Telegram Web Link
አንድ ምድራዊ ንጉሥ "ጠላቱን ያልወደደ ሰው በሞት ይቀጣል" ብሎ አዋጅ ቢያውጅ ሁሉም ሰው በአካለ ሥጋ ላለመሞት ሲል ሕጉን ለመጠበቅ የሚፋጠን አይደለምን? ወዮ! ምድራውያን ነገሥታት በሥጋዊ ሞት እንዳይቀጡን ብለን ፈርተን የሚያወጡትን ሕግ ለመፈፀም የምንፋጠን ሆነን ሳለ፥ ለነገሥታት ንጉሥ ለእግዚአብሔር ሕግ አለመታዘዛችን እንደ ምን ያለ ወቀሳ ያመጣብን ይሆን?

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
149🙏32👍1🏆1
ሰማዕት ቅድስት አርሴማ

መስከረም ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን ከቅድስት አርሴማ ከእመምኔቷ ከአጋታ ጋር ደናግል በሰማዕትነት አረፉ። ይህም እንዲህ ነው በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን እርሱ መልኳ ውብ የሆነ ብላቴና ድንግል ሊአገባ ሽቶ በየሀገሩ ሁሉ ሒደው መርጠው ያመጡለት ዘንድ አሽከሮቹን አዘዘ።

ይችንም የሚመስላት የሌለ ቅድስት አርሴማን በሮሜ አገር በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ አገኙዋት። ሥዕሏንም ሥለው ለንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ላኩለት ንጉሡም ሥዕሏን በአየ ጊዜ እጅግ ደስ አለውና ለሠርግ እንዲመጡ ወደ መኳንንቱ ላከ።

እሊያ ደናግልም ይህን ነገር በአወቁ ጊዜ ይረዳቸው ዘንድ ድንግልናቸውንም ይጠብቅ ዘንድ አልቅሰው ወደ እግዚአብሔር ለመኑ። ከዚህም በኋላ ተነሥተው በሥውር ሸሹ የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደ ሆነ ወደ አርማንያ ሀገርም ደርሰው በአንድ ቦታ ተቀመጡ ከእርሳቸውም ጋር የተሰደዱ ቁጥራቸው ሰባ አምስት የሆነ ወንዶች፣ ሴቶችም ሠላሳ ዘጠኝ የሆኑ ከእርሳቸው ጋራ አሉ። ምግባቸውን አያገኙም ነበርና በታላቅ ችግር ውስጥ ኖሩ ከእነርሱም መብራት የምትሠራ አንዲት ሴት ነበረች ከእርሷም የእጅ ሥራ ከሚገኘው በየጥቂቱ ይመገባሉ።

ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም የከበረች አርሴማን በፈለጋት ጊዜ አላገኛትም ግን በአርማንያ አገር እንዳለች ስለርሷ ሰማ። ደግሞ ለአርማንያ ንጉሥ ለድርጣድስ ስለርሷ ከዲዮቅልጥያኖስ ሸሽታ እንደ መጣች የአርሴማን ሥራ ነገሩት እርሱም አንዱን የአርማንያ መኰንን ለእኔ ጠብቃት ወደ እኔም ላካት ብሎ አዘዘው።

ደናግሉም ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ተሠወሩ ወደ ንጉሥም ወነጀሉአቸው ንጉሡም ቅዱስት አርሴማን በክብር አድርገው ያመጧት ዘንድ አዘዘ እርሷም ወደ እርሱ መምጣትን እምቢ በአለች ጊዜ እየጎተቱ ወስደው ወደርሱ አደረሷት።

የቅድስት አርሴማንም ላህይና ደም ግባቷን በአየ ጊዜ ድንግልናዋን ሊያረክስ ሽቶ እናቷ አጋታን አባብላ እሺ ታሰኝለት ዘንድ አዘዛት አጋታም ወደርሷ ሒዳ ልቧን አስጨከነች እንዲህም አለቻት። ዕወቂ ይህ ርኲስ አረሚ እንዳያረክስሽና ሰማያዊ ሙሽራሽን እንዳትተዪ እርሱም ክብር ይግባውና የእግዚአብሔር ልጅ ሕያው ክርስቶስ ነው።

ንጉሡም ይዞ ወደ እልፍኙ ሊአስገባት ከአደባባይ መካከል ተነሥቶ ድንግል አርሴማን ያዛት። በዚያንም ጊዜ በቅድስት አርሴማ ላይ የእግዚአብሔር ኃይል አደረባትና በምድር ላይ ጣለችው እርሱ ግን በጦርነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለ ነበር በታናሽ ሴት ብላቴና ስለተሸነፈ ያን ጊዜ አፈረ። ራሷንም በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጧት ከዚህም በኋላ ደናግሉን ሁሉ ከእናታቸው አጋታ ጋር ይገድሏቸው ዘንድ አዘዘ።

አንዲት የታመመች ድንግል ነበረች በዐልጋዋ ላይም እንደተኛች ወደ ወታደሮች ጮኸች መጥተውም እንደ እኅቶቿ ራሷን ቆረጡ ሁሉም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ እነዚያንም ከሮሜ አገር አብረው የመጡ ወንዶችን ገደሏቸው ቁጥራቸውም ሰባ አምስት ናቸው ሥጋቸውም በተራራ ላይ የተጣለ ሁኖ ቀረ።

ሰማዕታትም ከተገደሉ በኋላ በንጉሡ ላይ ጋኔን ተጫነበት መልኩም ተለውጦ እንደ እርያ ሆነ። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ወደርሱ መጥቶ በላዩ ጸልዮ እስከ አዳነው ድረስ ስለዚህም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ። የቅዱሳን ሰማዕታትንም ሥጋቸውን ከተጣለበት ሰብስበው በአማረ ቦታ አኖሩአቸው ያማረች ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ተሠራችላቸው። ከእነርሱም ታላላቅ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕት ቅድስት አርሴማ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(ስንክሳር ዘወርኅ መስከረም)
143🙏19😍3👍2
ቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ ተግባራትን ለመምራትም ሆነ ለማከናወን የማያስችል ምንም ዓይነት የጤና እክል ያልገጠማቸውና ከዚሁ ጋር በተያያዘም ያቀረቡት ጥያቄ የሌለ መሆኑን እንገልጻለን።

(የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት)
180🙏14👍6💔3
"ሰማዕትነት ስር ነው፡፡ ክርስቲያኖች ደግሞ ከዚኽ ስር የሚያቆጠቁጡ ምርጥ ዘሮች ናቸው፡፡ ብዙ ዛፍ የሚያቆጠቁጥበት ስር በለም አፈር ስለሚሸፈን አይታይም፡፡ ከዚያ በሚያቆጠቁጡ ዛፎች ግን ስሩ እንዴት እንደተመቸው ይታወቃል፡፡ ሰማዕታትም በግዙፉ ዓይናችን እንደምን ያለ አክሊል ሽልማት እንደተቀበሉ አይታየንም፡፡ ፍሬያቸው ግን እነርሱን መስለው እነርሱን አኽለው በሚጋደሉ ምርጥ ዘሮች ይታወቃል፡፡

ሰማዕታት አክብሩን ብለው አይናገሩም፡፡ ነገር ግን በክርስቲያኖች ልብ የሚዘሩት ፍሬ ምእመናንን በፍቅር ያስገድዳል፡፡ እነርሱን እንዲመስሉ ያሳስባል፡፡

ሰማዕታት እንደ ፍቅረኛ ናቸው፡፡ አንድ ሰው የፍቅረኛውን ስም በየአጋጣሚው ያነሣል፡፡ በዓይነ ሕሊናው ያስባል፡፡ በተለያየ መልኩ ያያል፡፡ ሰማዕታትም ለክርስቲያኖች እንደዚያ ናቸው፡፡ እጅግ የተወደዱና በፍጹም ከሕሊና የማይጠፉ ተወዳጆች ናቸው፡፡ የልጆቻችንን ስም በነርሱ ስም የምንሰይመው፣ ሥዕላቸውን ሥለን የምንተሻሸው የምንስመው ለሰማዕታቱ ያለንን ጥልቅ ፍቅር የምንገልጽበት መንገድ ስለኾነ ነው፡፡"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

የሰማዕት ቅዱስ አርሴማ ረድኤት በረከት አይለየን!
114🙏24👍2
“ልጄ ሆይ ባለ መድኃኒትን ስማ ሕማምህን ቸል አትበል” መ.ሲራክ ፴፰፥፩

በሚል መሪ ቃል የጣና ቅዱስ ቂርቆስ ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት በአይነቱ ልዩ የሆነ አጠቃላይ ሆስፒታል ለመገንባት ተነስተናል።   እርሶም ለዚህ ፕሮጀክት ከታች በተቀመጡት የባንክ አማራጮች አበርክቶ በማድረግ አሻራዎትን ያሳርፉ።

ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶች እና የእናቶች አንድነት ገዳም የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምሥክር ጉባኤ ቤት

TANA KIRKOS GEDAM 4TU G/METSAHFIT

1000680619488 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

TANA KIDUS KIRKOS YE-ABATOCH ENA YE-ENATOCH ANDNET GEDAM YE-ARATU GUBAYAT METSAHIFT MISKIR GUBAE BET
219553568 አቢሲኒያ ባንክ
2011111181981013 አባይ ባንክ
0068829811701 አሐዱ ባንክ
5020827358011 ዳሸን ባንክ

ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር
+251 982333444
+251 983333444
+251 984333444  ይደውሉ።
24🙏5
#መንፈሳዊ_ጉዞ_ወደ_አክሱም_ጽዮን
የወልድያ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል የፈለገ ሰላም ሰንበት ት/ቤት የኅዳር ጽዮን በዓልን ምክንያት በማድረግ ወደ #ርዕሰ_አድባራት_ወገዳማት_አክሱም_ጽዮን_ማርያም #መንፈሳዊ_ጉዞ አዘጋጅቷል! እርስዎም በዚህ መንፈሳዊ ጉዞ ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል!

#በጉዞዉ_የሚጎበኙ_ቅዱሳን_ቦታዎች
➛ አብርሃ ወአጽብሐ
➛ ደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ ገዳም
➛ ጽዋ ትመስክር (ማኅበረ ዶጌ)
➛ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም

#የጉዞ_መነሻ ቀን ህዳር 19/2018 ዓ.ም ሲሆን #መመለሻ ህዳር 22 /2018 ዓ.ም

#ትኬቱ_የሚገኘው
➛ በሰ/ት/ቤቱ ልማት ተቋም ሱቅ
➛ በሰ/ት/ቤቱ ጽ/ቤት
➛ አዳጎ ሀገረስብከት ሕንጻ ማኅበረ ቅዱሳን ሱቅ

#ለበለጠ_መረጃ
09-68-60-71-29
09-91-79-29-84

ሼር ይደረግ
54
ንስሐ በቅዱስ ኤፍሬም

ወንድሞቼ ሆይ! ጊዜ ሳለልን ንስሐ እንግባና ለንስሐ የሚገባ ፍሬ እናፍራ፡፡ ጌታችን ምን እንዳለ እስኪ አድምጡ፡- “ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይኾናል” /ሉቃ.15፥7/፡፡

ወንድሞቼ ሆይ! ስለምን ታድያ በኃጢአት፣ በስንፍና፣ በንዝህላል እንደተያዘዝን እንቆያለን? ስለምንድነው ተስፋ ቆርጠን የምንቆዝመው? በእኛ ንስሐ መግባት ምክንያት በሰማያት ታላቅ ደስታ የሚሆን ከሆነ ምንድነው የሚያስፈራን? ቅዱሳን መላዕክት ስለ እኛ ንስሐ እጅግ ደስ የሚላቸው ከሆነ ስለምንድነው እኛ ልል ዘሊል፣ ደንታ ቢስና ፈዛዛ የምንሆነው? የመላዕክት ጌታ ንስሐ ግቡ እያለ አስተምሮን ሳለ ምንድነው የምንፈራው? የማይከፈሉ ሦስት፣ የማይጠቀለሉ አንድ የሚሆኑ ሥላሴ ንስሐ እንገባ ዘንድ እየጠሩን ሳለ እኛ ያለምንም የንስሐ ፍሬ እንቆይ ዘንድ አግባብ ነውን?

ተወዳጆች ሆይ! በዚህ ጊዜአዊ ዓለም ርኵሰት ጣዕም አንታለል፡፡ እንዲህ ካልሆነ ግን እሳቱ የማይጠፋ ትሉ የማያንቀላፋ ምረረ ገሃነም ይጠብቀናል፡፡ ስለዚህ ከዘለዓለማዊው እሳት እንድን ዘንድ አሁን ጥቂት ብናለቅስ ይሻለናል፡፡

ተወዳጆች ሆይ! እስኪ እናስተውል፡፡ ስለምንናገረው ነገርም ችላ የሚለው ሰው ከቶ አይገኝ፡፡ ክርስቶስ ድንገት እንደ ብርሃን ብልጭታ ይመጣልና፡፡ ክርስቶስ ድንገት በመጣ ጊዜ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦም ለሁሉም እንደየሥራው ሲከፍለው ማየት አያስፈራምን? የዚያን ጊዜ ሁሉም የየራሱን ሸክም ይሸከማል፡፡እያንዳንዱ ሰው በዚህ ምድር የዘራውን ያጭዳል፡፡ ሁሉም ዕራቆቱ ይቆማል፡፡ ሁሉም ወደ ክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ይቀርባል፡፡ የዚያን ጊዜ ማንም ማንንም መርዳት አይችልም፡፡ ወንድም ወንድሙን ወይም ጓደኛ ጓደኛውን መርዳት አይችልም፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን መርዳት አይችሉም፡፡ ልጆች ወላጆቻቸውን መርዳት አይችሉም፡፡ ባሎች ሚስቶቻቸውን መርዳት አይችሉም፡፡ ሁሉም በፍርሐትና በረዐድ በመንቀጥቀጥም የእግዚአብሔርን ፍርድ ይጠብቃል እንጂ ማንም ማንንም መርዳት አይችልም፡፡

ወንድሞቼ ሆይ! ታድያ ለምንድነው ጊዜ ሳለልን የምንሰንፈው? ለምንድነው ልል ዘሊል የምንሆነው? ለምንድነው በምግባር በሃይማኖት የማንዘጋጀው? ለምንድነው ጊዜ ሳለልን የማናስተውለው? ለምንድነው ቃለ ሕይወትን ለመስማት የማንቻኰለው? ስለምንድነው ቃለ እግዚአብሔርን የማንሰማው? ስለምንድነው ቃለ ክርስቶስን ችላ የምንለው? ቃሉ በዚያ ሰዓት እንደሚፈርድብን አትገነዘቡምን? ቃለ ነቢያት ቃለ ሐዋርያት በዚያ ሰዓት እንደሚፈርድብን አታውቁምን? ካላወቃችኁ ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ ያላቸውን አድምጡ “የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል፤ እኔንም የጣለ የላከኝን ይጥላል” /ሉቃ.10፥16/፡፡ ዳግመኛም በሌላ አንቀጽ እንዲህ ብሏል፡- “የሚጥለኝ ቃሌንም የማይቀበለው እርሱ የሚፈርድበት አለው፤ እኔ የተናገርኩት ቃል ርሱ በመጨረሻው ቀን ይፈርድበታል” /ዮሐ.12፥48/፡፡ በመጨረሻው ቀን የሚፈርድብን ቃሉስ የትኛው ነው? በወንጌሉ እንዲሁም በሐዋርያትና በነቢያት አድሮ የተናገረው ቃሉ፡፡ እንኪያስ ወንድሞቼ ሆይ! ቃሉን ችላ የምንለው አንኹን፡፡ “ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም” ያለውን አንርሳው /ማቴ.24፥35/፡፡

እንኪያስ እጅግ የምወዳችሁ ሆይ! ኑ! አስፈሪው ቀን ሳይመጣ ቃሉን ሰምተን ንስሐ እንግባ፡፡ የእግዚአብሔርን ምሕረት እንቀበል፡፡ እግዚአብሔር ዛሬ ምሕረቱን እንድንቀበል እንዲህ እያለ ያበረታታናልና፡- “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ” ማቴ.11፡28፡፡ በዚህ ቃሉ ትዕግሥተኛው፣ አፍቃሪውና ሰው ወዳጁ ጌታ ሁላችንም እንድን ዘንድ ይጠራናል፡፡ የጠራው የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ አይደለም፤ “ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ” ብሎ ሁላችንም እንጂ፡፡ “ባለጸጋም ቢሆን ድኻም ቢሆን ሁሉም ወደ እኔ ይምጣ፡፡ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም፡፡ ወደ እኔ የሚመጣውስ ማን ነው ትዕዛዛቴን የሚጠብቀው፤ ቃሌን የሚሰማው፤ በላከኝም የሚያምነው፡፡” የክርስቶስን ቃል ሰምቶ ንስሐ የሚገባው ንስሐም ገብቶ የንስሐን ፍሬ የሚያፈራ ሰው ንዑድ ክቡር ነው፡፡ የማይሰማው ግን እጅግ ጐስቋላ ሰው ነው፡፡ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- “በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው” /ዕብ.10፥31/፡፡
102🙏11👍1
"ዲያብሎስ የሚያስጨንቀው የወደቁትን ሳይሆን ለመነሳት የሚታገሉትን ነው"

(ምክረ አበው)
194🙏28👍19😍4
ዘመቻ!

በዚህ የቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቴሌግራም ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን እና ሌሎች ቅዱሳን አበው ያስተማሩትን ትምህርት ወደ እናንተ እያደረስን እንገኛለን።

እርስዎም ይህ ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቻናል ለሌሎች ይደርስ ዘንድና እንዲቀላቀሉ ቤተሰብ እንዲሆኑ በተለያዩ ግሩፖችና ቻናሎች ሼር በማድረግ እና በመጋበዝ ይተባበሩ!

https://www.tg-me.com/beteafework
https://www.tg-me.com/beteafework
https://www.tg-me.com/beteafework
👍5336🙏3💯2🤩1
“ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየሐቱ
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ
አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ”

(የስሙና የሞቱ መታሰቢያ ባንቺ የተጻፈብሽ የሚያበራ ከሆነ ዕንቈ ባሕርይ ይልቅ የጠራ ወርቅ ክበብ ያለው የራስ ቊር የተባለ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ የራስ ልብስ ጌጥ ሽልማት የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ አንቺ ለእርሱ ሁሉን ታሰግጅለታለሽ (ታንበረክኪለታለሽ) እርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል።)
(አባ ጽጌ ድንግል)
132👍9🙏6🕊1
#ትመጫለሽ_አይደል?

ቤተ መቅደስሽን ከበን አለን - መቅደስ ገላችን ቢረክስም
በሕንጻ መቅደስሽ ከትመናል - ሕንጻ ሥላሴን ብናፈርስም

በልማድና በእምነት መሀል – በተወጠረ መንፈሳችን
በጎጥ በጎሳ በታጠረ - በተፍረከረከ አንድነታችን
ስቀለው ስቀለው እንጂ – ምን በድሎ? በማይል ልሳናችን

ለክፋት ባደገደገ - በጎ ግብር በራቀው
ኃጢአት ባጠራቀመ – የጽድቅ ፍኖት በናፈቀው
ነውርን መግለጥ እንጂ - ከባቴ አበሳነት በማያውቀው

በረከሰ ማንነት ነው – ንዒ ማርያም የምንልሽ
ከልዑሉ ሚካኤል ጋር ከደስተኛው ገብርኤል ጋር
ጽጌ ጸዐዳ ልጅሽን ይዘሽ
ነይ ርግባችን የምንልሽ
በሚገባን ንጽህና – ሆነን አይደለም ድንግል
ግን ነይ ስንልሽ አትቀሪም – ትመጫለሽ አይደል?

ልባችን ቂምን ቋጥሮ በአፍ ዜማ ብቻ – ብንጠራሽም ንዒ ብንልም ድንግል
ርሕርሕተ ሕሊና እመ ትሕትና – ትመጫለሽ አይደል?

ስለተጠራው ስምሽ ድንግል
ትመጫለሽ አይደል?

ስለኪዳንሽ ድንግል
ትመጫለሽ አይደል?

አልቦ ምግባር ብንሆንም - እንደ ቃና ማድጋ
ማርያም አትቅሪ እኛ ጋ

ንዒ ስንል
አዛኝቱ ድንግል
ትመጫለሽ አይደል?

(Agere Nuri )
290💔27🙏18👍9🕊7👌1😍1
እንድታውቁት
ከብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረሰብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና የቅዱስ ላልይበላ የበላይ ጠባቂ ጋር በተያያዘ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ "ብፁዕነታቸው ታግተዋል" በማለት እየተሰራጨ ያለው ወሬ ፍጹም ሀሰት ሲሆን። ብፁዕነታቸው አሁንም በመንበረ ጵጵስናቸው በሥራ ላይ ናቸው።

ኹሉም ነገር ሰላም ነው! ምንም የተፈጠረም፣ የሆነም ነገር የለም! በማንም አሉቧልታ እና የፈጠራ ድርሰት አትደናገጡ እላለሁ።
132🙏34👍13💯3😍1
ፈረስ የሚጋልብ ሰው ልጓሙን በአግባቡ ካልያዘው በቀር ፈረሱም ጋላቢውም ይጎዳሉ፡፡ አንድ እባብ የነደፈው ሰው ባለመድኃኒቶችን አግኝቶ መርዙ ወደ ሰውነቱ ኹሉ እንዳይሰራጭ ካላደረገ በቀር ወደ ሞት ሊደርስ ይችላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ አንድ ትንሽ ቁስል በጊዜው ጊዜ ካልታከሙት በቀር ሰፍቶና ተስፋፍቶ ትልቅ ቁስል ወደ መኾን ያድጋል፡፡

በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድም እንደዚህ ነው፡፡ የኃጢአት ቁስል የሚሰፋው ችላ ሲባል ነው፡፡ ገና ትንሽ ነው በሚባልበት ደረጃ ካላራቅነው በቀር ነገ ከነገ ወዲያ ትልቅ ቁስለ ነፍስ ይኾናል፡፡

ተመልከቱ! ዛሬ ላለመቈጣት የሚታገል ሰው ነገ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴን አይዘይድም፡፡ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴ ካልዘየደም ብዙ ባልንጀሮች ይኖሩታል፡፡ ብዙ ባልንጀሮች ካሉት የሚጠላቸውም የሚጠሉትም ሰዎች አይኖሩም፡፡ ባልንጀራ እንጂ ጠላት የሌለው ሰውም የምግባር ኹሉ ፍጻሜ የኾነውን ፍቅር ገንዘብ ያደርጋል፡፡

ስለዚህ ተወዳጅ ሆይ! ወደዚህ ምግባር ታድግ ዘንድ ወደዚህ እንዳታድግ የሚያደርጉህን ጥቃቅን ኃጢአቶችን ከአንተ አርቅ፡፡ ሰፍቶ ተስፋፍቶ ነገ እንዳይቸግርህ ዛሬ በእንጭጩ እያለ ችላ አትበለው፡፡

ይሁዳ ገና የገንዘብ ፍቅር ደረጃ ላይ እያለ ራሱን ቢመረምርና ይህን ለማራቅ ቢጥር ኖሮ በኋላ ከተሰበሰበው ገንዘብ ወደ መስረቅ ባላደገ ነበር፡፡ ገና ከመጀመሪያው ደረጃ እያለ ችላ ባይል ኖሮ የኃጢአት ኹሉ ራስ የኾነው ኃጢአት ወደ መፈጸም ባልደረሰ ነበር፡፡

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንደዚህ ልናደርግ እንደሚገባን ሲያስተምረን ከዝሙት ብቻ እንድርቅ ሳይኾን የእርሱ ሥር የኾነውንና አይቶ መመኘትን ችላ ልንለው እንደማይገባን ነገረን (ማቴ.5፡28)፡፡ ኃጢአት ሥር ሰዳና ሰፍታ ከመቸገራችን በፊት በችግኝ ደረጃ ላይ እያለች ነቅለን መጣል ቀላል ነውና፡፡ 

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
187🙏28💯6👍4🕊2
2025/10/19 21:01:22
Back to Top
HTML Embed Code: