Telegram Web Link
#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ገብርኤል (#ታኅሣሥ_19)

ታኅሣሥ ዐስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅ ያዳነበት ነው፡፡ ንጉሥ ናቡከደነፆር ከአባታቸው ከይሁዳው ንጉሥ ከኢዮአቄም ጋር የማረካቸው አናንያ፣ ሚሳኤልና አዛርያ እግዚአብሔር በዚህች ዕለት መልአኩን ልኮ ታላቅ ተአምር አድርጎላቸዋል፡፡

ንጉሥ ናቡከደነፆር እነዚህን ወጣቶች በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ጥበብን እያስተማረ ካሳደጋቸው በኋላ በባቢሎን ሀገሮች ሁሉ ውስጥ ሾማቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሡ የወርቅ ምስል በሠራ ጊዜ መኳንንቱንና በግዛቱ ውስጥ ያሉ ሁሉ ለዚያ ምስል እንዲሰግዱ አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ ለጣዖቱ ባለመስገድ እግዚአብሔርን ብቻ በማምለክ የጸኑት እነዚህ ሦስት ወጣቶች ብቻ ነበሩ፡፡ ስለ እነርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡-
‹‹ንጉሡ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቁን ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው፡፡ ንጉሡም ናቡከደነፆር መኳንንትንና ሹማምቶችን፥ አዛዦችንና አዛውንቶችን፥ በጅሮንዶችንና አማካሪዎችን፣ መጋቢዎችንም፣ አውራጃ ገዦችንም ሁሉ ይሰበስቡ ዘንድ፣ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ይመጡ ዘንድ ላከ፡፡ በዚያን ጊዜም መኳንንቱና ሹማምቶቹ፣ አዛዦቹና አዛውንቶቹ፣ በጅሮንዶቹና አማካሪዎቹ፣ መጋቢዎቹና አውራጃ ገዦቹ ሁሉ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ተሰበሰቡ፤ ናቡከደነፆርም ባቆመው ምስል ፊት ቆሙ፡፡ አዋጅ ነጋሪውም እየጮኸ እንዲህ አለ፡- ‹ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የምትናገሩ ሆይ! የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፣ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል፡፡ ተደፍቶም የማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል፡፡› ስለዚህ በዚያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉ የመለከቱንና የእንቢልታውን፣ የመሰንቆውንና የክራሩን፣ የበገናውንና የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፣ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የተናገሩ ሁሉ ተደፉ፤ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቅ ምስል ሰገዱ፡፡

በዚያን ጊዜም ከለዳውያን ቀርበው አይሁድን ከሰሱ፡፡ ለንጉሡም ለናቡከደነፆር ተናገሩ እንዲህም አሉ ‹ንጉሥ ሆይ! ሺህ ዓመት ንገሥ፡፡ አንተ ንጉሥ ሆይ የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ የሚሰማ ሰው ሁሉ ተደፍቶ ለወርቁ ምስል ይስገድ፤ ተደፍቶም የማይሰግድ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል ብለህ አዘዝህ፡፡ በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምሃቸው ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም የሚባሉ አይሁድ አሉ፤ ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ትእዛዝህን እንቢ ብለዋል፤ አማልክትህን አያመልኩም፥ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል አይሰግዱም፡፡› ናቡከደነፆርም በብስጭትና በቍጣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም ያመጡ ዘንድ አዘዘ፤ እነዚህንም ሰዎች ወደ ንጉሡ ፊት አመጡአቸው፡፡ ናቡከደነፆርም ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ሆይ! አምላኬን አለማምለካችሁ ላቆምሁትም ለወርቁ ምስል አለመስገዳችሁ እውነት ነውን? አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን የመሰንቆውንና የክራሩን የበገናውንና የዋሽንቱን የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ተደፍታችሁ ላሠራሁት ምስል ብትሰግዱ መልካም ነው፤ ባትሰግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ፤ ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው?›› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም መለሱ ንጉሡን ‹ናቡከደነፆር ሆይ! በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም፡፡ የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ነገር ግን ንጉሥ ሆይ! እርሱ ባያድነን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ› አሉት፡፡

የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት፡፡ የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው፡፡ እርሱም ተናገረ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት አዘዘ፡፡ ሲድራቅንና ሚሳቅንም አብደናጎንም ያስሩ ዘንድ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ፡፡ የዚያን ጊዜም እነዚህ ሰዎች ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸውም ከቀረውም ልብሳቸው ጋር ታስረው በሚነድድ በእቶን እሳት ውስጥ ተጣሉ፡፡ የንጉሡም ትእዛዝ አስቸኳይ ስለሆነ የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ፣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው፡፡ እነዚህም ሦስቱ ሰዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ታስረው በሚነድደው በእቶኑ እሳት ውስጥ ወደቁ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ፤ አማካሪዎቹንም ‹ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን?› ብሎ ተናገራቸው፡፡ እነርሱም ‹ንጉሥ ሆይ! እውነት ነው› ብለው ለንጉሡ መለሱለት፡፡ እርሱም ‹እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል› ብሎ መለሰ፡፡ የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ ‹እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም! ኑ ውጡ› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅም አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ፡፡

መሳፍንቱና ሹማምቶቹም አዛዦቹና የንጉሡ አማካሪዎች ተሰብስበው እሳቱ በእነዚያ ሰዎች አካል ላይ ኃይል እንዳልነበረው፣ የራሳቸውም ጠጕር እንዳልተቃጠለች ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ፣ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው አዩ፡፡ ናቡከደነፆርም መልሶ ‹መልአኩን የላከ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፣ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ፡፡ እኔም እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም አምላክ ላይ የስድብን ነገር የሚናገር ወገንና ሕዝብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ይቈረጣሉ፣ ቤቶቻቸውም የጕድፍ መጣያ ይደረጋሉ ብዬ አዝዣለሁ› አለ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም በባቢሎን አውራጃ ውስጥ ከፍ ከፍ አደረጋቸው፡፡›› ትንቢተ ዳንኤል 3፡1-30፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በመልአኩ አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

( ስንክሳር ዘተዋሕዶ )
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
ከጠላት ፈተናዎች ተጠንቀቅ!

ዲያብሎስ ቀስቱን ሲወረውርብንና በውጊያው ሲያውከን ይህ በእኛ ላይ ብቻ የተደረገ ቁጣና ጠላትነት አይደለም፤ ምክንያቱም እርሱ የእግዚአብሔርም ጠላት ነውና በእኛ ላይ ሚደርሰው መከራ በእግዚአብሔር ላይ የሚደረግ ተቃውሞ ነው። ዲያብሎስ እግዚአብሔርን ማጥቃት ባለመቻሉ ፍጥረታቱን በማታለልና ከእርሱ ከእርሱ ጋር ወደ ዘላለማዊ ቅጣት እንዲገቡ በማድረግ ሊበቀለው ይጥራል፡፡

የተወደድኸው ሆይ! ይህንን ነገር አስተውል! ዲያብሎስን ስትቃወመውና ስትዋጋው ክፉን ነገር ከእናንተ እያራቅህ ብቻ አይደለም፤ ለእግዚአብሔርም ክብር እየተዋጋህ ነው፡፡ ስለዚህም የክፉውን ዲያብሎስ ዲያብሎስ ማማለያና መደለያ በመቀበል እግዚአብሔርን ከማሳዘን ይልቅ ፈተናውን በጽናት ስትታገል በውጊያው ላይ ብትሞት ይሻልሃል፡፡

ለአፍታም ቢሆን ብቻህ እየተዋጋ እንዳለህ አድርገህ አታስብ፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር በጠላትህ ላይ ድል መንሣትን ይሰጥሃል፡፡ "አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ተነሥ እጅህም ከፍ ከፍ ትበል ድሆችን አትርሳ፡፡ ኃጢአተኛ ስለ ምን እግዚአብሔርን አስቆጣው? በልቡ:: አይመራመረኝም ይላልና፡፡" (መዝ ፲ ፥ ፲፪ -፲፫) ጥሩርና ጋሻ ያዝ፤ እኔንም ለመርዳት ተነሥ፡፡ ሰይፍህን ምዘዝ የሚያሳድዱኝንም መንገዳቸውን ዝጋ ነፍሴን፦ መድኃኒትሽ እኔ ነኝ በላት።›› (መዝ. ፴፭፥፪-፫)

"አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ፡፡ በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ  አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።" (ኢሳ. ፫፥፩-፪)

በነፍሳችን ላይ ደካማነትን እስካላየ ድረስ ሰይጣን አያጠቃንም፡፡ ጎበዝ አዳኝ ወፎችን ለማደን እንደሚያደርገው ዲያብሎስም ወጥመዱን ለማስገባት ሁልጊዜ ከእኛ ላይ ቀዳዳን ይፈልጋል፡፡ ብዙ ጊዜም ይዋጋናል፣ ይሸነግለናል በምኞቶቻችንም እየገባ ያገኘናል፡፡

አዳምን በሔዋን፣ ሶምሶንን በምወድደው ደሊላ፣ ንጉሥ ሰሎሞንን በእንግዶች ሴቶች ፍቅር፣ የአስቆሮቱ ይሁዳንም በገንዘብ ፍቅር እንደጣላቸው አላየህም፡፡ ስለዚህ እንደ ጎበዝ ሐኪም ሁን፣ ጉድለትህንና ሕመምህንም አክም፤ ኩራትህን በትሕትናና በየዋህነት ድል አድርገው፣ የትዕቢት በሽታህንም አንተነትህን በመናቅ ፈውሰው፡፡ በተአምራትና በታላቅ ነገሮችም ከመመካት ተጠበቅ ምክንያቱም ዲያብሎስ ራሱ በብርሃን መልአክ መመስል ይችላል፡፡ በስብ ውስጥ መርዙን ሊከት፣ በማጥመጃው ዘንግ ውስጥም የመደለያ ጣፋጭ ምግብን ሊያደርግና መልካምና ጠቃሚ ነገር ይከተላል ብለህ እንድታምን ሊያታልልህ ይችላል፡፡ አንተ ግን ፈጽሞ አትታለል፣ በከንቱም አትነዳ፡፡ ይልቅስ ከዲያብሎስ ጥቃት ትጠበቅ ዘንድ ሁሉን ነገር አስተውልና መርምር፡፡

ይሁዳ ጌታውን አልከዳምን? ኢዮአብስ ወዳጅና የሚታመን ሰው መስሎ አሜሳይን አልገደለውምን? (፪ነገ. ፳ ፥ ፱)

በእግዚአብሔር ታመን! ከመሪ በላይ አጥብቀህ ያዘው፤ ሁሉን ነገር ወደ እርሱ አምጣው፡፡ ድጋፍህና መጠጊያህ አድርገው፤ እርሱ ሁለንተናህ አድርገው።

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
​​ለምን ትቀናለህ?

በዜና አበው ላይ አጋንንት አንድን መነኩሴ ለማሰናከል ሲማከሩ የሚያሳይ ታሪክ ተጽፎአል፡፡ መነኩሴው ለብዙ ዘመናት በተጋድሎ አሳልፎ ከብቃት የደረሰ መናኝ ነበር፡፡ የአጋንንቱ ጭፍራ በአለቃቸው ተመርተው ይህንን መነኩሴ ለማሳት ዘመቱ፡፡ ተራ በተራ ወደ እርሱ እየሔዱ የፈተና ወጥመዳቸውን ዘረጉበት፡፡ በዝሙት ሊፈትኑት ሞከሩ፡፡ አልተሳካም፡፡ በምግብም ሞከሩ ድል ነሣቸው፡፡ የሚያውቁትን የፈተና ስልት በተለያየ መንገድ እየተገለጹ አንዴ ሰው አንዴ መልአክ እየመሰሉ ሊጥሉት ቢሞክሩም አልቻሉም፡፡

አለቃቸው ይኼን ጊዜ በሉ እኔ የማደርገውን ተመልከቱ አላቸውና መንገደኛ መስሎ ወደ መነኩሴው ቀረበ፡፡ በጆሮው የሆነ ነገር ነግሮት ወዲያው ተሰናብቶት ወጣ፡፡ ይህንን ጊዜ አጋንንቱ እያዩት መነኩሴው መንፈሳዊ ገጽታው ተገፍፎ ፊቱ በቁጣና በንዴት ሲለዋወጥ ተመለከቱት፡፡ በዚህም ተደንቀው ምን ብለህ ነው ያሸነፍከው? ብለው አለቃቸውን ጠየቁት፡፡ እርሱም እንዲህ አላቸው፦ ‘ከአንተ ጋር ያደገውና ከአንተ ጋር የተማረው ጓደኛህ እኮ የእስክንድርያ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ’ ብዬ ነገርኩትና ወጣሁ፡፡ አሁን ልቡ በቅናት እየነደደ ነው አላቸው፡፡ አጋንንቱ በደስታ ጨፈሩ፡፡

ሰይጣን የቅናትን ኃይል ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ መጽሐፈ ቅዳሴ ሞትን ሲገልጸው ‘በሰይጣን ቅናት ወደ ዓለም የገባ’ ይለዋል፡፡ ሰይጣን በሰው ልጅ ጸጋ ቀንቶ አዳምና ሔዋንን በፈጣሪያቸው እንዲቀኑና አምላክ መሆን እንዲመኙ አድርጎ ዓለምን ያመሰቃቀለ ነውና ይህንን መነኩሴ ለመጣል ለሺህ ዓመታት ብዙዎችን ወግቶ የጣለባትን ሰይፉን መዘዘበት፡፡ መነኩሴው የእኩያውን መሾም ሲሰማ ቅናቱን መቋቋም አቃተው::

ቅናት እጅግ ክፉ ኃጢአት ነው፡፡ ሰው ቢዘሙት ቢሰክር በሥጋው ነው:: ቅናት ግን በምታስተውል ነፍሱ ውስጥ የሚበቅል መርዝ ነው፡፡   ቃየልን በየዋህ ወንድሙ ላይ ያስጨከነው ቅናት ነበር፡፡ የአቤል ስኬት ለቃየል ውድቀት መስሎ ስለተሰማው በግፍ ሊገድለው በቃ፡፡

ዮሴፍ የለበሳት ቀለምዋ ብዙ የሆነ ጌጠኛ ቀሚስ በወንድሞቹ ዘንድ የመረረ ጥላቻን አትርፋለት ነበር፡፡ አንዱ አጊጦ አምሮ ሲታይ ቢሞትና ቢገላገሉት ደስ የሚላቸው የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ አሉ፡፡  

ዮሴፍም አርፎ አልተቀመጠም፡፡ እየሔደ ሕልሙን ይነግራቸው ነበር፡፡ ስለ ሕልሙም የበለጠ ጠሉት ይላል፡፡ ወዳጄ ሕልምህን ዝም ብለህ ለሰዎች አትዝራ፡፡ ሕልም ስልህ ተኝተህ የምታየውን ብቻ ማለቴ አይደለም፡፡ ራእይህን ፣ ተስፋህን ዕቅድህን ሲያውቁ የሚንገበገቡ የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ  አሉ፡፡ ፍቺው ባይገባቸውም ባልተፈታ ሕልም ይጠሉሃል፡፡ ምንም ነገር ሳታደርግ እንኳን "ለምን አለምከው?" ብለው ጥርስ ይነክሱብሃል፡፡ ዮሴፍ ግን ይኼ ስላልገባው ነገራቸው፡፡ ወዳጄ አንተም ሕልምህን እንደ ዮሴፍ በየዋህነት የምትዘራ ከሆንህ እንግዲህ የዮሴፍ አምላክ ይጠብቅህ፡፡

ቅናት እጅግ ከባድ ነው፡፡ እረኛው ዳዊት ጎልያድን የገደለ ዕለት የተዘፈነለት መዘዘኛ ዘፈንም ነበረ፡፡ ‘ሳኦል ሺህ ገደለ ዳዊት እልፍ ገደለ’ ብለው ዘፈኑለት፡፡ ይህች ዘፈን በሳኦል ጆሮ ስትደርስ ዳዊት ላይ ብዙ ጦር አስወረወረች፡፡ ሳኦሎች ሌላ ሰው ከእነርሱ በላይ ሲመሰገን የሰሙ ዕለት በቅናት ታውረው ገበታ ላይ ሳይቀር ሰይፍ ይመዛሉ፡፡

የጠፋው ልጅ ወንድምን አስበው፡፡ (ሉቃ 15:20) ወንድሙ ከጠፋበት ተመልሶ ደስታ ሲደረግ እርሱ ግን ከፍቶት ውጪ ቁጭ አለ፡፡ ወዳጄ ቅናት ከቤተ ክርስቲያንና ከእግዚአብሔር መንግሥት ያስወጣል፡፡ የሌላው ስኬት ካበሳጨህ እንደጠፋው ልጅ ወንድም ውጪ ቁጭ ብለህ አፈር እየጫርክ ‘እምቢየው አልገባም’ እያልክ እያልጎመጎምክ ትቀራለህ፡፡

ክርስቶስ ላይ አይሁድ ያቀረቡት ትችት ሁሉ ለሕግ ከመቆርቆር ሳይሆን ከቅናት ነበር፡፡ ጲላጦስ እንኳን ‘በቅናት አሳልፈው እንደሠጡት ያውቅ ነበር’ ይላል፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ቅናታቸውን በሌላ ነገር እንደ አይሁድ ሸፍነው ትችት ያቀርባሉ፡፡ ለእግዚአብሔር ሕግ እንደተቆረቆሩ ፣ ለሥርዓቱ እንዳዘኑ መስለው ውስጣቸው ያለውን ቅናትና ጥላቻ ያንጸባርቃሉ፡፡

የሰንበት መሻር ፣ ለቄሣር ግብር መከፈል ፣ የመቅደሱ በሦስት ቀን ፈርሶ መሠራት እንዳንገበገባቸው እርር እያሉ ቢናገሩም እውነታው ግን ቅናት ነው፡፡ ‘የቤትህ ቅናት በላኝ’ እንዳለው ጌታ በየዘመኑ የሰዎች ቅናት ብዙ ንጹሐንን ትበላለች፡፡

ወዳጄ በሌላው ትቀና እንደሆን አሁኑኑ ከዚህ ውስጥን በልቶ ከሚጨርስ ካንሰር ራስህን አድን፡፡

ራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር፡፡ በምድር ላይ እግዚአብሔር የፈጠረው አንተን የሚመስል ሌላ ሰው የለም፡፡ ካንተ ቀድሞም በትክክል አንተን የሆነ ሰው አልተፈጠረም ለወደፊትም አይፈጠርም፡፡ እግዚአብሔር ቀድሞ ያልሠራው ደግሞም የማይሠራው ምርጥ ዕቃው ነህና ራስህን ከሌላ ጋር አታወዳድር፡፡

ለአንተ ብቻ የሠጠው ጸጋ አለና ሌሎችን መመልከት ትተህ ውስጥህ ያለውን ውድ ማንነት ቆፍረህ አውጣ፡፡ ያንተ ሕይወት ቁልፍ የተቀበረው አንተው ውስጥ ነው፡፡ ሌሎችን ረስተህ ወደ ራስህ ጠልቀህ ግባ፡፡ መብለጥ ከፈለግህም አሁን ያለውን ራስህን ብለጠውና ሌላ ትልቅ አንተን ሁን፡፡ 

በቅናት እንዳትቃጠል ሌሎችን ሰዎችንም ውደዳቸው። ከወደድሃቸው ‘ፍቅር አይቀናም’ና የእነርሱ ስኬት የደስታህ ምንጭ ይሆናል፡፡ የቅናት ስሜት ሲሰማህም ‘ቀናተኛ ልቤን ፈውስልኝ’ ብለህ ለምነው፡፡

‘በአግባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን’ ሮሜ 13፡13
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
"ከእናንተ እያንዳንዱ በመጾሙ ያገኘውን ጥቅም ውስጡን (ሕሊናውን) ይጠይቅ ዘንድ እማልዳችኋለሁ፤ እማፀናችሁማለሁ! ብዙ ጥቅም እንዳገኘ ከተረዳ ይህን ያገኘው በመበርታቱ ምክንያት እንደ ኾነ ይቍጠር፡፡ ምንም ነገር ያላገኘ እንደ ኾነ ግን ቀሪውን ጊዜ ተግቶ በመጾም የንግድ ዕቃዎችን (መንፈሳዊ በቁዔትን) ለማግኘት ይጠቀምበት፡፡

ወርሐ ጾሙ እስከሚፈጸም ድረስ ባዶ እጃችንን እንዳንቀርና ታላቅ የኾነ ትርፍን እናግኝ ዘንድ ራሳችንን ልል ዘሊላን አናድርግ፡፡ በዚህ መንገድ የጾምን ዋጋ ልናጣ አይገባምና፡፡ እስከ አሁን ድረስ የጾሙን ድካም ታግሠናልና፡፡ የጾምን ድካም ታግሠው እያለ የጾምን ፍሬ ጻማ አለማግኘት አለና፡፡

ከምግበ ሥጋ ርቀን እያለ ከምግበ ኃጢአት ካልራቅን፣ ሥጋ የማንበላ ኾነን እያለ የድኾችን ቤት ተስገብግበን የምንበላ (የማንመጸውት) ከኾነ፣ ወይን ጠጥተን የማንሰክር ኾነን እያለ በክፉ መሻት የምንሰክር ከኾነ፣ ቀኑን ሙሉ በአፋችን እንጀራ የማያልፍ ኾኖ እያለ በምኞት ዓይን የምንቅበዘበዝ ከኾነ የጾምን ፍሬ አናገኝምና፡፡ የጾምን ድካም እየደከምን እያለ የዓመፀኞችን ተውኔት የምንመለከት ከኾነ የጾምን ዋጋ እንደማናገኝ ዕወቅ፤ ተረዳም፡፡"

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
#አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት (#ታኅሣሥ_24)

ታኅሣሥ ሃያ አራት በዚህች ዕለት ጌታችን በቃሉ ''ሐዲስ ሐዋርያ'' ብሎ የሾማቸው የኢትዮጵያ ብርሃኗ የሆኑ የደብረ ሊባኖሱ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ልደታቸው ነው፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ የመረጣቸው ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖት በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ጻድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› ማለትም ‹‹አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው›› በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነውታል፡፡ ወላጆቻቸውም ስማቸውን ፍሥሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ይኸውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡ የወላጆቻቸው የቀድሞ ስማቸው ዘርዐ ዮሐንስና ሣራ ይባል ነበር፡፡

ቅዱሳን አባቶቻችን እነ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና እነ አቡነ ዜና ማርቆስ ሌሎቹም እነ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ፣ አቡነ ሕፃን ሞዐ፣ አቡነ አኖሪዮስ(ትልቁ)፣ አቡነ ገላውዲዮስ፣ አቡነ ማትያስ ዘፈጠጋርና አቡነ ቀውስጦስ ዘመሐግል የትውልዳቸው መሠረት ኢያሱ ለሌዋውያን ክፍል ትሆን ዘንድ ከለያት ከኢየሩሳሌም ነው፡፡ ስማቸውን የጠቀስኳቸው እነዚህ ቅዱሳን አባቶቻችን የወንድማማቾች ልጆች ሲሆኑ ከአዳም ጀምሮ 61ኛ ትውልድ ናቸው፡፡ ይኸውም እንዴት ነው ቢሉ ትውልዱ ከአዳም ጀምሮ በካህኑ አሮን በኩል የሆነውና የሌዋዊያን ሊቀ ካህን የነበረው የሳዶቅ ልጅ አዛርያስ በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን ከታቦተ ጽዮንና ከብዙ ሌዋዊያን ካህናት ጋር ሊቀ ካህን ሆኖ ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ አክሱም ተቀምጦ ኖረ፡፡ የኦሪትንም ሕግ እየዞረ ለኢትዮጵያ ሰዎች አስተማረ፡፡ ትውልዱም በአብርሃ ወአጽብሓና በአባ ሰላማ ዘመን እስከነበረው እንበረም የሚባለው ጻድቅ ድረስ ደረሰ፡፡ የእንበረምም ትውልድ ደገኛው ሕይወት ብነ በጽዮን ድረስ ደረሰ፡፡ ሕይወት ብነ በጽዮንም የደማስቆ ምድር ከሚሏት ከወለቃ ሀገር የመኮንን ልጅ የሆነችውን ወለተ ሳውልን አግብቶ አበይድላን ወለደ፡፡ አበ ይድላም በንጉሡ ድልዓዥን ዘመነ መንግሥት ለ150 ካህናት አለቃ ሆኖ በወለቃ ሀገር የክርስቶስን የወንጌል ሕግ እያስተማረ ብዙዎችን አጠመቀ፡፡ እስከ ሸዋ ምድር ድረስ እያስተማረ መጥቶ በሸዋ ምድር ተቀመጠ፡፡ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትንም አሳነጸ፡፡ እጅግ አስደናቂ ተአምራትንም ያደርግ ነበር፡፡ ‹‹በሸዋ ጽላልሽ ተቀምጦ ሲያስተምርም በአንዲት ቀን እስከ ሁለት መቶ ሺህ ሕዝብ ያጠምቅ ነበር›› በማለት ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ይመሰክርለታል፡፡

አበይድላ በመጨረሻ በፈቃደ እግዚአብሔር ከሸዋ ጽላልሽ ምድረ ዞረሬ ሚስት አግቶ ሀበነ እግዚእን ወለደ፤ ሀበነ እግዚእም በኩረ ጽዮንን ወለደ፤ በኩረ ጽዮንም ሕዝበ ቀድስን ወለደ፤ እርሱም ነገደ እግዚእ የተባለ ነው፡፡ ሕዝበ ቀድስም ብርሃነ መስቀልን ወለደ፤ እርሱም ዐቃቢነ እግዚእ የተባለ ነው፡፡ ብርሃነ መስቀልም ሕይወት ብነን ወለደ፤ እርሱም ሴትን ወለደ፡፡ ሴትም ወረደ ምሕረትን ወለደ፡፡ ወረደ ምሕረትም ዘካርያስን ወለደ፡፡ ዘካርያስም የእነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አባት የሆኑ 6 ወንድማማች ልጆችን ወለደ፡፡ እነርሱም እንድርያስ፣ አርከሌድስ፣ ዘርዐ አብርሃም፣ ዘርዐ ዮሐንስ ወይም ጸጋ ዘአብ፣ ቀሲስ ዮሐንስና ቀሲስ ዮናስ ናቸው፡፡ እንድርያስም ሳሙኤል ዘወገግን ወለደ፤ አርከሌድስም ሕፃን ሞዐን ወለደ፤ ዘርዐ አብርሃምም ታላቁን አኖርዮስን ወለደ፤ ዘርዐ ዮሐንስ ወይም ጸጋ ዘአብም ተክለ ሃይማኖትን ወለደ፤ ቀሲስ ዮሐንስም ዜና ማርቆስን ወለደ፣ ቀሲስ ዮናስ ደግሞ የፈጠጋሩን ማትያስንና ገላውዲዮስን ወለዳቸው፡፡ ገላውዲዮስም የመሐግሉ ቀውስጦስን ወለደ፡፡ እነዚህ ደጋግ ቅዱሳን በእናታቸውም በኩል እንዲሁ በዝምድና የተሳሰሩ ናቸው፡፡ ማቴዎስ የተባለው ደገኛ ክርስቲያን የሸዋ ገዥ የነበረ ሲሆን አንድ ወንድ ልጅ መድኃኒነ እግዚእንና ሦስት ሴቶች ልጆችን ወለደ፡፡ ሶስቱ ሴቶች ልጆችም እምነ ጽዮን፣ ትቤ ጽዮንና ክርስቶስ ዘመዳ ይባላሉ፡፡ ሦስቱ እኅትማማቾችም ደጋጎቹን አባቶቻችንን ወለዱልን፡፡ እምነ ጽዮን የእነ ዜና ማርቆስን እናት ማርያም ዘመዳንና ወለደች፡፡ ትቤ ጽዮንም ሕፃን ሞዐን ወለደች፡፡ ክርስቶስ ዘመዳ ደግሞ ታላቁን አኖሬዎስን ወለደች፡፡ የፈጠጋሩ ገዥ መድኃኒነ እግዚእ ደግሞ የተክለ ሃይማኖትን እናት እግዚእ ኀረያን ወይም በሌላ ስሟ ሣራን ወለደ፡፡

አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከልጅነታቸው ጀምሮ በወላጅ አባታቸው በካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ግብረ ዲቁናን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያጠኑ ቆይተው በ15 እና በ22 ዓመታቸው ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ከአቡነ ቄርሎስ (ጌርሎስ) ዲቁናንና ቅስናን ተቀብለዋል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ቅድስት ቤተክርስቲያንን በወጣትነት ዕድሜያቸው ያገለግሉ እንደነበር በዚህ ይታወቀል፡፡

ከዕለታት በአንዱ ቀን አባታችን ከጓደኞቻቸው ጋር ለአደን ወደ ዱር ሄደው ሳለ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ታያቸው፡፡ ቅዱስ አባታችንም ‹‹እንደዚህ ባለ ገናንነት የማይህ ጌታዬ ማነህ?›› ባሉት ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ‹‹ዘወትር የምጠብቅህ ካንተ የማልለይ እናትህንና አባትህንም ስላንተ ከውኃ ስጥመትና ከምርኮ ያዳንኳቸው እኔ ሚካኤል ነኝ፡፡ ከእንግዲህ አውሬ አዳኝ አትሁን፤ ሰውን ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ ሰውን በትምህርት የምታድን ሁን እንጂ፡፡ እነሆ እግዚአብሔር ጽኑዕ ሥልጣን ሰጥቶሃልና፤ ሙት ታስነሣለህ፤ ድውያንን ትፈውሳለህ፤ አጋንንትም አንተን በመፍራት ይሸሻሉ፡፡ ስምህ ፍሥሐ ጽዮን አይሁን፤ ተክለ ሃይማኖት ይሁን እንጂ፡፡ ትርጓሜውም ተክለ አብ፥ ተክለ ወልድ፥ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው›› አላቸው፡፡

ቅዱስ ሚካኤል ይህን ሲነግራቸው ጌታችን በሥጋ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር እንደነበር ሆኖ መልከ መልካም ጎልማሳ መስሎ ታያቸው፡፡ ጌታችንም ‹‹ወዳጄ እንዴት ሰነበትክ? ቸር አለህን?›› አላቸው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ‹‹ጌታዬ ሆይ አንተ ማነህ?›› ብለው ሲጠይቁት ጌታችንም ‹‹እኔ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ነኝ፤ በናትህ ማኅፀን ፈጥሬህ ያከበርኩህ እኔ ነኝ፡፡ በተወለድክ በሦስተኛው ቀን አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብለህ ታመሰግነኝ ዘንድ የምስጋና ሀብት ያሳደርኩብህ እኔ ነኝ፡፡ በርሃብ ዘመን በቤት የሚያሻው ምግብ ሁሉ ቅቤው፣ የስንዴው ዱቄት በእናት በአባትህ ቤት ይመላ ዘንድ በእጅህ ሀብተ በረከት ያሳደርኩብህ እኔ ነኝ፡፡ ያንን ሰው አንተን በተጣላ ጊዜ በነፋስ አውታር የሰቀለኩት በመዓት ጨንገር የገረፍኩት እኔ ነኝ፡፡ ውኃ ጠምቶህ በለመንከኝ ጊዜ ከደረቅ መሬት የጣፈጠ ውኃ ያመነጨሁልህ እኔ ነኝ፡፡ ከልጅነትህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ ተአምራት እያደረግሁ በአንተ እጅ የታመሙትን ያዳንኳቸው እኔ ነኝ፡፡ ወደፊትም አደርግልሃለሁ›› አላቸው፡፡ ይህንን ብሎ በእጆቹ ባረካቸውና ‹‹ንሣእ መንፈስ ቅዱስ›› ብሎ የሹመትን ሀብት አሳደረባቸው፡፡ ዳግመኛም ‹‹በምድር ያሰርከው በሰማይ የታሰረ ይሁን፤ በምድርም የፈታኸው በሰማይ የተፈታ ይሁን፤ አንተን የሰማ እኔን መስማቱ ነው፤ የላከኝ አባቴንም መስማቱ ነው፡፡ አንተን እንቢ ያለ እኔን እንቢ ማለቱ ነው፡፡ የላከኝ አባቴንም እንቢ ማለቱ ነው፡፡ ይህን ሥልጣን ቀድሞ ለሐዋርያት ሰጥቻቸው ነበር፡፡ ከሐዋርያትም ሹመትን የተቀበለ ጳጳሱ ትሾምና ትሽር፣
ትተክልና ትነቅል ዘንድ ሥልጣንን ሰጠህ፡፡ ይህንንም ያደረኩልህ የጳጳሱን ቃል በመናቅ አይደለም፡፡ የፍቅሬን ጽናት ባንተ እገልጽ ዘንድ ነው እንጂ፡፡ ሐዋርያት ወዳልደረሱበት ሕዝብ በመምህርነት እልክህ ዘንድ በሚካኤል ቃል አዲስ ስም አወጣሁልህ፡፡ አንተም በማናቸውም ሥራ ከእነርሱ አታንስም፣ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጌሃለሁና፡፡ ሰውን ሁሉ በእኔ ስም እያስተማርክ ታሳምን ዘንድ፣ ሚካኤልም ባሰብከው ሥራ ሁሉ ረዳት ይሁንህ፣ ሁል ጊዜ ካንተ አይለይም፤ በምትሄድበትም ጎዳና ሁሉ እርሱ መሪ ይሁንህ፤ እኔም ባለ ዘመንህ ሁሉ አልለይህም›› ካላቸው በኋላ ሰላምታ ሰጥቷቸው ዐረገ፡፡

ብፁዕ አባታችንም እጅ ነሥተው ‹‹ለእኔ ለኀጥኡ የማይገባኝ ሲሆን ይህን ሁሉ ጸጋ የጠኸኝ ስምህ በሰማይ በምድር የተመሰገነ ይሁን›› አሉ፡፡ ከዚያች ቀን ጀምሮ ሀብተ ኃይልን የተመሉ ሆኑ፡፡ ወደቤታቸው ተመልሰው ያላቸውን ሀብት ንብረት ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን፣ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች ሰጥተው ጨረሱ፡፡ ከዚያም ‹‹አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የመንግሥተ ሰማያትን በር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደተከፈተ ተውኩልህ›› ብለው ቤታቸውን እንደተከፈተ ትተው ወንጌልን ለማስተማር ወጡ፡፡ ጻድቁ አባታችን በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ሕዝቡን ከኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ፣ ከክህደት ወደ ኃይማኖት ስለመለሱት በዚህም የተነሣ ለኢትዮጵያውያን ብርሃን ተብለዋል፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
"ልጆቼ! የሚያሳፍር ነገር፣ የስንፍና ንግግር ወይም ዋዛ ፈዛዛ የማይገቡ ናቸውና በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድ ከቶ አይሰሙ፡፡ እስኪ ንገሩኝ! የዋዛ ፈዛዛ ንግግር ጥቅሙ ምንድን ነው? እስኪ ንገሩኝ፤ አንድ ጫማ ሰፊ፣ ጫማ እየሰፋ በአንድ ጊዜ ሌላ ሥራ መሥራት ይችላልን? አይችልም፡፡ ከዋዛ ፈዛዛ የሚያሳፍር ንግግር ይወለዳል፡፡ የአሁኑ ጊዜ ደግሞ ለእኛ ለክርስቲያኖች ዋዛ ፈዛዛ የምንናገርበት ሳይኾን የንስሐችን ጊዜ ነው፡፡ እስኪ አሁንም ልጠይቃችሁና እናንተም መልሱልኝ! አንድ ቦክስ የሚጫወት ሰው ውድድሩን ችላ ብሎ ዋዛ ፈዛዛን ይናገራልን? እንዲህ የሚያደርግ ከኾነስ በተጋጣሚው በቀላሉ የሚሸነፍ አይደለምን? ታዲያ ባለጋራችን ዲያብሎስ‘ኮ የሚውጠውን ፈልጐ እንደሚያገሣ አንበሳ በዙርያችን ቁሟል፡፡ ጥርሱን እያንቀጫቀጨብን ነው፡፡ እኛን የሚጥልበት ወጥመድ በማዘጋጀት ላይ ነው፡፡ የደኅንነታችን መንገድ ላይ እሳት እየተነፈሰ ነው፡፡ ታዲያ ዲያብሎስ እንዲህ እኛን ለመጣል ሲተጋ እኛ ዋዛ ፈዛዛን፣ የሚያሳፍር ነገርን፣ የስንፍናንም ንግግር ስንናገር ቁጭ ልንል ይገባናልን?

የምወዳችሁ ልጆቼ! ጊዜው የምንተኛበት ጊዜ አይደለም፡፡ የተጋድሎ ጊዜ ነው እንጂ፡፡ ቅዱሳን ጊዜያቸውን እንደ ምን እንደሚያሳልፉት ማወቅ ትፈልጋላችሁን? እስኪ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስን አብረን እንስማው፤ እንዲህ ያለውን፡- “ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ”፤ … “በብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት በብዙም እንባ ጽፌላችኋለሁ…”፡፡ … “የሚደክም ማን ነው፤ እኔ አልደክምምን? የሚሰናከል ማን ነው፤ እኔም አልናደድምን?”፤ “… በድንኳኑ ያለን እኛ ከብዶን እንቃትታለን”፡፡ ታዲያ እነ ቅዱስ ጳውሎስ ጊዜያቸውን እንዲህ ካሳለፉ፣ ኃጥአን የምንኾን እኛ ጊዜያችንን በሳቅና ስላቅ ልናጠፋ ይገባናልን? በክርስቶስ ፍቅር የማፈቅራችሁ ልጆቼ! በንግግሬ አትማረሩ፡፡

ጊዜው የተጋድሎ ጊዜ ነው፤ ታዲያ ስለ ምንድን ነው የዘፋኞችን መሣርያ አንሥተን ከዓለም ጋር የምንዘፍነው? በጦር ግንባር ያለ ወታደር ከጠላት ሊመጣ የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል ከመዘጋጀት ይልቅ ጊዜውን በዋዛ ፈዛዛ ያጠፋልን? አያጠፋም፡፡ ታዲያ እኛም‘ኮ የክርስቶስ በጎ ወታደሮች ነን፡፡ ..."
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
አጉል ልማዶችን ተዉ

አጉል ልማዶችን ከሥር ጀምሮ ወላጆች ያስጥሉናል። ቀጥሎ መምህራን ያስተዉናል። መጻሕፍትም እንደ ሸለፈት የሆነውን ፣ ውበትና ጤንነትን የሚጎዳውን ክፉ ልማድ እንድንተው ያግዙናል። የሰው ልጅ በሕይወት እስካለ ድረስ ለማወቅና ለንስሐ ጊዜው አይረፍድበትም። አጉል ልማድ ባለማወቅ ምክንያት ፣ ሥነ ሥርዓትን ባለመማር ፣ ልቅ በሆነ ባሕል ውስጥ በማደግ ፣ ሥልጣኔ በሚመስል ዘላንነት በመያዝ ሊመጣ ይችላል። አጉል ልማዶች እጅግ ብዙ ሲሆኑ ሁሉንም መንቀስ አይቻለንም። አጉል ልማዶች ትንሽ የሚመስሉ ትልቅ ጥፋት የሚያስከትሉ ናቸው። አጉል ልማድ ውስጥ ካለን ከሰዎች ጋር እንጋጫለን። ሰዎች ባይጋጩንም ለእኛ ያላቸው ክብር ይቀንሳል። አንዳንድ ሰዎች ሊነግሩን ይችላሉ። የሚበዙት ግን እየታዘቡ ዝም ይሉናል። በአፍ መፍረድ ፣ በልብ መታዘብ ሁለቱም አንድ ዓይነት ኃጢአት ቢሆንም ሰዎች ታዝበው ዝም ይሉናል። መመከርን መቋቋም የማንችል ፣ ግን ብዙ ግድፈት ያለብን ሰዎች ልንሆን እንችላለን። በዚህ ምክንያት የበለጠ እኛን ላለማጣት ዝም የሚሉን ይበዛሉ።

መኝታ አታብዛ። ገንዘብ እየፈለግህ መኝታ እያበዛህ አይሆንም። አንተ እንድትተኛ የተጉልህ ሰዎች ይኖራሉ። ነገር ግን እነርሱ ጊዜያዊ እንጂ ዘላለማዊ በረከቶችህ አይደሉምና እልፍ ይላሉ። ያን ቀን በራስህ መቆም ያቅትሃል። የራስህ ሕይወት ስለሌለህ የእነርሱ ህልውና ሲያበቃ ያንተም ያበቃል። ወረተኛ አትሁን። ሸሚዝ እንጂ ሰው አይቀያየርም። ቶሎ ስልቹ ሆነህ መልሰህ እገሌን አታሳዩኝ ፣ አታሰሙኝ አትበል ። ሰው ብዙ ነው ፣ ሰው ጥቂት ነው። ካከበርከው ሰው ብዙ ነው። ከናቅኸው ግን ሰው ጥቂት ነውና አንድ ሰውም ታጣለህ። ወሬ አታጣጥም። “ፐ ፣ ይገርማል ፣ እስኪ ንገረኝ” እያልህ የወሬ ሱስህን አትወጣ። አንዳንዱን ነገር ባትሰማው የተሻለ ነው። ፊት ለፊት ልትነግረው የፈራኸውን ሰው ከኋላው አትማው። ስታወራ ከንፈርህን እየመጠጥህ ፣ ግንባርህን እያሸህ አታውራ። ስትሰብክ አትወራጭ ፣ ከቦታ ቦታ አትፍለስ። እጅህን አታወናጭፍ። ሰዎች በግልህ የነገሩህን ራሳቸው ያውሩ እንጂ ስማቸውን ጠርተህ በአደባባይ አታውራ።

ምግብ ስትመገብ በመጠኑ ጥቅልል እንጂ ሰሐኑን እንደሚወስዱበት ሰው ከልክ በላይ አትጠቅልል። ጥቂት በጥቂት መጉረስ ክብር ነው። ስትበላም አፍህን ገጥመህ ብላ እንጂ ስታላምጥ አጠገብህ ያለ ሰው መስማት የለበትም። በትልቅ ማዕረግ ላይ ያለህ ከሆንህ በአደባባይ ምግብ አትብላ። ጳጳሳት በአደባባይ ባይመገቡ ይመከራል። ወደ ድግስ ስትጠራ በልተህ ሂድ። በምንም መንገድ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጣ። ጠላት ያለበት ሰው በሴት ፣ በሆዱና በአልኮል መጠጥ ያጠምዱታልና ተጠንቀቅ። ሰዎችን ስታወራና ስታናገር ፊት ለፊት እያየሃቸው ተነጋገር። አፍረህ አንገትህን መቅበር ፣ እንደ ተንኮለኛም ግንባርህን አቀርቅረህ በዓይንህ ግልባጭ ሰውን ማየት በጣም ነውር ነው። ሰው አፍ ውስጥ የምትገባ እስክትመስልም አፍጥጠህ አታነጋግር። ሰዎቹን ራሳቸውን ተመልከት እንጂ የለበሱት ልብስ ፣ ያደረጉት ጫማ ላይ ዓይንህን አትላከው። እንደ ውሻም እግር እግር አትመልከት። ዜማ ስታዜም ፣ መዝሙር ስትዘምር የላይኛውንም የሥረኛውንም ጥርስህን አታሳይ። ጥርሱን የሚያሳይ የሞተና የረገፈ አጽም ብቻ ነው። እቤትህ ሳትጨርስ ደጅ ላይ ወጥተህ ቀበቶህን መፍታትና መዝጋት ነውር ነው። በሰው ላይ ማዛጋት ፣ ሰው ፊት መሐረብ ሳይሸፍኑ ማሳልና ማስነጠስ ተገቢ አይደለም።  ቀጠሮ አክብር። ሁለት ጊዜ ደውለህ ስልክ ያላነሣልህ ሰው ጋ መደወል አቁም።

ሰዎችን ሰላም ብለህ ከሸኘህ በኋላ ዞር ብለህ አትመልከታቸው። ጀርባን የሚያይ ጠላት ነውና ። ከሰዎች ጋር ሆነህ ስልክህን አትጎርጉር። ከተከበረ ሰው ፊት እግርህን አጣምረህ አትቀመጥ። ታላቅህ ሲመጣ ከመቀመጫህ ተነሥተህ ተቀበለው። ሲደወልልህ ስልክህን አንሣ። ማንሣት የማትፈልግ ከሆነ ጉዳዩን ገልጸህ እንዳይደውሉ አድርግ። ሰዎችን በገዛ ስህተታቸው ይቅርታ አትጠይቅ። ይህ እውነትን የሚቀብር ፣ መለማመጥን የሚያሰፍን ነው። ደግሞም ስህተታቸውን እንዳያዩ አስተዋጽኦ ታደርጋለህ። ካልተገራ ሰው ጋር ቀልድ አትቀልድ። ባለጌ ሥራውን አይረሳምና ለመደ ብለህ በርህን አትክፈትለት። ለሰዎች ቀጠሮ ስትሰጥ ጉዳዩንም አብረህ ንገራቸው። “እፈልግሃለሁ ብርቱ ጉዳይ አለ ፣ አሁን አልነግርህም” እያልህ የሰውን ሰላም አትንሣ። የማትጨርሰውን ወሬ አትጀምር። “ይህ ለምን ሆነ ?” አትበል ፤ እንዲህ እንዲሆን እኔ ምን አጥፍቻለሁ ? ብለህ ታረም ። የማምሸት ልማድህን ተው። በጊዜ መተኛትን ልመድ። ሰዎች ሲናገሩ አታቋርጣቸው። እኔ ብቻ ልናገር አትበል። ሁሉን እንደምታውቅ ከተሰማህ ታመሃልና እርዳታ ያስፈልግሃል። ምንም ብትቀራረብ ባለሥልጣንን በአደባባይ አንተ ብለህ አትጥራ። የጎሣና የቋንቋ ትችት ያለበት ወሬ አትጀምር። ያየኸውን የሰው ገመና ለሌላው አትናገር። ይህ የጸሎት እንጂ የወሬ ርእስ አይደለምና። መጓዝ ያለብህ ሰዎች እስከፈቀዱልህ ድረስ ብቻ ነው። ያልተፈቀደልህን መስመር ስታልፍ የተፈቀደውንም ታጣለህ።

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
ስለታሙ የሐሜት ጥርስህ የሚያርፈው በወንድምህ ሥጋ ላይ ሳይሆን ነፍስ ላይ ነው። በዚህም ጥርስህ ወንድምህን በእጅጉ ትጎዳዋለህ፡፡ እንዲህ በማድረግህ አንተም እርሱንም ሌሎችንም ብዙ ሺህ ጊዜ ትጎዳቸዋለህ፡፡

በሐሜትህ አንተን የሚሰማህ ባልንጀራህ የሐሜት ተባባሪ ይሆናል፡፡ በዚህም ምክንያት እርሱንም በደለኛ ታደርገዋለህ፡፡ እርሱም በእርሱ ላይ ከነገሠበት ኃጢአት የተነሣ ለሌላ ለወዳጁ ምን መርጦ ማውራት እንዳለበት ሳያውቅ ከሐሜተኞች ጎራ ይቀላቀላል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰው ጻድቅ ልንለው እንችላለንን? እንዲህ ዓይነት ሰው በመጦሙ ትልቅ የጽድቅ ሥራን እንደፈጸመ ቆጥሮ ይኩራራል፡፡ ሰዎችን ወደ ኃጢአት እየመራ ትልቅ ሥራን እንደሠራ ሰው ራሱን በከንቱ ያስኮፍሳል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ሊታይ የሚገባው ትልቁ ቁም ነገር ስለቤተክርስቲያን ጥቅም ሲባል የእንዲህ ዓይነቱን ሰው ንግግር ከመስማት መከልከል እንደሚገባ ነው፡፡ ምክንያቱም የዚህ ሐሜተኛ ወሬ እርሱን ብቻ ኃጢአተኛ የሚያሰኝ ጉዳይ ሳይሆን ቤተክርስቲያንንም ጭምር የሚያሰድብ ነውና፡፡

ስለዚህ በጦም ሰዓታችሁ ጊዜም ይሁን አይሁን ሦስት ነገሮችን በሕሊናችሁ ትይዙ ዘንድ እመክራችኋለሁ፡-
እነርሱም....
➛ ክፉ ከመናገር መከልከልን፣
➛ ማንንም ሰው እንደጠላት ከማየት መቆጠብንና
➛ እንደልምድ አድርጋችሁ ከያዛችሁት መሐላ ትርቁ ዘንድ እመክራቸኋለሁ፡፡"
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
የአዳም ተስፋ

የበደለ አዳም ቀና ብሎ ይሄድ ዘንድ ዳግማዊ አዳም ሁኖ መጣ ፣ የስህተት በር የሆነችዋን ሔዋንን ያጽናና ዘንድ ክርስቶስ በተዘጋ ማኅፀን ከሴት ዘር ተወለደ። ገነትን ላጣው አዳም ራሱ ክርስቶስ ገነት ሆኖለት መጣ። ስጦታውን ቢያጣ ሰጪው ዘመዱ ሆነ። ስጦታው የተፈጠረ ነው ፣ ሰጪው ግን ያልተፈጠረ ነው። አዳም ሰማይና ምድር የእርሱ ቢሆኑ ያለ ጌታ ኀዘን እንጂ ደስታ አይሆኑትም ነበር። አዳም የሰማይና የምድር ጌታ ለመሆን አስቦ ከሰይጣን ጋር መከረ ፣ እንኳን ሰማይን ሊያተርፍ ግዛቱ የሆነችውን ምድር አጣ። ክርስቶስ ግን በመወለዱ የሚታየውን ብቻ ሳይሆን የማይታየውን ዓለመ መንፈስ ፣ ሰይጣንንና ደዌያትን ይገዛ ዘንድ ባለሥልጣን ሆነ። ተጠቃን የሚሉ ወንድ ልጅ  ሲወልዱ ስሙን ደምመላሽ ይሉታል። ክርስቶስም ርስትን ይመልስልን ዘንድ ፣ ጠላትንም ይበቀል ዘንድ ወንድ ልጅ ሆኖ ተወለደ። ክርስቶስ በወንድ አምሳል ስለ መጣ ወንድ ልጅ ክቡር ነው። ክርስቶስ ከሴት ዘር በመወለዱ ከድንግል ማርያም የተነሣ ሴት ሁሉ ክብርት ናት። የሄደችውን ገነት አዳም በዕንባ ፣ አበው በምግባር ፣ ካህናት በመሥዋዕት ፣ ነቢያት በናፍቆት ሊያስመልሷት አልቻሉም። ክርስቶስ ግን በመወለዱ የሰማይ በር ተከፈተ። አዳም በወደቀ ቀን አጋንንት ዘፍነዋል ፣ ክርስቶስ በተወለደ ቀን መላእክት ዘመሩ። ዛሬም በክርስቶስ ልደት የሚዘፍኑ ፣ የሚሰክሩ በአዳም የውድቀት ቀን ከተደሰቱ አጋንንት ጋር ይተባበራሉ። አዳም ሳይወልድ በመበደሉ አንድ ራሴን ነኝ ብሎ ተመክቶ ነበር። ነገር ግን የአባት ዕዳ ለልጅ ይተርፋልና ልጆቹ በደለኛ ሆኑ ። በአንዱ አዳም የተኰነኑ ፣ በአንዱ ክርስቶስ ጻድቃን እንዲሆኑ ፣ ሚዛንም እንዲተካከል ይህ ሆነ።

አዳም በገደል ላይ በመጫወቱ ከጥልቁ ወደቀ። ነገሥታትና ጠቢባን ከገደል ሊያወጡት አልተቻላቸውም። ምድራዊ ሥልጣን ማዕሠረ ኃጢአትን ሊበጥስ ፣ ምድራዊ ጥበብም መቃብርን ሊበዘብዝ አልቻለም። ክርስቶስ ግን ጠቢብ ድሀ ሆኖ መጣ። ጌትነትን ተመኝቶ የሞተው አዳምን፣ ክርስቶስ ክብርን ንቆ ሊታደገው መጣ። የከፍታው ምሥጢር ዝቅታ መሆኑን ሊያስተምረው ክርስቶስ በበረት ተወለደ። ሔዋን ደመኛው ሆና ብትታየው ፣ በእርስዋ ላይ ቢነሣሣባት የመዳኛውን ዘር ያጣው ነበረ። አዳም ይቅርታ በማድረጉ ክርስቶስን አገኘ። ከክርስቶስ የለዩን አንድ ዘመን ላይ ወደ ክርስቶስ ያቀርቡናል። እግዚአብሔር ታሪክን ሲለውጥ ከበደሉን በላይ ይክሱናል። ከቆሸሸው በላይ የሚያጸዳ ባለሙያ አለ። ትልቁ ባለሙያ እግዚአብሔር ምድራዊት ገነትን ላጣው አዳም ሰማያዊ ርስትን ሰጠ። በልጅነት ላይ ክህነትን ደረበለት። መበቀል የፍጡር ጠባይ ነው። እግዚአብሔር ግን ኃይሉን በይቅርታ ገለጠ። ይቅር የሚሉ የሁልጊዜ ብርቱዎች ናቸው። መግደል ብዙዎች ችለዋል ፣ ይቅር ማለት ግን አልቻሉም። ይቅርታ የልዕልና መገለጫ ነው። አባቶችን ከተቀየምን መጀመሪያ የምንቀየመው አዳምን ነው። አዳም የወደቀባትን ቦታ ሳይሆን የተነሣባትን ጎልጎታ እናስታውሳለን።

አዳም ገነትን በራሱ አጣ ፣ በክርስቶስ እንደሚያገኛት ተስፋ አደረገ። ሰው ተስፋ ሰጥቶ ይጸጸታል። እግዚአብሐር ግን ተስፋን እንደ ክብሩ እንጂ እንደ ዕዳ አያየውም። አዳም መውደቅ በቻለበት አቅም መነሣት አልቻለም። ያለ መካሪ የበደሉ ሰዎች በመካሪ ኃይል ሊነሡ ይቸገራሉ። ሰውን ከኃጢአት የሚያላቅቀው ነጻ ፈቃዱ ከኃይለ መንፈስ ቅዱስ ጋር ሲዛመድ ነው። አዳም በሰማይና በምድር ብቸኛ ሆነ። ጥቂት ዘመን በደስታ ኖሮ 5500 ዘመን በስቃይ አሳለፈ። አዳም አባት እናት አልነበረውም ፣ አባትና እናቱ እግዚአብሔር ነበረ። አዳም ሙሉ ስሙ ሲጠራ “አዳም ወልደ እግዚአብሔር በጸጋ” ይባል ነበረ። አባትና እናትህን አክብር የሚለውን ትእዛዝ አዳም ሻረ። አዳም በገነት ውስጥ አነጋጋሪው ፣ የብቸኝነቱ መድኃኒት እግዚአብሔር ነበረ። አሁን ግን ወዳጁን አጣ። እግዚአብሔርም በወዳጁ ቤት ቆሰለ። ክርስቶስ ሰው የሆነው ለአዳም ያለውን ፍቅር ለመግለጥ ፣ የወጣ እንደ ወጣ ይቅር የማይል አምላክ መሆኑን ለማስታወቅ ነው።

አዳም የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ ሁኖ ተፈጠረ። ክርስቶስ ግን ሊያድነው የዕለት ሕፃን ሆኖ በበረት ተጣለ። አዳም በገነት ብቻውን ነበረ እንጂ ብቸኛ አልነበረም። ምክንያቱም እግዚአብሔር ያለው ብቸኛ አይባልምና። አሁን ሔዋን አጠገቡ ሳለች ብቸኝነት ተሰማው። ብቸኝነት ያለ ሰው ሳይሆን ያለ እግዚአብሔር መሆን ነው። አዳም ተስፋው የክርስቶስ መወለድ ነበረ። ይኸው ተወለደ። እርሱ አሻግሮ መወለዱን አየ ፣ እኛ መለስ ብለን መወለዱን አስተዋልን። ዕለት ዕለት ክርስቶስ መወለዱን የሚያምኑ ጥሙቃን /ተጠማቂዎች በቤተ ክርስቲያን ይገኛሉ። የእኛ አምላክ አብ የሚወልድ ፣ የእኛ ጌታ ክርስቶስ የሚወለድ ነው። ሰው በመሆኑ አምላክነቱን አልከሰረም። ጌታቸው ባለበት መላእክቱ ተገኝተው ምስጋናውን አቀረቡለት። የዘላለም አባት ፣ በሕፃን መልክ ሲገኝ በመደመም ዝም አሉ። ቅዱስ ገብርኤል ምን ቢያበስር ይህን የልደት ምሥጢር መልመድ አልቻለም። እኔ ደሃው ከመላእክት አእምሮ በላይ ለሆነው ልደትህ ክርስቶስ ሆይ ሰላም እላለሁ!

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
የአበው ተስፋ ተወለደ

አበው መንገዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር አደረጉ። በጽድቃቸው እንኳን ሌላውን ራሳቸውንም ማዳን ባልቻሉ ጊዜ የክርስቶስን መወለድ ናፈቁ። አዳም ገነትን አጥቶ ተስፋን ይዞ ወጣ። ከነበረችው ገነት ይልቅ ፣ የገነት ጌታ የእርሱ ልጅ እንደሚሆን በሰማ ጊዜ ልቡ በደስታ ዘለለ። ውድቀቱ ያመጣው መዳን ቢሆን ኖሮ እንኳን ወደቅሁ ባለ ነበር ፣ ለወደቀ ሰው የሚሆን ፍቅር ያለው አምላክ ግን አዳምን ከበደሉ በላይ ካሣ ሰጠው። ተስፋ የሚነገረው/የሚሰጠው በእግዚአብሔር ደግነት ፣ የሚፈጸመውም በእግዚአብሔር ታማኝነት ነው። አበውም ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚቀባበሉት ዕንቈ ነበራቸው ፤ እርሱም ክርስቶስ ይወለዳል የሚል ነው። የከፋውና ሁሉ የተነባበረበት ሕፃን “ቆይ አባቴ ይምጣ” እያለ እያለቀሰ ይስቃል። አባቱ እንባውን ያብስለታል ፣ ጠላቶቹን ያሸንፍለታል ። አበውም የክርስቶስን መወለድ ባሰቡ ጊዜ እያለቀሱ ሳቁ።

ጨርሶ እንዳይጨልም ለማታው ክፍለ ጊዜ ጨረቃና ከዋክብትን ያስቀመጠ እግዚአብሔር ፣ የሰው ልጅም በኃጢአት ፣ በመቃብርና በሲኦል ተጨንቆ እንዳይኖር ልደተ ክርስቶስን ተስፋ አድርጎ ሰጠ። አንድ ወንድ ልጅ ይወለዳል እየተባለ ለዘመናት ተስፋ ተደረገ። ያ ልጅ ከተወለደ በኋላም ዳግም ይመጣል እየተባለ ይሰበካል። ከገነት እስከ ምጽአት ፣ ከውድቀት እስከ ፍርድ ቀን የክርስቶስ መምጣት የሰው ልጆች ተስፋ ነው። ይህች ዓለም ያለ ክርስቶስ አድራ አታውቅም። የመጣውና የሚመጣ ጌታ አለን። በመጀመሪያ ምጽአቱ አዳነን ፣ በዳግም ምጽአቱ ይፈርድልናል። በመጀመሪያ ምጽአቱ ከሲኦል ወደ ገነት አፈለሰን ፣ በዳግም ምጽአቱ ከገነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ያፈልሰናል። ከክብር ወደ ክብር እንሻገራለን። በመጀመሪያው ምጽአቱ አጋንንት አፈሩ ፣ በዳግም ምጽአቱ የናቀን ዓለም ያፍራል። በመጀመሪያው ምጽአቱ ሞት ተገደበ ፣ በዳግም ምጽአቱ መከራ ይገደባል።

አብርሃም አገሩና ተስፋው ሩቅ ነበረ። ክርስቶስ ወደሚወለድበት ምድር ተጠራ። ዕድሜው እየመሸ ቢሆንም ሠርኩን ማለዳ የሚያደርገው ፣ በሞት ላይ ልደት የሚያውጀው እግዚአብሔር በመልካም አሰበው። ለሞት ሲሰናዳ ለሕይወት ተጠራ ። ሌጣውን ሊሞት መሆኑን አምኖ ከተስፋ ጋር ሊቀበር ሲል እግዚአብሔር የብዙዎች አባት አደረገው። የብዙዎች አባት መሆኑን እርሱ አላየም። አብርሃም ጥቂት ልጆችን ብቻ በዓይኑ አየ። እግዚአብሔር ባየለት ነገ ተደሰተ። ተስፋ ማለት እግዚአብሔር ባየልን “ነገ” መደሰት ማለት ነው። አብርሃም የተዘዋወረበትና ድንኳኑን የተከለበት ምድር በኋለኛው ዘመን ክርስቶስ የሚወለድበትና የማዳን ግብሩን የሚፈጽምበት ነው። አብርሃም ወደ ቤተልሔም በሄደ ጊዜ “እኔ በድንኳን ኖርሁ ፣ አንተ በበረት ተወለድህ ፣ ቤት አልባ ሆንህ” ብሎ ክርስቶስን በሩቅ ተሳለመው። ወደ ሞሪያ ተራራ ፣ ወደ ቀራንዮ መጥቶ ልጁን ይስሐቅን ሊሠዋ ባለ ጊዜ ፣ በይስሐቅ ሞት የሚድን ዓለም የለምና የክርስቶስን ቤዛነት ናፈቀ። ከመልከ ጼዴቅ ኅብስትና ጽዋውን ሲቀበል ፣ ዛሬ በሳሌም የተቀበልሁት ኅብስትና ወይን ፣ ነገ በኢየሩሳሌም በታላቁ ካህን በክርስቶስ የሚሰጠው ሥጋና ደሙ ነው ብሎ ተደነቀ። አብርሃም ያመነውና የኖረው የዛሬው አማኝ የሚያምነውና የሚኖረውን እውነት ነው። እምነት በዘመናት መካከል አንድ መልክ ለአማኞች በመስጠት የሚታወቅ ነው።

ይስሐቅን ከሞት ያዳነው ፣ በዱር የተገኘው፣ ያለ ቦታው የታየው ፣ ኃይል እያለው እንደሌለው የሆነው የእግዚአብሔር በግ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። አብርሃም የመሥዋዕቱን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል አለ ፣ ዮሐንስ መጥምቅም “የእግዚአብሔር በግ እነሆ!” አለ። ያዕቆብ በኤፍራታ ራሔልን ቀበረ። ራሔል በመውለድ ሞተች ፣ ሕያው ልጅን ሰጥታ እርስዋ አንቀላፋች። ራሔል በያዕቆብ መወደድዋ ከሞት አላዳናትም። ወድዶ ከሞት የሚያድን ክርስቶስ ብቻ ነው። መዝሙረኛው “ወዶኛልና አዳነኝ” ያለው ለዚህ ነው። የቤተ ልሔም የቀድሞ ስምዋ ኤፍራታ ነው። ተስፋ ባደረጉት አባቶች ርስት ክርስቶስ ተወለደ። የይሁዳ አንበሳ የይሁዳ ግዛት በሆነችው ቤተ ልሔም ተወለደ። የዳዊት ቤትን አልከዳም ብሎ የቀረው ፣ እናቱ በቤተ ልሔም የሞተችበት ፣ የራሔል ልጅ ብንያም ነው። በታማኙ በብንያም ርስት ክርስቶስ ተወለደ። ዛሬም እርሱ በሚጠብቁት ርስት በፍቅር ፣ በሰላም ይወለዳል። ታማኞችን መለኮት አድራሻ ያደርጋቸዋል። ብዙዎች የከዱትን እኔ አልከዳውም የሚሉ ፣ የቀድሞ ወዳጅነትን የሚያስቡ ዛሬም የክርስቶስ ቤተ ልሔም ናቸው። እርሱ የሚጸየፈው በረትን ሳይሆን ክዳትን ነው።

አብርሃም ፣ ይስሐቅና ያዕቆብ ክርስቶስ ከእኔ ወገን ይወለዳል እያሉ ቤታቸውን ንጹሕ አደረጉ። መጻተኝነታቸውን ረሱት። ወደውም ለክርስቶስ ድሀ ሆኑ። በዓለም መጠላታቸውን ናቁት። ነገሥታት አብርሃምን ተጋጠሙት። አንድም ቀን በቤተ መንግሥት አልተጋበዘም። ሁለት ጊዜ ግን ሚስቱን ነጥቀው ፈርዖንና አቤሜሌክ አስደነገጡት። አማኒ በቤተ መንግሥት ለግብዣ ሳይሆን ያመነውን እንዲጥል ይጠራል። እግዚአብሔር ቃሉን አክባሪ ነውና ደግሞም በአብርሃም ላይ የተጠራውን ስሙን አክብሯልና ፣ አሁንም እርሱ የሚወጣበትን ዘር ይከላከላልና ሣራን ከነገሥታት እጅ ፈልቅቆ አወጣት። ክርስቶስ ከነገሥታት ሳይሆን ከመጻተኞች ቤት መወለድን መረጠ። በአብርሃም ድንኳን ሥላሴ አደሩ። ወደ ድንግል ማርያም ሥላሴ መጡ ። አብ አጸናት ፣ ወልድ ልጅ ሆናት። መንፈስ ቅዱስ አከበራት።

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
ሰብአ ሰገል ይዘው የመጡት ወርቅ ዕጣንና
ከርቤ ከየት መጣ?


በቅድምያ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ልደት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ! በዓሉ የሰላምና የፍቅር ይሁንልን።

ጌታችን በተወለደ ጊዜ ሰብአ ሰገል የገበሩተለት ወርቅ ፣ ዕጣንና ከርቤ መገኛቸው ከገነት እንደሆነ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን? ነገሩ እንደምን ነው ቢሉ ጥንት አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን በገነት ውስጥ በሰላምና በተድላ ይኖሩ ነበር። ታዲያ ዲያቢሎስ አትብሉ የተባሉትን እንዲበሉ ሐሳብ  አቅርቦ ካሳታቸው በኋላ ያን አትብሉ የተባሉትን በመብላታቸው ትዕዛዝ በመተላለፋቸው ሰባት ዓመት ከ47 ቀን በተድላ ከኖሩበት ገነት ተባረሩ። ከገነት ከወጡ በሁላ አዳምና ሔዋን በዚህ ምድር ላይ ኑሮአቸውን ሀ ብለው ጀመሩ።

አንድ ቀን አዳም እናታችን ሔዋንን በባል ልማድ ሊጨዋወታት (ሊገናኛት) ወዶ በመንገድ ጠብቆ አስደነገጣት ታዲያ ይህን ጊዜ ሥላሴ ተገልጠው "ምነው ማጫውን ሳትሰጠን ልጃችን ትነካለህን?" ቢሉት አዳምም "ጌታዩ የአንተ ያልሆነ የኔ የሆነ ምን አለኝና እሰጥሀለው!" ቢሊ "አይ ለኋልኛው ዘመን ሥርዓት ነውና ይህን ለእርሷ ስጣት እንኳ" ብለው ቅዱስ ሚካኤል ወርቁን ፣ ቅዱስ ገብርኤል ዕጣኑን ፣ ቅዱስ ሩፋኤል ደግሞ ከርቤውን ለአዳም ሰጥተውታል። አዳምም ተቀብሎ ለሔዋን ሰጣት ፣ ሔዋን ለሴት ሰጠችው ፤ ከሴት ሲወርድ ሰዋረድ ከኖህ ደረሰ፡ ኖህ በጥፋት ውኅ ዘመን ወደ መርከብ ሲገባ የአዳምን አጥንትና ወርቅ ፣ ዕጣን ፣ ከርቤውን በአንድነት ይዞ ገባ።

ኋላ የጥፋት ውኀው ጎደለና ከመርከብ ይዞትጰወጣ በሁላ ለሴም ሰጠው ፤ ሴምም መልከጼዴቅን ተገናኘውና የአዳምን አጥንት በጎለጎታ ቀበሩት። ለዚህም ነው የጌታችን የሥነ ስቅለቱ ስዕል ሲሳል ከሥር የራስ ቅል አጥንት የሚደረገው ያም የአዳም አጥንት ምሳሌ ነው። ከዚያም ሴም ለመልከጼዴቅ ወርቅ ፣ ዕጣን ፣ ከርቤውን በአደራ አስጠበቀው፡ መልከጼዴቅ ለአብርሃም ሰጠው።

ከአብርሃም ሲወርድ ሲወረድ በዳዊት በሰለሞን አድርጎ ከአካዝ ደረሰ፡ በአካዝ ዘመን ቴልጌልፌልሶር ማርኮ ወስዶ ከቤተ መዛግብት አኑሮታል፡ አባታቸው ዥረደሸት ፈላስፋ ነበር፡ አንድ ቀን በቀትር ከውኃ ዳር ሆኖ ሲፈላሰፍ በሰሌዳ ኮከብ ድንግል ሕፃን ታቅፋ አየ ያየውን በሰሌዳ ቀርጾ አሰቀመጠው ከመሞቱ በፊትም እንዲህ ያለ ኮከብ ሲወጣ ባያችሁ ግዜ ሰማያዊ ንጉስ ይወለዳልና ወስዳቹ ይህን ወርቅ ፣ ዕጣን ፣ ከርቤ ስጡት ብሎ ለልጆቹ ተናዞ ሞተ። በዚህ መልኩ ከእነዚህ ነገሥታት እጅ ደርሷል። በእርግጥ ታሪኩን ለመተረክ አንድ መጽሐፍ የሚበቃውም አይደለም ከረጅም በአጭሩ ግን ይህን ይመስላል።

ታዲያ ኮከቡም በታየ ግዜ የታዘዙትን ለመፈፀም 12
ነገስታት ፍርሻኩር የተባለ ንጉሥ እየመራቸው ከሀገራቸው ተነሱ እያንዳንዱ ነገሰታት 10 ሺህ የሚሆን ሠራዊት ይዘው በጉዞ ላይ እያሉ ኤፍራጥስ ወንዝ ሲደርሱ ፍርሻኩር የተባለው መሪያቸው ዘጠኙን ነገስታት ከነሰራዊታቸው ይዟቸው ተመለሰ ከተመለሱበት ምክንያት ውስጥ ግማሹ ስንቅ አልቆባቸው ሌሎቹ ደግሞ በሀገራቸው ጠላት ተነስቶባችዋል የሚል ወሬ ሰምተው ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ኢየሩሳሌም ለሰላሳ ሺ ሠራዊት አትበቃም ጠባብ ናት ብለው የተመለሱም አሉ። ምስጢሩ ግን ከበረከተ ልደቱ እንዲሳተፋ የተመረጡት ሦስቱ ብቻ መሆናቸውን የጠይቃል የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ጥቂቶች ናቸው እንደተባለ።


ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
​​ከአንተ ባላውቅም

በገነተ አበው (The Paradise of Fathers) መጽሐፍ ላይ ይህ ታሪክ ተጽፎአል::

አንድ መነኩሴ በበአቱ ቁጭ ብሎ መጽሐፍ ቅዱስን ሲያነብ አንድ ቃል ሊገባው አልቻለም:: ለመረዳት በጣም ሲያስቸግረው "ይኼን ቃልስ እንዲገልጽልኝ ወደ እግዚአብሔር መጸለይ አለብኝ" ብሎ ወሰነ:: ነቢያቱ ያደርጉት እንደነበረውም እግዚአብሔር የቃሉን ፍቺ እስኪገልጽለት ድረስ መጾምና መጸለይ ጀመረ:: ነገር ግን ለሰባ ሳምንታት ያህል እየጾመ ቢጠባበቅም ምንም ነገር ሊገለጽለት አልቻለም:: በየሳምንቱ መጨረሻ ቃሉን ደግሞ ሲያነበውም የበለጠ እየተወሳሰበበት ሔደ እንጂ ጨርሶ ሊገባው አልቻለም::

በመጨረሻም ተስፋ ቆረጠ:: ስለዚህ ሌላ መነኩሴ ጋር ሔዶ ስለዚህ ቃል ትርጉም ሊጠይቀው ወሰነ:: በአቱን ዘግቶ መንገድ ሊጀምር ሲዞር ግን የእግዚአብሔር መልአክ በፊቱ ቆሞ ታየው::

"አይዞህ አትፍራ የፈለግኸውን የቃሉን ትርጉም ልገልጽልህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኬያለሁ" አለው::

መነኩሴው ግራ ገባው
"የጌታ መልአክ ሆይ ሰባ ሳምንት ሙሉ እየጾምሁ እንዲገልጥልኝ ስለምን ቆይቼ ምንም መልስ አላገኘሁም:: አሁን ተስፋ ስቆርጥ እግዚአብሔር ስለምን መለሰልኝ?" አለ በፍርሃት ውስጥ ሆኖ

"እግዚአብሔር ሰባ ሳምንታት ከጾምኸው ጾም ይልቅ ወንድምህን ለመጠየቅ በመሔድ ያሳየኸውን ትሕትና ተቀብሎታል" አለው::

አላዋቂ መስሎ መታየትን ያህል የምንፈራው ነገር የለም:: "አላውቀውም አንተ ንገረኝ" ከማለት ይልቅ ብዙ ሰው ሞት ይመርጣል:: ትንሽ ተምሬያለሁ የሚል ሰውማ ጥያቄ መጠየቅ ዲግሪውን ማቃጠል ይሆንበታል:: የብዙዎቻችን ትሕትና የሚፈቅድልን ሰዓት ለመጠየቅ ብቻ ነው:: "ከአንተ አላውቅም ..." ብለው የሚጀምሩ ዐረፍተ ነገሮች ራሱ ልብ ብለን ከሰማናቸው ይዘታቸው "ከእኔ አታውቅም" ነው::

የእውቀታችንን ውስንነት ለማመን የሚከብደን በሥጋችን ውስጥ ያለችው ለባዊት ነፍሳችን በሥጋዊ እውቀት ራስዋን መገደብ ስለምትቸገርም ነው:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "አሁን ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ" ብሎ የእውቀትን ውስንነት ማመን ግን ዕረፍት ይሠጣል:: 1ቆሮ. 13:12

በመንፈሳዊው ዓለም እንዲህ ሲሆን ደግሞ ይበልጥ አሳዛኝ እውነታ ነው::  አላውቀውም አላነበብኩትም አልሰማሁትም ከማለት ይልቅ ሁሉን አዋቂ ሆኖ ለመገኘት ስንል የምንበላቸው ዕፀ በለሶች ብዙ ናቸው::

"ብዙ የማውቀው ነበረ ሰዓት ገደበኝ እንጂ" ብሎ ውስን እውቀቱን ባሕር ለማድረግ የሚደክምና ሰዎች ከተናገረው ከጻፈው በላይ አድርገው እንዲያስቡት የሚገፋፋ ሰው የሚወለደው ካላዋቂነት ፍርሃት ውስጥ ነው::  በጥቂት ንባብ ውስጥ ራስን በጥልቅ ምሁር ዓይን ማየትና "እኔ የማውቀው ማወቄን ነው" ማለት የአላዋቂነት ፍርሃት የሚወልዳቸው ኢሶቅራጥሶች መርሕ ነው::

ከሌላው በታች አላዋቂ መስሎ መታየትን እንፈራለን:: ስለዚህ ሌላውን ከመጠየቅና እንደ ጃንደረባው "የሚመራኝ ሳይኖር እንዴት ይቻለኛል?" "ነቢዩ ይኼን ስለማን ተናግሮታል?" ብሎ ከመማር ይልቅ በራሳችን ለመረዳት ብንሟሟት እንመርጣለን:: ብዙ "የእምነት" denominations የተፈጠሩትም ሌላውን ከመጠየቅ ሞትን በሚመርጡ ትዕቢተኞችና "እንደገባኝና እንደተረዳሁት" በሚል አስተሳሰባቸው እንደነበር ታሪክ ያስረዳናል::

"ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር" ፊልጵ. 2:3

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
አጉል ልማዶችን ተዉ

አጉል ልማዶችን ከሥር ጀምሮ ወላጆች ያስጥሉናል። ቀጥሎ መምህራን ያስተዉናል። መጻሕፍትም እንደ ሸለፈት የሆነውን ፣ ውበትና ጤንነትን የሚጎዳውን ክፉ ልማድ እንድንተው ያግዙናል። የሰው ልጅ በሕይወት እስካለ ድረስ ለማወቅና ለንስሐ ጊዜው አይረፍድበትም። አጉል ልማድ ባለማወቅ ምክንያት ፣ ሥነ ሥርዓትን ባለመማር ፣ ልቅ በሆነ ባሕል ውስጥ በማደግ ፣ ሥልጣኔ በሚመስል ዘላንነት በመያዝ ሊመጣ ይችላል። አጉል ልማዶች እጅግ ብዙ ሲሆኑ ሁሉንም መንቀስ አይቻለንም። አጉል ልማዶች ትንሽ የሚመስሉ ትልቅ ጥፋት የሚያስከትሉ ናቸው። አጉል ልማድ ውስጥ ካለን ከሰዎች ጋር እንጋጫለን። ሰዎች ባይጋጩንም ለእኛ ያላቸው ክብር ይቀንሳል። አንዳንድ ሰዎች ሊነግሩን ይችላሉ። የሚበዙት ግን እየታዘቡ ዝም ይሉናል። በአፍ መፍረድ ፣ በልብ መታዘብ ሁለቱም አንድ ዓይነት ኃጢአት ቢሆንም ሰዎች ታዝበው ዝም ይሉናል። መመከርን መቋቋም የማንችል ፣ ግን ብዙ ግድፈት ያለብን ሰዎች ልንሆን እንችላለን። በዚህ ምክንያት የበለጠ እኛን ላለማጣት ዝም የሚሉን ይበዛሉ።

መኝታ አታብዛ። ገንዘብ እየፈለግህ መኝታ እያበዛህ አይሆንም። አንተ እንድትተኛ የተጉልህ ሰዎች ይኖራሉ። ነገር ግን እነርሱ ጊዜያዊ እንጂ ዘላለማዊ በረከቶችህ አይደሉምና እልፍ ይላሉ። ያን ቀን በራስህ መቆም ያቅትሃል። የራስህ ሕይወት ስለሌለህ የእነርሱ ህልውና ሲያበቃ ያንተም ያበቃል። ወረተኛ አትሁን። ሸሚዝ እንጂ ሰው አይቀያየርም። ቶሎ ስልቹ ሆነህ መልሰህ እገሌን አታሳዩኝ ፣ አታሰሙኝ አትበል ። ሰው ብዙ ነው ፣ ሰው ጥቂት ነው። ካከበርከው ሰው ብዙ ነው። ከናቅኸው ግን ሰው ጥቂት ነውና አንድ ሰውም ታጣለህ። ወሬ አታጣጥም። “ፐ ፣ ይገርማል ፣ እስኪ ንገረኝ” እያልህ የወሬ ሱስህን አትወጣ። አንዳንዱን ነገር ባትሰማው የተሻለ ነው። ፊት ለፊት ልትነግረው የፈራኸውን ሰው ከኋላው አትማው። ስታወራ ከንፈርህን እየመጠጥህ ፣ ግንባርህን እያሸህ አታውራ። ስትሰብክ አትወራጭ ፣ ከቦታ ቦታ አትፍለስ። እጅህን አታወናጭፍ። ሰዎች በግልህ የነገሩህን ራሳቸው ያውሩ እንጂ ስማቸውን ጠርተህ በአደባባይ አታውራ።

ምግብ ስትመገብ በመጠኑ ጥቅልል እንጂ ሰሐኑን እንደሚወስዱበት ሰው ከልክ በላይ አትጠቅልል። ጥቂት በጥቂት መጉረስ ክብር ነው። ስትበላም አፍህን ገጥመህ ብላ እንጂ ስታላምጥ አጠገብህ ያለ ሰው መስማት የለበትም። በትልቅ ማዕረግ ላይ ያለህ ከሆንህ በአደባባይ ምግብ አትብላ። ጳጳሳት በአደባባይ ባይመገቡ ይመከራል። ወደ ድግስ ስትጠራ በልተህ ሂድ። በምንም መንገድ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጣ። ጠላት ያለበት ሰው በሴት ፣ በሆዱና በአልኮል መጠጥ ያጠምዱታልና ተጠንቀቅ። ሰዎችን ስታወራና ስታናገር ፊት ለፊት እያየሃቸው ተነጋገር። አፍረህ አንገትህን መቅበር ፣ እንደ ተንኮለኛም ግንባርህን አቀርቅረህ በዓይንህ ግልባጭ ሰውን ማየት በጣም ነውር ነው። ሰው አፍ ውስጥ የምትገባ እስክትመስልም አፍጥጠህ አታነጋግር። ሰዎቹን ራሳቸውን ተመልከት እንጂ የለበሱት ልብስ ፣ ያደረጉት ጫማ ላይ ዓይንህን አትላከው። እንደ ውሻም እግር እግር አትመልከት። ዜማ ስታዜም ፣ መዝሙር ስትዘምር የላይኛውንም የሥረኛውንም ጥርስህን አታሳይ። ጥርሱን የሚያሳይ የሞተና የረገፈ አጽም ብቻ ነው። እቤትህ ሳትጨርስ ደጅ ላይ ወጥተህ ቀበቶህን መፍታትና መዝጋት ነውር ነው። በሰው ላይ ማዛጋት ፣ ሰው ፊት መሐረብ ሳይሸፍኑ ማሳልና ማስነጠስ ተገቢ አይደለም።  ቀጠሮ አክብር። ሁለት ጊዜ ደውለህ ስልክ ያላነሣልህ ሰው ጋ መደወል አቁም።

ሰዎችን ሰላም ብለህ ከሸኘህ በኋላ ዞር ብለህ አትመልከታቸው። ጀርባን የሚያይ ጠላት ነውና ። ከሰዎች ጋር ሆነህ ስልክህን አትጎርጉር። ከተከበረ ሰው ፊት እግርህን አጣምረህ አትቀመጥ። ታላቅህ ሲመጣ ከመቀመጫህ ተነሥተህ ተቀበለው። ሲደወልልህ ስልክህን አንሣ። ማንሣት የማትፈልግ ከሆነ ጉዳዩን ገልጸህ እንዳይደውሉ አድርግ። ሰዎችን በገዛ ስህተታቸው ይቅርታ አትጠይቅ። ይህ እውነትን የሚቀብር ፣ መለማመጥን የሚያሰፍን ነው። ደግሞም ስህተታቸውን እንዳያዩ አስተዋጽኦ ታደርጋለህ። ካልተገራ ሰው ጋር ቀልድ አትቀልድ። ባለጌ ሥራውን አይረሳምና ለመደ ብለህ በርህን አትክፈትለት። ለሰዎች ቀጠሮ ስትሰጥ ጉዳዩንም አብረህ ንገራቸው። “እፈልግሃለሁ ብርቱ ጉዳይ አለ ፣ አሁን አልነግርህም” እያልህ የሰውን ሰላም አትንሣ። የማትጨርሰውን ወሬ አትጀምር። “ይህ ለምን ሆነ ?” አትበል ፤ እንዲህ እንዲሆን እኔ ምን አጥፍቻለሁ ? ብለህ ታረም ። የማምሸት ልማድህን ተው። በጊዜ መተኛትን ልመድ። ሰዎች ሲናገሩ አታቋርጣቸው። እኔ ብቻ ልናገር አትበል። ሁሉን እንደምታውቅ ከተሰማህ ታመሃልና እርዳታ ያስፈልግሃል። ምንም ብትቀራረብ ባለሥልጣንን በአደባባይ አንተ ብለህ አትጥራ። የጎሣና የቋንቋ ትችት ያለበት ወሬ አትጀምር። ያየኸውን የሰው ገመና ለሌላው አትናገር። ይህ የጸሎት እንጂ የወሬ ርእስ አይደለምና። መጓዝ ያለብህ ሰዎች እስከፈቀዱልህ ድረስ ብቻ ነው። ያልተፈቀደልህን መስመር ስታልፍ የተፈቀደውንም ታጣለህ።

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
አጉል ልማዶችን ተዉ

አጉል ልማዶችን ከሥር ጀምሮ ወላጆች ያስጥሉናል። ቀጥሎ መምህራን ያስተዉናል። መጻሕፍትም እንደ ሸለፈት የሆነውን ፣ ውበትና ጤንነትን የሚጎዳውን ክፉ ልማድ እንድንተው ያግዙናል። የሰው ልጅ በሕይወት እስካለ ድረስ ለማወቅና ለንስሐ ጊዜው አይረፍድበትም። አጉል ልማድ ባለማወቅ ምክንያት ፣ ሥነ ሥርዓትን ባለመማር ፣ ልቅ በሆነ ባሕል ውስጥ በማደግ ፣ ሥልጣኔ በሚመስል ዘላንነት በመያዝ ሊመጣ ይችላል። አጉል ልማዶች እጅግ ብዙ ሲሆኑ ሁሉንም መንቀስ አይቻለንም። አጉል ልማዶች ትንሽ የሚመስሉ ትልቅ ጥፋት የሚያስከትሉ ናቸው። አጉል ልማድ ውስጥ ካለን ከሰዎች ጋር እንጋጫለን። ሰዎች ባይጋጩንም ለእኛ ያላቸው ክብር ይቀንሳል። አንዳንድ ሰዎች ሊነግሩን ይችላሉ። የሚበዙት ግን እየታዘቡ ዝም ይሉናል። በአፍ መፍረድ ፣ በልብ መታዘብ ሁለቱም አንድ ዓይነት ኃጢአት ቢሆንም ሰዎች ታዝበው ዝም ይሉናል። መመከርን መቋቋም የማንችል ፣ ግን ብዙ ግድፈት ያለብን ሰዎች ልንሆን እንችላለን። በዚህ ምክንያት የበለጠ እኛን ላለማጣት ዝም የሚሉን ይበዛሉ።

መኝታ አታብዛ። ገንዘብ እየፈለግህ መኝታ እያበዛህ አይሆንም። አንተ እንድትተኛ የተጉልህ ሰዎች ይኖራሉ። ነገር ግን እነርሱ ጊዜያዊ እንጂ ዘላለማዊ በረከቶችህ አይደሉምና እልፍ ይላሉ። ያን ቀን በራስህ መቆም ያቅትሃል። የራስህ ሕይወት ስለሌለህ የእነርሱ ህልውና ሲያበቃ ያንተም ያበቃል። ወረተኛ አትሁን። ሸሚዝ እንጂ ሰው አይቀያየርም። ቶሎ ስልቹ ሆነህ መልሰህ እገሌን አታሳዩኝ ፣ አታሰሙኝ አትበል ። ሰው ብዙ ነው ፣ ሰው ጥቂት ነው። ካከበርከው ሰው ብዙ ነው። ከናቅኸው ግን ሰው ጥቂት ነውና አንድ ሰውም ታጣለህ። ወሬ አታጣጥም። “ፐ ፣ ይገርማል ፣ እስኪ ንገረኝ” እያልህ የወሬ ሱስህን አትወጣ። አንዳንዱን ነገር ባትሰማው የተሻለ ነው። ፊት ለፊት ልትነግረው የፈራኸውን ሰው ከኋላው አትማው። ስታወራ ከንፈርህን እየመጠጥህ ፣ ግንባርህን እያሸህ አታውራ። ስትሰብክ አትወራጭ ፣ ከቦታ ቦታ አትፍለስ። እጅህን አታወናጭፍ። ሰዎች በግልህ የነገሩህን ራሳቸው ያውሩ እንጂ ስማቸውን ጠርተህ በአደባባይ አታውራ።

ምግብ ስትመገብ በመጠኑ ጥቅልል እንጂ ሰሐኑን እንደሚወስዱበት ሰው ከልክ በላይ አትጠቅልል። ጥቂት በጥቂት መጉረስ ክብር ነው። ስትበላም አፍህን ገጥመህ ብላ እንጂ ስታላምጥ አጠገብህ ያለ ሰው መስማት የለበትም። በትልቅ ማዕረግ ላይ ያለህ ከሆንህ በአደባባይ ምግብ አትብላ። ጳጳሳት በአደባባይ ባይመገቡ ይመከራል። ወደ ድግስ ስትጠራ በልተህ ሂድ። በምንም መንገድ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጣ። ጠላት ያለበት ሰው በሴት ፣ በሆዱና በአልኮል መጠጥ ያጠምዱታልና ተጠንቀቅ። ሰዎችን ስታወራና ስታናገር ፊት ለፊት እያየሃቸው ተነጋገር። አፍረህ አንገትህን መቅበር ፣ እንደ ተንኮለኛም ግንባርህን አቀርቅረህ በዓይንህ ግልባጭ ሰውን ማየት በጣም ነውር ነው። ሰው አፍ ውስጥ የምትገባ እስክትመስልም አፍጥጠህ አታነጋግር። ሰዎቹን ራሳቸውን ተመልከት እንጂ የለበሱት ልብስ ፣ ያደረጉት ጫማ ላይ ዓይንህን አትላከው። እንደ ውሻም እግር እግር አትመልከት። ዜማ ስታዜም ፣ መዝሙር ስትዘምር የላይኛውንም የሥረኛውንም ጥርስህን አታሳይ። ጥርሱን የሚያሳይ የሞተና የረገፈ አጽም ብቻ ነው። እቤትህ ሳትጨርስ ደጅ ላይ ወጥተህ ቀበቶህን መፍታትና መዝጋት ነውር ነው። በሰው ላይ ማዛጋት ፣ ሰው ፊት መሐረብ ሳይሸፍኑ ማሳልና ማስነጠስ ተገቢ አይደለም።  ቀጠሮ አክብር። ሁለት ጊዜ ደውለህ ስልክ ያላነሣልህ ሰው ጋ መደወል አቁም።

ሰዎችን ሰላም ብለህ ከሸኘህ በኋላ ዞር ብለህ አትመልከታቸው። ጀርባን የሚያይ ጠላት ነውና ። ከሰዎች ጋር ሆነህ ስልክህን አትጎርጉር። ከተከበረ ሰው ፊት እግርህን አጣምረህ አትቀመጥ። ታላቅህ ሲመጣ ከመቀመጫህ ተነሥተህ ተቀበለው። ሲደወልልህ ስልክህን አንሣ። ማንሣት የማትፈልግ ከሆነ ጉዳዩን ገልጸህ እንዳይደውሉ አድርግ። ሰዎችን በገዛ ስህተታቸው ይቅርታ አትጠይቅ። ይህ እውነትን የሚቀብር ፣ መለማመጥን የሚያሰፍን ነው። ደግሞም ስህተታቸውን እንዳያዩ አስተዋጽኦ ታደርጋለህ። ካልተገራ ሰው ጋር ቀልድ አትቀልድ። ባለጌ ሥራውን አይረሳምና ለመደ ብለህ በርህን አትክፈትለት። ለሰዎች ቀጠሮ ስትሰጥ ጉዳዩንም አብረህ ንገራቸው። “እፈልግሃለሁ ብርቱ ጉዳይ አለ ፣ አሁን አልነግርህም” እያልህ የሰውን ሰላም አትንሣ። የማትጨርሰውን ወሬ አትጀምር። “ይህ ለምን ሆነ ?” አትበል ፤ እንዲህ እንዲሆን እኔ ምን አጥፍቻለሁ ? ብለህ ታረም ። የማምሸት ልማድህን ተው። በጊዜ መተኛትን ልመድ። ሰዎች ሲናገሩ አታቋርጣቸው። እኔ ብቻ ልናገር አትበል። ሁሉን እንደምታውቅ ከተሰማህ ታመሃልና እርዳታ ያስፈልግሃል። ምንም ብትቀራረብ ባለሥልጣንን በአደባባይ አንተ ብለህ አትጥራ። የጎሣና የቋንቋ ትችት ያለበት ወሬ አትጀምር። ያየኸውን የሰው ገመና ለሌላው አትናገር። ይህ የጸሎት እንጂ የወሬ ርእስ አይደለምና። መጓዝ ያለብህ ሰዎች እስከፈቀዱልህ ድረስ ብቻ ነው። ያልተፈቀደልህን መስመር ስታልፍ የተፈቀደውንም ታጣለህ።

ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
​​የእግዚአብሔር ባህርይ

የእግዚአብሔር መለኮታዊ ባህርይ በሰው አእምሮ የማይመረመርና የማይወሰን ረቂቅ ነው። በዓለም ያለውን ማንኛውንም ነገር መመራመርም ሆነ ለሌላውም ማስረዳት ይቻላል። የመለኮትን ባህርይ ግን ሙሉ በሙሉ ተመራምሮ የሚያውቅም ሆነ የሚያስረዳ ማንም የለም። ነገር ግን ቅዱሳት መጻሕፍት በገለጹልን መሠረት እንደሚከተለው ለመግለጽ እንሞክራለን።

እግዚአብሔር መንፈስ (ረቂቅ) ነው እግዚአብሔር መንፈስ ነው የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእምነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል። ዮሐ 4 ፥ 24። በማለት ጌታችን እንደተናገረ እግዚአብሔርን ስናምን በዓይናችን አይተን ፣ በእጃችን ዳስሰን አረጋግጠን ሳይሆን በመለኮታዊ ባህርዩ በሥጋ ዓይን የማይታይ አምላክ መሆኑን አምነን በመቀበል ነው። እግዚአብሔር መንፈስ ነው ስንልም። በእኛ አእምሮ የማይታወቅ ፤ መጠን የማይሰጠው ፤ በላብራቶሪ ምርመራ የማይደረስበት ፤ከምርምር ውጭ የሆነ አምላክ ማለታችን ነው። እግዚአብሔር የፈጠረው ነፋስን እንኳን ከረቂቅነቱ የተነሳ በዓይናችን ማየት እንደማንችል ሁሉ። ዮሐ 3 ፥ 8። ረቂቃን ፍጥረታትን የፈጠረ አምላክ መለኮታዊ ባህርዩ ሊመረመርና ሊገመት የማይችል ረቂቅ ነው።

እግዚአብሔር በሁሉም ሙሉ ነው
ሰው በአንድ ጊዜ በሁሉም ቦታ መገኘት የማይችል በተወሰነ ቦታ ብቻ የሚወሰን ነው። ኤር 23 ፥ 23። እግዚአብሔር ግን ፍጡር የማይወስነው ፣ በሁሉም ቦታ የሚገኝ ፣ (ምሉዕ በኩለሄ የሆነ) አምላክ ነው። እግዚአብሔር በዓለም ሙሉ ነው ሲባል በዓለም ውስጥ ብቻ ተወስኖ ይኖራል ማለት ሳይሆን ዓለምን በውስጡ ይወስናል ማለት ነው። በኢሳ 8 ፥ 1። “ ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት።” የሚለው ቃል እግዚአብሔር በዚህ አካባቢ ብቻ አለ ተብሎ ቦታ የማይወሰንበት ፡ ሰማይም ምድርም ዓለማት በሙሉ ግዛቱ መሆናቸውን የሚያስረዳ ነው።

እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ነው ሰዎች በዚህ ዓለም መኖር የሚችሉት በሕይወት እስካሉ ድረስ ብቻ ነው። ጊዜያዊ የሆነው ምድራዊ ኑሯቸው በሞት ይለወጣል። ዘፍ 3 ፥ 19። እግዚአብሔር ግን ዓለማት ሳይፈጠሩ የነበረ ፣ አሁንም እየገዛ ያለ ፣ ወደፊትም ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ፣ በባህርዩ ሞት ፣በመንግሥቱ ሽረት የሌለበት ዘለዓለማዊ አምላክ ነው። እኛ ሰዎች የተወለድንበት ቀን መጀመሪያችን ፤ የምንሞትበት ቀን መጨረሻችን ነው ፤ አምላክ ግን ሰው በመሆኑ ዘመን ቢቆ ጠርለትም ፤ ሥጋ ፡ የመለኮትን ባህርይ በተዋሕዶ ገንዘቡ ስላደረገ “ስለተዋሃደ” ፤ ዘመናት የማይቀድሙት ቀዳማዊ ዘመናትን አሳልፎ የሚኖር ደኃራዊ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው ዘለዓለማዊ አምላክ ነው ። ራዕ 1 ፥ ፲፰ ለነበረበት መጀመሪያ ፤ የማይኖርበት መጨረሻ የለውም ፤ ለሁሉም ነገር መጀመሪያውም ሆነ መጨረሻው ራሱ ነው። ዘፍ 18 ፥ 14 ዘፀ 3 ፥ 14:

እግዚአብሔር ጥበበኛ (አዋቂ) ነው የሰው ልጅ ይዞት የተወለደው ልቅሶ ብቻ ነው። ሌላውን ሁሉ ፡ በማየት፣ በመስማት ፣ በመማር ፤ ከሰዎች ያገኘው ነው። ያውም ቢሆን ያለፈውን ታሪክ ከማውራትና አሁን የሚደረገውን ከማየት በቀር ወደ ፊት የሚሆነውን ለማወቅ የሚያስችል ዕው ቀትና ጥበብ የለውም። ዕውቀቱም ቢሆን የአንዱ ዕውቀት ከሌላው ይበልጣል ፤ በዚህ ዓለም ፍፁም የሆነ ዕውቀት የለም የተከፈለውም ቢሆን በጊዜው ያልፋል። 1ቆሮ 13 ፥ 8። እግዚአብሔር ጥበቡ የባህርዩ የሆነ ፣ ያለፈውን የማይረሳ ፣የሚያውቅ ፣ ለሰዎች ዕውቀትንና ጥበብን የሚገልጽ አምላክ ነው። ሰው ሊያውቅና ሊመራመር የሚችለው ውጫዊውንና ግዙፉን ነገር ብቻ ነው። እግዚአብሔር ግን ልብና ኩላሊትን (በሰው ህሊና የታሰበውን) አስቀድሞ የሚያውቅ አምላክ ነው። መዝ 7 ፥ 9።

እግዚአብሔር ቅዱስ ነው ቅድስና የእግዚአብሔር የባህርዩ ሲሆን “እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ” ዘሌዋ 19 ፥ 2። 1 ጴጥ 1 ፥ 15። ባለው ቃል መሠረት ቅዱሳን መላእክትና በሥራቸው ለቅድስና የበቁ ሰዎችም ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ። የመላእክትና የሰዎች ቅድስና ግን ፡ በሥራ የሚገኝ ፣ በሃይማኖት የተፈተነ ፣ከእግዚአብሔር የሚሰጥ የፀጋ ቅድስና ነው። የፍጡራን ቅድስና ደረጃ አለው ከአንዱ የሌላው ይበልጣል። 1 ቆሮ 15 ፥ 41። የእግዚአብሔር ቅድስና በመጠን አይወሰንም ፤ እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ማንም የለምና ። ኢሳ 6 ፥ 3። ዕንባ 1 ፥ 13።

እግዚአብሔር ቸር ነው የሰው ልጅ ቸርነቱ (ልግስናው) በኪሱ ያለው ሳንቲም እስኪያልቅ ፤ እሱንም ቢሆን የሚሰጠው ተለምኖ ነው። እግዚአብ ሔር ሁሉ ያለው ፣ ያለ ንፍገትና ያለ መሰሰት ለጋስ ፣ ስጦታው የማያልቅበት ፣ ኃጥዕ ጻድቅ ሳይል በቸርነቱ ለሁሉ ያለ አድልዎ የሚያድል ማቴ 5 ፥ 41። ሳንለምነው የሚያስፈልገንን አውቆ የሚሰጠን ፣ቸር አምላክ ነው። ማቴ 6 32። ሰው የሚሰጠው ከሌላው ያገኘውን ነው ፤ወደዚህ ዓለም የመጣው ራቁቱን ነው ፤ወደ ምድር ሲመለስም የሚያስከትለው ነገር የለውም። ኢዮ 1 ፥ 21። 1ጢሞ 6 ፥ 7። እኛ ለሌሌሎች የምንሰጠው ከተረፈን ብቻ ነው አምላካችን ግን ለእኛ የሰጠን ራሱን ነው። ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። ዮሐ 15 ፥ 13። ሰው የሚሰጠው ለወዳጁ ፣ ለወገኑ ፣ ለሚመስለው… ነው እግዚአብሔር ግን ጠላቶቹ ሳለን ራሱን ለሞት አሳልፎ በመስጠት ከራሱ ጋር አስታረቀን ፤ ከዘለዓለም ሞትም አዳነን። ሮሜ 5 ፥ 10።

እግዚአብሔር ፍቅር ነው ሰው ወዳጁን ይወዳል ለማይወደው ግን ቦታ አይሰጥም ፤ እንዲያውም ከተመቸው ከመበቀል ወደኋላ አይልም። እግዚአብ ሔር ግን እየበደልነው ለንስሐ እስክንዘጋጅ በብዙ ታግሶ ይወደናል። ሮሜ 2 ፥4። የሰው ፍቅሩ ተለዋዋጭ ፣ ወረት ያለበት ፣ ጊዜያዊ ነው። ሰው ለጥቅም ብሎ ወዳጁን ይገድላል። አምላካችን ፍቅሩ የማይለካ ፣ ለእኛ ለጠላቶቹ የሞተ ፤ ኢሳ 53 ፥ 1 ፥12። የሠራነውን ሁሉ በቸርነቱ ይቅር ብሎ ከበደል የሚያነጻን አምላክ ነው። ኢሳ 1 ፥ 18። እግዚአብሔር ፈቅደን እንድንገዛለት ይፈልጋል እንጅ ፤ ማንኛችንንም አስጨንቆ አይገዛንም። 1 ዮሐ 18

እግዚአብሔር በእውነት የሚፈርድ እውነተኛ ዳኛ (ፈራጅ) ነው እግዚአብሔር ለሰዎች የዳኝነት ሥልጣን የሰጣቸው ትክክለኛ ፍርድ እንዲፈረዱ ነው። ማንም ቢሆን እውነት መፍረድ እንዳለበት ህሊናው ይነግረዋል። በሐሰት ስንፈርድ በመጀመሪያ የሚወቅሰን ህሊናችን ነው። የህሊና ወቀሳን የማይፈራ ማንንም ሊፈራ አይችልም። ዳኞች ፡ በዘመድ ፣ በጥቅማ ጥቅም ፣ በዓላማ መመሳሰል ፡ እና በሌላም ፍርድ ሊያዛቡ ይችላሉ። እግዚአብሔር ግን ከማንም ምንም የማይፈልግ ፣ ከእውነት ጋር ደስ የሚለው ፣ ፍርዱ ትክክለኛ የሆነ አምላክ ነው። እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያደላም ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው መጠን ዋጋውን ይከፍለዋል። ራዕ 22 ፥ 12። መዝ 36 ፥ 28

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦  ሀልወተ እግዚአብሔር
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
​​​​​​✞ እንኳን ለአጋእዝተ ዓለም "ሥላሴ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ሥሉስ ቅዱስ

ምሥጢራት በእምነት ለማይኖር: በትሕትናም ለማይቀርብ የሚገለጡ አይደሉም::

እግዚአብሔር አንድም ነው: ሦስትም ነው:: ጊዜ ሣይሠፈር ዘመንም ሳይቆጠር እግዚአብሔር በስም: በአካል: በግብር ሦስትነቱ: በባሕርይ: በሕልውና: በመለኮትና በሥልጣን አንድነቱ የጸና አምላክ ነው::

ከዓለም መፈጠር በፊት ስለ ነበረው ነገር የሚያውቅ ራሱ ሥላሴ ብቻ ነው:: ዓለምን ከፈጠረ በሁዋላም ምሥጢረ ሥላሴ (መለኮት) ብለን የምንማረው ትምሕርት እንድንና እንጠቀም ዘንድ እርሱ የገለጠልንን ያህል ብቻ ነው::

ይኼውም በየጊዜው እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ቅዱሳኑ የገለጠው ምሥጢር ነው:: ከዚህ አልፈን በሥጋዊ አዕምሯችን ጌታን "እንመርምርሕ" ብንለው ግን ፍጻሜአችን ሞት: ማደሪያችንም ገሃነመ እሳት መሆኑ አይቀርም::

እግዚአብሔር በአንድነቱና ሦስትነቱ ሳለ ይህንን ዓለም ፈጠረ:: እግዚአብሔር ዓለምን ለምን ፈጠረ ቢሉ:- ስሙን ቀድሰን ክብሩን እንድንወርስ ነው:: ከዚህ የተረፈውን ምክንያት ግን ራሱ ያውቃል::

በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው:: አብ: ወልድ: መንፈስ ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::

ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት "ቅድስት ሥላሴ" እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው ያድራሉ::

ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን : በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል::

አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!) ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት::

ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ አብ ለአጽንኦ: መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ: ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::

በዓለ ሥላሴ በዚህ ቀን የሚከበረው ስለ 2 ምክንያቶች ነው:: ቀዳሚው ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው ሲሆን 2ኛው ደግሞ ቅዳሴ ቤታቸው ነው::

ሕንጻ ሰናዖር

ሰናዖር ከሺዎች ዓመታት በፊት በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ እንደ ነበረ የሚነገርለት ግዛት ሲሆን ስሙ ለሃገሪቱም: ለንጉሡም በተመሳሳይ ያገለግል ነበር:: ከናምሩድ ክፋት በሁዋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ::

ከጥፋት ውሃ (ከኖኅ ዕረፍት) በሁዋላ በሥፍራው በአንድነት ይኖሩ ነበርና እርስ በርሳቸው "ኑ ሳንበተን ስማችን የሚጠራበትን ሕንጻ እንሥራ:: በዚያውም አባቶቻችን በውሃ ያጠፋ እግዚአብሔርን እንውጋው" ተባባሉ::

ቀጥለውም ሰማይ ጠቀስ ፎቅን ገነቡ:: ከሕንጻው መርዘም የተነሳ በጸሐይ አብስለው በልተዋል ይባላል:: ቀጥለውም ጦር እያነሱ ፈጣሪን ሊወጉ ወርውረዋል::

መቼም የእነዚህን ሰዎች ክፋትና ቂልነት ስንሰማ ይገርመን ይሆናል:: ግንኮ ዛሬ ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም እየተሠራ ያለው ከዚህ የከፋ ነው:: ቸርነቱ ቢጠብቀን እንጂ እንደ ክፋታችንስ ጠፊ ነበርን::

ርሕሩሐን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም:: የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና:: ይልቁኑ "ንዑ ንረድ ወንክአው ነገሮሙ ለከለዳውያን-ቁዋንቁዋቸው እንደባልቀው" አሉ እንጂ::

ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቁዋንቁዎች ተፈጠሩ:: እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ:: ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ እንዲሆን በተኑት:: ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው "ባቢሎን (ዝሩት)" ሲባል ይኖራል::

ቅዳሴ ቤት

ልክ የዛሬ 324 ዓመት: አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮዽያ በነገሡ በ10ኛው ዓመት: (በ1684 ዓ/ም) በጐንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሰርታ ተጠናቃለች::

ጥር 7 ቀንም ሊቁ ክፍለ ዮሐንስን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን: ሠራዊት: መሣፍንትና ሊቃውንት ባሉበት ቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል:: በዕለቱም ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: ኢያሱ አድያም ሰገድ ኃያል: ደግ: ጥበበኛ: አስተዋይ: መናኝ ንጉሥ ነውና::

ቤተ ሥላሴን አስጊጿታልና ከዚህ ቀን ጀምሮ ጥር ሥላሴ በድምቀት የሚከበር ሆኗል:: ነገር ግን በተሠራች በ16 ዓመቷ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል:: ዛሬ የምናየው በ1708 ዓ/ም በልጁ በአፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው::

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ - ዝክረ ቅዱሳን
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
​​ጾመ ጋድ

ጥር አስር በዚች ዕለት ምንም ምን መብልን ሳይቀመሱ ምእመናን ሁሉ እስከ ምሽት ይጾሙ ዘንድ ከእኛ አስቀድመው የነበሩ ታላላቅ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሥርዓትን ሠሩ በምሽትም ቢሆን በታላቁ ጾም ከሚበላው በቀር ጥሉላትን እንዳይቀምሱ።

በዚች ዕለት ምእመናን እስከ ምሽት እንዲጾሙት ያዘዙበት ምክንያቱ ይህ ነው፦የልደትና የጥምቀት በዓል በረብዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ኃምሳ የሚበላውን የጥሉላት መብል በጥዋት በመብላት ምእመናን ሁሉ በአሉን እንዲአከብሩ የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት አዝዘዋል እሊህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓሎቹ ናቸውና ።

እኛ በዚህ በኃላፊው አለም ተድላ ደስታ ደስ የሚለን ለሌሎች እንዳይመስላቸው እንደ አይሁድና እንደ አረማውያን በዓል በመብልና በመጠጥ ብቻ እንዳናደርግ ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በአል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን እለታት እንድንፆም አዘዙን የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ላይ በሚሆን ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ እንድንጾማቸው ይገባልና በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው። እንዲሁም በግብጻውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው።

በይረሙን በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥር ቀን ነው በዋዜማው ዐርብ እስከ ምሽቱ ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላት አይብሉ የልደትና የጥምቀት በዓልም ሰኞ ቀን ቢሆን በሰንበት ቀን ይጾሙ ዘንድ አይቻልም ነገር ግን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ።

በጥምቀትም እለት ከእኩለ ሌሊት በፊት ተነስተው በውኃው ላይ ይጸልዩና ይጠመቁ ሕፃናትም በሚጠመቁ ጊዜ በውኃ እንዳይገድፉ ካህናቱም ከመንጋቱ በፊት ቀድሰው ቁርባኑን ያሳርጉ እጅግም ማልደው በጥዋት ከቤተ ክርስቲያን ይውጡ በከበረ ሥርዓታቸው ጌቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙ።

የመለካውያን ወገኖች ግን የልደትና የጥምቀት ዋዜማ በቅዳሜ ቀን ወይም በእሁድ ቀን ቢሆን በሶስት ሰዓት ይቀድሳሉ ከወደዱም የተባረከ ኅብስት ተመግበው ውኃ ይጠጣሉ ከዚህም በኋላ ካህናቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁነው በየሰአቱ በመጸለይ ለበዓሉ የሚገባውን የነቢያትን ትንቢቶች ያነባሉ በዚያም ቀን በምሽት ይኸውም ጥር ዓሥር ነው ። በውኃው ላይ ይጸልያሉ ይህም አባቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙት አልሆነም። እርሳቸው የኤጲፋንያን በዓል እንዲአከብሩ አዘዋል ይኸውም መድኀኃኒታችን የተገለጠበት ካኑን በሚባል በሮም ሁለተኛ ወር በሰባት ይህም ጥር ዐሥራ አንድ ቀን ነው።

መለካውያን ግን የከበሩ አባቶች የቤተ ክርስቲያን መምህራን ያዘዙትን ይተላለፋሉ በልደትና በጥምቀት በዓል ዓርብም ረቡዕም ቢሆን አስቀድመው በርሱ ፈንታ ሳይጾሙ በጥዋት ተነሥሥተው ይበላሉና።

እኛንም ከበደላችን ያነጻን ዘንድ በዮረዳኖስም ወንዝ እንደ ገለጸ የጌትነቱን ክብር በልቡናችን ይገልጥልን ዘንድ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው ጌትነት ክብር ስግደት ለእርሱ ይገባልና ። ከቸር አባቱ ጋር ይቅር ባይ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
ከተራ ምንድን ነው?

ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡

በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡

በተጨማሪ  በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት  አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።

በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

መልካም የከተራ በዓል
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
​​ጥምቀት

የሰው ልጅ ሕገ እግዚአብሔርን በመተላለፉና ለኃጢአት ተገዢ በመሆኑ ንጽሕት ነፍሱ አደፈች፤ ረከሰችም፤ በኃጢአቱም ምክንያት ከአምላኩ ተጣላ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ ምድርም በእርሱ የተነሣ ተረገመች፤ እሾህና አሜከላንም አበቀለች፡፡ እርሱም ለብዙ ዘመን አዝኖና በሥቃይ ኖረ፡፡

ቸርነቱ የማይልቅ መሐሪና ይቅር ባይ አምላካችን እግዚአብሔር በኀዘኑ አዝኖና ሥቃዩን ተመልክቶ ለእርሱ፤ ስለ እርሱ መከራና ሥቃይ ይቀበልለት ዘንድ ከንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሊያድነው በገባለት ቃል መሠረት ተፈጸመ፡፡ ከዚያም በኋላ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮርዳኖስን ብርህት ማኅፀን እንድትሆን፣ ምእመናንም ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ፣ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ዳግም ተወልደው መንግሥተ ሰማያት እንዲገቡ  እንደዚሁም ሥርዓተ ጥምቀትን ለማስተማርና አብነት ለመሆን በጥር ዐሥራ አንድ ቀን ተጠምቋልና ይህችን የተከበረች ቀን ሕዝበ ክርስቲያን ያከብር ዘንድ ይገባል፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስም ‹‹ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ፤ እናንተም ከርኵሰታችሁ ሁሉ ትጠራላችሁ›› ተብሎ አስቀድሞ በተነገረው መሠረት ጌታችን በውኃ ተጠመቀ፡፡ የዚህም ምክንያት ሊቀውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚያስረዱት ውኃ ለሁሉ አስፈላጊ በመሆኑና ያለ ውኃ መኖር የሚችል ባለመሆኑ  ያለ ጥምቀት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት አይቻልምና ጥምቀትም ለሁሉም የሚገባ ሥርዓት ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር ውኃ መልክ ያሳያል፤ መልክ ያለመልማል (ያጠራል)፡፡ ጥምቀትም መልክዐ ነፍስን ያሳያል፤ መልክዐ ነፍስን ያለመልማልና (ያጠራልና)፡፡ (ሕዝ.፴፮፥፳፭)

በዘመነ ሥጋዌ ‹‹ጌታችን  መድኃኒታችን  ኢየሱስ  ክርስቶስ  በዮሐንስ  እጅ  ይጠመቅ  ዘንድ  ከገሊላ  ወደ ዮርዳኖስ መጣ›› (ማቴ.፫፥፲፫፣ማር.፩፥፱፣ሉቃ.፫፥፳፩፣ዮሐ.፩፥፴፪)፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ግን አገልጋይ በጌታው እጅ ይጠመቃል እንጂ ጌታ በአገልጋዩ አይጠመቅም፤ ‹‹እኔ በእንተ ልጠመቅ እሻለሁ፤ አንተ ወደ እኔ ትመጣለህን?›› ብሎ አይሆንም አለው፡፡ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ ‹‹አሁንስ ተው፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባናልና›› አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ተወው፡ ጌታችን ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆ ሰማይም ተከፈተለት፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ሲቀመጥ አየ፤ እነሆም ‹‹በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው››የሚል ድምጽ ተሰማ፡፡(ማቴ.፫፥፲፫-፲፯)

መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል መውረዱም ምሥጢር አለው፡፡ ርግብ ኃዳጊተ በቀል ናት፤ መንፈስ ቅዱስም ኃዳጌ በቀል ነውና፡፡ ርግብ በኖኅ ጊዜ ‹‹ሐጸ ማየ አይኅ ነትገ ማየ አይኅ፤ የጥፋት ውኀ ጎደለ›› ስትል ቆጽለ ዕፀ ዘይት ይዛ ተገኝታለች፡፡ መንፈስ ቅዱስም ተስፋ መስቀልን ያበሥራልና፡፡

እኛም የሐዲስ ኪዳን ሕዝቦች ይህን ምሥጢር በመረዳት፣ መከራ መስቀሉን በመሸከምና እምነት በመጽናት እንድኖንር አስፈላጊ በመሆኑ ነገረ ድኅነቱን በመረዳት በልደቱ እንደዘከርነው ሁሉ በጥምቀቱም እንዲሁ እናደረግ ዘንድ ይገባል፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀውም በሠላሳ ዓመቱ ነው (ሉቃ. ፫፥፳፫)፡፡ በሠላሳ ዓመቱ የተጠመቀበት ምሥጢርም አዳም የሠላሳ ዓመት፤ ሔዋን የዐሥራ አምስት ዓመት ሰው ሆነው ተፈጥረው አዳም በዐርባ ቀን፣ ሔዋን በሰማንያ ቀን ከሥላሴ የተቀበሉትን ልጅነት በምክረ ከይሲ ዕፀ በለስን በልተው አስወስደው ነበረና በሠላሳ ዓመቱ ተጠምቆ መልሶላቸዋል፡፡ በሠላሳ ዓመት የመጠመቁ ምሥጢር ይህ ሲሆን እኛ ዛሬ ወንዶች በዐርባ ቀን፣ ሴቶች በሰማንያ ቀን በዕለተ ዓርብ ከቀኝ ጎኑ በፈሰሰው ማየ ገቦ ተጠምቀን ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ሁለተኛ የምንወለድበት ምክንያትም አዳም በዐርባ ቀኑ፣ ሔዋን በሰማንያ ቀኗ ከሥላሴ ያገኙትን ልጅነት መሠረት በማድረግ ነው /ኩፋ. ፬፥፱/፡፡ የምንጠመቀውም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነው፡፡  ‹‹ወእንዘ ታጠምቅመው በሉ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ ስታጠምቋቸውም በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቋቸው፤›› እንዲል(ማቴ. ፳፰፥፲፱)፡፡

በአሁኑ ጊዜም ታቦታቱን ወደ ጥምቀተ ባሕር በማውረድ በዓለ ጥምቀቱን ለሚያከብሩ ክርስቲያኖች በሙሉ ከታቦታቱ ሁለት ሺህ ክንድ ርቀው መከተል እንዲገባቸው በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ተብሎ ተገልጿል፤ ‹‹ሕዝቡን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ ከሠፈራችሁ ተነሥታችሁ ተከተሉት፡፡ በእናንተና በታቦቱ መካከል ያለው ርቀት በስፍር ሁለት ሺህ ክንድ ይሁን፡፡ በዚህ መንገድ በፊት አልሄዳችሁበትና፤ የምትሄዱበትን መንገድ እንድታውቁ ወደ ታቦቱ አቅርቡ፡፡›› (ኢያ.፫፥፩-፲፯)

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀትም ከተጠመቀበት ከ፴ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ በየዓመቱ ጥር ፲፩ ቀን ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ሲከበር ይኖራል፡፡

ከበዓለ ጥምቀቱ ረድኤት፣ በረከት ይክፈለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @dr_zebene_lemma
🔸🔹🔸 @dr_zebene_lemma
     🔸 @dr_zebene_lemma

✍️Comment @Channel_admin09
2025/07/04 12:21:44
Back to Top
HTML Embed Code: