Telegram Web Link
ሆሳዕና በአርያም 🌴

እንኳን አደረሳችሁ

የ “ሆሳዕና በአርያም” በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ ዛሬ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

ሆሳዕና በአርያም ከፋሲካ በፊት ያለው እና የዐቢይ ጾም የመጨረሻው ሣምንት ሲሆን÷ “አቤቱ እባክህ አሁን አድን፣ አቤቱ እባክህ አሁን አቅና፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ብሩክ ነው” የሚሉ ትርጉሞችም እንዳሉት የዕምነቶቹ አባቶች ያስተምራሉ።

የዕምነቶቹ ተከታዮች በሆሳዕና በአርያም በዓል መሪው ተመሪውን ዝቅ ማለትን ያስተማረበት እና ተመሪውም የሚመራውን ጨርቁን እያነጠፈ እና ዘንባባ እየጎዘጎዘ ያከበረበት የትህትና እና የፍቅር በዓል ተደርጎ የሚወሰድ ነው፡፡

ሆሳዕና በአርያም ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ በተለይም÷ አረጋውያን፣ ሴቶች፣ ወንዶች፣ ወጣቶች እና ሕጻናት “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ ሆሳዕና በዓርያም” በማለት በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መወያየት ብቻውን በቂ አይደለም፤ መተግበር አለበት።

በኢትዮጵያ መናናቅ እና የት ይደርሳል ማለት ችግር ሲፈጥር እየታየ መሆኑንም መወያየት ብቻውን በቂ አይደለም።ውጤቱ መተግበር ይኖርበታል።

እንደ ሀገር የመወያየት ችግር ባይኖርም መሠረታዊ ችግሩ አፈፆፀም ላይ ነው።ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ መስራት ያስፈልጋል።ብዙ ጊዜ የሚስተዋለው  እንወያይ እንጋገር ከማለት የዘለለ አይደለም>>

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሴቶችን ተሳፎ በተመለከተ በትናንትናው ዕለት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው ከተናገሩት የተወሰደ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ አቀባበል ተደረገለት

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በሆሳዕና እለት ወደ ሀገሩ ሲገባ በቤተሰቡ፣ በወዳጆቹ ቀነኒሳ ሆቴል አቀባበል ተደረገለት።
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በፈታኙ ሎንዶን ማራቶን 2.04.15 በመግባት ሁለተኛ ሆኖ ውድድሩን ማጠናቀቁ ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በትግራይ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር በዋሉ የራያ እና አላማጣ አካባቢዎች ህይወት ምን ይመስላል?

ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ የትግራይ ታጣቂዎች ወደ ራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መግባታቸውን ተከትሎ የዳግም ጦርነት ስጋት ደቅኗል።

የአማራ ክልል በህወሃት ታጣቂዎች ወረራ ተፈጽሞብኛል ቢልም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳድር ግን ተግሩን እየፈጸሙ ያት የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት ጠላቶች ናቸው ብሏል።

የራያ እና አላማጣ አካባቢ ነዋሪዎች በፌደራል መንግስት “ተከድተናል የሚል ስሜት ውስጥ መግባታቸውን” ተናግረዋል።

የትግራይ ታጣቂዎች ከአላማጣ 15 ኪሎ ሜት ራዲያስ ውስጥ ሆነው በየቀኑ ተጨማሪ ሀይል እያስገቡ እንደሆነም ነው ነዋሪዎቹ የሚናገሩት።


ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ የትግራይ ታጣቂዎች ወደ ራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መግባታቸውን ተከትሎ የዳግም ጦርነት ስጋት ደቅኗል።

የአማራ ክልል በህወሃት ታጣቂዎች ወረራ ተፈጽሞብኛል ቢልም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳድር ግን ተግሩን እየፈጸሙ ያት የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት ጠላቶች ናቸው ብሏል።

የራያ እና አላማጣ አካባቢ ነዋሪዎች በፌደራል መንግስት “ተከድተናል የሚል ስሜት ውስጥ መግባታቸውን” ተናግረዋል።

የትግራይ ታጣቂዎች ከአላማጣ 15 ኪሎ ሜት ራዲያስ ውስጥ ሆነው በየቀኑ ተጨማሪ ሀይል እያስገቡ እንደሆነም ነው ነዋሪዎቹ የሚናገሩት።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአዲስ አበባ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ ንጋት ላይ በጣለው ዝናብ ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ወረገኑ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸውን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ሕብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት መለየቱ ተገልጿል፡፡

ይህንን የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት በመሠረታዊነት የሚፈቱ ፕላኑን የጠበቁ ዘላቂ የመፍትሄ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡

በመሆኑም ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ከከተማ አስተዳደሩ እና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶች ተግባራዊ እንዲደረጉ ጥሪ መቅረቡን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
ኤፍ ቢ ሲበመዲናዋ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ ንጋት ላይ በጣለው ዝናብ ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ወረገኑ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸውን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ሕብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት መለየቱ ተገልጿል፡፡

ይህንን የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት በመሠረታዊነት የሚፈቱ ፕላኑን የጠበቁ ዘላቂ የመፍትሄ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡

በመሆኑም ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ከከተማ አስተዳደሩ እና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶች ተግባራዊ እንዲደረጉ ጥሪ መቅረቡን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
ኤፍ ቢ ሲ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የዩትዩብ ገፃችንን subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇
https://youtube.com/@Megenagnadaily?si=hYe79ngYPK8k3nbM
የአውሮፓ ህብረት #ለኢትዮጵያውያን በጊዜያዊነት ወደ አውሮፓ የመግቢያ ቪዛ ፈቃድ መከከሉን አስታወቀ‼️

ለዚህ ውሳኔ መነሻው ከመንግስት በቂ ትብብር እያገኘሁ ባለመሆኑ ነው ብሏል።

የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ለኢትዮጵያውያን በጊዜያዊነት ወደ አውሮፓ የመግቢያ ቪዛ ፈቃድ መስጠት የሚከልክል ውሳኔ አሳለፈ።

ለክልከላው የሰጠው ምክንያት ከኢትዮጵያ መንግስት በቂ ትብብር እያገኘሁ ባለመሆኑ ነው ብሏል።

በተጨማሪም የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን እዚህ ውሳኔ ላይ ያደረሰው በህብረቱ ሀገራት በህገወጥነት በሚቆዩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ዙሪያ ከሀገሪቱ መንግስት በቂ ትብብር እያገኘሁ ባለመሆኑ ነው ብሏል።
በዚህም የህብረቱ ለአባል ሃገራት ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያውያን ቪዛ አመልካቾች ቪዛ ሲፈልጉ
- አስፈላጊ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ እና በአውሮፓ ህብረት ህግ የተቀመጠውን መደበኛ መስፈርቶች እንዲያሟሉ እንደሚገደዱ ተጠቁሟል።
ውሳኔው ለምን ያክል ግዜ እንደሚቆይ ያለው ነገር የለም፤ መደበኛው ቪዛ ለማግኘት የሚጠበቀው የ15 ቀን ጊዜ ወደ 45 ቀን አራዝሞታል።
ይህ ውሳኔ የተወሰነው የህብረቱ ምክር ቤት ባደረገው ግምገማ መሰረት ኢትዮጵያ በህገ-ወጥ መንገድ በአውሮፓ ህብረት የሚቆዩ ዜጎቿን በማስመለስ ረገድ የምታደርገው ጥረት በቂ ባለመሆኑ እንደሆነ ተነግሯል።(Alain)
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ከሐምሌ 6 እስከ 7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። 

መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።

@sheger_press
የአዉሮፓ ህብረት ፤ "የኢትዮጵያ መንግስት ለአመታት በህብረቱ አባል ሀገራት ዉስጥ በህገወጥ መንገድ የኖሩ ዜጎቹን ለመመለስ ቸልተኛ ነበር" ሲል ኢትዮጵያዊያን ቪዛ የሚያገኙበትን መንገድ አጠበቀ

የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እና ባለስልጣናት አሁን ለጉዞ ቪዛ መክፈል አለባቸውም ተብሏል


የአዉሮፓ ህብረት ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለአመታት በህብረቱ አባል ሀገራት ዉስጥ በህገወጥ መንገድ የኖሩ ዜጎቹን ለመመለስ ቸልተኛ ነበር ሲል ወቅሷል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያዊያን ቪዛ የሚያገኙበትን መንገድ ማጥበቁን አስታዉቋል።

ዳጉ ጆርናል ከአሶሴትድ ፕረስ ዘገባ እንደተመለከተው ፤ የአውሮፓ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ ለመስራት የሚፈጅባቸዉን ጊዜ በሶስት እጥፍ መጨመሩን ነዉ።

ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያዊያን በ15 ቀናት ዉስጥ ቪዛ ያገኙ ነበር የተባለ ሲሆን በዚሁ ዉሳኔ መሰረት ወደ 45 ቀናት ከፍ እንዲል ተደርጓል። ይህም የኢትዮጵያ መንግስትን በህገወጥ መንገድ በአዉሮፓ ይኖራሉ የተባሉ ዜጎችን እንዲመልስ ጫና ለመፍጠር ነዉ ብሏል ዘገባው።

ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ከታዘዙ ሶስት ሰዎች መካከልም አንዱ ብቻ መመለሱ በህብረቱ የመንግስትን ተባባሪነት ጎድሎታል የሚለዉን ክስ ለማሳያነት ቀርቧል። ይህም በፈቃዳቸዉም ይሆን ካለፍላጎታቸዉ ህገወጦችን ለመመለስ የሚደረገዉን ሂደት አጓቶታል ብሏል።

በዚህ ዉሳኔ መሰረትም የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እና ባለስልጣናት አሁን ለጉዞ ቪዛ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ መባሉን ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል። አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊያን የቪዛ ቀናቸዉም ቢያልፍ የአዉሮፓ ምድርን ለቅቀዉ እንደማይወጡ ህብረቱ ገልጿል።

@sheger_press
@sheger_press
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን ማቋቋሚያ ሲያጸድቅ ትግራይ አልተወከለችም የሚል ቅሬታ ማቅረቡን ኮሚሽኑ እንደገለጠ ሸገር ዘግቧል።

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ይህን ቅሬታ ያቀረበው፣ ኮሚሽኑ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ጋር በተወያዩበት ወቅት እንደሆነ ዘገባው አመልክቷል።

የኮሚሽኑ አንዱ ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ግን፣ በወቅቱ ሕወሃት በሂደቱ አልተሳተፈም ማለት ትግራይ አልተወከለችም ማለት አይደለም በማለት ለጣቢያው ተናግረዋል። ኮሚሽኑ እስካሁን በትግራይ ክልል በይፋ ሥራ እንዳልጀመረ ይታወቄል።

ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አያይዘውም፣ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት ላይ የሚፈጸሙ እንግልቶች እንዲቆሙ ኮሚሽን ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን ገልጠዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሹመት‼️

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለአብን ከፍተኛ አመራር ሹመት ሰጡ!

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከፍተኛ አመራር ለሆኑት ለአቶ መልካሙ ፀጋዬ ሹመት ሰጥተዋል። ርእሰ መሥተዳድሩ አቶ መልካሙ ጸጋዬን የክልሉ ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አድርገው መሾማቸውን በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ በአዲስ አበባ የመንገድ ኮሪደር ልማት አፈጻጸም ዙሪያ ዛሬ ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች እና የኮሪደር ልማት ሥራው አስተባባሪዎች ጋር መምከራቸውን አስታውቀዋል።

ዐቢይ፣ የከተማዋ የመንገድ ኮሪደር ልማት በከተማዋ የላቀ ምቹ እና ዘላቂ የመኖሪያ ከባቢ የመፍጠር ጥረቶች እንደሆኑ ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ፣ አረንጓዴ ልማትን በማስፋትና መሰረተ ልማቶችን በማሻሻል የሕዝቡን ጤና ለመጠበቅና የስራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚያስችልም ዐቢይ ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ ካንድ ወር በፊት የኮሪደር ልማቱ በሚገኝበት ደረጃ ዙሪያ ከከተማዋ አስተዳደር ሃላፊዎች ጋር አጠቃላይ ግምገማ ማድረጋቸው አይዘነጋም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢሰመጉ፣ መንግሥት በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎችና ታጣቂ ቡድኖች የሚፈጽሟቸውን "ግድያዎች"፣ "ሕገወጥ እስሮች" እና "ድብደባዎች" እንዲያስቆምና ወንጀል ፈጻሚዎችን ለፍርድ እንዲያቀርብ አዲስ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ሚያዚያ 6 እና 7 በምሥራቅ ወለጋ ዞን ሰቡ ሲሬ ወረዳ 14 ነዋሪዎችን፣ ታጣቂዎች ደሞ በምዕራብ አርሲ ሽርቃ፣ ቃርሳ እና ኢተያ ወረዳዎች 5 ሰዎች መግደላቸውን ኢሰመጉ ገልጧል።

የፌደራሉና የክልል መንግሥታት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ “አፈናዎችን” እንዲያስቆሙና “የሰዎችን በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት" እንዲያስከብሩም ኢሰመጉ ጥሪ አድርጓል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መርማሪ ቦርድም፣ አማራ ክልል ውስጥ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በማጣራት ወንጀለኞችን በሕግ እንዲጠየቁ ለመንግሥት የውሳኔ ሃሳብ እንዲያቀርብ ኢሰመጉ ጠይቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጦርነቱን ተከትሎ በአማራ ክልል ስር የተቋቋሙ አስተዳደሮች እስከ ሰኔ 30 መፍትሔ እንደሚያገኙ ጄነራል ታደሰ ተናገሩ


የትግራይን ጦርነት ተከትሎ በአማራ ክልል ስር ተጠቅለው የተቋቋሙ አስተዳደራዊ መዋቅሮች እስከ ሰኔ 30/ 2016 ዓ.ም መፍትሔ እንደሚያገኙ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ጄነራል ታደሰ ወረደ ተናግረዋል።

ጄነራል ታደሰ ባለፉት ሁለት ቀናት የፕሪቶሪያ ግጭትን በዘላቂነት የማቆም ስምምነት አተገባበር በተመለከተ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከመከላከያ እና ከፌደራል መንግሥት ባለስልጣናት ጋር ያደረጉትን ውይይት መሰረት በማድረግ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው ይህንን የተናገሩት።

የአማራ ክልል ይገባኛል በሚላቸው እና የትግራይን ጦርነት ተከትሎ ክልሉ ጠቅልሎ እንደ አዲስ ያዋቀራቸው የደቡብ ትግራይ እና ጸለምቲ ወረዳዎች መፍትሄ ለማበጀት እስከ ግንቦት 30/2016 ዓ.ም የጊዜ ሰሌዳ ስምምነት ላይ መደረሱን ጄነራል ታደሰ ገልጸዋል።

በተጨማሪም በአማራ ክልል በኩል ወልቃይት ተብሎ በሚጠራው ምዕራብ ትግራይ እንደ አዲስ የተቋቋመው አስተዳደር እስከ ሰኔ 30 ባለው ጊዜ መፍትሔ ይበጅለታል ብለዋል።

በዚህም ውይይት ላይ ትጥቅ መፍታትን አስመልክቶ የትኞቹ አስተዳዳራዊ መዋቅሮች መፍረስ እንዳለባቸው እና የተፈናቀሉ ዜጎች እንደሚመለሱ ዝርዝር እቅድ የወጣ ሲሆን ይህንንም የሚቆጣጠረው እና የሚያረጋግጠው የአፍሪካ ኅብረት የስምምነት ክትትል አረጋጋጭ እና አስከባሪ ኮሚቴ እንደሚሆን ተገልጿል። ኮሚቴው መቀለ ላይ ቢሮ እንዳለው ከዚህ ቀደም ጄነራል ታደሰ መናገራቸው ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ለ926 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ እሸቱ ጎዴቶ እንደገለጹት÷ የክልሉ የይቅርታ ቦርድ በይቅርታ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ታራሚዎችን ከመንግስት፣ ከህዝብና ከታራሚ ጥቅም አኳያ ሲመረምር ቆይቷል።

በተደረገው ምርመራም በአጠቃላይ የይቅርታ ጥያቄ ካቀረቡ 978 ታራሚዎች መካከል መስፈርቱን ያሟሉ 926 ታራሚዎች ጥያቄያቸው ለክልሉ መንግስት ቀርቦ የይቅርታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉን ተናግረዋል።

የይቅርታው ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል 920 ታራሚዎች ከእስር የሚለቀቁ ሲሆን÷ስድስቱ ደግሞ የእስራት ጊዜያቸው የተቀነሰላቸው ናቸው።

ታራሚዎቹ በማረሚያ ቤት በነበራቸው ቆይታ በአግባቡ ስለመታረማቸው፣ ስለመታነጻቸውና ስለመልካም ባህሪያቸው ምስክርነት የተሰጠባቸው መሆኑንም አመልክተዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/05/24 17:28:50
Back to Top
HTML Embed Code: