Telegram Web Link
#እናመሰግናለን!| ዶ/ር ዘነበ መኮንን
#hawassa #Alphacare
በብቁ የህክምና ሙያው የምናውቀው ዶ/ር ዘነበ #የአልፋኬር መካከለኛ ክሊኒክ ባለቤት ማህበረሰብን ከሙያው በተጨማሪ በበጎ አድራጎት ስራ ሁሌም ቀድሞ ይገኛል። አሁን ደግሞ ለወጣት ፍሬህይወት ህክምና በሚደረገው የድጋፍ ጥሪ እኔም የበኩሌን በማለት አንድ ሺህ ብር ለግሷል። ደጋግ ልቦች ፈጣሪ ብድራቱን ይክፈልልን። እናመሰግናለን።
በነገራችን ላይ በእናቶችና ህፃናት እንዲሁም ዘመኑን የዋጀ ህክምና ለማግኘት ከፈለጋችሁ መምቦ ወደ ሪፈራል በሚወስደው መንገድ በስተግራ ከኮሜሳ ህንፃ ጎን አልፋኬር መካከለኛ ክሊኒክ ዶ/ር ዘነበን ያገኙታል።
መልካምነት ይከፍላል!
#እንኳን_ደስ_አላችሁ| ፍሬ ታክማለች
#hawassa
እህታችንን ፍሬ በዛሬው እለት ከ5 ሰዓት በላይ የፈጀውን የልብ ቀዶ ጥገና (የቫልቭ ለውጥ) ተደርጎላት ጥገናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ እሷም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ አባቷ አቶ ጌታቸው በደስታ ውስጥ ሆነው ምስጋናቸውን በስልክ ነግረውኛል። ክበሩልን።
ውድ ቤተሰቦች ለበጎነት ሁሌም ቀና የሆናችሁ ኢትዮጵያውያን የእህታችንን አትርፉኝ ጥሪ ተቀብላችሁ በሐሳብ፣ በገንዘብና ደግሞም በማህበራዊ ሚዲያ ተረባርባችሁ የተጠየቀውን 560,000 በማዋጣት ህይወት ስለታደጋችሁ ፈጣሪ ከክፉ ሁሉ ይጠብቃችሁ 😍
ቤተሰቦቿም ከቃል በላይ የሆነ ከፍተኛ ምስጋናቸውን አድርሱልን ብለዋል።
ሐምሌ 7/2015 ዓ.ም

2025/10/22 09:50:29
Back to Top
HTML Embed Code: