ለአንድ ውሻ ይህን ያህል ዋጋ መውጣቱ ተገቢ ነው ብለው ያስባሉ? ሀሳብዎን ቢያጋሩን👍
2025/07/05 08:34:06
Back to Top
HTML Embed Code: