Telegram Web Link
እኛ ስንት ክፍል ቤት ውስጥ እንኖራለን? አንድ ክፍል እንኳን ብንል ስንት ቤተሰብ ነን? ቢበዛ 10 ነው!

በሜቄዶንያ በአንድ ክፍል ውስጥ ከ7ዐዐ በላይ አረጋውያን ይኖራሉ:: ሌላ ሕመማቸውን ትተን በዚህ ሁኔታ መኖር ብቻ የሚያመጣው ብዙ ሕመም አለ::

የካቲት 1 የሜቄዶንያን ሕንፃ ለመጨረስ በሰይፉ ኦን ኢቢኤስ የዩቲዩብ ቻናል ላይ እንዘምታለን:: በዚህም ትልቁን ሆስፒታልና የአረጋውያን ማረፊያ እንሠራለን!

ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

የመቄዶንያ የክብር አምባሳደር
▫️@diyakonhenokhaile
2008 ዓ.ም. ከዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ ጋር የተባበሩት ዐረብ ኢመሬትስ ሻርጃ ሰአሊተ ምሕረት አብረን ለማገልገል ተጠርተን ነበር:: ከሃያ ቀናት በላይ በየቀኑ በሚካሔደው በዚህ ጉባኤ ላይ ዘማሪት ሕይወት መሣሪያ በማይፈልገው የተለየ ድምፅዋ “ና ና አማኑኤል ና መድኃኒቴ" የሚል ድንቅ መዝሙር ስትዘምር ሰማሁ::

"ስሸጥህ አቀፍከኝ ስወጋህ ዓይኔ በራ” እያለ ራስን ከይሁዳና ከሌንጊኖስ ጋር በትሕትና የሚያነጻጽረው ይህን መዝሙር በጣም ስለወደድሁት አንዲት ቃል ላይ ብቻ እርማት እንድታደርግ አስተያየት ሰጥቼ አብረን በሰነበትንበት ሻርጃ ሕዝቡ በቃሉ እስኪይዘው ድረስ 14ቱንም ቀን አስዘመርኳት::

ዘማሪት ሕይወት ተፈሪ በሙያዋ ነርስ ስትሆን ቤተ ክርስቲያን ቆንጥጣ ካሳደገቻቸው ወርቅ ዘማርያን አንድዋ ናት:: ሰዓታት የምትቆም ፣ አስቀድሳ የምቆርብ ፣ መምህሩ ያስተማረውን ቁጭ ብላ ሰምታ ለትምህርቱ የሚስማማ መዝሙር የምትዘምር ፣ በጣም በትሕትናና በታዛዥነት የምታገለግል ካላት የዝማሬ ጸጋ ገና የሚገባትን ያህል ያልተሰማች (Underrated) ያወቋትና የሰሟት ደግሞ እንዴት ሳልሰማት ቀረሁ የሚሉባት የቤተ ክርስቲያን ውድ ልጅ ናት:: እግዚአብሔር ይጠብቅልንና ዘማሪት ሕይወት ከ "ረ" ፊደል በስተቀር በመዝሙር ዘርፍ ገና ለመሥራት ምንም የሚቸግራት ነገር የለም::

ሰሞኑን በአእላፋት ዝማሬ ላይ "ና ና አማኑኤል" የሚለው መዝሙር በጃን ያሬድ መዘምራን ሲዘመር የሰሙና የወደዱት ምእመናን “ይኼ መዝሙር ግጥሙ የአንተ ነው" በሚል ሲመርቁኝ ሰነበቱ:: ምርቃቱን ሳላስተባብል አሜን ብዬ ብቀበልም ይህንን በሳል መዝሙር ግጥምና ዜማ የሠራውን ሰው ግን በጸሎት እንድታስቡትና እንድትመርቁት ማሳሰብ የግድ ሆነብኝ::

የመዝሙር ርእስ :- ና ና አማኑኤል ና መድኃኒቴ

ዘማሪዋ :- ዘማሪት ሕይወት ተፈሪ

ግጥም :- ዘማሪት ሕይወት ተፈሪ

ዜማ :- ዘማሪት ሕይወት ተፈሪ

#share
▫️@diyakonhenokhaile
https://www.tg-me.com/diyakonhenokhaile
"በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን"
1 ቆሮንቶስ 15:19
▫️@diyakonhenokhaile
We are now on TikTok

አሁን ቲክቶክም ላይ ያገኙናል
@diyakonhenokhaile
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የመጀመሪያው ቪድዮ ተለቀቀ

ዘወትር ዐርብ በ Henok Haile - Official Channel ይጠብቁ
#share #share
@diyakonhenokhaile
+ ምሕረት የለሹ ምሕረት +

የወንድሜ የዲያቆን ምሕረት መላኩንና የሁለቱን ፓስተሮች ውይይት ዘግይቼም ቢሆን አየሁት:: ውይይቱ በጣም በሰከነው የዲያቆኑ ኦርቶዶክሳዊ ጨዋነት የተነሣ ሁለቱን የፕሮቴስታንት ዋርካዎች በትሕትና ብቻ የገነደሰ ነበረ:: ቅመሙ ዲያቆን ምሕረት ውይይቱ እንደሚቀረጽ በደንብ ስላስተዋለ ጠይቆአቸው ሳይመልሱ ያለፉትን ወይም ያልተጠየቁትን ጉዳይ ያነሡበትን ቦታ ሁሉ ልክ ነጥብ “ተመልካች ይፍረድ” በሚመስል ብልጠት እየተወ ወደ ቀጣዩ ነጥብ የሚሸጋገርበት ፍጥነት ድንገት የገባበት ውይይት ሳይሆን የተጠና (scripted) ውይይት እንዲመስል አድርጎታል:: በጣም በትሕትና ሆኖ እየጠየቀ ዕርቃናቸውን ያሳየበት መንገድ ምን ያህል ሊያናድዳቸው እንደሚችል ሳስብ ውይይቱ በሰላም አለቀ እንጂ “ከአሁን አሁን ይመቱት ይሆን?” ብዬም ተሳቅቄያለሁ::

በውይይቱ ላይ ካየኋቸው ያስገረሙኝን ጥቂት እውነታዎች ላስቀምጥ:-

1. ቤተ ክርስቲያንን የሙጥኝ ማለት

ዲያቆን ምሕረት ውይይቱን የጀመረው የፓስተሮቹን አስተምህሮ ከቤተ ክርስቲያን ቅድምና አንጻር በማንሳት ነበር:: በዚህም ለፕሮቴስታንቱ ዓለም ደካማ ጎን የሆነውን ስስ ብልት በመምታት ጀመረ::
@diyakonhenokhaile
ነገሩ እንዲህ ነው:: መጽሐፍ ቅዱስን አሁን ባለው ቅርጽ እንዲህ አድርጋ የሠራችው ቤተክርስቲያን ናት:: ይህ እውነታ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን በቀጥታ ከሐዋርያት እጅ የተቀበሉትንና ሐዲስ ኪዳን በቀኖና ወስነው ለእኛ ያስተላለፉትን የመጀመሪያዎቹን ክርስቲያኖች ትርጉምና አረዳድ እንድንቀበል ያስገድደናል:: ልክ እስራኤል ሕግን ተቀብሎ የመጣውን ሙሴን እንደ ባለ ሥልጣን እንደተቀበሉትና ስለ ሕጉ የእርሱን አሳብ ያለማወላወል እንደተቀበሉ ሁሉ ሐዲስ ኪዳንን ከሐዋርያት እጅ የተቀበሉትን የመጀመሪያው ክፍለ ዘመን አባቶችም በሐዲስ ኪዳን ትርጉም ላይ ያላቸውን ሃሳብ መቀበል ግድ ይለናል:: ይህን ጠንቅቆ የተረዳው ዲያቆን ምሕረት:-

ጥምቀትና ቁርባን ተምሳሌቶች እንጂ ለድኅነት ፍቱን አይደሉም ስትሉን ነበር:: ከአንደኛ እስከ ሦስተኛው ክፍለ ዘመን ያሉ ክርስቲያኖችን ሃሳብ ስናይ ደግሞ እነዚህ ነገሮች ለመዳን የግድ እስፈላጊ መሆናቸውን ጽፈው እናገኛለን:: የእኔ ጥያቄ መጽሐፍ ቅዱስን በቀጥታ ከተቀበሉትና ሐዲስ ኪዳንን በቀኖና ከደነገጉ ክርስቲያኖች ጋር ትርጓሜያችሁ ካልገጠመ ምኑን በመጽሐፍ ቅዱስ አመናችሁ ይባላል? አላቸው::

በአጭሩ መጽሐፍ ቅዱስን ያዋለዱትን አዋላጆች ካልሰማችሁ ምኑን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሆናችሁት “ድምፅህ የያዕቆብን ይመስላል ጸጉርህ ግን የኤሳው ነው” ያለው ለእናንተ አይደል ወይ? እንደማለት ያለ ነው::
@diyakonhenokhaile
ዲያቆን ምሕረት በዚህ ጥያቄው ሰዎቹን ጨርሶ ወደማውቁት ጨለማ ክፍል ወስዶ ቆለፈባቸው:: የአንደኛው ክፍለ ዘመን አባቶች ሥነ ጽሑፍና ታሪክ ለእነርሱ የማያውቁት የውጊያ ዐውድ ነው:: ወደ በኋላም በምሥጢረ ቁርባን ዙሪያ ባለው ግልፅ አቋምና ከሐዋርያት ጋር በነበረው ቅርበት የተነሣ የፕሮቴስታንት ሊቃውንት “ምነው ባልተፈጠረ” የሚሉትንና አንዳንዶቹም “እሱ አልጻፈውም” ብለው መጽሐፉን ለመካድ የሚገደዱበትን ቅዱስ አግናጥዮስን በመጥቀስ አስጨንቆአቸዋል::

የሚገርመው የሠጡት መልስ :-

የምትለው እውነት ከሆነ ለምን ሚልዮኖች ሳይቀበሉት ቀሩ? የሚል ልፍስፍስ ጥያቄ ነው::

ምሕረት መለሰ :- ይህማ እጅግ ብዙ ሰዎች ወንጌልን ላለመቀበላቸውም የሚቀርብ ምክንያት ነው::

ብሎ የራሳቸውን አመክንዮ በራሳቸው ላይ መለሰው:: በሳልሽው ተመተሪ!

ፓስተሩ :- እስቲ በሁለቱም ወገን (ጥምቀትና ቁርባን ለድኅነት ያስፈልጋል አያስፈልግም) ከሚሉ ወገን አባቶችን በስም ጥቀስልኝ አለው::

“መረጃ ተጠናክሮ በሁለቱም ወገን ይቅረብልን” እንደሚል ዳኛ ውይይቱን ትቶ ዳኛ ሊሆን ተማጸነው::

“በሁለት ወገን ብሎ ነገር የለም:: ከዚህ ውጪ ሃሳብ ያለው ሰው ስለመኖሩምንም የተቀመጠ ታሪካዊ ማስረጃ የለም” አለ ምሕረት የለሹ ምሕረት::
@diyakonhenokhaile
እዚህ ላይ እንኳን ደንግጠው ነው እንጂ እርሱ የጠቀሳቸው እነ ቅዱስ ሄሬኔዎስና ቅዱስ አግናጥዮስ መልስ የሰጡት ታዲያ ለማን ነበር? ብለው መጠየቅ ይችሉ ነበር:: ዶሲቲስቶችና ግኖስቲኮች ሙሉ በሙሉ የፓስተሮቹን ሃሳብም ባይሆን ቁርባን ላይ ተቃዋሚዎች ነበሩ:: የምሕረት መልአክ ቀሳፊ መልአክ ሆኖባቸው ግን ትንሽ እንኳን አልታገሉም:: ግን ዶሲቲስቶችና ግኖስቲኮች ተጠቃሽ ክርስቲያኖች ስላልሆኑ ሁለት ወገን አልነበረም ቢል ዲያቆን ምሕረት ልክ ነው::

“So you are saying” አለ ፓስተሩ:: የJordan Peterson እና የCathy Newmanን አስቂኝ ቃለ መጠይቅ ከሰማሁ ወዲህ ክርክር ላይ “So you are saying” ብሎ ተከራካሪው አፍ ውስጥ ቃላት ለመክተት የሚሞክር ሰው የራሱን ቀብር ጡሩምባ እየነፋ ይመስለኛል::

ፓስተሩ “እሺ ሉተርስ?” አለ:: (ኸረ ባልወልድህም አደርስሃለሁ ተው በሰው ፊት አታዋርደኝ:: ሉተር እንኳን ቁርባንን ተቃውሞአል በልልኝ [በሆዱ ያለ ይመስለኛል])

ምሕረት ወይ ፍንክች የሉተርን መፍቀሬ ቁርባን የሆነ “I would rather drink pure blood with the pope than mere wine with the radicals” የሚል ንግግር ሊጠቅስበት ጀመረ:: (በዚህ ጉዳይ ሉተርና ሚካኤል የሚል ያልታተመ መጽሐፍና ያልተለቀቀ የYoutube video ስላለ ሁለቱንም በቅርብ እዚሁ ላይ Link አደርጋለሁ) “ነገሩ የመጣው ገና 500 ዓመት ከሆናቸው ከራዲካል ሪፎርመሮች ነው” ብሎ የሉተርን ባላንጦች ጠቀሰበት::
@diyakonhenokhaile
ፓስተሩ “ጊዜው ምን ያደርጋል” አለ:: ስለ ታሪክ እየተወራ ጊዜው ምን ያደርጋል ከሚል ሰው ይሰውራችሁ::

“ከታሪክ አንጻር ክርስትና ጌታ ለሐዋርያት የሠጠው እምነት ነው ብለህ ካመንህ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች የምታምነውን እንደሚያምኑ የሚያሳይ ነገር ልታገኝ ይገባሃል” አለው::

ፓስተሩ “ወዳጄ እመነኝ በዚያን ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች ሁሉ ክርስቶስ ‘የራሱን ሥጋ’ በልቶአል ብለው አላመኑም” ብሎ ነገሩን ridiculous ሊያደርገው ሞከረ:: ይህን ስሰማ ትዝ ያለኝ “ይህ ሰው ሥጋውን ልንበላ ይሰጠን ዘንድ እንዴት ይችላል?” ብለው አይሁድ የተከራከሩት ክርክር ነው:: ዮሐንስ 6:52
ጌታ ሥጋዬ እነሆ እያለ የለም ሥጋህ አይደለም ብሎ ክርክር እንዴት ያለ ነው::

ዲያቆኑ ሐዋርያውን ጠቅሰ “ሳይገባው ይህን እንጀራ የበላ ወይም የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ አለበት። ስለዚህ በእናንተ ዘንድ የደከሙና የታመሙ ብዙዎች አሉ አያሌዎችም አንቀላፍተዋል” 1 ቆሮ. 11:30 ከዚያም : “ሥጋና ደሙ ተራ እንጀራና ወይን ብቻ ከሆነ እንዴት ሳይገባቸው ተቀብለው የሞቱ ሰዎች ሊኖሩ ቻሉ?” ብሎ ጠየቀ::
አዝናኙ ውይይት እንደቀጠለ ነው:: ሰውዬው ጥያቄውን መመለስ ትቶ Unworthy ማለት worthy ያልሆነ ነው ብሎ ቃሉን አብራራ:: ቀጠለና ጉዳዩን ከማይገናኘው የሴት ጠጉር አለመሸፈን ጋር አገናኘው:: (ሲጀመር ጠጉር ስላልሸፈነች የሞተች የለችም እየተወራ ያለው ቆርበው ስለሞቱ ሰዎች ነው) አልበቃው ብሎ ስለ sex godess ስለ me too movement ዘባረቀ:: መልስ ስታጣ የምታውቀውን ሁሉ ልትዘባርቅ እንደምትችል ያሳያል::

ዲያቆኑን ማባበልም ጀመረ “የአንተን ሃሳብ የሚያራምዱ ሰዎችን ከልቤ አከብራለሁ:: እውነት እውነት እላችሁዋለሁ የሚለውን ይዘው ይህ እውነተኛ ሥጋው ነው የሚሉት ከልብ አከብራለሁ” አለ:: አክባሪ ይሥጥልን ግን እኛ ይሄን ጥቅስ እንደማስረጃ አላነሣንም:: ዲያቆኑ እዚያው ቆሞ “ለተራ እንጀራ ሰው እንዴት ይሞታል?” ብሎ የጠየቀውን ፍጥጥ ያለ ጥያቄ ትቶ ከዚህ በፊት ሌሎች ሰዎች ያነሡትን weak argument እየጠቀሰ እንዲህ በለኝና ልርታህ ብሎ ተለማመጠ:: (ተው ባልወልድህም አባትህ እሆናለሁ is in my head)

ከዚያ ደግሞ በmystical change የሚያምነውን ኦርቶዶክሳዊ በግድ transubstantiationን ካላመንክልኝና እርሱን ለመቃወም ያጠራቀምኩትን መከራከሪያ አንተ ላይ ልጠቀመው ይል ጀመር::

ቀጥሎ የተነሣው ድኅነት ሒደት ነው የሚለው ሃሳብ ነው:: ይሄን ጊዜ ፓስተሩ ከቁርባን ርእስ እርፍ ያለ መስሎት ፈነደቀ::
“It is now becoming a salvation issue” እያለ ሲቅበጠበጥ አሁን ገና ተመቻቸህልኝ ብሎ ደስ እንዳለው ያስታውቅ ነበር:: ምሕረቱ “ድናችኋል ብቻ ሳይሆን ትድናላችሁም ይላል” ብሎ የድህነትን ሒደታዊነት አብራራ::


ይህን ጊዜ ሌላው ፓስተር ጸጋ አላስቻለውምና ገባ

ፓስተር ጸጋ “ በጸጋው ድናችኋል” ይላል አለና ዘሎ ገባ::

ድኅነት synergetic ስለሆነ የጸጋው energy የእኛን ትብብር ይሻ የለም ወይ? አለና ምሕረቱ “መዳናችሁን ፈጽሙ”ን ጠቀሰ:: አብርሃምም ልጁን የመሠዋቱን ሥራ አነሣ:: እነርሱ ግን “work out your salvation” የሚለው ቃል ውስጥ “work” የሚል ቃል ሲሰሙ ደስታቸውን መሸከም አልቻሉም:: ቃሉን ጳውሎስየተናገረው መሆኑም አላሳሰባቸውም::

ሥራን ለማጣጣል የቀኙን ወንበዴ ጠቀሱ:: ተቸንክሮ ምን ሊሠራ ይችላል አለ:: (Though the thief on the cross was nailed, he still worked on his salvation. He confessed his sin, saying that he was worthy of the cross. He taught his companion to fear God, and he professed the purity of Christ and the coming of His kingdom)

እግዚአብሔር ባልሠጠው መክሊት አይጠይቅምና circumstantial ነው አለ:: ሊሞት አልጋ ላይ ስላለ ሰው አለመጠመቅ አላወራሁም ብሎ ሞገተ::
@diyakonhenokhaile
2025/06/27 13:16:26
Back to Top
HTML Embed Code: