Telegram Web Link
Forwarded from ሐመረ ኖኅ ሚዲያ (@sarina)
#መጋቢት_10

#ቅዱስ_ዕፀ_መስቀል

መጋቢት አስር በዚች እለት የክብር ባለቤት ጌታችን አምላካችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል የተገለጠበትና የተገኘበት ነው። የዚህም የከበረ ዕፀ መስቀል መገለጡና መገኘቱ ሁለት ጊዜ ሆኗል። መጀመሪያ የፃድቁ ንጉስ የቆስጠንጢኖስ እናት በሆነች በንግስት እሌኒ እጅ ነው።

«እርሷ ለእግዚአብሔር ተስላ ነበርና ልጇ ቆስጠንጢኖስ ወደ ክርስቲያን ሀይማኖት ቢገባ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዳ መስቀሉን እስከ አገኘችው ድረስ ልትፈልግው በኢየሩሳሌም ያሉ ቅዱሳት መካናትንና አብያተ ክርስቲያናትን ልታንፃቸው ነው።

ከዚህ በኋላ ልጇ አምኖ የክርስትና ጥምቀትን በተጠበቀ ጊዜ እሌኒ ቅድስት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች ከእረሷ ጋርም ብዙ ሰራዊት ነበር ደርሳም ስለ ከበረ መስቀል መረመረች የሚያስረዳት አላገኘችም የአይሁድ ወገን የሆነ አንድ ሽማግሌ ሰው አስራ በርሀብና በጥማት አስጨነቀችው።

በተጨነቀም ጊዜ ለንግስት እሌኒ የጉልጎታን ኮረብታ አስጠርጊ ብሎ ነገራት እርሷም ይጠርጉ ዘንድ አይሁድን አዘዘቻቸው።

ቤቱን የሚጠርግ ሰው ሁሉ ጥራጊውን በውስጡ የከበረ መስቀል በአለበት በጌታችን መቃብር ላይ እንዲጥል አይሁድ አስቀድመው አዝዘው ነበርና ንግስት እሌኒ እስከ ደረሰችበት ጊዜ ከሁለት መቶ አመት በላይ ጥራጊያቸውን ሲጥሉበት ኖሩ ኮረብታም ሆነ። አይሁድም በጠረጉ ጊዜ ሶስት መስቀሎች ተገለጡ የክብር ባለቤት ክርስቶስ የተሰቀለበት የትኛው እንደሆነ አላወቁም። የሞተ ሰውም አግኝተው አመጡ።

አንዱንም መስቀል አምጥተው በሞተው ሰው ላይ አኖሩት አልተነሳም ደግሞ ሌላውን መስቀል አምጥተው በሙቱ ላይ አኖሩ አሁንም አልተነሳም ከዚህም በኃላ ሶስተኛውን መስቀል አምጥተው በሙቱ ላይ አደረጉት ያንጊዜ የሞተው ሰው ተነሳ እሌኒም የክርስቶስ መስቀል እንደሆነ አውቃ ሰገደችለት የክርስቲያንም ወገኖች ሁሉ ሰገዱለት።

ለልጅዋ የላከችው ይህ መስቀል ነው የሚል በሌላ መፅሀፍ ይገኛል የቀረው ግን ግንዱ በውስጡ ተተክሎበት የነበረው ከእርሱም እኩሌታውን ከቅንዋቱ ጋራ ወደ ልጅዋ የላከችው ነው።

ከዚህም በኃላ ስራአታቸውና የህንፃቸው ነገር በመስከረም ወር በአስራ ሰባት ተፅፎ የሚገኝ አብያተ ክርስቲያናትንና የከበሩ ቦታዎችን አነፀች። ሁለተኛው በሮሙ ንጉስ በህርቃል ዘመን የሆነው ሲሆን የፋርስ ሰዎች በግብፅ አገር ሳሉ ወደ አገራቸው ሊመለሱ ወደዱ። ከሹማምንቶቻቸው አንዱ የጦር መኰንን ተነጥሎ ወደ ኢየሩሳሌም አልፎ ደረሰ ወደ ከበረ መስቀል ቤተ ክርስቲያንም ገባ። መስቀሉም በላዮ በተተከለበት ግንድ ፊት ታላቅ ብርሀን ሲበራ አይቶ ሊያነሳው እጁን ዘረጋ። እሳትም ወጥታ እጁን አቃጠለችው።

ከክርስቲያን በቀር ማንም ሊነካው እንደማይችል የመስቀልን የክብሩን ነገር ሰዎች ነገሩት። ሁለት ዲያቆናትንም ይዞ የከበረ መስቀልን እንዲሸከሙ አዘዛቸው ከኢየሩሳሌም ብዙ ሰዎችን ማርኮ ወደ አገሩ ተመለሰ።

የፋርስ ሰዎች ኢየሩሳሌምን እንዳጠፏት ብዙዎች ሰዎችንም እነድ ማረኩና የከበረ የክርስቶስንም መስቀሉን እንደ ወስዱ የሮም ንጉስ ህርቃል በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ። ስለርሱም እንዲፆሙ ምእመናንን አዝዞ ወደፋርስ ዘምቶ ወጋቸው ብዙዎችንም ገደላቸው የከበረ እፀ መስቀልንም እየፈለገ በሀገራቸው ሁሉ ዞረ ግን አላገኘውም።

ያ ዲያቆናቱና መስቀሉን የወሰደ መኰንን ከቦታዎች በቤቱ አነፃር ባለ በአንድ ቦታ ላይ ወስዷቸው ጥልቅ ጉድጓድ እንዲቆፍሩ አዝዞ በዚያ የከበረ መስቀልን አስቀበረ እነዚያንም ዲያቆናት ገደላቸው።

ነገር ግን ያ መኰንን የማረካት የካህናት ወገን የሆነች በእርሱ ቤት የምትኖር አንዲት ብላቴና ነበረች። እርሷም የከበረ መስቀልን ሲያስቀብርና ሁለቱን ዲያቆናት ሲገድላቸው በቤቱ ውስጥ ሁና በመስኮት ትመለከት ነበር ወደ ንጉስ ሀርቃልም ሂዳ መኰንኑ ያደረገውን ሁሉ ነገረችው።

ይህንንም ንጉስ ሰምቶ እጅግ ደስ አለው ያቺ ብላቴናም መራችው ከእርሱም ጋራ ብዙ ሰራዊት ሆኖ ኤጲስቆጶሳትና ካህናትም ነበሩ። ወደ ቦታውም እስከምታደርሳቸው ያቺን ልጅ ተከተሏት ቅፍረውም የከበረ እፀ መስቀልን አገኙት ከአዘቅቱም አወጡት ንጉሱና ሰራዊቱም ሰገዱለት።
በልብሰ መንግስቱም አጐናፀፈው ታላቀወ ክብርንም አከበረው እጅግም ደስ አለው ከሰራዊቱ ጋር። የዚህም መስቀል ሁለተኛ የተገለጠበትና የተገኘበት በዚች ቀን በመጋቢት አስር ነው፡፡ ከዚህ በኃላ ንጉሱ የከበረ እፀ መስቀልን ተሸክሞ ወደ ቁስጥንጥንያ ከተማ ወሰደው፡፡

የመድኃኒታችን የመስቀሉ በረከት ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_መጋቢት)
8.5k ቻናል መግዛት የሚፈልግ inbox me @kingo08bot
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽዕ
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ
መዝ ፵፱-፫
እግዚአብሔርስ በግልጽ ይመጣል
አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም
እሳት በፊቱ ይነዳል።
መዝ 49:1-3
የጌታችን ምጽአት በቅድስት ቤተክርስቲያን በዓመት ሁለት ጊዜ በተለየ መልኩ ይታሰባል
ክረምት እና የደብረዘይት (እኩለ ጾም)
ላይ
ደብረዘይት በዓብይ ጾም
መካከል 5ተኛዋ ሳምንት ስትሆን
የጾሙም እኩሌታ የሚሆንበት ነው።
የወይራ ዘይት የሚፈልቅባት ቦታ ስትሆን
ጌታችንም እጅግ የሚወዳት ቦታ ናት።
በዚህች ተራራ ጌታችን ለቅዱሳን ሐዋያርት ስለዳግም ምጽአቱ የነገራቸው ቦታ ነው።
የኢየሱስ ዳግም ምጽአት እንደቀድሞ ለመወለድ ፣ለመስቀል፣የጠፋውን ሰው(አዳም)ለማዳን ሳይሆን
ለፍርድ ነው የሚመጣው
መልካም ለሰራ ንዑ ኀቤየ(ወደኔ ኑ)
ክፉ ኀጢአት ለሰራ ሑሩ እምኔየ(ከኔ ሂዱ ወግዱ) ሊል ነው።
ስለዚህ ከየትኛው ፍርድ እንድንቆጠር
እንፈልጋለን ?
ከጥሪው ወይስ ሂዱልኝ ከሚለው
ከመጀመሪያው ያድርገን።
በእለቱ በአንዳንድ አድባራት የጌታችንና የአምላካችን የመድሐኒታችን ጽላት ይከብራል።
ምጽአቱ ድንገት ነው
ልክ ሌባ ሊገድል ሊሰርቅ እንደሚመጣ ሁሉ
ስለዚህ ከኅጢአት ከዝሙት ከመከፋፈል
ተቆጥበን በቀኙ የምንቆም በጎች (አባግዕ )🐑🐑🐑🐑🐑
እንድንሆን አምላካችንን በጸሎት
በጾም በመልካም ትሩፋት እየጸናን እንለምነው።🤲🤲🤲🤲
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

#ደብረዘይት

@eotchntc
ሐመረ ኖኅ ሚዲያ
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች ክፍል 52 ሮሜ 8:27 ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ ዐሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና። ልብን የሚመረምረው ማለቱ ልብን ስለማወቅ ነው። ልብ የተባለው የሰው ልጅ ውስጣዊ ሀሳብ፣ መንፈስ ነው። የእግዚአብሔር መንፈስ የሆነው መንፈስ ቅዱስ የሰውን ልጅ መንፈስ የልቦና እውቀት ካለ ምንም ነገር መቅረት መርምሮ ያውቃል። እንደ እግዚአብሔር…
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች
ክፍል 53
ሮሜ 8: 30:
አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው።

አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው

አሰቀድሞ የወሰናቸውን ጠራቸው ቢል የተመረጡ ሐዋርያት በቅድሚያ ወደ ክርስቶስ እና ወደ ክርስትና መጠራታቸውን ያመለክታል።(ማቴ 4:18-22፤9-9-10)
በሌላ መልኩ ደግሞ እግዚአብሔር ክርስቲያኖችን ወይም አማኞችን ለማጽደቅ መወሰኑን ያሳያል።

የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤

አጸደቃቸው ቢል መጠራታቸውን ተቀብለው ጌታችንን እንደ ጌትነቱ እና አምላክነቱ ያመኑት ጌታችን የልጅነት ስልጣን ሰጥቶ ማክበሩን ያሳያል።

ዮሐንስ 1:12 ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤

እነዚህን ደግሞ አከበራቸው

ማክበሩ በቅዱስ ስጋውና በደሙ ከኀጢአት መዋጀቱን ቤዛ(ለውጥ)በመሆን ማዳኑን ያሳያል።

ሮሜ 8:31 እንግዲህ ስለዚህ
ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል
?

ቅዱስ ጳውሎሰ ክርስትናን እና ክርስቲያኖችን የሚቃወሙ ሰዎች ወይም ሐሳቦች እንደሌሉ ዘንግቶ ወይ ለመጻፍ ሳይፈልግ ቀርቶ አይደለም።
በየዘመናቱ በቤተክርስቲያን እና በክርስቲያኖች ታሪክ ውስጥ ከቤተ መንግስት ፣ከራሷ ከቤተክርስቲያን ውስጥ፣ከመናፍቃን፣ከፈላስፎች ብዙ ፈተናዎች እና ተቃውሞች ነበሩ።
ሐዋርያው ግን እያለ ያለው ምንም እንኳን ብዙ ፈተናዎች ቢኖሩም ከክርስቶስ(ከእግዚአብሔር )ጋር ህብረትን ያደረገ ሰው በፈተናዎች ፈጽሞ ሊወድቅ ሊሰበር እንደማይችል ሊናገር እንጂ ይህም የሚሆነው ግን
በእግዚአብሔር ቸርነትና ምህረት ጥበቃ እና የማያቋርጥ መግቦት መሆኑን እንረዳለን።

ልክ መዝሙረኛው መዝ 117:-6 እግዚአብሔር ረዳታችን ከሆነ ሰው ምንም ማድረግ እንደማይችል እንደተናገረ

ሮሜ 8:32
ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?


ለገዛ ልጁ ያልራራ ማለቱ እግዚአብሔር የሰው ልጆችን ከኀጢአት ጨለማ፣ ከሞት አገዛዝ ፣ከሰይጣን አገዛዝ ነጻ ለማውጣት ምትክ የሌለውን ከአለም አስቀድም የወለደውን ብቸኛ ልጁን ኢየሱስን አሳልፎ ለኛ ቤዛ(ለውጥ)እንዲሆን መላኩን ማለትም የተቀደሰች ፈቃዱ መሆኑን ነገረን።

"ያው" ሲል ልጁን አሳልፎ በመስጠት እኛን የወደደን ያው(ራሱ)እግዚአብሔር ሌላውን ቀላሉን ተራውንማ በደንብ አትረፍርፎ እንደሚሰጠን ነገረን።

ሮሜ 8:33እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው?

እግዚአብሔር ካከበረ ከመረጠ መቃወም መኮነን አይሆንም ማለት የሚችል አንድም ኀይል አለመኖሩን ሲያመለክት
ሮሜ 8:33
እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው
?
ለማጽደቅም ሆነ ለመኮነን ፈራጁ ወይም ብቸኛ ወሳኝ እግዚአብሔር ነው።ሲል
ኢሳይያስ 50:8
የሚያጸድቀኝ ቅርብ ነው፤ ከእኔስ ጋር የሚከራከር ማን ነው? በአንድነት እንቁም፤ የሚከራከረኝ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅረብ።


@eotchntc
#ገብርሔር - 6ተኛው ሰንበት
" ቸር ፣ ታማኝ ፣ ደግና ምርጥ አገልጋይ ማለት ነው። እነሆ የዕለቱ " የገብር ሔር " ወንጌል :ምንባባት እና ምስባክ
የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሰንበት ገብር ሔር (ቸር አገልጋይ) የተሰኘው ሲሆን ይህንን ስያሜ...
ሐመረ ኖኅ ሚዲያ
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች ክፍል 53 ሮሜ 8: 30: አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው። አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው አሰቀድሞ የወሰናቸውን ጠራቸው ቢል የተመረጡ ሐዋርያት በቅድሚያ ወደ ክርስቶስ እና ወደ ክርስትና መጠራታቸውን ያመለክታል።(ማቴ 4:18-22፤9-9-10) በሌላ መልኩ ደግሞ እግዚአብሔር…
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች
ክፍል 54

ሮሜ 8:33
እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው?

እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማንም መክሰስ መቃወም እንደማይችል በመናገር አጽዳቂውም ሆነ የሚፈርደው(የሚኮንነው)ከእግዚአብሔር በቀር የሌለ መሆኑን ገለጸልን።
ይህም በብሉይ ኪዳን ላይ በግልጽ ተቀምጦ ይገኛል።

Isaiah 50 አማ - ኢሳይያስ
8: የሚያጸድቀኝ ቅርብ ነው፤ ከእኔስ ጋር የሚከራከር ማን ነው? በአንድነት እንቁም፤ የሚከራከረኝ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅረብ።
9: እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛል፤ ማን ይፈርድብኛል? እነሆ፥ ሁሉ እንደ ልብስ ያረጃሉ ብልም ይበላቸዋል።

ሮሜ 8:34
የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።


በዚህ ኃይለ ቃል ውስጥ ሐዋርያው ጌታችን መሞቱን ይናገራል። በመቀጠል ጌታችን ሞቶ ብቻ እንዳልቀረ ከሙታን መካከል ደግሞ መነሳቱን ያወሳል።በሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንዲሁ ቅዱሰ ጳውሎስ ጌታችን በኩር ሆኖ ከሙታን መካከል መነሳቱን ይናገራል።

1ኛ ቆሮንቶስ 15:20
አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።

በመቀጠል ያ የሞተው ሞቶም ያልቀረው አካል ደግሞ በእግዚአብሔር ቀኝ በልዕልና መኖሩን ነገረን።

ይህም መሞቱ ከእግዚአብሔር ቀኝ ከመቀመጥ ያልገደበው ኃያል መሆኑን አስረዳን

ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው.....

ይቀጥላል


@eotchntc
#ኃያል_አምላክ_እግዚአብሔር
ኢሳይያስ 6
1.ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፥ የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።
2: ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፥ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር።
3: አንዱም ለአንዱ፦ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች፡ እያለ ይጮኽ ነበር።
4: የመድረኩም መሠረት ከጭዋኺው ድምፅ የተነሣ ተናወጠ፥ ቤቱንም ጢስ ሞላበት።
5: እኔም፦ ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ! አልሁ።

@eotchntc
ሐመረ ኖኅ ሚዲያ
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች ክፍል 54 ሮሜ 8:33 እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው? እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማንም መክሰስ መቃወም እንደማይችል በመናገር አጽዳቂውም ሆነ የሚፈርደው(የሚኮንነው)ከእግዚአብሔር በቀር የሌለ መሆኑን ገለጸልን። ይህም በብሉይ ኪዳን ላይ በግልጽ ተቀምጦ ይገኛል። Isaiah 50 አማ - ኢሳይያስ 8: የሚያጸድቀኝ ቅርብ ነው፤…
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች
ክፍል 55 ሀ

የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።”
  — ሮሜ 8፥34

ስለኛ የሚማልደው ክርስቶስ ነው

ሀ.መማለድ ምን ማለት ነው?
ለ.ይህ ቃል ለምን ለክርስቶስ ተሰጥቶ ተነገረ?
ሐ.እውነት ክርስቶስ አማላጅ(የሚለምን) ነው?
ከዚህ በኋላ በሚኖረን መርሐግብር እነዚህን ነገሮች አንድ በአንድ እናያለን።

ማለደ፣መማለድ፣ምልጃ፣ልመና የሚሉት ሀሳቦች በግሪኩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ስንመለከት

"ἐντυγχάνω" የሚል ሲሆን በአማርኛ ደግሞ ኢንቱካኖ ተብሎ ይነበባል።
ይህ ቃል በሐዲስ ኪዳን  በ ሮሜ 8:34 ብቻ ላይ የሚገኝ ሳይሆን

በ ሐዋ 25:24 አንድ ጊዜ፣በሮሜ 8:27፣ሮሜ 11:12፣ በ ዕብ 7:25 ላይ ተጠቅሶ ይገኛል።

“ፊስጦስም አለ፦ አግሪጳ ንጉሥ ሆይ እናንተም ከእኛ ጋር ያላችሁ ሰዎች ሁሉ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንዳይገባው እየጮኹ የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ በኢየሩሳሌም በዚህም ስለ እርሱ የለመኑኝን ይህን ሰው ታዩታላችሁ።”
  — ሐዋርያት 25፥24

የለመኑኝን:- የሚለውን ቃል(ἐντυγχάνω) ብሎ ይገልጸዋል።
በሌላ በኩል በሮሜ 8:27
ላይ

“ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና።”
  — ሮሜ 8፥27

ያለውን "ይማልድልናል"   የሚለውን ἐντυγχάνω በማለት ይገልጸዋል።
በተጨማሪም
በ ሮሜ 11:2 ላይ ያለውን

“እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ሕዝብ አልጣላቸውም። መጽሐፍ ስለ ኤልያስ በተጻፈው የሚለውን፥ በእግዚአብሔር ፊት እስራኤልን እንዴት እንደሚከስ፥ አታውቁምን?”
  — ሮሜ 11፥2

......እንደሚከሰ  የሚለውን አሁንም

(ἐντυγχάνω) በማለት ይገልጸዋል።

አሁንም  በዕብ 7:25 ላይ

“ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።”
  — ዕብራውያን 7፥25

ያለውን  "ሊያማልድ" የሚለውን በግሪኩ  "ἐντυγχάνω" ይለዋል።

እስካሁን ባየናቸው ጥቅሶች

(ἐντυγχάνω) ኢንቱካኖ
ሀ.ለልመና
ለ.ለክስ
ሐ.ለምልጃ ተሰጥቶ ተነግሯል።በመሆኑም ቃሉን ለአንድ ነገር ብቻ መጠቀም አንችልም


ይቀጥላል.....

@eotchntc
#እኔ_እሆንን

ማቴዎስ 26
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ በመሸም ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ።
²¹ ሲበሉም፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከእናንተ አንዱ እኔን አሳልፎ ይሰጣል አለ።
²² እጅግም አዝነው እያንዳንዱ፦ ጌታ ሆይ፥ እኔ እሆንን? ይሉት ጀመር።

በዚህ የመጽሐፍ ክፍል ውስጥ ጌታችን
በተናገረው አሳልፎ የሚሰጠኝ ከዚህ አለ በሚለው ውስጥ

እጅግ ትልቅ ጭንቀት፣መረበሽ፣እንዲሁም ከልክ ያለፈ ደፋርነት ይስተዋል ነበር።
ሐመረ ኖኅ ሚዲያ pinned «#ወደ_ሮሜ_ሰዎች ክፍል 55 ሀ የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።”   — ሮሜ 8፥34 ስለኛ የሚማልደው ክርስቶስ ነው። ሀ.መማለድ ምን ማለት ነው? ለ.ይህ ቃል ለምን ለክርስቶስ ተሰጥቶ ተነገረ? ሐ.እውነት ክርስቶስ አማላጅ(የሚለምን) ነው? ከዚህ በኋላ በሚኖረን መርሐግብር እነዚህን ነገሮች አንድ በአንድ እናያለን።…»
ሐመረ ኖኅ ሚዲያ
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች ክፍል 55 ሀ የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።”   — ሮሜ 8፥34 ስለኛ የሚማልደው ክርስቶስ ነው። ሀ.መማለድ ምን ማለት ነው? ለ.ይህ ቃል ለምን ለክርስቶስ ተሰጥቶ ተነገረ? ሐ.እውነት ክርስቶስ አማላጅ(የሚለምን) ነው? ከዚህ በኋላ በሚኖረን መርሐግብር እነዚህን ነገሮች አንድ በአንድ እናያለን።…
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች
ክፍል 55 ለ

“የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።”
— ሮሜ 8፥34

በዚህ የመጽሐፍ ክፍል በግሪኩ ምልጃን፣መካሰስን፣መለመንን የሚያመለክተውን ቃል "ኢንቱካኖ"የሚለውን በ ክፍል 55 ሀ
አየን። አሁን ደግሞ ስለኛ የሚማልደው የሚለውን ሀሳብ ከግሪኩ በመቀጠል
በኩር ቋንቋ በሆነው በግዕዙ ቋንቋ
ወይትዋቀሰ በእንቲአነ በማለት ይገልጸዋል።

Romans 8 ግዕ - ሮሜ
34: ለእመ ለሊሁ ያጸድቅ፡ መኑ ዘይኴንን? ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ ወተንሥአ እምዉታን ወሀሎ ይነብር በየማነ እግዚአብሔር ወይትዋቀሥ በእንቲኣነ።

ይህም በአንድ በኩል ምልጃን ሲያመለክት በዋነኛነት ግን ስለኛ ይካሰሳል(ይከራከራል) በሚል ይወሰዳል። ይህም ደግም የሚካሰሰው (የሚከራከረው)ከማን ጋር ነው ከተባለ

ጠላት ዲያብሎስ ነው።ይህንንም ለማሳፈር የክርስቶስ ኢየሱስ የመስቀል ስራ ወይንም ያፈሰሰው ደም ለዘላለም ስለክርስቲያኖች(ልጆቹ) ይጮኻል።በደላቸው ተሽሯል ነጻ ሆነዋል ንስሐ ገብተዋል ስጋና ደሜን በልተዋል ይህም ደም ከአቤል ደም የተሻለ ትኩስና ንጹህ ያረጋ በመሆኑ ከበደል ኀጢአት ነጻ ሆነዋል እያለ የክርስቲያኖችን ድህነት ያጸድቃል።

“የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።”
— ዕብራውያን 12፥24

ይህ ደም መናገር(ድህነትን)መመስከር ብቻ ሳይሆን ደግሞ ከሞተ ሥራ፣ከኃጢአት ከበደል ደግሞ የሚያነጻ ጭምርም ነው።
“ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?”
— ዕብራውያን 9፥14

ሰዎች ንስሐ ቢገቡ ወደ ክርስቶስ ህብረት ፊታቸውን ቢመልሱ ደግሞ የኢየሱስ ደም ከኀጢአት ሁሉ ነጻ(καθαρίζω) ያደርጋል።

“ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።”
— 1ኛ ዮሐንስ 1፥7

የክርስቶስ ደም ሰዎች በኀጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር ጽድቅ ርቀው
ለነበሩቱ መቅረቢያ መንገድ ነው።

“አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።”
— ኤፌሶን 2፥13

በዚህ ላይ ደሙንና ምልጃ ምን አገናኘው ካልን
በብሉይ ኪዳን የሊቀ ካህናቱ ስራ ማስታረቅ ምልጃን ወደ እግዚአብሔር ማቅረብ ነበር። ይህ ግን ካለ አንድ ጊደር፣ኮርማ እና ከመሳሰሉት እንሰሳት ደም ውጭ አይታሰብም ነበር.....

ይቀጥላል

@eotchntc
ሐመረ ኖኅ ሚዲያ
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች ክፍል 55 ለ “የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።” — ሮሜ 8፥34 በዚህ የመጽሐፍ ክፍል በግሪኩ ምልጃን፣መካሰስን፣መለመንን የሚያመለክተውን ቃል "ኢንቱካኖ"የሚለውን በ ክፍል 55 ሀ አየን። አሁን ደግሞ ስለኛ የሚማልደው የሚለውን ሀሳብ ከግሪኩ በመቀጠል በኩር ቋንቋ በሆነው በግዕዙ ቋንቋ ወይትዋቀሰ…
#ወደ_ነው
_ሰዎች
ክፍል 55 ሐ

ዕብራውያን 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ ይህም እንደዚህ ተዘጋጅቶ ሳለ፥ ካህናት አገልግሎታቸውን እየፈጸሙ ዘወትር በፊተኛይቱ ድንኳን ይገቡባታል፤
⁷ በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፥ እርሱም ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ስሕተት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤
⁸ ፊተኛይቱም ድንኳን በዚህ ገና ቆማ ሳለች፥ ወደ ቅድስት የሚወስደው መንገድ ገና እንዳልተገለጠ መንፈስ ቅዱስ ያሳያል።

ይህም የሚቀርበው ደም ካህኑ(ሊቀ ካህኑ) ስለ ራሱ ሆነ ስለ ህዝቡ ኃጢአት የሚለምንበት ወይም የሚያስተሰርይበት ማስተሰረያ ነው።

በብሉይ ኪዳን መሰውያውም አብዛኛው የቤተመቅደስ ዕቃ በ እንስሳት ደም ይረጭ ዘንድ
ግድ ነበር።

“እንደ ሕጉም ከጥቂቶች በቀር ነገር ሁሉ በደም ይነጻል፥ ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም።”
— ዕብራውያን 9፥22
በመሆኑም ካህኑ ደሙን ይረጭ ዘንድ ይገባዋል።

“ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፥ ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም፤”
— ዕብራውያን 9፥25

ማስተዋል ያለብን ይህ ደም የጥጆችና የጊደሮች ላም ነው።የነዚህ ላሞች በቀደመው ኪዳን ነገሮችን የህዝቡን ኃጢአት ለማንጻት የዚህን ያክል ስልጣን ካላቸው።
የጌታችን ደም ደግሞ እንዴት ያነጻን ይሆን
ዕብራውያን 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ የኮርማዎችና የፍየሎች ደም በረከሱትም ላይ የተረጨ የጊደር አመድ ሥጋን ለማንጻት የሚቀድሱ ከሆኑ፥
¹⁴ ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?

የክርስቶስ ደም ሰዎችን ከኃጢአት የዋጀ የሚዋጅ ንጹህና ከብር ከወርቅ የሚበልጥ ክቡር ነው።

“ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 1፥18-19
በቀደመው ኪዳን የእንስሳትን ደም የሚሰዋው ካህን

1.ሰው ብቻ የሆነ
2.ልመናን የሚያቀርብ እንጂ ልመናን የማይሰማ
3.በኃጢአት ብሎም በሞት የሚሸነፍ
4.ስለ ራሱ ኃጢአት መሰዋት ያለበት የሚሰዋው ደም ከራሱ ያልሆነ ነው።
ወደ ጌታችን ስንመጣ

1.ሰው ብቻ ያልሆነ ይህም ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ የሆነ(perfect God perfect Human)
ሰው በመሆኑ ይጸልያል

ማቴዎስ 26
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴⁴ ደግሞም ትቶአቸው ሄደ፥ ሦስተኛም ያንኑ ቃል ደግሞ ጸለየ።
⁴⁵ ከዚያ ወዲያ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥቶ፦ እንግዲህስ ተኙ ዕረፉም፤ እነሆ፥ ሰዓቲቱ ቀርባለች የሰው ልጅም በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል።

አምላክ በመሆኑ ጸሎትን ይቀበላል ይሰማል።

“የናዝሬቱ ኢየሱስም እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ፦ የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ማረኝ እያለ ይጮኽ ጀመር።”
— ማርቆስ 10፥47
2.ራሱን በመስቀል ላይ የተወደደ መስዋዕት አድርጎ ያቀረበ ነው

“ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ።”
— ኤፌሶን 5፥2

መስዋዕት አቅራቢ ደግሞ ራሱ ነው

“እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥”
— ዕብራውያን 10፥12

እግዚአብሔር እንደመሆኑ እንደ እግዚአብሔርነቱ መስዋዕትን ተቀባይ ነው።
ክርስቶስ በግ ለተባሉ ልጆቹ በመስቀል በዕለተ አርብ ደሙን ያፈሰሰ የእግዚአብሔር ቅዱሱ ነው።

".......ለበጎቹ ቤዛ የተሰቀለ የናዝሬቱ ኢየሱስ አምላካዊ ደም እንጂ" እንዲል አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በ መጽሐፈ አርጋኖን 2:10

3.እንደ ብሉዩ ካህን በኀጢአት የማይሸነፍ ንጹሐ ባህሪ ነው።

“ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፥ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም።”
— ዕብራውያን 4፥15

ሞትን በፈቃዱ ቢሞትም በግርማና በኃይል በእግዚአብሔርነቱ ስልጣን ድል አድርጎ የተነሳ ነው።

“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።”
— ሮሜ 1፥3-4

በነዚህ እና በሌሎች ምክንያቶች የክርስቶስ ደም ካህኑ በብሉይ ኪዳን ይሰራቸው የነበረውን የማንጻት ስራን ቢሰራም የቀደመው ደም ደካማ የሆነ ሲሆን ሁለተኛው ግን የክርስቶስ የሆነ ነው። ደሙ ይናገራል ሲባል ክርስቲያኖችን ከኀጢአት ለማንጻት የማይታክት ትኩስና የማይደርቅ ነው። በዚህም ሐዋርያው
የሚማልደው ማለቱ የደሙን አይቀሬ የሆኑ የማንጻት ሥራ ሲገልጽ ነው።

ይቀጥላል .....

@eotchntc
ሐመረ ኖኅ ሚዲያ pinned «#ወደ_ነው። _ሰዎች ክፍል 55 ሐ ዕብራውያን 9 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶ ይህም እንደዚህ ተዘጋጅቶ ሳለ፥ ካህናት አገልግሎታቸውን እየፈጸሙ ዘወትር በፊተኛይቱ ድንኳን ይገቡባታል፤ ⁷ በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፥ እርሱም ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ስሕተት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤ ⁸ ፊተኛይቱም ድንኳን በዚህ ገና ቆማ ሳለች፥ ወደ ቅድስት የሚወስደው መንገድ ገና…»
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
+ ከልብ የፈለቀ መዝሙር +

‘የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር’’

ይህ ታላቅ ሕዝባዊ የአንድነት ዝማሬ መቼ የተጠና ዝማሬ ነው? ይህ ሁሉ ሕዝብ አንድ መዝሙር ለመዘመር ልምምድ የጀመረው መቼ ይሆን? ይህ ልዩ የሆነ የአቀባበል ሥነ ሥርዓትስ መቼ የተማሩት ነው? የሥራ ክፍፍል ያደረጉትስ መቼ ነበር? እናንተ ልብስ አንጥፉ ፣ እናንተ ከፊት ቅደሙ ፣ እናንተ ዘንባባ ያዙ ብሎ ሥራ ያከፋፈላቸው የመዝሙሩን ሥርዓት የምስጋናውን ወግ ያሳያቸው ማን ነው? ድንገት ሕዝብ ሁሉ አንድ አንደበት ሊኖረው እንዴት ይችላል?

ጌታ ሆይ የአንተን ፊት ያዩ ሰዎች የምስጋና ትምህርት ቤት አያስፈልጋቸውም፡፡ ምስጋና እንዲሁ ዝም ብሎ ከአንደበታቸው ይፈልቃል፡፡ ከሕፃናትና ከሚጠቡት ሰዎች አፍ ለራስህ ምስጋናን ታዘጋጃለህ፡፡ የማይተዋወቁ ሰዎች ያለ ልምምድ አንድ መዝሙር ይዘምሩልሃል፡፡ ዳግም ስትመጣ በቀኝህ አቁመን እንጂ እኛም የማናውቀው አዲስ ምስጋና እናቀርብልሃለን፡፡ ፊትህን ለማየት አብቃን እንጂ ልብሳችን ብቻ ሳይሆን ልባችንንም እናነጥፍልሃለን፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሆሳዕና 2013 ዓ ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!

ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :-

የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
የቴሌግራም ቻናል : https://www.tg-me.com/deaconhenokhaile
የዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
#ወደ_ሮሜ_ሰዎች መልእክት
አቀራረብ በሐመረ ኖህ ቻናል ምን ይመስላል ?
Anonymous Poll
88%
ሀ.ጥሩ ነው
18%
ለ.ጥሩ አይደለም
24%
ሐ.እርግጠኛ አይደለሁም
Zechariah 9 አማ - ዘካርያስ
9: አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።

እንኳን አደረሰን

@eotchntc
2025/07/01 05:29:29
Back to Top
HTML Embed Code: