Telegram Web Link
የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት ይፋ ይሆናል፡፡

የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ነጥቡ ላይ ውይይት ካደረጉ በሃላ ይፋ ይደረጋል።

የ2017 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል ሲሆን የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 10-12/2017 ዓ.ም ድረስ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 192 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለተከታታይ ሶስት ቀናት መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ ።

[የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ]

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
በአዲስ አበባ ከተማ የ2018 ዓ.ም የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ እንዲያደርጉ ከተፈቀደላቸው የግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ በጭማሪው ላይ ከስምምነት ያልደረሱ 11 በመቶ የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች ጉዳይ በአዲስ አበባ ትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን እንደሚወሰን ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላላም ሙላት (ዶ/ር) ከኢቲቪ ዳጉ ፕሮግራም ጋር የግል ትምህርት ቤቶች የአገልግሎት ክፍያ ደምብን በሚመለከት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ 1ሺህ 585 የግል ትምህርት ቤቶች መካካል ከሁለት ዓመት በፊት የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ያላደረጉ 1ሺህ 200 የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች የ2018 ዓ.ም የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ እንዲያደርጉ እንደተፈቀደላቸው ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

ጭማሪው የሚወሰነው በወላጆች እና በትምህርት ቤቱ መካከል በሚደረግ ውይይት እንደሆነ የገለጹት ኃላፊው፤ በዚህም በከተማዋ ካሉ ትምህርት ቤቶች 89 በመቶ የሚሆኑት ተወያይተው ስምምነት ላይ ስምምነት ላይ ደርሰዋል ብለዋል፡፡

ስምምነት ላይ ያልደረሱት የቀሪዎቹ ጉዳይ በአዲስ አበባ ትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን ታይቶ የሚወሰን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የከተማው አስተዳደር ካቢኔ ባፀደቀው የግል ትምህርት ቤቶች የአገልግሎት ክፍያ ደምብ መሰረት፣ ትምህርት ቤቶቹ ባላቸው ደረጃ ከ0 እስከ 65 በመቶ ባለው የክፍያ ጭማሪ ጣሪያ ከወላጆች ጋር ተወያይተው መጨመር እንደሚችሉ ጠቅሰዋል፡፡

በአዲስ አበባ እስከ 65 በመቶ የክፍያ ጭማሪ ጣሪያ የተወሰነለት ደረጃ 4 ላይ የሚገኝ አንድ የሁለተኛ ደረጃ ትመህርት ቤት ብቻ ነው ሲሉም አያይዘው ተናግረዋል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ATC NEWS
የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት ይፋ ይሆናል፡፡ የ2017 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ነጥቡ ላይ ውይይት ካደረጉ በሃላ ይፋ ይደረጋል። የ2017 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ…
" ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://aa6.ministry.et/#/result
ወይም በ @emacs_ministry_result_qmt_bot ላይ መመልከት ይችላሉ " - ትምህርት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ የ2017 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 95 % ያህሉ 50% እና ከዛ በላይ በማምጣት ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።

በ2017 ዓ.ም ፈተናውን ከወሰዱ 79,034 ተማሪዎች መካከል 75,085 ተማሪዎች ማለትም 95 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች 50% እና በላይ አስመዝግበው ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን ገልጸዋል።

ዘንድሮው በከተማ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች መካከል ከ1 እስከ 4 የሚሆኑት ከመንግስት ትምህርት ቤቶች መሆናቸው አመልክተዋል።

" በግልና በመንግስት ትምህርት ቤቶች መካከል ያለዉን የውጤት ልዩነት እጅግ እየተቀራረበ መጥቷል " ሲሉ ገልጸዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ተብሏል።

LINK ፦ https://aa6.ministry.et/#/result

Telegram Bot : @emacs_ministry_result_qmt_bot


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
እስከ ሰኔ 30 ብቻ በሶስቱም ቅርንጫፎቻችን ( መገናኛ፣ ሜክሲኮና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸዉ  ስልጠናዎች በ Advanced level እና 90% practical በሆነ ካሪኩለም እንዲሁም ዘመኑ ያፈራቸዉን ሙሉ የላብራቶሪና የስቱዲዮ እቃዎችን በማሟላት ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለዉጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!

ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕዉቅና ካለዉ ሰርተፊኬት ጋር!

እኛጋ ለመሰልጠን ኮምፕዩተር መግዛት አያስፈልግዎትም!

የብዙ አመት ልምድ እና ብቃት ባላቸዉ አሰልጣኞች!

🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe photoshop
🎯 Fullstack Web app development 
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯  Foreign & Local Languages

አድራሻ:-
1. መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 419 (ሊፍት ይጠቀሙ)  ☎️ 0991929303

2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 639 (ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929304

 3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️0991926707

Join telegram https://www.tg-me.com/topinstitutes

tiktok https://Tiktok.com/@topinstitute

Facebook https://www.facebook.com/Topinstitutes
You’re ready to work - but where’s the work?

Freelancer Academy helps you land Your First Gig and start earning. 💼

Apply now: https://www.tg-me.com/ALXFreelancerAcademy
ላለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የመጀመሪያው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ተጠናቋል።

አንደኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና የመጀመሪያ ቀን ካጋጠመው የሲስተም እና የኃይል መቆራረጥ በስተቀር በሰላም መጠናቀቁ ተሰምቷል።

በሦስቱ የፈተና ቀናት የስድስት ትምህርት አይነት ፈተናዎች በጠዋት እና ከሰዓት ፈረቃዎች ተሰጥተዋል። ተፈታኞችም ወደቤተሰቦቻቸው መመለስ ጀምረዋል።

ሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተናከነገ ጀምሮ ለሦስት ቀናት (ሐሙስ፣ አርብ እና ሰኞ) ይሰጣል።

በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይቆያል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
ከሰኔ 23 – 25/2017 ዓ/ም በበይነ መረብና በወረቀት ሲሰጥ የነበረው የአንደኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሰላምና በስኬት ተጠናቋል፡፡ ፈተናውን በወረቀት 231,761 በበይነ መረብ 43,367 በድምሩ 275,128 ተፈታኞች ወስደዋል፡፡

የመጀመሪያ ቀን የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜ ላይ ፈተናውን በበይነ መረብ ሲወስዱ በተወሰኑ የፈተና ማዕከላት ላይ በተለያየ ምክንያት የእንግሊዘኛ ፈተና ያልወሰዱ ተፈታኞች አብዛኞቹ ነገ ሐሙስ ጥዋት ከሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ጋር ያልወሰዱት ፈተና የሚሰጥ ይሆናል፡፡ በሁለተኛ ዙር ለመውሰድ ያልቻሉ ተፈታኞች ከሶስተኛውና ከአራተኛው ዙር ተፈታኞች ጋር የሚወስዱ ይሆናል፡፡ ፈተናውን በተለያዩ ዙሮች መስጠት መቻላችን በተለያዩ ችግሮች ምክንያት በተመደቡበት ዙር መፈተን ያልቻሉ ተፈታኞች በሌሎቹ ዙሮች ከሚፈተኑ ተፈታኞች ጋር መፈተን እንዲችሉ ዕድል ፈጥሯል፡፡

ስለሆነም የአንደኛው ዙር ፈተና በሰላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጋችሁ አካላት በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
You’re ready to work - but where’s the work?

Freelancer Academy helps you land Your First Gig and start earning. 💼

Apply now: https://www.tg-me.com/ALXFreelancerAcademy
እስከ ሰኔ 30 ብቻ በሶስቱም ቅርንጫፎቻችን ( መገናኛ፣ ሜክሲኮና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸዉ  ስልጠናዎች በ Advanced level እና 90% practical በሆነ ካሪኩለም እንዲሁም ዘመኑ ያፈራቸዉን ሙሉ የላብራቶሪና የስቱዲዮ እቃዎችን በማሟላት ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለዉጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!

ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕዉቅና ካለዉ ሰርተፊኬት ጋር!

እኛጋ ለመሰልጠን ኮምፕዩተር መግዛት አያስፈልግዎትም!

የብዙ አመት ልምድ እና ብቃት ባላቸዉ አሰልጣኞች!

🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe photoshop
🎯 Fullstack Web app development 
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯  Foreign & Local Languages

አድራሻ:-
1. መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 419 (ሊፍት ይጠቀሙ)  ☎️ 0991929303

2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 639 (ሊፍት ይጠቀሙ) ☎️ 0991929304

 3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️0991926707

Join telegram https://www.tg-me.com/topinstitutes

tiktok https://Tiktok.com/@topinstitute

Facebook https://www.facebook.com/Topinstitutes
ሁለተኛ ዙር የ2017 ዓ.ም ብሔራዊ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና በመላ ሀገሪቱ እየተሰጠ ነው።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በጠዋት መርሐግብር የእንግሊዝኛ ትምህርት ፈተና የወሰዱ ሲሆን፤ ከሰዓት የሒሳብ ትምህርት ፈተና ይሰጣል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈተናው በ108 የማስፈተኛ ጣቢያዎች እየተሰጠ ሲሆን፤ ዛሬ በተጀመረው ሁለተኛ ዙር ፈተና ከ13 ሺህ በላይ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናውን በበይነ መረብ በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።

በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይቆያል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
#NationalExam🇪🇹

ፆታዊ ትንኮሳ የፈፀሙ ሦስት ተማሪዎች ከሀገር አቀፍ ፈተና ታገዱ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ባለው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን ወደ መቱ ዩንቨርስቲ ከገቡት ተማሪዎች ውስጥ ሦስት ተማሪዎች በሴት ተማሪዎች ላይ ዕፆታዊ ትንኮሳ በመፈፀማቸው ከፈተናው መታገዳቸውን የመቱ ዩንቨርስቲ አስታወቀ።

ዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት አለሙ ድሳሳ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ " በርካታ ተማሪዎች ወደ ግቢ ከገቡ በኃላ ወጣ ያለ ፀባይ እያሳዩ ነበር " ብለዋል።

ዩኒቨርስቲውም ለፈተናው ከተቋቋመ ኮማንድፖስት ጋር በመሆን የመቆጣጠር ሥራ ሲሰራ እንደነበር በማንሳት፤ ሦስቱ ተማሪዎች በሴት ተማሪዎች ላይ ሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም አደባባይ ላይ ትንኮሳ መፈፀማቸውን ተበድለናል ብለው በመጡ ሴቶች ቅሬታ እና ዩንቨርስቲውም ባደረገው ማጣራትብ ድርጊቱን መፈፀማቸውን አረጋግጧል።

" ትንኮሳ አድራጊዎቹ በአደባባይ ሴቶችን በግድ መሳም፤ ልብሳቸውን መገለብ እና መንካት የማይፈቀድ የአካላቸውን ክፍል በመንካታቸው ሴቶቹ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል " ብለዋል።

በዚህ የተነሳ የትንኮሳ ወንጀል በፈፀሙ ወንዶች ላይ ከዘንድሮው አመት ፈተና እንዲታገዱ መደረጉን ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ አንዱ ከኢሉ አባቦር ዞን በቾ ወረዳ ሁለቱ ደግሞ ከምስራቅ ወለጋ የመጡ መሆናቸውን ፕረዝዳንቱ አክለዋል።

እርምጃ ከተወሰደ በኃላ በግቢው ሲስተዋል የነበረው የተማሪዎች ሥነ ምግባር መሻሻሉንም ተናግረዋል።

ወደፊትን ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠር ትምህርት ቤቶች የፈተና ሥነ ምግባር ላይ ለተማሪዎች ግንዛቤ መስጠት እንዳለባቸው የገለፁት  አለሙ ድሳሳ (ዶ/ር) ሴት ተማሪዎችም ራሳቸውን እንዲጠብቁና ለትንኮሳ ራሳቸውን እንዳይጋብዙም ጠይቀዋል።

የመቱ ዩንቨርስቲ በዘንድሮው ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከ14,000 በላይ ተማሪዎችን ለመፈተን መቀበሉንም ዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር አለሙ ድሳሳ አክለው ገልፀዋል።

#ቲክቫህ
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tg-me.com/atc_news
2025/07/05 04:51:44
Back to Top
HTML Embed Code: