#መስከረም_21
#ብዙኃን_ማርያም
በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም 21 ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው፡፡ ሁለቱንም ታሪኮች ከዚህ ቀጥለን እንመለከታቸዋለን፤
#ጉባዔ_ኒቅያ
በ325 ዓ.ም አርዮስ የሚባል መ*ና**ፍ*ቅ የእግዚአብሔር ወልድን የባሕርይ አምላክነት አልቀበልም በሚል ክህደት እርሱ ተሰናክሎ ለሌሎችም መሰናክል ኾነ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት አርዮስ ክህደቱን እንዲተው ቢመክሩትም ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይህ የአርዮስ ክህደትም በሊቃውንቱ መካከል መለያየትን ፈጥሯል፡፡ ጊዜው ታላቁ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ‹‹አብያተ ጣዖታት ይትአጸዋ አብያተ ክርስቲያናት ይትረኀዋ፤ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ! አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ!›› የሚል ዐዋጅ የነገረበት ወቅት ነበርና ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ በአር*ዮስ ክህ*ደት ምክንያት በኒቅያ የሃይማኖት ጉባኤ እንዲካሔድ በየአገሩ ላሉ ሊቃውንት መልእክት አስተላለፈ፡፡
በዚህም መሠረት ከሚያዝያ 21 ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 21 ቀን ድረስ 2348 ሊቃውንት በኒቅያ ተሰበሰቡ፡፡ ኒቅያ ለዚህ ጉባኤ የተመረጠችበት ምክንያትም ጳጳሱን ከማኅበረ ካህናቱ፤ ንጉሡን ከሠራዊቱ ጋር አጠቃላ ለመያዝ የምትችል ሰፊና ምቹ ቦታ ከመኾኗ ባሻገር ለኹሉም አማካይ ሥፍራ ስለ ነበረች ነው፡፡ በጉባኤው ከተሰበሰቡ ሊቃውንት መካከልም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙታንን ያስነሡ፣ ለምጽ ያነጹ፣ አንካሳ ያረቱ፣ የዕውራንን ዓይን ያበሩ ድውያንን የፈወሱ፣ ሌላም ልዩ ልዩ ተአምር ያደረጉ፤ እንደዚሁም ስለ ርትዕት ሃይማኖታቸው በመጋደል ዓይናቸው የፈረጠ፣ እጃቸው የተቈረጠ ይገኙበታል፡፡
ሊቃውንቱ ሱባዔ ይዘው በጸሎት ከቆዩ በኋላ ኅዳር 9 ቀን በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት፣ በእለእስክንድሮስ አፈ ጉባኤነት ጉባኤው ተጀመረ፡፡ ንጉሡ ሊቃውንቱን "ስማችሁን፣ አገራችሁንና ሃይማኖታችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ" ባላቸው ጊዜም ከ2348ቱ መካከል 318 ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን ሲገልጹ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነው "ዘዕሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ፤ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በመለኮት፣ በሥልጣን፣ በፈቃድ፣ በህልውና አንድ ነው" ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ንጉሡም "ሃይማኖት እንደ 318ቱ ሊቃውንት ይኹን" ብሎ ዐዋጅ አስነግሯል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በኦሪት ዘፍጥረት የተጠቀሱት 318ቱ የአብርሃም ብላቴኖች ምሳሌዎች ናቸው (ዘፍ.14፥14)፡፡
318ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮስን አውግዘው በመለየት "ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን" የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር 9 ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም 21 ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት "#ብዙኃን_ማርያም" እየተባለ ይጠራል፡፡ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ለሃይማኖታዊ ጉባኤ የተሳባሰቡበት ዕለት ነውና፡፡
#ዕፀ_መስቀል
በሌላ በኩል መስከረም 21 ቀን የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በአምባሰል ተራራ በግሸን ደብረ ከርቤ የገባበትና በዓሉ የከበረበት ዕለት ነው፡፡ ታሪኩም በአጭሩ የሚከተለው ነው፤
ዐፄ ዳዊት መንፈሳዊና ደግ ንጉሥ ነበሩ፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ቸነፈር ተከሥቶ ሕዝቡ ስለ ተሰቃየባቸው እጅግ አዘኑ፤ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላኩ ባሕታዊ መጥተው "የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስመጥተህ በአገርህ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አሠርተህ ብታስቀምጥ ረሃቡ፣ ቸነፈሩ ኹሉ ይታገሥልሃል" አሏቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ከብዙ ገጸ በረከት (ስጦታ) ጋር "የጌታችንን መስቀል ላኩልኝ" የሚል መልእክት አስይዘው መልእክተኞችን ወደ ኢየሩሳሌም ሰደዱ፡፡ መልእክተኞቹም በታዘዙት መሠረት መስቀሉን ይዘው መምጣታቸውን ዐፄ ዳዊት ሲሰሙ "ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት" ብለው መስቀሉን ለመቀበል ጉዞ ጀመሩ፡፡
ዐፄ ዳዊት ስናር (ሱዳን) ደርሰው ከመልእክተኞቹ ጋር ተገናኝተው መስቀሉን በክብር አጅበው ወደ መካከል ኢትዮጵያ ለማስገባት ሲነሡም ከበቅሏቸው ወድቀው ጥቅምት ፱ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ በዚህም ሠራዊታቸው ተደናግጠው የጌታችንን መስቀል እዚያው ትተው የዐፄ ዳዊትን አስከሬን ይዘው ተመለሱ፡፡ መስቀሉ በስናር ከቆየ በኋላ የዐፄ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ ሲነግሡ ወደ መሃል ኢትዮጵያ አምጥተው ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ለማስቀመጥ ቢያስቡም ምቹ ቦታ ግን ሊያገኙ አልቻሉም ነበር፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው ምቹ ቦታ ሲፈልጉ መስቀሉን በኤረር ተራራ፣ በደብረ ብርሃን፣ በመናገሻ ማርያም ዓምባ፣ በእንጦጦ ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡
መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ እግዚአብሔር አምላክ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ መስቀሉን ወደ ወሎ ሀገረ ስብከት እንዲወስዱትም አዘዛቸው፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው በእግዚአብሔር መሪነት መስቀሉን ይዘው ወሎ ሲደርሱም ጌታችን ወደ አምባሰል እያመለከተ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ" ይላቸው ነበር፤ ንጉሡ መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው በ1446 ዓ.ም የጌታችንን መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡
ከዚህ በኋላ ንጉሡ ‹‹መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!›› ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የእመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ ስለዚህም መስከረም 21 ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ ኀጢአታቸውን ለካህን ተናዘው፣ ንስሐ ገብተው በዚህ ዕለት ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ በመሔድ የሚጸልዩና የሚማጸኑ ምእመናን ኹሉ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ የምሕረት ቃል ኪዳን እንደሚያገኙም ጤፉት በተባለችው መጽሐፍ ተጠቅሷል፡፡
(በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው - #ማኅበረ_ቅዱሳን_ድረገጽ)

❤93🙏7👍3🏆3👌1
ጸጋ ክብርን የተመላሽ ቅድስት ድንግል ሆይ በጸሎትሽ ረዳትነት አምኜ ሳለሁ የማቸነፍ ጥሩር እንድለብስ የመለኮትንም ሰይፍ እንድታጠቅ አውቃለሁ፡፡
እርስ በርሳቸውም ይረዳዳሉ፡፡ የኔ ሃይማኖት ያንቺ ጸሎት የልዑል እግዚአብሔር ማዳን ዳግመኛም የኔ መታመን ያንቺ ልመና የልዑል አግዚአብሔር ይቅርታ እርስ በርሳቸው ይረዳዳሉ፡፡ እኔ ባንቺ አምኜ ሳለሁ ግዳጄን የማግኘቴ ተስፋ አንቺ ስለኔ ተግተሽ መለመንሽ እግዚአብሔርም ቸል ሳይልና ሳይነቅፍ ግዳጄን መስጠቱ እርስ በርሳቸው ይረዳዳሉ፡፡
እኔ በስምሽ እለምናለሁ አንቺም ስለኔ ትማልጃለሽ፡፡ ልጅሽም ስላንቺ የልመናዬን ዋጋ ይሰጠኛል እኔ ለፍቅርሽ ካልተጋሁ አንቺ እኔን ለማዳን አትተጊም፡፡ ልጅሽም እኔን ይቅር ለማለት አይተጋም፡፡
እኔ በስምሽ ግዳጄን ሁሉ ማግኘት እመኛለሁ፡፡ አንቺ ለኔ አማላጅ ነሽ፡፡ ልጅሽም ግዳጄን የሚሰጠኝ ነው፡፡ እኔ የተጸማሁ ነኝ፡፡ አንቺ የወርቅ መጥለቂያ ነሽ፡፡ ልጅሽም የሕይወት ውሃ አዘቅት ነው፡፡
የመለኮትን ዕንቁ ለመግዛት እኔ ነጋዴ ነኝ፡፡ አንቺ የሕይወት መርከብ ነሽ፡፡ ልጅሽም የበጎ ነገር ሁሉ ድልብ በውስጡ ያለበት የትርፍ ሥፍራ ነው፡፡
እኔ ገደሉን ለማለፍ ወደ ብርሃን ሥፍራ ለመድረስ የቸኮልሁ ነኝ፡፡ አንቺ የመድኃኒት ድልድይ ነሽ፡፡ ልጅሽም ለተገፉት መጠጊያ የተድላ ደስታ ሥፍራ ነው፡፡
እኔ የመንፈስ ቅዱስን ሀብት የምፈልግ ድሀ ነኝ፡፡ አንቺ የክብር ሁሉ መከማቻ ነሽ፡፡ ልጅሽም ለባለሟልነትና ለክብር ለማሞገስ የሽልማት ጌጽ ነው፡፡
እኔ እለምናለሁ አንቺ ጸሎቴን ታሳርጊያለሽ ልጅሽም ኃጢአቴን ያስተሠርያል፡፡ የልቤን ግዳጅ ይሰጠኛል፡፡ እኔ ቁስለኛ ነኝ አንቺ የመድኃኒት ሙዳይ ነሽ፡፡ ልጅሽም ባለ መድኃኒት ነው፡፡
እኔ ቁስለ ኃጢአቴ የሸተተ፡፡ የቅዱሳንንም መዓዛ ሽቱ የምሻ ነኝ፡፡ አንቺ ያማረ የተወደደ ሽቱ ብልቃጥ ነሽ፡፡ ልጅሽም ከሽቱ ሁሉ ይልቅ ያማረ የተወደደ የመለኮት ቅቤ ነው፡፡
እኔ የታረዝሁ የብርሃን ልብስ የምሻ ነኝ፡፡ አንቺ የሸማኔ ዕቃ ነሽ፡፡ ልጅሽም የማያልቅ የማያረጅ የሃይማኖት ልብስ ነው፡፡
በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ ድንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ! ሁልጊዜ በዓይነ ልቡናዬ አይሻለሁ በሃሳቤም በየሥፍራው ሁሉ አገኝሻለሁ በተኛሁ ጊዜ እኔን ለመጠበቅ የነቃሽ ነሽ፡፡ ከመኝታዬም ስነቃ እኔን ለማንሣት የተዘጋጀሽ ነሽ፡፡
ስቀመጥም እኔን ለመምከር ትደርሻለሽ፡፡ በቆምሁም ጊዜ በቀኜ ትቆሚያለሽ በተናገርሁም ጊዜ አንደበቴን ለማጣፈጥ ታከናውኛለሽ፡፡ በዝምታዬም ጊዜ ለመጠበቄ ማሞገሻ ነሽ ኃሴትም ባደረግሁ ጊዜ ተድላ ደስታ ነሽ፡፡
ባዘንሁም በተቆረቆርሁ ጊዜ የኃዘኔ መጽናኛ ነሽ፡፡ ባለቀስሁም ጊዜ የልቅሶዬ መተዊያ ነሽ፡፡ በዘመርሁ ጊዜ ለእጄ እንደ መሰንቆ ለጣቶቼም እንደ በገና ነሽ፡፡
በተራብሁም ጊዜ ለሆዴ ትመግቢኛለሽ በተጸማሁም ጊዜ እኔን ለማርካት የሕይወት ውሃን የተመላሽ ነሽ፡፡ የተፍገምገምሁም ጊዜ እኔን ለመደገፍ እጅሽን ትዘረጊያለሽ፡፡ በወደቅሁም ጊዜ እጅሽን ዘርግተሽ ታነሺኛለሽ፡፡
ተባሕትዎም በያዝሁ ጊዜ እኔን ለመጎብኘት አታቋርጭም፡፡ በማኅበር መካከል ወደኔ ትደርሻለሽ በደከምሁም ጊዜ ድካሜን ታበረቻለሽ፡፡ በታመምሁም ጊዜ ሥጋዬን ከሞት ታድኛለሽ፡፡ በተቸገርሁም ጊዜ ከችግሬ ታድኝኛለሽ፡፡
በተጨነቅሁም ጊዜ ጭንቄን ታርቂያለሽ፡፡ በቆሰልሁም ጊዜ ቁስሌን ታጠጊያለሽ፡፡ በርኩሰቴም ጊዜ ንጹሕ ታደርጊኛለሽ፡፡ በበደልሁም ጊዜ ኃጢአቴን ታቃልያለሽ፡፡ በደኸየሁም ጊዜ ለድህነቴ ባለጸግነት ሀብቴ ነሽ፡፡
(#አርጋኖን #በአባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ)

❤142🙏22👍5🕊4
በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ
ይድረስ ለተከፋኸው ወንድሜ መኖር ለደከመህ፣ ሕይወት ለታከተህ፣ የሚሰማህ ላጣኸው፣ የሚረዳህ ሰው ላላገኘኸው መከረኛው ወዳጄ!
ከሞት ውጪ ሌላ መፍትሔ አልታይ ካለህ የአንተ ቢጤ መከረኞቹ ጳውሎስና ሲላስ እስር ቤት ውስጥ ሆነው እንዲህ ይሉሃል። "በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ" ሐዋ. ፲፮፥፳፰ አውቃለሁ ዙሪያው ገደል ሆኖብሃል። ምነው ባልተፈጠርሁ እስክትል ድረስ ተጨንቀሃል። ግን ይህ ስሜት በአንተ አልተጀመረም።
ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ኑሮ ያልመረረው ማን አለ? መሞት ያልተመኘስ ማን አለ? ሞት ያማረህ አንተን ብቻ መሰለህ? "ስለ ምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ዓይን ሳያየኝ ምነው በሞትሁ" ያለውን ጻድቅ ኢዮብ አልሰማህም? (ኢዮ. ፲፥፲፰) "ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ" ብሎ እንዲሞት የለመነውን ኤልያስን አላየኸውም? (፩ነገሥ. ፲፱፥፬) ዮናስንስ "አሁንም፥ አቤቱ፥ ከሕይወት ሞት ይሻለኛልና እባክህ፥ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ፡ አለው" ሲል አልሰማኸውም? (ዮናስ ፬፥፫)
ወንድሜ እመነኝ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን መኖር ያላስጠላው ሰው በታሪክ ፈልገህ አታገኝም። ሞት ሞት የሸተተው ልቡ የተሰበረ ብዙ ነው። አንተ ላይ ብቻ የደረሰ ልዩ ፈተና የለም:: "ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል" ይላል መጽሐፍ:: ፩ኛ ቆሮ. ፲፥፲፫
ምናልባት የልብህን መሰበር የኀዘንህን ጥልቀት አይቶ ምቹ ጊዜ አገኘሁ ብሎ ራስህን እንድትጎዳ ሰይጣን ሊገፋፋህ ይችላል። እንዴት እንዲህ ዓይነት ሃሳብ በልቤ ሊመጣ ቻለ ብለህ አትረበሽ። ሰይጣን ይህንን ክፉ ሃሳብ ላንተ ብቻ ሳይሆን ለክርስቶስም አቅርቦለታል።
"የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር" ብሎ ክርስቶስን እንኳን [ማንነቱን ሳያውቅ] ራሱን እንዲወረውር ሊገፋፋው የሞከረ ደፋር ነው። የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው ግን ራሱን አይጎዳም። "ጌታ አምላክህን አትፈታተነው" "ሒድ አንተ ሰይጣን" ብለህ ሰይጣንን ገሥፀው። ሰይጣን ክርስቶስን "ከሕንፃ ጫፍ በመወርወር የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህን አሳይ" ሲለው ክርስቶስ ሰይጣንን ሒድልኝ ብሎ በመገሠጹ በክብር ወደ ሰማይ ዐርጎ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ።
ወንድሜ ሆይ አንተም ሰይጣንን አትስማው ሃሳቡ ራስህን ጎድተህ ከፈጣሪህ እንድትጣላ ሊያደርግህ ነው። ሰይጣንን ከገሠጽከው በእግዚአብሔር ቀኝ ከበጎቹ ጋር ትቆማለህ። አሁን ያለህበት ችግር ያልፋል። የሚሰማህ ክፉ ስሜት መቼም የማይለወጥ አይምሰልህ። ኀዘኑም ፣ ብቸኝነቱም ፣ ተስፋ ቢስነቱም ያልፋል። ጨለማው ይነጋል:: የተዘጋው በር ይከፈታል። ችግሩ ሲፈታ አንተ ከሌለህ ግን ትርጉም የለውም። ስለዚህ ለሚፈታ ችግር የማይቀለበስ ውሳኔ አትወስን:: ራስን ማጥፋት ከጊዜያዊ ችግር ለመሸሽ ሲሉ ዘላቂ ችግር ውስጥ መግባት ነው:: ጊዜያዊ ሕመምን ለማስታገስ የዘላለም ሕመምን ለምን ትመርጣለህ?
"የሞተ ተገላገለ" ሲሉ ሰምተህ እንዳትታለል ሞት ዕረፍት የሚሆነው ራሱ እግዚአብሔር ሲጠራህ ብቻ ነው። "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ" ያለው ጌታ ሳይጠራህ ራስን ማጥፋት የዘላለም ስቃይ ያመጣል።
ወዳጄ "በራስህ አንዳች ክፉ አታድርግ" የሕይወትህን ዋጋ ታውቅ ይሆን? አንተ እኮ የእግዚአብሔር ልጅ ለአንተ ሲል የሞተልህ ነህ። ሊፈውስህ የቆሰለ፣ ሊያከብርህ የተዋረደ፣ ሊያረካህ የተጠማ፣ ሊያለብስህ የተራቆተ ለአንተ እኮ ነው። ክርስቶስ ስለ አንተ ሞቶአል። አንተን ግን የጠየቀህ እንድትሞትለት ሳይሆን እንድትኖርለት ነው። ለሞተልህ አምላክ እንዴት መኖር ያቅትሃል?
ይቀጥላል ......
(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ - የኤፌሶን ወንዝ ገጽ 9-14)

❤118🙏25👍2👌2😍2
በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ
ወዳጄ ሆይ ሰውነትህ በአምላክ ደም የተገዛ ክቡር ሰውነት ነው። አካልህ "አንተ" እንጂ "ያንተ" አይደለም። "በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ" ይላል። ስለዚህ በከበረ የእግዚአብሔር ልጅ ደም የተገዛ ሰውነትህን ለሰይጣን በርካሽ አትሽጠው:: አትግደል የሚለው ሕግ ራስህንም ይጨምራል::
ቤተ መቅደስ የሆነ ሰውነትህን ለማፍረስ አታስብ። "ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ" ፩ኛ ቆሮ. ፫፥፲፯ ሰዎች አስቀይመውህ ይሆን? "አሳያቸዋለሁ፤ ስሞት የእኔን ነገር ይገባቸዋል" ብለህ በሰዎች ተቀይመህ ራስህን አትጉዳ። እመነኝ ብትሞት ሰዎች ከሳምንት በላይ አያስታውሱህም። ለሕይወትህ ዋጋ ያልሠጡ ሰዎች ለሞትህ ዋጋ አይሠጡም። ፈጥነውም ይረሱሃል። ለሚረሱህ ሰዎች ብለህ የማይረሳህን አምላክ አታሳዝን። ሰው ስለ አንተ ግድ የለውም እግዚአብሔር ግን የራስህን ጸጉር ሳይቀር በቁጥር ያውቀዋል። እንኳንስ ራስህን ልትጎዳ አንዲት ጸጉር እንኳን ከአንተ እንድትወድቅ አይፈልግም። እግዚአብሔርን በኃጢአት ብታሳዝነው እንኳን ኖረህ ንስሓ እንድትገባ እንጂ እንድትሞት አይፈልግም። አባትህ ነውና ከእርሱ ጋር ባትሆንም እንድትኖር ይፈልጋል።
በምሳሌ ልንገርህ፦ ሁለት ሴቶች አንድን ሕፃን "የኔ ልጄ ነው" ብለው እየተከራከሩ ጠቢቡ ሰሎሞን ፊት ቀረቡ። ጠቢቡ ሰሎሞን ሰይፍ አመጣና "ልጁን ቆርጬ ለሁለት ላካፍላችሁ" አላቸው። አንደኛዋ ሴት "እሺ እንካፈል" ስትል እውነተኛዋ እናት ግን "ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትውሰደው" አለች። እናት መሆንዋም በዚህ ታወቀ። (፩ኛ ቆሮ. ፫፥፩፮-፳፰)
ወዳጄ ያንተም ኑሮህ ከእግዚአብሔር ጋር ላይሆን ይችላል። ዓለም የራስዋ አድርጋህም ይሆናል። በሱስ ውስጥ ትዘፍቀህ፣ እንደ ሶምሶን በደሊላ እቅፍጀ፣ እንደ ዴማስ በተሰሎንቄ ውበት ተማርከህ ይሆናል። እግዚአብሔር ግን አባትህ ነውና ሞትህን አይፈልግም። "ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትውሰደው" እንዳለችው እናት ፈጣሪህ ከነኃጢአትህም ቢሆን እንድትሞት አይፈልግም። ከእርሱ ጋር ባትኖርም መኖርህን ይፈልጋል። "የሟቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ" ሕዝ. ፲፰፥፴፪
የይሁዳ ኃጢአቱ ጌታውን መሸጡ አልነበረም። ራሱን መግደሉ ነው። እግዚአብሔር የሚያዝነው ከበደልህ በላይ በእርሱ ተስፋ ቆርጠህ ራስህን ስትጎዳ ነው።
ወዳጄ የአንተን መኖር የሚፈልጉ ብዙ ናቸው። ፈጣሪ ወደዚህች ዓለም ያለ ምክንያት አላመጣህም። በአንተ አለመኖርም የሚጎድል ነገር አለ። አንተን የሚመስል ሌላ ሰው አልፈጠረምና ለዚህ ዓለም አንተን የሚተካ የለም፣ በክብር ወደዚህ ዓለም ያመጣህ አምላክ በክብር ወደራሱ እስኪወስድህ ድረስ "በራስህ ላይ ክፉ ነገር አታድርግ"
"የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ። ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ፦ ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ፡ ብሎ ጮኸ" ሐዋ. ፲፮፥፳፯-፳፰ ይህ ሰው እስረኛ ያመለጠ መስሎት ራሱን ሊያጠፋ ሲል ጳውሎስ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ" አለው።
ወዳጄ አንተስ ተስፋ የቆረጥኸው ምን ያመለጠ መስሎህ ነው? የትምህርት ዕድል ያመለጠህ መስሎህ ነው? ገና ሺህ የትምህርት ዕድሎች አሉህ። ዕድሜህ ያመለጠህ መስሎህ ነው? ነገ የሚጠብቁህ ብሩሕ ዘመናት እኮ ቁጭ ብለው አሉ? የሚረዳኝ ሰው የሚያስብልኝ ሰው አጥቼያለሁ? ብለህ ከሆነም ካልሰሙህ ጥቂቶች በላይ ልንሰማህ የምንሻ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ"
መከራ ጸናብኝ ኑሮ ጨለመብኝ የሀገሪቱ ሁኔታ ተስፋ አሳጣኝ ብለህ ይሆን? እኛስ አብረንህ አይደልንም? አብረን ከገባንበት ችግር አብረን ብንወጣ አይሻልም? ከአንተ በባሰ ሁኔታ የታሰርንና የተገረፍን ጳውሎሶችና ሲላሶች "ሁላችን በዚህ አለንና በራስህ ክፉ አታድርግ" ስንልህ ስማን። ይልቅ አንተም እንደ ወኅኒው ጠባቂ "እድን ዘንድ ምን ላድርግ ብለህ?" ነፍስህን የምታድንበትን መንገድ ወደ መቅደሱ ቀርበህ ጠይቅ።
ወዳጄ ይህንን ጽሑፍ ያነበብኸውም በሕይወት ስላለህ ነው። የአንተን ዓይን የሚጠብቁ ብዙ ጽሑፎች፣ የአንተን ጆሮ የሚፈልጉ ብዙ ድምፆች፣ የአንተን መሐረብ የሚፈልጉ ብዙ ዕንባዎች፣ የአንተን ሳቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀልዶች ... ገና ብዙ ብዙ አሉ። ስለዚህ ሰይጣንን አሳፍረው። እንዲህ በለው "ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልህ" ሚክ. ፯፥፰

❤134🙏33
ልጆቼ! በድህነቴ ላይ ቸርነትን አድርጉልኝ፡፡ በዚህስ አልችልም ካላችሁ እሺ በቁስሌ ላይ ዘይትን አፍስሱልኝ፡፡ አሁንም ይህን ማድረግ ካልቻላችሁ ወደ እኔ ጠጋ በሉና አናግሩኝ፡፡ እናንተን ማየት፣ ከእናንተ ጋር መጨዋወት ይናፍቀኛልና፡፡
በገዛ ደሜ የገዛኋችሁ ልጆቼ! ከባድ ነገር እኮ አልለመንኳችሁም፡፡ እኔ የምፈልገው ትንሽ ዳቦ፣ ጊዜአዊ ማደርያ፣ እንዲሁም የሚያጽናኑ ቃላትን ብቻ ነው፡፡ “ይህ ሁሉ ማድረጌ ምን ይጠቅመኛል?” ካላችሁ ስለ ምሰጣችሁን ርስት መንግሥተ ሰማያት ብላችሁ አድርጉት፡፡ አሁንም ልባችሁ አልተነካምን? ስለ መንግሥተ ሰማያት አታድርጉት፤ ግን ደግሞ ስለ ሰብአዊ ርኅራኄ ይህን አድርጉልኝ፡፡ የእኔን መራቆት የሚያሳዝናችሁ በቀራንዮ አደባባይ ስለ እናንተ ብዬ የተራቆትኩት ብቻ ነውን? ታድያ አሁንም ‘ኮ በደጃችሁ ላይ ተጥዬ ዕራቆቴን ነኝ፡፡ ለምን አላዘናችሁልኝም? የታሰርኩት በቀራንዮ ብቻ ነውን? አይደለም፡፡ ታድያ እንደምን አታዝኑልኝም?
የማፈቅራችሁ ልጆቼ! በመስቀል ላይ ተሰቅዬ ሳለሁ “ተጠማሁ” እንዳልኩ ዛሬስ ስለ እናንተ ብዬ ደጋግሜ ይህን ቃል አልተናገርኩምን? ጕሮሮዬ ደርቆ ስለምን ትንሽ እንኳ አላሳዝናችሁም? ስለምንስ ይህ ሁሉ ፍቅር ስለ እናንተ መሆኑን ትዘነጉብኛላችሁ? የምለምናችሁ እናንተን ባለጸጋ ለማድረግ አይደለምን? ይህችን ትንሽ ቸርነት ስላደረጋችሁልኝ በዐይን ያልታየች፣ በጀሮ ያልተሰማች፣ በሰውም አእምሮ ያልታሰበች ርስት መንግሥተ ሰማያት እንድታገኙ ብዬ አይደለምን? ስለ እናንተ ብዬ ደሀ የሆንኩት ያኔ በመዋዕለ ሥጋዌዬ ብቻ እንደሆነ አታስቡ ልጆቼ! ዛሬም ቢሆን በደጃችሁ የተጣልኩት ስለ እናንተ ጥቅም እንደሆነ ተረዱልኝ፡፡
ከባድ ነገር ‘ኮ አልለመንኳችሁም፡፡ እስር ቤት መጥታችሁ ጠይቁኝ እንጂ አስፈቱኝ አላልኳችሁም፡፡ ታምሜ ጠይቁኝ እንጂ ፈውሱኝ አላልኳችሁም፡፡ ከጠየቃችሁኝ ብቻ በቂዬ ነው፡፡ እስኪ ልጠይቃችሁና እናንተም መልሱልኝ! በዚያ በአስፈሪው ቀን ስመጣ “ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን” የሚለውን ቃለ ሕይወት መስማት አትፈልጉምን? ዛሬ የሰጣችሁኝ ሁሉ የምረሳ ይመስላችኋልን? ያኔ በክብር ስመጣ ከእልፍ ወለዱ ጋር እንድሰጣችሁ አትሹምን? የማፈቅራችሁ ልጆቼ! ከደጃችሁ ተጥዬ የምለምናችሁ፣ ከበራችሁ ላይ ቆሜ ማደርያን የምጠይቃችሁ፣ እጄን ዘርግቼ እናንተን እናንተን የማየው ያኔ ትሉ ወደማይጠፋው እሳቱ ወደማያንቀላፋው እሳት እንዳትሄዱብኝ ብዬ ነው፡፡ ታድያ ይህን ለምን አትረዱልኝ ልጆቼ? ስለምን እንዳስቸገርኳችሁ ታስባላችሁ? ለእናንተ ጥቅም እንደሆነ እንዳትረዱ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው? ከእናንተ ጋር ቁጭ ብዬ ልብላ ስላችሁ ስለምን ትገፈትሩኛለችሁ? ይህን ያህል ቸርነት አድርጌላችሁ ሳለሁስ ስለምን በግልምጫ አያችሁኝ? ይህን ያህል መውደድ ወድጃችሁ ሳለሁ ስለምን በቅጡ ልታነጋገግሩኝ አልወደዳችሁም? ከአዳም ጀምሮ ዓለም እስኪያልፍ ድረስ ያለው ሕዝብ ሁሉ በአንድ አደባባይ ላይ ቆሞ፣ እልፍ አእላፍ መላእክት በዙርያዬ ረበው “ይህ/ ይህቺ ልጅ ወዳጄ ነው/ ናት፤ በመሆኑም በታላቅ ክብርና ዕልልታ አጅባችሁ ወደ ዘለዓለም ደስታዋ አግቡት/ አግቧት” የሚለውን ፍርዴ አትናፍቁምን?
ልጆቼ! እኔን ላለማየት ስለምን ፊታችሁን ትሸፍናላችሁ? ስለምን፡ታፍራላችሁ? እኔ ሳላፍርባችሁ ስለምን እናንተ አፈራችሁ?
ልጆቼ! ልባችሁ እንደተነካ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ስሜት ብቻ አይሁን፡፡ ከንፈራችሁን ብቻ አትምጠጡብኝ፡፡ ከእናንተ የምፈልገው አንዲት ነገር ብቻ ነው፡፡ ከላይ የጠየቅኳችሁን ነገሮች ወደ ተግባር ቀይሯቸው፡፡ ለማይጠቅማችሁ ነገር አብዝታችሁ እየሮጣችሁ ለሚጠቅማችሁ ነገር አትስነፉ፡፡ “እኔኮ ሥጋ ለባሽ ነኝ፤ ይህን እንደምን እችላለሁ?” አትበሉኝ፡፡ አውቃለሁ! ነገር ግን ፈቃዳችሁን ብቻ ስጡኝ እንጂ እኔ ራሴ አደርግላችኋለሁ፡፡ “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ብዬ.ያስተማርኳችሁን ቃል ረሳችሁትን? /ዮሐ.15፡5/፡፡ እንግዲያውስ ከእናንተ የምፈልገው ፈቃዳችሁን ነው፡፡ አሁን ካላችሁበት ቦታ ተንቀሳቅሳችሁ ወጣ ስትሉ ታገኙኛላችሁ፡፡ አናግሩኝ! አፍቃሪያችሁ መድኃኔዓለም ነኝ፡፡
መቅረዝ ዘተዋሕዶ ብሎግ የተወሰደ

❤125🙏41💔14🕊2👍1
ተግሣፅ ዘቅዱስ ኤፍሬም
ሕይወትህን በአግባቡ መምራት ትፈልጋለህን? እንግዲያውስ ትሕትናን ተለማመድ፤ ያለ ትሕትና ተገቢውን ሕይወት መምራት አይቻልም፡፡ ሥራህን ሁሉ በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጀምር፡፡ ያን ጊዜ ፍሬዎችህ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይደርሳሉ።
ሰው ከትሕትና ከራቀ ከትክክለኛው መንገድ ርቋል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔርን የተወ ሰውን ርኵስ መንፈስ እንደ ሳውል ያስጨንቀዋል። የጠላት ወጥመድ በማር የተቀባ ነው፡፡ በማር ጣዕም የሚማረክ ሰው ሐዘንን ሁሉ በያዘ ወጥመድ ይያዛል። ትሕትናን ውደዱ፤ ያን ጊዜ ከሰይጣን ወጥመድ ውስጥ አትወድቁም፡፡ በትሕትና ክንፍ በበረራችሁ ቁጥር ሁል ጊዜ ከጠላት ወጥመድ በላይ ትሆናላችሁ።
ግልፍተኝነት እንደ በሰበሰ ረጅም ዛፍ ነው፤ ቅርጫፎቹ ሁሉ በቀላሉ የሚሰበሩ ናቸው᎓᎓ አንድ ሰው በወጣባቸው ጊዜ ከወጣበት ከፍታ ወዲያውኑ ይወድቃል፡፡ በመልካም ሐሳብ ልቡናው የበራ ሰው ግን ምስጉን ነው፤ ክብሩም ታላቅና ዘላለማዊ ነው።
እንግዲህ ራሳችንን ለመቆጣጠር እንጣር ያን ጊዜ ኃጢአታችንን እንረዳለን፡፡ ያን ጊዜም ሁል ጊዜ ራሳችንን ዝቅ እናደርጋለን፤ እንደ እባብ በእብሪት መወጠርን እና ራሳችንን ከፍ ከፍ ከማድረግ እንቆጠባለን፡፡ እንግዲህ ራሳችንን ዝቅ ዝቅ ማድረግን እንውደድ፤ በንጹሕ ልቡና ሆነን ምናልባት የተሰጠንን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኃጢአት ከማቆሸሽ እንታደግ ይሆናል።
መልካም ጸሎት በሳግ እና በዕንባ የታጀበ ነው፤ በተለይ ደግሞ በምሥጢር የሚፈስ ዕንባ፣ በልቡናው ከፍታ ሆኖ የሚጸልይ ጌታውን በፊቱ ያያል። እኛ የምንኖረውና የምንሔደው በእርሱ ፈቃድ ነውና። ልቡናችሁ ከጠነከረ በጌታችን ፊት አልቅሱ እርሱ የዕውቀትን ብርሃን ይገልጥላችኋል፤ ወደ እርሱ የሚወስዳችሁ አዲስ ልብንም ይሰጣችኋል።
ንስሓ የገቡና ምሕረት የለመኑ ሰዎች ዕዳቸው ተሰረዘላቸው፤ ነገር ግን ለሠራኸው በደል ምሕረት ስትለምን ወንጀልን እና በደልን፤ በወንድምህም ላይ ቂም መያዝን መተው ይገባሃል። ፍቅር ሳይኖርህ ወደ እግዚአብሔር የምታደርገው ልመና ከተዘጋው በር ውጭ ይቀራል፡፡ የጸሎትን በር የሚከፍት ፍቅር ብቻ ነው፡፡
ወንድምህን ብታስቀይም እግዚአብሐርን ታሳዝናለህ፤ ካንተ ጋር ካለው ከወንድምህ ጋር ሰላምን ከፈጠርህ ግን በሰማይ ካለው ከእግዚአብሔር ጋር ትታረቃለህ፡፡ ወንድምህን በፍቅር ብትቀበለው፣ በደሉንም ይቅር ካልከው እግዚአብሔርን ተቀበልክ፡፡
ስለዚህ በተናደዱ ሰዎች በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ታረቅ፤ እንግዲህ የተበሳጩትን በማስደሰት እግዚአብሔርን አስደስተው፣ በታሰሩት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን ጎብኘው፣ በተራቡት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አብላው፤ በታረዙ ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አልብሰው፣ መንገደኛን በመቀበል እግዚአብሔርን በአልጋህ ላይ አስተኛው፤ እግሮቹንም እጠበው፣ በማዕድህም አስቀምጠው፣ እንጀራህንም ከእርሱ ጋር ተካፈል፤ ጽዋህንም ስጠው᎓᎓ እርሱ ታላቅ ፍቅሩን አሳይቶሃልና፤ እርሱ ስለ አንተ ብሎ ትበላው ዘንድ ሥጋውን ቆርሶልሃል፣ ትጠጣው ዘንድም ደሙን አፍስሷል።
(ድርሳነ ቅዱስ ኤፍሬም ገጽ 334 - 336 በዲ/ን መዝገቡ ከፍያለው የተተረጎመ)

❤141🙏23👍3💯1
❤244🙏52💯9👌3
"ነፍስ አትግደል፤ ልበ ጎደሎ አትሁን፤ ተጠራጣሪና ሁለት ልብ የሆነ ሰው እግዚአብሔርን አያየውምና፡፡ ነፍስን የሚገድልም የዘለዓለም ሕይወትን አያያትም፡፡ ሐሰትን የሚናገር በገድሉ በጎ ዋጋ አያገኝባትም፡፡
ዳግመኛም እልሃለሁ ዝሙትን አትውደድ፤ ሐኬተኛና ልል ዘሊል አትሁን፤ ገንዘብንም አትውደድ፡፡ በሥጋው የሚያመነዝር በደለኛ ነው፤ መጨረሻው በማያንቀላፉ ትሎች መበላትና ጥፋት ነው፡፡ በሥራው ሁሉ ቸልተኛና ሐኬተኛ የሆነ ሰው የክርስቶስ ጸጋ ይለየዋል፡፡ ገንዘብን የሚወድ ሰው ጽድቅን ከቶ አያገኛትም፡፡
ዳግመኛም ስማኝ ልንገርህ፦ ጸሎትህን አታቋርጥ፤ ጾምህን አትሻር፤ ባልንጀራህን አትናቅ፤ ሰይጣን እንደ ጸሎት መቋረጥ አድርጎ የሚወደው ግብር የለውምና፡፡ ጾምን የሚሽር ሰው ልጓም የሌለው ፈረስን ይመስላል፡፡ ባልንጀራውን የሚንቅ እርሱንም እግዚአብሔር ይንቀዋል፡፡
ወዳጄ ሆይ ዳግመኛም ስማኝ ልንገርህ፦ ዕውረ ልብ አትሁን፤ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ፤ በፍጹም ሕሊናህ ፍራው፡፡ የምትሠራውን ሥራ ሁሉ ተማክረህ ሥራ፡፡ ምንም ምን ሥራ ቢሆን ያለ ምክር አትሥራ፡፡ በሌላ ሰው ኃጢአት አትሳተፍም፤ ራስህን ንጹሕ አድርግ፡፡ በልብ ድንቁርና ዓለም ሁሉ ይጠፋል፤ ፈሪሃ እግዚአብሔር ከሌለም ዓለም ይጎዳል፡፡ ያለ ምክር የሚሠራ ሥራ ሁሉ ስንፍና ነው፡፡"
(መጽሐፈ ወግሪስ - በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ - ገጽ 50)

❤138🙏30😍3
“ልጄ ሆይ ባለ መድኃኒትን ስማ ሕማምህን ቸል አትበል” መ.ሲራክ ፴፰፥፩
በሚል መሪ ቃል የጣና ቅዱስ ቂርቆስ ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት በአይነቱ ልዩ የሆነ አጠቃላይ ሆስፒታል ለመገንባት ተነስተናል። እርሶም ለዚህ ፕሮጀክት ከታች በተቀመጡት የባንክ አማራጮች አበርክቶ በማድረግ አሻራዎትን ያሳርፉ።
ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶች እና የእናቶች አንድነት ገዳም የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምሥክር ጉባኤ ቤት
TANA KIRKOS GEDAM 4TU G/METSAHFIT
1000680619488 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
TANA KIDUS KIRKOS YE-ABATOCH ENA YE-ENATOCH ANDNET GEDAM YE-ARATU GUBAYAT METSAHIFT MISKIR GUBAE BET
219553568 አቢሲኒያ ባንክ
2011111181981013 አባይ ባንክ
0068829811701 አሐዱ ባንክ
5020827358011 ዳሸን ባንክ
ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር
+251 982333444
+251 983333444
+251 984333444 ይደውሉ።

❤65🙏6💯2👍1
"ከበሮ ለምን ይጮኻል?"
የኔታ ለተማሪዎቻቸው አንድ ጥያቄ አቀረቡ "ልጆች ከበሮ ለምን ይጮኻል?" አሉ የኔታ "በቆዳ ስለተወጠረ ነው" አለ አንድ ተማሪ የዳዊት ማህደሩን በእጁ አንጠልጥሎ ለመመለስ እየቸኮለ። የኔታም "አይደለም አሉ" ሌላኛው ተማሪም "የኔታ ከእንጨት ስለ ተሠራ ነው" አለ የለበሰውን ለምድ ከፍ ከፍ እያደረገ የኔታም ትንሽ ዝም ካሉ በኋላ "አይደለም አሉ" ተማሪዎቹ ኹሉ ማውጣት ማውረድ ጀመሩ በሀሳብ ተወጠሩ።
ኹሉም የመጣለትን እና የገመተውን መናገር ቀጠለ ግን የሚመልስ ጠፋ። አንድ የኹሉንም ምላሽ በእርጋታ ይሰማ የነበረ ተማሪ እጁን አወጣ። "እሽ ልጄ" አሉ የኔታ ድምጹን ከፍ አደረገና "የኔታ እድሉን ስለ ሰጡኝ አመሰግናለሁ" ብሎ እጅ ከነሳ በኋላ "የኔታ ከበሮ የሚጮኸው ባዶ ስለሆነ ነው!" አለ። የኔታም የልጁን ምላሽ በማድነቅ ከወንበራቸው በመነሳት "ልጄ ተባረክ" አሉ። ተማሪዎቹም በጭብጨባ አጀቡት።
የኔታም ቀጠል አደረጉና ልጆች "ባዶ የኾነ ነገር ሁሉ ይጮኻል በውስጡ የኾነ ነገር ያለው እቃ ግን አይጮኽም። የተማረም ሰው እንዲሁ ነው። እውቀት ያለው አይጮኽም፣ ጥበብ ያለው አይጮኽም፣ ምንጊዜም ባዶ የሆነ ሰው ሲጮኽ፣ ጥበብ የሌለው ሲፎክር እውቀት የሌለው ሲያቅራራ ይታያል። እና ልጆቼ እናንተ 'ባዶ' እንዳትሆኑ እውቀትን ጨምሩ፣ በእውቀት ላይ ጥበብን፣ በጥበብ ላይ እግዚአብሔርን መፍራት ጨምሩ። ምድራችንን በማስተማርና በመስበክ የሞሉ ግን 'ባዶ' የሆኑ። ምድሪቱን በዝማሬ የሞሉ በሃይማኖትና በምግባር ግን 'ባዶ' የሆኑ። ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚሉ ግን ጌታ የማያውቃቸው እንደ ሰው ተፈጥረው እንደ እንሰሳ በደመ ነፍስ የሚኖሩ ሰዎች፣ በዝተዋልና" ብለው ቁጭ አሉ። ተማሪዎቹም የኔታን "ቃለ ሕይወትን ያሰማልን" ብለው ትምህርታቸውን ቀጠሉ።

❤200🙏24💔11🎉1
#ወርኃ_ጽጌ
(ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን እስከ ሕዳር 6 ቀን ያለው 40 ቀን የእመቤታችን ና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን (ዘመነ ጽጌን) ታከብራለች፡፡ ይህ 40 ቀን የእመቤታችንና የጌታ ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ ፡፡
በዚህ በወርኃ ጽጌ (በዘመነ ጽጌ) የሚጾሙ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾሙን መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም በመሆኑ (የፈቃድ) የትሩፋት ጾም ይባላል፡፡ በቀኖና ቤተክርስቲያን ከታዘዙት ከ7ቱ አጽዋማት ውጪ የሆነ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋ ያገኛል፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራልና፡፡ ‘’እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል፡፡ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል’’ (ሉቃ. 7፡47) እንዲል፡፡
የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ፡፡ ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸውም፡፡ የማይጾሙ ሰዎችንም መንቀፍና መክሰስ የለባቸውም፡፡ የጽጌ ጾም እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተደርጎ ስላልተወሰነ የማይጾሙ ሰዎች ሕገ ጾምን እንዳፈረሱ አድርጎ መውሰድ ስሕተት ነው፡፡ ይልቁንም የሚጾሙ ሰዎች ቢችሉ መጾማቸው እንዳይታወቅባቸው ቢያደርጉ የተሻለ ነው፡፡ "ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ" (ማቴ. 6፥16) የተባለው ለዚህ ዓይነቱ ጾም ነው፡፡
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ!

❤198🙏23🕊1
ስለ ሌሎች መዳን ከማይጨነቅ ክርስቲያን በላይ ሰነፍ ሰው የለም፡፡ ወዳጄ “እኔ ድኻ ነኝና ይህን ማድረግ አልችልም” የምትል አትኹን፤ ባለ ኹለት ዲናሯ ሴት ትወቅስሃለችና፡፡ ዳግመኛም “ወርቅም ብርም የለኝም” ብሎ የተናገረ ጴጥሮስ ይወቅሰሃልና፡፡
"ምናምንቴ ነኝ" አትበል፤ እንዲህ ስትል ምናምንቴዎቹ ሐዋርያት እንዳይሰሙህ! "እኔ በሽተኛ ነኝ" አትበል፤ በሽተኛው ጢሞቴዎስ ይታዘብሃልና፡፡ ፈጽመህ “እኔ ሌሎች ሰዎችን ወደ ክርስቶስ ማምጣት አይሆንልኝም” አትበል፡፡ በእውነት ክርስቲያን ከኾንክ ይህን ከማድረግ ይልቅ አለማድረጉ ይከብዳልና፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ እንድትኾን አድርጎ ፈጥሮሃልና ተፈጥሮህን መካድ አይቻልህም፡፡ ክርስቲያን በጨለማ ውስጥ ለሚኖሩ ወንድሞቹ ብርሃኑን ከሚከለክል ይልቅ ፀሐይ ብርሃኗን ብትከለክል ይቀላልና ስለዚህ አልጠቅምም አትበል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

❤169🙏24😍2
Forwarded from ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
“ልጄ ሆይ ባለ መድኃኒትን ስማ ሕማምህን ቸል አትበል” መ.ሲራክ ፴፰፥፩
በሚል መሪ ቃል የጣና ቅዱስ ቂርቆስ ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት በአይነቱ ልዩ የሆነ አጠቃላይ ሆስፒታል ለመገንባት ተነስተናል። እርሶም ለዚህ ፕሮጀክት ከታች በተቀመጡት የባንክ አማራጮች አበርክቶ በማድረግ አሻራዎትን ያሳርፉ።
ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶች እና የእናቶች አንድነት ገዳም የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምሥክር ጉባኤ ቤት
TANA KIRKOS GEDAM 4TU G/METSAHFIT
1000680619488 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
TANA KIDUS KIRKOS YE-ABATOCH ENA YE-ENATOCH ANDNET GEDAM YE-ARATU GUBAYAT METSAHIFT MISKIR GUBAE BET
219553568 አቢሲኒያ ባንክ
2011111181981013 አባይ ባንክ
0068829811701 አሐዱ ባንክ
5020827358011 ዳሸን ባንክ
ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር
+251 982333444
+251 983333444
+251 984333444 ይደውሉ።
በሚል መሪ ቃል የጣና ቅዱስ ቂርቆስ ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት በአይነቱ ልዩ የሆነ አጠቃላይ ሆስፒታል ለመገንባት ተነስተናል። እርሶም ለዚህ ፕሮጀክት ከታች በተቀመጡት የባንክ አማራጮች አበርክቶ በማድረግ አሻራዎትን ያሳርፉ።
ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶች እና የእናቶች አንድነት ገዳም የአራቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምሥክር ጉባኤ ቤት
TANA KIRKOS GEDAM 4TU G/METSAHFIT
1000680619488 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
TANA KIDUS KIRKOS YE-ABATOCH ENA YE-ENATOCH ANDNET GEDAM YE-ARATU GUBAYAT METSAHIFT MISKIR GUBAE BET
219553568 አቢሲኒያ ባንክ
2011111181981013 አባይ ባንክ
0068829811701 አሐዱ ባንክ
5020827358011 ዳሸን ባንክ
ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር
+251 982333444
+251 983333444
+251 984333444 ይደውሉ።
❤56🙏14👍4💔2🏆1
ቅናት ሰውን ወደ ዲያብሎስ ትለውጠዋለች፤ ስውን ክፉ ጋኔን ታደርገዋለች፡፡ የመጀመሪያው ነፍሰ ገዳይ [ቃኤል] የተነሣው ከቅናት ነው፡፡ ተፈጥሮውን (ሰው መኾኑን) የዘነጋው፣ ምድርንም ያረከሳት ከቅናት የተነሣ ነው፡፡ ከዚያም በኋላ ገና በሕይወተ ሥጋ እያሉ ዳታንን፣ ቆሬንና አቤሮንም፤ ሕዝቡንም ኹሉ ምድር አፏን ከፍታ የዋጠቻቸው ከቅናት የተነሣ ነው፡፡
“ቅናትን ተቃውሞ መናገር ቀላል ነው" የሚል ሰው ሊኖርይችላል፡፡ እኛ ግን ሰዎች ከዚህ ደዌ እንዴት መዳን እንደሚችሉም መናገር ይገባናል፡፡ እናስ ከዚህ ክፋት መላቀቅ የምንችለው እንዴት ነው? ዝሙት የፈጸመ ሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን መግባት እንደማይችል ኹሉ በቅናት የተያዘ ሰውም እንደዚሁ ወደ ቤተ ክርስቲያን መግባት እንደማይችል ብናስብ ይህን ደዌ ከእኛ ማራቅ እንችላለን፡፡ ቅናት ከዝሙት የሚተናነስ አይደለምና፡፡ ቅናት እንደ ቅቡል ተደርጎ ነው የሚቈጠረው፤ ከዚህ የተነሣም ሰው እንደ ቀላል ነገር አድርጎ ነው የሚያስበው፡፡ ነገር ግን እውነተኛ ክፋቱ ምን እንደ ኾነ ቢገለፅ በቀላሉ ከእርሱ መራቅ በተቻለን ነበር፡፡
ስለዚህ ስለ መቅናትህ አልቅስ፤ ቃትት፤ አንባ፤ ከዚህ ደዌ ይፈውስህ ዘንድም እግዚአብሔርን ማልደው፡፡ የቅናት ኃጢአት እጅግ የከፋ እንደ ኾነ ከልብህ አስበውና ንስሓ ግባ፡፡ በዚህ አግባብ የምትሔድ ከኾነ ከዚህ ደዌም ፈጥነህ ትፈወሳለህ፡፡
“ቅናት (ምቀኝነት) ክፉ በደል እንደ ኾነ የማያውቅ ማን አለና?” የሚል ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ ክፉ በደል እንደ ኾነ'ማ የማያውቅ ሰው የለም፡፡ ዳሩ ግን እንደ ዝሙትና እንደ ግልሙትና አድርገው አይቈጥሩትም፡፡ ቢያንስ አንድ ሰው በሌላ ሰው ላይ ከቀና፥ ልክ ዝሙት እንደ ሠራ ሰው ኾኖ አምርሮ ራሱን ይወቅሳልን? ከዚህ ክፉ ደዌ እግዚአብሔር ምሕረት ያደርግለት ዘንድ የተማጸነው መቼ ነው? ማንም እንደዚህ አያደርግም፡፡ ይልቅስ ቢጾምና ጥቂት ገንዘብ ለጦም አዳሪዎች ቢሰጥ፥ ሺሕ ጊዜ ቀናተኛ ቢኾንም፥ ከበደል ኹሉ የሚከፋ አንዳች ኃጢአት እንደ ሠራ አያስብም፡፡ እንዴ! እስኪ ንገረኝ! ቃኤል እንደዚያ የኾነው በምን ምክንያት ነው? ዔሣውስ? የላባ ልጆችስ? የያዕቆብ ልጆችስ? ቆሬ፣ ዳታንና አቤሮን ከወገኖቻቸው ጋርስ እንዲያ የኾኑት በምን ምክንያት ነው? ማርያም እኅተ ሙሴስ? አሮንስ? ዲያብሎስ ራሱስ ቢኾን?
ከዚሁ ጋር ይህንንም አስተውል! ቅናት ሲይዝህ የገዛ ራስህን በሰይፍ ትወጋለህ እንጂ የምትቀናበትን ሰው አትጎዳውም፡፡ እስኪ ንገረኝ! ቃኤል በወንድሙ ላይ በመቅናቱ ምክንያት አቤልን ጎድቶታልን? እ? እርሱ ሳይፈልግ ፈጥኖ ወደ ገነት እንዲሔድ አይደል እንዴ ያደረገው? እርሱ ግን ስፍር ቍጥር በሌላቸው ክፉ ክፉ ነገሮች ነው የገዛ ራሱን የወጋው፡፡ ዔሣው ያዕቆብን የጎዳውስ የት ላይ ነው? ያዕቆብ ባለጸጋ አልኾነምን? ቍጥር የሌላቸውን በረከቶች አልተቀበለምን? ዔሣው ግን በወንድሙ ላይ ከቀና በኋላ ከአባቱ ቤት ውጹእ፣ በባዕድ አገርም ተቅበዥባዥ ኾነ፡፡ የቀኑበትና ቅናታቸውንም [በኋላ ገንዘቡን ቢመርጡም ቅሉ] ደሙን እስከ ማፍሰስ ድረስ እንዲማማሉ ቢያደርጋቸውም የያዕቆብ ልጆችስ ዮሴፍን የጎዱት የት ነው? እነርሱ ራሳቸው በረሃብ በትር የተገረፉ አይደለምን? እርሱ የግብጽ ንጉሥ ሲኾን እነርሱ ግን እጅግ ጽኑ መከራ የገጠማቸው አይደሉምን? ለምን መሰለህ፥ ይበልጥ በቀናህ ቍጥር፥ በቀናህበት ሰው ላይ እንዲያውም ይበልጥ በረከትን ታመጣለታለህ እንጂ አትጎዳውም፡፡ እነዚህን ኹሉ የሚመለከት እግዚአብሔር አለና፤ በደል ያልፈጸመው ሰው እንደተበደለ ሲያይ እርሱን የበለጠ ያከብረዋል፥ ከፍ ከፍ ያደርገዋል፤ አንተን ግን ይቀጣሃል፡፡
ይቀጥላል......
(የማቴዎስ ወንጌል ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደተረጎመመው ድርሳን 40 ገጽ 330-333
ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው)

❤147🙏15😍8👌3🏆2
የቀጠለ..
“ጠላትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ፥ በመሰናከሉም ልብህ ሐሤት አያድርግ፡፡ እግዚአብሔር ያያልና፤ ደስም አያሰኘውምና፤ ቊጣውንም ከእርሱ ይመልሳልና'' እንዲል በጠላቶቻቸው ውድቀት ደስ ስለሚሰኙ ሰዎች እግዚአብሔር ቍጣውን የሚመልስ ከኾነ˖ ምንም በደል ባልሠሩ ሰዎች ላይ ይበልጥ ቍጣውን ይመልሳልና (ምሳሌ 24፥17-18)::
እንኪያስ ይህ ራሰ ብዙ የኾነውን አውሬ ፈጽመን ከእኛ እናቅ፡፡ የቅናት ራሶች (ዓይነቶች) በርግጥም ብዙ ናቸውና፡፡ የሚወደውን የሚወድ ሰው ከአንድ ቀራጭ የተሻለ ሥራ ካልሠራ፥ ምንም ያልበደለውን ሰው የሚጠላ ሰውስ ምን ተብሎ ሊጠራ ይችላል? ከአሕዛብ የባሰ ኾኖ ሳለስ እንዴት ከምረረ ገሃነም ማምለጥ ይቻለዋል? ስለዚህም ጭምር፥ ማለት መላእክትን ወይም ይልቅ የመላእክትን ጌታ እንድንመስል ታዘን እያለ ዲያብሎስን በመምሰላችን እጅግ አዝናለሁ። በእውነት በቤተ ክርስቲያን ሳይቀርብዙ ቅናት አለ፡፡ በዲያብሎስ ባርነት ሥር ካሉት ይልቅ ይበልጥ በእኛ ዘንድ ቅናት አለ፡፡ ስለዚህ እኛው ራሳችን ለራሳችን ሳይቀርማስተማር አለብን፡፡
እስኪ ንገረኝ! በባልንጀራህ ላይ የምትቀናው ለምንድን ነው? ሥልጣንንና በጎ ስምን ሲቀበል ስላየኸው ነውን? ክብርና ዝና ራሳቸውን ባልጠበቁ ሰዎች ላይ ምን ጉዳት እንደሚያመጣ አታስተውልምን? ወደ ትዕቢት፤ ወደ ውዳሴ ከንቱ፤ ወደ ዕብሪት፣ ወደ እንዝህላልነት፣ ይበልጥ ወደ ግድየለሽነት እንደሚወስዳቸው አታውቅምን? ይህ የምትቀናበት ሰው በእነዚህ ክፋቶች ከመያዙም በላይ ሥልጣኑና ዝናው ገና ከመታየታቸው የሚጠወልጉ ናቸው፡፡ እጅግ የሚከፋው ይህ ነውና፡- ከዚህ የሚመነጩ ክፋቶች የማያልፉ ሲኾኑ ከዚህ የሚገኘው ደስታ ግን እንደ ተባለው ገና ከመታየቱ የሚጠፋ ነው፡፡ ታዲያ ንገረኝ እስኪ፥ በዚህ ሰው ነው የምትቀናው?
“ባለ ሥልጣን ሲኾን'ኮ ብዙ ተዕዕኖ ያደርጋል፡፡ ኹሉንም ነገር እርሱ እንደ ወደደው ማድረግ ይችላል፡፡ የተቃወሙትን ይቀጣል፤ ያወደሱትን ደግሞ ይሾማል ይሸልማል፡፡ ማድረግ የሚፈልገውን የማድረግ ኃይልም አለው" ልትል ትችላለህ፡፡ እነዚህ ንግግሮች የዚህ ዓለምና ከምድር ጋር የተጣበቁ ሰዎች ንግግሮች ናቸው፡፡ መንፈሳዊውን ሰው ምንም ማንም ሊጎዳው አይችልምና፡፡
በምን መንገድ አብዝቶ ሊጎዳው ይችላል? ከሥልጣኑ ሊሽረው ይችላልን? ታዲያ ይኼ ምንድን ነው? ይህ በርትዕ ከተደረገ ጠቀመው እንጂ አልጎዳውምና፡፡ ሥልጣነ ክህነትን ሳይገባው የተቀበለን ሰው ያህል እግዚአብሔርን የሚያሳዝነው የለምና፡፡ ያለ ርትዕ ካደረገበት ግን ተጎጂው ካህኑ ሳይኾን ሌላው ነው። ያለ ርትዕ መከራን የሚቀበልና ይህንን በአኰቴት የሚታገሥ ሰው በእግዚአብሔር ፊት የበለጠ ባለሟልነትን (ሞገስን) ያገኛልና፡፡
ስለዚህ እንዴት ምግባርን ተላብሰን ራሳችንንም ክደን መኖር እንደ አለብን እንጂ እንዴት ሥልጣን፣ ክብርና ጌትነት ማግኘት እንዳለብን ዓላማ አድርገን አንያዝ፡፡ እግዚአብሔር የማይወዳቸውን ብዙ ነገሮች እንዲያደርጉ የሥልጣን ቦታዎች ሰዎችን ያባብላሉና፡፡ ሥልጣንን እንደሚገባ ለመጠቀምም ጽኑዕ የነፍስ (መንፈሳዊ) ብርታት ያስፈልጋልና፡፡ ሥልጣን የሌለው ሰው በፈቃዱም ይኹን ያለ ፈቃዱ ራሱን እንደሚገዛ ኹሉ፥ ጽንዓ ነፍስ ኖሮት ሥልጣን የሚይዝ ሰውም እንደዚሁ ፈቅዶም ይኹን ሳይፈቅድ ራሱን ይገዛል፡፡

❤74👍9🙏7