Telegram Web Link
ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ተሰጥቶ የነበረው የዘገባ ፈቃድ ለጊዜው ታገደ!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚሠሩ ኦርቶዶክሳውያን የሚዲያ ተቋማት በአንድ ማእከል  እንዲያገለግሉ፣ የመረጃ ፍሰቱ ወጥነት ያለውና ተቋማዊ መሆን ይችል ዘንድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የሁለት ቀናት ሥልጠና ተሰጥቶ የቤተ ክርስቲያን መሠረተ እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና ትውፊት አክብረው በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ዘገባ ማከናወን የሚችሉበት ፈቃድ ከመምሪያው መሰጠቱ ይታወሳል።

ከእነዚህ የሚዲያ ተቋማት መካከልም የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን አንዱ ሆኖ ዘገባዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል።

"'ሆኖም ግን በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በዕለተ ስቅለት "ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም አትባልም።" በሚል ርእስ  የተላለፈው ትምህርት ውዝግብ በማስነሳቱና ቋሚ ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ለመስጠት ለረቡዕ ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ የያዘ በመሆኑና ጉዳዩ በሚገባ ተጣርቶ ውሳኔ እስከሚሰጠው ድረስ ከመምሪያችን ለፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን የተሰጠው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው የታገደ መሆኑን እንገልጻለን።" ሲል የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ገልጿል።፡

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
#ቴምር ሪልስቴት
‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው ሱቅ

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251966244248
     +251984000520
WhatsApp. https://wa.me/251966244248
Telegram :@TemerRealEstateConsultant
ቋንቋ ስልጠና በመራህያን
የምንሰጣቸው የቋንቋ ስልጠናዎች ፦
ቻይንኛ 🇨🇳
እንግሊዘኛ 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿
ጀርመንኛ🇩🇪
አረብኛ 🇸🇦
ፈረንሳይኛ🇫🇷

•Online or Inperson

ለመመዝገብ:
       ☎️
0989747878
0799331774

አድራሻ፦ 22 ከ ጎላጉል አጠገብ

ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ : @merahyan
“ሲም ካርድ በመጠቀም ፈንጂዎችን ለማፈንዳት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን ይዣለሁ” ሲል የጎንደር ከተማ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ አስታወቀ

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ “ሲም ካርድ በመጠቀም ፈንጂዎችን በማፈንዳት የህብረተሰቡን ሰላም ለማደፍረስ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ሶስት ተጠርጣሪዎች” ይዣለሁ ሲል ገለጸ።

"ተጠርጣሪዎች ገበያ ስፍራዎች በትምህርት ቤቶችና እንዲሁም ህዝብ በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች ፈንጂዎችን በማጥመድ የሽብር ተግባር ለመፈጸም ዝግጅት እንደነበራቸው" ባካሄድነው ምርመራ አረጋግጠናል ሲሉ የመምሪያው ኃላፊ አቶ አለልኝ ዓለም ትላንት ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

"ፍንዳታውን የሚያካሂደው በፈንጂው ላይ በሚታሰር የሞባይል ቀፎና ሲም ካርድ በመታገዝ ወደ ሲም ካርዱ በመደወል ፍንዳታውን በርቀት ሆነው እንደሚያካሂዱ" ተደርሶበታል ብለዋል፡፡

የመምሪያው ኃላፊ አቶ አለልኝ ዓለም በመግለጫቸው "ተጠርጣሪዎቹ ከቀናት በፊት ምሽት ላይ በከተማው አንድ ፖሊስ ጣቢያና በክፍለ ከተማ ጽህፈት ቤት ላይ ፈንጂ በማፈንዳት ተሰውረው የቆዩ ናቸው" ማለታቸውን ከከተማዋ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

"የፀጥታ መዋቅሩ ባደረገው ጥብቅ ክትትልና ስምሪት ተጠርጣሪዎቹ ሌላ የሽብር ተልእኮ ለመፈጸም በአንድ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በድብቅ ካዘጋጁዋቸው የፈንጂ መሳሪያዎች ጋር በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል" ማለታቸውንም መረጃው አካቷል።


  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
በ ሰባት ዓመቷ ታዳጊ ላይ የመድፈር ጥቃት የፈፀሙት የ75 ዓመቱ አዛውንት በእስራት ተቀጡ

በባሌ ዞን ጎሮ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት የ75 አመቱ አዛውንት የሰባት አመቷ ታዳጊ ላይ የመድፈር ጥቃት በመፈፀማቸው በእስራት እንዲቀጡ የተወሰነባቸው መሆኑን የባሌ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታዉቋል። ብስራት ሬዲዮ ከባሌ ዞን ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮምኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘዉ መረጃ እንዳመለከተው ተከሳሽ ተሾመ ገመቹ የተባሉት ግለሰብ ህዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዐት ላይ በባሌ ዞን ጎሮ ወረዳ ውስጥ የሰባት ዓመቷ  ታዳጊ ከምትጫወትበት ስፍራ በመሄድ ጁስ ልግዛልሽ በማለት አታለው በመውሰድ ወደ እራሳቸው ሱቅ በማስገባት ፍራሽ ላይ በማስቀመጥ ጁስ ከሰጧት በኋላ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎቿን በመሣም እራሳቸው ካዘጋጁ በኋላ የመድፈር ጥቃት ሊፈፅሙባት እንደቻሉ በማስረጃ ተረጋግጧል።

ተጎጂዋ በ75 አመቱ አዛውንት የመደፈር ጥቃት ከተፈፀመባት በኋላ በከፍተኛ የደም መፍሰስ በማህፀኗ በኩል የተከሰተ ሲሆን ይህንን የተመለከቱ የህፃኗ ወላጆችም በመደናገጥ በልጅቷ ላይ የተፈፀመውን የመደፈር ጥቃት ወዲያውኑ ለፖሊስ በማሳወቃቸው በልጅቷ ጥቆማ መሠረት የ75 አመቱ አዛውንት በገዛ ሱቃቸዉ ውስጥ በቁጥጥር ስር ዉለዋል። ፖሊስም ተጎጂዋን ልጅ በህክምና ተቋም ሲያስመረምር የ75 አመቱ አዛውንት በግብረስጋ ግንኙነት የሚተላለፍ ህመም እንዳለባቸው እንዲሁም የጤና ክትትል የሚያደርጉ መሆኑ በመረጋገጡ ወዲያዉኑ ለተጎጂዋ የህክምና እርዳታ ተደርጎላት ከተላላፊው ህመም ነፃ መሆኗ ተረጋግጧል።ፖሊስ በ75 አመቱ አዛውንት ላይ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ የምርመራ መዝገቡን በህክምና እና በሌሎች ማስረጃዎች በማጠናከር ለአቃቤ ህግ ልኳል።

አቃቤ ህግም ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በወንጀል ህግ ቁጥር 627 በህፃናት ላይ የሚፈፀም የግብረስጋ ድፍረት እና በደል እንዲሁም በወንጀል ህግ ቁጥር 514 ህመምን በማስተላለፍ ወንጀል ክስ መስርቷል፡፡ ክሱን ሲከታተል የቆየው የባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተከሳሽ ተሾመ የተባሉትን የ75 ዓመት አዛውንት እድሜያቸው 13 ዓመት ባልሞላቸዉ ልጆች ላይ ለንፅህና እና ክብር ተቃራኒ በሆነ መንገድ የመድፈር ጥቃት በመፈፀም እንዲሁም ከባድ ጉዳት የሚያደርስ ህመም እና በሽታ እያለባቸው በተበዳይዋ ላይ የአእምሮ እና የአካል ጉዳት እንዲደርስ በማድረጋቸው በድርብ ወንጀል ጥፋተኛ ብሏል፡፡የባሌ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሚያዝያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ በ14 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
የሩሲያ ከፍተኛ የጦር አዛዥ በመኪና ላይ በተጠመደ የቦምብ ጥቃት ተገደሉ
***

የሩሲያ ከፍተኛ የጦር አዛዥ የሆኑት ሜጀር ጄኔራል ያሮስላቭ በሞስኮ ከተማ አቅራቢያ በመኪና ላይ በተጠመደ የቦንብ ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን የሩሲያ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡

ጄኔራሉ በአካባቢው እያለፉ በነበረበት ወቅት በሪሞት የሚዘወር ቦንብ የተጠመደበት መኪና ፈንድቶ ጥቃቱ እንደደረሰባቸው የሩስያው አርቲ ዘግቧል፡፡

ጥቃቱን ተከትሎ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ "ሞስኮ የዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም ከአሜሪካ ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ ዝግጁ ነበረች፤ ሆኖም ግን ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ጥቃቱ ከዚህ ቀደም ዩክሬን በሩሲያ አመራሮች ላይ ከሰነዘረቻቸው ጥቃቶች ጋር ተመሳሳይነት ያለው መሆኑን ዘ ጋርዲያን በዘገባው አመላክቷል፡፡

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቴምር ሪልስቴት
‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው ሱቅ

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251966244248
     +251984000520
WhatsApp. https://wa.me/251966244248
Telegram :@TemerRealEstateConsultant
በዛሬው እለት ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት አቶ ታዬ ደንዳአ ለምስክርነት የጠሯቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ እና ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፍርድ ቤት ሳይገኙ ቀርተዋል።

የፍርድ ቤቱ ፖስተኛ መጥሪያውን ይዞ ሲሄድ ጥበቃዎች መጥሪያ መሆኑን ካረጋገጡ በኋላ ወደ  ፅህፈት ቤታቸው እንዳይገባ ተደርጎ መመለሱ ታውቋል።

የአቶ ታዬ ጠበቃ "ተራ ፖስተኛ አድርጋችሁ ለምን ተመለሰ ትላላችሁ? የፍርድ ቤት መጥሪያ መሆኑን ሲያውቁ ከበር እንዲመለስ የተደረገው የፍርድ ቤቱን መናቅ ነው" በማለት በቀጣይ ማንኛውም ዜጋ አልቀርብ ሲል ተገዶ እንደሚመጣው ሁሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ከንቲባዋ ተገደው እንዲመጡ ለፌደራል ፖሊስ ትዕዛዝ ይፃፍልኝ ሲል ጠይቋል።(መሰረት-ሚዲያ)

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
የአለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት #በአማራ ክልል በበድሮን በመታገዝ የሚደረጉ ጥቃቶችን አወገዘ

በአማራ ክልል ምሥራቅ #ጎጃም ዞን ባሳለፍነው ሳምንት በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች መሞታቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳዘናቸው እና ድርጊቱ እጅግ እንዳሳሰባቸው #የአለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ ቄስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ጄሪ ፒሌይ አስታወቁ።

በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ባሳለፍነው ሳምንት ሐሙስ ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በትምህርት ቤት ዙሪያ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የዓይን እማኞች ማስታወቃቸውነ የተመለከተ ዘገባ መቅረቡ ይታወሳል።

“ይህ የከፋ ጥቃት በቅርብ ወራት ውስጥ ተፈጽመው የበርካቶችን ህይወት የቀሰፉ ተግባራት ተጨማሪ ማሳያ ነው፤ በርካታ ንጹሃንን የቀሰፉ የድሮን ጥቃቶችመ እ.አ.አ በ2024ትመ ተፈጽመዋል” ሲሉ ዋና ጸሃፊው መናገራቸውን ምክር ቤቱ ትላንት ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

“የአለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት በንጹሃን በብዛት በሚኖሩባቸው አከባቢዎች የሚፈጸሙ መሰል ጥቃቶችን በእጅጉ ይኮንናል” አመላክቷል።

በተጨማሪም ዋና ጸሃፊው ፒሌይ ተዋጎ ያልሆኑ ሰዎችን ከጥቃት በጠበቀ መልኩ እንዲሁም አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ህጎችን በጥብቅ ሳይከተሉ በግጭት አካባቢዎች የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች እንዳሳሰባቸው አስታውቀዋል።

ፒሌይ የሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ሁሉን አቀፍ ውይይት እና ሰላማዊ መፍትሄን እንዲከተሉ አሳስበዋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
ለፓስፖርት አገልግሎት የፋይዳ መታወቂያ ቅድመ ሁኔታ ሊደረግ ነው

የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት  ከሰኔ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያን ለፓስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ቅድመ ሁኔታ ለማድረግ እየሰራ ገልጿል፡፡

አገልግሎቱ ለፓስፖርት አሰጣጥ ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታ በማድረግ በዘርፉ የሚሰጡ አገልግሎቶች ደህንነታቸውን የጠበቁና ተደራሽ ለማድረግ ከዲጅታል መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በጋራ ለመሥራት ተስማምቷል።

ይህም ማንነትን በማጭበርበር የተለያዩ ሰነዶችን ለማግኘት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለመግታት እንደሚያስችል ተገልጿል።

በመሆኑም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የፓስፖርት አገልግሎት ጥያቄ አቅርበው በመጠባበቅ ላይ ያሉ ግለሰቦች ፓስፖርት ለመውሰድ ሲመጡ በቅድሚያ በፋይዳ ተመዝግበው ልዩ ቁጥር ሊኖራቸው እንደሚገባ ተመላክቷል።

ተገልጋዮች የፋይዳ መታወቂያቸውን በወረቀት መልክ አሳትመው እንዲሁም ዲጂታል ኮፒውን በስልካቸው ይዘው በመምጣት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታውቋል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቴምር ሪልስቴት
‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው ሱቅ

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251966244248
     +251984000520
WhatsApp. https://wa.me/251966244248
Telegram : @TemerRealEstateConsultant
ቋንቋ ስልጠና በመራህያን
የምንሰጣቸው የቋንቋ ስልጠናዎች ፦
ቻይንኛ 🇨🇳
እንግሊዘኛ 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿
ጀርመንኛ🇩🇪
አረብኛ 🇸🇦
ፈረንሳይኛ🇫🇷

•Online or Inperson

ለመመዝገብ:
       ☎️
0989747878
0799331774

አድራሻ፦ 22 ከ ጎላጉል አጠገብ

ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ : @merahyan
በሴቶች የለንደን ማራቶን አትሌት ትዕግስት አሰፋ አሸነፈች

በ45ኛው የለንደን ማራቶን በሴቶች ምድብ የፓሪስ ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ ባለቤቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በአንደኝነት አጠናቅቃለች፡፡

አትሌት ትግስት ርቀቱን ለመጨረስ 2 ሠዓት ከ15 ደቂቃ ከ50 ሠከንድ ፈጅቶባታል፡፡

በዚሁ ውድድር መርሐ-ግብር ኬንያዊቷ አትሌት ጄፕኮስፔ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ሲፋን ሀሰን ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡

የለንደን ማራቶን በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲንየም ደረጃ ያለው ከዓለም ትላልቅ ማራቶን ውድድሮች መካከል አንዱ ነው፡፡

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
ግንቦት አምስት በኋላ እንደሚሰረዝ በምርጫ ቦርድ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ህወሓት አሁንም እንደ አዲስ እንደማይመዘገብ አስታወቀ

ህጋዊ እውቅናየ አለመመለስ በስምምነቱ ላይ አደገኛ መዘዝ  ያስከትላል ብሏል

በምርጫ ቦርድ በተቀመጠው ቀን ገደብ መሰረት ህልውናው ሙሉ በሙሉ ሊሰረዝ ሁለት ሳምንታት የቀሩት ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት)፤ በድጋሚ “ምንም አይነት” ምዝገባ እንደማያካሂድ አስታወቀ።

ፓርቲው ሚያዚያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፤ “አደራዳሪዎች፣ የአፍሪካ ህብረት ፓነል እና አለም አቀፉ ማህበረሰብ የህወሀትን ህጋዊ እውቅና አለመመለስ በስምምነቱ ላይ የሚያስከትለውን አደገኛ መዘዝ ተረድተው የድርሻቸውን እንዲወጡ” ሲል ጠይቋል።

በፌደራል መንግስት እየተደረገ ያለው “#የፕሪቶርያ ስምምነትን የሚጥስ አካሄድ በተመለከተ ህወሓት ጉዳዩን ወደ አፍሪካ ህብረት ፓኔል መውሰዱን” ያስታወቀሰው መግለጫው “ፓኔሉም የህወሓት ህጋዊ ሰውነት እንዲመለስ እና እንደአዲስ መመዝገብ እንደማይገባው በመግለጽ ውጤቱም እስከ ቀጣዩ የፓኔሉ ስብሰባ ተጠናቆ እንዲቆይ ሃሳብ ሰጥቶበታል” ብሏል። “ነገር ግን ፓኔሉ እስካሁን ባለመሰብሰቡ በአጠቃላይ የስምምነቱ አፈጻጸም ሆነ የሚታዩ ጥሰቶችን መግምገም አለመቻሉን” አመላክቷል።


  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
አሳዛኝ ዜና

የቀድሞ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አሁን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ሆነዉ እያገለገሉ የሚገኙት አቶ አሊ ከድር በደረሰባቸዉ ድንገተኛ የመኪና አደጋ ዛሬ ህይወታቸዉ አልፏል።

አቶ አሊ ከድር ከስልጤ ዞን ምስረታ በኋላ ዞኑን የመሩ ስምንተኛው አስተዳዳሪ የነበሩ ሲሆን በዚህም ከህዳር 2012 እስከ ሀምሌ 2016 ዞኑን በዋና አስተዳዳሪነት መምራታቸው ይታወቃል።

ከሀምሌ 2016 ጀምሮ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ ነበሩ። የስልጤ ዞን አስተዳደር ሀዘኑን ገልጾ ለህዝቡ፣ ለቤተሰብ፣ እና ወዳጅ ዘመድ መጽናናትን ተመኝቷል።

  T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቴምር ሪልስቴት
‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው ሱቅ

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251966244248
     +251984000520
WhatsApp. https://wa.me/251966244248
Telegram :@TemerRealEstateConsultant
#update"..የመኪናው አንዱ የፊት ጎማ ከነቸርኬው ወልቆበት ፊት ለፊት ይጓዝ ከነበረ ሲኖትራክ ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው የደረሰው " - የኦሮሚያ ክልል ትራፊክ ደህንነትና ቁጥጥር ዋና መምሪያ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከድር ፤ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ  ከሞጆ ወደ ባቱ ይጓዙበት የነበረው ላንድ ክሩዘር ተሽከርካሪ ባጋጠመው የግጭት አደጋ ህይወታቸው አልፏል።

ቃላቸውን ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሰጡት የኦሮሚያ ክልል ትራፊክ ደህንነትና ቁጥጥር ዋና መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር  በላቸው ቲኪ ፥ በፈጣን መንገድ ከሞጆ ወደ ባቱ ይጓዝ የነበረ ላንድ ክሩዘር ተሽከርካሪ ከሲኖ ጋር በመጋጨቱ የአንድ ሰው ህይወት ወዲያው ሲያልፍ በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።

አደጋው የደረሰው ከቀኑ 9፡20 ሲሆን ኮድ3-75541 ኢት ላንድክሩዘር መኪና  አንዱ የፊት ጎማ ከነቸርኬው ወልቆበት ፊት ለፊት ይጓዝ ከነበረ ሲኖትራክ ጋር በመጋጨቱ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።

በወቅቱ ምንም ዓይነት ግጭት ሳይኖር የፊት ጎማው የወለቀበት ምክንያት እየተጣራ መሆኑን ለቴሌቪዥን ጣቢያው አመልክተዋል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ፥ በአቶ አሊ ከድር ድንገተኛ ህልፈተ የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸው ፤ ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ከተካሄደ የአመራሮች ስብስባ ወደ ስራ ሲመለሱ አደጋው እንዳጋጠመ ጠቁመዋል።
2025/07/04 23:26:06
Back to Top
HTML Embed Code: