በእንተ ስማ ለማርያም
መስከረም 11 ለተራሚዎች መጽሐፍ ቅዱስ በስጦታ እናበርክት
“ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” ማቴዎስ 25፥36
እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 15 የቻናላችን ቤተሰቦች 26,300 ብር አግኝተናል።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን የ29 ተሸፍኖልናል ማለት ነው፤ ቀሪ 51 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።
ቀሪውን ተጋግዛዘን እንሙላው።
በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ

❤24🙏5👍2
“እምነት አለኝ” ብሎ ምግባር የሌለው ሰውና፥ “ምግባር አለኝ” ብሎ እምነት የሌለው ሰው እኩል ናቸው፤ ኹለቱም መንግሥተ ሰማያት አይገቡም፡፡
ስለዚህ “እምነት አለን” ብለን ልል ዘሊላን አንኹን ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ይላልና፡- “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም” (ማቴ.7፡21)፡፡
ስለዚህ እምነት እንደሌላቸው ሰዎች ከመንግሥተ ሰማያት ውፁአን እንዳንኾን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ነቅተን እንሥራ፡፡ ምግባር ትሩፋትን ተግተን እንሥራ፡፡ አምነን ልጅነትን ከተቀበልን በኋላ ልጅነታችንን አጽንተን የምንጠብቀው፣ ርስቱንና መንግሥቱንም የምንወርሰው ይህን ያደረግን እንደ ኾነ ነውና ነቅተን እንሥራ፡፡
እኛ ሥራ ሠርተን አንበቃምና ጽዋ ተርታችን ዕድል ፈንታችን ይህ ይኾን ዘንድ ከባሕርይ አባቱ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነቱ፣ ኃይሉና ክብሩ አንድ የሚኾን ጌታችንና መድኃኒታችን በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ ይርዳን፤ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ አሜን!!!
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

❤104🙏19
ኑሮየን ንገረኝ
ታላቁ ቅዱስ አርሳንዮስ ቤተ መንግሥትን ለቆ ወደ በረሃ ለምናኔ ሲገባ ጌታን የለመነበት ትልቅ ጸሎት ነበር። "ጌታ ሆይ" አለው። ጌታም "አርሳኒ ምን ትሻለህ" አለው። ቅዱስ አርሳንዮስም "ጌታ ሆይ ኑሮየን ንገረኝ" ሲል ጠየቀ። ዳግመኛም "ጌታ ሆይ" ሲል ጮኸ። ጌታም "አርሳኒ ምን ትሻለህ" አለው። እርሱም "ጌታይ ሆይ ኑሮዬን ንገረኝ" አለው። ሦስተኛም አለ "ጌታ ሆይ" አለ። ጌታም "አርሳኒ ምን ትሻለህ?" አርሳኒም "ጌታ ሆይ ኑሮየን ንገረኝ" አለ ከሰማይም እንዲህ የሚል ቃል መጣ፦ጌታም መለሰ። ቦታ ምረጥ፣ ከሰው ተለይ፣ ዝም በል አለው። አርሳኒም ገዳም ገብቶ ለፍጹምነት በቃ።
ሰው መንገድ ሲሄድ በሁለት መንገድ ሊወድቅ ይችላል። አንደኛ በጠማማ መንገድ በመሄድ። ሁለተኛ በቅን መንገድ ሳያስተውሉ በመሄድ ነው። በጠማማ መንገድ በመሄድ መውደቅ ማለት በጠማማ ሃይማኖት መኖር ነው። በቅን መንገድ ሳያስተውሉ መጓዝ ማለት ደግሞ በቀናች ሃይማኖት እየኖሩ አካሄድን አለማወቅ ነው። መንገዱ የቀና ቢሆንም አረማመዱ ባለማየት ከሆነ እግሮቹ ተጣልፈውም ቢሆን ይወድቃል። አካሄዱ ካላማረ በክርስቶስ ማመንም ያስኮንናል። የምናውቀው ክርስትና በማናውቀው መንገድ ከኖርነው ያጠፋል።
አውቀን ለምናደርጋቸው እንኳ ቢሆን እንዴት ላድርገው እያልን መጠየቅ በየዕለቱ እናደርገው ዘንድ ይገባል። በየጊዜውና በየሰዓቱ ወደ ክርስቶስ የምንጓዝ ነንና ጥያቄያችን የዘወትር ነው። ጸሎት አይቋረጥም መባሉ ስለዚህ ነው። ቅዱስ አርሳንዮስ ኑሮው ምንኩስና እንዲሆን ወስኖ ነበር። ግን መነኩሴ መሆን እንዳለበት እያወቀ ኑሮየን ንገረኝ ይል ነበር። ለምን ቢሉ ኑሮውን ብናውቀውም አኗኗሩን ግን ካልጠየቅን የሚጠቅመውን በማይጠቅም መንገድ ልንኖረው እንችላለን።
ለምሳሌ ከቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ ጳውሎስን እንይ። ቅዲስ ጳውሎስ ምሑረ ኦሪት ነበር። 46ቱን የኦሪት መጻሕፍት ተምሯል። መጻሕፍቱ ግን የሚተረጎሙት በክርስቶስ መገለጥ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ግን ጌታን ያሳድድ ነበር። የሚያሳደደውም ለሕግ የተቆረቆርሁ መስሎት ነበር። ጌታም ቅንነቱን አይቷልና ጌታን እያገለገለ መስሎት ጌታን ያሳድድ የነበረውን አልተወውም። መንገዱን ያቀናለት ዘንድ መንገገድ ላይ በመብረቅ ተገለጠለት። ሊያሳድድበት የሄደውን መንገድ ወደ ክርስቶስ እንዲደርስበት መራው። እውቀትን ቅንነት ይመራዋል፤ ቅንነትን እውቀት ያበራዋል። ስለዚህ ስለምናደርገው ነገር በቂ እውቀት ቢኖረንም ያንን ግን እንደ መርከብ የሚመራው ረድኤተ እግዚአብሔር ነውና አዘውትረን ኑሮየን ንገረኝ እንበል!
(ርዕሰ ሊቃውን አባ ገብረ ኪዳን ግርማ )

❤184🙏36😍6💯4🏆1
በእንተ ስማ ለማርያም
መስከረም 11 ለተራሚዎች መጽሐፍ ቅዱስ በስጦታ እናበርክት
“ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” ማቴዎስ 25፥36
እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 15 የቻናላችን ቤተሰቦች 26,300 ብር አግኝተናል።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን የ29 ተሸፍኖልናል ማለት ነው፤ ቀሪ 51 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።
ቀሪውን ተጋግዛዘን እንሙላው።
በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
መስከረም 11 ለተራሚዎች መጽሐፍ ቅዱስ በስጦታ እናበርክት
“ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” ማቴዎስ 25፥36
እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 15 የቻናላችን ቤተሰቦች 26,300 ብር አግኝተናል።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን የ29 ተሸፍኖልናል ማለት ነው፤ ቀሪ 51 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።
ቀሪውን ተጋግዛዘን እንሙላው።
በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
❤24🙏20🕊1
በእንተ ስማ ለማርያም
መስከረም 11 ለተራሚዎች መጽሐፍ ቅዱስ በስጦታ እናበርክት
“ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” ማቴዎስ 25፥36
እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 16 የቻናላችን ቤተሰቦች 35,300 ብር አግኝተናል።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን የ39 ተሸፍኖልናል ማለት ነው፤ ቀሪ 41 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።

❤23🙏4💯2
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
በእንተ ስማ ለማርያም መስከረም 11 ለተራሚዎች መጽሐፍ ቅዱስ በስጦታ እናበርክት “ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” ማቴዎስ 25፥36 እስከዚህ ሰዓት መስከረም 11/2018 ዓም በህግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱም ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ 16 የቻናላችን ቤተሰቦች 35,300 ብር አግኝተናል። እግዚአብሔር…
የቀሩትን 41 መጻሕፍት እናሟላ እና እሁድ መስከረም 11/2018 ወልድያ በሰሜን ወሎ ማረሚያ ቤት ለታራሚዎች እናስረክብ!
በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
❤16
፩
ተግሣጽ በእንተ ቅንዓት
ቅንዓት ፍትሕ እንዲዛባ ያደርጋል፡፡ ቅንዓት አንድ ሰውን ማየት ከሚፈልገው ውጪ እንዲያይ አይፈቅድለትም፡፡ በዚህ አንዴ የተጠመደ ሰው የነፍሱን ዓይኖች ለዘለዓለም ያሳውራቸዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ስው እንዴት ትሕትና ማስተማር ይቻለዋል? ቀኝ ጉንጭህን ለሚመታህ ሌላውን አዙርለት ብሎ ትእዛዝን ሊሰጥ ይችላልን? መከራም ሲገጥመን እንድንታገሥ ይመክረናልን? መከራን ከመታገሥ ይልቅ እንድንበቀል የሚያስተምር አይደለምን? እስቲ ንገሩኝ እነዚህ ወገኖች በደልን የሚያበረታቱ እንጂ ግፍን የሚያርቁ ናቸውን?
ነገር ግን አስቀድሜ እንደተናገርሁት ከሁሉ የከፋው ተንኮል ነው፡፡ ተንኮል ሰውን ግብዝ ያደርገዋል፤ ዓለምንም ቊጥር በሌለው ኀጢአት እንድትሞላ ያደርጋታል፡፡ ይህ ኀጢአት ፍርድ ቤቶችን የሞላ ሲሆን ከዚህም ኀጢአት ከንቱ ውዳሴ፣ ገንዘብንና ሥልጣንን መውደድ እንዲሁም ድፍረት ይወጣሉ፡፡
በዚህ ኀጢአት የተያዙ ሰዎች ርኅራኄ የሌላቸው ዘራፊዎችና የባሕር ላይ ወንበዴዎች ይሆናሉ፡፡ ከዚህ ኀጢአት ነፍሰ ገዳዮች ተወልደው ወደ ዓለም ሁሉ ይበተናሉ፡፡ ሰዎችን በዘር ምክንያት ይከፋፍሏቸዋል፤ ስለዚህ ተንኮል የኀጢአቶች ሁሉ ምንጭ መሆኑን በእነዚህ እንረዳለን፡፡
ይህ ኀጢአት ወደ ቤተ ክርስቲያንም ስርጎ ገብቶአል፡፡ በዚህም ምክንያት ከመጀመሪያው ጀምሮ ብዙ ሺህ ክፉ ጥፋቶች መጥተውብናል፡፡ ቅንዓትም የስስት እናቱ ነው፤ ይህ ደዌ አኗኗራችንን የሚያመሰቃቅልና ፍትሕን የሚያዛባ ነው፡፡ ይህ ቅንዓት፡- “እጅ መንሻ መማለጃ ዐዋቆች ስዎችን ዓይነ ልቡናቸውን ይሰውራቸዋል፤ አፋቸውን ይዘጋዋል ቃላቸውንም ያስለውጣቸዋል፡፡” (ሲራክ ፳፥፳፱) እንዲል ነጻ የሆኑትን ሰዎች ባሮች የሚያደርጋቸው ነው:: ስለዚህ ይህን በተመለከተ ሳንታክት እናስተምራችኋለን፡፡
ከዚህ ኀጢአት ምንም በጎ ነገር አይወጣም፤ በዚህ ክፋት ውስጥ ካለን ከዱር አራዊት ይልቅ የከፋን እንሆናለን፡፡ ወላጅ አልባዎችን እንበዘብዛለን፣ መበለቶችን እንገፋለን፣ በደሃው ላይ እንጨክናለን፡፡ ይህ ኀጢአት በወዮታ ላይ ወዮታን የሚደራርብ ነው፡፡ ነቢዩም፡- “ደግ ሰው ከምድር ጠፍቶአል፥ በሰውም መካከል ቅን የለም፤ ሁሉ ደምን ለማፍሰስ ያደባሉ፥ ሰውም ሁሉ ወንድሙን በመረብ ለመያዝ ይከታተለዋል።" (ሚክ.፯፥፪) እንዲል ከዚህ በኋላ በዚህ ጉዳይ ከመናገር ይልቅ የማዘኑ ተራው የእኛ ነው፡፡
ይቀጥላል...
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ዮሐንስ ወንጌልን በተረጎመበት ድርሳኑ ቅጽ 2 ገጽ 156-159 በዲያቆን ሽመልስ መርጊያ የተተረጎመ)

❤64🙏18
#መጽሐፍ_ቅዱስ_ለታራሚዎች
“ታምሜ ጠይቃችኹኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” (ማቴዎስ 25፥36)
መስከረም 11/2018 ዓ/ም በሕግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሒደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎትና በእለቱ ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ የቻሉትን ታግዙን ዘንድ እንጠይቃለን።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲኾን የ40 ተሸፍኖልናል፤ ቀሪ 40 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።
ማነው 40 መጽሐፍ ቅዱስ የሚያግዘን!
በእመቤቴ ዛሬንና ነገን እጨርስ ፈቃደኛ የሆናችሁ በውስጥ መስመር አናግሩን!
በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
“ታምሜ ጠይቃችኹኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” (ማቴዎስ 25፥36)
መስከረም 11/2018 ዓ/ም በሕግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሒደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎትና በእለቱ ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ የቻሉትን ታግዙን ዘንድ እንጠይቃለን።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲኾን የ40 ተሸፍኖልናል፤ ቀሪ 40 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።
ማነው 40 መጽሐፍ ቅዱስ የሚያግዘን!
በእመቤቴ ዛሬንና ነገን እጨርስ ፈቃደኛ የሆናችሁ በውስጥ መስመር አናግሩን!
በዚህ @natansolo በመግባት አናግሩን!
ወይም +251910001445 ይደውሉ
❤34🙏5
፪
ተግሣጽ በእንተ ቅንዓት
...በጸሎታችን ወይም በምክራችን ወይም በተግሣጻችን ምንም አላተረፍንምና፤ ለእኛ የቀረልን ልቅሶ ብቻ ሆኖአል፡፡ ክርስቶስም ያደረገው እንዲህ ነበር፤ እርሱ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ብዙ ጊዜ የገሠጻቸው ቢሆንም፤ ምንም ትርፍ ስላላገኘባቸው ስለ ድንዳኔያቸው አልቅሶላቸዋል። ነቢያትም ለእስራኤላውያን አንብተውላቸዋል፡፡ እኛም እንዲሁ ስለ እናንተ እያነባን እንገኛለን፡፡ አሁን እኛ የምናዝንበትና የምናለቅስበት እንዲሁም ወዮ የምንልበት ወቅት ላይ ደርሰናል። “እንዲመጡ አልቃሾች ሴቶችን ጥሩ፤ እንዲመጡም ወደ ብልሃተኞች ሴቶች ላኩ" የምንልበት ወቅት አሁን ነው። (ኤር ፱፥፲፯)
በእርግጥ የሚያማምሩ ቤቶችን ለመገንባት የሚሹትን ሰዎች ስንመለከት የቅንዓት ደዌ ምን ያህል ጽኑ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ እነዚህ ሰዎች ከሰዎች በነጠቋቸው መሬቶች የተከበቡ ናቸው፡፡ አዎን ለማዘን አሁን ወቅቱ ነው፤ እናንተ መሬታችሁ የተነጠቀባችሁ በእነርሱም የተጎዳችሁ ኑ ከእኔ ጋር በአንድነት እዘኑ። ኀዘናችሁንም ተካፍዬ እንባዬን አፈስ ዘንድ ፍቀዱልኝ፡፡ ኀዘናችን ግን ለእኛ ሳይሆን ለእነርሱ ነው፡፡ እኛ ብንጎዳ በምድር ነው፣ የእነርሱ ጥፋት ግን ዘለዓለማዊ ነው፡፡ እናንተ ግን በእናንተ ላይ የተፈጸመባችሁ ግፍ ዋጋ ሆኖአችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ትወርሳላችሁ፡፡ ነጣቂዎቻችሁ ግን ገሃነምን ይወርሳሉ፡፡ ከመጉዳት መጎዳት አይሻልምን? ስለዚህ ስለ እነርሱ ማቅ ለብሰን እናልቅስላቸው! በሰዎች ዘንድ ባለው የልቅሶ ሥርዓት ግን አይደለም፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈው ነቢያት ያዘኑትን ኀዘን ዓይነት እንዘንላቸው። ከነቢዩ ኢሳይያስ ጋርም “ስፍራ እስከማይቀር ድረስ እናንተም በምድር ላይ ብቻችሁን እስክትቀመጡ ድረስ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚያያይዙ እርሻንም ከእርሻ ጋር ለሚያቀራርቡ ወዮላቸው! የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጆሮዬ እንዲህ አለ፦ በእውነት ብዙ ታላቅና መልካም ቤት ባድማ ይሆናል የሚቀመጥበትም አይገኝም" በማለት አምርረን እናልቅስላቸው፡፡ (ኢሳ ፭፡፰-፱)
ኤርሚያስም “ቤቱን በግፍ ሰገነቱንም በዓመፅ ለሚሠራ፥ ባልንጀራውንም እንዲያው በከንቱ ለሚያሠራ፥ ዋጋውንም ለማይሰጠው፤ ለራሴ ሰፊ ቤት ትልቅም ሰገነት እሠራለሁ ለሚል፥ መስኮትንም ለሚያወጣ በዝግባም ሥራ ለሚያሳጌጥ በቀይ ቀለምም ለሚቀባው ወዮለት!' ብለን እናልቅስላቸው፡፡ (ኤር.፳፪፥፲፬) ወይም ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን ለነበሩት “ነገር ግን እናንተ ባለ ጠጎች ወዮላችሁ፥ መጽናናታችሁን ተቀብላችኋልና፡፡ ብሎ እንዳዘነ እንዘንላቸው፡፡
ይቀጥላል.....
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ዮሐንስ ወንጌልን በተረጎመበት ድርሳኑ ቅጽ 2 ገጽ 156-159 - በዲያቆን ሽመልስ መርጊያ የተተረጎመ)

❤57🙏4💯4🏆2
መጽሐፍ ቅዱስ ለታራሚዎች 40 ይቀረኛል!
“ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።” (ማቴዎስ 25፥36)
እሑድ መስከረም 11/2018 ዓ/ም በሕግ ጥላ ሥር ከሚገኙ ታራሚዎች (እስረኞች) ጋር ለምናካሒደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎትና በእለቱ ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ የቻሉትን ታግዙን ዘንድ እንጠይቃለን።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ለማሰባሰብ ያቀድነው 80 መጽሐፍ ቅዱስ ሲኾን የ40 ተሸፍኖልናል፤ ቀሪ 40 መጽሐፍ ቅዱስ ይቀረናል።
ማነው ከ40 መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የአቅሙን የሚያግዘን!
በእመቤቴ ዛሬንና ነገን እጨርስ ፈቃደኛ የሆናችሁ በውስጥ መስመር አናግሩን!
በዚህ @natansolo አናግሩን!

❤41👌2
፫ (የመጨረሻ)
ተግሣጽ በእንተ ቅንዓት
.....ወንድሞች ሆይ! ለእነርሱ ማዘናችሁን እንዳትተው እለምናችኋለሁ፤ ይህ የማይሆን ለመሰላቸውም ከዚህ እንዲርቁ ደረታችንን እየደቃን እናልቅስላቸው። በሥጋ ለተለዩን ሳይሆን በሕይወት ላሉት ለስስታሞቹ፤ ለነጣቂዎቹ፣ ለቀናተቹ፤ ለሆዳሞቹ እናልቅስላቸው፡፡
ስለሞተው ስለ ምን እናለቅሳለን? እነርሱን በተመለከተ የምናመጣው አንዳች ነገር የለምና፡፡ ከዚህ ድርጊታቸው ሊመለሱ ጊዜው ለተሰጣቸው ኀጢአተኞች ግን እናልቅስላቸው። ለእነርሱ በማዘናችን ግን ሊሳለቁብን ይችላሉ፡፡ ይህ በራሱ ስለ እነርሱ ለማንባት በቂ ምክንያት ይሆነናል፡፡ ምክንያቱም በዚህ ኀጢአታቸው ማቅ ለብሰው ሊያዝኑ እንጂ ሊስቁ ባልተገባቸው ነበርና፡፡ በእኛ ኀዘን ተነክተው ከዚህ ኀጢአታቸው ለመመለስ ከፈቀዱ ግን ማዘናችንን እናቆማለን፡፡
ነገር ግን ይህን ባለማስተዋል የሚመላለሱ ከሆነ ስለ እነርሱ ማንባታችንን አናቋርጥም፡፡ ለባለጠጎቹ ብቻ አይደለም፣ በፍቅረ ንዋይ ለወደቁ፣ በስስት ለተያዙ ለስግብግቦችም እናለቅስላቸዋለን፡፡ ገንዘብ በራሱ መጥፎ ሆኖ ግን አይደለም፡፡ ገንዘብን በአግባቡ ከተጠቀምንበትና ለሚገባ ነገር የተገለገልንበት በራሱ ክፋት የለበትም፡፡ ነገር ግን ስስት ክፉ ነው፤ እርሱም ዘለዓለማዊ ሞትን ያመጣብናል፡፡
ስለሆነም የንስሐ ዕድሜ ቀርቶላቸዋልና እንዲህ ላሉ ሰዎች እንዘንላቸው ወይም በዚህ ኀጢአት ወድቀው ማምለጥ ላልቻሉ እናልቅስላቸው፡፡ ሌሎችም በዚህ ኀጢአት ተሰነካክለው እንዳይወደቁ ከዚህም ይጠብቃቸው ዘንድ በእንባ በመሆን ለሰው ሁሉ እንጸልይ፡፡ በሚመጣው ዓለም ከዚህ ኀጢአት ባርነት ነጻ ወጥተው ከእኛም መካከል አንዱ ስንኳ በዚህ በኀጢአት ሳይያዝ ተስፋ የተሰጠንን መንግሥቱን እንወርስ ዘንድ የበቃን ያድርገን፡፡

❤60🙏14
አንድ ተግሣጽ ለመኝታ
ተወዳጆች ሆይ! የዋህነትንና ትሕትናን ከእርሱ እንማር፡- “ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ, እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ!"(ማቴ.፲፩፥፳፱) ብሎናልና መራርነትን ከእናንተ አርቁ፡፡ በእኛ ላይ ማንም ቢታበይ እኛ ግን በትሕትና እንጽና፣ በእኛ ላይ ደፋር ቢሆን እንታገሠው፡፡ ማንም በእኛ ላይ ቢዘብትብን በእርሱ ተቆጥተን ተሸናፊዎች አንሁን፤ ራሳችንን በምንከላከልበት ጊዜ ጥፋት ላይ እንዳንወደቅ እንጠንቀቅ፡፡ ቁጣ የዱር አራዊቶች ጠባይ ነው፡ የዱር አራዊቶች ኃይለኞችና ቁጡዎች ናቸው፡፡ ራሳችንን በምግባር የምናስጌጥበትን የምናሳርፍበትን መርህ ከመጽሐፍ ቅዱስ እንውሰድ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፡- “እንግዲህ ትቢያ አመድ የሚሆን በሕይወትም ሳለ ሰውነቱ የሚተላ ሰው ለምን ይታበያል'' (ሲራክ.፲፥፱)
ስለዚህ “ጊዜዋ እስክታልፍ ድረስ ቁጣን ታገሣት ኋላ ደስ ታሰኝሃለች"(ሲራክ.፩፥፳፪) እንዲሁም “ቊጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ ትዕግሥተኛ ሰው ግን ጸጥ ያሰኘዋል፡፡'' (ምሳ.፲፭፥፲፰) ተወዳጆች ሆይ! በቁጣ ከነደደ ሰው በላይ የተዋረደና መልከ ጥፉ የለም፡፡ ውኃ የተኛበትን ረግረግ ጭቃን ስትነካኩት መጥፎ ጠረን ከውስጡ እንዲወጣ እንዲሁ በቁጣ የተያዘች ነፍስ ከውስጧ ያኖረችው ብስጭትና ቁጭት አጠገቧ ያሉት እርሷን በመጸየፍ ከእርሷ ፈጥነው እንዲሸሹ ታደርጋቸዋለች፡፡ ነገር ግን አንዱ፡- “ከጠላቴ የሚሰነዘርብኝን ነቀፋ መታገሥ አልችልም" ሊል ይችላል፡፡ ስለዚህ ምን ላድርግ? ቢል ነቀፋው ትክክል ቢሆን መልስ ከመስጠትህ በፊት ቁጣህን ከልብህ ቆርጠህ ጣለውና ጠላቶችህን ስለ ግሣጼአቸው አመስግናቸው፤ ነቀፌታቸው ግን ትክክል ካልሆነ ንቀህ እለፈው፡፡
እርሱ ጎስቋላ ሊልህ ይችላል፤ አንተ ግን ቸለል በለው፣ ዲቃላ ወይም ደንቆሮ ሊልህ ይችላል፤ እንዲህ ለሚልህ ግን እዘንለት፤ 'ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል፡፡'' (ማቴ.፭፥፳፪) ተብሎ ተጽፎአልና፡፡ ስለዚህ ማንም ቢሆን አንተን ቢሰድብህ እርሱ የሚቀበለውን ቅጣት ልብ በልና በእርሱ ላይ አለመቆጣት ብቻ አይደለም ነገር ግን ስለእርሱ አልቅስለት፡፡ ማንም ሰው ቢሆን በንዳድ ሕመም ውስጥ ባለ ሰው ላይ አይቆጣም፤ ነገር ግን ስለ እርሱ ያዝንለታል ያለቅስለታል፡፡ ቁጣም እንደሁ በነፍስ ላይ የበቀል እሳትን ታነዳለች፡፡ ስለዚህ ራስህን ተበቃይ አትሁን፣ ሰላምን ያዝ፤ እንዲሁም አጥፊህ የሆነውን ይህን ቁጣ ፈጥነህ አብርደው፡፡ ነገር ግን በቁጣ ላይ ቁጣን ከጨመርክ እሳቱን እያፋፋምከው ነው፡፡
“ነገር ግን እንዲህ ሆነን ሲያገኙን አንዳንዶች ሰላምን በመምረጣታችን እንደ ደካሞች ይቆጥሩናል" ልትሉ ትችላላችሁ፡፡ ደካማ በመሆናችሁ የሚወቅሷችሁ አይደሉም፤ ይልቁኑ ስለ ጥበባችሁ ያደንቋችኋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አንተ በእብሪት ከሰዎች ጋር የምታጋጭና ተሳዳቢ ብትሆን፣ በተጋጨህ ቁጥር ሰዎች ስለ አንተ የሚነገረው ሁሉ እውነት እንደሆነ ለማመን ይገደዳሉ፡፡
እስቲ ንገረኝ አንድ ባለጸጋ ሰውን ድሃ ብለው ቢሰድቡት አይስቅምን? እንዲህ መሆኑ እርሱ ድሃ እንዳልሆነ ስለሚያውቅ አይደለምን? ስለዚህ እኛም በሚሰድቡን ላይ አንዘን፣ ምክንያቱም እኛን የሰደቡበት ስድብ ትክክል አለመሆኑ ስለምናውቅ ነው፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን ለሰዎች ተገቢውን ክብርን መስጠትን ስለምን እንፈራለን? የሁላችንንስ አምላክ በእኛ ምክንያት ስለምን ይነቀፋል፤ ከሥጋዊ ነገር ጋር ስለምን እንጣበቃለን? ቅዱስ ጳውሎስም፡- “ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም፡፡ ቅንዓትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን? በማለት ይገሥጸናል፡፡ (፩ቆሮ.፫፥፫) ስለዚህ መንፈሳውያን እንሁን፣ ከዚህ አስፈሪ የአውሬነት ጠባይ ፈጥነን እንራቅ፡፡ ቁጣ ከእብደት በምንም አይተናነስም፣ ለጥቂትም ሰዓት ቢሆን ዲያብሎስን መሆን ነውና፤ እንደውም ከዲብሎስም የከፋ መሆን ነው፤ አንድ ሰው ሰይጣን ያደረበት ቢሆን ይቅርታን ሊያገኝ ይችላል፡፡ ቁጡ ሰው ሰው ግን ጽኑ ቅጣት ይቆየዋል፤ ምክንያቱም በፈቃዱ ራሱን ለጥፋት አሳልፎ ሰጥቶአልና፡፡
ወደ ሲኦል ከመውረዱ አስቀድሞም በዚህ ምድር ሳለ ቅጣቱን እየተቀበለ ነውና በነፍሱ ዕረፍትን አያገኝም፤ የእሳቱም ማዕበል በውስጡ ከመቀንቀል ዝም አይልም፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ቀኑን ሙሉ በልቡ ዐሳቡን ሲያወጣና ሲያወርድ ያድራል ይውላል፡፡ ስለዚህም በዚህ ካለው ቅጣት እንድን ዘንድ በሚመጣውም ከፍርዱ እናመልጥ ዘንድ ይህን ክፉ ጠባይን ከራሳችን እናርቀው፡፡ በዚህም ዓለም በመንግሥተ ሰማያትም ለነፍሳችን ዕረፍትን እናገኝ ዘንድ የዋሃንና ትሑታን እንሁን፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ለዚህ የተገባን እንድንሆን ያብቃን፡፡
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ዮሐንስ ወንጌልን በተረጎመበት ድርሳኑ ቅጽ 1 - ገጽ 442-443 - በዲያቆን ሽመልስ መርጊያ የተተረጎመ)

❤96🙏15🏆1
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ሰላም ተወዳጆች ለአንዲት በጉባላፍቶ ወረዳ ቤተክህነት ሥር ለምትገኝ ዝርጋ ማርያም እየተባለች ለምትጠራ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ንዋየ ቅድስት (መጻሕፍት፣ ልብሰ ተክህኖ፣ እጣን፣ ዘቢብ፣ ጧፍ፣ ሻማ....) ያስፈልጋልና ወደጆቼ አለን በሉኝ። @natansolo
ሰላም እንዴት አመሻችሁ?
በጉባላፍቶ ወረዳ ቤተክህነት ለዝርጋ ማርያም ቤተክርስቲያን ከሚያስፈልጉ ንዋየ ቅድሳት መካከል የአምስቱን ቀዳሲያን ልብሰ ተክህኖውን ገዝተናል። ሌሎች ለአገልግሎት የሚሆኑ ቅዳሳት መጻሕፍትን ለመግዛት ቃል የተገባልን ሲደርሰን ገዝተን የምናስረክብ ይሆናል።

❤80🙏13🕊3
#ጼዴንያ - #መስከረም_10
መስከረም ዐሥር በዚች ቀን ጼዴንያ በምትባል አገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል ሥዕል ከሠሌዳዋ ቅባት እየተንጠፈጠፈ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ተአምር ተገለጠ።
ይቺንም ሥዕል የሣላት ወንጌላዊ ሉቃስ ነው ይባላል። ወደ ጼዴንያ አገርም የመጣችበት ምክንያት አንዲት ስሟ ማርታ የሚባል መበለት ሴት ነበረችና ቤቷንም ለእንግዳ ማደሪያ ያደረገች ናት። አምላክን የወለደች እምቤታችን ድንግል ማርያምንም እጅግ ትወዳት ነበር። በሚቻላትም ሁሉ ታገለግላታለች።
በአንዲት ቀንም ስሙ ቴዎድሮስ የሚባል መነኩሴ ከእርሷ ዘንድ እንግድነት አደረ በመልካም አቀባበልም ተቀበለችው በማግሥቱም ስተሸኘው አባት ሆይ የምትሔደው ወዴት ነው አለችው። እርሱም በከበሩ ቦታዎች ውስጥ ልሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም እሔዳለሁ አላት እርሷም ከእኔ ገንዘብ ወስደህ የእመቤታችን ማርያምን ሥዕል ግዛልኝና በመመለሻህ ጊዜ አምጣልኝ አለችው። እርሱም በራሴ ገንዘብ ገዝቼ አመጣልሻለሁ አላት።
ከዚህም በኋላ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከቅዱሳት መካናት ተባረከና ሥዕሏን ሳይገዛ ወደ ጎዳናው ተመለሰ። ያን ጊዜም ሥዕል መግዛትን ለምን ረሳህ የሚል የሚያስደነግጥ ቃልን ሰማ ወደ ገቢያም ተመልሶ ላሕይዋና መልኳ ያማረና የተወደደ የሆነ የእመቤታችን ማርያምን ሥዕል አግኝቶ ገዛት በሐርና በንጹሕ ልብስም ጠቀለላት።
በጎዳናውም እየተጓዘ ሳለ ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ወንበዴዎች ተነሡበት ሊሸሽም ወደደ ከዚያቺም ሥዕል መንገድህን ሒድ የሚል ቃል ወጣ የተከተለውም ሳይኖር መንገዱን ተጓዘ። ሁለተኛም ነጥቆ ሊበላው አንበሳ ተነሣበት ያን ጊዜም ከዚያች ሥዕል የሚያሥፈራ ድምፅ ወጥቶ አንበሳውን አባረረው።
አባ ቴዎድሮስም ይህን ሁሉ ድንቅ ተአምር ባየ ጊዜ ያቺን ሥዕል ወደ አገሩ ሊወስዳት ወደደ ግዛልኝ ላለችው መበለት ይሰጣት ዘንድ አልፈለገም።
ከዚህም በኃላ በመርከብ ተሳፍሮ በሌላ አቅጣጫ ሲጓዝ ታላቅ ነፋስ ተነሣበት ወደ ማርታ አገር ወደ ጼዴንያም ወሰደው ከመርከቡም ወርዶ ከብዙ እንግዶች ጋር ወደዚያች መበለት ቤት ሔደ ማንነቱንም አልገለጠላትም እርሷም አላወቀችውም።
በማግሥቱም ተሠውሮ ወጥቶ ወደ አገሩ ሊሔድ በፈለገ ጊዜ የቅጽሩን ደጃፍ አጥቶ ሲያጥመሰምስ ዋለ በመሸ ጊዜም ወደ ማደሪያው ተመለሰ። ያቺም መበለት በአየችው ጊዜ ታደንቃለች እንዲህም ሁኖ እስከ ሦስት ቀን ኖረ በመሸ ጊዜ በሩን ያየዋል ነግቶ መሔድን ሲሻ የበሩ መንገድ ይሠወረዋል። ያቺም መበለት ያዝ አድርጋ አባቴ ሆይ አእምሮህ ተነክቷልን ስትቅበዘበዝ አይሀለሁና ምን ሆነህ ነው አለችው።
ከዚህም በኋላ ከዚያች ሥዕል የሆነውን ሁሉ ነገራት ራሱንም ገለጠላት። ያቺንም ሥዕል ሰጣት ተቀብላም የተጠቀለለችበትን ልብስ ፈታች ወዝ ከሥዕሊቱ ሲንጠፈጠፍ አገኘች። ከደስታዋም ብዛት የተነሣ የዚያን መነኩሴ እጆቹንና እግሮቹን ሳመች።
ከዚህም በኋላ ያቺን ሥዕል ወደ ጸሎት ቤቷ ወስዳ በታላቅ ክብር የምትቀመጥበትን አዘጋጅታ አኖረቻት ማንም እንዳይዳስሳትም የነሐስ መስኮትን ሠራችላት በቀንና በሌሊትም የሚበሩ መቅረዞችን በፊቷ ሰቀለች ከመቅረዞችም ውጭ የሐር መጋረጃን ጋረደች። ከሥዕሊቱ በታችም ከሥዕሊቱ እየተንጠፈጠፈ የሚወርደው የወዝ ቅባት የሚጠራቀምበት ከዕብነ በረድ የተሠራ ወጭት አኖረች ያም መነኩስ እስከሚሞትበት ቀን ድረስ የእመቤታችንን ድንግል ማርያምን ሥዕል እያገለገለ ኖረ።
የሀገሩም ሊቀ ጳጳሳት የዚያችን ሥዕል ዜና በሰማ ጊዜ ከኤጲስቆጶሳትና ከካህናት ከሕዝቡም ሁሉ ጋር መጣ በሠሌዳውም ውስጥ በአዩዋት ጊዜ ሥጋ የለበሰች ሁና አገኙዋት ከዚህ ከአምላካዊ ግብር የተነሣ አደነቁ ከዚህም ቅባት ቀድተው ለበረከት በተካፈሉ ጊዜ ወዲያውኑ በወጭቱ ውስጥ ይመላል።
ወደ ሌላ ቦታም ሊወስዷት በፈለጉ ጊዜ ንውጽውጽታ ሆኖ ብዙዎች በድንጋጤ ወደቁ ሥዕሊቱም እስከ ዛሬ በዚያች አገር ትኖራለች።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእናቱ በእመቤታችን በድንግል ማርያም ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መስከረም)

❤81🙏11🕊5💔2
ስለ ጌጠኛ ልብስ - ፩
ዕርቃናችንን የምንሸፍንበት ልብስ ብቻ ልንለብስ ይገባናል፡፡ ብዙ ወርቅን ብናደርግ ምንድነው ትርጉሙ? ብዙ ወርቅን ማድረግ በተውኔት ቤት ነው፤ ተዋንያን ብዙ ተመልካችን ለማግኘት ያደርጉታልና፡፡ ጌጠኛ ልብስ መልበስ የአመንዝራ ሴቶች ግብር ነው፤ ብዙ ወንዶች ይመለከቱአቸው ዘንድ ይህን ያደርጋሉና፡፡ እነዚህን ማድረግ ልታይ ልታይ ለሚሉ ሰዎች ነው፡፡ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት የምትሻ ሴት ግን ይህን ጌጥ ማድረግ አትፈልግም፡፡ ራስዋን የምታስጌጠው በሌላ መንገድ ነውና፡፡
እናንተም ይህን ጌጥ ማድረግ የምትፈልጉ ከኾነ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ተውኔት ቤትን የምትሹ ከኾነም ወርቀ ዘቦአችሁን የምታደርጉበት ሌላ ተውኔት ቤት አለላችሁ፡፡ ያ ተውኔት ቤትስ ምንድን ነው? መንግሥተ ሰማያት ነው፡፡ ተመልካቾቹ ቅዱሳን መላእክት ናቸው፡፡ ይህን የምናገረው በገዳም ለሚኖሩት መኖኮሳይያት ብቻ አይደለም፤ በማዕከለ ዓለም ለሚኖሩትም ኹሉ ጭምር ነው እንጂ፡፡ በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ውሉድ የተባለ ኹሉ የራሱ ተውኔት ቤት አለውና፡፡
ስለዚህ ተመልካቾቻችንን ደስ ለማሰኘት ራሳችንን ደኅና አድርገን እናጊጥ ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ለመድረኩ የሚመጥን ልብስን እንልበስ ብዬ እማፀናችኋለሁ፡፡ እስኪ ንገሩኝ! አንዲት ሴሰኛ ሴት ተውኔት ለመሥራት ብላ ብዙ ወርቋን አወላልቃ፣ ቄንጠኛ መጎናጸፍያዋን ጥላ፣ በሳቅ በስላቅ ሳይኾን ቁም ነገርን ይዛ፣ ተርታ ልብስን ለብሳ ወደ መድረኩ ብትወጣና ሃይማኖታዊ ንግግርን ብትናገር፣ ስለ ንጽህና ስለ ቅድስና ብትናገር፣ ሌላ ክፉ ንግግርም ባትጨምር በተውኔት ቤቱ የሞላው ሰው አይነሣምን? ተመልካቹ ኹሉ የሚበተን አይደለምን? ሰይጣን የሰበሰበው ተመልካቹ የማይፈልገውን ነገር ይዛ ስለ መጣች ኹሉም የሚሳለቅባትና እንደ ትልቅ አጀንዳ የሚወራላት አይደለምን? አንተም በብዙ ወርቅ፣ በጌጠኛ ልብስ ተሸላልመህ ወደ መንግሥተ ሰማያት ብትገባ ቅዱሳን መላእክት አስወጥተው ይሰዱሃል፡፡ ምክንያቱም በመንግሥተ ሰማያት የሚያስፈልገው ልብስ እንደዚህ ዓይነት አይደለም፤ ሌላ ነው እንጂ፡፡ “እርሱስ ምን ዓይነት ነው?” ትለኝ እንደኾነም “ነፍስን በትሩፋት ማስጌጥ ነው” ብዬ እመልስልሃለሁ፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ክቡር ዳዊት፡- “ልብሷ የወርቅ መጐናጸፍያ ነው” ያለውም ይህንኑ ነው እንጂ በዚህ ምድር የምንለብሰው ልብሳችንን ፀዓዳና አንጸባራቂ ስለ መኾን አይደለምና (መዝ.45፡13)፡፡ ምክንያቱም “ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ኹሉ ክብሯ ነው” እንዳለ በዚያ (በመንግሥተ ሰማያት) መራሔ ተውኔቷ እርሷ ናት፡፡
ይቀጥላል...
(የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች ቅዱስ ዮሐንስ_አፈወርቅ እንደአስተማረው ገጽ 47-55➛ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው)

❤77🙏18👍2
እናመሰግናለን
ነገ መስከረም 11/2018 በሰሜን ወሎ ወልድያ ማረሚያ ቤት ከሚገኙ ታራሚዎች ጋር በምናካሂደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በዕለቱ ለምናስረክበው የመጽሐፍ ቅዱስ ስጦታ ከ27 የቻናላችን ቤተሰቦች ብር 49,550 የተገኘ ሲሆን በዚህም ለመግዛት የሚያስችለውን 40 መጽሐፍ ቅዱስ በነገው እለት የምናስረክብ ሲሆን፤ በዚህ መልካም ተግባር የተሣተፋችሁ፣ ለመሣተፍ አስባችሁ ያልተሳካላችሁ እንዲሁም በጸሎት ያገዛችሁን ኹሉ በኃያሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም ምስጋናችን ይድረሳችሁ።
ማሳሰቢያ፦
መጽሐፍ ቅዱስ ለመግዛት ያሰብነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር በ900 ብር ሒሳብ የነበረ ቢሆንም በዚህ ወቅት በማኅበሩ ያለው የኅትመት መጠን አናሳ መሆን የተነሳ ከወልድያ መንበረ ንግሥት ኪዳነ ምሕረት የመሠረተ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት ልማት ተቋም ከመደበኛ ዋጋው በመቀነስ በብር 1200 ዋጋ 40 መጽሐፍ ቅዱስ የገዛን መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

❤56🙏7😍2